❁نُــــــــورْاَلْـــــــهُــــــدئ قَنَــــاةُ اُمُ عُــثَـيْـمِـيْـن
رفتن به کانال در Telegram
✍️أنا طالب اختي كُونِي سلفيّة .. على طريق السلف الصّالح و أبشري بالخير ምንም ነገር ቢሆን እፈለግንበት ቦታ ለመድረስ ሶብር ያስፈልጋል!የሶብር ዉጤቱ ደግሞ ያማረ ነዉ ያረህማን ከታጋሾች አድርን ➱የዚህ ዓለም ትልቁ ጌጥሽ ቅንነትሽ ➱ኢኽላስሽ ➱ትህትናሽ እና ወደ ➱ፈጣሪሽ መመለስሽ ነው።
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
473
مشترکین
-124 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-1730 روز
آرشیو پست ها
➡️እስኪ ስለማ ይቀረው ጣፋጭን ቆርጩ ሞት
➡️እድሜ በፈጠነ በሄደ ቁጥር
ሞትም እየመጣ ማንንም አይመርጥም የለው ቁጥር ስፍር
እኛም ተኝተናል ሞትም ገሰገሰ
ከመካከላችን ስንቱ ገነደሰ
ከቶ ማን አለና እንደሞት መካሪ
ባይንህ እያሳየ ለሁሉ አስተማሪ
ሁሉም እንደልቡ ሲበላ ሲጠጣ
ዱንያን እያጣጣምን ስንል ገባ ወጣ
ሞትም ሳያማክር በድንገት ይመጣል
ሳንወድ በግድ ከቤት ያስወጣናል
➡️ ከዛስ?!
በደቂ ቃዎች ውስጥ ስምህ ይቀየራል
ሙሀመድን ትተው ጀናዛው ይሉሀል
የራስህ ቤተስብ ከፈን ያልብሰሀል
አጣጥቦ ከፋፍኖ ቀብር ይወስድሀል
የራስህ ቤተሰብ ለህዱን ያዘጋጃል
ከታች ይሆን እና አቀብሉኝ ይላል
ቡለኬት ደርድሮ አፈሩን ጭኖብህ ወዳው ይመለሳል
አሏህ ይጠብቀን ን ከቀብር ቅጣት
ያአሏህ አድርገን ከጀነትህ ፀጋ የሚመጣለት!
ሁን ሲለው....
ከድንጋይ ውስጥ ውሀን
ከእንባ ውስጥ ፈገግታን
ይፈጥራል!
ሁን ሲለው እሱ ሲሻ
ሐዘንም ደስታ ድካምም
ብርታት ይሆናል...
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
⬆️🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙
በወር 1 መጽሐፍ አብበው ከቤተሰብዎ ጋር ዑምራ መሄድ ቢችሉስ?
አዎ! በጛሩ ሒራ የንባብ ውድድር ላይ በመሳተፍ ብቻ፡
🥇 1ኛ: ሙሉ የቤተሰብ ዑምራ 🕋 🥈 2ኛ: iPhone 13 Pro Max📱 🥉 3ኛ: ብራንድ ላፕቶፕ 💻 📖 መጽሐፉን በስልክዎ ያገኛሉ፤ ባሉበት ሆነው ይፈተናሉ!🚀 ቦታ ሳይሞላ አሁኑኑ ይመዝገቡ: 👉 https://sulmahira.et/register?ref=0023 ለበለጠ መረጃና በቀጥታ በቴሌግራም ለመመዝገብ ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ 0946248626 @Muhadil234 0942189967 @Su_lle2
اللهم امين يارب العالمين
ያረብ የዱንያ ሙሲባ የማያሰቃያት የተረጋጋችን🫀 ልብ ስጠን
𝐘𝐚𝐫𝐞𝐛
+1
👉አስተውይ 🌸
ስትሥቂ አለም አብሮሽ ይስቃል
ስታዝኒ ግን አዘኑ የብቻሽ ነው።
So. ይሁንጂ ደግሞ አላህ ሁሌም ካንችጋ ነው።
ልብ በተወከል ትፀናለች 🌸
አላህን. በማወቅ ትደሰታለች 🌸
አላህን. በማውስት. ትረካለች🌸
كوني قوي🌹
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ 🫀
ሰባኹል ኸይር /
አሏህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው
ነገሮች ሁሉ ከብደውን ጭልምልም ባለብን ሰዓት ድንገት እዝነቱን ይልክልንና አይሆንም ብለን ተስፋ የቆረጥንበት ነገር እንዲሆን ያደርጋል።
አልሃምዱሊላህ ለአለማቱ ጌታ ምስጋና የተገባ ይሁን
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
✨ የሕይወትዎን ትልቅ እድል ያግኙ፤ ያንብቡ፣ ይወዳደሩ፣ ያሸንፉ! 🕋📱💻በ አንድ ወር ብቻ የንባብ ውድድሩን በመቀላቀል የመጽሐፉ ባለቤት ይሁኑ፤ የእውቀት አድማስዎን እያሰፉ ለታላላቅ አጓጊ ሽልማቶች ይወዳደሩ!
