cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

الدعوة السلفية

الدعوة السلفية〰 ⬇ ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች ብቻ የሚገኝበት ቻናል https://t.me/Umuyahya_Bintmuhammed&Rozia ¶ َ~~® https://t.me/daawatusalfeyia قال تعالىٰ ®وَلَقَدْ بَعَثْنَا فٍي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولّاأَنِ اعْبُدُوا اللّهَ ...وَاجْتَنِنُوا الطَّاغُوتَ<<¶ َ

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
405
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

አቡ ሀቲም እንዲህ ይላሉ፦ ረሂመሁላህ አቅለኛ ሰው ተወኩሉን /በአላህ ላይ መመካቱን/አጥብቆ ይይዛል ሪዝቅን ሊሰጥህ ዋስትና በገባለት ጌታ ላይ፡ ተወኩል ከኢማን እሚገባ በመሆኑምጋር የተውሂድም ክፍል ከመግባቱምጋር ፡ ተወኩል (በአላህ ላይ መመካት ) ድህነትን ማጥፊያ ሰበብም ነው፡ በአላህ ላይ መመካትህ ለአካልህም ለልብህም መርጋጋት ያስገኛል ፡ /روضة العقلاء ٣٥٥/
نمایش همه...
በማጣትም በማግኘትም ውስጥ አላህን ሱብሃነሁ ወተዓላን ማመስገን መቻል ምንኛ መታደል ነው። አላህ ይወፍቀን https://t.me/daawatusalfeyia
نمایش همه...
الدعوة السلفية

الدعوة السلفية〰 ⬇ ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች ብቻ የሚገኝበት ቻናል

https://t.me/Umuyahya_Bintmuhammed&Rozia

¶ َ~~®

https://t.me/daawatusalfeyia

قال تعالىٰ ®وَلَقَدْ بَعَثْنَا فٍي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولّاأَنِ اعْبُدُوا اللّهَ ...وَاجْتَنِنُوا الطَّاغُوتَ<<¶ َ

