cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ከንባቤ ለቅምሻ

"በቀን ብዙ ሚሊየኖች ከሚያገኙ ሰዎች ይልቅ በቀን አንድ መፃፍ በሚያነቡት እቀናለው" ኑ በማንበብ ባዶነታችን እንሙላ!!! በሳምንት ሁለት ቀን በጣም ያልረዘሙ ታሪኮችን እናካፍላለን። ሌሎቹን ቀናት ደሞ አጫጭር ጥቅሶችን Share እንደራረጋለን። ለማንኛውም አስተያየት እንዲሁም ፁፎችን ለማካፈል @jer21

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
536
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

"ለጠላቶችክ ደስታ ብለክ ሳይሆን መሸነፍክ ለሚያስከፋቸው ሰዎች ብለክ ጠንካራ ሁን" ዛሬ ውስጥህ ሰላም አጥቶ መኖር አስጠልቶካል? ተስፋ እንዳትቆርጥ ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ሰዎች ከሰው ክብር ዝቅ አርገውክ በሚጠሉክ ሰዎች ተከበሀል? የሚወዱክ ይመጣሉ፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ስንት የደከምክበት ቢዝነስ ብልሽትሽቱ ወጥቷል? ቀና በልና አማራጮችን ተመልከት፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ በትዕምርትህ የተዘጋጀከውንና የደከምክበትን ያህል ውጤት አላመጣህም? ትምርት በቃኝ እንዳትል፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። የተሸነፍከው የወደክ ፣ የተሰበርክ ቀን አይደለም። የተሸነፍከው በወደክበት ለመቅረት አምነክ የተቀመጥክና ዳግም መሞከር ያቆምክ ዕለት ነው። በል ተነስ የእኔ አንበሳ፤ ይቺ ምድር ለተሸናፊ ቦታ የላትምና "ለችግሮችህ በሙሉ ትልቅ ችግር ሁንባቸው።" 🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌 @Kezimkezia
نمایش همه...
🙌
💪
እውነተኛ ታሪክ! ታሪኩን ያካፈለን ኮከብ አሳየ! 🧣"ድንግል አይደለሽም!"🧣የመጨረሻ ክፍል ታህሳስ ወር 1994 ዓ.ም አዲስ አበባ ትዕግስት ከዚህ በኃላ ቃሉን ያላከበረውን የአድማሱን ፈተና መቆጣጠር የቻለች አልመሰለችም። በአንድ አልጋ ላይ የተንጋለሉት ጥንዶች ወሲብ ፈፀሙ። በመካከል ላይ ግን ያልታሰበውና ዛሬም ድረስ አድማሱን ለፀፀት የዳረገው ችግር ተፈጠረ "ትዕግስት ልጃገረድ አይደለችም"ይላል አድማሱ "ይህን እንደተረዳው ወሲብ መፈፀሜን አቁሜ አናገርኳት እሷ ግን ከዚ ቀደም ሌላ ወንድ እንደማታውቅ ደጋግማ ገለፀችልኝ። ተበሳጨው። ይህቺ ልጅ እንዴት እንዲህ ታጭበረብረኛለች ብዬ አሰብኩ ከዚህ ቀደም እንዲህ ገንዘቤን ፈልገው ያታለሉኝ ሴቶች ታወሱኝ። ሌላ ወንድ እንደማታውቅ ደጋግማ ብትነግረኝም ንዴቴን መቆጣጠር ስላልቻልኩ ሰደብኳት። በዚህ ሳቢያ እኔን ደብቃኝ እንጂ ሌላ የወንድ ጓደኛ እንዳላት አሰብኩ። እሷ ግን 'ካልፈለከኝ ልትተወኝ ትችላለህ።እኔ ላንተ አላንስህም እበዛብህ ይሆናል እንጂ' አለችኝ። በዚህ ንግግሯ ብስጭቴ ጨመረና ሳላስበው ስህተት ፈፀምኩ" ብሏል ሁኔታውን ሲተርክ። በንግግራቸው መሃል አድማሱ ትዕግስትን በጀርባዋ በተንጋለለችበት አንገቷን አነቃት። ተንፈራገጠች። ጭንቅ ሲይዛት በጥፍሮቿ ቧጠጠችው።ይሄኔ ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ በትራሱ አፈናት። "የኔ መሆን ካልቻልሽ የማንም አትሆኚም ብሎ ትንፋሿ እስኳረጥ ድረስ አየር አሳጣት። በመጨረሻ ሲጋልበው ከነበረው ንዴትና ከቅናት መንፈስ ሲባንን ትዕግስት እስከወዳኛው አሸልባ ነበር ያገኛት። "በጣም ደነገጥኩ።የሆነውን ሁሉ ያወኩት እሷ መሞቷን ካየው በኃላ ነው። በጣም ፈራሁ" ይላል። ወድያው የትዕግስትን አስክሬን አልጋው ላይ እንደ ተጋደመ ትቶ በሩን ከፍቶ ውጪውን አየ። በአካባቢው ማንም የለም። ወደ ውስጥ ተመለሰና ልብሱን ለባብሶ በፍጥነት ከዚያ ክፍል ሾልኮ ወጣ። ይህንን ሲያደርግ የታየ ባይመስለውም ግን ከአንድ አይን አላመለጠም። የፅዳት ሠራተኛዋ። ይህቺ ፅዳት ሰራተኛ የጎልማሳውን ነገረ ስራ አልወደደችውም። ከሴት ጋር ገብቶ እየተገለማመጠ ብቻውን የወጣውን ሰው ተጠራጠረችው። ወድያው ፈጠን ብላ ገርበብ ወዳለው ክፍል መጣችና በተከፈተው በር ወደ ውስጥ አጮልቃ አየች። አልጋው ላይ በጀርባው የተዘረረችውና የማትንቀሳቀሰው ወጣት አይኗ ገባች። ደነገጠች። በጩኸት ግቢውን