cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

DIALOG-OF-IDIOLOGY💆

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ●በፍልስፍናቸውና፣በመጠቀ አስተሳሰባቸው፣ዓለምን ማስደመምና መሳብ የቻሉ የፍልስፍና ሰዎች ምልከታቸው፣ታሪካቸውና፣የተለያዩ ጉዳዮችን የሚያነሳ ●እንዲሁም ከናንተ ጋር በጥልቅ ውይይቶች የሚያምን ቻናል ነው ከኛ ጋር ስለሆናችሁ እናመሰግናለን...!👈 👆👆👆👆👆❤❤❤❤👆👆👆 👆👆👆👆👆❤❤❤❤👆👆👆

نمایش بیشتر
Advertising posts
1 555مشترکین
-124 ساعت
-47 روز
-1230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

🌿እግዚአብሔር እንድንጠፋ ስለሚፈልግ አይደለም ነፃነትን የለገሰን.!እርሱ በአገዛዙ፣በሥራውና፣በቃሉ የታመነ ነው። ይህ በመሆኑ በሐላፊነትና፣በምስጋና መቃኘት የእያንዳንዳችን ግዴታ ነው.!አኗኗራችንን በሰላም ለመምራት ይህንን ስጦታ በተገቢው መልኩ መጠቀም ያሻናል፥ ማስተዋል ተስኖን በነገሮች ተሰናክለን ህይወት ሲመረን ፈጣሪ መመለሳችንን ይጠባበቃል። በመሳሳታችን ምክንያት ፈቃዳችንን መልሶ የሚወስድ ተቀያያሪ ባህሪ የተላበሰ አይደለም.!በቸርነቱና፣በደግነቱ ወደር የማይገኝለት አምላክ ነው። በቸልተኝነታችን ተከበን ሰብአዊነት ሲጎድለን በምርጫ የመኖር አቅማችንን በመንሳት ቃሉን በፍጹም አላጠፈም.! የሰጠንን መልሶ ያልነጠቀን ከታማኝነቱ የተነሳ ነው። . ዲ/ን ተፈሪ(#PHILO)
نمایش همه...
👍 3
አንዳንዴ . . . ያለ ነው! አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም! አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም! አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም! አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም! አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም! አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዘም! አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አየቅተንም! አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም! አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም! አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም!
نمایش همه...
👍 6
አንዳንዴ . . . ያለ ነው! አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም! አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም! አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም! አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም! አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም! አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዘም! አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አየቅተንም! አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም! አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም! አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም! https://t.me/Dialog_of_Idiology
نمایش همه...
DIALOG-OF-IDIOLOGY💆

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ●በፍልስፍናቸውና፣በመጠቀ አስተሳሰባቸው፣ዓለምን ማስደመምና መሳብ የቻሉ የፍልስፍና ሰዎች ምልከታቸው፣ታሪካቸውና፣የተለያዩ ጉዳዮችን የሚያነሳ ●እንዲሁም ከናንተ ጋር በጥልቅ ውይይቶች የሚያምን ቻናል ነው ከኛ ጋር ስለሆናችሁ እናመሰግናለን...!👈 👆👆👆👆👆❤❤❤❤👆👆👆 👆👆👆👆👆❤❤❤❤👆👆👆

#ይመችህ👍 ሕይወት በረባ ባልረባው ለመጨቃጨቅ አጭር ናት... "ይመችህ👍" ብለህ መንገድህን ቀጥል #ስሜትን_በብልኃት_መምራት መጽሐፍ #EMOTIONAL_INTELLIGENCE ይህን በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያገኘ መጽሐፍ አንብበው ከወደዱት ታላላቅ ሰዎች መካከል፦ 👇🎀👇 - ኦፕራ ዊንፍሬይ - ዋረን ባፌት - ቢል ጌትስ - ባራክ ኦባማ - ኤለን መስክ - ቶኒ ሮቢንስ እና ሌሎችም ይገኙበታል። አንተም ይህን መጽሐፍ በማንበብ፣ የስሜት ብልኃት ጠቀሜታውን በመረዳት ስሜቶችህን ሁሉ ለስኬት በመጠቀም በሕይወትህ ላይ አስደናቂ ለውጥ እንደታመጣ ተጋብዘሀል። #ስሜትን_በብልኃት_መምራት መጽሐፍ በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡ 📕📕📕
نمایش همه...
👍 3
ሙዚቃ ውብ ነገር ነው፤ መንገዱ ግን... (አሌክስ አብርሃም) መጠጥ ፣ ልቅ ወሲብ፣ ጫት ፣ ዘግናኝ የሲጋራ ሱስ፣ ድራግ፣ ምቀኝነት ፣ መካካድ ፣ፀብ፣ ለገንዘብ መጋደል ፣ መናናቅ ፣ ፍች፣ የቤተሰብ መበተን ፣ የልጆች ሰቆቃ፣ ስደት ፣ በኑሮ መቸገር፣ የተጋነነ ስምና ስምን የማይመጥን ኑሮ ፣ ተቀባይነት ማጣት፣ በእዳ መዘፈቅ ፣ በብዙ ጉዳይ ነፃነት ማጣት፣ በጓደኝነትና ትውውቅ ስራ ማግኘት ፣ አድመኝነት ፣ ወረተኛነት በዚህ ጠንቅ የሚመጣ አካላዊ ህመም ወይም የአእምሮ መታወክ...ይሄ ሁሉ ተወዳጅ ዘፈን በዚህ እና በሌሎችም ያልተገለፁ ሰቆቃዎች ውስጥ ያለፈ ነው! የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች በተለይ ((በጣም ከጥቂቶቹ በስተቀር)) ህይዎታቸው በየቃለመጠይቁ እንደሚታየውና ሲሞቱ እንደሚንቆለጳጰሱት አይደለም ! ለእውቅና በየመድረኩ የሚጋደሉትን ወጣቶች ስመለከት ይሄን በማር የተለወሰ የሰቆቃ መንገድ ከወዲሁ ማየት ከቻሉ ለማሳሰብ ያህል ነው! "አርት" ውብ ነገር ነው ፤ ግን ወደከፍታው የሚወስደው መሰላል በብዙ ብዙ ቆሻሻ የተሞላ ነውና ወደከፍታው ለመውጣት ይህን ቆሻሻ ለመርገጥም ለመጨበጥም ትገደዱ ይሆናል! ከወዲሁ ጠንካራ መንፈስ ይዛችሁ ለመጓዝ ሞክሩ! በሁሉም ሰው ታውቃችሁ ለራሳችሁ ከጠፋችሁ ምን ዋጋ አለው?! ፨ https://t.me/Dialog_of_Idiology
نمایش همه...

👍 3
እረፍት ! እሁድ ደስ የሚል ቀን ነው ተማሪው ከትምህርቱ ሰራተኛውም ከስራ ገበታው እረፍት የሚወስድበት ቤተሰብን ጓደኞች የታመሙ የታሰሩ ሁሉ የምትጠይቅበት ቀን ነው ሁሉንም ጠይቀሀል? ነገር ግን አንድ ሰው እንዳትረሳ ይሄ ሰው በጣም መጠየቅ አለበት ዛሬ ሳትጠይቀው ከረሳኸው ሳምንቱን ሙሉ ታበላሽበታለህ ብዙ ሊያደርጋቸው ከሚችላቸው ተግባራት ትገድበዋለህ ይሄ ሰው አንተ ነህ ሁሉም ቦታ ስትደርስ ራስህንም አስታውስ በሳምንትህ ምን አደረግህ ቀጣይስ ምን ልታደርግ አቀድህ ትንሽ ደቂቃም ብትሆን ለራስህ ስጠው! የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏 የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊 ታገስ ! "የታገሰ መልካሙን ፍሬ ይበላል" ሁሉም ጥሩ ነገር ለመለምለም ጊዜያትን ይፈልጋል እናም መጠበቅ አቅቶህ ጥለኸው ከሄድክ የለፋህበትን ጣፉጩን ፍሬ እኔ ልበላብህ ነው 😀 ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏 @Inspire_Ethiopia https://t.me/Dialog_of_Idiology
نمایش همه...
DIALOG-OF-IDIOLOGY💆

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ●በፍልስፍናቸውና፣በመጠቀ አስተሳሰባቸው፣ዓለምን ማስደመምና መሳብ የቻሉ የፍልስፍና ሰዎች ምልከታቸው፣ታሪካቸውና፣የተለያዩ ጉዳዮችን የሚያነሳ ●እንዲሁም ከናንተ ጋር በጥልቅ ውይይቶች የሚያምን ቻናል ነው ከኛ ጋር ስለሆናችሁ እናመሰግናለን...!👈 👆👆👆👆👆❤❤❤❤👆👆👆 👆👆👆👆👆❤❤❤❤👆👆👆

👍 3 2
🌿ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ ሰው መሆን ሲሆን የሚፈልጉትን ሁሉ ማድረግ ግን አምላክ መሆን ነው:: 💫ናፖሊዮን ።።።። . ዛሬ በአድናቆት አጅቦ የሚከተለኝ ሕዝብ ነገ ለመሰቀል ስሄድ ደግሞ - አጅቦ ይከተለኛል፡፡ 💫ናፖሊዮን 🕊 ነገ መልካም ይሆናል ! 🕊 https://t.me/Dialog_of_Idiology👈🙏
نمایش همه...

👍 4🔥 1
🌿ህይወት በነብርና በሚዳቆ መካከል እንዳለዉ እልህ አስጨራሽ ሩጫ ናት፡፡ ብዙ ጊዜ ሚዳቆ ሮጣ ታመልጣለች፡፡ ነብር ደርሶ የሚይዛት ከስንት አንዴ ነዉ.. ይሄ ለምን እንደሆነ ታዉቃለህ? ነብር የሚሮጠዉ ‘ለአንድ ምሳ!’ ሚዳቆ ግን ‘ለዉድ ህይወቷ’ ስለዚህ አላማ ከጊዜያዊ ፍላጎት እንደሚበልጥ ትረዳለህ፡፡ የሚዳቆ አላማ ሕይወቷን ማትረፍና ሌላ ቀንን ማየት ሲሆን የነብር ደግሞ ‘በልቶ መዘረር’ ነዉ፡፡ ከስንት አንዴ ከበላና ከጠገባ በኋላ ሚሊየን ሚዳቆ በአፍንጫዉ ስር ቢያልፉ ምን ገዶት! ለመኖር እልህ ሲይዝህ ለመብላት መኖር ታቆማለህ፣ ለሻይ መጠጫ ተራራ መፈንቀል፣ የሌለዉን እንዳለ ማስመሰል ይደክምሃል...ወደ እዉነተኛዉ መንገድ የዛኔ መመለስ ትጀምራለህ፡፡ ያም ለአላማ መኖር! 🌿 #PHILO 🕊 ነገ መልካም ይሆናል ! 🕊 https://t.me/Dialog_of_Idiology
نمایش همه...
DIALOG-OF-IDIOLOGY💆

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ●በፍልስፍናቸውና፣በመጠቀ አስተሳሰባቸው፣ዓለምን ማስደመምና መሳብ የቻሉ የፍልስፍና ሰዎች ምልከታቸው፣ታሪካቸውና፣የተለያዩ ጉዳዮችን የሚያነሳ ●እንዲሁም ከናንተ ጋር በጥልቅ ውይይቶች የሚያምን ቻናል ነው ከኛ ጋር ስለሆናችሁ እናመሰግናለን...!👈 👆👆👆👆👆❤❤❤❤👆👆👆 👆👆👆👆👆❤❤❤❤👆👆👆

👏 2🤔 1
ጋዜጠኛው አርባ ዓመት በትዳር የቆዩትን ወ/ሮ እያናገረ ነው "ከባለቤትዎት ጋር አርባ ዓመት በትዳር ያለ ጸብ የቆዩበትን ምስጢር እስኪ ይንገሩን" "ምን መሰለህ የኔ ልጅ የሰርጉ ቀን መጀመርያ ከቤተሰቦቼ ቤት ይዘውኝ የወጡ ግዜ በሽልም ፈረስ ላይ አድርገው ነበረ አብረን ሆነን እሳቸው ልጓሙን ይዘው እየጋለቡ እኔ ከኋላቸው ሆኜ ትንሽ እንደሄድን ፈረሱ ለገመ ይሄኔ እሳቸው "አንተ ፈረስ ተው ብየሃለሁ አንድ" አሉ ፈረሱ መሄድ ቀጠለና ትንሽ ቆይቶ አሁንም ለገመ ይሄኔ እሳቸው "አንተ ፈረስ ተው ብየሃለሁ ሁለት" አሉ ፈረሱ የግዱን ሄደ ሄደና ሲደክመው እንደገና ቆመ ያኔ እሳቸው በንዴት ከፈረሱ ላይ ዘለው ወርደው እኔንም አውርደው ሽጉጣቸውን መዘዙና "አንተ ፈረስ ተው ብየሃለሁ ተው ሶስት" ብለው በግንባሩ ለቀቁበት ፈረሱ ክልትው አለ እኔም ደንግጬ "ምን ሆነው ነው አንቱዬ?" ስላቸው ወደኔ ዘወር አሉና "አንቺ ሴቲዮ ዝም በይ ብየሻለሁ ዝም በይ አንድ" አሉኝ በቃ ይሄ ነው አርባ ዓመት በትዳር ያቆየን ምስጢር ትዳር እንዴት ነው? ምን ትዳር ወስጥ ምን ችግር አጋጥሞት? በትዳር ደስተኛ ሆነዋል.!😂 https://t.me/Dialog_of_Idiology🙏
نمایش همه...

🥰 1😁 1
#እንዴት_ኃያል_መሆን_ይቻላል? • ተረጋጋ • አስተውል • ከጀርባህ ቀና በል • አይን እያየህ ተናገር • ከመናገርህ በፊት አስብ • ለጊዜህ ዋጋ ስጥ • አክብሮት አሳይ • እንቅስቃሴዎችህን በፀጥታ አድርግ https://t.me/Dialog_of_Idiology
نمایش همه...
👍 2