የሴቶች መስገጃ ችግር ~ በዚህ ዘመን በስፋት ከሚታዩ ክፍተቶች አንዱ የሴቶችን መስገጃ ኢማሙን ወይም ቀጥታ ተከትለው የሚሰግዱ ወንድ ሰጋጆችን መመልከት በማይችሉበት ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ከመስጂዶች እየለዩ መስራት ነው። አላስፈላጊ ቅልቅልን ለመገደብ ጥንቃቄ ማድረጉ ተገቢ ነው። በነብያችን ﷺ ዘመን ሰዎች ወደ መስጂድ ሲገቡ ወንዶችም ሴቶችም የፈለጉትን በር ይጠቀሙ ነበር። ለወንድ የብቻ ለሴት የብቻ አልነበረም። ሁኔታው ግን በዚህ መልኩ አልዘለቀም። ምክንያቱም ኋላ ላይ ነብዩ ﷺ لو ترَكنا هذا البابَ للنِّساءِ "ይሄኛውን በር ለሴቶቹ ብንተወው" በማለት ከመስጂዱ በሮች ውስጥ አንዱን ለይተዋልና። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 571] . ይህንን የምጠቅሰው ቅልቅልን ለመገደብ ትኩረት መስጠቱ ተገቢነቱን ለማስታወስ ያህል ነው። በተለይ በዚህ የወንዱም የሴቱም ተቅዋ እጅጉን የቀለለ በሆነበት ዘመን የዒባዳ ቦታዎች ክፉ ስሜት በልብ ውስጥ የሚላወስባቸው ቦታዎች እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረጉ የሚወደስ ጥረት ነው። . ይሄ እንዳለ ሆኖ ኢማሙ በሶላት ውስጥ እያለ ቢሳሳት ወይም መብራት ቢጠፋ ወይም ሱጁድ የሚወረድባቸውን የቁርኣን አንቀፆች ቢቀራ በትክክል ያለበትን አይቶ ለመከተል በማይቻል መልኩ ከነ ጭራሹ በግድግዳ መለያየት ግን ብዙ ሰጋጅ ሴቶችን ለትርምስ ማጋለጥ ነው። ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ ቀላል አማራጮች ባሉበት ዘመን ላይ "የራሳቸው ጉዳይ" በሚል አንድምታ እርግፍ አድርጎ መተው ተገቢ አይደለም። አንድ ምሳሌ ልጥቀስ:- በአንድ መስጂድ ውስጥ ኢማሙ እያሰገደ እያለ ሱጁድ የሚወረድበት የቁርኣን አንቀፅ ቀራ። ሱጁድ የሚወረድበት አንቀፅ ከቀራን ሱጁድ መውረድ የተወደደ ነው። ነገር ግን ግዴታ ስላልሆነ መተውም ይቻላል። ኢማማችን ሱጁድ ወረደ። ወንዶች በቀጥታ እየተከታተሉ ስለነበር በትክክል ተከትለውት ሰግደዋል። ለካስ ሴቶች ዘንድ ችግር ተፈጥሮ ኖሯል። - ከፊሎቹ የተቀራውን ተከታትለው ስለነበር ኢማሙ ሱጁድ እንደሚወርድ አስበው ሱጁድ ስለወረዱ በትክክል ኢማሙን ተከትለዋል። - ከፊሎቹ ደግሞ ወይ የተቀራውን ስላልተከታተሉ ወይ ደግሞ ቢከታተሉም ሱጁድ ላይወርድ ይችላል በሚል ሊሆን ይችላል ሩኩዕ አድርገዋል። ኢማሙ ከሱጁድ እየተነሳ "አላሁ አክበር" ሲል ጊዜ ሩኩዕ ላይ የነበሩት ዘንድ ግርታ ይፈጠራል። ከፊሎቹ ኢማሙን ተከትለው ያጠናቃሉ። ከፊሎቹ ተነስተው አንድ ረከዐ ይጨምራሉ። ከፊሎቹ ... የፈለግኩት በንዲህ አይነት አጋጣሚ ጊዜ ወይም ኢማሙ ሲሳሳት ወይም መብራት ሲጠፋ የሚያስቸግርበትን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ቢያንስ ከፊት ያሉ ሰጋጆች እንኳ በቀጥታ ኢማሙን ወይም በቀጥታ የሚከተሉ ሰጋጆችን ማየት በሚችሉበት መልኩ መስገጃዎችን ማስተካከል እንደሚገባ ማስታወስ ነው። ወሏሁ አዕለም። = https://t.me/daawatusalfeyia የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewo
نمایش همه...
الدعوة السلفية

الدعوة السلفية〰 ⬇ ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች ብቻ የሚገኝበት ቻናል

https://t.me/Umuyahya_Bintmuhammed&Rozia

¶ َ~~®

https://t.me/daawatusalfeyia

قال تعالىٰ ®وَلَقَدْ بَعَثْنَا فٍي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولّاأَنِ اعْبُدُوا اللّهَ ...وَاجْتَنِنُوا الطَّاغُوتَ<<¶ َ

