1 586
مشترکین
-424 ساعت
-157 روز
-6230 روز
آرشیو پست ها
1 586
ተሿሚዎች ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገቡ‼️
በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተሾሙ አዳዲስ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ለመውሰድ ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መወሰዳቸው ተሰማ። ይህ ያልተለመደ እርምጃ የመጀመሪያው ዙር ሲሆን በቀጣይም ሌሎች ባለስልጣናት በተከታታይ ተመሳሳይ ወታደራዊ ስልጠና እንደሚወስዱ ታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በፓርላማ እና በተለያዩ መድረኮች ላይ፣ የመንግስት ሹመኞች "ቦርጭ ማውጣት እና ከመጠን በላይ መወፈር እንደሌለባቸው" በማንሳት፣ ጂም በመግባት እና ስፖርት በመስራት ንቁና ቀልጣፋ መሆን እንዳለባቸው በሳቅ የታጀበ ማሳሰቢያ ሲሰጡ ተሰምተው ነበር።
Via:- ዘሐበሻ
1 586
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።
በስልክ ውይይቱ ወቅት አመራሮቹ በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እንዲሁም በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸው ተገልጿል። ይህ ውይይት በእንደገና አዲስ ምዕራፍ ላይ በሚገኘው የሁለቱ አገራት ግንኙነት ውስጥ በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን ታሪካዊ ወዳጅነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊና ተግባራዊ አጋርነት ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተጠቅሷል።
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ዘላቂ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል የሰጠችውን ማረጋገጫ ያደነቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያም በበኩሏ የሁለትዮሽ ትብብሩን ለማጠናከር እና የጋራ ትኩረት በሚሹ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረኮች ላይ በቅንጅት ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
1 586
ሽራሮ የተነሳው እሳት‼️
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ከባድ የአየር ድብደባዎች እየተደረጉ ነው።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባለፉት 2 እና 3 ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አካባቢዎች ከባድ ድሮን እና የአየር ድብደባዎችን ሲያካሂድ ቆይቷል።
የኤርትራ ጦር እና የትግራይ ተዋጊዎች ከዋና ዋና ከተሞች ሲወጡ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ደህንነታቸው ወደተጠበቁ ቦታዎች እንዳይሸሹ እና ጥቃቶችን እንዳይሰነዝሩ ለመከላከል ቀጣይነት ያለው የአየር ዘመቻዎችን እያደረገ ይገኛል።
ከአዲግራት እስከ ዛላምበሳ፣ ከአድዋ እስከ ራማ፣ እና ሺራሮ አካባቢዎች በኢትዮጵያ አየር ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል።
ይህንን ተከትሎ በኤርትራ አዋሳኝ ሽራሮ አካባቢ የእሳት አደጋ የተነሳ ሲሆን ባለፉት ሁለት ወይም ሶስት ቀናት ውስጥ ወደ ኤርትራ ድንበር እየተዛመተ መሆኑን ከሳታላይት ምስሎች ለማየት ተችሏል።
1 586
ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት ሊገቡ መቃረባቸውን ኢንተርናሽናል ክራይሲስ ግሩፕ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ኤርትራ ድንበር መድረሱን ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት ወደ ሙሉ ጦርነት የሚገቡበት ሁኔታ መጨመሩን ገልጿል።
