cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ግጥምን እንግጠም✍

#ግጥሞች✍️ #ወጎች🗣️ #ቀልዶች 😄እና ሌሎችም የጥበብ ስራዎችን ለአስተይየት ለጥያቄ እንዲሁም ፅሁፍ ለመላክ @BEKITADE ካርድ ለመላክ እና ስፖንሰር ለማድረግ ለምትፈጉ +251 0912336736😁😁🤪🤪

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
205
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ድህነት አራቀኝ ድህነት አራቀኝ አሸሸን ካንቺ ጋ ወደ ልብሽ ጓዳ ትንሽ ሳልጠጋ ያኮቦኮብኩ መስሎኝ ተንጠራራሁልሽ ድህነት አዶንቁሮኝ ድሪቶ አረኩልሽ ያንቺ አስተሳሰብ ዝነጣ ፋሽን ነው ያንን ለሟሟላት ኪሴ አቅም የለው እስኪ እንደኔ ሁኚ እሩቁን እልሚ ግዝያዊውን ነገር ካንቺ አታስማሚ ያንቺ ስብእና በዚ ከተለካ እንኳንስ ሊጋገር ጥቂትም አይቦካ አሁንም የቀረብኩ የደረስኩ ሲመስለኝ የማይረብው ነገር ድህነት አራቀኝ @BEKITADE ✍✍✍በ በረከት ታደሰ @yokiyaye
نمایش همه...
ሂጂ ንኪው ሂጂ እቴ አትምጪ ልቤን ደስ ይላታል የወደደ ሞቶ ኧረ ማን አይቶታል እኔን የሚቆጨኝ ከንቱ ሰው ማፍቀሬ ለቃሏ ታምኜ ለሷ ስል መኖሬ እሷማ ............ ወዳጇ ሲበዛ መስሏት የጀገነች አሸሼ ገዳሜ ከስንቱ ጨፈረች በፀሀይ ወጥታ በጨረቃ ገባች ለሷ ፍቅር ማለት ተራ እንደ እቃቃ ልቧ ተሰውሮ ከላይ ብቻ ስቃ ታዲያ ትሂድ እንጂ መንገዱን ያቅናላት ረከሰች መሰል ፈላጊ በዛላት ገላዋን የራበው አፍቃሪ መሰላት መንገድ ወስዶ መላሽ ቢሆንም ግን ዳሩ ሂጂ አትመለሽ አይመችሽ ምድሩ በአዳም መታጀብ አይደለም መታደል እንደዛማ ከሆን ታላቅ ነች ኤልዛቤል ስፍራ የለምና ሰሚ ከኔ ደጂ ከቶ ላንገናኝ አትመለሽ ሂጂ @BEKITADE ✍✍✍ በ ፍሬ @yokiyaye
نمایش همه...
በወዝጋባው አለም በዚ በወዝጋባ በውዝግብግብ አለም ተለዋዋጭ እንጂ ቋሚ ነገር የለም በዚ በወዝጋባ ለኔ በሚል አለም ለራሱ ካልሆነ ለሰው ሚያስብ የለም በዚ በወዝጋባ ትርኪ ሚርኪ አለም ጣትን ቀሳሪ እንጂ ጥፋተኛ የለም በዚ በወዝጋባ ሸቀጥ አቋሚ አለም ለላይ ሚሆን እንጂ ውስጥ ገብቶ ሚያይ የለም በዚ በወዝጋባ በጨቀየ አለም ቤተ ሰሪ እንጂ አጋዥ አካል የለም በዚ በወዝጋባ ተናጋሪ አለም ቃላት ሸቃጭ እንጂ ለሀቅ የቆመ የለም እና ልንገራቹ አሁንም ደግሜ ያየሁትን ጓዶች እንድንጠነቀቅ እኛ እንዳንሆን መስዋቱን ከፋዮች በዚ በወዝጋባ አፈር ለባሽ አለም ያለ ይምሰል እንጂ ምንም ነገር የለም @BEKITADE ✍✍✍ በ በረከት ታደሰ @yokiyaye
نمایش همه...
ፍለጋ አንቺን ለማየት ስል ኩይሳ ላይ ወጣው ለመቆም ከማይመች ከዛ ከጎርባጣው አንቺን ለማየት ስል ወጣው ከጣራው ላይ ሳልቀምሰው ሳላየው የፍቅርሽን ሙዳይ አንቺን ለማየት ስል ከፎቅ አፋፍ ላይ ነኝ ያ ውብ ገፅታሽ ጎልቶ እንዲታየኝ አንቺን ለማየት ስል ገና እጓዛለው ያለኝን ሰውቼ እረጅም ነው ህልሜ መች በዚ አብቅቼ ከታየሽኝማ... ልውጣ ከ ዳሽን ላይ ወይንም ከፕሉቶ ከእቅፌ ላኑርሽ ሳልሰለችሽ ከቶ አንቺን ለማየት ስል..... @BEKITADE ✍✍✍በ በረከት ታደሰ @yokiyaye
نمایش همه...
