fa
Feedback
Book for all Ethiopia

Book for all Ethiopia

رفتن به کانال در Telegram

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 881
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-147 روز
-2330 روز
آرشیو پست ها
photo content

ሳይኮሎጂው the spotlight effect ይለዋል!እዚህ መንደር በየቀኑ ይህንን ያህል ሰው ብሎክ አደረግኹ፣እንደዚህ ፎሎወር አለኝ፣ጀንጃኜ በዛ ቅብጥሴ የሚል ፖስት በአንድ ሰው ሲደጋገም ካያችሁ የዚህ ተፅእኖ ውጤት ነው! ቶማስ ጊሎቭች የሚባል ሳይኮሎጂስት በዚህ መስክ አንድ ጥናት አጥንቷል። ሰዎች ምንያህል በሰዎች እይታ ውስጥ ለመውደቃቸው ያላቸውን ግንዛቤ ለማዳበር የአንድ ሰው ፊት(ታዋቂ የሆነ) በትልቁ የተለጠፈበት ቲሸርት ለብሰው ወደሚማሩበት ክፍል ክፍለ ግዜው ከጀመረ በኋላ እንዲገቡ ተደረገ። ውጤት-በክፍሉ ውስጥ ከነበሩት ተማሪዎች ግማሽ ያህሉ ቲሸርቱን ሲያስተውሉ የዚህ ግማሽ የሚሆነው ግማሽ ወይም25% ብቻ ነው ሰውየው (ፎቶው)ማኒሎው መሆኑን ያስታወሰው እነሱም ከጥቂት ቀናት በኋላ ለባሹን ከነልብስ ፎቶው ከነመፈጠሩ ረስተውታል! የአክቲቪስቶቹማ ለጉድ ነው!ባለፈው እንዲህ ብዬ ነበር ይልሃል!እሱ ተሳስቶ ሰዉ ከሚተርፍ ሰው አልቆ እሱ ያለው ትክክል ቢሆን የሚመርጥ ይመስለኛል። ነውም!አንዳንዱ ከአርሽ የሚፖስት ይመስል ባለፈው እንዳጫወትኳችሁ እዚህ ዲዝኒላንድ ያለው መዝናኛ ብሎ ይጀምርልሃል!ደሞ ወረድ ስትል እንደምታውቁት ፀጉሬን መቆረጤ የፊት ገፅታዬን ቢለውጠውም ትልሃለች .... ይሄን እሳት ኑሮ ላስታም የሷን ፀጉር ልይ!ፎ! The truth is that real world is far less likely to give a shit bout you ስላንተ ሞት ራሱን ከመታመም ይልቅ በያዘው ራስ ምታት ምትክ አንተ ብትሞትለት የሚመርጥ ሰው ነው ዙርያህን የከበበህ! የመጠኑ መለያየት እንጂ everyone is Egocentric! ቼኾቭ የዛሬ 100 ጨርሶታል እኮ ሰውየው ሸቃላይ ነው ለፍቶ አዳሪ በአንድ አጋጣሚ በኃይል ያስነጥስና ቀና ቢል አንድ ጄኔራል ከፊቱ አለ! ጌታዬ አስነጠስኩብዎ እንዴ አይ ችግር የለም አረ!(የዛኔ ኮቪድ የለም) ግዴለም አስነጥሼቦታለሁ ኦኦ ችግር የለውም አልኩህኮ! ሊፈታው ነው! በቀን በሌሊት!በሽማግሌ! የዚህ ዝብዝብ ሁለት ገፅታዎችን ስናጤን አንዱ የሶልዲው ገፅታ መልካሙ ሲሆን ለምሳሌ You spill a drink at a party. You get a ወጥ stain on yourመብረቃዊ ነጭ t-shirt. Your forehead is breaking out on the day you have to do a presentation. Oh no. What will people think?Chances are, they won’t think anything.ሰለዚህ አትጨነቅ ሲሆን ሌላው ገፅታ ደግሞ The next time you get a pimple on your forehead, or buy a new pair of shoes, or post about how boring your day is, don’t expect anyone to notice. You are not so smart or special. አለቀ አትጨቅጭቁን ለማለት ጨቀጨኳችሁ! Ephrem Jemal

