Skylink Technologies
رفتن به کانال در Telegram
For Simple and Modern life ለቀላልና ዘመናዊ ህይወት Contact us - 📞0974967171 || 0936177777 📍Bole, Tropical Mall 2nd floor, 217 📍Bole Shop, Garad Mall 1st Floor , B43 🌐 www.skylinkict.com
نمایش بیشتر1 425
مشترکین
-124 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-1230 روز
آرشیو پست ها
1 425
የምርኩዝ 31 የመግቢያ ትኬት ከ ሚንበር ሱፐር አፕ በነጻ ይሸለሙ!
📆 እለተ እሁድ ነሐሴ 10/2018 ⏰ ከማለዳው 02፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 07፡30 ሰዓት ድረስ 📍በተንጣለለው በአዲሱ #አራዳ_ፓርክ
ቲኬቶቹን በዳሽን ባንክ ሱፐርአፕ አልያም በሚንበር ሱፐርአፕ በ690 ብር ብቻ ያገኙታል!
Download the app from Skylink telegram channel the link is pinned
#ምርኩዝ 🇪🇹 #MERKUZ
1 425
Download the Minber super app
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.minbertv.minber
1 425
🎫 ዕለታዊ ጥያቄዎችን ይመልሱ ፡ የምርኩዝ መግቢያ ትኬት ይሸለሙ! 🏆
በሚንበር ሱፐር አፕ ዕለታዊ ጥያቄዎችን በመመለስ የምርኩዝ መግቢያ ትኬቶችን ይሸለሙ!
🌴 ምርኩዝ 34
8️⃣ የከውኑ ሞገስ 8
💭 ህልም 🏃♂️ትጋት 🎯ስኬት
ምርኩዝ!!
Powered by @skylinktechnologies
#ምርኩዝ
1 425
ከዩቲዩብ ገቢ ለማግኘት የሚጠየቀው መስፈርት በሁለት እጥፍ አደገ
ዩቲዩብ አዲስ ይዘት የሚፈጥሩ አካላት ከማስታወቂያ እና ከዩቲዩብ ፕሪሚየም ገቢ ማግኘት የሚጀምሩበትን የዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም መስፈርት በሁለት እጥፍ ማሳደጉን አስታወቀ።
እ.ኤ.አ Feb 1, 2027 ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው በዚህ አዲስ መመሪያ መሠረት፣ አዳዲስ ፈጣሪዎች በዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም ተቀብለው ገቢ ማግኘት ለመጀመር ፦
⚫ በመደበኛ/ ረጃጅም ቪዲዮዎች ላለፉት 12 ወራት 8,000 የታዩ ሰዓታት /Watch Hours/ ማሟላት አለባቸው። ይህም ቀደም ሲል ከነበረው 4,000 ሰዓታት በሁለት እጥፍ ያደገ ነው።
⚫ በአጭር ቪዲዮዎች /Shorts / በኩል ማመልከት የሚፈልጉ ደግሞ ባለፉት 90 ቀናት ውስጥ 20 ሚሊየን የታዩ ዕይታዎች ማሳካት ይኖርባቸዋል። ይህም ከዚህ ቀደም ከነበረው 10 ሚሊየን እይታ በሁለት እጥፍ ጨምሯል።
⚫ የ1,000 ተከታዮች መስፈርት አልተለወጠም።
ይህ ለውጥ ከፈረንጆች 2018 ወዲህ በዩቲዩብ የገቢ አስተዳደር ደንብ ላይ የተደረገ ትልቁ ማሻሻያ ነው ተብሏል።
በተጨማሪም ቀደም ሲል በፕሮግራሙ ውስጥ ያሉ የአጭር ይዘት ፈጣሪዎች የገቢ ክፍያቸውን ለማስቀጠል በየ90 ቀናት ውስጥ 10 ሚሊየን እይታዎችን ጠብቀው መቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል።
Source : Tech Crunch
@tikvahethmagazine
1 425
💭 የህልም፣ 🏃♂️የትጋትና 🎯ስኬትን ትስስር እያጎላ 3️⃣4️⃣ኛ መድረኩ ላይ በደረሰው ምርኩዛችን፤ የነቢያቱን ሁሉ አውራና የከውኑን ሞገስ በተለየ ድምቀትና ዝግጅት ለመከወን ቀጠሮ ይዘናልና፤ እርስዎም ከወዲሁ ቀጠሮዎን ከኛ ጋር ያድርጉ፡፡
📌 ያስታውሱ!