አናጋችው። ሰው ተሰበሰበ። የሆነውን ከሰሙት ሰዎች መካከል በርከት ያሉ ሰዎች አድማሱን ፍለጋ በየአቅጣጫው ተበታተኑ። ፍለጋው አድካሚ አልነበረም። አድማሱ እነደ ንፁ ሰው ተዝናንቶ ታክሲ ሲጠብቅ ከአካባቢው ሳይርቅ ተያዘ። በነዚህ ሰዎች እጅ የገባው አድማሱ ሰውነቱ ወባ እንደያዘው ሰው ይንቀጠቀጣል። ፖሊስ በተደረገለት ጥቆማ በአካባቢው ደርሶ ጉዳዩን ካጣራ በኃላ የትዕግስት አስክሬኗን ለምርመራ ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ፣ አድማሱን ደግሞ ለጥያቄ ወደ ጣብያ ወሰዳቸው። አንድ ላይ የመጡት ጥንዶች በህይወትና በሞት በተለያየ አቅጣጫ ተጓዙ። አድማሱ በተጠየቀ ቁጥር "የቅናት ሰይጣን ነው እንዲህ ያረገኝ" እያለ ብቻውን ያለቅሳል። ምርመራው በራሱ እምነትና በማስረጃ ተጣራ። ወደ ማረምያ ቤት ወረደ። ለረጅም ግዜ አብሯት ለመኖር ሲያልማት የነበረችውን ወጣት ሊቆጣጠረው ባልቻለው የቅናት መንፈስ ተነድቶ ገደላት። ፖሊስ ምርመራውን በሚያደርግበት ጊዜ ከዚህ ቀደም አድማሱ ትምህርት ቤቷ ደጃፍ አግኝቷት ያናገራት የሟቿን ጓደኛ አግኝቶ ጠይቋታል። በዚህም ዕለት አድማሱ 'ሲሸኛት አይቼዋለሁና ፍቅረኛዋ ነው" ያለው ወጣት የክፍል ጓደኛቸው መሆኑን ብቻ ነበር ያቺ ልጅ የመሰከረችው። አድማሱ ግን "ልጁ የትዕግስት እጮኛ ነው። ክብረ-ንፅህናዋንም የገሰሰው እሱ ነው።" ብሎ ነበር ያመነው። ይህ ያልተረጋገጠ ዕምነቱ ለእርሱ የጠቀመው ነገር የለም። ፍቅሩን ማጣቱ ብቻ ሳይሆን የወደፊት ህይወቱንም አደጋ ላይ ጣለበት እንጂ። ያቺ እናቷ እንደ አይናቸው ብሌን በስስት የሚጠብቋት የቤተሰቡ ተስፋ የሆነች ወጣትም በማይታመን አጋጣሚ በድንገት ህይወቷ ተነጥቆ እንደወጣች ቀርታለች። አድማሱ "ድንግልአይደለሽም!!" በሚል ቃል ከዚህች ንፁህ ልጅ ጋር ለራሱም ሰላማዊ ህይወት ጋር የነበረውን ሰንሰለት በጥሷል። *ተፈፀመ* ✍ከታሪኩ ብዙ እንደተማራችሁ እምነቴ ነው፡፡ በሌላ ታሪክ እስክንገናኝ ቸር እንሰንብት🙏 @kemtsahft
نمایش همه...
👍16
👎5
Comments(1)
Repost
እውነተኛ ታሪክ! ታሪኩን ያካፈለን ኮከብ አሳየ! 🧣"ድንግል አይደለሽም!"🧣 ክፍል5 ታህሳስ ወር 1994 ዓ.ም አዲስ አበባ መስከረም የ11ኛ ክፍል ውጤቷ ወደ ቀጣዩ ክፍል ያሸጋገራት ትዕግስት ዛሬ የ12ኛ ክፍል ትምህርቷን አሀዱ የምትልበት ወር ላይ ደርሳለች።የአድማሱ ተስፍ በዚያው መጠን አብቧል።ይህቺ ዓመት ለርሱ የብ ቸኝነት ኑሮ የመጨረሻ ናት። ተለያይቶ መኖር ያከትማል። ሁለቱ እንደ ዕቅዳቸው ደግሞ ቀለበት ያስራሉ። ያኔ እስከ ወዳኛው ድረስ አብረው ይዘልቃሉ አድማሱ የትምህርት ቤት ወጪዋንና ለትምህርቷ የሚያስፈልጋትን ማንኛውንም ነገር አሟልቶላታል ወጪዋን ከመሸፈን ባሻገር አዳዲስ ልብስ የምትገዛበትን ገንዘብም ሰጥቷታል። መውደዱን የሚገልፀው ለርሷ በሚውልላት ውለታ መጠን መሆኑን ደግሞ የዚህ ወጣት ሌላኛው ባህሪው ነው። ከእናቷ ጋር በጉዳዩ ላይ የተግባባችው ትዕግስት አሁን የእናቷን መሃረብ በጥቂት ብሮች መደጎም ጀምራለች። የትምህርት ዘመኑ ገና ከመጀመሩ የአድማሱን ስሜት የሚፈታተን ነገር ተፈጠረ። ትዕግስት ት/ቤቷ ውስጥ ከአንድ ልጅ ጋር በተደጋጋሚ እንደምትታይና እንደውም ልጁ የረጅም ጊዜ ጓደኛዋ መሆኑ ተወራለት።ይህንን ወሬ የሰማው አድማሱ ወዲያው ትዕግስትን ሊጠይቃት ቢያስብም ጉዳዩን የነገረው ጓደኛው ግን እንዲታገስና ነገሩን በራሱ ዐይን እንዲያጣራ ነገረው። በማግስቱ ከት/ቤት ስትወጣ ራሱ ተከታትሎ ሊደርስባት አሰበ። እናም የመለቀቅያ ሰዓቷን ጠብቆ ወደ ትምህርት ቤቷ ሄደ። አብሮት ከነበረው ጓደኛው ጋር ሆኖ በርቀት ጠበቃት። ትዕግስትና ሌላ አንዲት ሴት እንዲሁም አንድ ወንድ ሆነው ከት/ቤት ግቢ ሲወጡ አያቸው። ወንድየው የትዕግስትን ክንድ ያዝ አድርጓል። ሶስቱም ቆመው ጥቂት አወሩና እነትዕግስት አብራቸው ያለችውን ልጅ ተሰናበቷት። ከዚያም ጥቂት ፈንጠር ብለው መጓዝ ሲጀምሩ ለብቻዋ ወደ ቤቷ ምትሄደውን ልጅ በአጠገባቸው እስክታልፍ ጠብቆ ሊያናግራት ወሰነ። መጣች። አልፋው ልትሄድ ስትል ከተል ብሎ አናገራት። "ትዕግስት ከማን ጋር ነው ወደ ቤቷ የምትሄደው?" ብሎ ሲጠይቃት ልጅቷ መልስ ከመስጠቷ በፊት አመነታች። ጓደኛው ቀበል አድርጎ ጠየቃት። "ይህ ልጅ የእውነት ወንድሟ ነው?"