cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🙊ጠቃሚ መረጃ

አናንተን ይጠቅማል ብለን የምናሰበዉን የተለያየ መረጃ ከተለያየ የመረጃ ምንጮት share በማረግ ለናንተ የምናቀርብ መሆኑን በትህትና አንገልጳለን።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
706
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏 "ደስተኛ መሆን ከፈለክ ሲፈልጉህ ከሚያገኙህ ስትፈልጋቸው ከምታጣቸው ሰዎች ሙሉ በሙሉ ዕራቅ" የሰው ልጅ ሀዘን 99 በመቶ የሚሆነው የሚፈጠረው በእራሱ በሰው ልጅ ድርጊት ነው፡፡ ከእዚህ ውስጥ ደሞ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስዱት የእኔ የምንላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ለዛም ነው "በጣም የሚጎዳህ በጣም የምትወደው ሰው ነው" የሚባለው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ልክ እንደ ወባ ትንኝ ናቸው፤ እነሱ ሲፈልጉና ደስ ሲላቸው ብቻ አንተ ጋር ይጣበቃሉ፡፡ አንተ ስትፈልጋቸው ግን ርቀው ሂደዋል፡፡ እናም ሁሌ እንዳሳዘኑክና እንዳስከፉክ ይኖራሉ፡፡ እናም እንደዚህ አይነት ሰዎችን መራቁ ትልቁ መፍትሄ ነው፡፡ ✍ፈጣሪ ስንፈልገው የምናገኘው መልካም ጓደኛና ወዳጅ ይስጠን፡፡ 🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን🙌
نمایش همه...
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏 ✍ከመሞትክ በፊት ቀድመክ አትሙት✍ በድሮ ጊዜ ሁለት አገልጋዮች ትልቅ ጥፋትን ያጠፉና ለፍርድ በንጉሱ ፊት ይቀርባሉ፡፡ ንጉሱም የጥፋታቸውን ከባድነት ከተረዳ በኀላ ሁለቱም በሞት እንዲቀጡ ይወስንባቸዋል፡፡ ለመሞትም ሁለቱም መርዝ እንዲጠጡ ያዛል፡፡ እናም ለሁለቱም በዋንጫ ተቀድቶ ይሰጣቸውና ግጥም አድርገው ይጠጡታል፡፡ ከሰከንዶች በኀላ አንደኛው አገልጋይ እዛው ተንፈራፍሮ ይሞታል፡፡ አንደኛው ግን ምንም ሳይሆን ይቀራል፡፡ ለካ ንጉሱ ምንም እንኳን አገልጋዮቹ ከባድ ጥፋት ቢያጠፉም በሞት ሊቀጣቸው አላሰበም ነበር፡፡ ይልቁንም ምን ያህል መንፈሰ ጠንካራ መሆናቸውን ለመፈተን ሲል ሁለቱንም መርዝ ጠጥታችሁ ትሞታላችሁ በማለት ንፁ ወይን በዋንጫ እንደሰጣቸውና እንዲጠጡ ነበር ያደረገው፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳን የጠጡት ንፁ ወይን ቢሆንም አንደኛው አገልጋይ ገና መርዝ ጠጥቶ እንደሚሞት ሲነገረው ልቡ እና መንፈሱ ቀድሞ በመሞቱ ምንም መርዝ በሌለበት ወይን ጠጥቶ ሞቷል፡፡ ✍ወደ እኛ ህይወትም ስንመጣ ተመሳሳይ ነው፡፡ ብዙዎቻችን በየቀኑ በሚገጥሙን ጥቃቅን ውጣውረዶች የተነሳ ምንም የሚገድል ነገር በሌለበት ቀድመን እንሞታለን፡፡ ችግሮቻችን የቱንም ያህል የገዘፉ ቢሆንም የፈጠረን እና የማይተወን አምላክ ክንዶች ደሞ ከችግሮቻችን ሺ እጥፍ የበረቱና የገዘፉ መሆናቸውን እናስብ፡፡ 🙌መልካም የእረፍት ቀን🙌
نمایش همه...
የአሜሪካ የመረጃ ደህንነት ኤጀንሲ የመረጃ መረብ ጥቃት ደረሰበት....... የአሜሪካ መረጃ ደህንነት ኤጀንሲ የበይነ መረብ ጥቃት ሰለባ መሆኑ ተገለጸ። ኤጀንሲው የሃገሪቱ ትላልቅ ወታደራዊ ግንኙነቶችን ጨምሮ ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎችን የሚከታተልና የመረጃ ደህንነት ስርአቱን የሚቆጣጠር ነው። የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴርም የኤጀንሲው የኮምፒውተር ስርአት ላይ ጥቃት መድረሱን ገልጿል። በዚህ ሳቢያም የ200 ሺህ ሺህ ሰዎች የግል መረጃ ለጥቃት መጋለጡ ነው የተገለጸው። ለጥቃት ተጋልጠዋል የተባሉት መረጃዎች፥ ስሞችን እና የማህበራዊ ደህንነት ቁጥሮችን ያካተቱ መሆናቸውም ተገልጿል። ኤጀንሲው ለወታደራዊ የመረጃ መረብ ደህንነት እንዲሁም በውጊያ ቀጠናዎች ውስጥ የግንኙነት መረቦችን የመከታተልና የመቆጣጠር ሃላፊነትም አለበት። ከጥቃቱ በኋላም ኤጀንሲው ምርመራ ማድረጉን እና ችግሩን ለማስተካከልና ተጨማሪ ጥቃቶችን ለመከላከል እርምጃ መውሰዱን ገልጿል። ተፈጽሟል የተባለው የበይነ መረብ ጥቃት ዝርዝር ጉዳይ ባይገለጽም ኤጀንሲው ግን ስጋት ላይ መሆኑ ነው የተነገረው። [ BBC ~ FBC ]
نمایش همه...
አስደናቂ ጤና ነክ 40 እውነታዎች 1. ግማሽ ሊትር ደም በመለገስ ብቻ የአራት ሰው ህይወት ሊታደጉ ይችላሉ። 2. ሴቶች በአማካይ 4.5 ሊትር ደም ሰውነታቸው ውስጥ ሲኖር ወንዶች በአማካኝ 5.6 ሊትር ደም ውስጣቸው ይኖራል። 3. ሁሉም ህፃናቶች ሲወለዱ ቀለማትን መለየት አይችሉም። 4. ስታለቅሱ አፍንጫችሁ ፈሳሽ የሚያበዛው እንባችሁ ከአይናችሁ ወደ አፍንጫችሁ ስለሚሄድ ነው። 5. አይናችሁን ከፍታችሁ ማስነጠስ በፍፁም አትችሉም። 6. ወንዶች በአማካይ ከዕድሜያቸው ላይ አምስት ወር ያህል ፂማቸውን በመላጨት ያጠፋሉ። 7. ፀጉር እና ጥፍር የተሰሩት ከተመሳሳይ ንጥረ ነገር ነው። 8. ከ90% በላይ የሚሆኑ በሽታዎች የሚፈጠሩት እና የሚባባሱት በውጥረት ምክንያት ነው። 9. ሴት ልጅ በጡት ካንሰር የመያዝ እድሏ አልኮል አለልክ በመጠጣት ይባባሳል። 10. በየዓመቱ አሜሪካን ሀገር ከውፍረት ጋር የተያያዘ 300.000 ሞት ይከሰታል። 11. የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች 6.5 ዓመት ቀድመው ይሞታሉ፡፡ በቀን በአማካይ አንድ ፓኬት ሲጋራ የሚያጨስ ሰው በየአስር ዓመት ልዩነት ሁለት ጥርስ ያጣል። 12. ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ሙዚቃ ማዳመጥ ለምግብ ለመፈጨት ሂደት ጠቃሚ ነው። 13. የእንቅልፍ እጦት በሽታ የመከላከል አቅምን ይቀንሳል። 14. ከአርባ ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን የከፋ የአፍ ጠረን ችግር አለባቸው 15. ካርቦን ሞኖክሳይድ ከአስራ አምስት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሰው ሊገድል ይችላል። 16. በየዕለቱ ሰውነታችን ሁለት ሊትር ያህል ሀይድሮ ክሎሪክ አሲድ ያመነጫል። 17. ሳቅ ፍቱን የህመም ማስታገሻ (pain killer) እንደሆነ የህክምና ጥናቶች አረጋግጠዋል። 18. የእርጉዝ ጥርስ ጤንነት ያልተወለደውን ልጅ ጤንነት ሊወስን ይችላል። 19. ሴት ልጅ እርግዝና ውስጥ ስትሆን ሁሉም የስሜት ህዋሶቿ ከልክ በላይ ይነቃቃሉ። 20. መሳሳም የጥርስ መበስበስን ይከላከላል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው መሳሳም የሚፈጥረው ምራቅ የጥርስን እርጥበት መጠን ስለሚያስጠብቅ ነው። 21. ጡት ጠብተው ያደጉ ልጆች ጡት ሳይጠቡ ከማያድጉ ልጆ ይልቅ ሸንቃጣ ናቸው። 22. ነጣ ያለ ቆዳ ያላቸው ሰዎች ጠቆር ያለ ቆዳ ካላቸው የበለጠ ቆዳቸው ቶሎ ይጨማደዳል። 23. አለርጂ ያለባቸው ሰዎች በመሳቅ የአለርጂ መጠናቸውን መቀነስ ይችላሉ። 24. የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች የበለጠ ቆዳቸው ይጨማደዳል። 25. ጡት ጠብቀው ያደጉ ልጆች ጡት ጠብተው ካላደጉ ልጆች የበለጠ IQ ሊኖራቸው ይችላል። 26. በወር ሶስት ጊዜ ቸኮሌት መብላት ከልክ በላይ ከሚበሉና እንደውም ከማይበሉ ሰዎች የበለጠ ረጅም ጊዜ ለመኖር ያስችላል። 27. በአማካይ አንድ ሰው በአንድ ሌሊት ውስጥ 7 ህልም ይመለከታል። 28. አንድ ሰው በዕድሜ ዘመኑ በአማካይ የምድርን ዙሪያ ሁለት እጥፍ ያህል ይጓዛል። 29. አንድ ሰው በአማካይ በቀን 15 ጊዜ ያህል ይስቃል። 30. የአንድ አማካይ ሰው መዝገበ ቃላት ብዛት ከ5,000 እስከ 6,000 ነው። 31. የዓለማችን 10% ያህል ህዝብ ግራኝ ነው። 32. የሰው ልጅ አንድ ነጠላ ፀጉር ሶስት ኪሎ ግራም ክብደት መሸከም ይችላል። 33. ፈገግ ከማለት ይልቅ ኮስተር ማለት ብዙ ጡንቻ ይጠይቃል። 34. 1/3 የካንሰር ህመምን መከላከል ይቻላል። 35. በምታስነጥሱበት ወቅት ሁሉም የሰውነታችሁ ስራ ይቆማል ልባችሁን ጨምሮ። 36. የሰው ልጅ ጉበት ከአምስት መቶ በላይ ተግባሮችን ያከናውናል። 37. የልባችሁ መጠን የአንድ እጅ ጭብጣችሁን ያህል ነው። 38. በሳምንት ለሶስት እና አራት ሰዓት ያህል ፈጣን የእግር ጉዞ ማድረግ በልብ ህመም የመያዝ ዕድልን በ65% ይቀንሳል። 39. ከመሳሳም የበለጠ በመጨባበጥ ከሰው ወደ ሰው ሊተላለፉ የሚችሉ ብዙ ጀርሞች አሉ። 40. እንቅልፍ ከምግብ የበለጠ አስፈላጊ ነው፡፡ አንድ ሰው በእንቅልፍ እጦት ከምግብ እጦት አስቀድሞ ሊሞት ይችላል።
نمایش همه...
ጠቃሚ መረጃ
نمایش همه...