"አንባቢ ከዋሻው መውጣት ሳይታክተው፤ ከዋሻው ያልወጡ ትውልዶች መምጣት ይናፍቀዋል"
🏆 የአሸናፊዎች ልዩ ልዩ ሽልማቶች: 🥇 1ኛ ደረጃ: የቤተሰብ ዑምራ 🥈 2ኛ ደረጃ: iPhone 13 Pro Max 🥉 3ኛ ደረጃ: Brand Laptop 🎁 ከ4ኛ – 10ኛ ደረጃ: ሌሎች ልዩ ልዩ ሽልማቶች
✨ በተጨማሪም ከተመዘገቡና ከተወዳደሩ ሁሉ መካከል ለዕድለኞች የእምራ ዕጣ ማሸነፊያ ቁጥር ይሰጣል! 📖 ስለ መጽሐፉ እና ውድድሩ: የመጽሐፉ ርዕስ: "ሙሐመድ!" (የኢማም ሙሐመድ ቢን ዐብዱልወሃብ የሕይወት ታሪክና ተሞክሮ) የገጽ ብዛት: ለአንድ ወር የሚሆን 150 ገጽ ብቻ የሚገኙ ቋንቋዎች: አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ እንግሊዝኛ እና ዐረብኛ 📲 አሁኑኑ ይመዝገቡ! 🌐🏢 በአካል ለመመዝገብ: አዲስ አበባ፤ አብነት አደባባይ፣ ኖህ ህንፃ 5ኛ ፎቅ 📞 ለበለጠ መረጃና ለቀጥታ ምዝገባ: 📱 0946248626 | @Muhadil234 📱 0942189967 | @Su_lle2
የጽናትና የእምነት ተ symbolName፡ ኽባብ ኢብኑ አል-ዐረት (ረ.ዐ)
መግቢያ
በኢስላም ታሪክ ማህደር ውስጥ ስማቸው በወርቅ ቀለም ከተጻፉት ታላላቅ ሶሃቦች መካከል አንዱ ኽባብ ኢብኑ አል-ዐረት (ረ.ዐ) ናቸው። ኽባብ ማለት የፅናት ማ ማደሪያ፣ የእምነት ተጋድሎ ምሳሌ እና ለአላህ دين ሲሉ የመከራን እሳት በደስታ የተቀበሉ ድንቅ ሰሐቢ ናቸው።
መነሻና የእስልምና ብርሃን
ኽባብ ገና በወጣትነቱ በወገኖቹ መካከል በተከሰተ የጎሳ ግጭት ምክንያት በምርኮኝነት ተይዞ በባርነት ተሸጠ። በመጨረሻም ወደ መካ መጥቶ 'ኡሙ አነማር' ለተባለች ሴት በባርነት ተሸጠና በሰይፍና በብረት ጥረዛ ሥራ ላይ ይሰማራ ጀመር።
በዚያ የመካ ጨለማ ወቅት የነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የእስልምና ጥሪ ሲደርሰው ያለ ምንም ማንገራገር እስልምናን ተቀበለ። ከእሱ በፊት እስልምናን የተቀበሉት ጥቂቶች ብቻ የነበሩ ሲሆን፣ ኽባብ ስድስተኛው ሰው በመሆን የቀደመ ባለታሪክ ሆነ።
የመከራውና የጽናቱ ግዙፍነት
እስልምናን መቀበሉ በታወቀ ጊዜ፣ እመቤቱ ኡሙ አነማር እና የመካ ቁረይሾች እጅግ አሰቃቂ ቅጣቶችን ያወርዱበት ጀመር። በእሳት የጋለ ድንጋይና የብረት ቁርጥራጮች ላይ እርቃኑን በጀርባው ያስኙት ነበር። የኽባብ ጀርባ በእሳቱ ላይ ሲቃጠል፣ ከጀርባው የሚፈሰው ስብና ደም እሳቱን እስኪያጠፋው ድረስ ይሰቃይ ነበር።
