cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የቡራዩ ደ/ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ሰላም ሰንበት ት/ቤት

ይህ ገፅ የቡራዩ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት መልዕክቶችን ዘመኑ በሚፈቅደው መንገድ እንዲተላለፍበት በህዝብ ግንኙነት ክፍል የሚመራ ይፈዋዊ ገጽ ነው። 📞+251944247165 ሀሳብ አስተያየት ካሎት @finoteselam27 inbox አድራሻችን ነው።

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 188
مشترکین
+324 ساعت
-17 روز
+3030 روز
توزیع زمان ارسال

در حال بارگیری داده...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تجزیه و تحلیل انتشار
پست هابازدید ها
به اشتراک گذاشته شده
ديناميک بازديد ها
01
#ቀዳም_ሥዑር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት ዕለት ማግስት ያለው ቅዳሜ በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል ፩ ቀዳም ሥዑር ይባላል በዚህች ዕለት ከወትሮው  በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች እንጂ በዓል መሻርን አይመለከትም:: ይህች ዕለት እንደውም በጌታ ስቅለት የበለጠ ክብር ተሰጥቷታል ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ ይሄን ሲገልጹ    " ዓለም መፈጠር በፈጸመ ጊዜ በሰንበት ቀን እንዳረፈ አሁንም ከድካምና ከመከራ ዐረፈ ከአርብ ምሽት እስከ እሁድ ሌሊት በመቃብር ውስጥ ተኛ ቀድሞ ዓለምን ከመፍጠር በማረፍዐ አከበራት አሁን ደግሞ የዓለም መድኃኒት በሞቱ ቀደሳት ቀድሞ በጸጋው ባረካት አሁን በመስቀሉ አተማት " ብለዋል ፪ #ለምለም_ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡ ፫ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ ቀዳም ሥዑር ደስታም ኃዘንም የሚታስብባት ዕለት ናት በዕለተ አርብ ጌታ እኛን ለማዳን ሲል የተቀበላቸውን ሕማማተ መስቀል እያሰብን እናዝናለን በፈጸመልን ድህነት ደግሞ ንሴብሖ እያልን እናመስግነዋለን " ገብረ ሰላም በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ " በመስቀሉ ሰላምን አደረገ ትንሣኤውን ገለጠልን እየተባለ የምሥራች ቄጤማ እየታደለ ይዘመርባታል ወደ ከርሠ መቃብር መወረዱን እያሰብን እናዝናለን የነፍሳት ከሲኦል መወጣትን እያሰብን እንደሰትበታለን። | ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
822Loading...
02
ሥዐር ቅዳሜ
831Loading...
03
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 27) ---------- 45፤ ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ። 46፤ በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ። ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም። አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው። 47፤ በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው። ይህስ ኤልያስን ይጠራል አሉ። 48፤ ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠ፤ ሰፍነግም ይዞ ሆምጣጤ ሞላበት፥ በመቃም አድርጎ አጠጣው። 49፤ ሌሎቹ ግን። ተው፥ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደ ሆነ እንይ አሉ። 50፤ ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ። 51፤ እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤ 52፤ መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ
1891Loading...
04
በዓለ ስቅለት በግብፅ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ታዎድሮስ 2ኛ በተገኙበተት ተከብሯል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ከካህናትና ምእመናን ጋር በሥርዓቱ ተሳትፈዋል ። |ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
1801Loading...
05
የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት (የድኅነት ቀን) በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስ ፓትርያርኩ እና አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል። | ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
1610Loading...
06
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል ------------------------------------- 1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር) 2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ) 3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር(በምድር ላይ መውደቅ) 4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ) 5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም) 6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ) 8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት) 9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት) 10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር) 12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ(በመስቀል ላይ መሰቀል) 13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)            + + + + + + + ---------------------------- ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
1471Loading...
07
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል ----------------------------------- 1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር) 2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ) 3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር(በምድር ላይ መውደቅ) 4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ) 5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም) 6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ) 8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት) 9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት) 10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር) 12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ(በመስቀል ላይ መሰቀል) 13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)            + + + + + + + -------------------------------- |ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
20Loading...
08
Media files
1470Loading...
09
ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፳፩ : ፲፮ ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ ወኆለቊ ኲሎሙ አዕፅምትየ ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ (መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 21) ---------- 16፤ የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ። 17፤ አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም።
1261Loading...
10
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 22) ---------- አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም።ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ። ዐገቱኒ ከለቢት ብዙኃን ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 27) ---------- 15፤ በዚያም በዓል ሕዝቡ የወደዱትን አንድ እስረኛ ሊፈታላቸው ለገዢው ልማድ ነበረው። 16፤ በዚያን ጊዜም በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው። 17፤ እንግዲህ እነርሱ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ። በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤ 18፤ በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። 19፤ እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ። ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ ብላ ላከችበት። 20፤ የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ግን በርባንን እንዲለምኑ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፉ ሕዝቡን አባበሉ። 21፤ ገዢውም መልሶ። ከሁለቱ ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤ እነርሱም። በርባንን አሉ። 22፤ ጲላጦስ። ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው? አላቸው፤ ሁሉም። ይሰቀል አሉ። 23፤ ገዢውም። ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አለ፤ እነርሱ ግን። ይሰቀል እያሉ ጩኸት አበዙ። 24፤ ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውኃ አንሥቶ። እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ። 25፤ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው። ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን አሉ። 26፤ በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ። 27፤ በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ። 28፤ ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት፥ 29፤ ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው። የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ ዘበቱበት፤
1361Loading...
11
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 19) ---------- 14፤ ለፋሲካም የማዘጋጀት ቀን ነበረ፤ ስድስት ሰዓትም የሚያህል ነበረ፤ አይሁድንም። እነሆ ንጉሣችሁ አላቸው። 15፤ እነርሱ ግን። አስወግደው፥ አስወግደው፥ ስቀለው እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም። ንጉሣችሁን ልስቀለውን? አላቸው። የካህናት አለቆችም። ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም ብለው መለሱለት። 16፤ ስለዚህ በዚያን ጊዜ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጣቸው። 17፤ ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ። 18፤ በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ። 19፤ ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም። የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበረ። 20፤ ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር። 21፤ ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን። እርሱ። የአይሁድ ንጉስ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ አሉት። 22፤ ጲላጦስም። የጻፍሁትን ጽፌአለሁ ብሎ መለሰ። 23፤ ጭፍሮችም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ሆኖ በአራት ከፋፈሉት፤ እጀጠባቡን ደግሞ ወሰዱ። እጀ ጠባቡም ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ አልነበረም። 24፤ ስለዚህ እርስ በርሳቸው። ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ። ይህም። ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። 25፤ ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ። ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። 26፤ ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን። አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት። 27፤ ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን። እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት። 28፤ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ። ተጠማሁ አለ። 29፤ በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት። " ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።"
1421Loading...
12
#ዓርብ #የስቅለት_ዓርብ_ይባላል፦ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል። #መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡- ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል። ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ | ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
1671Loading...
13
#በግብረ_ሕማማት_ውስጥ_የሚገኙ_እንግዳ_ ቃላት_እና_ትርጉማቸው በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ #ኪርያላይሶን፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን»ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡ #ናይናን፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡ #እብኖዲ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው #ታኦስ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡ #ማስያስ፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው #ትስቡጣ፦ «ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው #አምነስቲቲ_ሙኪርያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡ #አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡ #አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡ ✍"ጸልዩ ከመ እግዚእ አምላክነ ይምሐረነ ወይሣሃለነ ወይትወከፍ ስእለተነ ወያፈጽመነ ዛተ ሰሙነ በደኅና ወበሰላም ወያርእየነ ብርሃነ ትንሣኤሁ በፍስሐ ወበሐሴት ወይስረይ ለነ ኃጣዉኢነ" ጌታችን አምላካችን ራርቶ ይቅር ይለን ዘንድ ልመናችንንም ተቀብሎ ይችን ሳምንት በደኅናና በሰላም ያስፈጽመን ዘንድ የትንሣኤውንም ብርሃን በፍጹም ደስታ ያሳየን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሰርይልን ዘንድ ጸልዩ" ✞በእንተ ጽንዐ ዛቲ(ግብረ ሕማማት ገፅ ፻፳፪) ----------------------------------- ኪርያላይሶን እብኖዲ ናይን ኪርያላይሶን ታኦስ  ናይን ኪርያላይሶን ማስያስ ናይን    ኪርያላይሶን ኢየሱስ ናይን ኪርያላይሶን ክርስቶስ ናይን ኪርያላይሶን አማኑኤል  ናይን ኪርያላይሶን ትስቡጣ  ናይን [በቀኝና በግራ በመቀባበል በል፡፡]                               "እንበለ ደዌ ወሕማም፣         እንበለ ጻማ ወድካም፣           አመ ከመ ዮም         ያብጽሐነ፤ያብጻሕክሙ     እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም፡፡"አሜን
1563Loading...
14

10Loading...
15
#ዓርብ #የስቅለት_ዓርብ_ይባላል፦ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል። #መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡- ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል። ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ #የቡራዩ_ደ/ሰ መድኃኔዓለም_ካቴድራል  ፍኖተ_ሰላም_ሰንበት_ትምህርት ቤት
20Loading...
16
የሰሙነ ሕማማት የጸሎተ ሐሙስ የድምጸ ፍኖተ ሰላም የራዲዮ መርሐግብር የሙከራ ሥርጭት ------------------------ ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
2003Loading...
17
#እኔ_እሆንን ???? -አላውቅህም ብየ በሰው ፊት የምክድህ ለጠላት አንስቸ አሳልፌ የምሰጥህ እኔ እሆንን ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? እኔ እሆንን አምላክ ሆይ እኔ እሆንን? --- -ይሁዳ ነኝ ወይስ ጴጥሮስ ሐሙስ ማታ እኔ ማን ነኝ ? የዛሬን መቆሜን እንጅ አላውቅም መጨረሻየን እወድሀለሁኝ ብየ የዛሬን እናገራለሁ አላውቅህም እንዳልልህ ስለነገ ግን እፈራለሁ --- -ስንት የአጥቢያ ኮከቦች ለአንተ ዘምረውልህ ወደቁ በሰማይ መቅደስ አጥነው በትእቢት ረግፈው አለቁ እፈራለሁ እኔም ለራሴ መንገዴን ንገረኝ ጌታ ጠዋት በዘመርኩበት አፍ እንዳልሳደብ በማታ --- -ሳጥናኤል መልአክ ነበረ ይሁዳም ሐዋርያ ንስጥሮስም ጳጳስ ነበር አርዮስም ባለሙያ እነዚህ ሁሉ ከወጡ ከአምላካቸው ጉያ ደካማ ለሆንኩትማ የት ይሆን የእኔ መገኛ? --- -ታናሹን ጅማሬ አንተው ታላቅም አድርግልኝ ነበረች ከመባል ፈተና አንተ በፍቅር አድነኝ ያስጀመርከኝ  አምላኬ ሆይ እንግዲህ መንገዴን አደራ በፊትህ ቆሜ ለማመስገን አብቃኝ ከቅዱሳን ጋራ _ ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ግጥም: ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
2294Loading...
18
ሐሙስ ማታ እኛ ማነን ?
2121Loading...
19
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 13) ---------- 13፤ እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ። 14፤ እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል። 15፤ እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።
2350Loading...
20
Media files
2210Loading...
21
Media files
2430Loading...
#ቀዳም_ሥዑር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት ዕለት ማግስት ያለው ቅዳሜ በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል ፩ ቀዳም ሥዑር ይባላል በዚህች ዕለት ከወትሮው  በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች እንጂ በዓል መሻርን አይመለከትም:: ይህች ዕለት እንደውም በጌታ ስቅለት የበለጠ ክብር ተሰጥቷታል ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ ይሄን ሲገልጹ    " ዓለም መፈጠር በፈጸመ ጊዜ በሰንበት ቀን እንዳረፈ አሁንም ከድካምና ከመከራ ዐረፈ ከአርብ ምሽት እስከ እሁድ ሌሊት በመቃብር ውስጥ ተኛ ቀድሞ ዓለምን ከመፍጠር በማረፍዐ አከበራት አሁን ደግሞ የዓለም መድኃኒት በሞቱ ቀደሳት ቀድሞ በጸጋው ባረካት አሁን በመስቀሉ አተማት " ብለዋል ፪ #ለምለም_ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡ ፫ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ ቀዳም ሥዑር ደስታም ኃዘንም የሚታስብባት ዕለት ናት በዕለተ አርብ ጌታ እኛን ለማዳን ሲል የተቀበላቸውን ሕማማተ መስቀል እያሰብን እናዝናለን በፈጸመልን ድህነት ደግሞ ንሴብሖ እያልን እናመስግነዋለን " ገብረ ሰላም በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ " በመስቀሉ ሰላምን አደረገ ትንሣኤውን ገለጠልን እየተባለ የምሥራች ቄጤማ እየታደለ ይዘመርባታል ወደ ከርሠ መቃብር መወረዱን እያሰብን እናዝናለን የነፍሳት ከሲኦል መወጣትን እያሰብን እንደሰትበታለን። | ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 27) ---------- 45፤ ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ። 46፤ በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ። ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም። አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው። 47፤ በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው። ይህስ ኤልያስን ይጠራል አሉ። 48፤ ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠ፤ ሰፍነግም ይዞ ሆምጣጤ ሞላበት፥ በመቃም አድርጎ አጠጣው። 49፤ ሌሎቹ ግን። ተው፥ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደ ሆነ እንይ አሉ። 50፤ ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ። 51፤ እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤ 52፤ መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ
نمایش همه...
🙏 6
በዓለ ስቅለት በግብፅ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ታዎድሮስ 2ኛ በተገኙበተት ተከብሯል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ከካህናትና ምእመናን ጋር በሥርዓቱ ተሳትፈዋል ። |ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
نمایش همه...
👍 1
የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት (የድኅነት ቀን) በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስ ፓትርያርኩ እና አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል። | ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
نمایش همه...
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል ------------------------------------- 1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር) 2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ) 3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር(በምድር ላይ መውደቅ) 4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ) 5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም) 6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ) 8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት) 9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት) 10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር) 12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ(በመስቀል ላይ መሰቀል) 13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)            + + + + + + + ---------------------------- ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
نمایش همه...
👍 2😢 2