cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኢስላማዊ እውነታ

ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
11 355
مشترکین
+424 ساعت
+517 روز
+5430 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

02:33
Video unavailableShow in Telegram
ጣፋጭ አቀራር #27 ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን Click and like በቴሌ ግራም ለመከታተል https://t.me/islamictrueth በቲክቶክ ለመከታተል tiktok.com/@sadamsuleyman
نمایش همه...
«በጌታ ብታምን ትድናለህ» በአቡ ሀይደር በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው በሱናው መሰረት ቀኜን ይዤ በመንገዱ ዳር እየተጓዝኩ ሳለ አንድ ሰው ወደኔ መጣ፡፡ ከዛም፡- እሱ፡- ወገኔ ኢየሱስ ጌታ ነው! ለኃጢአትህ ዋጋ ከፍሎልሀል፡፡ አንተና ቤተሰቦችህም ብታምኑ ትድናላችሁ አለኝ፡፡ እኔ፡- ጌታማ አንድ አላህ ብቻ ነው፡፡ ከሱ ውጪ ማንም የሚያድን የለም፡፡ ደግሞስ ቅድሚያ ሰላምታ አይቀድምም ነበር? ሰላምታ የልብ መክፈቻ ቁልፍ እኮ ነው፡፡ እሱ፡- እሺ ወገኔ ሰላምህ ይብዛ እኔ፡- ሰላም ቀጥታን በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን እሱ፡- ኢየሱስ ይወድሀል፡፡ እኔ፡- እኔም በጣም እወደዋለሁ፡፡ እሱን ብቻም ሳይሆን ወላጅ እናቱን መርየምንም፡፡ እሱ፡- ታዲያ ከወደድከው ለምን አታምንበትም ወገኔ? እኔ፡- አላህ ከላካቸው ነቢያትና መልክተኞች አንዱ መሆኑን እኮ በሚገባ አውቃለሁ፡፡ አምኜም ተቀብያለሁ፡፡ ይህንንም ያስተማሩኝ ነቢዩ ሙሐመድ ናቸው፡፡ እሱ፡- እሱ የተላከው እንደሌሎቹ ነቢያት ለትምህርት ብቻ ሳይሆን ላንተ ኃጢአት ዋጋ ለመክፈልም ጭምር ነው፡፡ እኔ፡- ስለየትኛው ኃጢአቴ ነው ዋጋ የሚከፍልልኝ? እሱ፡- ከአዳም ስለወረስከው ኃጢአት ነዋ! እኔ፡- ከአደም ሰው ሁኜ፣ ሰዋዊነትን ባሕሪ ወርሼ ተወለድሁ እንጂ ኃጢአትን አልወረስኩም፡፡ ኃጢአት በውርስ የሚተላለፍ ንብረትና ቤት አይደለም፡፡ በግለሰቦች ነጻ ፈቃድ አማካኝነት ህግን በመጣስ የሚፈጸም ተግባር እንጂ፡፡ ስለዚህ ተሳስተሀል፡፡ እሱ፡- መጽሐፍ ቅዱስ እኮ በሮሜ 3፡23 ላይ ፡- ‹‹ሁሉ ኃጢአትን ሰርተዋል የእግዚአብሄርም ክብር ጎድሏቸዋል›› ይላል፡፡ እኔ፡- የአላህ ቃል ደግሞ በሱረቱል ኢስራእ ቁ 15 ላይ፡- ‹‹ኃጢአትን ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም›› በማለት የኃጢአት መወራረስ እንደሌለ ይገልጻል፡፡ አንተ ያቀረብከውም ቃል እኮ የሚለው ‹‹ሁሉ ኃጢአትን ሰርተዋል›› ነው እንጂ ‹‹ሁሉ ኃጢአትን ወርሰዋል›› አይደለም፡፡ እሱ፡- ታዲያ ከአዳም ኃጢአት ካልወረስክ ለምን ፍጹም ሰው አልሆንክም? እኔ፡- ኃጢአት ላይ የወደቅሁት በራሴ ደካማነት፣ በነፍሲያዬ አሳሳችነት፣ በጠላቴ ሸይጧን ጎትጓችነት፣ በዚህ ዓለም ብልጭልጭ ነገሮች በመሳቤና በመታለሌ ምክንያት ነው፡፡ ያ ነው ፍጽምናዬን ያፈረሰው እንጂ፤ ማንም ሰው በተፈጥሮው ከኃጢአት የነጻ ሁኖ ነው የሚፈጠረው፡፡ እሱ፡- ደግሞስ ለምን ትሞታለህ የወረስከው ኃጢአት ከሌለብህ? እኔ፡- የምሞተውም ቀድሞውኑ ዘላለም እንድኖር ስላልተፈጠርኩ ነው፡፡ በዚህ ምድር ላይ አላህ የፈጠረኝ አጭር የዕድሜ ቆይታን በመስጠት እሱን በብቸኝነት እንድገዛው እንጂ ዘላለም እንድኖር አይደለም፡፡ ዘላለም የምኖርበት ዓለም ገና ነው አልመጣም ወደፊት ይመጣል፡፡ እሱ፡- ሞት በአዳም ምክንያት የመጣ መሆኑን አታምንም ማለት ነው? እኔ፡- አላምንም ብቻ ሳይሆን የምልህ በአደም ምክንያት የመጣ ነው የሚለውም ፍጹም የተሳሳተ አመለካከት መሆኑን ጭምር ነው የምነግርህ፡፡ እሱ፡- መጽሐፍ ቅዱስ በሮሜ 5፡12 ላይ ‹‹በአንድ ሰው ምክንያት ኃጢአት ወደ-ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት›› ይላል እኮ? እኔ፡- በሮሜ 5፡12 ላይ ያለውን ሀሳብ የተናገረው ማነው? እሱ፡- ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ነው፡፡ እኔ፡- ቅዱስ ቁርኣን ደግሞ በሱረቱል ሙልክ 67፡2 ላይ ‹‹ያ የትኛው ስራችሁ ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ህይወትን የፈጠረ ነው›› በማለት ሞት በአላህ ዘንድ ቀድሞ የተወሰነ ፍርድ እንጂ የኃጢአት ውጤት እንዳልሆነ ይገልጻል፡፡ እሱ፡- በሱረቱል ሙልክ ላይ ያለውን ሀሳብ የተናገረው ማነው? እኔ፡- ፈጣሪ አምላካችን አላህ ነው፡፡ እሱ፡- ዋናው ኃጢአተኛ መሆንህን ማመንህ ነው፡፡ ታዲያ ለኃጢአትህ ዋጋ ማን ከፈለልህ? እኔ፡- የጌታዬ ይቅር ባይነት! እሱ፡- እንዴት? እኔ፡- ጌታዬ አላህ፡- ከቁጣው እዝነቱ፣ ከቅጣቱ ምሕረቱ የቀደመ አምላክ በመሆኑ፤ በኃጢአት ምክንያት ስወድቅ በዛው እንዳልቀር ተመልሼ እንድነሳ የተውበትን (ንሰሀ) በር ከፍቶልኛል፡፡ እንዲህም በማለት ውስጤን በተስፋ ይሞላዋል፡- "በላቸው፦ እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ አላህ ኃጢአቶችን በመላ ይምራልና። እነሆ እርሱ መሐሪው አዛኙ ነውና።" (ሱረቱ-ዙመር 53)፡፡ ይህ ነው የኔ ተስፋ!! እሱ፡- መጽሐፍ ቅዱስ በዕብራዊያን 9፡22 ላይ ‹‹ደም ካልፈሰሰ ስርየት የለም›› ስለሚል የግድ ለኃጢአት ደሙን በማፍሰስ ዋጋ የከፈለልህ ክርስቶስ ያስፈልግሀል፡፡ እኔ፡- አላህ ኃጢአቴን እንዲምረኝ፡- ኃጢአተኛ መሆኔን ማመኔን፣ እንዲሁም የተጸጸተና የፈራ ልብ ይፈልጋል እንጂ፤ ደም ማፍሰስ ለሱ ጉዳዩ አይደለም፡፡ ስለዚህም እንዲህ ይላል፡- ‹‹አላህን