01:21
Video unavailableShow in Telegram
⛔⛔⛔⛔ከላይ ያለውን ቪድዮ ከፍታችሁ እየታባለ ያለውን በደንብ አድምጣችሁ ጥንቃቄ አድርጉ። አልሰማሁም ነበር አይሰራም⛔⛔⛔⛔ ⛔⛔⛔⛔ለሌሎችም ሼር አርጉላቸው
نمایش همه...
ይሄ ነው አቋማችን ወቅታዊ ጉዳይን የተመከለተ https://t.me/Muhammedsirage
نمایش همه...
ሙስሊማት ያልሆኑ ሴቶችን ማግባት ~ ~ ~ ~ ~ ለሙስሊም ወንዶች ከነ ጭራሹ ሃይማኖት የሌላቸውን ሴቶች ማግባት ፈፅሞ አይፈቀድላቸውም። ሙስሊማት ያልሆኑ ሴቶችን ባጠቃላይ ማግባትም እንዲሁ የተፈቀደ አይደለም። ከዚህ ተለይቶ የሚወጣው እራሳቸውን ከዝሙት የሚጠብቁ ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴቶችን (ኪታቢያት) ማግባት ብቻ ነው። ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴቶችን (ኪታቢያት) ማግባት እንደሚፈቀድ ግን ቁርኣን ውስጥ ተጠቅሷል። አላህ እንዲህ ይላል፡- (وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِنْ قَبْلِكُمْ) “ከነዚያ ከናንተ በፊት መፅሐፍ ከተሰጡት (አይሁድና ክርስቲያን) ሴቶች ጥብቆቹም (ልታገቧቸው የተፈቀዱ ናቸው።)” [አልማኢዳህ፡ 5] . ይህንን መነሻ በማድረግ ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች ጋር ጋብቻ የሚመሰርቱ ሙስሊም ወንዶች አሉ። ነገር ግን እዚህ ላይ የቁርኣኑን መልእክት በደንብ ማጤን ያስፈልጋል። ጋብቻ የተፈቀደው በመልካም ስነ ምግባር ከሚታወቁ እራሳቸውን ከዝሙት ከጠበቁ ሴቶች ጋር ነው። ይሄ ሁኔታ ባልተሟላበት ዝም ብሎ ልብ ስላዘነበለ ብቻ ወይም ፍቅር ላይ ስለወደቁ ብቻ የሚፈፀም ልቅቅ ያለ ህግ አይደለም። ስለዚህ የቁርኣኑን መልእክት ለስሜታዊ ዝንባሌያችን ምርኩዝ እንዳናደርግ መጠንቀቅ ይገባል። . በዚህ ዘመን ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦች ከጋብቻ በፊት ያለ ህይወታቸው እጅግ የተጨመላለቀ እንደሆነ በተጨባጭ እያየን ነው። ዝሙቱ ቀርቶ ከትዳር ውጭ መውለዱ እንኳ እንደ ‘ኖርማል’ እየተቆጠረ ነው። ሰፊ እውቅና ያላቸው ስብእናዎች ሳይቀሩ ህዝብ በሚከታተለው ሚዲያ ላይ ቀርበው “ትዳር የለኝም፣ ግን ልጅ አለኝ” ሲሉ ምንም አይሰቀጥጣቸውም። ልጅ እንዳላቸው የሚታወቁ ግን ትዳር ባለመመስረታቸው የተነሳ ዛሬም “ወይዘሪት እንትና” እየተባሉ የሚጠሩ ብዙ ናቸው። ባጭሩ ከትዳር በፊት የዝሙት ህይወት ማሳለፍ ብዙዎቹ ዘንድ ነውርነቱ ቀርቷል። እንዲያውም “ዝሙት” መባሉ ቀርቶ “ከጋብቻ በፊት ግንኙነት” እየተባለ ነው እየቀረበ ያለው። ይሄ ከጋብቻ በፊት ያለ ግንኙነት ምናልባት በስሱ ከተነቀፈም በፀያፍነቱ እየተኮነነ ሳይሆን