የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥
رفتن به کانال در Telegram
6 776
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-257 روز
-9530 روز
آرشیو پست ها
6 776
እድሌ ነው መሰል
ዙሪያዬ ላለ ሰው _ ልክ ሁኜ አልታይም
የምደክምላቸው _ ልፋቴን አያውቁም
ለሳቃቸው ስጥር _ሰርክ ያስለቅሱሳኛል
ጥፋት አይቼ ባልፍ _ እንደ ሞኝ ያዩኛል
መሳሳታቸውን _ ደግሞ ስነግራቸው
ተጨቃጫቂ ነህ _ ይሆናል ወሪያቸው
ባስፈለጉኝ ሰአት _ ከኔ ይርቃሉ
ለብቻዬ ስሆን
ምን አገኜህ ብለው _ ሀሜት ያወጋሉ
ሳቄን ሰርቀው ወስደው
አኩራፊ ይሉኛል _ እነሱው መልሰው
#ሼን ✍️
@seanlph
6 776
ስታጠፋ እያየች _ ዝም ካለቺህ ሴት
ፍፁም እንዳታየው _ ልክ እንደሞኝነት
ውስጧ እየሞተ ነው _ ላንተ ያላት ስሜት
ወይ እየሰራች ነው _ የሚያዋጣትን ቤት
እናም እልሀለሁ......
ደጋግመህ ስትዋሻት _ በደል ስትሰራ
ንዝንዟን ሳይሆን _ ዝምታዋን ፍራ
#ሼን ✍️
6 776
በደሉን እያወኩ _ የዝቋላውን ግፍ
ሙስሊም ስለሆንኩኝ _ ችላ ብዬ ባልፍ
ይህ ያሁኑ ሴራ _ ነገ ላይ ውሎ አድሮ
መድረሱ ማይቀር ነው _ ከኔ ከመስጊዴ ጓሮ
እናም ዝም አልልም _ አወግዛለሁ ግፉን
እስከመች ድረስ ነው _ ልጥሉ ምትገፉን
በዘር ማባላቱ _ ብሏችሁ አልበቃ
መጫወት ያዛችሁ _ በእምነት እንደቃቃ
😢
እኛን እሺ ናቁ _ አትቁጠሩ እንደሰው
በሟችም አፊዙ _ ደሙ በሚፈሰው
እንዴት ጥቂት እንኳ _ ፈጣሪን አትፈሩም
ህሊናስ አለ አይደል _ እንዴትስ አትራሩም
😢
የማይፋቅ ስህተት _ በደም ስትፅፉ
እንዴት ሰው አጣችሁ_ የሚል ተው እረፉ
ዛሬ ቀን ቢስቅም _ አይቀርም ማኩረፍ
ወቅት አመቼን በሚል _ ድንበር አትለፍ
ቆይቶ ሰንብቶ _ ጊዜ ሲገለበጥ
የበደላችሁ መልስ
ቤታችሁ ይመጣል _ ካሁኑ በመብለጥ
#ፍትህ_በዝቋላ_በግፍ_ለሞቱት 🙏🙏
#ሼን ✍
6 776
#እባክህ_አንድዬ 🙏🇪🇹
ሁሉንም አድራጊው የበላዩ ዳኛ
ህመማችን ፀንቷል ላክልን መዳኛ
በክፋት ተነክረን ጨቅይተን በ በደል
እጅግ ቆሽሸናል ስራ ሁኗል መግደል
🙏 እባክህ አንድዬ 🙏
በማያልቅ እዝነትህ በምረትህ አፅዳን
'ሰው' ነት አላብሰን እውሬነቱ ይብቃን
#ሼን ✍
6 776
በብቻ ጓዳችን _ በእንባ በመራስ
.. ያለፍነውን ጊዚያት ..
ስለማያወራ አፍ አውጥቶ ትራስ
ማንም አይገባውመም ....
ከቀኑ ሳቃችን _ ፈገግታችን ጀርባ
ዕልፍ ህመም እንዳለ _ ሆድን የሚያባባ
ትራሱ ግን ያውቃል ..
ባይተነፍስም ቃል ...
#ሼን ✍
6 776
"ከባድ ነው ስሜቱ"
መጣ ያልከው ቀርቶ ደግ ያልከው ሲከፋ
አምነህ ያስቀመጥከው ከቦታው ሲጠፍ
ይወደኛል ባልከው ደረትህን ነፍተህ
በድንገት ስትደማ ልብህን ተወግተህ
ምንም ብትሆን ብርቱ
ከባድ ነው ስሜቱ ...
