cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

ማኅቶት ማለት መብራት ነው ቶኔቶር ደግሞ የኢትዮጵያ የጥንት ስሟነው እናም ማኅቶተ ቶኔቶር ማለት የኢትዮጵያ መብራት ማለት ነው መብራቷ ደግሞ መካከሏን ገነት ዳሯን እሳት እያለች የምትጠብቃት የምትጸልይላት እምነቷ ቅድስት ተዋህዶ ጥንት የሌላት ጥንታዊት ዘመን የሌላት ዘመናዊት ናት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምሮ ነው አስተያየት ካለዎት @mahtotetonetor2 @mahtotetonetor1

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 184
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-57 روز
+1630 روز
توزیع زمان ارسال

در حال بارگیری داده...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تجزیه و تحلیل انتشار
پست هابازدید ها
به اشتراک گذاشته شده
ديناميک بازديد ها
01
በዓመት ሁለት ጊዜያት ከሚካሔዱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት አንዱ የግንቦት 2016 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ነው፡፡ ይህ ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ርእሰ መንበርነት ረቡዕ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከጧቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
6811Loading...
02
Media files
8790Loading...
03
Media files
1 1780Loading...
04
ምኞቴ ነበር ዛሬ አንድ ነገር ፈጽሞ አሰብኩት በትላልቅ ከተማ ያሉ ሁሉም አጥቢያ ቤተክርስቲያን ሁለት ሁለት ባስ ቢገዙ መግዛት ለማይችሉ ጠቅላይ ቤተክህነት እገዛ ቢያደርግ ከዚያ ቅዳሜ እሁድ እና በእረፍት ቀናት ማታና ጠዋት ከ11:30 ጀምረው የሁሉም ኦርቶዶክሳውያንን  ልጆች ባሶቹ ከየሰፈራቸው እያነሱ ወደ ቤተክርስቲያን ቢወስዱ ሁሉም የሐዲስ ኪዳን መምህራን በየአጥቢያ ቤተክርስቲያን ቢበተኑና መጽሐፍ ቅዱስን በቅደም ተከተል ቢያስተምሩ ከተማሩ በኋላ ያመጧቸው ባሶች ወደ ቤታቸው ቢመልሱ  ። ዲ/ን ኤርምያስ @mahtotetonetor2
1 8489Loading...
05
በራሺያ የሥነ መለኮት ትምህርት ለመማር በሄደ ጊዜ .. በቀይ ምልክት ያደረኩበት የበኲረ መዘምራን ኪነ ጥበብ (የኪነ )ነው በዕውቀት ሙሉ የሆነ ዘማሪ ብቻ ሳይሆን የድጓ፣ የቅኔ፣ የዜማ መምህርም ነው ። እንደው ዘማሪ ብቻ አይደለም ኪነ ራሱን ዝቅ አድርጎ ምንም እንደማያውቅ በትህትና ከታናናሾቹ ጋር ስለ ተቀመጠ ፥ ዘማሪ ብቻ የሚመስለው ሰው አለ ! የውጭ ቋንቋን ጨምሮ የሚያውቅ ብቁ ሰው ነው። ይህን ግን ማሳወቅም መናገርም አይፈልግም። ራሱን ሰውሮ የሚኖር የትህትና አባት ነው ጳጳስ አይደለም ፥ ሊቀ ጳጳስ መሆን የሚችል ሙሉ ሰው ነው ። አይ ኪነ ከአንተ ምን ይማሩ ይሆን የዘመኖቹ አገልጋዮች ! እኛስ ልጆችህ..? እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን 🙏🙏❤ ምንጭ :- ቅድስት ጋረደው @mahtotetonetor2
1 5500Loading...
06
+ የሚሮጥ ዲያቆን + የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ነው:: አቧራማውን የጋዛ ምድረ በዳ በፈጣን ሩጫ እያቦነነ የሚከንፍ አንድ ወጣት ታየ:: ሩጫው የነፍስ አድን ሠራተኞች ዓይነት ፍጥነት ያለው ነበረ:: አንዲትን ነፍስ ሳታመልጠው ለማትረፍ እየከነፈ ነው:: የሚሮጠው ደግሞ በፍጥነት በሚጋልቡ ፈረሶች የሚጎተት የቤተ መንግሥት ሠረገላ ላይ ነው:: በሰው አቅም ፈረስ ላይ ሮጦ መድረስ ባይቻልም ይህ ወጣት ግን ፈረሶቹ የሚያስነሡትን የጋዛን አቧራ በአፉ እየቃመ በአፍንጫው እየታጠነ እንደምንም ደረሰ:: በሠረገላው ውስጥ አንድ ጸጉረ ልውጥ የሩቅ ሀገር ሰው ተቀምጦ በእርጋታ መጽሐፍ እያነበበ ነው:: እግሩን እንደ ክንፍ ያቀለለው ሯጩ ዲያቆን ፊልጶስ ይባል ነበር:: በዚያ ምድረ በዳ ብቻውን ሲሮጥ የሚያጨበጭብለት ሰው የሚሸልመው ደጋፊ አልነበረም:: እንዲያውም ልብ የሚሰብ ኀዘን ላይ ነበረ:: እስጢፋኖስ የሚባል አብሮት ዲቁና የተሾመ የቅርብ ጓደኛውን በድንጋይ ወግረው በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉበት ገና አርባ ቀን አልሆነም:: "ቤተክርስቲያን ስደት ላይ ሆና ምን ስብከት ያስፈልጋል?" በሚል ቀቢጸ ተስፋ እጁን አጥፎ ያልተቀመጠው ፊልጶስ ግን የወንድሜን ኀዘን ልወጣ ሳይል የምሥራች ለማብሠር በበረሃ ሮጠ:: ቀርቦ ያናገረው ጃንደረባ ደግሞ "የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻለኛል?" የሚል