cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
410
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
"እሱን በመሻት ብታዝን አግኝተኸው ደስ ይልሃል።...እያለቀስህ መከራ እየተቀበልክ እሱን ለማየት መንፈሳዊ ቅንዓት ብትቀና መልኩን በዓይነ ነፍስ ታየዋለህ። ....አቤቱ ጌታዬ ሆይ ወዮልኝ። በፍቅርኽ መንደዴን የሚያበርድልኝ ማነው?... መወደድ ያለህ አቤቱ አንተን የሚወድኽ ንዑድ ነው እላለኁ። አንተን አይቶ የሚሰለችኽ የለምና።" ....... "እሱን አይቶ ልቡ እሱን ከማየት የሰለቸ ማነው? የቃሉን ነገር ሰምቶ እሱን ከመስማት የሰለቸ ማነው?መዓዛዉን ያሸተተ እሱን ለመያዝ እየቸኰለ ደረቱን ያልደቃ ማነው? አረጋዊ መንፈሳዊ
نمایش همه...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በውስጤ ያለችው የኃጢአት ፍቅር ለአንተ ካለኝ ፍቅር ስትበልጥ ይሰማኛል አንተንም እንዳላይ የልቦናዬን አይን የምትጋርድ እርሷ ናትና አቤቱ እንድወድህ ግድ በለኝ ፈቃዴን አልሻውምና። ከኃጢያት ከምትለየዋ ከአንተ ፍቅር አድርሰኝ።
نمایش همه...
እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ -> በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እርሱን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ መዝ 27:4
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#ስለ_እርሱ_አንብቡ እግዚአብሔር በአሳባቸሁ ውስጥ እንዲኖር ስለእርሱ አብዝታችሁ አንብቡ። እርሱን ለማወቅ ስለእርሱ አንብቡ። እርሱን ካላወቃችሁት እንዴት እርሱን ልትወዱት ትችላላችሁ? ስለእርሱ አንብቡ፤ ስታነቡ ግን በሳይንሳዊ ወይም በፍልስፍና ጠባይ አታንብቡ ወይም ደግሞ ስለእርሱ ጥናታዊ ጽሑፍ ወይም ትምህርት ለመስጠት አታንብቡ። ነገር ግን ወደ እርሱ ጥልቀት ለመግባት ወይም እርሱ ወደ እናንተ ጥልቀት እንዲገባ አንብቡ። ለነፍሳችሁ ውድ የሆኑትን የእርሱን ባሕርያት ለማወቅ ስትሉ አንብቡ ይህ እውቀት አሳባችሁ ከእርሱ ጋር እንዲጣበቅና ፍቅሩ ከእናንተ ልብ ጋር እንዲቀናጅ ያደርግላችኋልና ። ስለ ስምምነቱ ስትሉም አንብቡ። ከወደዱት ሰዎች ጋር ስላለው ግንኙነት በጠላቶቹ ላይ ስላለው አቋም ስትሉ አንብቡ! በጽሑፎች ውስጥ ስለእርሱ "ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል" (መዝ 44÷2) የሚለውን ቃል በማንበብ የእርሱን ውበት ታውቁ ዘንድ አንብቡ። እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቀምሳችሁ ታዩ ዘንድ ስለእርሱ አንብቡ። ታዲያ ንባባችሁ ለልባችሁ ምግብ እንዲሆን እንጂ እንዲሁ ተራ ንባብ እንዲሆን አትፍቀዱ። ስለ እግዚአብሔር ብዙ ካነበባችሁ በእርሱ ዘንድ ያለውን ፍጹምነት በሙሉ ታገኛላችሁ። እርሱን ስለምትወዱትም በሰሎሞን መዝሙር ውስጥ ካለችው ድንግል ጋር አብራችሁ "እርሱ ፈጽሞ ያማረ ነው" (መኃ. 5÷16) ትላላችሁ። ከወደዳችሁት ስለእርሱ ማንበባችሁን ትቀጥላላችሁ። እግዚአብሔር ስለእርሱ የሚያነቡትን ስለእርሱ ዜና የሚጠይቁትን ከእርሱ ታሪኮች መካከል አንዱን ለማወቅ የሚናፍቁትንና እርሱን የሚያደንቁትን ሰዎች ይወዳቸዋል። ስለእርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከአባቶች ብሒሎች ወይም ከቤተክርስቲያንና ከቅዱሳን ታሪክ ልታነቡ ትችላላችሁ። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ ለመዳሰስ ስትሞክሩ በጥበቡ፣ በኃይሉና በርኅራኄው ውስጥ እንደምትወዱት ታውቃላችሁ። #አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09
نمایش همه...
"ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ፣ በዐብይ ሃይል ወስልጣን ፣ አሠሮ ለሰይጣን ፣ አጋዝኦ ለአዳም ፣ ሰላም ፣ እምይእዜሰ ፣ ኮነ ፣ ፍስሐ ወሰላም ።" እንኳን አደረሳችሁ! ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE 🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS 🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09
نمایش همه...
ኢሳይያስ 53 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል? ² በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም። ³ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም። ⁴ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። ⁵ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ⁶ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ። ⁷ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። ⁸ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? ⁹ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር። ¹⁰ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል። ¹¹ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል። ¹² ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
نمایش همه...