እንከኔን ለማውጣት እናንተ እዳላችሁኝ አዲስ እንግዳ ነኝ ለሰው ግራ አጋቢ በቆመ አገዳ ያመሳስሉኛል ብለው ጆሮ ጠቢ ወንጂ ሆኜ ብገኝ አሉኝ ድቡልቡል ነህ ለሌላው ማታስብ ርህራሄ የሌለህ አዛሮ ሆንኩላቸው ስሜ እንዳይጠፋ ይኸው ጦፍኩላቸው ሰው ሁሉ ሲከፋ በመጦዝ ውስጥ ሆኜ ቀኑን ሳንቀላፋ እንከኔን ለማውጣት ከላይ ታች ሚለፉ አሉ የአዳም ዘሮች አሉ የሄዋን ዘሮች ስሜት ሚያከረፉ ልክ እንደ ሸንኮራ ቀለሜ ሲለያይ ወጣ ሲልባቸው በርካሽ ለወጡኝ ሎጬ መስያቸው @BEKITADE ✍✍✍ በ በረከት ታደሰ @yokiyaye
نمایش همه...
ለየቅል ስሚኝ እባክሽን ለየቅል ነው ስልሽ ምነግርሽን ሁላ በተግባር እየኖርሽ ምንኖረው ሌላ ቃላችን ለየቅል ውስጣችንም ዝሏል እየኖረ ለግል ሀኬት ብቻ አሳቢ ሸርን የሚበትን አንዳንዴ ደግ መሳይ ማይጨበጥ ሚፈትን ጨለማና ብርሀን የተጋጩ ለታ ለዓመል ይስቃል በጭፍን ፈገግታ የሌላው ማይጥመው ለግሉ ሚያቁላላ ቁሌቱን ሚደፋ ከሰራ በኋላ ቡናውን ማያወርድ ከፈላም በኋላ ወጡን አጠንዝቶ ደረቁን ሚበላ ይሄ ነው ተግባሩ የሰው ልጅ በሞላ ምሰሶን ይንዳል ዋናውን ቋሚውን መልሶ ይገነባል መሰረት እንዲሆን ስራውን የማያውቅ ማዘዝ የሚቀለው ብፌ ለመስራት ነው ጥጡን ሚፈትለው እና ልድገምልሽው ስሚኝ እባክሽን ለየቅል ነው ስልሽ ምነግርሽን ሁላ በተግባር እየኖርሽ ምንኖረው ሌላ ቃላችን ለየቅል ውስጣችንም ዝሏል እየኖረ ለግል @BEKITADE ✍✍✍ በ በረከት ታደሰ @yokiyaye
نمایش همه...
በአንድ ወቅት አንድ ባለ ፀጋ በአንድ አካባቢ ይኖር ነበር እናም የዚን ባለፀጋ ሀብት የተመኙ ሌቦች የባለፀጋውን እግር ጠብቀው አለመኖሩን ያዩና ቤቱ ያለውን ሀብትና ንብረት በጠቅላላ ይወስዳሉ። ነገር ግን አንድ ነገር አስቀርተውለት ነበር የሄዱት አልጋውን ብቻ ሆኖም ግን በጣም ተደሰተና እግዚአብሔርን አመሰገነ አምላኬ ሆይ ይሄን አልጋ ባያስቀሩልኝ ምን ላይ እተኛ ነበር ብሎ ነበር ያመሰገነው እኛ ሰዎችም ባጣነው ነገር ብቻ ሳይሆን ባለንም እናመስግን ። @BEKITADE @yokiyaye
نمایش همه...
ወዳጄ አትቸኩል ከመሬት ተነስተህ ሀብታም ካልሆንኩ እያልክ እሱ ላይ ለመድረስ ስራ እየተፀየፍክ እንዴት ታልማለህ ለራስህ ታኮ ሆነክ ጠመኔ ሰንቆ ፊደል ሳይጠቀጥቅ እህልን ሳይዘሩ ፍሬ እንደመጠበቅ ባለ እውቀት ለመባል ናሳንም ለመምራት ሁሉም ዝናን ይሻል እውቅናን ለማግኘት ግና ለሁሉም ነገር ² ከ እጫፍ ለመድረስ ለማግኘት መስላል ለመሮጥም ቢሆን መንደርደር ግድ ይላል @BEKITADE ✍✍✍ በ በረከት ታደሰ @yokiyaye
نمایش همه...
ይድረስ ለ.... የውስጤን ችግሮች ባንተ እረሳሁኝ ሺህ ጊዜ ወድኩህ ሺህ ጊዜ አፈቀርኩህ መካሻ እንዲሆነኝ አንተ ግን እራከኝ ላትመለስ እሮጥክ ትናንሽ ቀዳዳን መሸፈን አቅቶክ እኔ የማወራው ስላንተ ፍቅር ነው እኔ የማወራው ስላንተ ግርማ ነው እኔ የማወራው ስላንተ ጉብዝና እኔ የማወራው ስላንተ ቁንጅና ዳሩ ምን ያደርጋል እንደ ሀሳዊ መሲ ስታታልኝ ከረምክ ልቤን በጭጋጉ ሸፍነህ አኑረክ እሱ እልበቃ ብሎህ ሀማል አደረከኝ የፍቅርህ ወላፈን አፍኖ እንድገድለኝ የተራበው ልቤ ሀሴት የሚያደርገው ውቡ ደረትህ ላይ ተንጋሎ ሲኖር ነው እና አትንፈገው ይፈንጭ እንዳሰኘው እንደ አዲስ በቅሎ ገና እንዳልተገራው @BEKITADE ✍✍✍ በ በረከት ታደሰ @yokiyaye
نمایش همه...
bbbbbby.m4a1.30 MB
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.