cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች

✞ ይህ ቻናል መንፈሳዊ የሆኑ ግጥሞች ፣ ወጎች እንዲሁም መልዕክቶች የሚቀርቡበት ነው ✞ አስተያየት ካለ እንዲሁም ግጥም ወግ እንዲተላለፉ የምትፈልጓቸው መንፈሳዊ መልክቶች ለማድረስ https://t.me/+a3-5g5CslOkwNjBk ተጠቀሙ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
2 879
مشترکین
-224 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+2530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ቅዱስ ያሬድ ከዚያ በኋላ ወደ አከሱም ተመልሶ በመደባይ ታብር በተባለ ቦታ ቅዳሴያትን በዜማ አዘጋጅቷል፡፡ ይህ ቦታ ከአከሱም 15 ኪ.ሜ ርቆ ይገኛል፡፡ ከዚህ በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ አክሱምን ተሰናብቶ ለመሄድ ወደ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገባና «ቅድስት ወብጽዕት ስብሕት ወቡርክት ክብርት ወልዕልት አንቀጸ ብርሃን ማዕርገ ሕይወት» እያለ አንቀጸ ብርሃን የተባለውን ድርሰቱን ሰተት አድርጎ አዘጋጀው፡፡ ይህንን ድርሰት ሲያዜም አንድ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ብሎ ይታይ ነበር ይባላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በሰሜንና ወገራ፣ አገውና በጌምድር እየተዘዋወረ አስተምሮ ከሰሜን ተራራዎች ውስጥ እየጾመና እየጸለየ በብሕትውና ለብዙ ዘመን ከኖረ በኋላ በሰሜናዊ ምሥራቅ በኩል ባለው በጸለምት ዋሻ ውስጥ በ571 ዓ.ም ግንቦት 11 ቀን ተሠውሯል፡፡ ይህ ቦታ በተለምዶ የሰሜን ተራሮች በሚባለው ወስጥ የሚገኝ ከፍተኛና ብርዳማ ቦታ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሰማያዊ ዜማን ከማበርከቱም ሌላ በትምህርት ሂደትም አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡ የድጓን፣ የጾመ ድጓን የዝማሬ መዋሥዕትንና የቅዳሴን ትምህርት ከማስተማሩም በላይ ለቅኔ ትምህርትም መሠረት ጥሏል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በዓለም የመጀመርው የዜማ ኖታ/ ምልክት/ ባለቤት ነው። በእውነት የቅዱስ ያሬድን ጸጋ ያብዛልን ረድኤቱ ፣ በረከቱ ፣ ቃል ኪዳኑን ያብዛልን አሜን አሜን።
نمایش همه...
👍 2
​​እንኳን ለቅዱስ ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ። #ቅዱስ_ያሬድ_ማነው? የቅዳስ ያሬድ አባቱ አብድዩ / ይስሐቅ/ እናቱ ክርስቲና /ታውክልያ / ይባላሉ። በሌላም በኩል አባቱ እንበረም እናቱ ትውልያ ይባላሉ የሚል ታሪክም አለ፡፡ የትውልድ ሥፍራው አክሱም ነው፡፡ የተወለደው በ505 ዓ.ም/ ሚያዝያ 5 ቀን ሲሆን በተወለደ በ7 ዓመቱ ወላጅ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ጽዮን መምህር ለነበረው ለአጎቱ ለጌዴዎን እያስተማረ እንዲያሳድገው ሰጠችው፡፡ ከአባ ጌዴዎንም ዘንድ እየተማረ ለ25 ዓመት ተቀመጠ፡፡ ሆኖም ቃለ እግዚአብሔር የመቀበል ችሎታው ደካማ ስለሆነ በጣም ያዝን ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ከትምህርት ድክመቱ የተነሣ አጎቱ በጨንገር ቢገርፈው በዚህ ተበሳጭቶ ትምህርቱን ትቶ ሄደ፡፡ በመንገድም ሲጓዝ ውሎ በቀትር ደክሞት ከዛፍ ሥር ዐረፈ፡፡ በዚያ ጊዜ አንድ ትል ከዛፉ ላይ ያለውን ፍሬ ለመብላት ስድስት ጊዜ በመውደቅና በመነሣት ዛፉ ላይ ለመውጣት ሞክሮ በሰባተኛው ሰተት ብሎ ወጥቶ ሲበላ ተመለከተ፡፡ እርሱም በፈጸመው የብስጭት ተግባር በመጸጸት ተመልሶና አጎቱን ይቅርታ ጠይቆ ትምህርቱን ቀጠለ፡፡ አጎቱም ተደስቶ ዓይነ ልቡናውን ያበራለት ዘንድ እያለቀሰ ፈጣሪውን ለመነለት፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ለቅዱስ ያሬድ ዕውቀትን ገልጾለት መጻሕፍተ ብሉያትንና ሐዲሳትን ዐወቀ፡፡ ከዚያም በኋላ ወደ መምህሩ ተመልሶ ትምህርቱን ቀጠለና ቅዱሳት መጻሕፍትን በሚገባ አጠና፡፡ ሢመተ ዲቁናን ቀጥሎም ሢመተ ቅስናን ተቀበለ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ግእዝ፣ እዝልና አራራይን ከሦስት ወፎች/መላእክት በወፎች ተመስለው/ መማሩን ሊቃውንት ይገልጣሉ፡፡ እነዚህ በወፍ የተመሰሉ መላእክት እየመሩት ወደ አርአያም አርጎ የ24ቱን ካህናተ ሰማይ ዜማ ከተማረ በኋላ ጠዋት በ3 ሰዓት በአክሱም ቤተ ክርስቲያን «ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሣረረ ወበዳግመ አረአዮ ለሙሴ ዘከመ ይግበር ግብራ ለደብተራ» ብሎ አዜመ፡፡ ይህን ዜማ የደረሰበት ወሩ ታኅሳስ ቀኑም ዕለተ ሰኞ ነው ይባላል፡፡ የቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያ ዜማው «አርያም» በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም ከመላእክት ወይም ከሰማይ የተገኘ መሆኑን ለማጠየቅ የተሰጠው ስም ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ይህንን ዜማ በተመስጦ ሲያዜም ንጉሡ ፣ ንግሥቲቱ ፣ ጳጳሱ መኳንንቱና ካህናቱ ወደ አኩስም ቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው መጥተው በአድናቆት ያዳምጡት ነበር፡፡ ምክንያቱም ገድለ ቅዱስ ያሬድ እንደሚገልጥልን ከዚያ በፊት በውርድ ንባብ ከሚደረግ ጸሎትና መንፈሳዊ አገልገሎት በቀር ይህን የመሰለ ዜማ አልነበረምና፡፡ የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ብሉይን ከሐዲስ ያስማማ ፣ የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በሚገባ የያዘ ፣ እንዲሁም ለልዑል እግዚአብሔር ፣ ለእመቤታችን ፣ ለቅዱሳን መላእክት ፣  ለሰማዕታት ተገቢ የሆነውን ምስጋና የያዘ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ለአራቱ የዓመቱ ወቅቶች እንዲስማማ አድርጎ ለበጋ፣ ለክረምት ፣ ለመጸውና ለጸደይ እንደሚሆን አድርጎ ከፋፍሏቸዋል፡፡ ለየበዓላቱም ተስማሚ ድርሰት መድቦላቸዋል፡፡ ይህንን ድርሰቱን በግእዝ ፣ በእዝልና በአራራይ ዜማ ያዘጋጀው ሲሆን ለነዚህም ስምንት የዜማ ምልክቶች ሠርቶላቸዋል፡፡ የቅዱስ ያሬድ ዜማ አንዴት ሁሉንም ይመስጥና ወደ አርያም በመንፈስ ይወስድ እንደ ነበር ለማስረዳት በገድሉም በሌሎችም መጻሕፍት የተመዘገቡ ታሪኮች አሉ፡፡ አንድ ቀን ንጉሥ ገብረመስቀል ፣ ንግሥቲቱ ፣ ጳጳሱ ፣ ካህናቱና ምእመናኑ በተሰባሰቡበት ቅዱስ ያሬድ ዜማውን ሲያዜም ንጉሡ በመመሰጡ የተነሣ በመሰቀል ተሰላጢኑ ጫፍ የቅዱስ ያሬድን እግር ወጋው፡፡ ነገር ግን ማንም አላወቀም ነበር፡፡ ቅዱስ ያሬድ መዝሙሩን ሲፈጽም ንጉሡ መስቀል ተሰላጢኑን ቢያነሳው የቅዱስ ያሬድ ደሙ ፈሰሰ፡፡ ንጉሡ በዚህ ደንግጦ ለዚህ ካሣ ይሆን ዘንድ የፈለግከውን ጠይቀኝ እሰጥሃለሁ ብሎ ቃል ገባለት፡፡ ቅዱስ ያሬድ ግን ከዚህ ዓለም ተለይቶ በምናኔ መኖርና መዝሙሩንም በሚገባ ማዘጋጀት እንደሚፈልግ ገለጠ፡፡ ምንም እንኳን አክሱምን ለቅቆ መውጣቱ ንጉሡን ቅር ቢያሰኘውም ቃሉን አንድ ጊዜ በመስጠቱ ምንም ሊያደርገው አልቻለም፡፡ ቅዱስ ያሬድም ከዚህ በኋላ አኩስምን ለቅቆ ወደ ስሜን ተራራ ጸለምት መጓዙ ይነገራል፡፡ በጐንደር ፎገራ በሚባል ሥፍራ ቅዱስ ያሬድ ጣዕም ያለው ዜማውን ሲዘምር ተጠምደው የሚያርሱ በሬዎች ድምፁን እየሰሙ ገበሬውን ሥራ ስለ አስፈቱት በዚህ ተናዶ ቅዱስ ያሬድን በጅራፍ እንደ ገረፈው ይነገራል፡፡ ቦታውም « ወርቀ ደም እየተባለ እስከ ዛሬ ይጠራል፡፡ ወርቃማና ንጹሕ ደሙ የፈሰሰበት ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ዜማውን ያዘጋጀበት ዘመን ከ540-560 ዓ.ም ባለው ጊዜ መሆኑ ይነገራል፡፡ ዜማውን ካዘጋጀ በኋላ 11 ዓመት አስተምሯል፡፡ በእርሱ ዘመን ተሰዓቱ ቅዱሳን በሃይማኖት ችግር ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው መጥተው ስለ ነበር ቅዱስ ያሬድ ከአንዱ ከአባ ጰንጠሌዎን የውጭውን ሀገር ቤተ ክርስቲያን ባሕልና ሥርዓት ይጠይቅ ነበር፡፡ በጆሮ የሰማውንም በዓይን ለማየት ሁለት ጊዜ ሮም የተባለችውን የቁስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያን ጐበኘሁ ይላል፡፡ «ወሪድየ ብሔረ ሮሜ ለቤተ ክርስቲያን ርዒክዋ» እንዲል፡፡ የታሪክ ምሁሩ ሥርግው ሀብለ ሥላሴ ለቁስጥንጥንያ ዜማ መነሻው ቅዱስ ያሬድ ነው ይላሉ፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚያደርጉት የቁስጥንጥንያን ዜማ የደረሰው ሊቅ ዜማውን አገኘው የሚባለው የቅድስት ሶፍያን ቤተ ክርስቲያን ሲዞር ከሰማው ዜማ ነው፡፡ ይህ ዘመን ደግሞ ቅዱስ ያሬድ ከተነሣበትና ወደ ሮሜ ሄድኩ ካለበት ዘመን ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ እናም ምናልባት ያ ሰው ዜማውን የሰማው የቅድስት ሶፍያ ቤተ ክርስቲያንን እየዞረ ሲዘምር ከነበረው ከቅዱስ ያሬድ ሳይሆን አይቀርም ይላሉ፡፡ Ancient and medival Ethiopian History/ ቅዱስ ያሬድ ማትያስና ዮሴፍ በተባሉ የአቡነ አረጋዊ ደቀ መዛሙርት መሪነት ወደ ደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ወጥቶ ከጻድቁ ጋር በመገናኘትና የቤተ ክርስቲያኑን ሥራ እያደነቀ ዙሪያውን ከዞረ በኋላ «ዖድክዋ ወርኢኩ ሥነ ሕንፃሃ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን» ሲል ዘመረ፡፡ በዚያም ለአንድ ሳምንት ሰንብቶ ሄዷል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከአቡነ አረጋዊ እና ከዐፄ ገብረ መስቀል ጋር በመሆን በወሎ፣ በጎንደር፣ በሸዋ እና እስከ ጋሞጎፋ ብርብር ማርያም ድረስ በመሄድ አስተምሯል፡፡ አንዳንድ መረጃዎች የዐርባ ምንጭን ታሪክ ከቅዱስ ያሬድ፣ ከአቡነ አረጋዊ እና ከዐፄ ገብረ መስቀል ታሪክ ጋር ያያይዙታል፡፡ ሦስቱም ብርብር ማርያምን ለማየት ሄደው በነበረ ጊዜ በዛሬው ዐርባ ምንሥ አካባቢ ሠፍረው ነበር፡፡ በዚያ ቦታ ለወታደሩ የሚበቃ የሚጠጣ ውኃ በመጥፋቱ አቡነ አረጋዊ ጸልየው መሬቱን በመስቀል ቢመቱት ዐርባ ውሃዎች ፈለቁ ይባላል፡፡ ዐፄ ገብረ መስቀል የጣና ቂርቆስን ቤተ ክርስቲያንን በሚያሠራ ጊዜ በዚያ ቦታ ለሁለት ዓመት ተቀምጦ ድጓውን በማስተማሩ ምልክት የሌለው ድጓው እስከ ዛሬ በገዳሙ ይገኛል፡፡ ቀጥሎም የዙር አባን ቤተ ክርስቲያን ለማሠራት ወደ ጋይንት በተጓዙ ጊዜም በዚያ ሁለት ዓመት ዝማሬ መዋሥዕት የተባለ ድርሰቱን አስተምሯል፡፡ ይህ ቦታ እስከ ዛሬ የዚህ ትምህርት ማስመስከሪያ ነው፡፡
نمایش همه...
👍 3
ዳግማይ ትንሳኤ ማለት ዳግም መነሳት (ሁለተኛ መነሳት) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ #ዳግማይ\ትንሳኤ ተብሏል። ሁለተኛ ለምን ተገለጠ? 👉 ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጉኔን ዳስስ ብሎታል። ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል ።ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው ።ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች (የዳሰሰች)እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች ።እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ። 👉 ሰንበትን ሊያጸናልን የአይሁድ ሰንበት፣እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም(ቅዳሜ)ናት ።በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ከሙታን መካከል የተነሳባት፣አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት(ዳግማይ ትንሳኤ)፣መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች ።ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች ።ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት ።እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን)የምናሳልፈው ማለት አይደለም ።እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ 👉 ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል ።በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ። "ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ" (ዮሐ20:29) የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
نمایش همه...
👍 9 2
#ቅዳሜ ቅዱሳት_አንስት የዛሬው ዕለት #ቅዱሳት_አንስት ወይም #አንስት_አንከራ ተብሎ ይጠራል 👉"አንስት አንከራ ትንሣኤሁ ነገራ" እንዲል ቅዱስ ያሬድ ፤ ሴቶች አደነቁ ትንሣኤውን ተናገሩ ማለት ነው ለጊዜው የጌታን ትንሣኤ ያበሠሩ ሴቶች መታሰቢያ ቢሆንም ፍጻሜው ግን ለክርስቲያን ሴቶች ሁሉ መታሰቢያ ቀን ነው። ዛሬም ብሥራተ ትንሣኤውን በዝማሬ በምስጋና በማስቀደስ በመቁረብ በሚዲያ በቃል በተግባር በማብላት በማጠጣት በማስተናገድ በጸሎት....በልዩ ልዩ አገልግሎት የሚፋጠኑ የሚመሰክሩ ሴቶች "ቅዱሳት አንስት" ይባላሉ (የተለዩ የተመረጡ የጸኑ  ማለት ነው)። እግዚአብሔር እናቶችንና እህቶችን ይጠብቅልን!
نمایش همه...
#ዐርብ ቅድስት_ቤተክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ዐርብ የእግዚአብሔር ቅድስት ማደሪያ በሆነችው ቤተ ክርስቲያን ተሰይማለች፤ ይህም ሁሉም ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመባት ዕለት በመሆኗ ነው፤ ዕለተ ዐርብ፤ የሥራ መከተቻ፤ ምዕራብና መግቢያ በሚሉት ስያሜዎችም ትጠራለች፡፡ በዕለቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ያደረገውን ተአምር በመስቀሉ ድኅነትን እንዳሳየ፤ በቀራንዮ የሕንጻዋ መሠረት እንደተተከለላትና ሥጋ መለኮት እንደተቆረሰላት፤ ልጆቿን ከማሕፀነ ዮርዳኖስና ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ የምትወልድበት ማየ ገቦ እንደፈሰሰላት ተገልጾባታል፤(ኤፍ.፪፥፲፱፤ራዕ.፩፥፮-፰)፡፡ https://telegram.me/Melikt_weg_gitim
نمایش همه...
መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች

✞ ይህ ቻናል መንፈሳዊ የሆኑ ግጥሞች ፣ ወጎች እንዲሁም መልዕክቶች የሚቀርቡበት ነው ✞ አስተያየት ካለ እንዲሁም ግጥም ወግ እንዲተላለፉ የምትፈልጓቸው መንፈሳዊ መልክቶች ለማድረስ

https://t.me/+a3-5g5CslOkwNjBk

ተጠቀሙ

👍 1
#እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +*" #ልደታ ለማርያም ድንግል "*+ #ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ: ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ:: " ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን: ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) " =>የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን:: +ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል:: +እመቤታችን ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9) +ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ2,022 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: "ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" (መኃልይ. 4:8) =>ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር:: +ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም:: +የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች:: +ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን 2ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ:: +እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ:: +በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ:: +እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች:: "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . . ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም) +"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ." "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9) +እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች:: =>የእመቤታችን የዘር ሐረግ:- *አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ= *በእናቷ:- -ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና:: *በአባቷ በኩል:- -ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል:: +ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,026 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: =>የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን:: =>ግንቦት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ልደታ) 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቴክታና በጥሪቃ 4.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3

https://youtu.be/csxxAMGtC4I

ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን • አሰሮ ለሰይጣን ~ አግአዞ ለአዳም • ሰላም ~ እምይእዜሰ • ኮነ ~ ፍስሐ ወሰላም። #ረቡዕ -አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን
نمایش همه...
ማክሰኞ ~ ቶማስ " ቶማስም አለ ለእኔ የእጆቹንና የእግሮቹን ችንካሮች የቅድስት ጎኑን መወጋትም አሳየኝ አስቀድሜ እጠራጠርና ትንሣኤውን ሳላምን ሳለው የቀኝ ጎኑን መወጋት ገልጦ አሳየኝ ደስም አለኝ " መጽሐፈ ዲድስቅልያ ይህ ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ የጌታችንን ትንሣኤ ካላየው አላምንም በማለቱ ጎኑን ያዳሰሰበት እና እጁ የደረቀበት መልሶም ያዳነበት ትንሣኤውን አይቶ ማመኑ እና ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ የሚታሰብበት ዕለት ነው ዮሐ 20፥27 ቶማስ ማለት የስሙ ትርጉም ጸሐይ ማለት ነው ከአሥራ ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኃላ ትንሣኤውን ለቅዱሳን ሐዋርያት ሲገልጥላቸው ቅዱስ ቶማስ በቅርብ በአካባቢው አልነበረም ሲመለስ የጌታ ሞትን ድል አድርጎ መነሳት ከቅዱሳን ሐዋርያቱ ሲሰማ ትንሣኤውን ከራሱ ከክርስቶስ መስማት ሽቶ ነበርና ካላየው አላምንም አለ ሊቃውንቱ ለዚህ ሀሳቡ በትርጓሜ ላይ ሦስት ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ ፩ የጌታን ትንሣኤ ሰምቶ ከመመስከር ይልቅ አይቶ ለማመስከር ስለፈለገ ፪ ሌሎቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ተነሳ እያሉ ሲያስተምሩ ከባልንጀሮቼ እንደ ሰማሁት ተነሳ እያለ ማስተማሩ ከእነርሱ የሚያሳንሰው ስለመሰለው ፫ ውልደቱ ትንሣኤ ሙታን የለም ከሚሉ ከሰዱቃውያን ወገን ስለነበር ከልጅነት ጀምሮ ስለትንሣኤ ሙታን ካለው የተሳሳት መረዳት ለመላቀቅ አይቶ በማመን እና በማረጋገጥ በፍጹም እምነት መመስከር ስለፈለገ ነው ይላሉ በእነዚህ ምክንያቶች ጌታ ተነሣ ቢሉት የተወጋ ጎኑን የተቸነከረ እጁን ካለየው አላምንም አለ ጌታችንም ጣትህን ወደ እኔ አምጣና በጎኔ አግባው ያመንክ እንጂ ያለአመንክ አትሁን አለው ቶማስም እጆቹን ከጌታ ጎን ሲያስገባ እሳት እንደገባ ጅማት ተኮማተሩ በዚህ ጊዜ ጌታዬ አምላኬ ብሎ መሰከረለት ቅዱስ ያሬድም ይሄንን በዝማሬው ሲገልጽ እንዲህ ይላል " ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ ቶማስ እጄን ወደ ጎኑ ጣቶቼንም ወድ ቅንዋቱ ካላስገባው አላምንም አለ ኢየሱስም እኔ እንደሆንኩ እመንብኝ እንጂ እትጠራጠር አለው ቶማስም ጌታዬ አምላኬ አለ " ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ወደ ዓለም ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ የሚለውን የጌታ ትዕዛዝ ለመፈጸም እጣ ወደ ደረሰችው ሀገር ወደ ህንድ ሄዶ በብዙ ተጋድሎ ወንጌልን የሰበከ ሰዎችን ካለማመን ወደ ማመን ከጨለማ ወደ ብርሃን ያመጣ በጥምቀት ብዙዎችን የእግዚአብሔር ልጆች ያደረገ ሐዋርያ ነው ዛሬ ላለችው የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም የወንጌልን መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ የጣለ አባት ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ግንቦት ሃያ ስድስት በሰማዕትነት ያረፈበትን ቀን ታከብራለች ጸሎት እና በረከቱ አይለየን
نمایش همه...
3
• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን • አሰሮ ለሰይጣን ~ አግአዞ ለአዳም • ሰላም ~ እምይእዜሰ • ኮነ ~ ፍስሐ ወሰላም። የትንሣኤ ማግስት ሰኞ "…የትንሣኤ ማግስት ሰኞ ማዕዶት ይባላል፦ ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ መሻገሩ እስራኤል ባህረ ኤርትራን፣ ኢያሱና ካህናቱ፣ ኤልያስና ኤልሳዕ ባህረ ዮርዳኖስን እንደተሻገሩት ያለ መሻገር አይደለም። ይህኛው መሻገር በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን እንጂ፡፡
نمایش همه...