fa
Feedback
TheDeepThingsOfGod

TheDeepThingsOfGod

رفتن به کانال در Telegram

Glorious Church the bride of Christ. Rapture ready!

نمایش بیشتر
1 810
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
Get ready! ተዘጋጁ! እግዚአብሔር ለረጅም ዓመታት የሰራቸውን! ራሱን የገለጠላቸውን! ፍጹም የሆነውን እውነት የገለጠላቸውን! የመንፈስን ሃይል የሰጣቸውን! ልጆቹን የሚገልጥበት ጊዜ ተቃርቧል! በዚህ ጊዜ የሌላ ዓለም ፍጥረታት(aliens) ምድር ላይ እየተመላለሱ ነዉ ይባላል! አይናችሁን ከፍታችሁ ተመልከት! የእግዚአብሔር ልጆች እናንተ ናችሁ!!! @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

ይሄንን መልእክት ለወዳጆቻችሁ ሁሉ ሼር አድርጉ! ወደ ጉሩፖችም! ፀጋ ያግኛችሁ!

...በመጀመሪያ እግዚአብሔር.... የዘፍጥረት መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያው መጽሐፍ: የመጀመሪያ መጽሐፍ የመጀመሪያው ምዕራፍ እና የመጀመሪያው ቁጥጥር: የሚጀምረው "በመጀመሪያ እግዚአብሔር" በማለት ነዉ። ይህ ለእኛ ለምናምን እጅግ ጥልቅ መልእክት ያለው መንፈሳዊ መርህ ነዉ። ከእግዚአብሔር የመጀመር በረከቶች። የመጽሐፍ ቅዱስን ተጽዕኖ አስቡት! በዓለም ታሪክ: ፖሎቲካ እና ማህበራዊ ሁኔታዎች ላይ ከዚህ በፊት በነበሩ አሁን ባሉ እና ወደፊት በሚኖሩ ሰዎች ላይ እና የተለያየ ስርዓት ግንባታ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግልጽ የሆነ ተጽእኖ አሳድሯል ያሳድራልም! አስቡት የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል በዓለም ሁሉ የተሰራጨ መጽሐፍ ይቅርና አንድም ነገር የለም! ከዚህም ሁሉ በላይ ....መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ብቻ ሳይሆን የእውነት መለኪያ መሆኑን ትክክለኛ ብቻ ሳይሆን የትክክለኝነት ሚዛን መሆኑን አስቡት! ይህ የሆነበት ምክንያት አጀማመሩ እና ጀማሪው ነዉ ብዬ አምናለሁ። "በመጀመሪያ እግዚአብሔር" እነዚህ ቃላት ፊደል ብቻ እንዳልሆኑ እኛ የምናምን እናውቃለን! ለእኛ ለምናምን ሕይወትና መንፈስ ከእነዚህ ፊደላት በላይ ሆኖ በግልጽ ይነበባል! በመጨረሻም ማለት የምፈልገው እውነት: ሰዎች የሚጀምሩት ነገር ሁሉ እውነተኝነቱ: ትክክለኝነቱ ቀጣይነቱ እና በዓለም ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ በቀጥታ አጀማመሩ ለይ የተደገፈ ነዉ! ለዚህ ነዉ ደቀመዛሙርት የትኛውንም ነገር ስንጀምር "ከእግዚአብሔር" መጀመር ያለብን። ትምህርት: ስራ: ንግድ: አገልግሎት: እጮኝነት: ትዳር: ልጆች...ወዘተ የነገራችን ሁሉ መጀመሪያ መሆን ያለበት እግዚአብሔር ነዉ። 'ትክክለኛ ነገር ሁሉ የሚጀምረው ከእግዚአብሔር ነዉ'። ለምሳሌ የእጮኝነታችሁት እውነተኝነት በምን ማወቅ ትችላላችሁ? ቀላል ነዉ! መልሱ የሚሆነው: የጀመራችሁት ከማን ነዉ? የጀመራችሁበት መንፈስ ምንድነው? ጥቅም ነዉ: መልክ ነዉ? ወይስ እግዚአብሔር? "በመጀመሪያ እግዚአብሔር" የሚል ሕይወት እና መንፈስ ያለው ነገር ሁሉ ትክክል ነዉ: ይቀጥላል! ተጽእኖም ይፈጥራል! ማነው የእናንተ መጀመሪያ ? የነገራችሁ መጀመሪያ? ቀናችሁን የምትጀምሩት ከማን ነዉ? ንግድ: አገልግሎት: ትዳር ወዘተ የምትጀምሩት ከማን ነዉ? መልሳችሁ ከእግዚአብሔር ነዉ ከሆነ: ነገሩ ትክክል ነዉ! እውነት ነዉ! ይቀጥላል! ይበዛል! ተጽእኖ ይፈጥራል! ዘላለማዊ ትርፍ ያስገኛል!!! #𝓿𝓲𝓬𝓽𝓸𝓻#𝓻𝓮𝓿𝓮𝓵𝓪𝓽𝓲𝓸𝓷𝓼 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