ለቀጣይ ህይወት መሰናክል እንዳይሆን ያክል ብቻ ተራ የግል አስተያየት ሆኖ ነው የሚቀርበው። በዝሙትነቱ ሳይሆን ለሴቷ ከሚያስከትለው ጥቅምና ጉዳት አንፃር ብቻ ነው የሚቃኘው። ዝሙት፣ ማመንዘር ይህን ያክል ቀሏል። ቁርኣናችን ደግሞ ከመፅሐፉ ሴቶች ጋር ጋብቻን የፈቀደው “ከዝሙት የተጠበቁ መሆናቸው” ከታወቁት ጋር ብቻ ነው። ይሄ መስፈርት ባልተሟላበት ከነሱ ጋር ትዳር መፈፀም አይፈቀድም። ይሄ አንድ ነው። ሁለተኛ ልጆችህን በኢስላማዊ ስርአት የምታሳድግበት ሁኔታ መኖር አለበት። አንዲት ሙስሊም ያልሆነች ሴት ከዝሙት የተጠበቀችና ግብረ ገብ ብትሆን እንኳ በዚህ ዘመን ልጆችህን እርሷ በምትፈልገው እምነትና መንገድ ላይ ማሳደግ ብትሻ የሚያግዳት ገደብ የለም። በዚህ የተነሳ ልጆች እምነታቸው ሊቀየር ይችላል። ይሄ በተጨባጭ እየገጠመ ያለ ዘግናኝ ጥፋት ነው። ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች ጋር ትዳር ፈፅመው ከዚያ ልጆቻቸው የከፈሩ ስንቶች ናቸው? አንዳንዶቹ እንደዋዛ ልጆቹ 18 አመት ሲሞላቸው ሃይማኖታቸውን ይመርጣሉ ይላሉ። ይሄን ሁሉ አመት ኢስላምን አልተማረም፣ ሶላት የለም፣... ። በዚያ ላይ ለልጆች ከአባቶች ይልቅ እናቶች የበለጠ የቀረቡ ናቸው። ጊዜው አይነቱ የበዛ የሞራል ዝቅጠት የተንሰራፋበት ነው። በነዚህና መሰል ምክንያቶች የተነሳ ልጆቹ ኢስላምን የመያዛቸው እድል የመነመነ ይሆናል። እንዲህ አይነት ከባቢ ባለበት ደግሞ ሙስሊም ያልሆኑ ሴቶችን ማግባት አይፈቀድም። . ስለዚህ እነዚህ ሁለት መስፈርቶች ባልተሟሉበት ከመፅሐፉ ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም የሚፈቀድ አይደለም። ታላቁ የዘመናችን የሐዲሥ ሊቅ ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአባኒይ ረሒመሁላህ እነዚህን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች በመጥቀስ በዚህ ዘመን ከክርስቲያን ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም እንደማይቻል አጥብቀው ያሳስባሉ። [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር ቁጥር 523] እንዲያውም ኢስላም አላህን መፍራትና ግብረ ገብነት ያላቸውን ሴቶች እንዲያገቡ ነው ወንዶችን የሚያነሳሳው። ይህንን ህግ መጠበቅ ለራስም፣ ለቤተሰብም፣ ለሚወለዱ ልጆችም፣ ለሙስሊሙ ማህበረሰብም፣ ለኢስላምም ውለታ መዋል ነውና ተገቢውን ትኩረት ልንሰጠው ይገባል። = Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ። https://t.me/IbnuMunewor
نمایش همه...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

