cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አማናዊ ቃል

#አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ #የማይቀላቀል_ሶስትነት #የማይነጣጠል_አንድነት በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ዮሐንስ 1፥1 ሌሎችንም ይጋብዙ ➟ ➟ @amanawikal ለመልዕክት እና ለአስታያየት➟ @amanawikalbot የፌስ ቡክ ገጻችን 👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=100082291043634

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
13 086
مشترکین
-1724 ساعت
+1347 روز
+27130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የተማሪዎች የ2017 የትምህርት ዘመን ምዝገባ በonline ስለሆነ። ይህን አገልግሎት የምትፈልጉ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ገብተው ያናግሯቸው። 🔻ኤልሮኢ የኦንላይን አገልግሎት 🔻 @ElroiOS @ElroiOS @ElroiOS @ElroiOS @ElroiOS @ElroiOS @ElroiOS @ElroiOS @ElroiOS
نمایش همه...
3
#ጠብታ_እና_ዓለት የውሃ ጠብታ በውስጡ እጅግ አቅም አለው። በተደጋጋሚ ጠብ ጠብ የሚል ውሃ እጅግ ጠንከራ የሆነውን ዓለት ይሰነጥቃል። በብረት ሀይል የሚሰነጠቅ ድንጋይ በውሃ ጠብታ ሲቦረቦር ማየት እጅግ አስደናቂ ነው። እንዴት ሆነ ብለን እንድንመረምር የሚጋብዝም ጭምር ነው። ነገር ግን በገሃዱ አለም ላይ ያለ ሃቅ ነው። በውሃ መፍሰሻ ቶቦዎች ስር የተሰነጠቀ እና የተቦረቦረ ዓለት የማየታችን ምክንያቱ የውሃው ጠብታ ነው። እስኪ አንድ ነገር እንድናስብ ይሁን። እግዚአብሔር ስንት ጊዜ ምክሮን ይሆን? በስብከት መሃል ነግሮን፣ በመዝሙር ውስጥ አሰምቶን፣ በተጻፈ መልዕክት ውስጥ አድርሶን፣ በአጋጣሚ በሰዎች ወሬ መካከል ተናግሮን፣ እጅግ ክቡር የሆነውን ቅዱሱን ወንጌል አንስተን ስናነብ ሹክ ብሎን፣ በህይወት ምልልሳችን ውስጥ ለእኛ የሚሆን መልዕክት አድርሶን .... ስንት ጊዜ ሰማነው? የእግዚአብሔር ቃል የሰውን አዳፋ ማንነት የሚያጸዳ ውሃ ነው። በቃሉ ውሃነት ሰው ወደ መጥራት እንዲደርስ እና ህይወቱን በንጽህና እንዲኖር እግዚአብሔር በአንድም በሌላ መንገድ ያስተምራል። ምክሩን እና ተግሳጹን የሚቀበል ግን ማን ነው። “ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውኃ ነው፤ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል።” (ምሳሌ 20፥5) ተብሎ እንደተጻፈ ጠቢብ ሆኖ ምክሩን መቅዳት፣ መቀበል እና መኖር ያስፈልጋል። እስኪ ስንት ጊዜ የእግዚአብሔር ምክር ወደ ልባችን መጣ? ልባችን ደንድኖ ህያው ለሆነው ለእግዚአብሔር ቃል መሸነፍ ስንት ጊዜ አቃተን? የእግዚአብሔርን ፍቃድ እያወቅን ለራሳችን ፍቃድ ስንት ጊዜ ተገዛን? ውሃ ለሆነው ለእግዚአብሔር ቃል ልባችን ስንት ጊዜ ድንጋይ ሆኖ ይሆን? የውሃ ጠብታ እንኳን