fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 290
مشترکین
-1224 ساعت
-267 روز
-9530 روز
آرشیو پست ها
+1
🇮🇱❗️በአሜሪካ ለእስራኤል በመሰለል ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው እና 30 ዓመት በአሜሪካ እስር ቤት ታስሮ በቅርቡ በእስራኤል ውትወታ የተፈታው ሰላይ ጆናታን ፖላርድ፣ ኢራንን፣ ጋዛን እና ሊባኖስን ካጠናቀቅን በኋላ እስራኤል ከቱርክ እና ከግብፅ ጋር ጦርነት መግጠም እንደሚኖርባት ተናግሯል። “አውሎ ነፋሱ እየመጣ ነው፣ ዓለም ከዚህ በፊት ከተመለከተችው ከማንኛውም ነገር የተለየ" ይላል። “ለሚቀጥለው ጦርነት ዝግጁ መሆን አለብን፣ ይህም ምናልባት በቱርክ እና በግብፅ ላይ ሊሆን ይችላል” ሲል ተናግሯል። ፖላርድ፣ ለእስራኤል በመሰለል እስከታሰረበት ጊዜ ድረስ የአሜሪካ የደህንነት ባለሙያ ነበር። ባለፈው ዓመት ወደ እስራኤል የተመለሰ ሲሆን፣ ዛሬ ላይ ለእስራኤል ፓርላማ ወንበር እየተወዳደረ ነው።

🇳🇬 የናይጄሪያ ፓስተር ባሕሩን ለመክፈል ሞክሮ ሳይሳካለት ቀረ።

—❗️🇮🇷/🇺🇸 የኢራኑ የበላይ መሪ አያቶላህ ሙጅተባ፣ ከአሜሪካ ጋር ተደረሰ የተባለውን የመግባቢያ ሰነድ ነጥቦች አንዱንም አልተቀበለም። ለዚህ ነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስምምነቱን ማዘግየት ባይፈ
—❗️🇮🇷/🇺🇸   የኢራኑ የበላይ መሪ አያቶላህ ሙጅተባ፣ ከአሜሪካ ጋር ተደረሰ የተባለውን የመግባቢያ ሰነድ ነጥቦች አንዱንም አልተቀበለም። ለዚህ ነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስምምነቱን ማዘግየት ባይፈልግም፣ እያዘገየ ያለው። ምክኒያቱም ሙጅተባ በምንም ነጥቦች ላይ ለመስማማት አልፈቀደም-- i24ዜና

🇷🇺❌🇺🇦🇪🇺🇺🇸— የሩሲያ የደህንነት ምክር ቤት ፀሐፊ ሰርጌ ሾይጉ፦ "
የውጭ አምባሳደሮች ኪየቭን እንዲለቁ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ፍጹም ከባድ እና ሊፈጸም የሚገባው ነው... ሩሲያ ያስጠነቀቀችበት በኪየቭ ላይ የሚደረግ ጥቃት በማንኛውም ጊዜ ሊፈጸም ስለሚችል ነው፣ ስለዚህ ለቅቃችሁ ብትወጡ የተሻለ ይመስላል"
 አሜሪካ የሩሲያን ማስጠንቀቂያ አክብራ ከቀናት በፊት አምባሳደሯን እና የኤምባሲው ሠራተኞቿን ማስወጣቷ የሚታወቅ ነው። በሌላ በኩል አውሮፓዊያን ሀገሮች ሩሲያን 'ምንም አታመጪም' በማለት ማስጠንቀቂያዋን ወደ ጎን ትተውታል።

—❗🇮🇱/🇱🇧፦ እንደ ዕብራይስጥ ሚዲያ ዘገባ፣ የግድያው ሙከራው ሳይሳካ መቅረቱ ተገልጿል። ከየካቲት ወር ጀምሮ በተከሰተው አዲሱ የግጭት መባባስ፣ ሁለቱ በሂዝቦላ መሪ በሼክ ናኢም ቃሴም ላይ የተደረጉትን ጥቃቶች ጨምሮ፣ ሁሉም ከፍተኛ የእስራኤል የግድያ ሙከራዎች ማለት ይቻላል፣ አልተሳኩም። ሂዝቦላ በ2023-2024 ጦርነት ወቅት ከገጠሙት የስለላ ውድቀቶች የተማረ ይመስላል።

—❗🇮🇱/🇱🇧 ሰበር ዜና፦ ከተኩስ አቁም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በደቡብ ቤሩት ዳርቻ፣ እስራኤል ከፍተኛ የሂዝቦላ መሪ ላይ የግድያ ጥቃት አከናውናለች። ጥቃቱ የተፈለገውን አመራር በመግደል ላይ የተሳካ ይሁን አይሁን አልታወቀም።