1 586
ባድመ ብቻ ቀረች ተባለ - አህዮቹ ተወሰዱ - የትግራይ አሁናዊ መረጃዎች‼
📌 የአክሱም፣ ሽራሮ እና ዛላምበሳ ከህውሃት ኃይሎች ነፃ መውጣታቸው ታውቋል። ቀጣዩ ጉዕዞ ወደ ኢትዮጵያ ባድመ አቅጣጫ መሆኑ ተነግሯል።
📌 የሕወሓት ኃይሎች በአሁኑ ወቅት በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር አካባቢ መከማቸታቸው ተሰምቷል።አመራሮች ወደ ኤርትራ ድንበር መሻገር እንዳለባቸው እና እንደሌለባቸው በሚለው ሃሳብ ዙሪያ ከፍተኛ ክፍፍልና ውጥረት እንደነገሰ የቡድኑ ዕላዊ መግለጫ አሳይቷል።
📌 ከመንግስት ለህውሃት ኃይሎች «ወደ ኤርትራ ምድር በህይወት እያሉ መሄድ ወደ ሲኦል መውረድ ማለት ነው። ስለዚህ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር የተሰበሰባችሁ ታጣቂዎችና ካድሬዎች ሀገራችሁን ጥሎ ለመሰደድ አትሞክሩ፤ የትግራይ መጻኢ እድል ብሩህ ነው። ተስፋ በመያዝ እና ምሕረት እንደሚደረግልችሁ ተገንዝባችሁ በሀገራችሁ እንድትቆዩና ለሰራዊታችን እጅ እንዲሰጡ እንመክራለን» የሚል መልእክት መተላለፉ ተገልጿል።
📌 ትግራይ በፍያ ቀሺ እና ፋፂ አካባቢዎች የሚገኙ የትግራይ አርሶ አደሮች እንስሳት (አህዮች) በኤርትራ ሰራዊት በኃይል ተነጥቀው ወደ ኤርትራ መወሰዳቸው ተሰምቷል። በጎ አድራጊ አካላት አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ ቀርቧል።
1 586
" የኢትዮጵያ ጦር ከኤሊዳር እና ቡሬ ከተሞች አልፎ ወደ ኤርትራ ድንበር አልገባም ! " - እማኞች‼️
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይል በርካታ ዋና ዋና የትግራይ ከተሞችን በቁጥጥር ስር እያዋሉ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከሚዋሰኑበት የድንበር አካባቢዎች ተቃርበዋል።
በሌላ በኩል፣ ከትናንት እሁድ ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የኢትዮጵያ ወታደሮች የኤርትራ ድንበርን አልፈው ገቡ " የሚሉ ዘገባዎች ሲሰራጩ ውለዋል።
እነዚህ ዘገባዎች የኢትዮጵያ ጦር የቡሬ ከተማን አልፎ " ደባይ ሴማ " የተባለች የኤርትራ መንደር መቆጣጠራቸውን ይገልጻሉ።
ነገር ግን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ የአይን ምስክሮች ጠቅሶ እንደዘገበው የኢትዮጵያ ጦር ከኤሊዳር እና ቡሬ ከተሞች አልፎ ወደ ኤርትራ ድንበር አልገባም።
በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢዎች ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ መኖሩን የገለጹት ነዋሪዎቹ ለጊዜው ግጭት አለመፈጠሩን አረጋግጠዋል።
በ1991 የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ዉጊያ ከተደረገባቸውን አካባቢዎች የቡሬ ግንባር አንዱ ነበር።
1 586
በጅቡቲ ባህር ዳርቻ እስካሁን በታወቀው የ139 ስደተኞች ህይወት አለፈ።
👉ሁሉም ኢትዮጵያን ሲሆኑ ስማቸው እንኳን ሳይፃፍ በጅምላ ተቀብረዋል።
በጅቡቲ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ስደተኞችን የጫነ አንድ ጀልባ ትናትንት ሌሊት ላዛሬ አጥቢያ ሰጥሞ እስካሁን 139 ሰዎች መሞታቸውን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (አይኦኤም) አሳወቀ።
ከሟቾቹ መካከል 15ቱ ህፃናት መሆናቸው ተገልጿል።
ከአደጋው 82 ሰዎች የተረፉ ሲሆን 84 ሰዎች ደግሞ እስካሁን የት እንዳሉ አይታወቅም።
ወደ የመን በመጓዝ ላይ የነበረውና 350 ሰዎችን አሳፍሮ እንደነበር የሚገመተው ይህ ጀልባ፣ አደጋ የገጠመው በጅቡቲዋ ኦቦክ አካባቢ ነው።
ከትላንት ለሊቱ አደጋ የተረፉት ከ80 በላይ ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ተገልጿል።
እስካሁን ከተገኙት አስከሬኖች መካከል 52ቱ ወንዶች፣ 42ቱ ሴቶች ሲሆኑ 15ቱ ደግሞ ህጻናት ናቸው።
እስካሁን የት እንዳሉ የማይታወቁ 84 ሰዎች ያሉ ሲሆን የፍለጋና የነፍሥ ማዳን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ድርጅቱ አሳውቋል።
ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ/ም
========================
1 586
በቡሬ ግንባር ወደ አሰብ ተኩስ መከፈቱ ተሰማ‼
ጥቅምት 1 ቀን በቡሬ - አሰብ ግንባር በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እናበኤርትራ ኃይል መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉ የአንዳፍታ ዘገባ አመልክቷል።
ከአሰብ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው በዚሁ የቡሬ ግንባር ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ ኃይል የሚገኝ ሲሆን፣ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱ ይቀርባሉ።
1 586
+1
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ እና የኢትዮጵያ የኑክሌየር ሀይል ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዶክተር አብርሃም በላይ ዛሬ ጥቅምት 1/2019 ዓ.ም ወደ ትግራይ መቀሌ በተደረገው የመጀመሪያ በረራ ወደ ትግራይ ማቅናታቸው ታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ አብረው የተጓዙ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ሌ/ጄ ገ/እግዚያብሄር (ወንዲ አንጥሩ) እና ሜ/ጄኔራል ዘውዱ ኪሮስ ይገኙበታል።
ዶክተር አብርሃም በላይ ወደ ትውልድ ቦታቸው አዲግራት ያመራሉ ተብሏል።
1 586
ሰበር❗ኤርትራ ደብዳቤ ፃፈች‼️
ኤርትራ ኢትዮጵያ "ጦርነት እወጃብኛለችና ይወገዝልን ስትል በዛሬው ዕለት መስከረም 30/2019 ዓ.ም ለተመድ ደብዳቤ ፃፈች።
ኤርትራ የጦርነት አዋጁን የተባበሩት መንግሥታት እንዲያወግዝላት በዛሬው ዕለት ደብዳቤ መፃፏ ታውቋል።
የኤርትራ ጦር በአዲግራት በኩል ገብቶ በጦርነቱ ላይ መሳተፉን ተከትሎ የኤርትራ ጦር በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣና ኢትዮጵያ ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማሳወቋ ይታወሳል።
1 586
ካርታ በእርሳስ አይሳልም-ኤርትራ❗
የኤርትራ አዲስ መግለጫ የኤርትራ ህዝብ ያካሄደው ትግል ነፃነትን ለማስመለስ የተደረገና የኢትዮጵያን ወረራ ለመቀልበስ የተከናወነ መሆኑን አውስቶ ‹‹በዚህ መራራና ረጅም የትግል ጉዞ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ የሞራልና ሌሎችም ድጋፎች ማግኘቱ የሚካድ አይደለም›› ብሏል፡፡ ጨምሮም ‹‹አሁን የሚሰማው የታሪክ ማዛባት ጫጫታ ግን ሊበሏት ያሰቧትን ጥንቸል ጅግራ ይሏታል እንደማለት ነው›› ያለው መግለጫው ‹‹የአለም ካርታ በተረት ተረት፣ ከአቅም በላይ በመመኘት፣ የቀይ ባህር መስኮት በመፈለግና ለጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በመቅረብ›› የማይለወጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በማጠቃለያውም ‹‹የአለም ካርታ በእርሳስ የሚሳል ሳይሆን በአለም አቀፍ ህግና ስምምነቶች የሚገዛ የሉአላዊነትና የግዛት አንድነት ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህም የኤርትራ ሉአላዊነት በደምና በህግ የተረጋገጠና የተገደበ ነው፡፡ እሱን የሚነካም ወዮለት፡፡ አራት ነጥብ›› ብሏል፡፡
ኤርትራ ‹‹ኢትዮጵያን የባህር በር ለማሳጣት በተደረገ ሴራ የተፈጠረች አገር›› ናት የሚለው ፍራጃ ተቀባይነት የለውም ብሏል።
1 586
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዴሊቨሪ ክትትል ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
ሹመቱ በዛሬው ዕለት የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል::
1 586
ከትግራይ ከተለያዩ አካባቢዎች ያሰባሰብናቸው መረጃዎች‼️