ዓለትን እየሰጠቀ ስንት ጊዜ ልባችን ለቃሉ አልረታ ብሎ ይሆን? እግዚአብሔር በምክሩ ግሩም ነው። በምህርቱም ያለስስት ለጋስ ነው። እስኪ ጀግንነት የሚሰማውን ልባችንን በእግዚአብሔር ፊት አቅመ-ቢስ እናድርገው። እስኪ አልቀየር ያለ አቋማችንን ትተን ከማይቀየረው ከእግዚአብሔር ጎን እንቁም። ብዙ ዘመን እምቢ ባልነው ፈንታ እስኪ ለአፍታ እሺ ብለን እግዚአብሔርን እንታዘዘው። እሺ ለእግዚአብሔር እምቢ ደግሞ ለራስ ፍቃድ ሲሆን እጅግ ይጠቅማልና። በመጽሐፍ “አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።" (ሕዝቅኤል 36፥26) ተብሎ እንደተጻፈ አልረታ ያለውን ልብ አውጥቶ የስጋን ልብ እንዲሰጠን በእግዚአብሔር ፊት በመቅረብ መጠየቅ ያሻል። ለጋሱ እግዚአብሔር ኃጢአት ባልሆነ መሻት የምንጠይቀውን ሊሰጠን ታማኝ ነውና። ለእግዚአብሔር ምክር እና ቃል መሸነፍ የአሸናፊነት ቁንጮ ነው። ሰው ለእግዚአብሔር ምክር ሳይሸነፍ በምንም መልኩ ባለድል የሆነ ቢመስለው ሞኝ ነው። እግዚአብሔርን እሺ ብላችሁ ከብዙ ልክ ካልሆነ ልማዳችሁ ለመውጣት ጥረት እያደረጋችሁ ከሆነ የቃሉ ጠብታ ደርሷችሁ ውስጣችሁን እያነጸ ነውና በሙሉ ደስታ የቃሉን ውሃ ተጋቱ። የእግዚአብሔር ቃል ወደ ውስጣችን ገብቶ ሳያንጸን እና ሳይሰራን አያልፍም። ለሰማነው ቃል ተገቢውን ምላሽ መስጠትና እንደ ቃሉ ህይወትን መምራት ያስፈልጋል። ጠብ ባለ ውሃ ተሰንጥቆ ዓለት ጠብ በሚል ቃልህ እኔም ልሰራበት ምክርህ ጠብ ብሎ ይግባ ወደ ውስጤ እንደ ወንዞ ጎርፍ ሆኖ ትጥለቅለቅ ህይወቴ ዝናብ ሆኖ ምክር ውስጤን ካለገኘ ልቤ ድንጋይ ሆኖ አንትን ካልተመኘ አውጣልኝ የራሴን የአንተን ልብ ሰጠኝ በቃልህ ባህር ውስጥ ሰጥሜ እንድገኝ ነግረኸኝ መክረኸኝ መልሴ እምቢ ሆኖ ልቤ ላይሸነፍ በጽኑ ጀግኖ እንዳልኖር እንደዚህ ስራኝ አብጅና ልታዘዘህ ጌታ ቃልህ ይርታኝና ከመሻቴ ይልቅ ይሁን ያንተ ፍቃድ ቀና ነው መንገዱ በምክርህ ለሚሄድ ከራሴ ጎዳና ልውጣ ከመንደሬ ልኑር በፍቅርህ ስር ከቃልህ አብሬ አልየው ሴኬምን የኃጢአትን መንደር አልገኝ ጨርሶ በደልን ስከተል ይለውጠኝ ቃልህ ያረስርሰን ገብቶ ልቤም ይበል እሺ ይቀመጥ ተረቶ እኔ አሸናፊ አልሁን በህይወቴ ቃልህ ይርታኝ እንጂ ቀርቶ እኔነቴ ጠብ ሲል በውስጤ ይክሰም አሮጌዬ ሲነካኝ የአንተ ቃል ይለወጥ ኑሮዬ አልሁንብህ ብርቱ የምይለወጥ ሰው አልሁን ቃልህ ወጥቶ ከቶ ማይዳስሰው ለብርቱ ለቃልህ ብርታቴን ልፍታና ልሸነፍ ለምክርህ ነገዬ እንዲቀና ሸክላ ሰሪው ጌታ ሸክላህን አብጀኝ ትላንቴን አፍርሰህ እንደገና ስራኝ እምቢ ባልኩ ፈንታ ልታዘዝህና ልማረክ ለቃልህ እጆቼን ላንሳና አሜን ✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት 📆 ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም ተጻፈ ይቀላቀሉ  ➟ @amanawikal ለሌሎች ያጋሩ  ➟  @amanawikal
نمایش همه...
21👍 11🙏 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ይቀላቀሉ  ➟ @amanawikal ለሌሎች ያጋሩ  ➟  @amanawikal
نمایش همه...
🙏 39 15🥰 13
Ejig Destegna.mp36.56 MB
👍 30 15👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
ይቀላቀሉ  ➟ @amanawikal ለሌሎች ያጋሩ  ➟  @amanawikal
نمایش همه...
44👍 20🔥 3
ጸሎት ቅዱስ ህያው እና ዘላለማዊ፣ ለዘመንህ ቁጥር የሌለህ፣ ለግዛትህ ድምበር የሌለህ፣ ከዘላለም በፊት የነበርክ፣ ከፊት ያለውን ዘላለም የምትመለከት፣ ጨለማ በፊትህ የማይጨለም፣ የሰማይን ስፋት በስንዝር የምትለካ፣ የምድርን ዳር ያለከልካይ የምትመለከት፣ ሁሉን ያስገኘ የሁሉ የበላይ፣ አቻ የሌለህ ሁሉኝ ቻይ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ተመስገን። ምንም አለ ከመባሉ በፊት የነበርክ፣ ሁሉ የለም ቢባልም ብቻህን ጸንተህ የምትኖር፣ የጊዜ ቀመር የማይለካህ፣ የጸሐይ ብርሃን የማያደበዝዝህ፣ የባህር ጥልቀት የማይርቅብህ፣ የሰማይ ስፋት የማይከልልህ፣ የምድር አድማስ የማይጋርድህ፣ የፍጥረት ሁሉ ገዢ እና ባለቤት ቅዱስ አምላካችን ሆይ እናመሰግንሃለን። አሜን ✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት 📆 ስኔ 21  2016 ዓ.ም ተጻፈ ይቀላቀሉ  ➟ @amanawikal ለሌሎች ያጋሩ  ➟  @amanawikal
نمایش همه...
🙏 66 13👍 8👏 2🥰 1
#ዘጠኙስ_ወዴት_አሉ ? አስር ሰዎች ከኃጢአታቸው ለመንጻት በጌታ ፊት ቀረቡ እንደመሻታቸው ሁሉም ከኃጢአታቸው ነጹ ነገር ግን መፈወሱን አውቆ እግዚአብሔር ሊያከብር የቻለው አንዱ ብቻ ነው። ጌታም ዘጠኙስ ወዴት አሉ? በማለት ተናገረ። ይህን ጽሑፍ በማንበብ ላይ ያለህ ወንድሜ ወይም እህቴ አንተ ከዬተኛው ወገን ነህ? ምስጋናውን ከበሉ ከዘጠኙ ወይስ እግዚአብሔርን እንዳከበረው እንደ አንዱ? እግዚአብሔር በባህሪው ምስጉን ነውና የሰው ምስጋና ምንም ከፍ አያደርገውም ምንምም ደግሞ ዝቅ አያደርገውም። ምክንያቱም እርሱ እግዚአብሔር ያለሿዋሚ የነገሰ ያለምርጫ የሚገዛ ጌታ ነውና። ነገር ግን እግዚአብሔር ባደረገላችሁ ነገር ምን ያኽል ጊዜ አመሰገናችሁት? ምን ስጥቶኝ ላመስግነው እንዳማትሉኝ ተስፋ አለኝ። እስኪ ትንሽ የሚመስለውን ነገር ግን ያላችሁን ነገር አስተውሉ። እና እግዚአብሔርን ለማመስገን በቂ ምክንያት የላችሁም? እግዚአብሔር ስለምፈጠሩ፣ የውስጥ እረፍት ሰጪ በመሆኑ፣ በሰላም ምሽትን የሚያነጋ በመሆኑ፣ ከዘላለም ሞት አዳኝ በመሆኑ፣ ታምኖ የሚያኖር በመሆኑ፣ አቅፎ የሚያባብል በመሆኑ፣ ከክፉ ፍላጻ የሚታደግ በመሆኑ፣ ታማኝ እረኛ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባዋል። ሰው አጥታችሁ እግዚአብሔር ደርሶላችሁ እንደሆነ አመስግኑት፣ በችግር ውስጥ ጠርታችሁት አለው ብሎ ከሆነ አመስግኑት፣ በሀዘን ምጥ ውስጥ ሆናችሁ አይዞን ብሏችሁ እንደ ሆነ አመስግኑት፣ አይነጋልኝም ያላችሁትን መሽት አንግቶ በህይወት አቁሟችሁ እንደሆነ ክበር በሉት፣ አበቃ ብላችሁ እርሱ ግን አይ ብሎ እንደ አዲስ ነገሮችን አስተካክሎላችሁ እንደሆነ ተመስገን በሉት። የተቆረጠ የመሰለ ተስፋችሁን ቀጥሎት እንደሆ አክብሩት፣ ተቋጨ ያላችሁትን ዘመን አድሶላችሁ እንደሆነ ከፍ በል በሉህ፣ ለቅሷችሁን በደስታ ቀይሮት እንደሆነ አመስገኑት፣ ሞታችሁን በህይወት ተክቶት እንደሆነ ተመስገን በሉት፣ እርዳኝ ብላችሁት አመት ረድቷችሁ እንደሆነ ለእርዳታው እውቅና ስጡ የምስጋናን ነዶ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ። ምንም ያልሰጣችሁ ቢመስልም እስኪ ምን እንደ ሰጣችሁ አስተውሉ። እግዚአብሔር ምን ሰጥቶኝ ላመስግነው የሚል ሰው ሰምቼ እንደማውቅ አስታውሳለሁ። ጠላት እግዚአብሔር እንዳታመሰግኑ ሊያደርጋችሁ ሲፈልግ እግዚአብሔር በህይወታችሁ ያዳረገውን እንዳታስተውሉ ያደርጋል። ይህም አመስገኝ እንዳትሆኑ ያደርጋችኋል። የእግዚአብሔር ስራው በህይወታችሁ ታውቆም እንደ ዘጠኙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ምስጋና መሸሸግ ደግሞ ሌላ ትልቅ ችግር ነው። ለአስተዋይ ትውልድ የምስጋናው ርዕስ እልፍ ነው። ምስጋናውን አትሸሽጉ፣ ተደርጎለት እንዳልተደረገለት፣ ተስጥቶት እንዳልተሰጠው፣ ተርፎ እንዳልተረፈ፣ እጅግ ተረድቶ ምንም እንዳልተረዳ አንሁን። ጸሎት እግዚአብሔር ሆይ ባደረክልኝ ነገር ሁሉ ምስጋናህን በልተን እና ሸሽገን እንደሆነ ምህረትህ እንለምሃለን። ያልተሸሸገ ምስጋናችን ለአንተ ይሁን ለምትረዳን ምስጋና ይድረስህ፣ አናልፈውም ያልነውን በአንተ አልፈናልና እናመሰግንሃለን እናከብርህማለን። አቤቱ አምላካችን ሆይ ምስጋና ለአንተ ይሁን። በስራህ ልክ ልናመሰግንህ ባንችልም ከምስጋናህ አንደባችን እንዳይባዝን በጸጋህ ከልለን። አሜን ✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት 📆 ስኔ 20  2016 ዓ.ም ተጻፈ ይቀላቀሉ  ➟ @amanawikal ለሌሎች ያጋሩ  ➟  @amanawikal
نمایش همه...
36🙏 24👍 18
እምቢ ብሎ ማመስገን የህይወታችን ክፍል ብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ገብቶ ለምስጋና የማይጋብዝ ህይወት እያሳለፍን ይሆናል። ብዙ ጊዜ በምስጋና ፈንታ ማማረር በውዳሴ ፈንታ ማጉረምረም የህይወታችን መልክ ሆኖ ሊታይ ይችላል። አስተውሉ ለማመስገን ያለን ምክንያት እጅግ እልፍ ነው። ለቁጥርም የሚታክት ነው። ጠላት እግዚአብሔር ላይ አጉረምራሚ እንድሆን በትጋት ይሰራል። ለዚህም ካለን ነገር ይልቅ ጉድለታችንን አጉልቶ ያሰየናል። ቁጭ ብለን ባዶ የሆነውን እንድንቆጥር በማድረግ ምስጋናችንን ከአንደባችን ይነጥቃል። አመሰጋኝ መሆን እንዳንችል አይናችንን ጉድለታችን ላይ እንድናደርግ ያደርጋል። ከጠላት የትኩረት ቀጠና አይንን በማንሳት እግዚአብሔር ያደረገልንን ውለታ በማሰብ እና በማሰላሰል ጠላትን እምቢ ብሎ ማመስገን ይገባል። ብዙ ነገር ቢደራረብም እምቢ ብሎ እግዚአብሔርን ማመሰገን ንቁ መሆን ነው። የጠላት ሀሳብ ላይ መንቃት እና ምክሩን እምቢ ማለት ነው። ተቆጥሮ ከማያልቀው ከእግዚአብሔር ምህረት፣ ይቅርታ፣ ቻይነት፣ እና አኗሪነት በላይ ትንሹ ክፍተት አይናችን ላይ እንዳይጎላ መጠንቀቅ ያሻል። የህይወት ጥቃቅን ክፍተቶች በጊዜያቸው መፈታታቸው አይቀርም ነገር ግን ነገ ለሚቃና ነገረ ዛሬ በእግዚአብሔር ላይ ማጉረምረም ክስረት ነው። የጠላትን ትኩረት እምቢ ማለት መቻል እና የማይነጥፈውን የእግዚአብሔር እጅ ተስፋ ማድረግ የክርስትና በረከት ነው። እርግጥ ነው ክፍተቱ ብዙ ነው የጎደለውም እንደዛው። ነገር ግን ያለንን ቆጥረን ጨርሰን ይሆን? ብር አይኖረን ይሆናል ነገር ግን ጤናን በብር እንኳን መግዛት ያቀታቸው ስንቶች ይሆኑ? አዎ የከበሩ ማዕድናት በእጃችን የሉም በእጃቸው ባለው የከበረ ማዕድን ሰላም መለወጥ ያቃቸው እና ያላቸው ነገር ጤናን ሊያመጣላቸው ያልቻሉትን ስንቱ ይቁጠራቸው? አስኪ በዚህ ልክ ጥቂት የመሰለንን ነገር ግን ያለንን ውድ ነገር እናስተውል። ህይወት ጣዕም የሚኖረው በምስጋና ውስጥ እያለፉ ለመቀበል በመዘጋጀት ነው። በማጉረምረማችን የሚለወጥ ምንም ነገር ባይኖርም ምስጋናችን ግን ከነገሮች በጎውን እንድንመለከትና እግዚአብሔር ላይ ያለን መተማመን እንዲጠነክር የማድረግ አቅም አለው። በሁኔታ ሁሉ እግዚአብሔርን ማመስገን እና አንተ ትክክል ነህ ማለት የህይወትን ማዓዛ ያውዳል። ሁኔታውን እምቢ ብሎ እግዚአብሔርን እያዩ ማመስገን ይሁንልን። አሜን ✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት 📆 ግንቦት 21 2016 ዓ.ም ተጻፈ ይቀላቀሉ  ➟ @amanawikal ለሌሎች ያጋሩ  ➟  @amanawikal
نمایش همه...
57👍 34🙏 18👏 7🥰 5
#ዋናው_እኔ_ነኝ ብዙ የበደሉህ ዋኖች ይኖራሉ እንደ እኔ ግን አልበደለሁም፣ አንተን ያስከፉህ ቢሰለፉ ከፊት የምገኘው እኔ ነኝ፣ በኃጢአት ባህር መዋኘት ድሎት የሆናቸው ብዙ አሉ ዋናው ግን እኔ ነኝ፣ ልክ ባልሆነው ጎዳና የሚራመዱ አሉ መሪያቸው ግን እኔ ነኝ፣ አንተን በመቅረብ ፈንታ ጀርባ የሰጡህ አሉ እኔ ግን እብሳለሁ፣ ጌታዬ መድሃኒቴ ኢየሱስ አንተን የምትል ነፍሴ በስጋ ድካም ውስጥ ሳለ አለሁሽ ያልካት አንተ ነህ። እኔ መማርህ እንዴት ያለ ምህረት ነው። የምህረትህ ድልድልነት ለእያንዳንዱ መንገዴ መሸጋገሪያ ሆኖኛል። እኔን ለማዳን ወደዚች አለም የመጣ አስታዋሼ አንተ ነህ። ከነ ኃጢያቴ እንዳልጠፋ እኔ ባለሁበት ተገኝተህ ያገኘኸን ፈላጊዬ ነህ፣ በሞት ጥላ ውስጥ ያለሁትን በደምህ ድምጽ የጠራኸኝ ባለውለታዬ አንተ ነህ፣ በምድረበዳው ብቻዬን ስባዝን ና ወደ እኔ ያልከኝ አስጠጊዬ አንተ ነህ። እኔ ብቻ እንኳን በኃጢያት የጠፋው ብሆን የራስህ ጉዳይ ብለህ ከነበደሌ የማትተወኝ ለእኔ ብቻ እንኳን ብለህ ልትሞትልኝ የምትመጣ አፍቃሪዬ ነህ። ለእኔ ስትል ሰው የሆንክ አምላኬ ክርስቶስ ሆይ ክበር ተመስገን። እኔን ዋናውን ለማዳን ስትል ከሰው ተርታ ተገኝተህ በሰው ልክ የተመላለስክ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ተመስገን። ወደ ክብሬ ልትመልሰኝ ክብርህን እንደመቀመት ሳትቆጥር ከላይ ከሰማያት የመጣህልኝ አንተ ነህና አመሰግንሃለሁ። እኔን ከማርከኝማ እኔን ይቅር ካልከኝማ ማንም ትምራለህ። እኔን ዋናውን ከተቀበልክማ መዳፍህ ሰፊ ነው ሁሉን ይቀበላል። ለእኔ ስለሆነው በጎነትህ ክብር ይሁንልህ። አሜን “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤”  1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥15 ✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት 📆 ከ 1 ዓመት በፊት የተጻፈ ይቀላቀሉ  ➟ @amanawikal ለሌሎች ያጋሩ  ➟  @amanawikal
نمایش همه...
👍 36 21👏 5🤔 1
#ቅዱስ መሆን “፤ እንግዲህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።” ዘሌዋውያን 11፥45       ምድር በእርክስና ተሞልታለች። ክፉ መስራት እና ሌላውን ረግጦ ማለፍ እንደ ጀብድ የሚቆጠርበት ዘመን ላይ ደርሰናል። የሰው ልጅ በአጉአጉል ሱሶች ራሱን ጠምዶ ልማዱ ይሆን ዘንድ ፈቅዱአል። ይህ ልማድ ደግሞ አድጎ እና ጎልምሶ ባህሪይ ከመሆን የሚያግደው ነገር አይኖርም። ባህሪይ የሰው ልጅ መገለጫ ነው። አንድ ሰው ማንነቱን የሚወስነው ባለው እና በሚያሳየው ባህሪይ ነው። ባህሪይ የስብዕና መለኪያም ተደርጎ ይወሰዳል። መልካም ባህሪይ በሰዎች ዘንድ ክብርን ሲያጎናፅፍ፣ በተቃራኒው ደግሞ እኩይ የሆነ ምግባር ውርደትን ያስከትላል። እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ ሲፈጥር ፍፁም አድርጎ ነበር። ነገር ግን ኃጢአት በሰው ልጆች ላይ ከሰለጠነ በኃላ ፍፅምናውን አጣ። ነገር ግን የሰው ልጅ መጨረሻው ይህ ይሆን ዘንድ አምላክ አልፈቀደም። “ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ (ፊል 2፥7) በመስቀል ላይ በመቸንከር ድነትንም ሠጠን። ፍፁማንም አደረገን  !      “እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። ” (ማቴ 5፥48) የእግዚአብሔር ሀሳብ እና መሻት፣ የሰው ልጅ በቅድስና ይመላለስ ዘንድ ነው። ባህሪውንም በልጆቹ ላይ መትከል ይፈልጋል። ለዚህም ነው “፤ እንግዲህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ። ” (ዘሌ 11፥45) የሚለን። እግዚአብሔር ቅዱስ ነው። ከሌሎች አማልክት የተለየ። ወገኖቼ፣ ዛሬ ይህንን ጥሪ ልንቀበል ያስፈልጋል። ምን አልባት እስከዛሬ በዙሪያችን ያሉትን ሰዎች ላለማጣት እና ላለማስቀየም ስንል ተመሳስለን ኖረን ይሆናል። ነገር ግን ይህ ሊያዘልቀን አይችልም። የዘላለምን ሕይወት ወራሾች አያደርገንም። ስለዚህ ተብትበው ከያዙን ነገሮች በአምላክ ፀጋ ጥሰን እንውጣ። የባህሪያችን መለኪያ ቅድስና ይሁን። እንደ ሰማያዊው አባታችን ቅዱስ እንሁን። እግዚአብሔር ከማይከብርበት ስፍራ ራሳችንን በማቀብ እንለይ ከአነበብኩት   ይቀላቀሉ  ➟ @amanawikal ለሌሎች ያጋሩ  ➟  @amanawikal
نمایش همه...
👍 35 21🤔 2
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.