photo content

ፍቅርን በጥፊ…! የከርታታው ይሁዲ ተረት "ታሪክ" ሆኖ ሳነብ የመጀመሪያዬ ነው። እንጂ በሌጀንድ ደረጃ ብዙ ከተባለላቸው የተረት ገፀባህሪዎች ይህ ሰው አንዱ ነው። ጋሼ ስብሃት "በማስታወሻ" ላይ ስለዚህ ሌጀንድ ለዘነበ ሲያጫውተውም ሰምተህ ይሆናል። ነገር ግን ይህ ሰው ኢትዮጲያዊ መሆኑ እንደተፃፈ ሰምተህ ታቃለህ? Johannes Moschos የሚባል መነኩሴ በ 5ኛው ክፍለዘመን ከጥንታዊቷ ግሪስ በመነሳት መካከለኛው ምስራቅና አሌክሳንደሪያ ጭምር በመጓዝ በወቅቱ በነበሩ ገዳማት ውስጥ በመገኘት ገዳማዊ ህይወታቸውን ሲሰንድ ኖሮ " The Spritual Meadow " የተሰኘ መፅሃፍ አሳትሞ ነበር። በአሌክሳንደሪያ የገጠመው ይህ ነበር። " ራሱን በጨርቅ የሸፈነ ኢትዮጵያዊ መነኩሴ ገጠመኝ። አምርሮ ያለቅስ ነበር። እኔና አንተ ተመሳሳይ ፍርድ ነው የተፈረደብን አለኝ። ማነህ አንተ? በማለት ጠየኩት። እሱም " እኔ ስቃይን በመቀበል ለአለም ፍቅሩን እየገለፀ የነበው የሁሉን ቻዩን ፈጣሪ ልጅ የክርስቶስን ጉንጭ በጥፊ የመታሁት ሰው ነኝ። ዘላለማዊ እንክርትና ለቅሶ ተፈርዶብኝ ይሄው አለሁ " አለኝ … ---------- ለማንኛውም ያ ከርታታ ፍርደኛ • ፍቅርን ለማፍረስ የሞከርክ ዕለት • መስዕዋትነትን ያራከስክ ዕለት • በቅኖች የተዘባበትክ ዕለት • ደካሞችን ያጠቃህ ዕለት በአንተ ውስጥ ነፍስ ይዘራል። እርጅናም ሆነ ሌላ አይነካውም። ምክኒያቱም በየዕለቱ የሚሸከሙትና ግብሩን የሚያስቀጥሉለት ብርቱ እልፍ አላፎች እስከ ዳግም ምፅኣት ይኖራሉና። -- " እውነት እላችኋለሁ፣ እዚህ ከቆሙት ሰዎች መካከል የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስከሚያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አሉ። " እንዲል። ማቴ 16:28 ---- ፍቅርን በጥፊ አለማጋጨትህን በየቀኑ መርምረህ ራስህን አንፅ። ሱ አ

photo content

ባለፀጋው ( A rich man on possessions) -------------------- "አንድ ቀን እንዲህ በማለት ጠየኩት ። 'የመንፈስን ሰላም አገኝ ዘንድ ምን ማድረግ አለብኝ? ' እሱም ንብረትና ሀብቴን ለድሆች ሰጥቼ እንድከተለው ነገረኝ ።" . "ቤተሰቤ ውስጥ ሰባት ባሮች እና ብዙ አገልጋዮች አሉ ። አንዳንዶቹ በእርሻዬ እና በወይን ቦታዬ ሲሰሩ የተቀሩት መርከቦቼን በመያዝ ሀብቴን ያበዛሉ ። . አሁን ይሄን ሁሉ ንብረቴን ትቼ እንድከተለው ያሳስበኛል ። የኔ ቀርቶ ባሮቼና ቤተሰቦቻቸው ምን ሊሆኑ ነው? ወድቀው ፣ለማኞች መሆናቸው አይደለምን? እንዴትስ ለነሱ ማሰብ ተሳነው?? እርግጠኛ ነኝ ይህ ሰው የሀብትን ምስጢር አልተረዳውም ምክንያቱም እሱና ተከታዮቹ በሌሎች ስጦታ ስለሚኖሩ ሰው ሁሉ እንደዛ ይመስለዋል ።(He and his followers lived on the bounty of others. He thought all men should live like wise.) . እነሆ ተቃርኖ እና እንቆቅልሽ! ባለፀጎች ሃብታቸውን ለድሆች ከሰጡ ድሆቹ ባለፀጎች መሆናቸው ይቀራል??! ድሆችስ የባለፀጋ ገበታና ድስት የግድ ያስፈልጋቸዋል??! አንድ ቀን ዘፍኖ ሌላ ቀን ከሚያዝን አንበጣ ሁሌም በርትቶ ምግቡን የሚሰበስበው ጉንዳን አይሻልምን??!" ......... በማለት ይህ ባለፀጋ ተቃርኖ ያለውን ሀሳብ ያስቀምጣል ። ቀሪውን ለናንተ ንባብ ልተው ። --- ንባብ: - #JesusTheSonofMan በሚል ርዕስ የሊበኖሱ ባለቅኔ ሰዓሊና ፈላስፋ ካህሊል ጂብራን በ 1928 እኤአ ባሳተመው መፅሀፍ በኢየሱስ ዘመን በዙሪያው የነበሩ ሰዎችን ገፀ ባህሪ በማድረግ ስለእሱ ያናግራቸዋል። http://4umi.com/gibran/jesus/rich ሱ አ