እመቤቱ ኡሙ አነማር ወደ ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ይሄዳል በሚል ምቀኝነት በእሳት የጋለ ብረት በጭንቅላቱ ላይ ታስቀምጥበት ነበር። ነቢዩም (ሶ.ዐ.ወ) የእሱን ሰቃይ አይተው "አላህ ሆይ! ኽባብን እርዳው" ብለው ዱዓ አደረጉለት። ብዙ ሳይቆይ አላህ የነቢዩን ዱዓ ተቀብሎ እመቤቱን በጽኑ የራስ ምታት ህመም በመቅጣቱ፣ እሷን ለማዳን በጋለ ብረት ጭንቅላቷን እንዲተኩሷት ተገደደች። አላህም የሰራችውን ግፍ በራሷ ላይ አሳያት።
የቁርዓን አስተማሪና የዑመር እስልምና መቀበል
ኽባብ (ረ.ዐ) የመከራው ብዛት ከእምነቱ አላወጣውም። ይልቁንም የመጀመሪያው የቁርዓን አስተማሪ በመሆን ሙስሊሞችን ያስተምር ነበር። ታላቁ ሶሃቢ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ) እስልምናን ከመቀበሉ በፊት፣ የእህቱን ፋጢማን እና የባለቤቷን ቤት በቁጣ ሰብሮ ሲገባ፣ ሁለቱን ተማሪዎች የሱረቱ ጣሃን አንቀጾች ያነብቡላቸውና ያስተምራቸው የነበረው ኽባብ ነበር። የዑመርን ልብ የለወጠው ያ የቁርዓን ድምፅ በኽባብ አስተማሪነት የቀረበ ነበር።
የቁርዓን አንቀጽ ያወረደው ክስተት
ኽባብ ለአስ ኢብኑ ዋኢል ለተባለው ሀብታም ከሐዲ የሰይፍ ሥራ ሰርቶለት ክፍያውን ሲጠይቀው፣ አስ፦ "በሙሐመድ እስክትክድ ድረስ ገንዘብህን አልከፍልህም" አለው። ኽባብም በጽናት፦ "ብትሞትና እንደገና ብትቀሰቀስ እንኳ በሙሐመድ አልክድም" አለው። አስ በፌዝ፦ "እንግዲያው ከሞትኩ በኋላ ሀብትና ልጅ ሲሰጠኝ እከፍልሃለሁ" ባለው ጊዜ አላህ የሚከተለውን የቁርዓን አንቀጽ አወረደ፦
"በአንቀጾቻችን የካደውንና «ሀብትንና ልጅን በእርግጥ እሰጣለሁ» ያለውን አየህን?..." (ሱረቱ መርየም 77-80)
የታሪካዊው ጀርባ ምስክርነት
በኋላ ላይ ዑመር (ረ.ዐ) የሙስሊሞች መሪ በነበሩበት ወቅት፣ ሶሃቦች የተቀበሉትን መከራ ሲያስታውሱ ኽባብን ጀርባውን እንዲያሳያቸው ጠየቁት። ኽባብ ጀርባውን ሲገልጥ፣ ዑመር (ረ.ዐ) በደንግጠው፦ "እስከ ዛሬ ድረስ እንደዚህ ያለ የሰው ጀርባ አይቼ አላውቅም" አሉ። ጀርባው በእሳቱ መቃጠል ምክንያት ሙሉ በሙሉ ቅርፁን ቀይሮና ወደ ውስጥ ጎድጉዶ ነበር። ኽባብም፦ "እሳቱ ሊጠፋ የቻለው ከጀርባዬ በፈሰሰው ስብ ብቻ ነበር" በማለት የጽናቱን ታሪክ መሰከረ።
የህይወቱ ፍጻሜና ትህትናው