ሪቫይቫል በግል ሕይወታችሁ ይጀምራል: በመቀጠልም ወደ ማህበሩ(ወደ ቤተክርስቲያን) ያድጋል ቤተክርስቲያን በፍጹም የመንፈስ አንድነት እና ፍቅር ከተቀበለችው ሃገሩን ሁሉ ይሞላዋል። @TheDeepThingsOfTheSpirit

"አይበልጥብኝም! ምንም ከኢየሱስ!" #ተባረኩበት! 👇👇👇👇ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

"አይበልጥብኝም! ምንም ከኢየሱስ!" #ተባረኩበት! 👇👇👇👇ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

“ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።” — ሮሜ 8፥11 👉የእግዚአብሔር ልጆች ከላይ ያነበባችሁትን የመጽሐፍ ክፍል: የምንፈታበት የተለመደ አፈታት አለ: አስተውለን ማየት ግን ይጠይቃል: ይህ ቃል የሚያወራው የታመሙ የሰውነት ክፍሎችን ወይም የሞተን የሰውን ክፍል ስለማደስ ወይም የሞተን ስለማስነሳት ብቻ አይደለም! "ለሚሞተው ሰውነታችሁ ሕይወትን ይሰጠዋል" ማለት: ከኃጢአት በላይ ያደርጋችኋል ማለትም ነዉ! ምክንያቱም ኢየሱስን ከሙታን ያስነሳው መንፈስ ነዉ የሚለው! አስተውሉ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው መንፈስ አይደለም የሚለው! ከሙታን መነሳት እና ከሞት መነሳት ትልቅ ልዮነት አላቸው! ኢየሱስ መስቀል ላይ እኛ የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ እርሱ #ኃጢአት እንደሆነ አስታውሱ! (2ኛ ቆሮንቶስ 5:21)ኢየሱስን ከኃጢአት ለይቶ ነው ያስነሳው! አንተንም አንቺም ፈጽሞ ከኃጢአት የመለየት ሥራ ይሰራል!....ይህ የህይወት መንፈስ ከኃጢአትም በላይ የሚያደርግ ነዉ! አሜን!! 👇👇👇join the chariot 👇👇 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️በጣም ብዙ ልጆች ከኃጢአት ከዓለም እና ከሰይጣን በላይ እየሆኑ ነዉ....ምን ማለት እችላለሁ ክብር ለኢየሱስ ይሁን!! ሼር እያደረጋችሁ ሌሎችም ነጻ ይውጡ! “እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል።”” — ዮሐንስ 8፥32

