cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Dire Dawa government communication affairs office

government organization

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 034
مشترکین
+824 ساعت
+277 روز
+14630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#Oduu "Eegatummaa irraa gara Oomishtummaatti, Walabummaa fi Kabajaa Guutuu biyyaaf" Mata duuree jedhuun Bulchiinsa Dirree Dhawaatti Ilaalcha eegatummaa keessaa baasuuf Waltajjiin marii gaggeefame. #DGC Caamsaa 21/2016 Sadarkaa biyyaalessaatti Hawaasa Ilaalcha eegatummaa keessaa baasuun Oomishaa fi Oomishtummaa dabaluuf kan jalqabame "Eegatummaa irraa gara Oomishtummaatti, Walabummaa fi Kabajaa Guutuu biyyaaf" Mata duree jedhuun marii gaggeefame irraa ka'uun Guyyaa arraa Caamsaa 21/2016 Bulchiinsa Dirree Dhawaatti Waltajjiin marii gaggeefame. Biyyi teenya Itoophiyaan ofirra dabartee Biyya Qaanqee Walabummaa biyyoota Afrikaaf qabsiifte Biyya Walabummaa fi Bilissummaan Uumamuu biyyi mirkaneesite Ilaalcha Deegaramtummaatiin akka hin dhabneef Paartiin Badhaadhina damee Dirree Dhawaa Gaggeesota giddu galeessaa fi ol'aanoon fayyadamtumaa hawaasaa mirkaneessuuf Hojiiwwan dandeesisan irratti waltajjiin marii gaggeessan. Gaggeesotni Dhimma Carraa hojii dargaggootaaf uumaman guddisuuf kutannoon hojjachuu Akka qabu waltajjii marii Guyyaa arraa Sa'aa boodaa gaggeefame irratti ibsameera Waltajjii kana irratti Kantiibaan Bulchiinsa Dirree Dhawaa Obbo Kadiir Juhaar Akka jedhanitti bara bajataa dhufu 2017tti carraa hojii dargaggoota dabaluuf hooggansi kutannoodhaan hojjechuu qabnaa jedhan. Waltajjii marii kana irratti dhimmoota bara bajataa 2017 dhufuu fi ji'oota Gannaa kana hojiiwan sochiidhaan raawatamuu qaban irratti Kan mari'atee fi Dhimma carraa hojii dargaggootaaf uumaman dabaluu, Sochii Barnoonni Dhalootaaf, Hojiiwwan Misooma Sululaa fi akkasumaas Oomishaa fi Oomishtummaa hawaasaa dabaluun hojiiwan raawatamuu qaban Sanadoonni mul'isan dhiyaatanii Mariin bal'aan irratti gaggeefameera. Muktaar Ahmadiin Suuraan: Salaam Ababaa
نمایش همه...
👍 3
#warka Waxaa la sheegay in SM 2017ka diirada lasaari doono shaqo abuurka dhallinyarada. #DGC /MIICAAD 21/2016 Kulan uu ujeedkisu yahay sidi looga wada tashan laha fikirka dulsaarnimada oo si heer qaran ah loo bilaabay hal kudhagna looga dhigay ‘’madax bannaanida iyo sharafta dalka oo dhamaystiran han kaga gudubno dulsaarnimada anago u gudbayna wax-soo-saar’’ ayaa waxaa kasoo qayb galay kulankani masuuliyinta ismaamulka ee heerarka kala duwan. Dalkeenani itoobiya ayaa hormuud u ah waddamada afrika dhanka madax bannaanida sidaa awgeed iyado laga duulayo in sumacada iyo meeqaamka wanaagsan ee uu leeyahay hoos u dhigmin ayaa waxaa la sheegay in ay masuuliyintu si ka go`naanshiyo leh door kooda uga qaataan kor u qaadida madax banaanida iyo jiritaanka qarankeena. kulan lagaga wada xaajood ah oo ay yeesheen maamulka sare iyo kuwa dhexe ee xisbiga barwaaqo ee ismaamulka dir dhabe ayaa lagaga wada hadlay sidi bulshada looga faa`idayin lahaa arrimaha bulshada. Maayerka ismaamulka diri dhabe mudane khadiir jawhar ayaa furitaanki kulanka sheegay in shaqooyinka xooga lasaari doono 2017ka iyo bilaha xagaaga ay ka mida yihiin xoojinta shaqo abuurka dhallinyarada, arimaha waxbarashada ee faca danbe, hawlaha daryeelka deegaanka iyo waxsoosarka dalaga beeraha.
