fa
Feedback
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

رفتن به کانال در Telegram

የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com

نمایش بیشتر
1 719
مشترکین
-124 ساعت
-47 روز
-1430 روز
آرشیو پست ها
አንቺን ላለማሰብ - ሰይፈ ተማም.aac1.26 MB

እሺ እንዴትናችሁልኝ? አዲሱ አመት አያያዙ የተመቻችሁ ይመስላል ። የግጥም ውድድራችን ተጀምሯል እስከ እሁድ አስር ሰዓት ይቆያል ። ግጥማችሁን በ @Seifdman አድርሱኝ ። ከመሳተፍ ማንበብን የምትመርጡ ከሆነ ለ 👍 እንዲሁም ለ 👎 በመምረጥ አሸናፊ ግጥሞችን እንለይ ። በድምጽ የተቀዱም ካሉ እቀበላለሁ ። መልካም ውድድር ።

ጥንብ አንሳ በዘመነ ጥንባት ሰው ከሰው ተሻትቶ በረከሰበቱ ብዙኃን አሉና ሰውነታቸው ውስጥ ሞተው የሸተቱ ወይ ልብህን አንፃ ሙታኑን ቀስቅሳ ወይ ሆድህን ሙላ ሁንና ጥንብአንሳ @seifetemam #seifetemam

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 በዚህ አመት ደግሞ ሌላ ውድድር አዘጋጅቼላችኋለሁ በማንኛውም ርዕስ ላይ የተጻፈ የራሳችሁ ግጥም ። format: ርዕስ ፣ ግጥም ፣ የጸሃፊ ስም መልካም ዕድል!!! የሽልማቱን አይነት እና መጠን ከነገ ወድያ አሳውቃለሁ ። ልብ በሉ ተሸላሚ የሚሆነው በብዙ ሰው የተወደደው ብቻ ሳይሆን የ 👎 ምልክት የተሰጠውም ጭምር ነው ። ለመላክ @seifetemam የሚለውን በመጠቀም በቀጥታ አድርሱኝ ። በድጋሚ መልካም በዓል!!! 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ዘመነ... በድጋሚ ከአመራሩ ተባልተን ከየጎረቤቱ ተዋርፈን ሳሙና መምጠጥን ለምዶ ገላችን በመጋገሪያ ዕጦት ተደፍቶ ሊጣችን የዘር ሀረጋችን ሰፍሮ ከመታውቂያችን በበላይነት ስሜት ታመን በዘር ምጥ በሽታ . . . እንኖር ይሆን ፤ እንኖር ይሆን በዘመነ ማርቆስ ዘመነ...በድጋሚ በረከትአብ ፍ.

4 👍 4 👎 ቅድስት እና ፍሰሐ እየመሩ ነው

አበባዮሽ ስል ለምለም በል ደሃ ብንሸለም መብራት ብንሸለም ውሃ ፍሰሐ ተ.

መልካም የበአል ቀን ለሁላችሁ ። ውድድራችን 10 ሰአት ላይ ያበቃል ።

እባካችሁ ድምጽ በመስጠት የ👍 አና የ👎 አሸናፊዎችን እንለይ

እንቁጣጣሼ የኔ በአል እጓጓልሻለው እንደ እንቁላል ቅድስት በ.

እሺ..... እስካሁን ምንም ባለመቀበሌ ሽልማቱን ለማሳደግ ተገድጃለሁ ለ'👍' 25 ብር ለ'👎'ግን እዛው 5 ። በሏ....!

የአዲስ ቀን አብሳሪ ለብሩህ ተስፋ ዘማሪ የእንቁጣጣሽ ለዛ እና ጣእም ያለው የስንኝ ቋጠሮ በ @Seifdman ስማችሁን አክላችሁ ላኩልኝ ግጥም ሲጥም ላይ በብዙ ሰው የተወደደው የ15 ብር የሞባይል ካርድ ይሸለማል። ብዙ ሰው የ👎 ምልክት የሰጠው ደሞ የ5 ብር ካርድ ያገኛል ። እስቲ በአሉን አድምቁት ። እንኳን አደረሳችሁ!