#አስገራሚ_ምስክርነት!!! #ከፖርኖግራፊ እና ከሰይጣን #ኩነኔ ነጻ ሆኛለሁ.....!!! ፍጹም ብርሃን በራልኝ ይላል ወንድማችን ..አንብቡት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ...እባላለሁ። ጌታ ያረገልኝን መመስከር እፈልጋለሁ። 👉በመጀመሪያ በነገር ሁሉ የረደኝን ጌታ አመሰግነዋለሁ። ከ9ነኛ ክፍል ጀምሮ ፓርኖግራፊ የመመልከት ልምድ ነበረኝ። በጣም deep የሆነ ባይሆንም በሁለት ሳምንት አንዴ እራሴን እዛ ዉስጥ አገኝ ነበር። ከልጅነቴ አንስቶ church ዉሰጥ ስለነበርኩ፡ ንስሃ ገብቼ ፣ተፀፅቼ ፣ተናዝዤ,,,,, ግን totally መመለስ አልችልም ነበር።አሁን መለስ ብዬ ሳይ,,,ፈጽሞ ነጻ መዉጣት እናዳልችል ስየደርገኝ የነበረዉ፦ኩኑኔዉ ነበር።ራዥም ለምባል ጊዜ እንኳን ሳላይ ቆይቼ ባለፈዉ ስህተቴ በጣም እኮነናለሁ።ከዚህ የተነሳ ጭንቀት፣ ጸጸት ስሰማኝ ወደ አሮጌው ልምምድ እመለሳለሁ።ከለፈዉ ስህተት እስረት ታስሬ፡ ከትናንት መፈታት አቅቶኝ፡ጌታ ያየልኝን(በሮሜ 8vs29:30) እግዚአብሔር በልጁ ያሰበልኝን ዘላለማዊ ማንነት ጥዬ የባርነትን ህይወት ስኖር ነበር። ግን በዚህ ዉስጥ ጌታ በተባረከ ወንድም Victor በኩል፡ ነጻ አወጣኝ ፤የእዉነት ብርሃን አበራልኝ።በልቤ ጨላማ ዉስጥ የቃሉን እዉነት ብርሃን አበራልኝ።በርግጥ ለብዙ ጊዜ የልምድ ክርስቲና ዉስጥ ነበርኩኝ።ሐዋ ሥራ 18:25,26,,,አጵሎስ እዉነቱ እስከሚበራለት ድረስ በመንፈስ ስቃጠል ነበረ፤ አቂላና ጵርስቂላ ከፊት ይልቅ እዉነትን እንደገለጡለት ፨፨፨ ለእኔም በVictor በኩል ይ ሆኖልኛል።ገላ5:1,,,አሁን ነጻ ነኝ!,,,ገላ4:6,7,,,አሁን ልጁ ነኝ!,,,,አሁን የእግዚአብሔር ወራሽ ነኝ!,,,,2ጴጥ 1:4,,,የመለኮቱ በህርይ ተካፋይ ነኝ!,,,በእርሱ በእርግጥ ሆኜአለሁ!,,,it is my eternal identity,,,i repeat it,,it's my eternal eternal eternal eternal,,,,identity,,, 2ቆሮ 5vs 17,,,,i am new creation!!!!!!!!!!!!!! በእርግጥ ለቅዱሳን ወንድመቼ ላስተላልፍ የሚፈልገዉ፡ሳይጣን የሚላችሁ አብዘኛዉ ዉሸት ነዉ።መቼም ዛላለማዊ ማንነታችሁን አይነግራችሁም፡ምክንያቱ ምን መሰላችሁ?እርሱ የዉሸት አባት,,,ምንጭ,,,ባለቤት,,,ነዉ።እርሱ እዉነት የለዉም።ትንሹ ስህታታችሁን አግዝፎ ያሳያል።ለምን መሰላችሁ?መልካሙን ስራ ልያስጥላችሁ፡ወደ ባሰ ጥፋት እንድትገቡ፡ለአብነት እኔ ብዙ ራዕይ አላማ ያለኝ ልጅ ነኝ። ፖርን ከማየት ያለፈ ወደ ዝሙት ህይወት እንድገባ ነበር።ከዛ ዘመኔ ሁላ እንድበላ፡ከዛ መች ልተዉ፡ልያርድ+ልያጠፋ>>>ዘላላምን,,,ልያበላሽ፡ዛሬ ምነልባት መጠኑ ይለያይ እንጅ ፓርን photo,video,... በአንድም በሌላ ያለየ ፣ያልተጋለጠ ወጣት specially ታዳጊ ወጣት አለ ማለት ይከብዳል።ምናልባት በዝህ ችግር challange ዉስጥ ያላችሁ :ለእናንተ የከበዳችሁ ለጌታ ብታቀርቡ በጣም በጣም ቀላል ነዉ።(እናንተ ሸክም የከበዳችሁ ወደ አኔ ኑ ይላችኃል።) ለቅዱሳን ወንድሞች አዉሩ ፤ አጋሩ፤ ምናልባት እነርሱ የሆነ ጊዜ አልፈዉበት የመጡቀት ይሆናል።,,,,''የተሰበሰበና በአላማ የተመራ ''ሕይወት ዉስጥ ግቡ። በመንፈስ ተመሩ፤ እንደመንፈስ ፈቃድ አስቡ፤እንደ መንፈስ ፈቃድ ዋሉ+እደሩ ደግሞም ኑሩ!!!!! በምገርም ሁናቴ ኃጥአት ማድረግ ቀርቶ ለመሰብ ''ጊዜ አይኖራችሁም''። በዝህ experience ያልተነካካችሁ ...: እኔ መጀመሪያ expose አንድሆን ያረገኝ ነገሮችን ነክቼ ለማየት ያለኝ ፊላጎት ነበር።ስለዝህ ''አጥብቃችሁ ሽሹ'' እላችኃለሁ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ወንድም Victorን ለመሰግነዉ እወዳለሁ። ጌታ በነገር ሁሉ ሁሉ ባለጠግነቱን ያብዛልህ!!! 1ቆሮ 1:6 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ የክርስቶስ ኢየሱስ ሰላምና ጸጋ በመንፈስ ቅዱስ ህብረት ይብዛላችሁ!!! 2ቆሮ 13:14 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ በመጨረሻ :ይህንን ብዬ ልደምድም፦ “ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ ''የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ''፥ ''ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ'' ''ቅኖችና አለ ነውር'' እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ''ከፊት ይልቅ'' እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ።” — ፊልጵስዩስ 1፥9-11 በክርስቶስ ፍቅር እወዳችኃለሁ!!! ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ 👇👇👇 join the chariot👇👇 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