በስተመጨረሻም እስልምና አሸንፎ፣ የሀብት በሪ ሲከፈት ኽባብ ብዙ ሀብት አገኘ። ነገር ግን የወርቅና የብር ገንዘቡን እያየ አልጋው ሥር አስቀምጦ ይበቃው የነበረው አልቃሽ ነበር። "ወደፊታችን የሄዱት ወንድሞቻችን ከዚህ ዓለም ምንም ሳያገኙ አልፈዋል። እኛ ግን የምንሰራው በጎ ሥራ ምንዳ በዚህች ዓለም ተከፈለብን ብለን እንፈራለን" ይል ነበር።
በ37 ዓመተ ሂጅራ በኩፋ ከተማ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ፣ ከእሱ በኋላ ላሉት ሙስሊሞች በሙሉ የእምነት፣ የጽናትና የትህትና ታላቅ ትምህርት ትቶ አልፏል።
+2
ሂጃብሽ—የጽናትሽ ብርሃን!
~
ሂጃብሽ ለአንቺ ብቻ መሸፈኛ ሳይሆን ልቦችን የሚቀሰቅስ ዝምተኛ መልእክት ነው! በተሟላ ሂጃብሽ ላይ የምታደርጊው ጽናት ለሌሎች ሴቶች የጽናት ስንቅ ይሆናል፤ የደከሙ ልቦችንም ያበረታታል።
ሂጃብ ተራ ጨርቅ አይደለም—የክብር፣ የሐያእ እና አላህን የመታዘዝ ምልክት ነው!
መገላለጥና እርቃን መሄድ በበዛበት በዚህ ዘመን አላህ በወደደልሽ አለባበስ ላይ ፀንተሽ መልካም አርአያ ሁኚ። በአንቺ ጽናት ሰበብ አላህ የብዙዎችን ልብ ይከፍት ይሆናል!
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
💼ለሽያጭ የቀርብ አስቾካይ እስላማዊ የቲክ ቶክ አካዉንት እና ቴሌግራም ቻናል
እጃችን ላይ 1 አካውንት ብቻ አለ ፍጠኑ
👉 12k ፎልሎዎርስ Tik tok
👉5.5k subscribers ቴሌግራም
አስቾካይ ነዉ ቶሎ በሉ
🎯በጣም በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ አስቾካይ ነዉ 🔽
የقال ابن_القيم رحمه الله :
( الذنوب والمعاصي تضرّ ولا بد !
وضررُها في القلوب ؛ كضرر السّموم في الأبدان ).
[ الجواب الكافي: ٦٥ ]
«ኃጢአቶችና ወንጀሎች ጉዳት ማድረሳቸው አይቀሬ ነው! በጥልቀታቸውም በልቦች ላይ የሚያደርሱት ጉዳት፣ መርዝ በሰውነት አካል ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ጋር ተመሳሳይ ነው።»
(አል-ጃዋብ አል-ካፊ፡ ገጽ 65
📚ማለትም፦ ሰውነት በመርዝ እንደሚጎዳ፣ ልብም በኃጢአትና በአለመታዘዝ ይጎዳል። መርዝ ካልታከመ ሰውነትን እንደሚያዳክም፣ ኃጢአትም በተደጋጋሚ ከቀጠለ ልብን ያዳክማል።
✍አንተነትህ ቁርአን ውስጥ
እንደተወሳ ታውቃለህን?
ማነህ አንተ?
ማንንስ ትመስላለህ?