አርብ ስቅለት👇👇👇 ሕግም ከእምነት አይደለም ነገር ግን፦የሚያደርገው ይኖርበታል ተብሏል። በዕንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፏልና፥ክርስቶስ ስለ እኛ ርግማን ኾኖ ከሕግ ርግማን ዋጀን  ገላ3÷12-14 🙏🙏🙏 ሼር በማረግ ሐዋርያዊ ስራን እንስራ እርግማን የጠፋበት እርግማንን አጥፍቶ ወደ ህይወት ላመጣን 🙏🙏🙏 ክርስቶስ ክብር ይግባዉ
نمایش همه...
✞" የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና። ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው እያሉ ጮኹ።       የዮሐንስ  12 : 13 ✞" የተከበራቹ  ሰንበት ተማሪሰዎች የልዑል እግዚአብሔር ሰላም እና የድንግል ማርያም ፍቅር ከሁላችን ጋር ይሁን !            እንደምን ቆያቹ !! ✞"እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም አደረሳችሁ !! እያልኩኝ ከዚህ ቀደም በሰንበት ትምህርት  ቤታችን የአገልግሉት መቀዝቀዝ ተነጋግረን እና ተወያይተን እንደነበር አይዘነጋም ያለብንን ችግር ሙሉ ለሙሉ ባንፈታም በጥቂቱ  እንዳስተካከልን እናውቃለን   ሆላችንም ወደነበረበት መመለስ ይኖርብናል ሁላችንም እንበርታ አደራ በማለት።   በከተማው ያሉት አጠቃላይ የሰንበት ትምህርት ቤት የጋራ አገልግሎት እንደጀመርን ይታወቃል ሆኖም በሰንበት ትምህርት ቤት መቀዛቀዝ  መቀነስ የጋራ አግልግሎታችንን እንዳናደረግ አድረጉናል እናም የሰበከተ ወንጌል አገልግሎት ባለመሰጠት በከተማው ባሉት ወጣቶች እና ማህበራት ምንም እንዳልተሰራ ምታውቁት  እና በእጅጉ እየተስተዋለ ነው።  እናም ሰንበት ትምህርት ቤቱን ወደ  ነበረበት የጋራ አገልግሎት መመለስ የኹላችንም ኃላፊነት ስለሆነ    በምክንያቶች ሁሉ እግዚአብሔር  ይጠራል በጋራ አገልግሎት የመረጥናቸው ኮሚቴ ስላሉ ወጣቱን እና በከተማው ያሉትን ማህበርተኞች እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ሐላፊዎች እንዲያናግሩ የቤት ስራ ሰተናቸው ነበር የደረሱበትን  የዐቢይ ጾም ሰባተኛ  ሳምንት ሆሳዕና በዓል ላይ ማለትም እሁድ በቀን 1/08/2015 ዓ.ም8:30 ሰዓት ጀምሮ   አጠቃላይ  ከሁለቱም ቤተክርስቲያን ማለትም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስብከተ ወንጌል እና ሰንበት ተማሪአባላት ወደኛ  በመምጣት የሰንበት ት/ቤት መርሀ-ግብር እና የአንድነት ውይይት  ስለምናደርግ እኛ ባለቤት ሆነን በጊዜ በመገኝት እንኳን ደና መጣቹ ብለን ውይይቱን ከእኛም ስብከተ ወንጌል በተገኙበት  እናደርጋለን። በምናደርገው ወይይት በዝምታ ሳይሆን በመናገ አንድነታችንን እናጠንክር የተከበራቹ  ሰንበት ተማሪሰዎች ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ነው ሆሣዕና ማለት እባክህ አሁን አድን ክርስቶስ ባለ መድኃኒት ሆኖ፦ በኃጢአት ለታመሙ ደቂቀ አዳም ሁሉ ሕይወትን ይሰጥ ዘንድ ወደዚህኛው ዓለም መጣ፡፡ በምድራዊ ሥርዓት እንደምናየው መድኃኒትና ባለ መድኃኒት እንደሚለያዩ አይደለም፡፡ ሁለቱንም እርሱ በመምጣቱ (ሰው በመሆኑ) ፈጸመ እንጂ፡፡ መድኃኒት አድርጎ ሥጋውን ደሙን የሰጠ እርሱ ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር በምክንያት የጋራ አገልግሎት አስጀምሮናል እንድንቀጥልም  ይህን በዓል ስናከብር ሰላምንና ፍቅርን የእርሱን የክብር አመጣጥ እያሰብን ልንተገብረው ይገባል። እግዚአብሔር በካህናት አድሮ ሰው በንስሐ ሲመለስ እና መድኃኒት ወደሆነው ወደ ራሱ የሚመራ እርሱ ነው፡፡ሰለዚህ እኛም በተሰጠን ፀጋ እንደየ አቅማችን የከተማ ወጣቶች ፣ ማህበራትን ወደ ጋር  (ወደ አንደነት) አገልግሎት እንዲመጡና መንፈሳዊ ትምህርት እንዲማሩ ወደ መድኃኒቱ እናቅርባቸው እኛም በንስሐ ሳሙና ታጥበን መድኃኒቱን እነድነቀበል እርሱ በቸርነቱ ይፍቀድልን ። ✞" አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፤ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን     መዝሙር 118 : 25 ማሳሰብያመልክቱን የሰማቹ የነበባቹ ላልሰሙት እንድታስተላልፉ በሰንበት ትምህርት ቤት ስም አደራ በማርያም
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.