ብሎ ጠየቃት። ልጅቷ ራሷን ነቀነቀች። "ወንድሟ አይደለም ጓደኛዋ ነው" አለችው። "ጓደኛዋ ነው ስትይ ቦይፍሬንዷ ነው??" አላት። ልጅቷ "አላውቅም ራሷን ጠይቃት" ብላው ተቻኩላ ሄደች። አድማሱ ራሱ ተበጠበጠ። ቅናት መላው ሰውነቱን ሲወረው ተሰማው። ትዕግስትን ተከታተሏት። ከልጁ ጋር እየተላፋች እየተቃቀፈች ጥቂት መንገድ ከተጓዙ በኃላ ቆመው ብዙ አወሩ። ልጁ በመጨረሻ አቅፎ ጉንጯን ሳም አደረጋትና በአንድ መገንጠያ ወደሌላ ቦታ አመራ። አድማሱ ትዕግስትን ተከትሎ ሊያናግራት ሞክሮ እንደነበር ይናገራል። ጓደኛው አስቀረው። "በኃላ አንተ ጋር ስትመጣ ዝም ብለህ አወጣጣት። የምትዋሽክ ከሆነ ችግር አለ ማለት ነው።" ብሎት በታክሲ ወደ ወፍጮ ቤታቸው አመሩ። ቀድመዋትም ደረሱ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ትዕግስት መጣች። አድማሱ ተበሳጭቷል። እንዳያስታውቅበት ግን ተጠንቅቆ ሥራ የበዛበት መሰለ። በዘዴ ጠየቃት። "ከት/ቤት ሁሌ ብቻሽን ነው ምመጪው?" ብሎ። ትዕግስት ሳታመነታ"ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ጥቂት መንገድ እንመጣና ከዚያ እሷ ወደ ቤቷ ትሄዳለች እኔ ግን ብቻዬን እዚህ ድረስ እመጣለሁ።" አለችው። "ቦይፍሬንድሽ አብሮሽ ይመጣ የለ?"አለ። የተናገረው ፍፁም ውሸት መሆኑንና የወንድ ጓደኛ የሌላት መሆኑን ገለፀችለት። በዚህ ወቅት ተበሳጭቶ ያየውን ሁሉ ነገራት። ለመጀመርያ ጊዜ ተጣሉ። አኮረፋት። ውሸታም ልጅ መሆኗን እንደማያውቅና እንዳዘነባት ገለፀላት። ከዚህ ቀደም ሌላ ወንድ አላውቅም ያለችው የውሸት ጭምር መሆኑን። እሷ ግን በአቋሟ ፀንታለች። ለጥቂት ቀናት ተኮራረፉ። ስትመጣ ብዙም ደስ በሚል ስሜት አያናግራትም። ኃላ ላይ አቋሟን ሊፈትሽ ፈለገና የግድ በስራ ቀን ወይም እሁድ አንዱን ዕለት መገናኘት እንዳለባቸው አጥብቆ ጠየቃት። አሁን እንቢ ልትለው አልቻለችም። በመስከረም ወር የመጨረሻው እሁድ ዕለት ሊገናኙ ቀጠሮ ሰጠችው። መስከረም 29 ቀን 1995 ዓ.ም አሁድ ዕለት "ጥናት አለብኝ"ብላ ደብተር ይዛ ወጣች። ከቀኑ በ7 ሰዓት ከአድማሱ ጋር ተገናኙ። ታክሲ ይዘው ወደ ኮተቤ መናፈሻ መስመር አቀኑ። ሲደርሱ የሺሃረግ ምግብ ቤት የሚባል አነስተኛ ሆቴል ውስጥ ገቡ። ምሳ የበሉት እዚያው ነበር። አድማሱ በጣም እንደሚወዳትና እንደሚያፈቅራት ከርሷ ውጪ ሌላ የማግባት ሃሳብ እንደሌለውና ነገር ግን የምታደርገውን ነገር ስላየ እሷን ሊያምናት እንዳማይችል ገለፀላት። "በድጋሚ ሌላ ወንድ የማታውቅ መሆኑን በመሃላ አረጋገጠችልኝ።" ይላል። ልጁ የት/ቤት ጓደኛዋ ብቻ መሆኑን ጭምር ገለፀችለት። በዚያ ሬስቶራንት ውስጥ ብዙ ተቀመጡ። ከዚያም አድማሱ አግባብቶ አባብሎ ቁጭ ብለው ለመጫወት እንዲመቻቸው መኝታ ክፍል እንዲይዙ ጠየቃት። ብዙ አንገራገረች። ከፍቃዷ ውጪ ምንም እንደማያደርግ ቃል ገብቶላትና አባ ብሏት በመጨረሻም ለውትወታው ተሸነፈች። ይዟት ገባ 40 ብር ወደከፈለበት አነስተኛ ቤርጎ። *ይቀጥላል............... @kemtsahft
نمایش همه...
እውነተኛ ታሪክ! ታሪኩን ያካፈለን ኮከብ አሳየ! 🧣"ድንግል አይደለሽም!"🧣 ክፍል4 ታህሳስ ወር 1994 ዓ.ም አዲስ አበባ ዓመቱ እየተገባደደ ነው። አድማሱ ከዚህች ልጅ ጋር በቀለበት ጥምረቱን ማወጅ ፈልጎዋል። ትዕግስት ደግሞ 'ትምህርቴን ልጨርስ' ብለዋለች። ከሥራ ውጪ ባላቸው ጥቂት የእረፍት ቀን ወጣ ብለው እንዲዝናኑ በተደጋጋሚ ጊዜ ቢጠይቃትም 'ቤት ይጠረጥሩኛል' በማለት ፈፅሞ ፍቃደኛ ልትሆንለት አልቻለችም። እሱ በበኩሉ ፍቅሩ እየጠናበትና ሳያያት ማደር እየተሳነው መጥቷል። ከዚህ ቀደም የነበረው ባህሪ ሁሉ ተቀየረ። ቀልድ፣ ሳቅ፣ ጨዋታ ፈፅሞ የሚነካካው ልጅ አልሆነም። ጉዳዩ ሁሉ ከትዕግስት ጋር ሆኗል። በለበሰች ቁጥር ውበቷ የሚጨምረው፤ በተዋበች ቁጥር በየቀኑ ለርሱ አዲስ ምትሆንበት ትዕግስት የዛሬ ስሜቷን በውል ሊያውቀው አልቻለውም። እንደምትወደው ትነግረዋለች። ግን ለብቻው ልታገኘው አትፈልግም፤ ቀጠሮ ሲሰጣት ሌላ ጊዜ እንደርስበታለን ትለዋለች። ይህ ደግሞ "ከዚህ ቀደም ሌላ ወንድ በዚህ መልኩ ስለማታውቅ ይሆናል"ብሎ እንዲያስብ አድርጎታል። ስለዚህ በልጅቷ "የቤት ልጅ መሆን" ይደሰታል እንጂ አይከፋም።