📆 እለተ እሁድ ነሐሴ 10/2018 ⏰ ከማለዳው 02፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 07፡30 ሰዓት ድረስ 📍በተንጣለለው በአዲሱ #አራዳ_ፓርክ በብዙ 🧡 ፍቅር እና አክብሮት አንድ ላይ እናሳልፋለን!! 🥰
🎫 የመግቢያ ዋጋ
🏦 በልዩ ቅናሽ በስልክዎ ላይ 📱 የሚንበር ሱፐር አፕን አውርደው በ5️⃣9️⃣0️⃣ ብር ብቻ #እስከ_ነሐሴ_3 መግዛት ይችላሉ።
🌴 ምርኩዝ 34
8️⃣ የከውኑ ሞገስ 8
✍️ በሱናዎ ላይ ...
💭 ህልም 🏃♂️ትጋት 🎯ስኬት
🌄 ምርኩዝ!!
1 425
🎯 የድርጅትዎን አሰራር በአንድ ዘመናዊ ERP System ያቀላጥፉ!
የድርጅትዎ የፋይናንስ ቁጥጥር፣ የሰራተኞች መረጃ፣ የዕቃ ክምችት (Inventory) እና የደንበኞች ግንኙነት በተበታተነ አሰራር ምክንያት ያስቸግሮታል?
Skylink Technologies PLC ሁሉንም የቢዝነስዎን ክፍሎች በአንድ ቦታ አቀናጅቶ የሚቆጣጠር ዘመናዊ ERP System ይዞሎታል!
የስርዓቱ ዋና ዋና ጥቅሞች፦
🔹 የፋይናንስ አስተዳደር (Financial Management): የድርጅትዎን ወጪና ገቢ፣ የትርፍና ክሳራ ሪፖርቶችን በግልጽ ለመቆጣጠር
🔹 የሰው ሃይል አስተዳደር (HR & Employee Self-Service): የሰራተኞችን መረጃ፣ የደመወዝ ስሌት (Payroll) እና የመገኘት መዝገብ ለማስተዳደር
🔹 የዕቃ ክምችትና አቅርቦት (Inventory & Supply Chain): የምርትና ዕቃ ዝውውርን ያለ ስህተት ለመከታተል
🔹 የፕሮጀክትና የሰራተኞች መርሃግብር: የስራ ሂደቶችን በጥራት እና በጊዜ ለመጨረስ
🔹 የደንበኞች ግንኙነት (CRM & Sales): የሽያጭ መጠንን ለመጨመር እና ከደንበኞች ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር
ስራዎን ያዘምኑ፣ ጊዜና ወጪዎን ይቆጥቡ!
👉 ለነፃ ዲሞ (Free Demo) እና ለበለጠ መረጃ አሁኑኑ ያናግሩን፦
📞 ስልክ፦ +251 974 967 171 / +251 936 177 777
🌐 ድህረ ገጽ፦
📲 ቴሌግራም / ሶሻል ሚዲያ፦ @Skylinktechnologies
Skylink Technologies PLC – For a simple and modern life!!
#ERP #SkylinkTechnologies #DigitalTransformation #BusinessSoftware #EthiopiaTech #ICTSolutions #BusinessGrowth
1 425
እጃችን ላይ ያለው ኢንተርኔት ውቅያኖስ አቋርጦ ስለሚመጣባቸው ገመዶች ምን ያህል ታውቃላችሁ?
በአለማቀፍ ደረጃ ከሚንቀሳቀሱ የኢንተርኔት መረጃዎች ውስጥ 99% የሚጠጋው የሚጓዘው በውቅያኖስ ውስጥ በተዘረጉ የfiber optic ገመዶች አማካኝነት ነው።
በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በ1988 እ.አ.አ ለመጀመሪያ ጊዜ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የተዘረጋው የፋይበር ኦፕቲክ ገመድ TAT-8 (Trans-Atlantic Telephone 8) ከተዘረጋ ከ38 ዓመታት በኋላ ከባህር ውስጥ ወጥቷል። ይህ ገመድ ከ2002 ጀምሮ ለሩብ ክፍለ ዘመን ያህል (ለ25 ዓመታት) ስራ በማቆም በአትላንቲክ ውቅያኖስ ግርጌ ተቀምጦ ነበር።
ይህ ገመድ ዩናይትድ ስቴትስን ከአውሮፓ የተለያዩ ሀገሮች ጋር digitally ያገናፕ ሲሆን አለምን ከተለመደው የመዳብ ኢንተርኔት ወደ ፋይበር connection እንድትቀየር የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ለመሆኑ የFiber optic ገመዶች እንዴት ይሰራሉ? ይህን የTAT-8 ገመድስ ከባህር ማውጣት ለምን አስፈለገ?