እስቲ አብረን እንከታተል…
⇨ አህነፍ ኢብኑ ቀይስ ይባላል
ከእለታት አንድ ቀን ቁጭ ባለበት
ሀሳቡ ላይ አንድ አንቀፅ ትመጣለች
አንቀጿም እንዲህ ትላለች
(لَقَدْ أَنْزَلْنَا إِلَيْكُمْ كِتَابًا فِيهِ ذِكْرُكُمْ ۖ أَفَلَا تَعْقِلُونَ)
" ስለናንተ (ክብራችሁ) በውስጡ ያለበትን
መጽሐፍ ወደእናንተ በእርግጥ አወረድን
አታውቁምን "
[አንቢያእ 10]
↪ ከዚያ ቁርአንን አነሳና
እኔ ማነኝ? ማንንስ ነው የምመስለው?
ብሎ እራሱን ቁርአን ውስጥ
መፈለግ ጀመረ…
๏ እንዲህ የሚባሉ ሰዎችን አየ
(كَانُوا قَلِيلًا مِنَ اللَّيْلِ مَا يَهْجَعُونَ)
" ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ "
(وَبِالْأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ)
" በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ
ምሕረትን ይለምናሉ "
(وَفِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ لِلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ)
" በገንዘቦቻቸውም ውስጥ ለለማኝና
(ከልመና) ለተከለከለም (በችሮታቸው)
መብት አልለ "
[ዛሪያት ከ17-19]
አሁንም መፈለጉን ቀጠለ
እንዲህ የሚባሉ ሰዎችን አየ
(الَّذِينَ يُنْفِقُونَ فِي السَّرَّاءِ وَالضَّرَّاءِ وَالْكَاظِمِينَ الْغَيْظَ وَالْعَافِينَ عَنِ النَّاسِ)
" እነዚያ በድሎትም ሆነ በችግር የሚለግሱት
ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ
አድራጊዎች የሆኑት "
[ዒምራን 134]
(وَيُؤْثِرُونَ عَلَىٰ أَنْفُسِهِمْ وَلَوْ كَانَ بِهِمْ خَصَاصَةٌ ۚ وَمَنْ يُوقَ شُحَّ نَفْسِهِ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ)
" በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸውም
በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ይመርጣሉ
የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው
እነዚያ እነሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው ፡፡"
[ሀሽር 9]
(يَجْتَنِبُونَ كَبَائِرَ الْإِثْمِ وَالْفَوَاحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُوا هُمْ يَغْفِرُونَ)
" የኀጢኣትን ታላላቆችና ጠያፎችን
የሚርቁ በተቆጡም ጊዜ እነሱ የሚምሩት "
[ሹራ 37]
⇨እነዚህን ካየ በኋላ በመተናነስ
እንዲህም አለ
" ጌታዬ ሆይ ነፍሴን ከነዚህ ውስጥ
የቷ እንደሆነች ማንን እንደምትመስል አላውቅም "
⇨ ከዛም መቅራቱን ቀጠለ
እንዲህ የሚባሉ ሰዎችንም አየ
(إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ)
" እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም
በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ ፡፡"
[ሳፋት 35]
(مَا سَلَكَكُمْ فِي سَقَرَ)
" በሰቀር ውስጥ ምን አስገባችሁ? "
(قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ)
"(እነርሱም) ይላሉ «ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡"
(وَلَمْ نَكُ نُطْعِمُ الْمِسْكِينَ)
" ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም ፡፡"
(وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ الْخَائِضِينَ)
" ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን "
(وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوْمِ الدِّينِ)
" በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን "
[ሙደሲር ከ42-46]
⇨ካየ በኃላም እንዲህ አለ
" ጌታዬ ሆይ እኔ ከነዚህ እንዳልሆን
ወዳንተ እገለላለሁ "
⇨አሁንም መቅራቱን ቀጠለ
እንዲህ የምትል አንቀፅ እስከሚያገኝ ድረስ
(وَآخَرُونَ اعْتَرَفُوا بِذُنُوبِهِمْ خَلَطُوا عَمَلًا صَالِحًا وَآخَرَ سَيِّئًا عَسَى اللَّهُ أَنْ يَتُوبَ عَلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ)
" ሌሎችም በኃጢአቶቻቸው የተናዘዙ
መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ አሉ
አላህ ከእነሱ ጸጸታቸውን ሊቀበል ይከጀላል
አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና ፡፡"
[ተውባህ 102]
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
👇ይሄንን ያውቃሉ
መፅሐፍ በማንበብ ብቻ ራሳችሁን ጨምሮ ለቤተሰብም የምታገኙትን የኡምራ ሽልማት እድል ልታስመልጡ ነው ?? ?? ?? ?