photo content

ከዜን ተረቶች መሀል ስንመዝ ሳሙኤል በለጠ(ባማ) ጎን ለጎን ያሉ ሁለት ቤተ መቅደሶች ነበሩ፡፡ የሁለቱ ቤተ መቅደሶች ካህናት ተጣልተዋል፡፡ አይነጋገሩም፡፡ ለነገሩ እነዚህን ካህናት ለማለት እንኳ ይከብዳል፡፡ የይስሙላ ካህናት ናቸው፡፡ ስለዚህም ተጣልተው እርስ በርስ አይነጋገሩም፡፡ ሁለቱም ቤተ መቅደሶች ደግሞ ሁለት የሚላላኩላቸው ትንንሽ ልጆች ነበሯቸው ከገበያ አትክልቱን፣ ፍራፍሬውን ሌላ ሌላውን እንዲገዙ የሚልኳቸው እነዚህን ልጆች ነበር… እናም ካህናቱ ተጣልተው የለ እርስ በርስ አይነጋገሩም አይደል - ልጆቹንም እንዳትነጋገሩ ብለዋቸዋል፡፡ ልጆች ደግሞ ያው ልጆች ናቸው - ማውራት ይፈልጋሉ - ደግሞ የተከለከለ ነገር እንዴት እንደሚጥም… ስለዚህም አንድ ቀን አንደኛው ልጅ ሌላኛውን ልጅ እንዲህ ሲል ጠየቀው፣ “ወዴት ነው የምትሄደው ?” “ንፋሱ ወደ ወሰደኝ ቦታ” አለ ሁለተኛው ልጅ፡፡ እንግዲህ ይሄ ሁለተኛው ልጅ ቤተመቅደሱ ውስጥ መንፈሳዊ ክርክር ሲደረግ የሰማትን መመለሱ ነው…፡፡ ሥነ መለኮት ሲሰማ ስለሚውል በልጅነቱ ፈላስፋ ሆኗል… የመጀመሪያው ልጅ የሚመልሰው ጠፋው፡፡ ምን ይበል ? ዝም አለ፡፡ ያልጠበቀው መልስ ነበራ፡፡ ተናደደ…እናም ደግሞ ተፀፀተ - ‘መምህሬ ተው ሲለኝ ! እውነትም እነዚህ የሌላኛው ቤተ መቅደስ ሰዎች አደገኞች ናቸው፡፡ መጥፎዎች ናቸው፡፡ እኔ ‘ወዴት ነው የምትሄደው’ ብዬ ቀላል ጥያቄ ብጠይቀው እሱ የተራቀቀ ፍልስፍና ይመልስልኛል ?’ ልጁ ወደ ቤተ መቅደሱ ተመልሶ፣ “ትዕዛዝዎትን አፍርሼ አጥፍቻለሁ መምህር ሆይ …”አለ እናም የሆነውን ነገራቸው… “ኦ … ይሄማ አይሆንም” አለ መምህሩ በንዴት፣ “ማሸነፍ አለብህ፡፡ እንዳሳፈርህ ማሰፈር አለብህ፡፡ መቼም ቢሆን ከእነሱ ጋር በክርክር ተሸንፈን አናውቅም፡፡ አንድም ግዜ! ስለዚህም ነገ እዛው ቦታ ትጠብቀውና ‘ወዴት ነው የምትሄደው’ ትለዋለህ፡፡ እንደ ልማዱ ‘ንፋሱ ወደ ወሰደኝ ቦታ…’ ሲል፣ ‘ንፋሱ ባይነፍስስ… ምን ታመጣለህ ?’ ብለህ ታፋጥጠዋለህ” ልጁ በጣም ተደሰተ፡፡ ነግቶ ብድሬን በመለስኩ ብሎ እንቅልፍ ባይኑ ሳይዞር አደረ፡፡ ለሊቱን ሙሉ እንዴት ብሎ እንደሚጠይቀውና እንደሚያሳፍረው ያጠናትንን ሲደጋግም አደረ፡፡ በቀጣዩ ቀን በጠዋት መንገድ ላይ ሆኖ ልጁን ይጠብቀው ጀመር፡፡ ልጁ ሲመጣ “ወዴት ነው የምትሄደው ?” ሲል ጠየቀው፡፡ “እግሬ ወደ ወሰደኝ ቦታ” አለ ልጁ፡፡ ያልተጠበቀ መልስ፡፡ አሁንም ልጁ የሚመልሰው አጥቶ እንደሞኝ ፈዝዞ ቀረ፡፡ ምክንያቱም ያጠናት መልስ አሁን ለዚህች ጥያቄ አትሰራማ… ‘ምን አይነት መጥፎ ሰዎች ናቸው ግን እነዚህ የዛኛው ቤተ መቅደስ ሰዎች’ አለ ልጁ፡፡ ወደ ቤተ መቅደስ ተመልሶ ለመምህሩ የሆነውን ሁሉ ነገረው፡፡ “ችግር የለውም፡፡ የፈለገ ቢሆን ማሸነፍ አለብን፡፡ እርግጥ እነሱ መሰሪዎች ናቸው፡፡ ቢሆንም በክርክር ተሸንፈን አናውቅማ፡፡ ስለዚህ መሸነፍ የለብህም፡፡ ነገ እዛው ቦታ ትጠብቀውና፣ ‘ወዴት ነው የምትሄደው’ ትለዋለህ፡፡ ‘እግሬ ወደ ወሰደኝ ቦታ…’ ሲልህ ወዲያው ቀበል አድርገህ ‘ሽባ ሆነህ ብትወለድስ ኖሮ … በምንህ ትሄዳለህ’ ትለዋለህ አዎን እንዲያ ብለህ ታፋጥጠዋለህ” አለ መምህሩ፤ “እንጂ መሸነፍማ የለብህም” በቀጣዩ ቀን እዛው ቦታ መጠበቅ ጀመረ፡፡ ልጁ ሲመጣ፣ “ወዴት ነው የምትሄደው ?” አለው፡፡ "ሰላጣ ለመግዛት ወደ ገበያ እየሄድኩ ነው” አለ ልጁ… እሺ አሁን ልጁ ምን ይበል… ሕይወት እንዲሀ ነች፡፡ ጥያቄ አዘጋጅተህ ስትመጣ እሷ ትቀይረዋለች ምንጭ:-101 Zen Stories by Nyogen Senzaki Samuel Belete