ሰጋዎቿም ደሞቿም ፈጽሞ አይደርሰውም፤ ግን ከናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርስዋል…›› (ሱረቱል ሐጅ 37)፡፡ አላህ የሚያየው ልባዊ ፍራቻን እንጂ መስዋእትን አይደለም፡፡ እሱ፡- ስለዚህ መሐመድ ያድናል እያልክ ነው? እኔ፡- ወዴት ወዴት ነው የምትሄደው? ደሞ ማነው መሐመድ? መሐመድ የኔ ወላጅ አባት ነው፡፡ ስለዚህ እሱ አያድነኝም፡፡ እድናለሁ ብዬ የምከተላቸው ግን ነቢዩ ሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነው፡፡ እሳቸውን በመከተሌ አላህ ያድነኛል በማለት በጌታዬ ላይ ባለ-ተስፋ ነኝ፡፡ እናም የሚያድን አላህ እንጂ ማንም አይደለም፡፡ እንዲህ ይላል ጌታችን፡- "እነዚያን የተጠነቀቁትን በማግኛቸው ስፍራ ሆነው አላህ #ያድናቸዋል፤ ክፉ ነገር አይነካቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም" (ሱረቱ-ዙመር 61)፡፡ እሱ፡- መጽሐፍ ቅዱሳችን ደግሞ በዮሀንስ ወንጌል 14፡6 ላይ ሲናገር፡- ‹‹ኢየሱስም፡- እኔ መንገድና እውነት ህይወትም ነኝ፣ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም›› ይላል፡፡ እኔ፡- ኢየሱስ ብቻውን አዳኝ ከሆነ፤ ለምን በሱ በኩል ወደ አብ መሄድ አስፈለገ? አዳኝ ወደ ሌላ የሚያድን ይወስዳል እያልከኝ ነው? ወይስ ኢየሱስ በዚህ መሀል የመልክተኝነት ሚናውን እየገለጸ ነው? እሱ፡- ኢየሱስና እግዚአብሄር አንድ ናቸው፡፡ በዮሀንስ ወንጌል 10፡30 ላይ ‹‹እኔና አብ አንድ ነን›› ይላልና፡፡ እኔ፡- ናቸው የሚባሉት እነማንን ነው? አምላክ እስከዛሬ ‹‹ነው›› እየተባለ እንጂ ‹‹ናቸው›› ተብሎ አይጠራም፡፡ ደግሞም በጠቀስክልኝ ጥቅስ ላይ እኮ ‹‹እኔና አብ አንድ ነን›› የሚለው የሚያመላክተው ሁለት መሆናቸውን ነው፡፡ ‹‹እኔ እና አብ›› የሚለው ከአንድ በላይ ስለሆኑ አይደል? እሱ፡- የሥላሴን ምስጢር መንፈስ ቅዱስ ካልገለጸልህ በስተቀር በሂሳብ ስሌትና በቃላት ፍልስፍና ልትረዳው አትችልም፡፡ ለማንኛውም ደህና ሁን ኢየሱስ ጌታ ነው! እኔ፡- አላህ አእምሮ የሰጠን ልናስተነትንበት ነው፡፡ መለኮታዊ ቃሉን ያወረደልን አንብበን ልንረዳው ነው፡፡ ስለዚህም እሱ ‹‹አንድ ብቻ›› መሆኑን በብዙ ቦታ ዘርዝሮ ነግሮናል፡፡ እኛም አንድ ብቻ ነህ እያልን እንገዛዋለን፡፡ ላንተም ሂዳያውን ለኛም ጽናቱን አላህ ይለግሰን፡፡ ና ወደ አላህ መንገድ ትድናለህና! ዒሳ ነቢይ እንጂ ጌታ አይደለም! https://t.me/islamictrueth
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) እንዲህ ይላሉ:- «አላህን የሚያስታውስ እና አላህን የማያስታውስ ምሳሌዉ እንደ ሕያዋን እና እንደ ሙታን ነው።» [ቡኻሪ ዘግበውታል] https://t.me/islamictrueth
نمایش همه...