እስቲ በዝርዝር እንየው።
በአሁኑ ጊዜ በመላው ዓለም ከ500 በላይ የሚሆኑ እንደዚህ ያሉ ገመዶች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። እነዚህ ገመዶች ተቀጣጥለው ቢዘረጉ ከ1.6 ሚሊዮን ኪሎሜትር በላይ የሚረዝሙ ሲሆን ምድርን ደጋግመው የመዞር አቅም አላቸው።
እያንዳንዱ ገመድ የውሃ ማጠጫ ቱቦ የሚያክል ስፋት ያለው ሲሆን በውስጡ ግን ከሰው ፀጉር የሚያንሱ Glass fiber ገመዶችን ፍዟል። በእነዚህ ቀጫጭን ገመዶች ውስጥ መረጃዎችን የያዙ የብርሃን ጨረሮች ያልፋሉ። እያንዳንዱ ገመድ በሰከንድ በመቶዎች የሚቆጠሩ Terabits መረጃዎችን ማንቀሳቀስ ይችላል።
እነዚህን ገመዶች በባህር ወለል ውስጥ ማስቀመጥ እጅግ ረጅም እና አድካሚ ሂደት ነው። በቅድምያ መሐንዲሶች ገመዱን ከመዘርጋታቸው በፊት በውቅያኖስ ውስጥ ያሉ እንቅፋቶችን በማስወገድ የሚያልፍበትን መንገድ design ያደርጋሉ። ይህ ሂደት ብቻውን አንድ ወር ገደማ ሊወስድ ይችላል። አስተካክለው ከጨረሱ በኋላ ገመዱን ከግዙፍ መርከቦች ውስጥ በመሳብ ወደ ባህሩ ይለቁታል።
በመጨረሻም ገመዱ የሌላኛውን አህጉር ጠረፍ ሲደርስ ከዋናው Data center ጋር ያገናኙታል።
እነዚህ ገመዶች ብዙ ነገሮችን መቋቋም ቢችሉም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለጸው በዓመት ከ150 እስከ 200 የሚደርሱ ገመዶች ጉዳት ይደርስባቸዋል። አብዛኞቹ አካባቢዎች አንድ ገመድ ቢበላሽ ተክቶ የሚሠራ ሌላ ተጨማሪ የመጠባበቂያ ገመድ ቢኖርም አንዳንድ ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች አንድ ገመድ ብቻ ስለሚይዙ ይህ ገመድ ከተበላሸ ለሳምንታት ሙሉ የኢንተርኔት አገልግሎት ሊቋረጥ ይችላል። እ.ኤ.አ. በ2022 በደቡብ ፓሲፊክ የምትገኘው የቶንጋ ደሴት የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ አጋጥሞ ከሌላው ዓለም ጋር የሚያገናኛት ብቸኛ ገመድ በመጉዳቱ ለአንድ ወር ያህል የኢንተርኔት እና የስልክ ግንኙነት አጥታ ነበር።
ምንም እንኳን እንደዚህ ያሉ መቆራረጦች በተፈጥሮ አደጋዎች ሊከሰቱ ቢችሉም ወደ 80 በመቶ የሚጠጋው ግን በሰው ልጅ እንቅስቃሴ ማለትም በመርከብ መልሕቆች ወይም በዓሣ ማጥመጃ መረቦች ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ሆን ተብሎ የሚፈጸሙ የአሸባሪዎች ጥቃት ችግሩን አሳሳቢ አድርገውታል።
በሌላ በኩል ገመዶች በዕድሜ ብዛት አገልግሎት ሊያቆሙ ይችላሉ። እያንዳንዱ ገመድ በአማካይ የ25 ዓመታት የዕድሜ ዘመን አለው።
ቀደም ሲል እንደገለፅኩት ምንም እንኳን TAT-8 በዚህ ዓመት ከባህር ውስጥ ቢወጣም ከ2002 ጀምሮ ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ ነበር። በወቅቱ ብልሽት አጋጥሞት የነበረ ሲሆን እሱን ለመጠገን የሚጠይቀው ወጪ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ሳይጠገን ቀርቷል። ስለዚህ ለሩብ ክፍለ ዘመን ያህል ያለምንም አግልግሎት በአትላንቲክ ውቅያኖስ ግርጌ ሳይጠቅም ተቀምጧል። አሁን ግን ለአዳዲስ ገመዶች ቦታውን ክፍት ማድረግና በውስጡ ያለውን ውድ የመዳብ ማዕድን መልሶ ማግኘት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በመጨረሻም ሊወጣ ችሏል።
©bighabesha
#technews #skylink #techinfo

OpenAI "Codex Micro" የተሰኘ የ AI ኪቦርድ ይፋ አደረገ
ኦፕንኤአይ ከዎርክ ላውደር (Work Louder) ጋር በመተባበር የኮዴክስ (Codex) AI ኤጀንቶችን ለማስተዳደር የሚረዳ $230 ዋጋ ያለው አነስተኛ የኪቦርድ መቆጣጠሪያ (Keypad) አስተዋውቋል። መሣሪያው የኤጀንቶቹን የሥራ ሂደት በተለያዩ ቀለማት (ለምሳሌ ሰማያዊ ለስራ ላይ፣ አረንጓዴ ለተጠናቀቀ ተግባር) የሚያሳይ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች በአንድ ጊዜ በርካታ የ AI ኤጀንቶችን በንክኪ በቀላሉ እንዲቆጣጠሩ ያግዛል።
1 425
+5
At Skylink, we understand that uninterrupted connectivity is the backbone of modern business efficiency.