You are free...... ነጻ ነህ/ ነሽ! ነጻነታችሁን ተቀበሉ በዚህ ማለዳ! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

The power of resurrection will be at work in you! Receive by faith! ኤፌሶን 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁹ ለእኛ ለምናምነውም ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነውን ኀይሉን እንድታውቁ እጸልያለሁ። ይህም ኀይል እንደ እርሱ ታላቅ ብርታት አሠራር፣ ²⁰ ክርስቶስን ከሙታን ሲያስነሣውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው የታየው ነው። ይህ ለሙታን ሕይወትን የሚሰጥ የትንሳኤ ሃይል በአንተ/በአንቺ ይሰራል! እመን ብቻ!! @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

#falling_in_love+with+Jesus! #the+best+thing+i+ever+done! ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ I love him because He loved me first! 👇👇 join the chariot 👇👇👇 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

ከሁሉ የሚበልጥ የእግዚአብሔር ሃይል አሁን መገለጥ መጀመር አለበት! ደግሞም ይገለጣል! በእኛ በምናምን! 🔥 #የትንሳኤው_ ሃይል!!! @TheDeepThingsOfTheSpirit

አሁን ጫዋታ የምንጫወትበት ጊዜ አይደለም! የትንሳኤው ሃይል በእኛ መስራት እንድጀምር የምንጸልይበት ጊዜ ነዉ! 👉ሃገራትን ለመፈወስ ተዘጋጁ! 👉ቤተሰዎቻችሁን ለመፈወስ ተዘጋጁ! 👉ከአንተ/ከአንቺ ቤተሰብ በዚህ መሪዝ ተነድፎ የሚወድቅ አይኖርም! ምክንያቱም አንተ/አንቺ አለሽ/አለህ! የትንሳኤውን ሃይል መተዋወቅ ጀምሩ!