ሸይኽ ሑሴን ጂብሪል ማነው? የሸህ ሑሴንን ታሪክ የሚገልፀው አንድ ለናቱ ስራ ይሄው ቦጋለ ተፈሪ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ የጠቆመው ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ሰውየው ምናባዊ ይሁን እውነተኛ ሰው ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ፀሐፊው እንዲህ ይላል፡- “ሼህ ሁሴን የነቢዩ መሐመድ ተከታይ ነበሩ፡፡ ቢሆኑም እንደ እስላሞች ጫት አይቅሙም፣ ሶላት አያደርሱም፣ መስገጃ ቁርበት፣ ውኃ መያዛ ጦሌ አያንጠለጥሉም፡፡ እንደ ዓባይ ጠንቋይም መጽሐፍ አይገልጡም፣ ጠጠር አይጥሉም። ግን ሱረት (ሐቀኑር) ያሸታሉ፣ ብርዝ ይጠጣሉ፣ ፍርድም ሲፈርዱ ማለት የሚታያቸውን ሲናገሩ ብርዝ በፎሌ (በሽክና) ይዘው ነበር ይባላል። [ቦጋለ፡ 23] አያችሁ አይደል? ውዱእ እንኳ ያልነበረው ሰው ነው። በነገራችሁ ላይ መጽሐፉ አንዳንድ የሃገራችን ህዝቦችንና ቋንቋዎችን የሚያነውሩ ቆሻሻ ስንኞች አሉት። ይህም የሚያሳየን አቶ ቦጋለ አንዳንድ በብሄር ጥላቻ የታወሩ ሰዎች የገጠሙትን አሰስ ገሰስ እንደሰበሰበ ነው። እኔ እንዲያውም እራሱን ቦጋለን ነው የምጠረጥረው። በሸህ ሁሴን ትንቢት ስም የራሱን ቅርሻት ለቅልቆ ሊሆን ይችላል። በነገራችን ላይ ቦጋለ ተፈሪ ጥሩ ነጋዴ ነው። ይህንን ብሽቅ መፅሀፍ ከ15 ጊዜ በላይ በማሳተም በደምብ አድርጎ ቸብችቧል። ታዲያ ገበያው እንዳይቀዘቅዝበት የኋላ ኋላ አሪፍ ዘዴ ዘይዷል። የመጽሐፉ የኋላኛው እትሞች ላይ እነዚያ ትግሬውን፣ አሮሞውን፣ ጉራጌውን የሚያንቋሽሹ ፀያፍ ፀረ ህዝብ ስንኞችን አውጥቷቸዋል። ችግሩ ግን የሱን ፈለግ የተከተሉ አያሌ ቦጋለዎች መፈልፈላቸው ነው። ከቀደሙ ህትመቶች ላይ ያሉትን ጨምሮ የራሳቸውን ጅምላ ፈራጅ የሆኑ ፀያፍና መደዴ ስንኞችን በማከል በኢንተርኔት ይለቃሉ። ወገኔ ሆይ! የቦጋለዎች መጫወቻ አትሁን። እንዴት ከቦጋለ ያነሰ ግንዛቤ ይኖርሃል? ቦጋለኮ ቢያንስ 15 ጊዜ ይህንን ኮተት እያተመ ቸብችቦታል። ሞኝነት ብዙ ደረጃ አለው። እንደ ቦጋለ ባሉ ቂሎች በዚህ መጠን መታለል ግን የእውነት በጣም የሚያሸማቅቅ ነው። Ibnu Munewor https://t.me/daawatusalfeyia
نمایش همه...
الدعوة السلفية