We provide robust Enterprise Network Solutions, high-speed WLAN, and dedicated ICT Support to ensure your team is always synchronized, secure, and focused solely on achieving your business goals.
Choose reliable connection; choose Skylink
1 425
ቻይና የመጀመሪያውን የፋርማሲስት ሮቦት ይፋ አደረገች
በቤጂንግ ስራ የጀመረው ይህ ሮቦት፤ መድኃኒቶችን ከመደርደሪያ በመውሰድ፣ የታዘዙ ትዕዛዞችን በማሸግ እና በቀን እስከ 370 የሚደርሱ ትዕዛዞችን በ99.9% ጥራት ያከናውናል።
1 425
በወረቀት ደረሰኞች መታገል እና በእጅ ሪፖርት ማዘጋጀት አበቃለት! 👋
ንግድዎን ወደ ዘመናዊ ዲጂታል ሥርዓት የሚቀይር፣ ደረሰኝ፣ ሽያጭ፣ ግዥ እና አካውንቲንግን በአንድ ቦታ የሚያስተዳድሩበት መፍትሔ ስካይሊንክ ይዞላቹ መጥቷል።
ምን ያገኛሉ?
📄 የደረሰኝ ዲጂታላይዜሽን (Receipt Digitization): ሰነዶችዎን በቀላሉ ዲጂታል ያድርጉ።
📊 የሽያጭ፣ ግዥና አካውንቲንግ አስተዳደር: የንግድዎን እንቅስቃሴ በቅርብ ይከታተሉ።
📑 የታክስ ሪፖርቶች በጥቂት ጠቅታዎች: ወርሃዊ የ-VAT፣ Withholding Tax፣ TOT እና ዓመታዊ የትርፍ ግብር (Profit Tax) ሪፖርቶች።
💼 የደመወዝ (Payroll) አስተዳደር እና ፋይናንስ ሪፖርቶች።
አሁኑኑ ያናግሩን!
ሰነዶችን ያደራጁ፣ ሪፖርቶችን በፍጥነት ያዘጋጁ፣ የታክስ ግዴታዎችን በመተማመን ያሟሉ።
ለኢትዮጵያ ንግዶች የተሰራ ዘመናዊ የአካውንቲንግና የታክስ አስተዳደር ሶፍትዌር!
1 425
አዲሱ #ChatGPT 5.6 ሞዴል ታግዷል!
የላቁ የAi ሞዴሎች ለምን ይታገዳሉ...!?
.
.
.