photo content

photo content

አስፈሪው ነገር ሞት አይደለም። ከተካነው እና ከምንተካው በላይ ስናጣ ያ ከባድ ስጋት ነው። ዛሬ ደግሞ ታላቁን የሕክምና ሰው ተነጥቀናል። በሁሉም መንገዶች በሚባል ሁኔታ የተሳካ ህይወት የነበራቸው "እረኛው ሐኪም" ዛሬ የሉም። ትተውት የሄዱት አሻራ ትልቅ ነውና የሰላም እረፍት ያርፋሉ። እንደ ማህበረሰብ ልንተካቸው ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ስናስብ ብቻ ልባችን ዝቅ ይላል። ለሰው ልጆች ስላበረከቱት ነገር ምስጋነ አለን። ከታሪካቸው ያስተዋወቀችን አዜብ ወርቁን ጭምር እናመሰግናለን። "እረኛው ሐኪም" የተሰኘው በአዜብ ወርቁ የተተረጎመው ግለታሪክ ባሳለፍነው አመት ከወጡ ግሩም ንባቦች አንዱ ነው። ሱ አ

photo content

"አፍሪካውያን ለሁለተኛ ጊዜ በነጮች ተበልጠናል" ''ጆሞ ኬንያታ እንዳለው ከዘመናት በፊት ክርስትናን እየሰበኩና ስለሰማያዊ መንግስት እያወሱ 'የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያሉ በግራ ወንጌል አንግበው በቀኝ ጠመንጃ ጨብጠው ገቡ፡፡ የምድሩን ተውት አሉ'፡፡'ዋናው የሰማዩ ነው' አሉ፡፡ 'ቀኙን ሲያጉኗችሁ ግራውን ስጡ 'አሉ፡፡አመንናቸው፤ተንበርክከን ጭንቅላታችንን ደፋን፡አልፍተውን አላሽቀውን ሲጨርሱ በተርታ አሰልፈው ለባርነት ሸጡን፤ለዘመናት እንደ በግና ፍየል ጥጃና ግመል ወይፈንና ግመል ላትና ሻኛችንን ደንደስና ፍርምባችንን እያማረጡ ሸጡን፤ሸመቱን፡፡ "ዛሬ ደግሞ የተገላቢጦሽ ስለዲሞክራሲና ስለሰው ልጅ ሊሰብኩልን ተነሱ፡፡ ያለፈው ሁሉ ተረሳና የሰሩን ሁሉ ተዘነጋና ስለበጎውና ስለትክክለኛው መንገድ ሰባኪዎቹ ዛሬም እነሱ ሆኑ፡፡ ቃልኪዳናቸውን ሰብረው ወንጌልን በሰበኩበት አፋቸው ገበያ አውጥተው በዋጋ እንዳልተከራከሩብን ዛሬ ድጋሚ ቅዱስ መስለው 'ረከሳቹ 'አሉን፤' የሰው መብት አፍሪካ ተረገጠ' አሉ፡፡ 'አፍሪካ ውስጥ ዲሞክራሲ ድምጥማጡ ጠፋ አሉ'፡፡ እነ አምኔስቲ ኢንተርናሽናል የዛሬዎቹ ሚሽነሪዎች ሆኑ፡፡በግራ ዲሞክራሲን በቀኝ ብድርና እርዳታ ድጋሚ መጡ፤ 'የዲሞክራሲን መንገድ አዘጋጁ ፖለቲካውንም