📌የህወሓት ተዋጊዎች ለሊቱን አዲግራትን ለቀው ግማሹ ወደ አድዋ ግማሹ በሰንአፌ በኩል ወደ ኤርትራ አዲ ኬይህ የሚባል ቦታ መድረሱን ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
ይህንን ተከትሎ የአዲግራት ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ንብረቱን ከሌቦች ሲጠብቅ ማደሩን ገልፀውልናል።
መከላከያ ሰራዊት ከአዲግራት በቅርቡ እርቀት ላይ የምትገኘውን እደጋ ሐሙስን ዛሬ መስከረም 29 ጠዋት ላይ ተቆጣጥሯል።
አዲግራት ከኤርትራ ድንበር በ25 ኪሎሜትር እርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች።
📌ህወሓት ወታደሮቹ የተንቤን ህዝብ የሚያቀርብላቸውን ምግብ እንዳይበላ ውሳኔ አሳልፈዋል፣ ምክንያቱ አልታወቀም።
📌በሽሬ ዙሪያ ልዩ ስሙ አዲ ግዳድ ለሊቱን የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል።
ተጨማሪ ትክክለኛ ወቅታዊ መረጃዎችን አጠናቅረን እንመለሳለን።
1 586
Update❗ሽሬ‼️
ከማይፀብሪ-አዲ ገብሩ-እንዳ ባጉና-ሽሬ-አክሱም መስመር ላለፉት ሁለት ሳምንታት ከፍተኛ ውጊያ ሲስተናገድበት የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት መስከረም 28 የህወሓት ተዋጊዎች ከእንዳባጉና እና ሽሬ ለቀው የወጡ ሲሆን መከላከያ ሠራዊት ዛሬ አመሻሽ ላይ ሽሬ መግባቱን የአካባቢው ምንጮች ከምስል ጋር አጋርተውናል።
1 586
ትግራይ ክልል አሁናዊ ትክክለኛ መረጃ‼️
በትግራይ ክልል በተለይ በሶስት አቅጣጫ ወጊያው ቀጥሏል።
📌ከመቀሌ-ሀገረ ሰላም-አብዪ አዲ(ተንቤን-አድዋ መስመር አንዱ የውጊያ መስመር ሲሆን በዚህ መስመር መከላከያ ሰራዊት የተንቤን ዋና ከተማ የሆነችውን አብዪ አዲን ተቆጣጥሯል፣አድዋ ከተማ ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴ ቆሟል ብለዋል።
📌ከመቀሌ-ውቅሮ-ነጋሽ-አዲግራት-ዛላንበሳ---- ሌላኛው ውጊያ እየተደረገበት ያለ መስመር ሲሆን በዚህ የውጊያ መስመር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ መስከረም 28 ከሰዓት በኋላ ውቅሮን አልፎ ነጋሽ የምትባል ከተማን ተቆጣጥሯል።
በውቅሮ መከላከያ ሰራዊት ፓትሮል መጀመሩን የአዩዘሀበሻ ምንጮች በምስል አጋርተዋል።
📌ከማይፀብሪ-አዲ ገብሩ-እንዳ ባጉና-ሽሬ-አክሱም ---ሌላኛው የውጊያ መስመር ሲሆን የህወሓት ተዋጊዎች ከእንዳባጉና እና ሽሬ ለቀው ቢወጡም መከላከያ ሠራዊት ገና እንዳልገባ የአካባቢው ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
📌አዲግራት በዛሬው ዕለት ተደጋጋሚ የጀት ድብደባ ተፈፅሟል፣ የደረሰው ጉዳት አልታወቀም።
1 586
ሱዳን‼️
የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት (STC) ሊቀመንበር እና የሱዳን ጦር መሪ የሆኑት ጄኔራል አብደል ፋታህ ቡርሃን ትናንት መስከረም 27/2019 ዓ.ም በኤርትራ ድንበር በካሽም ኤል ግሪባ የሚገኘውን የሱዳን ጦር ኃይሎች 11ኛ እግረኛ ክፍል ዋና መሥሪያ ቤትን ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱ ኤርትራዊያን ወታደሮች በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ውስጥ ስለመሰማራታቸው ከወጡ ዘገባዎች ጋር በተመሳሳይ ቀን የተከናወነ ሲሆን፤ ይህም በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ቀጠናዊ ውጥረት ያባብሰዋል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።
1 586
አሜሪካ-ኢራን አዲስ ውጥረት‼️
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ባይደርሱም፣ የፔንታጎን ኃይሎች ለጥቃት ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ ትዕዛዝ መሰጠቱን 'አክሲዮስ' ዘግቧል። ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ባለሥልጣናት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ይህ ወታደራዊ ጥቃት ኖቬምበር 3 ከሚካሄደው የአሜሪካ አጋማሽ ዘመን ምርጫ እና ከአንድ ሳምንት በፊት ከሚጠበቀው የእስራኤል ምርጫ አስቀድሞ ሊፈጸም ይችላል።