የላቁ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎች መንግስታት እና የደህንነት ተቋማትን የሚያስጨንቁበት እና እንቅልፍ የሚነሱበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። በዚህ ምክንያት የተለያዩ ህጎችን ከማውጣት ጀምሮ በሞዴሎች ጥብቅ እገዳዎችንም እየጣሉ ይገኛሉ። የበርካታ መንግስታት እና የደህንነት ተቋማትን የእገዳ ከተጣለባቸው መካከል የClaudeው Fable 5 የተሰኘ ሞዴል ተጠቃሽ ነው። ይፋ በተደረገ ማግስት ነበር መጠነ ሰፊ እገዳ የተጣለበት። ከትናንት በስቲያ ይፋ የተደረገው ሦስት ሞዴሎች ያሉት ChatGPT 5.6 (ChatGPT 5.5 update/ዝመና) ደግሞ የአሜሪካ መንግስት በየትኛውም አገር ለህዝብ አገልግሎት እንዳይውል እገዳ ጥሎበታል። ይህ ሞዴል ከClaude Fable 5 ሞዴል በእጅጉ የላቀ እንደሆነ ተነግሮለታል።
ይህ እገዳ በAi ሞዴሎች ልህቀት ምክንያት በመንግስታት እና በደህንነት ተቋማት እንዲሁም በመላው የዓለም ህዝብ ላይ ሁለት አሳሳቢሽ ተግዳሮቶች መጋረጣቸው ተከትሎ የመጣ ነው::
🔺 እነዚህም:-
1. የሳይበር ደህንነት ስጋት
አንድ የAI ሞዴል በዚህ ዘርፍ "ከፍተኛ አቅም አለው" ሲባል ፋይዳው የኮምፒውተር ሲስተሞችን መጠበቅ ብሎም የላቁ ተግባራትን ማከናወን ብቻ አይደለም። የመጥለፍ (Hacking) እና የማጥቃት ብቃቱ የላቀ ነው ማለትም ነው። የAi ሞዴሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኮድ መስመሮችን በአንድ ጊዜ በማንበብ የሰው ልጅ ባለሙያ በቀላሉ ሊያገኛቸው የማይችላቸውን የደህንነት ክፍተቶች (Zero-day vulnerabilities) በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ ማግኘት ይችላል።
የተገኙትን ክፍተቶች ተጠቅሞ የኮምፒውተር ሲስተሞችን ወይም የአንድ ሀገር ወሳኝ መሠረተ ልማቶች (እንደ መብራት፣ ውሃ፣ ባንክ፣ ወታደራዊ . . .) ሊያሰናክሉ የሚችሉ የቫይረስ ኮዶችን በራሱ መጻፍ መቻሉም አደጋውን ግልጽ እና ተጨባጭ ያደርገዋል።
በልብ ወለዱ ዓለም በስፋት እንደሚታወቁት "ሶል አልትራ" የመሰሳሰሉ ኤጀንቶች የሰው ልጅ ትዕዛዝ ሳይጠብቁ ራሳቸው አቅደው፣ መርምረውና የሳይበር ጥቃት ሰንዝረው የተፈለገው ሲስተም የመቆጣጠር አቅማቸው የላቀ ነው። የሳይበር ጥቃቶችን በከፍተኛ ፍጥነት ማካሄድ ይችላል ማለት ነው።
2. የባዮ-ምርምር ስጋት
ይበልጥ ዓለምን እያስጨነቀ ያለው ይህ ስጋት ነው። ምክንያቱም ከሳይንሳዊ ምርምር አልፎ ወደ ባዮሎጂካል መርዞች እና ተላላፊ በሽታዎች (Bioweapons) የሚያመራ አደገኛ አቅም አለው።
ሞዴሉ በጂኖሚክስ እና ባዮሎጂ ላይ ባለው ከፍተኛ እውቀት ነባር የቫይረስ እና የባክቴሪያ መዋቅሮችን ይበልጥ ተላላፊ፣ ለክትባት የማይበገሩ ወይም ገዳይ አድርጎ የማሻሻያ መንገዶችን የመስራት አቅም አለው።
በተመሳሳይም አንድ ክፉ አላማ ያለው አካል/ሰው የሳይንስ እውቀቱ ሳይኖረው፣ አደገኛ የሆኑ ባዮሎጂካል ቁሶችን በምስጢር እንዴት ማዘጋጀት እና ማደባለቅ እንደሚቻል ደረጃ በደረጃ የሚያሰለጥኑ መመሪያዎችን ማዘጋጀት መቻላቸው ለእገዳ አጋልጧቸዋል።
በአጠቃላይ እነዚህና መሰል ሞዴሎች ክፉዎች እጅ ላይ ከወደቁ መላውን ዓለም ለአደጋ የሚያጋልጥ የሳይበር ደህንነት አደጋ፣ የጦር መሳሪያ ወይም ተላላፊ በሽታ መስሪያ እንዳይውሉ ማገድ እንደመፍትሄ ተወስዷል። እነዚህ ሞዴሎች ህዝብ አገልግሎት እንዳይሰጡ የሚታግዱ ከሆነ መጀመሪያውኑ ከፍተኛ በጀት አውጥቶ መስራቱ ለምን አስፈለገ?" የሚለው ጥያቄ ተደጋግሞ እየተነሳ ነው።
@skylinktechnologies
#technews #techsolution #ai #chatgpt