نمایش همه...
#ዜና'' ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ለተሟላ ሀገራዊ ሉዐላዊነትና ክብር" በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር ከአስተሳሰብ ለመላቀቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሄደ #DGC ግንቦት21/2016 በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ''ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ለተሟላ ሀገራዊ ሉዐላዊነትና ክብር" በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው የምክክር መድረክ ተከትሎ በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ አስተዳደር ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመላቀቅ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሄደ ። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለአፍሪካ የነፃነት ቀንዲልን ያበራች ሀገር በመሆኗ የነፃነት እና የሉአላዊነት ተፈጥሮዋን በተረጂነት እሳቤ እንዳታጣው የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ መካከለኛ እና ከፍተኛ አመራሮች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደዋል ፡፡ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ለማሳደግ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በተካሄደው የምክክር መድረክ ተገልፃል። የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በንግግራቸው በመጪው በ2017 በጀት አመት የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ለማሳደግ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ በምክክር መድረኩ በመጪው 2017 በጀት አመት እና በክረምት ወራት በንቅናቄ ሊሰሩ የሚገቡ ጉዳዮች ዙሪያ የመከረ ሲሆን የወጣቶችን የስራ እድል ፈጠራ ማሳደግ፣የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ፣የተፋሰስ ስራዎች እንዲሁም የህብረተሰቡን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚተገበሩ የማስፈጸሚያ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጓል፡፡ በሰላም ለማ ፎቶ፡- ሰላም አበበ
نمایش همه...
#ዜና'' ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ለተሟላ ሀገራዊ ሉዐላዊነትና ክብር" በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር ከአስተሳሰብ ለመላቀቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሄደ #DGC ግንቦት21/2016 በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ''ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ለተሟላ ሀገራዊ ሉዐላዊነትና ክብር" በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው የምክክር መድረክ ተከትሎ በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ አስተዳደር ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመላቀቅ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሄደ ። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለአፍሪካ የነፃነት ቀንዲልን ያበራች ሀገር በመሆኗ የነፃነት እና የሉአላዊነት ተፈጥሮዋን በተረጂነት እሳቤ እንዳታጣው የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ መካከለኛ እና ከፍተኛ አመራሮች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደዋል ፡፡ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ለማሳደግ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በተካሄደው የምክክር መድረክ ተገልፃል። የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በንግግራቸው በመጪው በ2017 በጀት አመት የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ለማሳደግ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ በምክክር መድረኩ በመጪው 2017 በጀት አመት እና በክረምት ወራት በንቅናቄ ሊሰሩ የሚገቡ ጉዳዮች ዙሪያ የመከረ ሲሆን የወጣቶችን የስራ እድል ፈጠራ ማሳደግ፣የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ፣የተፋሰስ ስራዎች እንዲሁም የህብረተሰቡን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚተገበሩ የማስፈጸሚያ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጓል፡፡ በሰላም ለማ ፎቶ፡- ሰላም አበበ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.diredawacommunication.org ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/DDGCAB ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCQNCC5tcc6Jd9zCKcmzQ-eA ቴሌግራም፦ https://t.me/DDGCAB ትዊተር፦ https://twitter.com/DawaOffice በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
نمایش همه...