ኦሪትን ይዞ ትርጓሜ ፍለጋ የሚቃትት ፣ ጥላው ይዞ አካሉን ፍለጋ የሚጨነቅ ትምህርት የተጠማ ኢትዮጵያዊ ነበረ:: ስለዚህ ይህ ዲያቆን መዳን የምትሻውን የጃንደረባውን ነፍስ በመዳን እውቀት አረስርሶ አሁኑኑ ካልተጠመቅሁ አሰኛት:: ብቻውን የሮጠውና አንድ ሰው ያስተማረው ዲያቆን ፊልጶስ ሮጦ ያዳነው አንድ ሰውን ብቻ አልነበረም:: በአፍሪቃ ቀንድ ለምትገኘው ሀገር ኢትዮጵያና ሕዝቦችዋ የመዳን ቀንድ የሆነ ክርስቶስን አሳያቸው:: አንድ ኢትዮጵያዊ አጥምዶ በእርሱ ብዙዎችን ከማጥመድ በላይ ምን ሙያ አለ? ጴጥሮስን በጀልባው ላይ ከዓሣ አጥማጅነት ወደ ሰው አጥማጅነት የቀየረ አምላክ ገንዘብ ያዡን ባኮስ ነፍሳት ያዥ አድርጎ ሸኘው:: "የህንደኬ ሹም ባኮስ ሆይ ከአሁን ወዲህ በህንደኬ ገንዘብ ላይ ብቻ አትሠለጥንም ፤ የእግዚአብሔር ገንዘቦች የነፍሳት ግምጃ ቤት ላይ የሠለጠንህ የመንግሥተ ሰማያት በጅሮንድ አደርግሃለሁ" ብሎ ሾመው:: ይህ ከሆነ ሁለት ሺህ ዓመት አለፈ:: የጃንደረባው የልጅ ልጅ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከሠረገላ አልፎ በፍጥነት በሚሔድ ብዙ ዓይነት መጓጓዣ ሊሳፈር ተሰለፈ:: ትዕግሥት አጥቶ በገንዘብ ላይ ከመሠልጠን ይልቅ ገንዘብ ሠልጥኖበት በፍጥነት ከነፈ:: አንዱ ፊልጶስ ብቻ ሮጦ የማይደርስበት እልፍ ሕዝብ ዛሬ ሠረገላውን አጨናንቆታል:: እንደ ጃንደረባው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሳይሆን ስልኩ ላይ ያቀረቀረ ፣ ስለ ትንቢት ትርጉም ሳይሆን ስለ ኑሮ ብልሃት የተመራመረ ትውልድ ተነሥቶአል:: የኢሳይያስ ትንቢት ስለማን ቢነግር የማይገደው የሕይወት ውጣ ውረድ ፍቺ የሚሻ ትንቢት የሆነበት ፣ በመንፈስ ጭንቀት የታወከ ምስኪን ትውልድ ተነሥቶአል:: በእርግጥ ይህ ትውልድ ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት የሚመራው ሳይኖር እንዴት ይቻለዋል? ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ፊልጶስ ከወዴት ይምጣ? ኸረ የዲያቆን ያለህ? ነፍስ አድን ፊልጶሳዊ ዲያቆን ሆይ ከወዴት ነህ? ነፍሳትን ለማዳን የሚያሳድድ እንጂ የሥጋ ምኞቱን የሚያሳድድ ዴማሳዊ ዲያቆን አልጠፋም:: እንደ እስጢፋኖስ በድንጋይ የሚወገር ዲያቆን እንጂ ድንጋይ አንሥቶ የሚማታ ዲያቆን አልጠፋም:: ሰረገላ ላይ ሆነው ግራ የተጋቡ ባኮሶች ብዙ ናቸው የፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ችግራቸውን ፈትቶ ጥያቄያቸውን መልሶ የሚሰወር ከሠረገላ አልወርድም ብሎ የማያስቸግር ፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ከእናንተ ቀድመን በተሾምን ዲያቆናት አንገትዋን የደፋች ቤተ ክርስቲያን በእናንተ ቀና እንድትል እንመኛለን:: የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ምእመናን እሱን ፍለጋ የሚሮጡለት ዲያቆን ሳይሆን ነፍሳትን ፈልጎ የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ከመቅደሱ ጠፍቶ የሚፈለግ ሳይሆን ፈረስ የማያመልጠው ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ዲበ ሠረገላ ሰማይ @mahtotetonetor2
1 4712Loading...
07
Media files
1 5470Loading...
08
✝፭. እሱ ብዙ ተአምራትን እንዳደረገ እነሱንም ♥እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል♥ ብሏቸዋል፤ ዮሐ 14 ፡12፡፡ ከዚህ በኋላ የተረፈውን ምግብ እንደሰጣቸው ሁሉ ከ3 ዓመት ከ3 ወሩ የተረፈውን ትምህርት አስተማራቸው.... የነገርኳችሁ ሁሉ ቃሌ ይህ ነው ብሎ አእምሯቸውን እንደተዳመጠ ብራና ንጹሕና ቀለም ለመቀበል የተዘጋጀ አደረገላቸው፡፡ ...... ....ሐዋርያትም ማስተዋል ጀመሩ...!!! እንድናስተውል ይርዳን!!! አሜን! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው @mahtotetonetor2
1 5077Loading...
09
#ጌታችን_ከትንሣኤው_በኋላ_ለምን_በላ?(ሉቃ 24፡36-46) 1. ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ 2. ሥጋውንም ነፍሱንም ተዋሕዶ እንደተነሣ ለማጠየቅ 3. ቀጠሮ ስለነበረው ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ በኅብረት ሳሉ 3 ጊዜ እንደተገለጠላቸው የታወቀ ነው ፤ በኅብረታቸው ውስጥ የተገለጠው 3 ጊዜ ይሁን እንጂ በ40ው ቀናት ውስጥ ለእያንዳዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት ሆነውም ሳይገለጥላቸው የዋለበት ያደረበት ጊዜ እንደሌለ መተርጉማነ ሐዲስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ በተገለጠላቸው ጊዜም አስገራሚና አስደናቂ ያልተለመዱ ነገሮችን በማሳየት ነበር፡፡ በተዘጋ ደጅ መግባቱ አስደንግጧቸዋል፤ እሱ መሆኑን በአካለ ሥጋ እየተመለከቱ ቢሆንም ምናልባት ምትሐት ቢሆንስ? መንፈስ እሱን መስሎ አስመስሎ ተገልጦልን ቢሆንስ? የሚል ከባድ ጥያቄ በኅሊናቸው ይወጣ ይወርድ ነበር፡፡ ረስተዉት ነው እንጂ በባህር ላይ ሲራመድ አይተዉት ነበር፤ ባህሩን ሲገሥጸው ማዕበሉን ጸጥ ሲያደርገው ነፋሱን ሲያዘው ተመልክተው ነበር ዘንግተዉት እንጂ የአራት ቀን ሬሳ ሲቀሰቅስ የዕለት ሬሳ ከእንቅልፍ እንደማንቃት ሲያስነሣ በዓይናቸው አይተው ነበር ግን ሌሎችን ከሞት ያስነሣውን አምላክ የእሱን ከሞት መነሣት ለማመን ተቸገሩ! በዚህ ምክንያት "በምትሐትነት" ጠረጠሩት! ጌታም  በተዘጋው ደጅ ብቻ ሳይሆን በተዘጋው ልባቸውም ውስጥ ገብቶ ሀሳባቸውን እየመረመረው ነበርና  "ለምንት የዐርግ ኅሊና እኩይ ውስተ ልብክሙ፤ ክፉ ሀሳብ በልባችሁ ለምን ይመላለሳል?" እኔ ራሴ እንደሆንኩ እጆቼንና እግሮቼን እዩ ...መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ግን ዳስሳችሁ አረጋግጡ አላቸው፡፡ ይህንም ብሏቸው ግን አላመኑም ነበር ቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው "ወእንዘ ዓዲ ኢአምኑ እምድንጋፄ.." ከድንጋጤም ከደስታም የተነሣ ገና አለማመናቸውን ተመልክቶ ♥በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን?♥ በማለት ጠየቃቸው አነሱም የተጠበሰ ዓሣና የማር ወለላ ሰጡት፤ ተቀብሎም በፊታቸው በላ፡፡ ለልማዱ ጌታችን ሲመገብ 6ቱ ይቆማሉ ስድስቱ ይቀመጡ ነበር በዚህ ጊዜ ግን ሁሉም ቆመው ዓይን ዓይኑን እያዩት በፊታቸው በላ፡፡ በፊታቸው የበላበት ምክንያት፦ 1. ምትሐት እንዳልሆነ ለማረጋገጥ ፦ ✝ጌታችን ፍጹም ሰው መሆኑን ለማረጋገጥ ያከናወናቸው ብዙ ነገሮች አሉ ፤ መራብ መጠማት መብላት መጠጣት፤መተኛት መነሣት፤ ራሱን ከምእመናን ጋር መቁጠር፤ መፍራት መጸለይ ...ሁሉ ለአጽድቆተ ትስብእቱ (ሰው የመሆኑ ትክክለኛነት) ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ሐዋርያት ምትሐት እንዳልሆነ ያምኑ ዘንድ ቀድሞ ሲበላ እንዳዩት ሁሉ ዛሬም እያዩት በፊታቸው መመገቡ ምትሐት ላለመሆኑ ማረጋገጫ ነበር፡፡ 2. ሥጋውንና ነፍሱን ተዋሕዶት እንደተነሣ ለማጠየቅ፦ ✝ ብዙ መናፍቃን ከጥንት ጀምሮ ይሰናከሉ ከነበረበት ትልቅ ጉዳይ አንዱ የጌታችንን ትንሣኤያዊ ማንንነት የተመለከተ ነው ፤ መለኮቱና ሥጋው በመስቀል በሞት የተለያዩ የሚመስላቸው ፤ ያም ባይሆን ሥጋን በመቃብር ትቶት የተነሣ የሚመስላቸው ፤ ወይም በሌላ የተለየ አዲስ ሥጋ የተነሣ የመሰላቸው ብዙዎች አሉ፡፡ ጌታችን እዩት እጄን እዩት እግሬን እዩት ጎኔን ብሎ የቀኖትና የጦር ምልክቱን ያሳያቸው ያንኑ የተገረፈውን የተሰቀለውን ሥጋ ተዋሕዶት የማይፈርስ የማይበሰብስ አድርጎ እንዳስነሣው ለማጠየቅ ነው፤ ቶማስም በተወጋው ጎኑ ቀዳዳ እጁን እንዲያስገባ የፈቀደለት ከሌላ የክህደት ቀዳዳ ለመታደግ ነው ፡፡ መብላት መጠጣት የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ ምልክት ነው፤ ጌታም ይህንን ተዋሕዶ ለማረጋገጥ እንጂ ርቦት ወይም ከትንሣኤ ወዲያ መራብ መጠማት መብላትና መጠጣት ያለ ሆኖ አይደለም፡፡ The Orthodox Study Bible ላይ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ኅዳግ (Foot note) ላይ እናገኛለን " Christ eats not because He in His resurrected body needs food, but to prove to the disciples that He is truly risen in the flesh" ክርስቶስ የተመገበው በተነሣበት አካል ምግብ የሚያስፈልገው ሆኖ ሳይሆን በእውነት በሥጋ መነሣቱን ለደቀመዛሙርቱ ለማረጋገጥ ነው እንጂ" ይላል፡፡ ትርጓሜ ወንጌልም "ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ" ካለ በኋላ "ትንሣኤውን እንዲረዱ እንዲያምኑ" በፊታቸው በላ በማለት ግልጽ አድርጎታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም "አኮ ፈቂዶ ለመብልዕ አላ በልዐ ወሰትየ ከመ ይእመኑ ከመ ውእቱ ተንሥአ እምውታን፤ ምግብ የሚያስፈልገው ሆኖ እይደለም፤ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን ያምኑ ዘንድ በላ ጠጣ እንጂ" ብሏል፤ ሃይ.አበ 66፡8፡፡ 3. ቀጠሮ ስለነበራቸው፦ ዕለተ ሐሙስ ማታ ላይ "ኢይሰቲ እምዝንቱ አጺረ ፍሬ ወይን እስከ አመ እሰትዮ ምስሌክሙ ሐዲሰ በመንግሥተ አቡየ ዘበሰማያት፤ በአባቴ ሥልጣን ታድሼ እስከምነሣ ድረስ ከዚህ የወይን ጭማቂ አልጠጣም" ብሏቸው ነበር ፡፡ ይህ አነጋገር ብዙ ምሥጢራት ያሉት ቢሆንም በዋናነት የሚያመለክተው ግን ትንሣኤን ነው፦ "በአባቴ ሥልጣን.." የሚለው የማይራብ የማይጠማ የማይደክም አይሁድ ለመከራ የማይፈልጉት፤ ከእንግዲህ ወዲህ የመስቀል ሞት የሌለበት ሆኖ መነሣቱን የሚያመለክት ሲሆን የወይኑን ጭማቂ ጽዋ አለመጠጣቱ ግን እሱ የሚጠጣው የመስቀል ጽዋ ስለነበረው ነው ...ይኸውም ሊታወቅ "ይህቺ ጽዋ ከእኔ ትለፍ" እያለ መላልሶ ይጸልይ እንደ ነበር ተገልጧል፤ ያን ጽዋ እሱ ካልጠጣልን እኛ የወይኑን/የደሙን ጽዋ መጠጣት አንችልምና፡፡ ያንን ሁሉ አጠናቆ በሐዋርያት ፊት የማር ወለላ ቀረበለት እሱንም በፊታቸው በመብላትና በመጠጣት የዕለተ ሐሙሱን ንግግሩን አስታወሳቸው፡፡ ይህንንም ግእዝ በግእዝ ትርጓሜ ወንጌል "በበሊዖቱ አዖቀ ጽድቀ ትንሣኤሁ ወሰትዮቱኒ ያሌቡ እንበይነ ቃሉ ዘይቤ "ኢይሰቲ እምዝንቱ አጺረ ፍሬ ወይን"" በማለት ገልጦታል፡፡ ✝ማስታወሻ፦ የቀድሞው የፋሲካ በግ ሥጋው ተጠብሶ መራራ ቅጠል ይጨመርበት ነበር፤ አሁን ግን አዲሱ ፋሲካ ክርስቶስ ስለታረደ መራራ ቅጠል ሳይሆን እርሱ ባወቀ የማር ወለላ ቀረበለት! ✝ሌላው በጣም የምንገረምበት ጉዳይ ደግሞ "ወነሥአ ዘተርፈ ወወሀቦሙ፤ የተረፈውን አንሥቶ ሰጣቸው" የሚለው ነው፡፡ ☞ለምን ሁሉንም አልበላውም? ☞ለምን ቀምሶ አልተወውም? ☞ለምን አስተረፈ? ☞ካስተረፈስ ለምን የተረፈውን ለነሱ ሰጣቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች በመገረም መጠየቅ እንችላለን!!! የተጠበሰው ዓሣና የማር ወለላው፦ ➊የትንቢተ ነቢያት ምሳሌ ነው ➋የዘመን ምሳሌ ነው ➌የሥራ ምሳሌ ነው ➍የትምህርተ ወንጌል ምሳሌ ነው ➎የተአምራት ምሳሌ ነው ጌታ የበላውን በልቶ የተረፈውን ለሐዋርያት መስጠቱ፦ ✝፩. በእሱ የተፈጸመውንና ወደፊትም በእነርሱ የሚፈጸመውን ትንቢት ለትውልድ፡እንዲገልጡ የተረፈውን ሰጥቷቸዋል፡፡ ✝፪. ዘመነ ነቢያትንና የእርሱን ዘመን (33 ዓመት ከ 3 ወር) አሳልፎ የተረፈውን ዘመን ሰጥቷቸዋል (ዘመነ ሐዋርያት) ✝፫. እሱ ሠራዬ ኃጢአት ሊቀ ካህናት ከባቴ አበሳ እንደሆነው ሁሉ እነሱም እንዲያጠምቁ እንዲያቆርቡ እንዲያስሩ እንዲፈቱ ሥልጣነ ክህነትን ሰጥቷቸዋል ✝፬. እሱ 3 ዓመት ከ 3 ወር እንዳስተማረ እነሱንም "ሑሩ ወስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት" ብሏቸዋል
1 53011Loading...
10
"አትጨነቁ ያሳያችሁኝ ፍቅር ጥንካሬ ሰጥቶኛል ብሏል።" በኩረ መዘምራን ኪነጥበብ ቤተክርስቲያን ያሳደገቻቸው በዓለም ዘሪያ ያሉ ያልደወሉለት ፕሮፌሰሮች እና ዶክተሮች የሉም...የሆነው ሆኖ መቅረዝ ሆስፒታል በVIP አቀባበል ተቀብሎ በኩረ መዘምራን ሕክምናውን ጀጀምሯል። ቤተክርስትያን ያፈራቻቸው ዶክተሮች እና ነርሶች ተረባርበው... "የሚቻል ቢሆን ከእድሜአችንም እየቀነስን በጨመርንልህ" ብለው እንደ ህመምተኛ ሳይሆን እንደ ንጉስ ተቀብለው አስተናግደውታል። አሉ የተባሉ ስፔሻሊስቶች አይተውታል ክትትል እያደረጉለት ነው። መ/ር አብርሃም ኃይሉ (ዘጎርጎርዮስ) @mahtotetonetor2
1 6223Loading...
11
Media files
1 9470Loading...
12
ዘማሪ ኪነ ጥበብ ታሟል እግዚአብሔር ምሕረቱን እንዲሰጠው ጸልዩ
2 3775Loading...
13
"እንደ ሞተ ሰው ሁን" ❖ ከወንድሞች አንዱ ወደ አባ መቃርዬስ መጥቶ " አባክህ ለህይወቴ የሚሆን መመርያ ስጠኝ" አለው ፡፡ አባ መቃርዬስም ያንን ወንድም ወደ መቃብር ሂድና በሙታን ላይ ክፋ ነገር አድርግባቸው፡፡ ብሎ ላከው ሰውየውም በሙታኑ ላይ ድንጋይ በመወርወርና በመሳደብ የተላከውን ፈፅሞ መጣ ፡፡ " አባ መቃርዮስም ምን አሉህ ? ሲል ጠየቀው " ያም ወንድም "ምንም አላሉኝም " ብሎ መለሰ ፡፡ በነጋታውም ተመልሰህ ናና አመስግናቸው  አለው፡፡ በነጋታውም ያ ወንድም ወደ መቃብሩ ስፋራ ተጉዞ ሙታኑን " ሐዋርያ ፣ ቅዱሳን ፣ጻድቃን ፣ እያለ አመሠገናቸውና ተመለሰ ፡፡ መቃርዮስም  " ምን መለሱልህ አለው" ምንም አለ ፡፡" መቃርዮስም " ስትሰድባቸው ፣በድንጋይ ስትመታቸው ፣ ስታመሰግናቸውም ፣ ስታወድሳቸው ፣ ምንም አልመለሱልህም ፡፡ አንተም ለነፋስህ ድህነት ከፈለግክ  እንደ "ሞተ ሰው ሆነህ ኑር"  ፡፡ ሰዎች ክፋ ቢያደርጉብህም ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ አለው ፡፡፡ ወዳጄ ሆይ የታላቁን አባት ምክር ልብ አልክን ? የሚሰድብህንና ድንጋይ የሚወረውርብህን እንዴት ማለፋ እንዳለብህ ተማርክ ? የሚያመሰግኑህንና የሚያወድሱህን እንዴት መቀበል እንዳለብህ አስተዋልክ ? ☞ ቀልብህን የሚቀሙህን ብዙ ሰዳቢዎች አሉብህ ፡፡ የሚያስጎነብሱህ ብዙ ድንጋይ ወርዋርዎች አሉብህ ፡፡ ☞ አንዱ ድህነትህን እያነሳ ያሸማቅቅሀል ፤ሀብት የሌለህና ገንዘብ መቁጠር ያልቻልከው የማትረባ ስለሆንክ ብቻ እንሆነ በማሰብ ያሳንስሀል ☞ በምግባርህ የሞትህ እንደሆንክ እየጮኸ ይነግርሀል ☞ ሃይማኖትህና ኢትዮጲያዊነትህ ለድህነት አስተዋፅኦ እንዳደረገና ማንነትህ ራሱ የተዋረደ እንደሆነ በመንገር ተፈጥሮህን " ንቀህ "አርቴፋሻል እንድትሆን ኦርጅናልነትህን አርክሰህ ፌክ እንድትሆን