ማውጋት እየፈለክ ሲቸግርህ ሰሚ
ከቀድሞው ሳትሽር ሲያምህ በድጋሚ
ዙሪያህን ተከበህ አጂቦህ እልፍ ሰው
ልክህን ስታጣ ሆድህን ሲብሰው
ምንም ብትሆን ብርቱ
ከባድ ነው ስሜቱ ...
ማልቀስ አየፈለክ እንባህ ግን ሲደርቅ
የደላው ሊመስል ጥርስህ ደግሞ ሲስቅ
እንዴት ነህ ስትባል ታሞ ሳለ ጎንህ
ውጋቱን ደብቆ ደህ ነኝ ሲል አፋህ
ምንም ብትሆን ብርቱ
ከባድ ነው ስሜቱ ....
#ሼን ✍
6 776
ምስቅልቅል አድርገው ሰላም ሂወትህን
ትርጉም አሳጥተው የሂወት ግብህን
ልብህን ሰባብረው ውስጥህ አድምተው
በጊዜህ ቀልደው ተስፋህን ቀምተው
መልካም ሂወት እመኝልሀለሁ
ብለውህ ይሄዳሉ
6 776
የማፍቀሬኔ መጠን ልቤን ስለፈተሽክ
አንዴ ወዳኛለች _ የትም አቴድ ብለክ
እንዳሻህ እየሆንክ _ በስሜቴ አትስቅ
ዋጋዬን ዘንግተህ _ ሴትነቴን ስትንቅ
ካቅሜ በላይ ሁኖ መቻሌ ተሟጦ
ልቤም እነገሽግሾት ባንተ ተስፍ ቆርጦ
ያሳየሁህ እንደሁ ....
በወደድኩት መጠን መጥላት እንደምችል
መርሳትም እንደማውቅ የማሰቤን ያህል
ሌላ ሴት መስዬህ ...
እንዳትወዛገብ _ እንዳይገባህ ግራ
እስከዛው ድረስ ግን _ ደስ እንዳለህ ኩራ
#ሼን ✍️
👇👇
@seanlph
6 776
አንዳንዴ ደህና ነን የምንለው የእውነት ደህና ሁነን ሳይሆን አሞናል ብንልም ህመማችንን የሚረዳልን ስለሌለ ነው 🤔
ዝም የምንለውም የምናወራው ስለሌለን ፣ስላልተጎዳን ፣ ስላልቆሰልን፣ ስላልተገፋን አይደለም ቁስላችንን ብናወጋውም በኛ ቦታ ቆሞ በኛ ልክ ተረድቶ የሚያደምጠን ሰው ስለሌለ ነው 🤔
..... አንዳንዴ ተገለን ዳር የምንቆመው ብቸኛ የምንሆነውም ሰው ስለጠፋ አይደለም ለእኛ ልክ የሚሆን ፡ እኛን በእኛነታችን አምኖ የሚቀበል የራስ ሰው የምንለው ስለሚቸግረን ነው 🤔
#ደግ_ምሽት 🙏
@seanlph
6 776
እንባ ለሴት ብቻ _ የተሰጠ ያክል
ለሱ ነውር ሁኖ _ተደርጎበት ክልክል
ወንድ አይደለህ እንዴ _ እንዴት ታለቅሳለህ
ቆፍጠን በል እንጂ _ ምን እንዲህ አረገህ
እየተባለ አድጎ
ያን ልማድ አድርጎ
ብሶቱን ሀዘኑን _ ውጋቱን ሸሽጎ
ብዙ ወንድ ይኖራል _
ከፍቶት እንዳልከፋው _ እንባውን ዋጥ አርጎ
#ሼን ✍
6 776
........ ⏰🚶♀
የጊዜና እድሜ _ የሁለቱ ትርጉም
ለሴትና ለወንድ _ ፍፁም አንድ አይደሉም
ይሄን አትዘንጋ
ጊዜ ከወንድ ይልቅ _ ለሴቷ አለው ዋጋ
እናም እልሀለሁ .....
አብራህ ያለችን ሴት _ የእውነት ካልወደድካት
እቅድህ ካልሆነ _ ሚስትህ ልታደርጋት
ውስጥህ እያወቀው _ እንደማታገባት
አለሁልሽ እያልክ _ ባዶ ተስፋ አትሙላት
ያለፈው ይበቃል .....
ቀኗ ላይ አትቁም _ አትጋርድ እድሜዋን
ውበቷን አታርግፍ _ አትስረቅ አሁኗን
ማስመሰሉ ይብቃህ _ ከሂወቷ ውጣ
እሷም ቁርጧን ትወቅ
ሳይረፍድባት ትኑር _ የራሷን ሰው መርጣ
#ሼን ✍️
@seanlph