الدعوة السلفية〰 ⬇ ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች ብቻ የሚገኝበት ቻናል

https://t.me/Umuyahya_Bintmuhammed&Rozia

¶ َ~~®

https://t.me/daawatusalfeyia

قال تعالىٰ ®وَلَقَدْ بَعَثْنَا فٍي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولّاأَنِ اعْبُدُوا اللّهَ ...وَاجْتَنِنُوا الطَّاغُوتَ<<¶ َ

እንዳትሆን ጠንቀቅ በል! أَفَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَهَهُ هَوَاهُ وَأَضَلَّهُ اللَّهُ عَلَى عِلْمٍ وَخَتَمَ عَلَى سَمْعِهِ وَقَلْبِهِ وَجَعَلَ عَلَى بَصَرِهِ غِشَاوَةً فَمَنْ يَهْدِيهِ مِنْ بَعْدِ اللَّهِ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ ((ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን፣ አላህም ከእውቀት ጋር ያጠመመውን፣ በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን፣ በዐይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው አየህን! ታዲያ ከአላህ በኋላ የሚያቀናው ማነው አትገሰፁምን)) (አልጃሢያህ፡ 23) 9. በኳስ ምክኒያት የራስህንም ሀላፊነት ያለብህን አካላትም ሐቅ እንዳትሸራርፍ፡፡ ሰርክ ኳስ እያሳደድክ በዚያ ሳቢያ ሀላፊነትህን ባግባቡ እየተወጣህ ካልሆነ አደጋ ላይ ነው ያለኸው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሁላችሁም እረኛ ናችሁ (ሀላፊነት አለባችሁ)፡፡ እያንዳንዳችሁም ስለእረኝነታችሁ (የተሸከማችሁት ሀላፊነት) ተጠያቂ ናችሁ) ይላሉ፡፡ መከታተሉ በጤናም ይሁን በትኛውም መልኩ እራስህንም የሚጎዳ መሆን የለበትም፡፡ አይደለም በቀልድና በዛዛታ ቀርቶ በዒባዳም እራስን መጎዳት አይፈቀድም፡፡ እስኪ ይህን ታሪክ አንዴ እንመልከት፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መዲና ሲገቡ ሰልማኑልፋሪሲን እና አቡ ደርዳእን ረዲየላሁ ዐንሁማ ወንድማማች አድርገው አቆራኟቸው፡፡ ሰልማን አቡደርዳእን ሊጎበኝ ቤቱ ሲመጣ ሚስቱ ኡሙ ደርዳእ ረዲላሁ ዐንሃ እራሷን ጥላ አያት፡፡ “ምን ሆነሻል?” አላት፡፡ “አይ ወንድምህ አቡደርዳእ ለዱንያ ደንታ የለውም” ስትል እንዲያ የሆነችበትን ምክኒያት ነገረችው፡፡ ወዲያው አቡ ደርዳእ መጣ፡፡ ለሰልማን ምግብ አዘጋጀለትና “ብላ እኔ ፆመኛ ነኝ” አለው፡፡ ሰልማን ግን “አንተ ካልበላህ የምበላ አይደለሁም” አለው፡፡ ከዚያም (ፆሙን አፍርሶ) በላ…፡፡ ሌሊቱ ሲመጣ አቡ ደርዳእ ለሰላት ተነሳ፡፡ “ተኛ” አለው ሰልማን፡፡ ቆይቶም ተነሳ፡፡ “ተኛ” አለው አሁንም፡፡ የሌሊቱ መጨረሻ ሲደርስ ሰልማን እራሱ “ተነስ” አለውና አብረው ሰገዱ፡፡ ከዚያም ሰልማን እንዲህ አለው “ለጌታህ ባንተ ላይ ሐቅ አለ፡፡ ለራስህም ባንተ ላይ ሐቅ አለ፡፡ ለቤተሰብህም ባንተ ላይ ሐቅ አለ፡፡ እያንዳንዱን ባለሐቅ ሐቁን ስጥ!!” አቡ ደርዳእ ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ሄደና የሆነውን ነገራቸው፡፡ እሳቸውም “ሰልማን እውነት ተናገረ” አሉ፡፡ (ቡኻሪ የዘገቡት ነው) እንግዲህ አስተውል ሰሐባው በኳስ ሳይሆን በዒባዳ እንኳን እራሱን መጠበቅ እንዳለበት ተነግሮታል፡፡ አንተስ? 10. በኳስ ምክኒያት አጉል ወገንተኝነትና ዘረኝነት ውስጥ አትግባ!! ዘረኝነት የመሀይማን መገለጫ ነው!! ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ((ተዋት! ምክኒያቱም እሷ (ዘረኝነት) ጥንብ ነችና!)) ይላሉ፡፡ 11. በኳስ ምክኒያት አጉል ቁጣ ውስጥ አትግባ፡- ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ምከረኝ” ያላቸውን ሰው (አትቆጣ!) ብለውታል፡፡ ደጋግሞ ሲጠይቃቸው ደጋግመው ((አትቆጣ!!) ብለውታል፡፡ “እከሌ ቡድን ተሸነፈ” ብሎ አጉል ብስጭት ውስጥ የሚገባን “ቂል” የሚለው ቃል በበቂ ሁኔታ ይገልፀው ይሆን?!! እኔ እንጃ! 12. አንዱን ቡድን ለመደገፍ በሚል ተልካሻ ሰበብ አታጨብጭብ! አትዝፈን! አትጨፍር፡፡ ዘፈን የተፈቀደው ውስን