ይሰብክሃል፡፡ ☞ በዘር ገመድ ተብትበው ከወንድምህ ጋር የሚያናቁሩህ ሃይማኖትህንና ሰብአዊነትህ  ሳይቀር በዘረኝነት ሰፌድ የሚያበጥሩ ድንጋይ ወርዋርዎችን እንዴት ይሆን ያለፋካቸው ፡፡ ☞ ጾምህን የሚያንቋሽሹ ፣ ሱባኤህን የሚረብሹ ፣ ጸበል መጠጣትህን ፤እምነት መቀባትህን የሚያንሻፋፉ ፤እግዚአብሔር በሞተ ነገር ላይ ታሪክ እንደሚሰራ ስትነግራቸው የሚስቁ ፤ በሰማይ ህይወት አለ ስትላቸው በሙት አምራቸው የሚሳለቁ ፤ይልቅ ዓለምህን ቅጭ ጊዜህን ተጠቀምበት  የሚሉ አለማውያንና ማንነትህን ለማርከስ ማንነታቸውን ለማንገስ የሚወረውሩት ጥቁር ድንጋይ አቁስሎህ ይሆን ???? ወዳጄ ሆይ ታላቁ አባት እንዲህ ይልሃል ለስጋውያን ለስሌታውያን እንደ ሞተ ሰው ሁን !!!! ☞ ደግሞስ ገና ልትሰራ የምትችለውን ገና በልዑልነትህ ንጉስ ብለውህ ገና በወጣትነትህ ጻዲቅ አድርገውህ ገና በተማሪነትህ ረብኒ ብለውህ ዳዴህን ሳትጨርስ የአትሌትነት ማዕረግን ሰጥተውህ በዲያብሎስ መዝሙር ከፋ ከፋ በጣሙን ከፋ ከፋ ሗላ ስትወድቅ አጥንትህ እንዳይተርፋ ሰቅለው በአፋጢምህ የሚደፋህን አድር ባዮችና ህሊና ቢሶች እንዴት አልፈሀቸው ይሆን ? ለእነርሱም ወሬ መንኩሰህ እንደ ሞተ ሰው ሆንክን ?? ☞☞  እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታድነው ትዳር አለህ ፡፡ ☞☞ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታድነው ህይወት አለህ ☞☞ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታጠነክረው ወዳጅነት አለህ ☞☞ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምትሰራው እልፋ ስራ አለህ ፡፡ ✞ ደግሜ ደግሜ እልሃለሁ የታላቁን አባት ቃል ተውሼ ለእነዚህ እንደሞተ ሰው ሁን!!!! ✍ እንደ ሞተ ሰው ሁን እንጂ ሙት ሁን አልተባልክም  ፤ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ በግብርህ ሕያው ሁን እንጂ ሙት አትሁን፡፡ @mahtotetonetor2
1 9278Loading...
14
"እኛን ኃጥኣንን ምትምረን ያን ጊዜ መኃሪ ትባላልህ!... ጻድቃንን ግን በስራቸው ትምራቸዋልህና፤"
1 5441Loading...
15
ነገሮች ወዴት እየሄዱ ነው?? ነገሮች በከፍተኛ ጡዘት ላይ ናቸው አቡነ አብርሃምን የማጥፋት ሴራው ፊት ለፊት ገሃድ ወጣ:: የፖሊስ የምርመራ ደብዳቤ ወጣባቸው::
1 8630Loading...
16
ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ተከታዮች ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። እንደሚታወቀው ግንቦት 21 የፃድቃኔዋ እመቤት ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው ሁሉንም ህዝበ ክርስትያን በጋራ ስለመጣብን መከራ እግዝአብሔርን በጋራ ሁነን እንለምነው ዘንድ በምላጃ ያልተለየችን የፃድቃኔዋ እመቤት ድንግ ማርያም ቤት ተጠርታችኋል ። ስለዚህም የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዝችኋል ። ጉዟችንም ማክሰኞ ግንቦት 20 አዳር ረቡዕ ግንቦት 21 ደርሶ መልስ ከእኛ ጋር ለመጓዝ ከፈለጋችሁ 0912494703 0902414679 መነሻችን :-ከአዲስ አበባ አዳር 800 ደርሶ መልስ 700 ደውለው ይመዝገቡ።
1 8251Loading...
17
ዮም ዕለተ ብዙኅ ትፍሥሕት እንዳሉ ባለቅኔው ዛሬ ልዩ ቀን ነው። የታላቁ ሊቅ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራና የክቡር ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በዓል ነው። እንኳን አደረሳችሁ።
1 6953Loading...
18
Media files
1 7700Loading...
19
የድጓው የአቋቋሙ የዝማሬው መምህር ሊቀ አእላፍ ልሳነወርቅ በሚያስተምሩበት በዚሁ በየካ ደብረሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን   በሊቃውንቱ  በደቀ መዛሙርቶቻቸው ታጅበው ሥርዓተ-ተክሊል ፈጽመዋል።እንኳን ለኢትዮጵያ ብርሃን ፣ ለቤተክርስትያን ምስጢር አስገኝ ፣ ለዓለም የዜማ ምንጭ ለቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል ለሆነበት ለዚች ዕለት እና ለዚህ ታላቅ ምሥጢር አበቃዎት መምህሬ እንኳን ደስ አልዎት የአብርሃም የሣራ ጋብቻ ይሁንላችሁ። ዲ/ን ኤርምያስ @mahtotetonetor2
2 0203Loading...
20

10Loading...
21
የድጓው የአቋቋሙ የዝማሬው መምህር ሊቀ አእላፍ ልሳነወርቅ በየካ ደብረሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በደቀመዛሙርቱ ተከበው በሊቃውንቱ ታጅበው ሥርዓተ-ተክሊል ፈጽመዋል። መምህሬ እንኳን ለዚህ ታላቅ ምሥጢር አበቃዎት ዲ/ን ኤርምያስ @mahtotetonetor2
500Loading...