23 peoples died in Norway after vaccination! But they silenced the Media! May be many more happened. አሜሪካ ኖርዌይ 23 ሰዎች የ ኮቪድ ክ
23 peoples died in Norway after vaccination! But they silenced the Media! May be many more happened. አሜሪካ ኖርዌይ 23 ሰዎች የ ኮቪድ ክትባት ከተቀበሉ በኃላ ሞተዋል: ሚድያው ግን እየሆነ ያለውን አይዘግብም: ምክንያቱም ቁጥሩ ከዚህ ከፍ ያለ ነዉ! እቅዳቸው በጥቅት አመታት ውስጥ 3 ቢሊዮን ሰዎችን እንደ ቅጠል ማራገፍ ነዉ: አፊሪካ ደግሞ ዋና ታርጌታቸው ናት! የእግዚአብሔር ልጆች አገራትን ለመፈወስ ተዘጋጁ! ጸልዩ! እግዚአብሔር የትንሳኤውን ሃይል በአንዳንዶቻችን ላይ ያፈሰዋል! #GetReady To heal Nations!!! #ThePowerOf #Resurrection is going to be at work in Us! @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

አምልኮ....አብራችሁን አምልኩ...ተባርካችኋል!!😍😍😍😍😁😁😁🔥🔥🔥

!.....ከእግዚአብሔር የተወለደ.... ዓለምን....እና በዓለም.... ያለውን ሁሉ አሸንፏል.....! ((ይነበብ)) “ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።” — 1ኛ ዮሐንስ 4፥4 "አሸንፋችኋቸውማል"! አስተውሉ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው "አሸንፋችኋል" አይደለም! "አሸንፋችኋቸውማል" ነዉ የሚለው። ይህ ማለት አንድ ነገር ብቻ አይደለም ማለት ነዉ ያሸነፍነው! በዓለም ዓለምን እና በዓለም ያለውን ሁሉ አሸንፈናል! ሌላ እንድታስተውሉ የምፈልገው "ታሸንፏቸዋላችሁ" እያለ ተስፋ እየሰጠን አይደለም! የሚነግረን #የተጠናቀቀ ነገር ነዉ። አሸንፈናል! ስለዚህ ዓለምን እና በዓለም ያለውን ለማሸነፍ የምናደርገው የተለየ ነገር የለም! ያሸነፈ ሰው የሚያደርገው: በድል ንቃተ-ሕሊና (The consciousness of victory) መመላለስ እና ከጠላት ቀጠና ምርኮን መበዝበዝ ነዉ። ከዓለም እና በዓለም ካለው ጋር ያለውን ውጊያ ያሸነፈልን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ። አስተውሉ ከዓለም እና በዓለም ካለው ጋር ያለ ውጊያ ነዉ ተጠናቋል ያልኩት እንጅ "ከመንፈሳዊ ሃይላት" ጋር አሁንም ውጊያ አለን! በነገራችን ላይ ይህኛውም ውጊያ ለድል የምናደርገው ሰይሆን ከድል የምናደርገው ውጊያ ነዉ። ለድል መዋጋት እና ከድል መዋጋት ይለያያሉ! ለማንኛውም ዛሬ የማወራው ዓለምን እና በዓለም ያለው ላይ ስላለን ድል(አሸናፊነት) ነዉ። 👉ዓለም ምንድነው? በዚህ ክፍል ላይ መንፈስ ቅዱስ "ዓለም" በማለት የሚያወራውን ስለ "ኮስሞስ" አይደለም: በዓለም ስላለው "የተበከለ ስርዓት" (Corrupt system) ነዉ። ስለዚህ ዓለምን አሸንፈናል! ስንል በዚህ ዓለም ካለው የተበላሸ ስርዓት (እግዚአብሔራዊ ካልሆነ ስርዓት) በላይ ነን! ለዚህ ስርዓት ተገዥ አይደለንም! የሚገዛን እና የሚያስተዳድረን የራሳችን ስርዓት አለ ማለት ነዉ። ሃሌሉያ! ይህም ፍጹም የሆነ እና ዘላለማዊ አምላካዊ ስርዓት ነዉ( Eternal and Godly System)! አሜን!! 👉በዓለም ያለውስ ምንድነው? "በዓለም ካለው በላይ ናችሁ" ስለን መንፈስ ምን እያለን ነዉ? በዓለም ያለው ሁሉ በሦስት ነገር ይጠቀልላል: ....የመጀመሪያው #የሥጋ_ምኞት ነዉ። ሁለተኛው #የዓይን_አምሮት ሦስተኛው ደግሞ #ስለ_ገንዘብ_መመካት ነዉ። “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።” — 1ኛ ዮሐንስ 2፥15-16 ስለዚህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት ዳግም ስንወለድ ለስጋ ምኞት፣ ለዓይን አምሮት እና ስለ ገንዘብ ባለ ትምክህት ተገዥዎች አይደለንም! "አሸንፈናቸዋል!" ምክንያቱም በሥጋ ምኞት ፈንታ በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለምንኖር: በዓይን አምሮት ፈንተ በእምነት ስለምንመላለስ እና በገንዘብ በመመከት ፈንታ በእግዚአብሔር ብቻ ስለምንመካ ነዉ። ለዚህ ነዉ ከዓለም እና በዓለም ካለው በላይ የሆንነው! 👉በእግዚአብሔር ፈቃድ ከኖራችሁ: በእምነት ከተመላለሳችሁ እና የምትመኩት በእግዚአብሔር ብቻ ከሆነ: ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ከላይ ሆናችሁ ወደታች ማየት ትጀምራላችሁ!! #𝚟𝚒𝚌𝚝𝚘𝚛#𝚛𝚎𝚟𝚎𝚕𝑎𝚝𝚒𝚘𝚗𝚜! 👇👇👇👇ተቀላቀሉን 👇👇👇👇 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