እንኳን አደረሰኝ ከሰማዩ ጓሮ መላክ የቀደሳት የውሃ ጠብታ ከምድሩ ወለል የሰው ጥሬ እቃ የአፈሩ ሽታ መሬቴን ሳጸዳ ሳሳጥብ ከርሜ ሳሳሽ በበረዶ ክብሬን ሳንደባልል ባልነቃው ሃሳቤ ተሻግሮ ከማዶ የመራስ ወራቴን አሳልፌው ኖሮ ቀን ጨረስኩ እያለ በጉማጅ ወር አዝሎ ከነባዶ ቤቴ ልቤን ቀንላይ ጣለ . . . እንኳን አደረሰኝ! እንኳን አደረሰኝ እያወዛወዘ ደሞ እያገጫጨኝ አመት አለሁ ብሎ አመት እያሸሸኝ ውስኪ በብርሌ ብርንዶ በካቻፕ አደይ በግራፊክስ ቤት ሆኜ ቤት ጠፋኝ ቤት መምቻዬን ሳስስ ቤት ሆኜ ቤት አሻኝ ደግሞ ቤት መቀለስ ልጆቹን በትኜ ከመስኩም ከወንዙ ከጫካው ከጨፌ በረጠበ ሙዳይ ትንሽዬ ተስፋ ከቀን ላይ ጨልፌ እጠባበቃለሁ 'አበባ አየሁ' የሚል ለማበብ ነጥፌ አመት አለሁ ብሎ አመት እያሸሸኝ እያወዛወዘ ደሞ እያገጫጨኝ እን ኳን ደረሰብኝ እንኳን አደረሰኝ @seifetemam #seifetemam

መመለስሽን ሳስብ (በ ሰይፈ ተማም) 'አሁን ይብቃን' ብለሽ ተነስተሽ ስትሄጂ ልቤን መች ዘጋሽው በሬን ነበር እንጂ አንቺ የሌለሽበት ይህ የሰብ ስብስብ ምንም እንኳ ባይስብ አብዝቼ እኖር ጀመር መመለስሽን ሳስብ የቤቴ ደጃፉን ደረጃ ባፀዳ አቆሽሾ ሂያጅ ነው አይዘልቅም እንግዳ ኩሽናው ቢኮሸን ኦልፍኙ ቢፈለኝ ተመኝታው ላይ ነው እንቅልፌን የማገኝ መመለስሽን ሳስብ መምጣቴ እየታየኝ አይጠረቃም ሃሳብ ጭንቅላት ቦርጭ የለው መጣች ሄደች ብዬ ያልሆነ ምራየው መመለስሽን ሳስብ እንደው ቀድሞነገር አለመሄድሽ ነው ለልቤ ሚታየው እግርሽስ ባዳ ነው ይመጣል ይሄዳል ፍቅርሽን ወደድኩት መች ከልብ ይወጣል . . . . . . . . መመለስሽን ሳስብ እንዲህ ያረገኛል መመለስሽን ሳስብ ባሳብ ይበልጠኛል ያላጣሁት ልቤ እንዳዲስ ይገኛል @seifetemam #seifetemam

መሄድሽን ሳስብ ከህይወቴ መሄድሽ እኔን ግን አመጣኝ ከፍቅር መዝገብ ላይ ሰው ሁሉ እንዳላጣኝ መሄድሽ አልከፋም ፍቅር ላይ ካሰጣኝ ማነው ያለው ሆዴ? ከህይወቴ ስቴጂ ይጠፋል ወይ ገዴ? ያላንቺ ተሳትፎ አይደምቅም መውደዴ? ማነው ያለው ከቶ ኧረ ማነው እንዴ? መምጣትሽን ሳስብ የፀዳው ደረጃ ላንቺ ክብር ነፅቷል በያ በሱ ሂጃ ሰው አለምድም አልል የነገን እኔእንጃ መምጣትሽ ያመጣኝ መሄድሽ ያልገታኝ የመውደድ ታላቁ የፍቅር ኩረጃ ሆኜልሽ አለሁኝ መሄድሽን ሳስብ መታነበር ያልኩኝ ስትሄጂ ቀርቶ ሳቴጂም ነይና መውደዴን ላስኪደው ቀና አርጊኝ ቀና በሰማይ በምድሩ እንዳንቺ ባይኖርም በሳር በቅጠሉ ስምሽን ባትምም መሄድ አስደስቶት እግርሽም ቢያዘግም መምጣትሽ ባነቃው ይህ ቀጥቃጣ ቀልቤ መሄድሽ ሊያሰኬደኝ እጅግ ተቃርቤ ስንብት በእጄ ፍቅርን ግን በልቤ ….. መሄድሽን ሳስብ እንደህ ነው አንቺ ሴት መሄድሽ አይደል ወይ ያረጋገጠለት የኔም ልብ እንደሰው ፍቅር እንዳለበት @seifetemam #seifetemam

መምጣትሽን ሳስስብ ህይወቴ መምጣትሽ እኔኑ አምጥቶኝ መምጣትሽን ሳስብ እኔው ነኝ የመጣሁ ደረጃ ወልውዬ ኩሽናውን ኮሻኝ እዚህ እሚያመጣኝ ፈልጌ እንዳላጣሁ መምጣትሽን ሳስብ መምጣትሽ ተሰማኝ አገር እንደሰጡት አደብ እንደነሱት ከሰማያት መርጠው አንዱን እንደቸሩት ለዛውም በጥምቀት እንዳሽሞነሞኑት ́ሚያደርገኝ ፍቅርሽ ሲመጣ ተሰማኝ አቴጂበት ነገር ውጅንብር ጎዳና ካይኖችሽ ታየቶኛል ያለሽበት ቀና መጣሁ ስትይቀርቶ ሳትመጪም ነይና መምጣቴን ላምጣልሽ ቀና በዪቀና ስትመጪም ነይና ከከንፈርሽ ላውጋ ስትመጪም ነይና አይንሽን አይኔጋ ጣ́ምሽን ጣ́ሜ ጋ ጎህ እስከሚናጋ መምጣትሽን ሳስብ እንደዚህ ነው ሆዴ መምጣትሽ አይደል ወይ መምጣትሽን መውደዴ @seifetemam #seifetemam

ገራገር ገል የተሰበረ ገል ለጋ ገር ገራገር ያልቦረቀ ግልገል ካ'ለም ጋር ሲታገል 'ራሱን ያገኘው በመከራ ነበር መከራም ያጠናው አልነቃም ሲነከር ሰይፈ 2008 @seifetemam #seifetemam

ስህተቴ ያለፈውን ትቼ ከአሁን ጋር ለመኖር ከራሴ ስማከር 'አሁን' ጣዕም አለው ልብን የሚያሰክር 'አሁን' እውነታ ነው አለምን የሚያስር ብዬ ፎከርኩና ትናንትናን ትቼ ወደ ዛሬ መጣሁ ካለፈው ወጥቼ የሰበሰብኩትን ሳልይዘው በእጆቼ ግን በግዜ ቀመር ከቀደመው ሁሉ ዕልፍ እና ዐዕላፍ ጥቅሞች ነበሩ … … … ስህተት የሚባሉ @seifetemam #seifetemam

ኋላ የቀረን ኋለኞች “ፊተኞች ኋለኞች … ‘’ ልክነው አምነናል ከፊት የነበርነው ከኋላ ቀርተናል ግና ይህ ሰልፍችን ምነው ግፉ በዛ መጨረሻ ስንቆም ፊት አንሆንም ‘ሳ @seifetemam #seifetemam 2008

ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem - آمار و تحلیل کانال تلگرام @gitemsitem