በአላህ ላይ መመካት ላይ የተገነባ ሰዉ የሚከተሉትን ፍሬዎች ያፈራል! በአላህ ብቻ መመካት የእምነታችን አንድ ክፍል ነው። እኛ የተውሂድ ህዝቦች ነን። ተውሂድ (አላህን ብቻ መገዛት) የስብዕናችን፣ የባህሪያችንና የህይወታችን መሰረት ነው። 1) በራስ መተማመን፡- የተውሂድ ሰው ኃይልና ችሎታ ሁሉ ለአላህ ብቻ የተገባ መሆኑን ያምናል። ማንም ከአላህ ውጪ በምንም ሁኔታ ኢምንት ሊለግስም ሆነ ሊነሳ እንደማይችል ይገነዘባል። ይህም ልቡን በከፍተኛ ራስ መተማመን ይሞላዋል። የተውሂድ ሰው፣ ለሰው በማጎብደድና ለፍጥረታት በመስገድ ራሱን አያዋርድም። በሰዎች ስኬትም ቅጥ ባጣ ሁኔታ አይገረምም። ክብሩ መጠን አለው። ተውሂዱ ልቡን በቁርጠኝነት፣ በትዕግስትና በፅናት ሞልቶታል። በየትኛውም ችግር አይንቀጠቀጥም፤ እጁን ለዱንያ ፈፅሞ አያስገዛም። ፈፅሞ!! እምነቱ በአላህ ላይ ብቻ ነው። ይህ ሁሉ ለፈጣሪው እጁ በመስጠቱ፣ ተውሂድን ወደ መቀበሉ የለገሰው ድንቅ ስጦታ ነው። 2) መተናነስና ቁጥብነት፡- የተውሂድ ሰው ለህይወቱ የህሊና ልጓም ያበጃል። የልቅና ባለቤት፣ የስጦታዎች ለጋሽ፣ የሰጠውንም የሚነሳ አላህ ብቻ እንደሆነም ያውቃል። ትልቅም ይሁን ትንሽ፣ ይጥቀምም ይጉዳ፣ ይጨምርም ይቀንስ፣ ሞትም ይሁን ህይወት፣ ስኬትም ሆነ ውድቀት፣ ጤናም ሆነ ህመም፣ ሀብትም ይሁን ድህነት፣ የዚህች ዓለም ክስተት ሁሉ በፈጣሪው ፍቃድ እንደሚከወኑ ጠንቅቆ ይረዳል። ስለዚህ፤ አይኮራም። ስላዚህ፤ ማናለብኝነት ልቡን አያሳብጠውም። የተውሂድ ሰው ሁሌም አመስጋኝ፣ ሁሌም የጌታውን ፀጋ አዋቂ፣ ሁሌም ለአላህ የሚተናነስ ነው። 3) መልካም ስብዕና፣ ትዕግስተኝነትና ብሩህ አዕምሮ፡- አንድን ፈጣሪ ብቻ መገዛት መልካም ስብዕና ለመያዝ እጅግ ያስፈልጋል። የተውሂድ ሰው በአንድ ፈጣሪ ህግ ብቻ ይዳኛል። ለማንም ሰው አድሏዊ ውሳኔ አይሰጥም። ማንንም አይበድልም፣ በማንም ላይ ወሰን አያልፍም። ፍጥረታት ሁሉ የአላህ ብቻ እንደሆኑ ይገነዘባል። ይህም የብሩህ አእምሮ ባለቤት ያደርገዋል። ችግሮችን በትዕግስት ያልፍ ዘንድ ይረዳዋል። ምክንያቱም፤ ይሄ የዚህኛው ፈጣሪ ያኛው ደግሞ የሌላኛው የሚለው ንብረት የለውም። አዕምሮው ሰላም አለው። የመረበሽ ህይወት በውስጡ የለም። 4) ፍፁም ሰላምና መረጋጋት፡- የተውሂድ ሰው ጥላቻን አይወድም፣ ለምቀኝነትና ፀብም ቦታ አይሰጥም። መሠረቱ ሰላም ነው። ለራሱ ስኬት የሌሎችን ቀብር አይቆፍርም። የራሱን ቪላ ለመገንባት የሰዎችን ድንኳን አያፈርስም፤ ፀጥታን አያደፈርስም። ይልቁንስ፤ ከአላህ ዘንድ በተሰጠው ሰላም ይኖራል። ፍፁም እርካታ ያገኛል። እምነቱ ሁሌም እንዲለፋ፣ ጥሩን እንዲሰራና በአላህ እንዲተማመን ያግዘዋል። ድንቅ እምነት! ኢስላም! #ethio muslims ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከተሉን በቴሌ ግራም ለመከታተል https://t.me/islamictrueth
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ሶስት ነገራት ኹፍን ያበላሻሉ! 1) ጀናባ መኾን፡- የገላ ትጥበት ግድ ስለሚኾን፡ የዛኔ ኹፍ (ጫማው ወይም ካልሲው) ከእግር መውጣት ይኖርበታል፡፡ 2) ጊዜው መጠናቀቅ፡- ለኹፍ የተመደበው ሰአት ከተጠናቀቀ፡ ግለሰቡ ድጋሚ ኡዱእ ማድረግን ቢፈልግ፡ ኹፍፉን አውጥቶ የተሟላ ዉዱእ እግርን ከማጠብ ጋር አድርጎ ኹፍፉን በመልበስ ይቀጥላል እንጂ፡ ኹፍን ሳያወልቅ ላዩ ላይ በማበስ ብቻ መቀጠል አይችልም፡፡ የተሰጠው ጊዜው ተጠናቋልና፡፡ 3) ኹፍን ከእግር ማውለቅ፡- ግለሰቡ ኹፍፉን ከእግሩ ካወለቀ፡ ማውለቁ ብቻ የነበረውን ዉዱእ አያበላሸውም፡፡ በዚህ ዉዱእ ቀጣዩን ሶላት መስገድ ይችላል፡፡ የኹፍፉ ከእግር መውለቅ የሚያበላሸው ኹፍፉን (የማበሱን ስርአት) ብቻ ነው፡፡ ማለትም፡- ያወለቀውን ኹፍ ተመልሶ ካጠለቀው በኋላ ዉዱእ ቢፈታ ዉዱኡን በሚያደርግበት ወቅት ኹፍፉ ላይ ማበስ አይችልም፡፡ ቅድም ከእግሩ ስላወለቀው ኹፍ ላይ የማበስ ስርአቱ ተበላሽቶበታልና ኹፍፉን አውልቆ እግሩን አጥቦ ከዛም ኹፍፉን በማጥለቅ ድጋሚ አዲስ ስርአት ይጀምራል እንጂ ወላሁ አዕለም፡፡ (መጅሙዕ ፈታዋ ኢብኑ-ዑሠይሚን 11/179፣ መጅሙዑል-ፈታዋ፡ ኢብኑ ተይሚያህ 21/179)፡፡ ከአቡ ሀይደር ትምህርት የተወሰደ! ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን በቴሌ ግራም ለመከታተል https://t.me/islamictrueth
نمایش همه...
ማወቅና መረዳት ያለብን የእስልምና እውቀት! አምስቱ እጅግ አስፈላጊ ነገሮች! ተግባራችን ተገቢ ወዳልሆነ ተግባር ቢያሰማራንም የሰው ልጅን ነፍስ መጠበቅ እንደሚኖርብን አላህ አዞናል፡፡ እነዚህ አምስት ነገሮች ሰው ተገቢ በሆነ መልኩ ይኖር ዘንድ የሚያስፈልጉ ወሳኝ የሆኑ ጥቅሞች ናቸው፡፡ ለሁሉም መለኮታዊ ህግጋት የተደነገጉት እነዚህን ነገሮች ለመጠበቅና እነዚህን ተቃርነው የተገኙ ነገሮችን ለመከላከል ነው፡፡ እስልምና የተደነገገው፤ አንድ ሙስሊም ለዱንያዊ ሆነ አኼራዊ ህይወት በዚህ ዓለም ላይ ተረጋግቶ ይሰራ ዘንድ፤ እነዚህን አምስት ነገሮች ለመጠበቅና ለመንከባከብ ነው፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የሚኖረው፤ እርስ በርሱ ተደጋግፎ እንደቆመ ግንብ በመተሳሰር ነው፡፡ አንዱ አካል ሲጎዳ ሌላውም ጉዳቱ በትኩሳትና በእንቅልፍ ማጣት እንደሚሰማው እንደ አንድ የሰውነት አካል ሆነው ይኖራሉ፡፡ ይህንኑ መጠበቅ የሚቻለው በሁለት መንገድ ነው። በመገንባትና በመንከባከብ 1) ሃይማኖት:- ማለት አላህ ሰዎችን ለዚሁ ዓላማ ሲል የፈጠረበትና ታላቅ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ መልእክተኞች የላከውም ይህንኑ እንዲጠብቁ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል "በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትንም ራቁ በማለት መልእክተኛን በእርግጥ ልከናል" (አል-ነሕል 36) የሃይማኖትን ብፁዕነት የሚያቆሽሹና እንደ ሽርክ፣ ከንቱ እምነት፣ ወንጀልና ኃጢአት የመሳሰሉ ነገሮች ሃይማኖትን ለመጠበቅ ሲባል ኢስላም ተከላክሏቸዋል፡፡ 2) አካል፡- ተግባራችን ተገቢ ወዳልሆነ ነገር ቢያሰማራንም የሰው ልጅን ነፍስ መጠበቅ እንዳለብን አላህ አዞናል፡፡ በአስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ እስከ ሆንን ድረስ አላህ ለእኛ ምህረትን ይለግሰናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል:- "ሽፍታና ወሰን አላፊ ሳይሆን(ለመብላት) የተገደደ ሰውም በርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡” (አል-በቀራህ 173) የራስን ነፍስ መግደልና መጉዳትንም ከልክሏል፡፡ እንዲህ ይላል:- "በአላህም መንገድ ለግሱ በእጆቻችሁም(ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ…" (አል-በቀራህ 195) የእስልምና ሃይማኖት አንድ ሰው የትኛውም ሃይማኖት ይከተል በሱ ላይ ድንበር እንዳይታለፍበትና ወንጀል እንዳንፈፅምበት በሚል ወሰኖችን አበጅቷል መቀጣጫ ህግጋትንም አኑሯል፡፡ እንዲህ ይለናል:- «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተገደሉ ሰዎች ብድር መመለስ በናንተ ላይ ተጻፈ…» (አል-በቀራህ 178) 3) አዕምሮ፡- አላህ ከለገሳቸው ታላላቅ ፀጋዎች ውስጥ አንዱ በመሆኑ፤ እርሱን የሚጎዱና አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳርፉበትን ነገሮች እስልምና ከልክሎዋል፡፡ የሰው ክብርና ማንነት የሚገለፀው በርሱ ነው፡፡ በዚህ ዓለም(ዱንያ) ሆነ በቀጣዩ ዓለም አኼራ ሂሳቡን የሚያወራርደውና ጥያቄ የሚቀርብለት በርሱ ነው፡፡ ለዚህ ነው አላህ ማንኛውንም ዓይነት አስካሪ መጠጥና አደንዛዥ ዕፅን የከለከለው(ሐራም) ያደረገው ከፀያፍና ከሸይጣን ተግባራት ተርታ መድቦታል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል:- "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ፣ ቁማርና ጣዖታትም የመጠንቆያ እንጨቶች(አዝላምም) ከሰይጣን ስራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፤ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡" (አል-ማኢዳህ 90) 4) ዘር፡- የሰውን ክብርና ዘር መጠበቅ ከኢስላማዊ መርህ ታላላቅ ዓላማዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የእስልምና ሃይማኖት ዘርን ለማስቀጠልና ለቤተሰብ ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት የሰጠውና ጥበቃ ያደረገለት ነገር መሆኑ በተለያዩ መርሆቹና ህግጋቶቹ ውስጥ ጎልቶ ሲታይ ይስታዋላል፡፡ ከዚህ ውስጥ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡- የእስልምና ሃይማኖት ለትዳር በጣም ያበረታታል፡፡ ቀለል ባለ አኳኋን እንዲመሰረተም ይገፋፋል፡፡ ቅድመ ሁኔታዎቹ እንዳናካብዳቸውም ያዘናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል:- "ከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፡፡" (አል-ኑር 32) እስልምና ሕገ-ወጥ የሆኑ ማንኛውም ዓይነት የፆታ ግንኙነቶችን ከልክሎዋል፡፡ ወደ እርሱ የሚያደርሱ ጎዳናዎች ሁሉ ዝግ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ እንዲህ ይለናል፡፡ "ዝሙትን አትቅረቡ፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ!" (አል-ኢስራእ 32) እስልምና የሰው ዘርና ክብር ማንቋሸሽና ማጥላላትንም በጥብቅ አውግዞዋል፡፡ ይህ መሰሉን ተግባር ከከባባድ ወንጀሎች ውሰጥ መድቦታል፡፡ ይህን ወንጀል የፈፀመ ሰው በአኼራ ከሚጠብቀው ቅጣት በተጨማሪ፤ ዱንያ ላይም ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቀው አላህ አስጠንቅቋል፡፡ የወንድም ሆነ የሴት ልጅ ክብር እንዲጠበቅና እንዳይጣስ አዞዋል፡፡ የራሱንም ሆነ የቤተሰቦቹን ክብር ለማስጠበቅ ሲል የተገደለ ሰው በአላህ መንገድ እንደተሰዋ ሰማዕት ቆጥሮታል፡፡ 5) ገንዘብ፡- ጥበቃ ይደረግለት ዘንድ እስልምና ግዴታ አድርጓል፡፡ የዕለት ጉርስን ፍለጋ መንቀሳቀስንም እንዲሁ ከተለያዩ ሰዎች ጋር የሚደረግ የንግድ ግብይትና የቢዝነስ ልውውጥንም የተፈቀደ ተግባር አድርጎታል፡፡ ለገንዘብ ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል ከሚል እሳቤ በመነሳትም አራጣን፣ ስርቆትን፣ ማታለልን፣ ማጭበርበርንና በሀሰት መንገድ የሰው ገንዘብ መብላትን ሀራም አድርጓል፡፡ እነዚህን የወንጀል ተግባራት የሚፈፅም ሰው በቅዱስ ቁርኣን ከፍተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል፡፡ ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን በቴሌ ግራም ለመከታተል https://t.me/islamictrueth
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram