cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

@yene poem የግጥም ቻናል✍🇪🇹❤️

👉 ኑ አብረን ሀሳቦቻችንን እናፍልቅ 👉 ትናት ትናት ነው ዛሬ ደግሞ ሌላ ቀን ነው 👉 የማይቻል ነገር የለም ሁሉም ይቻላል ሀሳብ አስተያየት 👉 @Amelakyyy ………… ግጥም የውስጣችንን እምቅ ሀሳብ የምናፈልቅበት የመፃፍ ጥበብ ነው፡ 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹🇪/Ethiopia/❤ @yenepoem

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
201
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

እስኪመስለኝ ድረስ ብዕሬን ጨበጥኩኝ ልፅፍ እያሰብኩኝ በሀሳብ ሄጃለሁ በድቅድቅ ጭለማ ብርሃን እሻለሁ፤ የጠፉትን ቃላት ፍለጋ ይዣለሁ ካልጋዬ ቁጭ ብዬ ሻማ ለኩሻለሁ ብርሀኗ ገርሞኝ እግዚኦ ተሰኜሁ፤፤ እደሰም ቀላልጦ የሚወርደው ሻማ ሂወቴ መሰለኝ የሚበራው ደግሞ ህልሜን አስታወሰኝ፤ የሻማዋ ትርጉም ለኔ ብቻ ሲታይ ብርሃኗ ትላንት ቀለሟ ዛሬ ናት አልሁኝ በልቤ ውስጥ ያሳለፍኩት ሁሉ ድንገት ትዝ ብሎኝ ከማያልቀው ባህር በትዝታ ነክሮኝ፤ አይዞሽ አትዘኝ አይክፋሽ ግድ የለም ምንም ጊዜው ቢርቅ ቀኑ ቢጨልምም፤ በሀሳብ ትካዜ ልብሽ ቢዋልልም ምን አልባት ቢዘገይ እንጂ ፍርድ አይቀርም ለዋለላት ሁሉ እደዚ ናት አለም፤፤🤷‍♀ ✍ ኤፍራታ @yenepoem @yenepoem
نمایش همه...
ጠይቋት ብዕሬን እሷ ማናት በሏት ስለኔ ጠይቋት፤ ካንቺ ጋር ቁርኝት እንዴት ያዛት በሏት ጠይቋት ትናገር ብዕሬ ታሪክ ናት፤ ጠይቋት ብዕሬን ከቃላቶች ጋራ ያለኝን መግባባት የውስጤን ሀሳቦች በግጥም የማውጣት ጥበብና ክነት እዳገኜሁ እዴት ጠይቋት ብዕሬን ለኔ ምስክር ናት፤፤ ✍ኤፍራታ @yenepoem @yenepoem
نمایش همه...
ከሰጎኖች መኃል ያች ገብስማ ዶሮ ያንገቷ ላይ ጸጉር የሸሸባት በሮ ነጣ ያለ ክንታት ማንቁርቷ ግመሮ ጥሬ ቤቷ እባብ አክናፏ አሰርሳሮ ለቅዱስ ዮሐንስ.... ድንገት ደህና ብንደርስ ደግ ትሠዬጥ ይሆን? ደግሞ ቀኗ ይደርስ
نمایش همه...
ትዝብቴን ልንገርሽ አሁን መቼ 'ለታ ካንቺ ስተዋወቅ ካጠገብሽ ቆሞ ልቤም ሲል ከፍ ዝቅ ጨረቃ ነበረች በጣሙን አብርታ ያለመደባትን ካለችበት መጥታ ረጅሙ ፀጉርሽ እንዲዘናፈልም ንፋሱም ነበረ ፈዝዤ እንዳይሽ ከአንቺ ጋር አበረ አሁን መቼ 'ለታ ራት ስጋብዝሽ ክዋክብት ነበሩ በጨዋታ በሳቅ አብረውን አደሩ ባለፈው 'ለት ደግሞ አብሬሽ ወክ ሳደርግ ፀሀይን ታዘብኳት ቃጠሎዋን ትታ ለሰስ ባለ ብርሀን ሰትወጣ አየኋት እንግዲ ልብ በይ አንቺን ሳላውቅ በፊት በስለት አትወጣ ቆንጆ አጥታ ይሁን ጨረቃ አትመጣ አመትም አልፎታል ንፋስ ከነፈሰ ላንቺ ሲሆን ግን ያኔ ካለበት ከነፈ ለምሳሌ እንኳን የጠፉት ክዋክብት አንቺን ሲያዩ ጊዜ ከያሉበት ፍክት ኧረ የጥላ ያለህ ታስብል የነበረች እሳቷን ቀንሳ ረጋ ሰከን አለች ታዘብኳት ተፈጥሮን ላንቺ ታዳላለች እኛን ዘንግታ ካንቺ ጎን ቆማለች። ✍✍✍Selito
نمایش همه...
✍እዚነኝ እዛነኝ??? እዚነኝ እዛነኝ ቆይ የቱ ጋ ነኝ እዲህ እደዘበት ምኑስ አባዘነኝ፤ አካሌ ብቻውን የትም የትም ሆኗል አለች ብቻ ስባል እኔነቴ ጠፍቷል፤ ሀሳቤ ሌላነው አልተገጣጠመም ልቤ ሚረዳውን አካሌ አያውቀውም፤ እዚነኝ እዛነኝ?? በሀሳብ ስዋትት ሌላ አለም ፈጥሬ መጥፎ ትውስታዬን በቀለም አጥቁሬ፤ የደስደስ ያለበት ኑሮ ህልም አልሜ እዚህ ልሁን እዛ በሀሳብ ተምሜ እሄው እስከዛሬ አልተፈታም ህልሜ፤ 😂🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀😳 ✍ ኤፍራታ
نمایش همه...
እያለህ እያለህ እደሌለህ ኖረህ እዳልነበርህ፤ አልጨበጥ ብትል ብጠፋ በድንገት ከልቤ ሽራ ላይ ልፍቅህ ስሰስት፤ ካወኩህ ጀምሮ እያንዳንዷን ቀናት ስላተ እያለምኩ ከራሴው ስሟገት እያሰብኩህ አለሁ ስሞክር ለመርሳት፤ ግና እያሰብኩህ ትዝ እያልከኝ ሁሌ ድንገት ብነጫነጭ ቢቀዬር አመሌ አትርሳ ባንተ ነው🤷‍♀ እያለህ የለህም የነገርኩህን ቃል አ'ዱን አልሰማህም ከኔ ጋር ቁጭ ብለህ ባ'ሳብ አልነበርክም፤
نمایش همه...