🏢በአካል ለመመዝገብ: አዲስ አበባ አብነት አደባባይ ኖህ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ በመምጣት
📓📓📓📓📓📓📓📓📓📓📓
⬇️የንባብ ውድድሩን በዌብሳይት ለመመዝገብ⬇️
https://sulmahira.et/register?ref=010
ለበለጠ መረጃና በቀጥታ ለመመዝገብ🤌🏻
0946248626 @Muhadil234
0942189967 @Su_lle2
+1
~>ጁሙዓ የሳምንቱ ምርጥ ቀን!!
ከቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን ጁሙዓ ነው ብለዋል ረሱሉና ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
(ሱረቱ አል- ጁሙዓህ - 9)
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው ፡፡
••◉❖◉●••በጁምአ ሱናዎች እንበርታ!
✅ገላን መታጠብ
✅ሽቶ መቀባት ለወንድ
✅ልብስ መቀየር
✅ጥፍርን ማሳጠር
✅በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ
✅ሰለዋት ማብዛት
✅ሱረቱልነካህፍን መቅራት
✅ሲዋክ መጠቀም
✅ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ
✅ከጁምአ ቡሀላ የሱና ሰላት መስገድ
✅ዱአ ማድረግ
✅ዱአ መደጋገም ተቀባይ እንዲሆንልን ሀያሉን ጌታ ደጋግመን መማፀን!
┈•✿•˚•❀•˚•✿•˚•❀•˚•✿•┈
መልካም ጁምዓ
ይሁንላችሁ{ን }!
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
አንብበው 1ኛ ከወጡ የቤተሰብ ዑምራ አሸናፊ ይሆናሉ።
በተጨማሪ ከ2 _ 10ኛ ለወጡ ልዩ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋሉ
✍ የጛሩ ሒራ ንባብ ውድድር ሂደት
ለአንድ ወር የተመረጠውን መጽሐፍ ማንበብና ማጥናት
ለአንድ ሳምንት የሙከራ ፈተና መለማመድ
በመጨረሻ የማጠቃለያ ኦንላይን ፈተና ባሉበት ሆኖ መፈተን
የንባብ ውድድራችን ምዝገባ እየተካሄደ ነው።
ይህ እድል አያምልጣቹ ተሳተፉ የምትወዱትን ሁሉ አሳትፉ ......
🏢በአካል ለመመዝገብ: አዲስ አበባ አብነት አደባባይ ኖህ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ በመምጣት
📓📓📓📓📓📓📓📓📓📓📓
⬇️የንባብ ውድድሩን በዌብሳይት ለመመዝገብ⬇️
https://sulmahira.et/register?ref=010
ለበለጠ መረጃና በቀጥታ ለመመዝገብ🤌🏻
0946248626 @Muhadil234
0942189967 @Su_lle2
●(
ሙሳም) አለ «ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ፡፡ ●«ነገሬንም ለእኔ አግራልኝ፡፡ ●«ከምላሴም መኮላተፍን ፍታልኝ፡፡ ●«ንግግሬን ያውቃሉና፡፡ ●«ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ፡፡ ●«ሃሩንን ወንድሜን፡፡ ●«ኅይሌን በእርሱ አበርታልኝ፡፡ ●«በነገሬም አጋራው ●«በብዙ እናጠራህ ዘንድ፡፡ ●«በብዙም እንድናወሳህ፡፡ ●«አንተ በእኛ ነገር ዐዋቂ ነህና፡፡» [Surah Ṭā-Hā: 25-35]
ኢላሂ‼
_ሶላትን ለማይሰግደው ቅናቻን፣
ለሚያቋርጠው ፅናትን፣
_ከሶላት
ለሚደክመው ብርታትን፣
ለሚሰንፈው ትጋትን፣
ስጠው። አልሀምዱሊላህ
ሰባሐል ኸይር ቤተሰቦች!!