22
ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰት (ለጾመ ፍልሰታ )ሱባኤ የሚሆን ፩) ጧፍ ፪) እጣን ፫) ዘቢብነ ፬) ሻማ ማገዝ ተምትችሉ ሁሉ ከእጓ ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ገዳም ጥሪ ቀርቦላችኋል።
1 7101Loading...
23
ቅዱስ ያሬድ ግንቦት ፲፩ ቀን ከቀደሙት ቅዱሳን እንደነ ሄኖክ እንደነ ኤልያስ፥ከኋለኞቹ ቅዱሳን እንደነ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ የተሰወረበት ዕለት ነው። በረከቱ ረድኤቱ ይደርብን፥በአማላጅነቱ አይለየን።
1 8576Loading...
24
☺️☺️☺️☺️ቅዱስ ያሬድ ይህ እሱን አይገልጽም
1 8193Loading...
25
መንዝ "ነዝኀ" ከሚል የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ነዛ ፣በተነ ፣ረጨ ፣ፈነጠቀ የሚል ትርጉም ይኖረዋል።በመሆኑም ይህ ስያሜ በዕለተ አርብ ስቀለተ ክርስቶስ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል የክርስቶስን ደም በብርሃን ፅዋ ቀድቶ ከረጨበት ጊዜ ጀምሮ የተሰጠ መሆኑን እንረዳለን።ለዛሬው ስለመንዝ ሰፊ ነገር ለማለት ሳይሆን በመንዝ ውስጥ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ንዝኀተ ደሙን ጨርሶ ቅዱሱን ፅዋ በቦታው ላይ ከመሰወሩ በፊት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስያሚያቸውን ይዘው ስለሚገኙ ቦታዎች ትንሽ ላደርሳችሁ ወደድኩ።በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙዎች አምልታችሁና አስፍታችሁ መፃፍና ማስረዳት እንደምትችሉ ባምንም እኔም ባለችኝ አቅም ስለ አራት ቦታዎች ስያሜ ይህችን ለመፃፍ ወደድኩ። በመንዝ እመጓ(እመእጓል)፣ እጓ ፣ እመ - ገነት የሚባሉ ቦታዎች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ቦታዎች የእመቤታችንን እና የልጇን ስደት መነሻ ተደርጎ የተሰጠ ስያሜ እንደሆነ ይነገራል ። በመሆኑም የእነዚህን ቦታዎች ትርጓሜ በሚመለከት በተወሰነ መልኩ ለማየት ያክል:- ፩)እመጓ ~ እመ እና እጓል ከሚሉ ሁለት የግዕዝ ቃላት ጥምረት የተገኘ ሲሆን እመ መለት እናት፣እጓል ማለት ደግሞ ልጅ ማለት ነው።በመሆኑም የሁለቱ ጥምረት እናትና ልጅ የሚል ትርጉም የሚሰጥ ሲሆን ለቦታው በተሰጠው ስያሜ መሰረት የእናትና የልጇ የጋራ መታወሻ መጠሪያ ቦታ መሆኑን እንረዳለን።በዚህ ቦታ ላይ የእናታችን የቅድስት ማርያም እና የደብረ ቆጵሮስ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን መገኘት በሚስጥራዊነቱ እንድንደነቅ ያደርገናል። ፪) እጓ ~ከእመጓ ዑራኤል ከገሊላ ተራራ ላይ ሆነው ፊትዎን ወደ ምስራቅ ሲያደርጉ በስተግራ በኩል ከተራራው ስር ከሚገኘው ወንዝ ባሻገር የሚገኝ ቦታ ሲሆን ይህም እጓ ተብሎ ይጠራል።እጓ ማለት እጓል ከሚል የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ልጅ ማለት ነው።በመሆኑም ለቦታው በተሰጠው ስያሜ መሰረት ደግሞ የልጇ የመድኃኔዓለም ሀገር እንደ ማለት ሲሆን ለዚህም የደብረ ምሕረት እጓ መድኃኔዓለም ገዳም መገኘቱ ምስጢራዊነቱን ጥልቅ ያደርገዋል። ፫) እመ -ገነት ።እመ-ገነት " እመ" እና "ገነት" የሚል የሁለት ቃላት ጥምረት ሲሆን።"እመ" ማለት እናት ማለት ሲሆን ገነት ማለት ደግሞ የእመቤታችን ምሳሌ ነው።ገነት ደስታን የምትሰጥ ለምለም ቦታ ስትሆን በሌላ በኩል የእመቤታችንም ምሳሌ ናት። በጣም የሚገርመው የአካባቢው ልምላሜ የአይን ማረፊያ የልብ ተስፋ መሆኗ ነው። የበረከትና የረድኤት አገር የሆነችው በቀላሉ ሊረዷትና ሊተረጉሟት የማይቻል የስውር ድብቅ ቅኔ ማህደር !!በጊዜ ሂደት በዘመን ዑደት ምስጢር ፈቺ ትውልድ ሲፈጠር ምስጢር ሰሚ ትውልድ ሲኖር ሊገለጥ የሚችል እውነትን ሰንዳ የያዘች የምስጢር ጎጆ፣የእውቀትና የጥበብ ደጅ መንዝ!! መልካም ቆይታ!!! @mahtotetonetor2
1092Loading...
