cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ወራቤ[ ደርሶች እና ፈዋኢዶች ]

በሰለፊይ ኡስታዞች በሀገራችኝ በተለያዩ አከባቢዎች በሚገኙ መስጂዶች፣መርከዞች የሚሰጡ ደርሶች፣ኮርሶች፣ሙሓዳራዎች፣ እና የቁርዓን ተፍሲሮች እና ሙስሊሞችን የሚመለከት ልዩ ልዩ ወቅታዊ ጉዳዮች የሚለቀቁበት ቻናል ነው ። { وَقُل رَّبِّ زِدْنِى عِلْمًا } سورة طه : ١١٤ [ " ጌታዬ ሆይ! እውቀትንም ጨምርልኝ" በል። ] ሱረቱ-ጧሃ: 114

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
2 967
مشترکین
-524 ساعت
-47 روز
+8130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

🎊🎊በአይነቱ ልዩ የሆነ የWEL GO  ፕሮግራም 🎊🎊 🎉🎉🎓🎓በአይነቱ ልዩ የሆነ የዳዕዋ እና የተመራቂ ተማሪዎች WELL GO ፕሮግራም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ🎓🎓🎉🎉 🎓🎓እነሆ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ የዘንድሮ ተመራቂ ሙስሊም ወንድም እህቶቻችንን ምክንያት በማድረግ የፊታችን እሁድ ማለትም በ ቀን 11/09/2016 ዓ.ል ከ 2:30 ጀምሮ በ አይነቱ ልዩ የ ሆነ የዳዕዋ እና የ WELL GO ፕሮግራም አሰናድቶ ይጠብቃችኃል።🎓🎓 በፕሮግራሙ ከሚታደሙ እንቁ ተጋባዥ የሱና ዱዓቶች እና እንግዶች መካከል:- 🎋(ከአዲስ አበባ)🎋 ኡስታዝ ጂብሪል አክመል (ኢንጂነር) ኡስታዝ ኢብራሂም ሙሳ 🎋(ከወራቤ)🎋 ሸይኽ ኑረዲን ኸሊል ኡስታዝ ሙሀመድ ሰኢድ ኡስታዝ ኻሊድ ሙሀመድ 🎋(ከሻሸመኔ)🎋 ወንድም አብዱልመሊክ አደም 🎋(ከጂማ)🎋 ወንድም ሙባረክ ሙኽታር
🎋🎋በእለቱም የግጥም ፣ የሰነፅሁፍ እንዲሁም አጓጊ ሽልማቶችን የያዙ ጥያቄ እና መልሶችም ይኖራሉ።🎋🎋
🌳በአላህ ፍቃድ ከ Gc ተማሪዎች ብዙ ተሞክሮዎችን እንቀስማለን ፣ ዲናችንን እንማማራለን ፣ የማይረሳ ጊዜን አብረን እናሳልፋለን!!! N.B 1.በእለቱም የሻይ ቡና & የምሳ ፕሮግራም ተሰናድቶ ይጠብቃችኋል። 2. ዉድ ተመራቂ ተማሪዎች በእለቱ የፕሮቶኮል ጉዳይ ይታሰብበትhttps://t.me/wru_ms_officialgroup
نمایش همه...
Werabe university muslim students official group

ይህ ግሩፕ ትክክለኛው የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሲሆን፣ በግሩፑም፦ ➲ ሙስሊም ተማሪዎችን የተመለከቱ መረጃዎች ➲ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መስጂድ ስለሚደረጉ ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ ➩ የዳዕዋ ፕሮግራም ➪ የቂርአት እንቅስቃሴ ➪ ሌሎችም ዝግጅቶች ሲኖሩ የሚለቀቁ ይሆናል።👇