ታግሶ እየጠበቃት ነው። ብዙ እየቆየ ሲመጣ ግን አንድ ዕቅድ አወጣ ወፍጮ ቤት በወር አንድ ጊዜ የገብርኤል ዕለት ሥራ አይሠራም። ይህ ቀን የእረፍት ቀኑ ስለሆነ ውጪ ተገናኝቶ ሻይ ቡና ሊላት ፈለገ። ይህንን ዕቅዱን ነገራት። ከፊት ለፊት የሚመጣው ሰኔ 19 ቀን ሊያገኛት እንደሚፈልግም ጭምር። ትዕግስት ፈራ ተባ እያለች እንደምታስብበት ገለፀችለት። በዕለቱ የጠዋት ፈረቃ ተማሪ ስለነበረች የከሰዓት በኃላውን ጊዜ ጥናት እንዳለባት ተናግራ ከርሱ ጋር ልትገናኝ ተስማሙ። የቀጠረችው መገናኛ አካባቢ ያለ አንድ ካፌ ውስጥ ነው። ያቺ ቀን እስክት ደርስ ድረስ በምጥ ያለፈው አድማሱ በሁለቱ የ9 ወር ግንኙነት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ውጪ ሊያገኛት የጠራትን ፍቅረኛውን ለማየት ቸኩሏል። ዕለቱ ደረሰ። አድማሱ "ሽክ ያደርገኛል" ያለውን ሙሉ ልብስ ለብሶ ወደ ቀጠሮው ቦታ ሄደ። ትዕግስት በዚያን ዕለት ከት/ቤት ከተለቀቀች በኃላ ወደ የቤታቸው ሄደው እስኪያልቁ ድረስ ጊቢ ቆየችና ወደ ቀጠሮዋ ቦታ መጣች። እንደተገናኙ እየተሳቀቀች ካሉበት ሰፈር ሌላ ቦታ እንዲሄዱ ጠየቀችው። በርግጥ እሱም ከኮተቤ ውጪ ብዙ መዝናኛ ስፍራ አያውቅምና በታክሲ ወደ 22 አካ ባቢ ይዟት መጣ። ከታክሲ ሲወርዱ የገጠመው አድዋ ሆቴል ነበር። ገብተው ምሳ በሉ። ሰወር ያለ ቦታ ተቀምጠው ስለነበር ሰው ያየናል የሚል ስጋት አልነበራቸውም። በዚች ዕለት አድማሱ ከልቡ ተደሰተ። አወራት፤ አቀፋት፤ ሳማት። እሷም እንደምትወደው ገለፀችለት። ወደፊትም አብረው እንደሚኖሩ ተነጋገሩ። እስከዚያው ግን ታግሶ እንደሚጠብቃት ቃል ገባላት። ትምህርቷን ከ አንድ ዓመት በኃላ ትጨርሳለችና ሩቅ የሚባል ጊዜ አይደለም። ለርሷ ያለው ፍቅር አቅሉን ሊያስተው ደርሷል። ያለፈ ህይወቱን እንደቀልድ ጠየቀችው። ከዚህ ቀደም አንድ ሁለት ፍቅረኞች እንደነበሩት አልሸሸጋትም። ከሁለቱም ጋር ግን በማይረባ ምክንያት መለያየቱን ገለፀላት። እነዚህ ሴቶች እሱን ሳይሆን ገንዘቡን ፈልገው መጡ፤ ከዚያም አሰናበታቸው፤ በቃ ይህ ነበር ያለፈ ታሪኩ። በርሷ በኩል ግን እሱ እንዳለው በድጋሚ 'ከዚህ ቀደም ምንም ወንድ እንደማታውቅ' ገልፃለታለች። *ይቀጥላል........... @kemtsahft
نمایش همه...
እውነተኛ ታሪክ! ታሪኩን ያካፈለን ኮከብ አሳየ! 🧣"ድንግል አይደለሽም!"🧣 ክፍል3 ታህሳስ ወር 1994 ዓ.ም አዲስ አበባ ትዕግስት ድንገት በጀመራት ብርድ ብርድ በሚል የህመም ስሜት ሳቢያ ሳይታወቅ ለሳምንት ያህል አልጋ ላይ ስትውል አድማሱ መታመሟን በመስማቱ ተጨነቀ። ወደ ቤቷ ሄዶ ሊጠይቃት ቢፈልግም በአካባቢው በሚያውቁት ደንበኞቹ ዘንድ ጥርጣሬ እንዳይፈጥርበት በመስጋት አጣብቂኝ ውስጥ ገባ። በመጨረሻ ላይ ግን ማድረግ እንዳለበት ስለወሰነ ከአንድ ጓደኛው ጋር ተያይዞ ወደነትዕግስት ቤት ሄደ። እናቷ ጠላ እየሸጡ አገኛቸው። ትዕግስት የተኛችበት አልጋ ያለው እዚያቹ ባለ አንድ ክፍሏ ቤት ውስጥ ነው። በድህነት ጥላ ስር ያለውን የዚህን ቤተሰብ ህይወት አይቶ አዘነ። ቀስ ብሎ ደንበኞች ወጣ ወጣ ማለት ሲጀምሩ ለእናትየው 200 ብር ሰጥቷቸው "አሳክሟት" ብሏቸው ወጣ። የትዕግስት እናት ያላሰቡት ነገር በመሆኑ ተደናግጠዋል። ልጅቷ ሳምንት ሙሉ ወደ ህክምና ያልሄደችው በገንዘብ እጦት ነው። አሁን ይህን ልጅ የሚያመሰግኑበት አፍ ጠፋባቸው። ይህንኑ ጉዳይ ማታ አባት ሲመጡም ነግረዋቸዋል። ትዕግስት የዚህ ወጣት ውለታ እየበዛበት መጣ። ወደፊት አብረው በትዳር እንዲጠቃለሉ እንደሚፈልግ ነግሯታል። የልጁን ማንነት በቅርበት እያየችው ቢሆንም በኃላ ላይ ህይወቷን እንዳያበላሽባት ሰግታለች። "በተለያየ ጊዜ ስላለፈ ህይወቷ ጠይ ቄያት "ልጃገረድ" እንደሆነች አስረግጣ ነግራኛለች ይህንን ቃሏን ሰምቼም ታግሼ ለመቆየት ወስኜ የወሲብ ጥያቄ ሳላቀርብላት ቆይቻለሁ።" ይላል አድማሱ። ለትዕግስት ይህ ወጣት ልዩ የሆነ ባህሪ ያለው ሰው ነው። ያከብራታል፤ ይወዳታል፤ ያስብላታል ይረዳታል። እናትየው በርግጥ ይህን ገንዘብ ያገኘችው ከዚህ ወጣት መሆኑን ቢያውቁም አባቷ እንዲሰሙ ግን አይፈልጉም። ልጅቷንም "ተጠንቀቂ" ይሏታል። እንደውም በአንድ ወቅት ታላቅ ወንድሟ እንዲሰልላት መድበውት ነበር። ወንድሟ ትዕግስትን 'እዚህ ወፍጮ ቤት አስሬ ምን ያመላልስሻል!' ብሎ ስላስጠነቀቃት ቤተሰብ ጉዳዩን እንዳወቀ አስባ ፈርታለች። እግሯንም ሰብሰብ አድርጋለች። ቀስ በቀስ የሁለቱ ወጣቶች ግንኙነት ቀን በቀን መሆኑ እየቀነሰ መጣ። ይህ አጣብቂኝ ደግሞ በአድማሱ ውስጥ የፈጠረበት ስሜት ጥሩ አልነበረም። *ይቀጥላል................