አቅኑ' አሉ፡፡ኢኮኖሚውን ተውት፤ ተደጋግፎና ተረዳድቶ መስራቱ፤'ስለማደጉ ስለመበልፀጉ አትጨነቁ'አሉ፤ስለኋላቀርነታችሁ አትመራመሩ አሉ፤ 'መጀመሪያ ዲሞክራሲ' አሉ መጀመሪያ 'የሰው ልጅ መብት'፤ 'መጀመሪያ የራስን እድል በራስ መወሰን' አሉ… የሚያሳዝነው ግን የኛ ድጋሚ መታለል ነው፤ድጋሚ መታለል ነው፤ ድጋሚ እየተንበረከክን ድጋሚ ጭንቅላታችንን እየደፋን መሆናችን ነው፡፡ "ቴዎድሮስ ከአንድ ምዕተ ዓመት በፊት ያለውን ታስታውሻለሽ በመጀመሪያ የሃይማኖት ሰባኪዎችን ትልካላችሁ፡፡ ቀጥሎ እነሱን የሚጠብቅ ቆንሲል፡፡ ቆንሲሉን ለመጠበቅ ደግሞ ወታደሮቻችሁን፡፡ በመጨረሻም አገራችንን ትወስዳላችሁ ነበር ያለው፡፡ የዛሬ ስልታቸው የተለየ አደለም፡፡ ዲሞክራሲን ይሰብኩናል፡፡ ቀጥሎ እሱን ማጠናከሪያ ብድርና ዕርዳታ ያጎርፉልናል፡፡ ብድርና እርዳታውን ውጤታማ ለማድረግ ተብሎ ደግሞ በኢኮኖሚያችን ገብተው መሪ ቀያሽ፤ደጋፊ አማካሪ፤ ፈላጭ ቆራጭ ይሆናሉ፡፡በመጨረሻ አድቅቀውን አላቁጠውን ሲያበቁ ተረጅ ተደጋፊ ለምኝ ተመጽዋች ያደርጉናል፡፡ እምቢ ካልንና ተንኮል ሸራቸውን ቀድመን ካወቅንባቸው እርስ በርስ በዘርና በሃይማኖት እያጎናተሉና እያስታጠቁ እያራገቡ ያጨፋጭፉናል፤ ሳንወድ በግድ ያንበረክኩናል፤ አንገታችንን ያስደፉናል፡፡ ሃቅን ሀሰቱን አማተው አገለባብጠው እኛኑ እራሳችንን ያስወቅሱናል፤ ሳናውቅ ሳንጠረጥር ነጭ አምላኪ ያደርጉናል፡፡ የነሱ ጨቋኝነት ወደጎን ተብሎ እኛኑ ጨቋኝና ተጨቋኝ ብለው ይለያዩናል፡፡ "አፍሪካውያን ለሁለተኛ ጊዜ በነጮች ተበልጠናል፡፡ ለዘመኑ ሃይማኖት ለዲሞክራሲ ለዘመኑ ሚሽነዎች ለነጭ ጋዜጠኞች ተበልጠናል፡፡ለዘመኑ የኢኮኖሚ ጦረኞች ለ አይ.ኤም.ኤፍ፤ለአለማ ባንክና ለሌሎች ተንበርክከናል፤አንገታችንን ደፍተናል፡፡ ዳግማዊ ሞት ሞተናል፤ዳግማዊ ትንሳኤ ያሻናል፡፡ "ሬሳው የሚሸትና የሚከረፋው ሬሳው ያልተማረውና ያላወቀው ምስኪን አፍሪካዊ አይምሰልሽ፡፡ በተማረውና አወቅን ሰለጠንን ብልነው ይብሳል ድሮም ጥቁር…ድሮም አፍሪካ… ብሎ ነገር በሚጀምረው አወቅሁ ባይ ስልጡን አፍሪካዊ ይብሳል፡፡ ሳንጠረጥር ሳናውቅ ሳንሰማ ሰልበውናል፡፡"… Page 162-163 Abenezer Gebeyaw

photo content

ጋሽ አየለ ማሞ ባለቤታቸውን በሞት ካጡ በኋላ ሃዘን ወርሷቸው ነበር። በህልማቸው ደጋግሞ የሚመጣው የሚስታቸውን ምስል ለረጅም ጊዜ የዘውትር ሰቀቀን ነበር። በአንኛው ቀን ጋሽ ጥላሁን ገሰሰ ሊጠይቃቸው ወደ ቤታቸው ሲዘልቅ በመንዶሊን ሙዚቃ እየተጫወቱ ነበር። ጋሽ ጥላሁን በጥሞና አደመጠው። ሲሰናበታቸው " ይህን ስራ እኔ ነኝ የማዜመው " ጋሽ አየለ ማሞ አላቅማሙም። ጥላሁን ገሰሰ ከልብ ፈልቆ የተሰጠውን ግጥምና ዜማ አዜመው። " ናፍቆቷ ነው ያስጨነቀኝ ሌት በህልሜ እየመጣ እየታየችኝ … ቁም ነገሯን ሳስብ በልቤ መርምሬ የረሳኋት ቆንጆ ትዝ አለችኝ ዛሬ ትቻት እሷም ረስታኝ ተራርቀን ሳለ ዛሬ ትዝታዋ ድንገት ከቸች አለ… " ------ ጋሽ አየለ ማሞ በሰላም ይረፉ ። ሱ አ

photo content

Fuck You Hemingway! Fuck your bullshit pattern. Let's do it. " አንባረቀች። በእንግሊዝ አፍ። የተጨራመተ ሽሮ መልክ ያለው ወረቀት ወዳለሁበት ወረወረች። የ 80 ውል አይደለም። ① ምን እንዲህ አደረጋት? ከለታት አንደኛው ቀን ላይ መለያየት እንዳለብን ነገርኳት። ምክኒያት ጠየቀች። በረጅሙ ተነፈስኩ። ልትረዳኝ እንደምትፈልግ ነገረችኝ። የሚነገር ነገር አልነበረኝም። "ሰለቸኝ" አልኳት። "ለአራተኛ ጊዜ የተፈጠረ ነው፣ አንቺ ላይ ብቻ አደለም ይህ የሆነው "፣ ምናምን በሚል ላባብላት ፈልጌ ነበር። ተውኩት። የምጠጣው ነገር ሲያልቅ ባለሁበት ፎቴ ላይ ተኛሁ። ርግፍ አድርጌ ረስቻታለሁ። ሲነጋ የሚደጋገመውን ወለፈንዴ የህይወት ጉድ እንደ አንዱ በመሆን ለመቀላቀል ብቻ ነው ምፈልገው። ከነቃሁ ማለት ነው። ② ከዚያ ምን አደረገች? አላለቀሰችም። ነፍራቃ ማንነት የላትም ለካ?! ትታኝ ተነሳች። አልኮል እያገሳሁ በግድየለሽነት ሳንኮራፋ ሙሉ በሙሉ ነቅታ ነበር። ምኝታ ቤት ገባች የግል ወንበሬ ላይ ተቀመጠች። መደርደሪያውን ገላመጠችው። አቧራ ውጦታል። ባልተለመደ ሁኔታ በአንደኛው ጥግ አቧራ የለም። 4/5 መፅሃፍቶች ደጋግመው ተነስተው ይጣላሉና ያ ቦታ ሸረሪት አልደፈረውም። በሁኔታው ተስባ ነበር ማለት ነው። አወረደቻቸው። የኤሚንግዌይ ስብስቦች ነበሩ። ዕልባት የተደረገበት ሳባት። አነበበችው። ስትጨርሰው ነግቶ ነበር። ③ ዕልባቱ ደረቴ ላይ የሆነ ወረቀት ወደቀ። ስድቧ ተከተለ። ጩኸቷ ሙሉ በሙሉ ከእንቅልፌ አነቃኝ። " Fuck You Hemingway! Fuck your bullshit pattern. Let's do it. " አንባረቀች። በእንግሊዝ አፍ። ወረቀቱን በግድየለሽነት አንስቼ ዘረጋሁት። ያው ነው። የገዛ ፅሁፌ። " ሞት የማይደፍረው በመሰለው በጉብዝናው ወራት ኤሚንግዌይ ቸኮላትና ሲጋር እያንጠለጠለ ፊት ተሰላፊ ለነበሩ የጣሊያን ጦር አጋሮቹ ምሽጋቸው ድረስ እየሄደ ሲያቀብል አንዲት ጥይት ትቦተርፈዋለች። ሞትን አምልጦ ለማገገም ታዲያ የ ነርሷ አግኔስ ፍቅር ረድቶት ነበር። እሷን እያሰበ ከአልጋ ወደ መሬት ረገጠ። ቆመ። በፍቅር አበደ። ወደ አሜሪካን ተመለሰ። በጥቂት ወራት ውስጥ ለመጋባትም ጭምር ወሰኑ። በወሰኑ በ2 ወራት ውስጥ ደብዳቤ ደረሰው። "ጣሊያናዊ ሎጋ አግብቻለሁ ፣እርሳኝ የኔ ኧረንስት! " የሚል። አሁን ደግሞ በ ንዴት አበደ። ጅልነቱን ሲረግም ቆየ። ቆየና ወሰነ። ድብቁ የኤሚንግዌይ ልቡናዊ ሚዛንን ለመጠበቅ የሚረዳው ህግ ይህ ነው። "abandoning a woman before she abandons" ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነን ልበል? --- ④ ወጥታ ሄደች። አልተመለሰችም። ማወቋ ሰላም አልሰጠኝም። ጥቂት ካዛጋኝ በኋላ እረሳታለሁ ብዬ ነበር። አ! አ! … ------------ From Old Notes ሱ አ

photo content

የገና ወግ:— ከጎጆው የሚሰማው ዘፈን -------------- በገና ዋዜማ ንጉሱ ሚኒስቴሩን ሁሌም እንደሚያደርገው ለከተማ እግር ጉዞ ይጋብዘዋል። በጎዳናው የሚታዩት ጌጦች በሙሉ ያስደስቱታል፣ ይሁንና ህዝቡ ለሌላ አላስፈላጊ ወጪ እንዳይዳረግ ሁለቱም ከሩቅ ሃገር የመጡ ነጋዴዎች በሚል ማንነታቸውን ሸሽገው ነበር የሚንቀሳቀሱት። የመብራቶቹን ውበት፣ የገና ዛፎቹን፣ በየቤቶቹ ደጃፍ ላይ የሚነዱትን ሻማዎች ፣ ስጦታ ዕቃ ነጋዴዎች፣ በዓሉን በምግብ ከተሞላ ጠረጴዛ ዙሪያ ለማክበር ከሚጣደፉ ወንዶች ሴቶችና ህፃናትን እየቃኙ በከተማዋ እምብርት ዙሪያ ተጓዙ። ሲመለሱ ድባቡ በተቃራኒው ለየት በሚል የድሆች መንደር አቋረጡ። መብራት የለም፣ ሻማዎችም፣ የጣፋጭ ምግብ መዓዛም አይሸትም። ሰው ያለበትም መንደር አይመስልም። ንጉሱ በየአመቱ እንደሚያደርገው ለሚኒስቴሩ በግዛቱ ላሉት ድሆች ከፍተኛ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳሰበ፣ ሚኒስቴሩም በአወንታ ራሱን ቢነቀንቅም በእለት ተዕለት አውድና ቢሮክራሲ ተመልሶ እንደሚረሳ ያውቅ ነበር። በድንገት ከአንድ የድሆች ጎጆ ሙዚቃ ሰሙ። የጎጆው ስንጥቃት ከመክፈቱ የተነሳ በውስጡ ምን እየተከወነ እንደሆነ ያሳያል። እናም ወደ ውስጥ ሲመለከቱ ግራ አጋቢ ክስተት ያያሉ። አካል ጉዳተኛ አዛውንት ጋሪው ላይ ተቀምጦ ያለቅሳል፣ ሙሉ በሙሉ የተላጨች ወጣት ሴት ደግሞ ትጨፍራለች፣ አይኑ ላይ ንዴት የሚንፀባረቅበት ወጣት ደግሞ ባህላዊ ዘፈን በድምፁ ይጫወታል። "ገብቼ ምን እያረጉ እንደሆነ ማወቅ አለብኝ "አለ ንጉሱ። በሩን አንኳኳ ፣ ሙዚቃው ቆመ፣ ወጣቱ ልጅ ወደበሩ ሲመጣ ይታያል። "ማረፊያ የምንፈልግ የሩቅ ሃገር ነጋዴዎች ነበርን። ሙዚቃ ስንሰማ እስካሁን እንዳልተኛችሁ ተረድተን ለዛሬ ማ ደሪያ ካለ በሚል ነበር መምጣታችን " "ከተማ ሄዳችሁ ማደሪያችሁን በሆቴል አድርጉ። እኛ ልንረዳችሁ አንችልም። ምንም ሙዚቃ ብትሰሙ ይህ ቤት የሃዘንና የስቃይ ጎጆ ነው። " "ምክኒያቱን ማወቅ እንችል ይሆን? " "ሁሉም በኔ ምክኒያት ነው።" በጋሪ ላይ የተቀመጠው አዛውንት። " የቤተመንግስቱ ፀሃፈ—ትዕዛዝ ይሆን ዘንድ ህይወቴን ሙሉ ልጄን ፅህፈት ሳስተምረው ነበር።ነገር ግን አንድመ የቅጥር ማስታወቂያ ሳይወጣ አመታት ተቆጠሩ። ትናንት ማታ አንድ ረብ የለሽ ህልም አለምኩ። መልዓክ ይገለጥና የከተማው ንጉስ ሊጎበኘኝ ስለሚመጣ የብር ፅዋ እንድገዛ ይናገረኛል። አነጋገሩ አሳማኝ ነበረና እንደ ቃሉ ላደርግ ወደድሁ። ፅዋውን መግዣ ግን ስላልነበረን የልጄ ሚስት ገበያ ወጥታ ፀጉሯን መሸጥ ነበረባት። ልጄና ሚስቱ የበዓል መንፈስ እንዲኖር በቤቱ እየዘመሩና እየጨፈሩ ነው ነገር ግን ዋጋ ቢስ ነው። ንጉሱ የብር ጥዋውን አየና ጥሙን የሚቆርጥበት ውሃ እንዲሰጡት ጠየቀ። ተሰናብቶ ከመውጣታቸው በፊት እንዲህ አላቸው። "ታውቃላችሁ፣ ሚኒስቴሩን ማውራት ችለን ነበር ዛሬ እና በሚቀጥለው ሳምንት ለቤተኘንግስት ፀሃፊነት ስራ ውድድር እንዳለ ሲያወራ ሰምተነዋል።" አዛውንቱ የሰማውን ባለማመን በቸልታ ሰምቶ ተሰናበታቸው። ይሁንና በማግስቱ ቤተመንግስቱ ለፀሃፊነት ቦታ ማስታወቂያ ማስለፈፍ ጀመረ። በተባለው ቀን ለዚህ እጅግ ተፈላጊ ባለማዕረግ ስራ ውድድር አዳራሹ በሰው ተሞላ። ሚኒስቴሩ ወደ አዳራሹ ዘለቀ እናም ተፈታኞች ብዕርና ወረቀት ያዘጋጁ ዘንድ አዘዛቸው። ቀጥሎ ፈተናውን እንዲህ ሲል አቀረበ። "የምትፅፉት ድርሰት ይህ ነው። ለምን ነበር አዛውንቱ የሚያነባው?፣ ፀጉሯን የተላጨችዋ ጉብል የምትጨፍረው? ያዘነው ወጣት የሚዘፍነው? " በአዳራሹ ማጉረምረምና ግራመጋባት ሰፍኗል ማንም ሰው ይሄን ታሪክ እንዴት መፃፍ እንደሚችል አያውቅም ፤ እንደነገሩ አዳፋውን ለብሶ በፈገግታ ታሪኩን መፃፍ ከጀመረው ልጅ ውጪ። ----------- Translated from : Christmas Tale : The music coming from the house December 24, 2018 by Paulo Coelho Translated by: Surafel Ayele