https://t.me/wru_ms_officialgroup

t.me/WRU_MSJ_Official_channel

👍 11 1
👍
نمایش همه...
//ብዙዎች ያለንበት አሳዛኝ እውነታ// በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡ ብዙዎቻችን ለጀነት መግቢያ የሚሆኑ መልካልም ስራዎችን እንድንሰራባቸው ተቆጥረውና ተለክተው የተሰጡንን ብርቅዬ የዱንያ ቀናትን እያባከንበት ያለው ሁኔታ በጣም ያሳዝናል! ብቻ ለሁላችንም አላህ ይድረስልን።ከተውሂድ ቀጥሎ የባሪያው መዳን መሰረት የሆነችውን ሰላት ጭምር በአለማዊ ጉዳዮች ሰጥመን መድረሷን እንኳን ሳናውቅ ጊዜዋ ገብቶ ይወጣል።አላህ ያላዘነልን በርካታዎች ደግሞ ጭራሽም አንሰግዳትም።ነገር ግን ለኛ ምንም አይነት ተጨባጭ ፈይዳ የማያስገኘውን፣ያውም የሌላ የጠገበ አለም ላይ ያለን የፈረንጅ እግር ኳስ ጫወታ ግን ገና ወራትና ሳምንት ሲቀሩት፣መች፣በዬትኛው ቦታ፣ማን ከማን ጋር እንደሚጫወት፣የምንደግፈው ቡድን ስንት እንዳሸነፈና እንደተሸነፈ፣ማን እንደሚመራ፣ከነ ተጫዋቾቹ የግል ሕይወትና ፕሮፋይል ሁሉ ሳይቀር ሸምድደን፣ለክርክር ብሎም ዘመድ፣አብሮአደጎቻችንና ባልደረቦቻችን ጋር ሳይቀር ባለን የድጋፍ ልዩነት ለመበሻሸቅ፣እዝሁ ሚዲያ እያመጣን እንቸከችካለን።ኢስላም ሀላል የሆነ መዝናኛን አይከለክልም።ነገር ግን አንድ ጥቅል የሆነ መርህ ኣለ፣እሱም፦ «ግዴታ ከሆኑ ነገሮች የሚያርቅ ማነኛውም ነገር ሀራም ነው።» የሚል ነው፣ተግባባን። ፈርድ ሰላት ለመስገድ መስጂድ ገብተን እንኳን ሱና መድገም ሞት እየመሰለን ጨንቆን ነው ከመስጂድ የምንወጣው።ስራችንን እየሰራን እንኳን በእጃችን ባለው ስልካችን በየ ቀኑ ለአምስት ደቂቃ የአላህን ቃል ቁርዓንን አናደምጥም፣መቅራቱንስ ብዙዎቹ ምክንያት ባይሆንም በተለያየ አስባብ አልችልም ወዘተ እንበል፣ማድመጥም ተስኖን ነውን?።ነገር ግን ወደ ስፖርቱ አለም ስንመጣ፣በአንድ ሳምንት ውስጥ ቢያንስ በትንሹ የአንድ የምንደግፈውን ቡድን አንድ ጫወታ ብቻ ለማየት ቅድመዝግጅቱን ሳይጨምር ሁለት ሰዓታትን እንቀመጣለን።ከዝያ አሸንፎ ከሆነ በፉከራ፣ተሸንፊ ከሆነም ደግሞ በውዝግብና ዝርጠጣ የምናባክነውን ጊዜ ብዛት ተውት።በቃ በዝህ ተጨባጭ በየ አመቱ ተጫዋቾቹ የሚፈልጉትን አለማዊ ጥቅም አግኝተውና አሳክተው፣ትናንት ሲጫወቱለት ከነበረው ቡድን ዛሬ ተቃራኒ ሆነው ሲገጥሙ፣ጥቅማቸውን ሲያሳድጉ፣አንተ ግን እዝያው ተቸንክረህ የንትና ደጋፊ ነኝ ትላለህ።ሙሉ የቡድኑ ስታፍ አንተ ዱንያ ስለመኖርህ እንኳን አያውቁም።ጊዜ እንደቀጠለ አይቀጥልምና አጀልህ ደርሶ ኣኺራ ሄደህ በምትቀበርባት ቅፅበት እንኳን ያ ቡድን ግጥሚያ ቢኖረው፣ስላንተ መኖርም ሆነ መሞት ስለማያውቅ ይጫወታል።ቆይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ! እንበልና የምትደግፈው ቡድን አንተ እንደምትፈልገው ተሳክቶለት ሁሌም አሸነፈ እንበል።እስቲ የአንተ ከፌሽታ ያለፈ ጥቅምህ ምንድነው? ከሚያገኘው ገቢ ያካፍልሃልን?። በድጋፍ መለያየት የተነሳ ከተደባደብከው፣ከተጣላሀው ዘመድህ፣ጓደኛህ ያስታርቅሃልን?።ይሄ ቁማር አስይዘው ቡድን የሚደግፉትን አይመለከትም።እየፃፍኩ ያለሁት የቀልብያ ሕይወት ላላቸው ሙስሊም ወንድሞቼ ስለሆነ።እባካችሁ! ለሁሉም ነገር ወሰን ሲኖረው ጥሩ ነው።በተለይ ከእግር ኳስ ጋር በተያያዘ አብዛኛው ትውልድ መረን የለሽ አካሄድ ውስጥ ነው።እንደዝህ ስንል ብዙዎች ስለ ስፖርቱ ስለማናውቅ ወይም ስለማይገባን ወዘተ ይመስላቸዋል።ይሄ የተሳሳተ አመለካከት ነው።አላህ ይድረስልን።በቀብር ስለ አላህ ተጠይቀህ በዱንያ የሱን ስምና ባህሪያት ሳታውቅ፣በነርሱም ሳታመልከው የሰጠህ ጊዜ አልቆ ኣኺራ ሄደህ አስበህዋልን? መልስህስ ምን ሊሆን ይችላል?።ስለ ዲንህ ተጠይቀህ፣ስለ ነቢያችን ተጠይቀህ።ለነዝህ መልስ የሚሆን ስራና እውቀት ሳትገበይ እድሜህን በኢንቶ-ፈንቶ ስላሳለፍከውስ ምክንያት ይኖርህ ይሆን!። ኢላሂ ኻቲማችንን አደራ። ✍️አቡ አብዲላህ ሙከሚል ከማል https://t.me/fewaidworabe
نمایش همه...
👍 13