نمایش همه...
እውነተኛ ታሪክ! ታሪኩን ያካፈለን ኮከብ አሳየ! 🧣"ድንግል አይደለሽም!"🧣 ክፍል2 ታህሳስ ወር 1994 ዓ.ም አዲስ አበባ አድማሱ የዚህችን ልጅ ዐይን አፋርነት ይወደዋል። ውበቷን ያደንቀዋል። ዝምታዋን በልቡ ከትቦታል። ዐይኑን ጣለባት። የቀይ ዳማ፣ ባለጥቁር ፀጉርና ጎላ ጎላ ያሉ ዐይኖች ያሏት ትዕግስት እዚህ ወፍጮ ቤት በመጣች ቁጥር ይህ ልጅ በጫወታ ይይዛት ጀመር። በአካባቢው ከሚገኝ መዝናኛ ክበብ ሻይ ወይም ወተት ያስመጣላታል። ወሬው ያስቃታል። እህል አስመዝና ወደ ወፍጮ ቤት ይዛ እንድትገባ አይፈልግም። ሁሉንም በነፃ ይሰራላታል። የሚዛን፣ የወፍጮ የሚባል ክፍያ አያስከፍላትም። በዚህ ላይ እህሉን እራሷ ነፍታ ማስፈጨት ሲገባት ከዚህ ሥራ ገላግሏታል። ከአስፈጪዎች አንዱን ጠርቶ ገንዘቡን ራሱ ከፍሎ ጣጣውን ይጨርስላታል። እሱ የሚፈልገው ልጅቷ አጠገቡ ተቀምጣ እንድት ጫወት፤ ሲያወራላት እንድትስቅ ብቻ ነው። ስትስቅ ደስ ትለዋለች። ዲምፕሏን ማየት ይናፍቃል። እናቷ ጠላ እየጠመቁ ይሸጣሉና የጠላ እህል ለማስፈጨት በየጊዜው ወደ ወፍጮ ቤት መመላለሷ ጨምሯል። ከዚህ በፊት ጤፍና ስንዴ ለማስፈጨት ብቻ እንጂ ለሌላ ጉዳይ መጥታ አታውቅም። አሁን ግን የጠላ እህል ለማስፈጨት በየጊዜው የምትመላለሰው እሷ ሆናለች። ወራት ክንፍ አውጥተው በበረሩ መጠን የትዕግስትና የአድማሱ ቅርርብ የዚያኑ ያህል እየበረታ መጣ። ፍቅር ቀስ በቀስ ከአድማሱ ተርፎ የሷንም ደጅ ያንኳኳ ጀመር። ከዚ በኃላ ትዕግስት ወደዚህ ቤት ለመምጣት ወፍጮ ቤት መላክ አለመላኳ ብቻ መጠበቅ አልቻለችም። ከትምህርት ቤት ስትመለስ በቀጥታ ጎራ የምትለው አድማሱ ጋር ነው። አውርተው ተጫውተው የልባቸውን ተነጋግረው ይለያያሉ። አድማሱ ከዚያች ወንበር ላይ ለአፍታ መነሳት አይችልም። ደንበኞቹ ሁሌም ብቅ ጥልቅ ስለሚሉ ከእርሱ ሌላ ሂሳብ የሚቀበላቸውና የሚያስተናግዳቸው ሰው የለም። ከጎኑ ተቀምጣ እየሰራ ሲያጫውታት ደስ ይላታል። ልጁ ከፍቅሩ ባሻገር የተለያየ ነገር ያደርግላታል። የቤተሰቧን ምስኪንነት ፣የቤታቸውን የድህነት ታሪክ አሳምሮ ያውቃል። ጠላ ሽጠው የሚተዳደሩ እናት በአንድ ፋብሪካ ውስጥ በዘበኝነት የሚሰሩ አባት ለዚህች የ11ኛ ክፍል ተማሪ ፍላጎት ማሟያ ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር የላቸውም። የት/ቤት ክፍያዎችን፣ አንዳንድ ወጪዎችን አልፎ አልፎም ፀጉር መሠሪያ እና ጫማ መግዣ ብር ከአድማሱ ማግኘት ጀምራለች። ልጁ የተማረው እስከ አምስተኛ ክፍል ቢሆንም የርሷ ተምሮ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ መድረስ ሁሌም ቢሆን የሚመኘው ነገር ነው። ስለሆነም በየወቅቱ ከትምህርቷ ጋር በተያያዘ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ያደርግላታል። ወፍጮ ቤት ውስጥ የተጀመረው ትውውቅ ቀስ እያለ ወደ ጠንካራ ፍቅርና መተሳሰብ አመራ። ትዕግስት ወደዚህ ወፍጮ ቤት ብቅ ጥልቅ ማለቷ ለጎረቤት ዓይን አጋለጣት። አድማሱ ከሴት ጋር መጫወቱ፣ መቃለዱ፣ ማውራቱ አንዳንዴም ለነርሱ ቅናሽ ማድረጉ 'ሴት ይወዳል' የሚል ስም አሰጥቶታል። የአካባቢው ሰው አድማሱን የሚያውቀው በዚሁ ስሜት ነው። የትዕግስትን በዚህ ልጅ መውደቅ ያየ ጎረቤት ነገሩን ቸል ማለት የፈለገ አልመሰለም። ብዙ የቤት ሰራተኞችም ይሁኑ ወጣት ሴቶች ከእርሱ ጋር መጫወት ደስ ይላቸዋል። ደግነቱ ለሰው አዛኝነቱን ደግሞ ሌላ የሚወደድለት ነገሩ ነው። ትዕግስት ከእርሱ ጋር መቀራረቧን ግንኙነትታቸውን ከሌሎች ለየት ማለቱን ያዩ ሁሉ የሚነግሯትና የሚያስጠነቅቋት ይህንኑ የእሱ ባህሪ ቢሆንም ብዙ ቦታ አልሰጠችውም። በዚህ ሁኔታ የሁለቱ ጥንዶች ግንኙነት 6 ወር አስቆጠረ። በብዝዎች ዘንድ አድማሱና ትዕግስት ያላቸው ቅርርብ በደንብ የተረጋገጠው ግን በአንድ ወቅት ታማ ሊጠይቃት ወደ ቤቷ በሄደበት ጊዜ ነው። *ይቀጥላል...................
نمایش همه...