26
እንግልቱ ግን በረከትዎ ነው።"ወደ መድኃኔዓለም አባትዎ ሲሄዱ አልጋ ለአልጋ ነው መንገዱ"እያሉ ይጓዙ።ሰው ቀዝቃዛ ፀበል ውስጥ ገብቶ"እሰይ!እሰይ!"የሚለው ለምን እንደሆነ ያኔ ይገባችኋል! ሞላሌ ስትደርሱ መካከል ከተማውን ቆርጠው ሲሄዱ በግራ በኩል እመጓል ደብረ ቆጵሮስ ቅዱስ ዑራኤል(እመጓ) ፣አቡነ ሲኖዳን ፣ዘብር ገብርኤልን እያለፉት ይሄዳሉ።ከዚያ ላሎምድር ወረዳ (ወገሬ ከተማ )ይደርሳሉ ከሞላሌ 18.5 ኪ•ሜ 🚌 ከ7ኪ•ሜ ጉዞ በኋላ እስካሁን ወደዚህ ስፍራ ሄዳችሁ የማታውቁ ከሆነ ካሁን በፊት ፈፅሞ አይታችሁት የማታውቁትን ተፈጥሮ ታያላችሁ።መንዝ ደብረ ምሕረት እጓ መድኃኔዓለም የእናቱ የስደት መቀመጫ የነበረችውን ቀጭን አባ ማርያም እና እመዕጓል ቅዱስ ዑራኤልን(እመጓ) በግራ እጁ ቀያ ቅድስት ማርያምን ደግሞ በቀኝ እጁ እየዳሰሰ እየባረከ ገዳም አቦ ማዶ ጫካውስጥ በዓይኖቹ እየተመለከተ እናቴ ሆይ የአስራት አገርሽ የሰው ልጅ መትረፊያ ቦታ ይህ ነው የሚል ይመስላል ይምጡ የምትፈልጉት ቦታውን እራሱን ጠይቁት እራሱ ይመልስላችኋል።መንዝ የቅዱሳን ሀገር እጨጌ ዮሐንስ ፣የአቡነ ሐብተማርያም ከነገስታትም የአፄ ዘርዓ ያእቆብ፣የአፄ በእደማርያም •••••••ልብ ያለው ይቆፍረው።የታላቁ ሊቅ የቦሩሜዳው መምህር አካለወልድ፣የሊቀ ሊቃውንት ድጓ በጉንጩ የተባለላቸው የኔታ አክሊሉ እትብትም በዚያ አለ። 🚌በዚህ ታላቅ የምሕረት የፈውስ ቦታ ይምጡና ይፈወሱበት ፣ሰላምዎትን ይጎናጸፉበት ።መቼስ ይህን ካላዩ ለማመንም በቃላት ለመግለፅም ይቸግራል።ያደለው ያየዋል። ምስክርነትም ይሰጣል።እኛም ለነፍስም ለሥጋም የሚሆን ስንቅ እናቀርባለን! #በተለያዩ የሀገራችን ክፍል የምትገኙ የጉዞ ማኅበራት መጥታችሁ ተጋብዛችኋል በክብር እንቀበላችኋለን ይህን የበረከት ሥራ በመስራታችሁም ሰላምና ጤንነት ይብዛላችሁ ቴሌግራም ግሩፕ @mahtotetonetor2 ላይ በመቀላቀል የበለጠ መረጃ ያግኙ ወይም @sekokaw ይጻፉልን ሼር ሼር
1933Loading...
27
ዋሻ ውስጥ በመገኘቱ በተለምዶ የዋሻው ንጉሥ እየተባለ የሚጠራው ደብረ ምሕረት እጓ መድኃኔዓለም ነገስታት ቋሚ መቀመጫ ባልነበራቸው መካከለኛው መቶ ክፍለ ዘመን ለማረፊያነት የመረጡት የሰላድንጋይ ማርቆስን ተሳልማው ጻድቃኔን ተማጽነው የሚኖሩት ነገስታት እግር ጥሎት ወደ መንዝ የሚጓዝ ሲሰሙ እባክህ ከእጓ መድኃኔዓለም ጸበል አደራ የተባለለት የፈውስ የምሕረት ቦታ ደብረ ምሕረት እጓ መድኃኔዓለምን ማወቅ እና መጎብኘት ይፈልጋሉ!? 🚌 መልካም፣እንግዲያውስ የሚከተሉትን አቅጣጫ መጠቆሚያ ይከተሉ።ከአዲስ አበባ ወይም ደብረ ብርሃን ከተነሱ ለስለስ ያለውን ነፋሻ አየር እየተቀበሉ እስከ ጣርማ በር ይጓዙ። ከዚያም የጠጠር መንገዱን ተከትለው የመንዝ ሰንሰለታማ ተራራዎችን እንደ ጉም እየጋለቡ፣ተፈጥሮን ከእግር እስከራሷ እየመረመሩ፤ እርሷም በቅዝቃዜ ማሽኗ እየመረመረችዎት ተባብረው ይጓዙ።ምናልባት ከጣርማበር አንድ አንድ ጣሳ ቆሎ ገዝተው ከሆነ እሷን በጥርስዎት እየፈጩ ብርዱ እንዳይሰማዎ ማድረግ ይችላሉ። 🚌 ከብዙ እንግልት በኋላ ሞላሌ ይደርሳሉ።
1612Loading...
28
#ከትንሣኤ_እስከ_ዕርገት የጌታችን መዋዕለ ሥጋዌ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፦ 1. ቅድመ መስቀል፦ ቅድመ መስቀል የምንለው 33 ዓመት ከ 3ወሩን ነው፤ ይህ ጊዜ ኃጢአት ያልሆነ ማንኛውም ነገር በክርስቶስ የተከናወነበት ልዩ ጊዜ ነው፡፡ 2. ጊዜ መስቀል፦ በመስቀል/በጽኑ ስቃይ የቆየበት ሰዓት 3. ድኅረ መስቀል፦ ድኅረ መስቀል የምንለው ደግሞ በአካለ ሥጋ ከመስቀል ወደ መቃብር ፤ በአካለ ነፍስ ወደሲኦል ከሄደበት ቅጽበት ወዲህ ያለውንና 40ዎቹን ቀናት ወይም 1 ወር ከ10 ቀናትን ነው፡፡ *(ከዕርገት እስከ ጰራቅሊጦስ ያሉትን 10 ቀናት ለብቻ እናያቸዋለን)* ✝ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኀላ 40 ቀን በዚህ ምድር ቆይቷል ፡፡ በነዚህ ቀናት ውስጥም በዋናነት 2 ዋና ዋና ሥራዎችን እንደሠራ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ 1. ለሐዋርያት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እና መጽሐፈ ኪዳንን ማስተማር፦ ለቅዱሳን ሐዋርያት በጉባኤ የተገለጠላቸው 3 ቀናት ቢሆንም ለእያንዳንዳቸው ለየብቻም 2 ወይም 3 ሆነው ግን ሳይገለጥላቸው የዋለበት ያደረበት ጊዜ አልነበረም፡፡ "ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው" እንዲል ሉቃስ ፤ሐዋ 1 : 3፡፡ በተገለጠላቸውም ጊዜ ቤተ ክርስቲያን እንዴትና በምን በማን መተዳደር እንዳለባት አስተምሯቸዋል፡፡ ለምሳሌ ፦ " እርሱም። መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ አላቸው። ስለዚህ ጣሉት፤ በዚህም ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጐትቱት አቃታቸው" ፤ ዮሐ 21 :6 ፤ በማለት ቅዱስ ዮሐንስ እንደጻፈው መረቡ በቀኝ እንዲጣል ማዘዙ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሁሉ በቀኝ በክብርና በፍቅር እንደሚፈጸም ያሳያል፡፡ ሐዋርያት "እንደቃልህ እናደርጋለን" ብለው እንደ ቃሉ መሠረት ማድረጋቸው ደግሞ ቤተ ክርስቲያን የምትፈጽመው ሥርዓት ሁሉ መሠረቱ የጌታ ቃል እንደሆነ ይህም በማመን የሚፈጸም መሆኑን ያመለክታል፡፡ ዓሣዎቹም በየጊዜው የሚያምኑ የሚጠመቁ ምእመናን ምሳሌዎች ናቸው፤ ቀጥሎ በተዘጋጀው ማእድ በአንድነት መመገባቸውም የሁላችን ማእድ የሚሆነውን ከመላእክት ጋር የምናመሰግነውን የምስጋናችንን አንድነት ያመለክታል፦ " ወደ ምድርም በወጡ ጊዜ ፍምና ዓሣ በላዩ ተቀምጦ እንጀራም አዩ"፤እንዲል ዮሐ 21 : 9፡፡ ይህንም ማእድ መላእክት እንዳዘጋጁት መተርጉማነ ሐዲስ ገልጸዋል፦ ትርጉሙ ኅብረተ መላእክት ወሰብእ ነው፡፡ "ወኅብስተ መላእክቲሁ በልዑ እጓለ እመ ሕያው"( ሰዎች የመላእክትን ምግብ በሉ) የሚለው ትንቢተ ዳዊት የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜው በዚህ ፍጻሜውን አግኝቷል፤ መዝ 77፡25፡፡ በዓለም መጨረሻም የሚሆነው ይኸው ነው፤ ከመላእክት ጋር ለዘለዓለም ማመስገን!!! ከዚህም ቀጥሎ ደግሞ ለጴጥሮስ በጎቹን የመጠበቅ ኃላፊነቱን (ክህነትን) አጠንክሮ አደራ ይለዋል፡፡ ስለዚህ ይህ ሁሉ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ነበር፡፡ ለዚህም መጠበቂያ መመሪያ የሚሆን ጸሎት 7ቱን ኪዳናት አስተምሯቸዋል፡፡ 2. ለነፍሳት አህጉራተ ገነትን ማካፈልና ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያትን ማሳየት/ማስተማር፦ ገነት በ15 አህጉራት እኩል የተከፈለች መሆኗን አበው አስተምረውናል (መጽሐፈ ቀሌምንጦስ)፤ ዓለማችን በሰው ሰራሽ አከፋፈል መሠረት 7 አህጉራት አሏት፤ ገነት ግን የአንዱ አህጉር መጠን ባይታወቅም ቅሉ በ15 አህጉራት የተከፋፈለች ሰፊ መሆኗን ያሳያል፤ ይህች ዓለም የቅጣት ቦታችን ናት (ምድረ ፋይድ/ምድረ ፍዳ) ገነት ግን ጥንተ ርስታችን ናት፡፡ ጌታ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ካወጣ በኀላ ወደ ገነት አሳልፏቸዋል፤ እርሱ ባወቀም ነፍሳት መኖር በሚገባቸው እያመሰገኑ እንዲኖሩ ቦታ ቦታቸውን አስይዟቸዋል፤ ፍጡር ሆኖ ያለ ቦታ መኖር አይቻልምና፡፡ "በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው" እንዲል ቅ.ጴጥሮስ፤ 1ኛ ጴጥ 3 : 19፡፡ ✝ገነት ከገቡ በኀላም ገነት የዘለዓለም መኖሪያቸው እንዳልሆነችና ለዘለዓለም የሚያወርሳቸውን የማታልፈውን የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር አስተምሯቸዋል፡፡ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር በዓይነ ሥጋ ማየት፤ በእዝነ ሥጋ መስማት፤ በአእምሮ ጠባዕይ ማወቅ አይቻልም፤ የሚታወቀው በአእምሮ መንፈሳዊ በዓለመ ነፍስ ነውና ለነፍሳት አስተማራቸው፤ ይህም መዓርግ ወይም ደረጃ ነው፤ ምሥጢራትን የምናውቅበት ደረጃ አለ በዓለመ ነፍስ የምንረዳውን በዓለመ ሥጋ አንረዳውም ፦ "ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ፤ እንዳለ ቅ.ጳውሎስ፡፡ 1ኛ ቆሮ13 : 12፡፡ ዳግመኛም፦ "ነገር ግን ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን"፤ ብሏል፡፡ 1ኛ ቆሮ 2 : 9፡፡ እኛም በዚህ በዓለ ሃምሳ ስለ ምሥጢረ ትንሣኤና ስለ ዘለዓለማዊው ሕይወት አብዝተን የምንማርበትና የምንመረምርበት ሊሆን ይገባል፡፡ 40ዎቹ ቀናት፦ • አዳም ከተፈጠረ በኋላ ገነት ከመግባቱ በፊት 40 ቀን በምድር ቆይቷል፦ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስም ከዕርገቱ በፊት 40 ቀናትን በዚህ ምድር ቆይቷል፡፡ • የሰው ተስእሎተ መልክዕ በማኅፀን የሚፈጸምለት በ 40 ቀንናት ውስጥ ነው፤ ቤተ ክርስቲያንም የሥርዐቷ ተስእሎተ መልክዕ ተቀርጾ የተጠናቀቀው በ40 ቀናት ነው፡፡ • ሰገኖ እንቁላል ከጣለች በኋላ 40 ቀን ዓይኗን ከአንቁላሉ አትነቅልም፤ ትታው ብትሄድ እንደ ድንጋይ ይደርቅባታል! ጌታችንም ለ40 ቀናት ከቤተክርስቲያን ሐዋርያትን ዓይኑን ሳይነቅል ትክ ብሎ ሲመለከታት ነበር፤ ተለይቷቸው ቢሆን ሐዋርያት በቀቢጸ ተስፋ በደረቁ ነበረና፡፡ (ዛሬም አልተለያትም!) ወነበረ አርብዓ መዋዕለ እንዘ ይሜሕሮሙ ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያት" እንዲል መቅድመ ወንጌል፡፡ “ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው።” እንዲል ሉቃስ — ሐዋርያት 1፥3 ጌታችን 40 ቀናት መቆየቱ እነዚህን ምሥጢራት ያመለክታል፡፡ አምላካችን ምሥጢሩንና ጥበቡን ሁሉ ይግለጥልን!!! ከዕለት እኪት፣ ከዘመን መቅሰፍት ይሠውረን!!! አሜን! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
1 96514Loading...
በዓመት ሁለት ጊዜያት ከሚካሔዱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት አንዱ የግንቦት 2016 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ነው፡፡ ይህ ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ርእሰ መንበርነት ረቡዕ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከጧቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram