cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ሻሚል - shamil

ወደ ፊት! ልቅና እና ክብር ለአሏህ ፣ ለመልክተኛው እና ለሙእሚኖች ይሁን።

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
895
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-67 روز
-2630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

❝ለአሏህ ብሎ ለተናነሰ ሰው አሏህ ደረጃውን ከፍ ያደርግለታል❞ ረሱል ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም
نمایش همه...
⭕️የአሏህን ወዴታ ለማግኘት ብቻ ስራ📿
نمایش همه...
⭕️•ዓሹራእ ላይ አሏህ የአዩብን ችግር አንሰቶላቸዋል•⭕️ አሏህ አዩብን በሰውነታቸው ፣ በገነዘባቸው እና በልጆቻቸው ችግርን አደረሰባቸው ፤ ገነዘባቸው ጠፋ ልጆቻቸው ሞቱ ፤ ለአስራ ስምንት አመት ያክል ታመሙ። ነገር ግን በሽታቸው ትል እንደመውጣት ያለ ሰውን የሚያርቅ በሽታ አልነበረም ፤ ነቢያቶች ዐለይሂሙ ሰላም ሰውን ከሚያርቁ በሽታዎች እና በአጠቃላይ ጥሪያቸውን ከመቀበል ሰውን ከሚያርቅ ሁሉ የተጠበቁ ናቸው። ከዛም አሏህ በትግስታቸው እና ለአሏህ እጅ በመስጠታቸው ደረጃዎችን ጨመራቸው ፤ በዓሹራእ ቀንም ጤንነታቸውን እና ዓፊያቸውን መለሰላቸው ገንዘብንም ሰጣቸው ባጧቸው ልጆች ምትክም ከነበሩት የበለጠ ብዙ አድርጎ ሰጣቸው። #ዓሹራእ #የአዩብ_ችግር_ተነሳላቸው ❮❮❮t.me/shamilunkamil❯❯❯
نمایش همه...
⭕️•ዓሹራእ ላይ አሏህ ሙሳን ከፊርዐውን አድኗቸዋል•⭕️ 💡አሏሁ ተዓላ ሰይዱና ሙሳን ከሳቸው ጋር ያመኑትን እና የተከተሏቸውን በኑ ኢስራኢሎች ይዘው ከግብፅ እንዲወጡ አዘዛቸው ፤ እናም እነሱን ይዘው ጉዞ አደረጉ በዛ ቀን ቁጥራቸው ስድስት መቶ ሺ ነበር። ◉ እናም አንባገነኑ ፊርዐውን አብረውት በመሳሪያዎች እና በፈረሶቻቸው የታጠቁት ስድስት መቶ ሺ ሚሊዮን ሰራዊቶች ሊያጠፏቸው ተከተሏቸው ◉ ወደ ባህሩ ሲደርሱ በከባድ ማእበሎቹ እርስበርሱ የማታ ነበር ፤ ከዛም አሸናፊው እና ሀያሉ አሏህ በብትራቸው ባህሩን እንዲመቱት ለሙሳ ወህይን አወረደላቸው ፤ ባህሩን ሲመቱት በአሏህ ፍቃድ ከአስራ ሁለት ተከፈለ በየሁለት ክፍሎችም መካከል የየብስ መንገድ ያለው ሆነ። በዚህ መልኩም ሙሳ ዐለይሂ ሰላም እና አብረዋቸው ያሉት ሙእሚኖች ባህሩን አለፉት። ◉ ከዛም ፊርዐውን ባህሩ ውስጥ ሲገባ አሸናፊው አና ሀያሉ አሏህ ባህሩን እንደነበረው እንዲሆን እና እንዲውጣቸው አዘዘው ባህሩም እንደነበረው ሆኖባቸው እሱ እና ሰራዊቶቹ ባህሩ ውስጥ ሰምጠው አለቁ። #ዓሹራእ #የሙሳ_ከፊርዐውን_መዳን ❮❮❮t.me/shamilunkamil❯❯❯
نمایش همه...
Repost from N/a
⭕️•ዓሹራእ ላይ አሏህ ሙሳን ከፊርዐውን አድኗቸዋል•⭕️ 💡አሏሁ ተዓላ ሰይዱና ሙሳን ከሳቸው ጋር ያመኑትን እና የተከተሏቸውን በኑ ኢስራኢሎች ይዘው ከግብፅ እንዲወጡ አዘዛቸው ፤ እናም እነሱን ይዘው ጉዞ አደረጉ በዛ ቀን ቁጥራቸው ስድስት መቶ ሺ ነበር። ◉ እናም አንባገነኑ ፊርዐውን አብረውት በመሳሪያዎች እና በፈረሶቻቸው የታጠቁት ስድስት መቶ ሺ ሚሊዮን ሰራዊቶች ሊያጠፏቸው ተከተሏቸው ◉ ወደ ባህሩ ሲደርሱ በከባድ ማእበሎቹ እርስበርሱ የማታ ነበር ፤ ከዛም አሸናፊው እና ሀያሉ አሏህ በብትራቸው ባህሩን እንዲመቱት ለሙሳ ወህይን አወረደላቸው ፤ ባህሩን ሲመቱት በአሏህ ፍቃድ ከአስራ ሁለት ተከፈለ በየሁለት ክፍሎችም መካከል የየብስ መንገድ ያለው ሆነ። በዚህ መልኩም ሙሳ ዐለይሂ ሰላም እና አብረዋቸው ያሉት ሙእሚኖች ባህሩን አለፉት። ◉ ከዛም ፊርዐውን ባህሩ ውስጥ ሲገባ አሸናፊው አና ሀያሉ አሏህ ባህሩን እንደነበረው እንዲሆን እና እንዲውጣቸው አዘዘው ባህሩም እንደነበረው ሆኖባቸው እሱ እና ሰራዊቶቹ ባህሩ ውስጥ ሰምጠው አለቁ። #ዓሹራእ #የሙሳ_ከፊርዐውን_መዳን ❮❮❮t.me/shamilunkamil❯❯❯
نمایش همه...
✨ሱራቀቱ ኢብኑ ጁዕሹም ቢን ማሊክ✨            |የመጨረሻው ክፍል| ▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️ ✍ በኡስታዝ ሰኢድ አህመድ በኃያሉ ንጉስ የኪስራ እጅ ላይ ተጠልቀው የሚገኙትን በውድ ጌጦች ያሸበረቁ አምባሮች በአንድ ተራ ግለሰብ እጅ ላይ ሊውሉ ይችላሉ ብሎ ማሰቡ ትንግርት ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ይኸን ይሆናል ያሉት፥ ንግግራቸው መሬት ጠብ የማይለው፤ ከልጅነት እስከ እውቀት አንደበታቸው አንዲትንም ውሸት የማያውቀው፤ እውነተኛውና ታማኙ ሙሐመድ ﷺ ናቸውና የተባለው ነገር ጊዜን ይፈጅ ይሆናል እንጂ በገሃድ መስተዋሉ ግን አይቀሬ ነው። ሆኖም አሁን ላይ "ንጉስ ኪስራ ቢን ሁርሙዝ"  ዙፋኑ ላይ ነው። የኛ ነቢይ ﷺ እድሚያቸው ስልሳ ሶሰት ሞላና የዱንያን ሃያት ተሰናበቱ። "አቡበክር አስ ሲዲቅ" ኸሊፈቱ ረሱሊላህ ሆኑ። የነቢዩን ﷺ ናፍቆት መቋቋም ያቃታቸው ሲዲቅም ከናፍቆት ብዛት ህይወታቸው አለፈና ወዳጃቸውን ተከተሉ። ታዲያ በነዚህ ሁሉ አመታት "የሩሙ ንጉስ ኪስራ"  በተለያዩ ውድ ጌጦች የተሽቆጠቆጠ ዘውዱን ጭንቅላቱ ላይ እንደደፋና ውድ አምባሮቹንም እንዳጠለቀ ነው። "ሰይዱና ዑመር አል ፋሩቅ" አሚረል ሙዕሚኒን ሆነው ተሾሙ። በሳቸው ዘመን ብዙ አገራት ፈትሕ የተደረጉ ሲሆን በ"ሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ" መሪነት  ፈትሕ የተደረገው ታላቁ የሩም ቤተ መንግስት በዋናነት ይጠቀሳል። በአይነቱና በፈታኝነቱ እጅግ እንግዳ የሆኑ ውጊያዎችን ያስተናገዱበት እና ብዙሃን ሙስሊሞች ሰማዕት የሆኑበት ከባድ ጊዜ ነበር። የሆነው ሆኖ በሰዕድ የተመራው ጦር ያን ታላቅ ቤተ መንግስት ሊቆጣጠር ችሏል። ሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ፥ በቤተ መንግስቱ ያሉትን ጌጦች፣ መሳሪያዎችና ሌሎች ንብረቶችን በመሰብሰብ መልዕክተኞችን መርጠው አሚረል ሙዕሚኒን ዑመር ዘንድ ላኩዋቸው።  ከነዚያ የምርኮ ንብረቶች ውስጥ፥  በወርቅ ጥለት የተሰፋው የንጉስ ኪስራ ቀሚስ፣ በውድ ጌጦች ያሽቆጠቆጠው የጭንቅላቱ ዘውድ፣ ሁለቱ ውድ አምባሮቹ እና ሌሎች ውዳ ውድ ቁሶች ይገኙበታል። ያ ሁሉ ውድ ዕቃ በሙስሊሞች ግምጃ ቤት ስር ሊውል መዲና ገባና ከሰይዱና ዑመር ፊት ተዘረገፈ። ዛሂዱ መሪ ሰይዱና ፋሩቅም በሰራዊቶቻቸው ፍፁም ታማኝነት ተደንቀው በያዙት በትር እያገላበጡ ሲያዩት ቆዩ። አጠገባቸው የነበሩት ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብም የፋሩቅን ሁኔታ ካዩ በኋላ የሚከተለውን አሉ፥ "አንቱ የሙዕሚኖች መሪ ሆይ! ታማኝነታቸው ደነቃችሁ እንዴ?! አንቱ ታማኝ ብትሆኑ እኮ ነው ታማኝ ሰራዊትን ያፈራችሁት እንጂ አንቱ ብትስቱ ኖሮ እነርሱም ስተው ይገኙ በነበር።" ከዚያም ሰይዱና ዑመር (ረዲየሏሁ ዓንሁ) "ያን የበኒ ሙድሊጁን የገጠር ሰው ጥሩልኝ" አሉ፤ "ሱራቀቱ ኢብኑ ጁዕሹም ቢን ማሊክ አል ሙድሊጂይ"ተጠሩና ቀረቡ፤ ሰይዲ ፋሩቅ ከሱራቃ ፊት ቆሙና የንጉሱን ውድ ቀሚስ አለበሱት፤ ያንን ውድ ዘውድም ጫኑለት፤ ሁለቱንም አምባሮችንም ከእጁ አጠለቁለት፤ ንጉሱ ኪስራ በጣም ወፍራም የነበር ሲሆን አምባሮቹ ለሱራቃ እጅግ ሰፍተውት ወደ ትከሻው ሄደው ነበር ይባላል። ሰይዱና ዑመር ሱራቃን በዚያ ሁኔታ ሆኖ ሲያዩ እንዲህ አሉ፥ "ለአሏህ ምስጋና ይድረሰው የታላቁ ንጉስ አምባሮች ይኸው በበኑ ሙድሊጁ ሱራቀቱ ኢብኑ ጀዕሹም ቢን ማሊክ እጅ ላይ ተስተዋሉ።" የአሏህ መልዕክተኛ ሙሐመድ ﷺ በእርግጥ ዕውነትን ተናገሩ። አሏሁ አክበር! ሷዲቁል መስዱቁ ነቢይ ﷺ የገቡት ቃል በእርግጥ ተፈፀመ፤ ታሪካችንም ተፈፀመ።
نمایش همه...
አንብበው ምናልባት ከጀሀነም ሳት ነፃ ትደረግ ይሆናል! እኔ እና አንተ እናንቀላፋለን ማንቀላፋት ደግሞ በዐረበኛ ቋንቋ (السنة) ይባላል ፤ እንደዚሁ እኔ እና አንተ እንተኛለን ፤ አሏህ ደግሞ በኪታቡ እንዲህ ብሏል፡ {{لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ}} سورة البقرة- آية (255) {{ማንቀላፋት እና መተኛት አይዘውም}} ሱረቱል በቀራህ- አንቀፅ (255) እንደዚሁ አሏህ እንዲህ ይላል፡ {{لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ}} سورة الشورى- آية (11) {{አሏህ ከፍጡሮች ውስጥ አንዱንም በማንኛውም መልኩ አይመስልም እሱም ሰሚ እና ተመልካች ነው}} ሱረቱ ሹራ- አንቀፅ (11) በጥቅሉ፦ የትኛውም ፍጡር የሚገለፅበትን ባህሪ ሁሉ ፈጣሪያችንን አሏሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ አንገልፅበትም። እኔ እና አንተ በቦታ ነው የምነንኖረው አሏሁ ተዓላ ግን በየትኛውም ቦታ የሚኖር አይደለም ይልቁንም አሏህ ያለ ቦታ ያለ ነው። ይህንን ቃል ሸምድደህ ለምታየው ሁሉ አስተምረው ለምታውቀውም ሁሉ ላከው ምናልባት በዚህ ስራ ምክኒያት ከሳት ነፃ ትደረግ ይሆናል። ❮❮❮t.me/shamilunkamil❯❯❯
نمایش همه...
⭕️•ዓሹራእ ላይ የኑህ ዐለይሂ ሰላም መርከብ አርፋለች•⭕️ ◉ በዛ ታላቅ የዓሹራእ ቀን የሰይዱና ኑህ ዐለይሂ ሰላም መርከብ አረፈች ዒራቅ ውስጥ መውሲል ከተማ አቅራቢያ "ጁዲይ" ተራራ ላይም ተደላደለች ◉ ውሃ ላይ ለመቶ ሀምሳ ቀን አካባቢ ከቆየች በኋላ ◉ በውስጧ ነቢዩ ሏሂ ኑህ ዐለይሂ ሰላም አብረዋቸው ሙእሚኖች እና አሏህ መርከባቸው ላይ እንዲያደርጎቸው ያዘዛቸው እንስሳቶች ነበሩ። #ዓሹራእ #የኑህ_ሰፊና ❮❮❮t.me/shamilunkamil❯❯❯
نمایش همه...
⭕️•በዓሹራእ የአደም ተውበት ተቀባይነትን አግኝቷል•⭕️ 💡ዓሹራእ አሏሁ ተዓላ የሰይዱና አደምን ተውበት በመቀበል ልዩ ያደረገው ቀን ነው። ሰይዱና አደም የሰረቱም ወንጀል ከትላልቅ ወንጀሎች ውስጥም ሆነ ኩፍር ያልሆነ ፣ ትንሽ ወንጀል ሆኖ ውርደትን የሚያስከትል እና ደረጃን ዝቅ የሚያደርግም አልነበረም። ◉ ይልቁንም ወንጀላቸው ከባድ ሀጢያት የሌለበት ከትናንሽ ወንጀሎች ውስጥ ነበር። ◉ ሰይዱና አደም ዐለይሂ ሰላም አሏህ ተዓላ ከልክሏቸው ከነበረው ከጀነት ዛፎች ውስጥ አንዱ ከሆነው ዛፍ በልተው ነበር። ◉ አሏሁ ተዓላ እንዲህ ብሏህ፡ {{አደምም ጌታውን ወንጀለ (ትእዛዙንም) ጣሰ ከዛም ጌታው መረጠው ተውበቱንም ተቀበለው እንደዚሁም መራው}} [ሱረቱ ጧሀ 121-122] ◉ እናም ይሄ ተውበት ከሙሀረም ወር አስረኛው ቀን ላይ ነበር ማለትም በዓሹራእ ቀን ነበር። #ዓሹራእ #አሏህ_የአደምን_ተቀበሏል ❮❮❮t.me/shamilunkamil❯❯❯
نمایش همه...
🔸ሱራቀቱ ኢብኑ ጅዕሹም ቢን ማሊክ"              |ክፍል አምስት| ✍በኡስታዝ ሰዒድ አህመድ :)✨ የኛ ነቢይ ﷺ እድሚያቸው ዓርባ በሞላ ጊዜ የሪሳላን ኃላፊነት ተረከቡ። እዛው ከተወለዱባትና እጅግ በሚወዷት አገር "መካ"ም  ለአስራ ሦስት አመት ያክል ወደ ኢስላም ተጣሩ። መካዊያን ግን በነቢዩም ﷺ ሆነ እሳቸውን በሚከተሉ ምዕመናን ላይ አይከፉ ከፉባቸው። አሏህም፥ መካን ለቀው ወደ "የስሪብ" እንዲጓዙ አዘዘ። ጉዟቸውን ሊያደናቅፍ የሚመጣን ነገር ሁሉ ጠባቂው ጌታቸው በረቂቅ ጥበቡና ተቀናቃኝ በሌለው ኃይሉ ያስወግድላቸው ነበር። ሱራቃን ምን እንኳን መንገድ አዋቂነቱና ፈረሰኛነቱ እሳቸው ጋር ቢያደርሰውም፤ ጠባቂያቸው አሏህ ነውና የፈረሱ እግሮች በመሬት እንዲዋጡ አድርጎና የሳቸውን ሩህሩህነት አሳይቶ ሊገድል የመጣውን ሰውዬ በሳቸው ማንነት ተማርኮ እጅ እንዲሰጥ አደረገላቸው። የመካ ሙሽሪኮችም ቢሆኑ እሳቸውን ለመግደል ከመቋመጥ፣ ታጥቀውና ተሰናድተው ዳናቸውን በማነፍነፍ ከገቡበት ዋሻ በሩ ድረስ ቢደርሱም፤ ጀሊሉ በረቀቀው ጥበቡ "በሸረሪት ድር" እና "በእርግብ ዕንቁላል" ውዱን ወዳጁን ጠብቋል።   /አሏህ ሲጠብቅ/  ምን እንኳ የአሞራ ዱካን አነፍንፎ መንገድን የማወቅ መክሊትን ቢያዳብሩም፤ የራቀን አቅርቦ የሚያይ አማታሪ ዓይን ቢኖራቸውም፤ ዳሩ፥  አሏህ ሲጠብቅ ከቤቶች ሁሉ በጣም ደካማ የተባለው "የሸረሪት ድር (ቤት)" ከሰማይ ጠቀስ የብረት ግንቦች በላይ ከለላ እንዲሆን ያደርጋል።  ገደሉን ሜዳውን በማቆራረጥ ያልደከመን ገላ እና ያልጨለመን ተስፋ "እርግብና ዕንቁላሏ" ተስፋ ቢስ እንድታደርጋቸው ያደርጋል። እንዲህ አይነቱ  የጀሊል ጥበቃ ሳይለያቸው ሰይዳችን ﷺ የስሪብ በሰላም ገቡ። ከዚያም በክፉ ወረርሽኟ፣ በአሩራማ ሙቀቷና በበረሃማነቷ የማትመቸውን "የስሪብን" ከመጠሪያ ስያሜዋ ጀምረው፥ ገፅታዋንም አየር ንብረቷንም ቀየሩላት። "መዲና" ሲሉ ሰየሟት፤ በሳቸው በርታለችናም "አብሪይቷ" (ሙነወራ) የሚል ማዕረግም ታከለላት። ከዚያም ትልቁ ሰው ﷺ እልፍ አእላፍ ተከታዬችን አሰልፈው  እዬወደዷት የለቀቋትን፤ ሁሌም የምትናፍቃቸውን አገር "መከቱል ሙከረማህን" ፈትሕ አድርገው በድል ገቡ። የዚህን ጊዜ ነበር "ሱራቀቱ ቢን ማሊክ" በድጋሚ ነቢያችንን ﷺ በአካል የማዬቱን ዕድል ያገኘው። ሰይዳችን ሱራቃን ገና ከማዬታቸው አስታውሰው አወቁት። እርሱም ውድ እጃቸው ላይ እጁን በማሳረፍ እስልምናውን ይፋ አጸደቀ።     አሁን ላይ ሱራቃ እንደ ነቢያችን ﷺ የሚወደው፤ ከሳቸው የሚያወዳድረው ሆነ በሳቸው የሚለውጠው አንዳችም ነገር የለም። ለመቶ ግመሎች ብሎ እሳቸውን ሊገድል የወጣበትን ቅፅበት ሲያስብ ልቡ በኃፍረት ይደማል፤ በፀፀት ይዋጣል።      ✨ "አሁን ላይ ለሱራቃ፥ መቶ ግመሎች ይቅርና በዱንያ ያሉ ግመሎችና ነዋያቶች ሁሉ ቢሰበሰቡለትም ከሙሐመድ ﷺ ከአንዲቷ የፀጉር ዘለላ ወይም ከጥፍራቸው ቅንጣት ቁራጭ ጋር ፈፅሞ አይነፃፀሩም። ✨ ሙሐመድን ﷺ ጥቂት አወቃቸው፤ እጅግ በጣም ወደዳቸው፤ አምኖባቸውም ተከታያቸው ሆነ። ✨ "የኪስራ የእጅ አምባሮች" ጉዳይስ ምን ላይ ደረሰ ✨ በእርግጥ የኪስራ አምባሮች ለአሁኑ ሱራቃ ምንሙም አይደሉም። ምክኒያቱም የርሱ ሃብቱም ወረቱም ቀኑም ሌቱም በጠቅላላው ሃያቱም በሙሐመዲይነት ተወርሷልና። ታዲያ በታማኙ ነቢይ ﷺ ቃል የተገባለት የንጉሱ አምባሮች ጉዳይስ ፍፃሜው እንዴት ነበር??? ይቀጥላል•••
نمایش همه...