እውነተኛ ታሪክ! ታሪኩን ያካፈለን ኮከብ አሳየ! 🧣"ድንግል አይደለሽም!"🧣 ክፍል1 ታህሳስ ወር 1994 ዓ.ም አዲስ አበባ ከቀበሌው ፅ/ቤት ጥቂት ዝቅ ብሎ የሚገኘው ወፍጮ ቤት ከማለዳ ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ጥርሱ የገባውን እህል ሁሉ ያለማቋረጥ እያደቀቀ እምምም የሚል ድምፁን ያሰማል። አፍ የገባውን የእህል ዘር ሁሉ ዱቄት እያደረገ ያወጣዋል። እዚህ ቤት ውስጥ የሚሰሩትን ሁሉ ያለ ዕድሜያቸው ሸበቱ የሚያስመስላቸው የዱቄት ብናኝ ከዐይን ሽፋሽፍቶቻቸው እስከ ፂምና ፀጉራቸው ድረስ በነጭ ቀለም አጥለቅልቋቸዋል። አንዱ በወንፊት ሌላው በማራገቢያ ፍሬ ከገለባ ለመለየት ሲወዛወዝ ያቺ ጠባብ ወፍጮ ቤት ቀውጢ ትሆናለች። ጤፍ፣ ስንዴ፣ ማሽላ፣ በቆሎ ከወፍጮ ቤቱ ፈንጠር ብላ በተሰራች ሚዛን ቤት እስከ አፉ ሞልተውታል። ከሚዛኑ ጀርባ ተቀምጦ በሌባ ጣቱና በአውራ ጣቱ ወደግራና ቀኝ የሚለጋው የኪሎ መስፈርያ ላይ ዓይኑን የተከለ አንድ ወጣት የዚህ ቤት ነጋዴ ነው። የወፍጮ ቤቱ ባለቤት የሩቅ ዘመዱ ቢሆንም ቤቱን ልክ እንደራሱ ንብረት ነው የሚቆጥረው። ሚዛን ቤት ውስጥ ያለውን እህልና ጥራጥሬ በሙሉ የሚሸጠው እሱ ነው። ራሱን "እህል ነጋዴ"ብሎ ይጠራል። ከክፍለሀገር እያስጫነ የሚያስመጣው እህል በየሳምንቱ በሸማቾች ይሟጠጥለታል። ሰዎች እዚያው ገዝተው እዚያው አስፈጭተው ወደ ቤታቸው መሄድ ስለሚችሉ ለቅርበቱም ለቅለቱም ይህን ቤት በደንበኝነት ይዘውታል። አድማሱ ማሞ በ34 ዓመት ዕድሜው ኪሱ ደለብ ያለ ባለገንዘብ ጎልማሳ ነው። እዚህ ወፍጮ ቤት ውስጥ እህልና ጥራጥሬ ለሚሸጥበት ሥፍራ የቦታ ኪራይ ይከፍላል። ዘመዱ የሆኑት የወፍጮ ቤቱ ባለቤት ደግሞ የአድማሱ ደንበኞች እዚያው ገዝተው እዚያው የሚያስፈጩ በመሆኑ ተጠቃሚ መሆናቸውን ያስባሉ። ላለፉት 6 ዓመታት ሁለቱ ሰዎች እንደዚህ እየተደጋገፉ ኖረዋል። በማያውቁት ሰዎች ዘንድ አድማሱ ሳቅ ወዳድና ተጫዋች ነው ይባላል። ከመጡት ጋር መቃለድ ከቤት እመቤቶች ጋር መሳሳቅ ከሰራተኞች ጋር መላፋት ከቆንጆዎች ጋር መጎነታተል ይወዳል። ብዙዎቹ ወፍጮ ቤቱን 'አድማሱ ወፍጮ' ብለው ይጠሩታል። የእርሱ ስለመሆኑ አይጠራጠሩም። ውስጥ አዋቂዎች ካልሆኑ በቀር። እሱም 'ንብረቱ የኔ ነው' ማለቱን አላቆመም። በየወሩ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ወደዚህ ወፍጮ ቤት ብቅ የምትለው የ20 ዓመት ወጣት ከአድማሱ ጋር ትግባባለች። ትዕግስት ደመረ። ትዕግስት ስትስቅ ጎድጎድ የሚል ጉንጭ ያላት ቆንጆ ልጅ ናት። አድማሱ ይህቺን ልጅ ሲግባባት ከማንኛውም ደንበኞቹ ጋር እንደሚያደርገው በቀልድና ጨዋታ ነበር የጀመረው። ልጅቷ ግን ልፊያ አትወድም። የተላከችበትን ጨርሳ ወደ ቤቷ መመለስ ነው ፍላጎቷ። የ11ኛ ክፍል ተማሪ በነበረችበት በዚያ ዘመን ከትምህርት ቤት መልስ ልብሷን ቀይራ ወላጆቿን ታገለግላለች። ለእናቷ ያለቻቸው አንድ ልጅ እሷው ብትሆንም ቤት ውስጥ ግን አባቷ ከሌላ የወለዱት የእርሷ ታላቅ የሆነ ልጅ አለ። ትዕግስት ነፍስ ስታውቅ ይህ ልጅ የአባቷ ልጅ መሆኑን ከእናቷ ብትረዳም ብዙም ስሜት አልሰጣትም። ለርሷ መወለድ ቋንቋ ነው። እህል ልታስፈጭ ስትመጣ ወንድሟ እህሉን ተሸክሞላት እዚህ ወፍጮ ቤት ድረስ ይመጣና ተመልሶ ይሄዳል። ተፈጭቶ ሲያልቅ እንደ አመጣጡ ተሸክሞ ወደ ቤት ያደርሳል። ሁለቱም ልክ እንደ አንድ እናት ልጆች ነው የሚዋደዱት። *ይቀጥላል............
نمایش همه...