No longer Slave! I am no longer slave to fear! I am no longer slave to sin! Hallelujah! 👇👇👇👇👇 join 👇👇👇👇 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

የኔ አዋጅ! My Confession 👉በዳግም ልደት ከእግዚአብሔር ተወልጃለሁ! የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ: ከኃጢአት፤ ከዓለም፤ ከሰይጣን እና ከመናፍስቱ በላይ ነኝ! በፍጹም ለሞት ተገዥ አይደለሁም! የክርስቶስ ፍቅር ውጪና ውስጤን ተቆጣጥሮታል! በቀጣይነት በመንፈስ ቅዱስ እየተመራሁ: እና የጽድቅን ፍሬ እያፈራው ቅጽበታዊውን የቤተክርስቲያን ንጥቀት በመጠባበቅ: በዚህ ዓለም ላይ በገዥነት እኖራለሁ! በፀጋው ሃይል ፍጹም ተደርጌ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ነኝ! በንጹ ሕሊና በፊቱም ለመቆም ድፍረት አለኝ! ምክንያቱም አድስ ፍጥረት ነኝ! የድሮ ሚባል ታሪክ የለኝም! በእኔ ሽንፈት፣ ትንሽነት፣ ኃጢአት፣ በሽታ፣ ድህነት፣ ሞት እና የትኛውም ከሰይጣን የሆነ ነገር የለም! የእግዚአብሔር ሕይወት ተስፋ የማደርገው ብቻ ሳይሆን አሁን የምለማመደው ነዉ! በእያንዳንዱ ቀን የዓለም ብርሃን የምድር ጨው ነኝ! በጣም አስፈላጊ ነኝ! በሄድኩበት ሁሉ የእግዚአብሔርን ፍጹም እውነት በመንፈስ ቅዱስ ሃይል በመስበክ እና በማስተማር ነፍሳትን ለክርስቶስ ማሸነፍ ትልቁ ፍላጎቴ እና የደስታዬም ምንጭ ነዉ። ይህንን በየቀኑ አደርጋለሁ! ለዚህ ተልኬአለሁና! ሃሌሉያያ😆😆😆😆!!!!!! ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን! ይህንን አዋጅ ድምጻችሁን አሰምታችሁ አውጁ! እኔ ሁልጊዜ የማውጀው አዋጅ ነዉ። በመጨረሻም የ 5 ደቂቃ ልሳን ቀጥሉበት😁! እና በመንፈስ ንደዱ! 👉ለምትወዱት ሰው ሁሉ#ሼር በማድረግ ለእግዚአብሔር እውነት አንቁት/አንቋት! ፀጋ ይብዛላችሁ! 👇👇👇👇ተቀላቀሉን👇👇👇👇 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

እዩልኝ_By_Kalkidan_Tilahun_Lilyየዮሐንስ_ራእይ_1:12_16128k.mp38.02 MB

TheDeepThingsOfGod - آمار و تحلیل کانال تلگرام @thedeepthingsofgod