አረንጓዴ አሻራ ለኢትዮያውያን እንደ ባህል እስኪቆጠር ተግተን በመሥራት አረንጓዴ የለበሰች ኢትዮጵያን እውን አናደርጋለን ! ባለፉት ዓመታት በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች በመጀመሪያዉ ምዕራፍ ከ32 ቢሊየን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን የተተከሉት ችግኞችም በዘርፉ ሙያተኞች በተደረጉት ክትትል 90% ለመፅደቅ ችለዋል፡፡ የተፈጥሮ ሃብትና የሕይወታዊ ሃብት ጥበቃ ሥራ ሲጠናከርና ተከታታይነት ባለው መንገድ ሲሰራ ከአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ነጻ የሆነና መልካምድራዊ አቀማመጥን መሰረት ያደረገ አካባቢያዊ የአየር ንብረት እንዲኖር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ እድል ይሰጣል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ የተራቆተ መሬትና አከባቢ በኢኮኖሚ፤ በማህበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚኖረው ተጽዕኖ ቀላይ አይሆንም፡፡ የልምላሜ ስነ ልቦናዊ፤ ሠላም፤ ደስታ፤ ፍቅርና ተስፋዎችም ይሰጣሉ፡፡ በመጀመሪያው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመላ ሃገሪቱ በተተከሉ ችግኞች ቀደም ሲል ተራቁተው የነበሩና የአፈር መሸርሸር አጋጥሟቸው የነበሩ አከባቢዎች በአሁኑ ወቅት ወደ ቀድሞ ገጽታቸው እየተመለሱና መሬቱም እያገገመ መሆኑን የግብርና ባለሙያዎች ምስክርነታቸውን እየሰጡ ነው፡፡የአረንጓዴ አሻራ ሥራችን በተለያዩ ዘርፎች ውጤቶችን እያሳየን ነው፡፡ ተደጋጋሚ ድርቅ ሲያጠቃቸው የነበሩ አካባቢዎች ዝናብ ማግኘት ጀምረዋል፣ የጎርፍ አደጋን ለመቀነስ ተችሏል፣ የደረቁ ምንጮችና ሀይቆች እንደገና ቀድሞ ወደ ነበሩበት መመለስ ችለዋል፣ ለበጋና የመኽር እርሻ ተስማሚ የሆነ ዝናብ ማግኘት ተችሏል፡፡ከሥራ እድል ፈጠራነት አንጻር ለእንስሳት መኖነት፤ ለንብ ማነብ ፤ ለካርቦን ሽያጭና ለጎረቤት ሀገራት መልካም ጉርብትና እና የዲፕሎማሲ ግንኝነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በዘንድሮ 2016/17 በ132 ሺህ 144 ችግኝ ጣቢያዎች ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሩ ችግኝ ተዘጋጅቶ 6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል የቅድመ-ተከላ ዝግጅቶች በሁሉም አካባቢዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ 25 በመቶ የሚሆነው በአባይ ተፋሰሶች የሚተከል ይሆናል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ዝግጅትና ተከላ ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶች ሰፊ የስራ እድል እየፈጠ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በዘንድሮው የችግኝ ተከላ በ6 ሺህ 200 ተፋሰሶች የስነ-አካላዊ ስራ በመስራት በስነ-ህይወታዊ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ ለተከላ የተዘጋጁ ችግኞች ዘርፈ ብዙ ገቢ የሚየስገኙ አትክልትና ፍራፍሬ፤ ጥምር ደን፤ ለከተሜነት ዉበት የሚዉሉ እና ለደን የሚዉሉ ናቸዉ፡፡ ለሁለተኛው አረንጓዴ አሻራ ሁለተኛ ዓመት የአረንጓድ አሻራ ስኬት የሁላችንም ተሳትፎና ዝግጁነት ከወዲሁ ይጠበቃል፡፡ አረንጓዴ አሻራ ለኢትዮያዊያን እንደ ባህል እስኪቆጠር ተግተን በመሥራት አረንጓዴ የለበሰች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በጋራ ልንቆም ይገባል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
نمایش همه...