ከቅን ልቦች ፉፁም አስፋው ማንበብ የሚችል ሁሉ ያንብበው በውስጥ መስመር የአንዲት እናት ልብ የሚነካ ታሪክ ደረሰኝ። ምናልባት ብዙዎችን (በተለይ ሴት እህቶችን) ያስተምራል ያስጠነቅቃል ብዬ ስላሰብኩ እንዲህ አቅርቤዋለው። ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች እናት ነኝ። አንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ተቀጥሬ እሰራለሁ። ከዛች ክፉ ምሽት በፊት በትዳሬ፣ በልጆቼ ባጠቃላይ በኑሮዬ እንደኔ ደስተኛ ሰው አልነበረም። ያንን ቀን እንደ ሁልግዜው በስራ ገብታዬ ነበር ያሳለፍኩት፤ ሆኖም አመሻሽ ላይ መጨረስ የሚኖርብኝ ስራ ስለነበር በመደበኛ ሰዓቴ አልወጣሁም። ለባለቤቴም ትንሽ ማምሸቴ ስለማይቀር በጊዜ ልጆቹ ጋር እንዲገባ ደውዬ ነግሬው ወደ ስራዬ ተመለስኩ። ከምሽቱ 3:40 ስራዬን አጠናቅቄ ከቢሮዬ ወጣሁ። በዛን ሰዓት ሚኒባስ ታክሲ ማግኘት የማይታሰብ ስለነበር የኮንትራት ታክሲዎች ከተደረደሩበት ስፍራ ደርሼ በወቅቱ ከነበሩት ሹፌሮች እድሜው በ40ዎቹ አጋማሽ የሚገመት ጎልማሳ መርጬ ወደሰፈሬ ለማድረስ የጠየቀኝን ሂሳብ ምንም ሳልከራከር ተስማምቼ ገባሁ። ላዳዋ ግን ከፊትም ከኃላም ታርጋ አልነበራትም። ግራ ገብቶኝ ስጠይቀው "አሁን ነው ትራፊኮች የፈቱብኝ" አለኝ። እኔም ብዙ ሳልጨነቅ ጉዞ ጀመርን። የአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ስላማረረን እኔና ባለቤቴ ከከተማ ትንሽ ወጣ ያለ ቦታ (ቡራዩ) አከባቢ መሬት ገዝተን ቤት ሰርተን ከገባን ገና አመት አልሆነንም ነበር። ሹፌሩ በማላውቀው ወይም ባልለመድኩት መስመር ላዳዋን አዙሮ ሲነዳ ግራ ተጋብቼ "የኔ ወንድም ወዴት ነው የምትወስደኝ?" ስለው "አይ በዚ በኩል አቋራጭ መንገድ አለ፤ ይቀርበናል ብዬ ነው" አለኝ። እኔም በጣም ስለመሸ ምናልባት እንዳለውም ቶሎ ያደርሰን ይሆናል ብዬ ዝም አልኩሐ ጥቂት ከተጓዝን በኃላ የመብራት ብርሃን እንኳን በሌለበት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ በድንገት መኪናዋን አቆማት። "ምነው? ምን ሆንክ?" አልኩት ደንግጬ። "እኔንጃ መኪናዋ ተበላሽታ ነው መሰለኝ፤ ቆይ ወርጄ ከኃላ ልያት" አለኝና ወርዶ የኃላውን ኮፈን ከፈተው ብዙም ሳይቆይ እኔ የነበርኩበትን የኃላ በር ከፍቶ "ይቅርታ ከጎንሽ የእጅ ባትሪ አለ አቀብይኝ" አለኝ። ግራ ተጋብቼ "የቱጋ ነው?" ብዬ ወደጎኔ ስዞር አንገቴ ስር የሽጉጥ አፈሙዝ ደቀነብኝ። "አንዲት ነገር እተነፍሳለው፣ እጮሃለው ብትይ በአንዲት ጣቴ ብቻ ምላጯን ስቤ እስከዘላለሙ አሰናብትሻለው" አለኝ። "ወንድሜ ገንዘብ ከፈለክ ቦርሳዬ ውስጥ ያለውን ሁሉ ውሰድ" እያልኩ ተንተባተብኩ። "ገንዘብሽን ሳይሆን ገላሽን ነው የምፈልገው፤ አሁን አንድ በአንድ የለበስሽውን አውልቂ" አለኝ። ለመንኩት፤ "እባክህ የሁለት ልጆች እናት ነኝ፤ እባክህ ባለትዳር ነኝ" አልኩት። ግን አልተሳካልኝም። ሽጉጡን ወደኔ እያቀረበው በሄደ ቁጥር ነፍሴ ተጨነቀች። ልጆቼ በአይምሮዬ ውስጥ ተመላለሱ። እንባ ሳይሆን ደም እያነባሁ ያለኝን ነገር ሁሉ ፈፀምኩ፤ የተመኘውን ገላ እንደልቡ ተጫውቶበት ሲያበቃ "ለፖሊስ እጠቁማለው፣ ለሰው አወራለው ብትይ እጨርስሻለው" አለኝ። እራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩና ህመሜን ስብራቴን ዋጥ አድርጌ ውይ ምን ችግር አለው በፊትም እኮ ሳታስገድደኝ እንዲሁ ብትጠይቀኝ እንስማማ ነበር፤ ሽጉጡን ስላየሁ ነው እንጂ የደነገጥኩት፤ ምንም ችግር አልነበረውም፤ ባይሆን ስልክ ቁጥርህን ስጠኝና ሌላ ጊዜ ተደዋውለን በሰፊው አሪፍ ጊዜ እናሳልፋለን አልኩት። ከት ብሎ ሳቀና "ባንቺ ቤት አሁን ምንም የማላውቅ ፋራ አርገሽኛል" አለኝ። እኔም ያለ የሌለ መሀላ እየደረደርኩ ላሳምነው ሞከርኩ። በመጨረሻም "ያንቺን ስልክ ቁጥር ስጪኝና እኔ ደስ ባለኝ ቀን እደውልልሻለው" አለኝ፤ ሰጠሁት። ከዛም ወደ ቤቴ አድርሶኝ ልክ ምንም እንዳልተፈጠረ እየሳኩኝ ደስተኛ መስዬ አመስግኜው ተለየሁት። እቤት ስደርስ ቁጭ ብሎ የሚጠብቀኝ ባለቤቴ ላይ ተጠምጥሜ እያለቀስኩ ያጋጠመኝን ሁሉ ነገርኩት። ድንጋጤ ድንዝዝ ቢያደርገውም እኔ እንድረጋጋ ብቻ አቅፎ ሲያባብለኝ ቆየና ጠዋት ለፖሊስ እንደምናመለክት ነግሮኝ አደርን። በንጋታው ወደ ሆስፒታል ሄጄ ሙሉ ምርመራ አድርጌ ኤች አይ ቪ ለመመርመር ከ3 ወር በኃላ ደግሜ እንድመጣ ነግረውኝ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደን ካመለከትን በኃላ ወንጀለኛውን ለመያዝ ብቸኛው አማራጭ ያን ቀን ስልኬን ስለሰጠሁት እስኪደውል ብቻ መጠበቅ ነበርና ከ1 ሳምንት በኃላ ቅዳሜ ቀን የማላውቀው ቁጥር ተደወለ። ሳነሳው እሱ ነው። ምንም እንዳልተፈጠረ እንባዬን ወደ ውስጤ እየመለስኩ በሰላም አወራሁት። ድምፁንም እየቀዳሁት ነበር። ሰሞኑን ሁኔታዎችን አመቻችቶ እንደምንገናኝ ነገረኝና ዘጋው። እሄን ለፖሊስ አመልክቼ በቀጣይ እስኪደውል መጠባበቅ ጀመርኩ ከ3 ቀን በኃላ በሌላ ስልክ ቁጥር ደወለ። አሁንም ሰላም ብሎኝ ዘጋው። በንጋታው በሌላ ስልክ ቁጥር ደወለ፤ አሁንም አናግሮኝ ዘጋው፡፡ በ4ኛው ላይ ልክ መጀመርያ ቀን በደወለበት ስልክ ደግሞ ደወለ፤ ሰሞኑን እንደምንገናኝ ነገረኝ ፖሊሶችም ድጋሜ የደወለበትን ስልክ ይዘው የታክሲ ደንበኛ በመምሰል ደወሉለትና ለስራ እንደሚፈልጉት ነግረው ያዙት። እኔም ተጠርቼ ሄድኩኝ፤ ሳየው እራሱ ነው። ዘልዬ ላንቀው ስል አጠገቤ የነበረው ፖሊስ ያዘኝ። የክስ መዝገብ ተከፍቶ ምርመራ ተደርጎበት ሰውዬው ከዚ በፊትም ብዙ የወንጀል ሪከርድ እንደነበረበት ታውቆ የ16 አመት እስራት ተፈረደበት። እኔ ከ 3 ወር በኃላ ሀኪም ቤት ሄጄ ኤች አይ ቪ ስመረመር በደሜ ውስጥ ቫይረሱ እንዳለ ተነገረኝ። ዛሬ ፈጣሪና ውዱ ባለቤቴ ከጎኔ ባይኖሩ ኖሮ በህይወት አልኖርም ነበር፤ እራሴን ለማጥፋት ስሞክር ስንቴ ከሞት አፋፍ ተርፌያለሁ። ቆይቼ ሳስበው ግን ቢያንስ ለልጆቼና በቫይረስ መያዜን እንኳን እያወቀ እስከዛሬ ከጎኔ ላልተለየኝ ባለቤቴ ስል መኖር እንዳለብኝ ገብቶኛል። ግን ሁሌም እፈራለው፤ ምክንያቱም ሴት ልጆች ወልጃለው። የኔ እጣ እንዳይደርሳቸው ሁሌም እፈራለው። ከትምህርት እስኪገቡ እንኳን ልቤ አይረጋጋም። እንደ እስረኛ ከግቢ አላሶጣቸውም፤ ሱቅ እቃ እንዲገዙ እንኳን አልካቸውም። ይህ ሁሉ ከሆነ 7 አመት አልፎታል፤ እኔ ግን ዛሬም ህመምተኛ ነኝ። ልቤ ተሰብሯል፤ ፈሪ ነኝ፤ ትንሽ ነገር ያስደነግጠኛል። እራሴን አሞኝ ከተኛሁ በዛው ሞቼ የምቀር ይመስለኛል። ልጆቼ የኔ እጣ እንዳይደርሳቸው ያስጨንቁኛል። እኔን ብሎ ብዙ የተጎዳው ባለቤቴ ያሳዝነኛል። ቅን ልቦች ፕሮግራማቹን ሁሌም በእንባ ነው የማዳምጠው የኔ ውድ ባለቤቴ፣ የልጅነቴ፤ ታመምሽ፣ ተበላሸሽ ብሎ ያልሸሸኝ እሱ ብቻ ነው። በናንተ ፕሮግራም ውስጥ ባለቤቴን ሁሌም አየዋለው። ሴት እህቶቼ፣ ሴት ልጆቼ ከኔ ታሪክ ተማሩ፤ ተጠንቀቁ። #ምንጭ :- እውነተኛ ፍቅር የፌስቡክ ገፅ 🔊share and join @kemtsahft
نمایش همه...
👍29
👎2
Comments(3)
Repost
ልጅነት
نمایش همه...
ይህች ምራቅ ሳትደርቅ(ዘነበ ወላ) ልጅነት "ና! የእኔ ፉንጋ! ዓረብ ቤት ትሄድና የአራት ፍራንክ ዘይት፣ የሁለት ፍራንክ ጨው፣ አራት ፍራንክ መልስ አለው፡፡ እንካ ስሙኒውን፡፡ ስትመለስ የማደርግልህን አታውቅም! ብርር በል ቱፍ!" (ምራቃቸውን እየተፉ) ይህች ምራቅ ሳትደርቅ ከተፍ በል አሉ እማማ ረታሽ፡፡ "እሺ፡፡" "ቆይ አትንከውከው፤ ምንድነው ግዛ ያልኩህ?" "የአራት ፍራንክ ዘይት፣ የአራት ፍራንክ ስኳር!" "ይኸው! አላልኩም፡፡ ይሄ ልበቢስ! ስኳር መቃምዋ ሱስ ሆናብሃለች ማለት ነው? ልብ በልና አድምጠኝ!" ብለው ያርሙኛል፡፡ ከአፋቸው ነጥቄ "የአራት ፍራንክ ጨው፡፡" "ኧረ እኔ አልወጣኝም!" የአራት ፍራንክ ጨው ምን ላደርግበት ነው? ድግስ የለብኝ!" ብለው እማማ ረታሽ አረሙኝ፡፡ እኔና አብሮ አደጎቼ በሰፈራችን ውስጥ ትላልቅ ሰዎችን ዓረብ ቤት በመላላክ አገልግሎት መስጠቱ እንድ የውዴታ ግዴታችን ነበር፡፡ ጎረቤቶቻችን ከእናታችን ማሕፀን ስንወጣ ሁሉ የዓይን ምስክር ናቸው፡፡ እንደ አሳዳጊዎቻችን ስለሚቆጠሩም ከቤታችን ውጪ ሁሉም ትላልቅ ሰዎች በእኛ ሕይወትና ደኅንነት ላይ የወላጆቻችንን ያህል የመወሰን መብት ነበራቸው፡፡ ተልከን ስንመለስ ልዩ ልዩ ጉርሻ ይሰጠን ነበር፡፡ መላላኩ ከመደጋገሙ የተነሳ ጉርሻቸው ምን እንደሚሆን ከወዲሁ እናውቀዋለን፡፡ የአንዳንዱ ጉርሻ የሚናፈቅ ነበር፡፡ እማማ አመለወርቅ ከጅሩ ዘመዶቻቸው በሚጭኑላቸው ጥቁር ስንዴ የሚጋግሩት ሙልሙሉ አሁንም ሳስበው ምራቄን እውጣለሁ፡፡ የኃይሉ ዶሮ እናት እማማ ሸጊቱ በውብ ቋንቋቸው ሲመርቁን እዚያው በዚያው አድገን እንዲታየን እያደረጉ አሹቁን በኪሳችን ያጭቁታል፡፡ እማማ ቀለሚቱ….ከተላላክንላቸው በኋላ ከዕለታት አንድ ቀን የወሰዱብንን የጨርቅ ኳስ ይመልሱልናል፡፡ በእኔና በእማዬ ብቻ የሚታወቅ የጋራ ምስጢር አለን፡፡ ልትልከኝ ስትፈልግ ትጠራኝና መልዕክቱን ነግራኝ "ስትመለስ እማደርግልህን አታውቅም" ካለችኝ ስመለስ በጣም የሚጣፍጠኝን የቅንጬ ፍቅፋቂ እንደምትሰጠኝ አውቃለሁ፡፡ ✍እስቲ እናንተስ ከጣፋጩ የልጅነት ግዚያቹህ ምን ትዝ ይላችኀል? @kemtsahft
نمایش همه...
👍14
👎2
Comments(1)
Repost
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.