የሆኑ ክስተቶችን ምክኒያት በማድረግ ለሴቶች ብቻ ነው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡ (ሁለት ድምፆች የተረገሙ ናቸው!! የፀጋ ጊዜ መዝሙር እና የፈተና ጊዜ ዋይታ!!) “ወንድ ከዘፈነ ሴት ሆነ” ይላሉ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እና ሸይኹል አልባኒ አላህ ይማራቸውና፡፡ 13. ኧረ ከአቅል ሁን! ለመሆኑ ኳስ ሲከታተሉ ገደብ የለሽ ስሜት ውስጥ ስለገቡ ብቻ የሚሞቱ ሰዎች እንዳሉ ታውቅ ይሆን? ካላወቅክ በዚህ ላይ የተደረጉ ጥናቶችን አፈላልግ፡፡ “እከሌ ቡድን ተሸነፈ” ብለው እራሳቸውን የሚያጠፉ እንደሚያጋጥሙስ ይሰወርህ ይሆን? ብቻ ከኳስ ጋር በተያያዘ በየትኛውም ምክኒያት ህይወትህን ብታጣ ነገ አላህ ፊት መልስህ ምን እንደሚሆን ከወዲሁ አስብበት!! ጂሃድ ላይ አስደናቂ ጀብዱ ሲፈፅም ውሎ በደረሰበት ቁስለት ስቃዩን መቋቋም አቅቶት እራሱን የገደለውን ሰው ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የእሳት ነው!” ማለታቸውን አትዘንጋ፡፡ አንተ ከሱ የተሻለ አሳማኝ ምክኒያት ካለህ ቀጥልበት!! አስተውል! ሞት አማክሮ አይመጣም፡፡ 14. በኳስ ምክኒያት አንዱን በመደገፍ ሌላውን በመንቀፍ፣ ሌሎችን ለማናደድ፣ ወይም እንዲሁ በአጉል ብስጭት ፀያፍ ቃላትን አታውጣ! ዘወትር “ሐያእ” አይለይህ፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምን እንደሚሉ አስተውል! ((الْبَذَاءُ مِنَ الْجَفَاءِ, وَالْجَفَاءُ فِي النَّارِ, وَالْحَيَاءُ مِنَ الْإِيمَانِ, وَالْإِيمَانُ فِي الجنة)) ((ፀያፍ ቃላት መጠቀም ዋልጌነት ነው! ዋልጌነት ደግሞ ወደ እሳት ነው!! “ሐያእ” ከኢማን ነው፡፡ ኢማን ደግሞ ወደ ጀነት ነው!!)) ሸይኹል አልባኒ “ሰሒሕ” ብለውታል፡፡ (አስ-ሰሒሐህ፡ 495) 15. ኳስ ለመመልከት ብለህ ከአጅነቢ ሴት ጋር ተቀላቅለህ እንዳትቀመጥ፡፡ መቀላቀሉ ሌላው ቀርቶ ሰይጣናዊ ጉትጎታ ከሚቀንስበትም ቦታም አልተፈቀደም፡፡ ለሴቶች ከመስጂድ ይልቅ ቤታቸው እንዲሰግዱ መመረጡን ለመስገድ ከወጡም ሽቶ ሳይቀቡ፣ ሳይዋዋቡ መሆኑን አስተውል፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ከወንዶች የሰላት ሰፎች በላጩ የመጀመሪያው ነው፣ የከፋው ደግሞ የመጨረሻው (ለሴቶቹ የሚቀርበው) ነው፡፡ ከሴቶቹ የሰላት ሰፎች ደግሞ በላጩ የመጨረሻው (ከወንዶች የራቀው) ነው፡፡ የከፋው ደግሞ የመጀመሪያው (ለወንዶቹ የቀረበው) ነው” ማለታቸውን አስተውል፡፡ ሌላው ቀርቶ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወንዶችና ሴቶች ከመስጂድ ውጭ ከሰላት ሲመለሱ ቢቀላቀሉ ሴቶቹን “ወደ ኋላ ሁኑ” ብለው ዳር ይዘው እንዲሄዱ ነው የነገሯቸው፡፡ 16. ኳስ ለማየት ብለህ አስካሪ መጠጥ ከሚሸጥበት ወይም ከሚጠጣበት “ባር” እና “ካፍቴሪያ” ውስጥ ወይም ሌሎች ወንጀሎች ከሚፈፀሙባቸው አካባቢዎች ድርሽ እንዳትል፡፡ አላህን ፍራ! እምነትህንም እራስህን አክብር፡፡ ኢን ሻአላህ ከቻልኩ በዚህ ጉዳይ የኡለማዎችን ብይን አሰባስቤ ለመመለስ እሞክራለሁ፡፡ ~----~~ ---- (ኢብኑ ሙነወር፣ ሃምሌ 03/2006) የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
نمایش همه...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

وَيَقُولُ الْإِنسَانُ أَإِذَا مَا مِتُّ لَسَوْفَ أُخْرَجُ حَيًّا ሰውም «በሞትኩ ጊዜ ወደፊት ሕያው ኾኜ (ከመቃብር) እወጣለሁን» ይላል፡፡ أَوَلَا يَذْكُرُ الْإِنسَانُ أَنَّا خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ وَلَمْ يَكُ شَيْئًا ሰው ከአሁን በፊት ምንም ነገር ያልነበረ ሲኾን እኛ የፈጠርነው መኾኑን አያስታውስምን فَوَرَبِّكَ لَنَحْشُرَنَّهُمْ وَالشَّيَاطِينَ ثُمَّ لَنُحْضِرَنَّهُمْ حَوْلَ جَهَنَّمَ جِثِيًّا በጌታህ እንምላለን ሰይጣናት ጋር በእርግጥ እንሰበስባቸዋለን፡፡ ከዚያም በገሀነም ዙሪያ የተንበረከኩ ኾነው፤ በእርግጥ እናቀርባቸዋለን፡፡ https://t.me/daawatusalfeyia
نمایش همه...