የትራምፕ የብሔራዊ ደህንነት ቡድንም በካምፕ ዴቪድ ተሰብስቦ ስለ ጦርነቱ እና ቀጣይ ስትራቴጂዎች በጥልቀት መክሯል።
ጥቃቱ የሚጀመር ከሆነ በኢራን የኃይል ማመንጫዎች፣ የመሠረተ ልማት አውታሮች እና የኑክሌር ተቋማት ላይ ሰፊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተጠቁሟል። አሜሪካ እና እስራኤል በጥቃቱ ላይ በጋራ ሊሠሩ እንደሚችሉ እና፣ ኢራንም በአጸፋው በመቶዎች የሚቆጠሩ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ልትተኩስ እንደምትችል የእስራኤል ባለሥልጣናት ስጋታቸውን ገልጸዋል።
1 586
አሜሪካ በ #ኢትዮጵያ «ወታደራዊ ተቋማት ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ ይችላሉ» ስትል የደህንነት ማስጠንቀቂያ አወጣች‼️
አሜሪካ በአዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል፣ በተያዘው የፈረንጆቹ ጥቅምት ወር «በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተቋማት» ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ ይችላሉ በሚል በኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜጎቿ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የደህንነት ማስጠንቀቂያ አስተላለፈች።
አሜሪካ ረቡዕ ምሽት ባወጣችው መግለጫ «በጥቅምት ወር [እ.አ.አ.] በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተቋማት ላይ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ሊሰነዘሩ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ ዘገባዎች ደርሰውኛል» ብላለች። አሜሪካ አክላም ዜጎቿ «አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና» ባለሥልጣናት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከተሉ አሳስባለች።
አሜሪካ ማምሻውን ባወጣችው የደህንነት ማስጠንቀቂያ በተጨማሪም ዜጎቿ «በማንኛውም ምክንያት» ወደ #አማራ ክልል (#ላሊበላን ጨምሮ)፣ ወደ #ትግራይ ክልል ወይም ወደ #ዓፋር ክልል ከማንኛውም ዓይነት ጉዞ እንዲቆጠቡ መክራለች። ቀደም ሲል በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎቿ ደህንነታቸው የተጠበቀ ከሆነ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ፣ ካልሆነ ደግሞ ሁኔታዎች እስኪሻሻሉ ድረስ ባሉበት ቦታ እንዲጠለሉ አሳስባለች።
1 586
ሰበር መረጃ❗
የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ይበልጥ ጠልቆ በመግባት ከመቀሌ ቀጥላ ክልሉ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ የሆነችውን አዲግራትን መቆጣጠሩን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ድርጊት "ወረራ" ሲል በይፋ ኮነነ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለብሉምበርግ የዜና አውታር እንደተናገሩት፣ "በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም የጊዜ ገደብ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ለቀው መውጣት አለባቸው" በማለት የመንግስትን ጥብቅ አቋም አንጸባርቀዋል። ምንም እንኳን የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መኖሩ ከዚህ ቀደም በከፍተኛ የፖለቲካ እና የወታደራዊ መኮንኖች ሲነገር ቢቆይም፣ የሚኒስትሯ የዛሬው መግለጫ ግን ኤርትራ ጦሯን በቀጥታ በማስገባት ሉዓላዊ አገር መውረሯን የሚያረጋግጥ "ይፋዊ የመንግስት ማረጋገጫ" ሆኖ ተመዝግቧል።