#ዜና የኢ.ሬ.ዴ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሊከፍት ነው #DGC ግንቦት 2016 የኢ.ሬ.ዴ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ቀደም ሲል ለድሬዳዋ አስተዳደር በውክልና ሰቶ የተለያዩ የልማት ስራዋች ሲያከናውን መቆየቱ ይታወሳል። ይህን የአሰራር ሂደት ለማስቀረት እና የሲቪል ማህበረሰብ ባለስልጣን የተቋቋመበትን አላማ በራስ አቅም ለመፈፀም በአስተዳደሩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በቀጣይ በመክፈት ለመስራት እንቅስቃሴዎች መጀመሩን የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ሐርቢ ቡህ ገለፁ። የሲቪል ማህበረሰብ ባለስልጣን ከአስተዳደሩ ጋር በቀጣይ የልማት ስራዎች ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ላይ ተደርሷል። የድሬዳዋን አስተዳደር ሞዴል ለማድረግ እንዲሁም ህብረተሰቡ ከልማቱ ቀጥተኛ ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲቻል እና ከመንግስት ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት እንደሚገባ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና ንግድ ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሐርቢ ቡህ ገልፀዋል። በቀጣይ በድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በመክፈት ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ጋር በመቀናጀትም በአስተዳደሩ የሚገነቡ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመከታተልና ለመገምገም እንዲቻልም ከፅፈት ቤቱ ጋር በጋራ እንደሚሰራ ተጠቅሷል። ከፌደራል መንግስት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት የሲቪክ ማህበረሰብን መፍጠር በዋናነት አላማ አድርጎ የሚሰራው ተቋሙ በአስተዳደሩ በፋይናንስ ተቋማት መካከል የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደርን በማቋቋም የተሳለጠ አሰራርን ተግባራዊ እንደሚደረግ የአስተዳደሩ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሐመድ ገልፀው በተቋማት ግንባታ ላይ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች እንደሚሰሩ ተጠቅሷል። የሲቪክ ማህበረሰብ ህብረት በሰው ሐይል ፣በቢሮ መገልገያና በማጠናከርም በቀጣይ ከአስተዳደሩ ጋር ለመስራት እንዲቻልም የድጋፍ ስራዎች እንደሚሰሩ የተጠቆመ ሲሆን በአዋጁ ላይ ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሠራት እንደሚገባ አቶ ሐርቢ ቡህ በማጠቃለያ አሳስበዋል። በኤደን ሳሙኤል ፎቶ፦ የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ
نمایش همه...
#ዜና በ 3ኛው ትውልድ ወደ ሪፎርም የገቡ ተቋማት የሪፎርም ትግበራቸው ተገመገመ #DGC ግንቦት 2016 በድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አማካኝነት ወደ 3ኛ ትውልድ ሪፎርም የመጀመሪያ ዙር የገቡ ተቋማት ቀሪ ስራዎች የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተገምግሟል ። በዚህም የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ በሪፎርም ትግበራ ሂደት የመሬት ልማት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር መዘርጋቱን በተመሳሳይም፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ባለስልጣን የደንበኞችን አገልግሎትን ለማዘመን ጊዜውን ያማከለ የህግ ማእቀፍ በማዘጋጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል። በአስተዳደሩ ወደ ሪፎርም የገቡ ተቋማት የህግ ማእቀፍ በማዘጋጀት የአደረጃት ስራዎቻቸውን በሰኔ ወር አጋማሽ ላይ ማጠናቅ እንደሚገባቸውም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ተናግረዋል ። የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አይር ሐጂ ኑር በበኩላቸው በአስተዳደሩ ባሉ ተቋማት ውስጥ በተጀመረው የሪፎርም ሥራ የአደረጃጀት መሻሻል መደረጉን ገልፀዋል ። የ3ኛው ትውልድ ሪፎርም ትግበራ ሂደት በአስተዳደሩ ዉጤት ማሳየቱን በማንሳት፤ የተጀመረው ክትትል እና ድጋፍ መጠናከር እንደሚገባው የጠቆሙት ደግሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ናቸው። በተጨማሪም በ3ኛው ትውልድ በመጀመሪያው ዙር ከገቡት 7 ተቋማት በተጨማሪ በሁለተኛ ዙር ወደ ትግበራ የሚገቡ 5 ተቋማትም የትግበራ ሂደቱን በተመለከተ በክቡር ከንቲባ አቅጣጫ ተሰጥቷቸዋል። በኤደን ሳሙኤል ፎቶ:-ሰላም አበበ
نمایش همه...