የሐማስ ተዋጊዎች፣ ትናንት በጋዛ የአረፋ በዓል ገበያ ላይ በጥበቃ ሥራ ላይ ታይተዋል።

🇷🇺 🗣🇮🇷የሩሲያ የደኀንነት አለቃ፣ ምዕራቡ ዓለም የ ISIS ተዋጊዎችን በኢራን ላይ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። የሩሲያ የፌዴራል ደህንነት አገልግሎት (FSB) ዋና ኃላፊ፣ አሌክሳንድር
🇷🇺 🗣🇮🇷የሩሲያ የደኀንነት አለቃ፣ ምዕራቡ ዓለም የ ISIS ተዋጊዎችን በኢራን ላይ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። የሩሲያ የፌዴራል ደህንነት አገልግሎት (FSB) ዋና ኃላፊ፣ አሌክሳንድር ቦርትኒኮቭ ፣ የምዕራብ ሀገራት የስለላ ኤጀንሲዎች የቀድሞ የአይሲስ ታጣቂዎች እና የሌሎች የታጠቁ ቡድኖችን አባላት፣ ከሶሪያ እስር ቤቶች አውጥተው ወደ ኢራቅ በመውሰድ በልዩ ካምፖች ውስጥ በማሰልጠን ኢራን ላይ ያነጣጠረ ኃይል እንደገና ለማደራጀት ዕቅድ ይዘው እየሠሩ መሆናቸውን አስጠንቅቋል። 🗣ቦርትኒኮቭ፣ ታጋዮቹ ቀደም ሲል በሶሪያ ከመታሰራቸው በፊት ለISIS እና ለሌሎች የታጠቁ ቡድኖች የተዋጉ እንደነበሩ አስታውሶ፣ የምዕራቡ የስለላ ተቋማት እነዚህን ተዋጊዎች ወደ ኢራን አስርገው በማስገባት ሀገሪቱን ከውስጥ እንዲያምሱ ስልጠና እየወሰዱ ናቸው ብሏል። “በተገኘው መረጃ መሠረት፣ የምዕራብ የስለላ ኤጀንሲዎች ከሶሪያ የመጡ አሸባሪዎችን ከኢራን ጋር በሚደረግ ጦርነት ውስጥ እንደ ወኪል ኃይሎች ለመጠቀም ጥረታቸውን ቀጥለዋል” ብሏል።

—❗️🇮🇷/🇰🇼/🇺🇸 አራን በኩዌት የአሜሪካን የጦር ሰፈር መምታቷን አስታወቀች። ይሄ የሆነው ከጥቂት ሰዓታት በፊት የአሜሪካ ጦር የኢራንን ወታደራዊ ዒላማዎችን መምታቱ ከተረጋገጠ በኋላ ነው። የIRGC መግለጫ፦
'የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃት በንጋት በባንዳር አባስ አውሮፕላን ማረፊያ ዳርቻ ላይ ባለው ቦታ ከተከሰተ በኋላ፣ የዚህ ጥቃት መነሻ ነጥብ የነበረው፣ በኩዌት ያለው የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ኃይል ማእከል ከሌሊቱ በ10:50 ላይ ዒላማ ተደርጎ ነበር። ይህ ምላሽ፣ ጠላት በኢራን ላይ ለሚያደርገው ማንኛውም ጥቃት መልስ ማግኘቱ እንደማይቀር እንዲያውቅ እንደ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ያገለግላል፣ ከተደጋገመም፣ የእኛ ምላሽ የበለጠ ወሳኝ ይሆናል። ለሚያስከትለው መዘዝ ተጠያቂው አጥቂው ብቻ ይሆናል።'

🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ አዲስ የተቋቋመው የኢራን የፋርስ ባሕረ ሰላጤ የሆርሙዝ ወሽመጥ አስተዳደር ላይ ማእቀብ ጣለ።
🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ አዲስ የተቋቋመው የኢራን የፋርስ ባሕረ ሰላጤ የሆርሙዝ ወሽመጥ አስተዳደር ላይ ማእቀብ ጣለ።

⚡🇴🇲 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኦማንን 'እንዳላፈነዳዳሽ' ሲል አስፈራራ። የኦማን ከኢራን ጋር ወዳጅ መሆን፣ ብዙ የአሜሪካና የእስራኤል ካምፕ ሀገሮችን አስቆጥቷል።

— 🇺🇸/🇮🇷 የአሜሪካ ባለስልጣን ለNBC NEWS፦ 'እነዚህ ጥቃቶች ራስን የመከላከል እርምጃዎች ነበሩ እና የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማስቀጠል የታሰቡ ናቸው።'

🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካ "የተኩስ አቁም ስምምነት" በኢራን፡ ኢራንን በቦምብ ይደብድቡ። ራስን መከላከል ነው ብለው ይጥሩት። ኢራንን ይውቀሱ። ይደጋግሙ።

— 🇺🇸/🇮🇷 ትኩስ ዜና፦ እንደ አክስዮስ ዘገባ፣ ኢራን በፋርስ ባሕር ውስጥ በአሜሪካ የጦር መርከብ ላይ አራት ድሮኖችን እንዳስወነጨፈች ገልጿል፣ ድሮኖቹም በአሜሪካ የባሕር ኃይል መውደቃቸውን እና በባንዳር አባስ ውስጥ ያለ ሌላ ቦታ ተጨማሪ ድሮኖችን ከመልቀቁ በፊት መወደሙን ገልጿል።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ አሜሪካ፣ በዚህ ሰዓት በኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ተዘግቧል።
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ አሜሪካ፣ በዚህ ሰዓት በኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ተዘግቧል።

🇮🇷🇺🇸| በኢራን ብሔራዊ ቴሌቪዥን (IRIB) መሠረት፦ የኢራን ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፦ • ቋሚ የተኩስ አቁም • የአሜሪካ ከቀጠናው መውጣት • በኢራን ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ አለመግባት • ሙሉ የማዕቀብ እፎይታ • የታገዱ ገንዘቦች መልቀቅ • $300 ቢሊዮን ዶላር የመልሶ ግንባታ ካሳ • የባሕር ትራፊክ ቁጥጥር/አስተዳደር። በምላሹ፣ ኢራንም የምላሽ እርምጃዎችን ትወስዳለች። ** አሜሪካ ለኢራን አንዱንም እንኳ በገደምዳሜ ከመለሰችላት አደንቃታለሁ። ኢራኖች ያስቀመጧቸው ነጥቦች፣ ምናልባት፣ ዩራኒየማቸውን ለአሜሪካ ካስረከቡ በኋላ ብቻ፣ ሊደረጉ የሚችሉ ናቸው። ከዚያ ውጭ ይሄ ነው የሚባል፣ የሚያረካ ነገር፣ አሁን ላይ ባለው ድርድር የሚያገኙ አይመስለኝም። ብዙዎች፣ ኢራን ጦርነቱን ማቆም አልነበረባትም ይላሉ፣ ብዙዎች አሜሪካና እስራኤል ኤግሶስት አድርገው ነበር፣ ኢራን ባሳደረችባቸው ከፍተኛ ጫና ሊሰበሩ ትንሽ ነበር የቀራቸው ይላሉ። የጦርነቱን መቆም፣ እነ አሜሪካ ራሳቸውን ዳግም ሊያስታጥቁበትና ትንፋሽ ሊሰበስቡበት እንጂ በቅንነት ሰጥቶ በመቀበል ሊደራደሩ ፈልገው አይደለምም፣ ይላሉ። የኢራን አድቫንቴጅ ጦርነቱን በመቀጠል ላይ ነበር ብለው እየተከራከሩ ናቸው። የሆነው ሆኖ፣ ዛሬ ኢራን በድርድሩ እየጠየቀች ያለችው እነዚህን ነው። ይሰጣታል?

+2
⚡️🇮🇱 እስራኤል፣ በትናንትናው ዕለት የገደለችውን አዲሱን የሐማስ መሪ ይተካሉ ብላ ያሰበቻቸውን ሁለት የሐማስ አመራሮችን፣ አሁን፣ ከመሸ፣ በጋዛ በወሰደችው እርምጃ እንደገደለቻቸው ታወቀ - የእስራኤል ጦር ራዲዮ ** የትናንቱን በጫጉላ ቤት እያለ ነበር የገደለችው፣ እኒህኞቹን ገና ሳይሞሸሩ። በውስጥህ ብዙ 'ባንዳ' ካለ መታገል ከባድ ነው። ኤክስፐርቶች መጀመሪያ የውስጥህን ማጥራት ይገባል፣ ይላሉ። ጋዛ ብዙ ለእስራኤል የሚሠሩ የእስራኤል ጆሮ ጠቢ ፍልስጤማዉያን አሉ። በዚህ በኩል፣ እስራኤል ትልቅ የቤት ሥራዋን እንደሰራች ያሳያል።

🇺🇸🇮🇱🇸🇦🇮🇷 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በድጋሜ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ እና የገልፍ ሀገሮች፣ ከእስራኤል ጋር በፍጥነት 'አብርሃም Accord' በተባለ የስምምነት ጎጆ ውስጥ ካልተደመሩ፣ ከኢራን ጋር ለመፈራረም እንደሚከብደው ተናገረ። 'ምንም ማድረግ አልችልም፣ አዝናለሁ'፣ ያለው ፕሬዝዳንቱ፣ ከኢራን ጋር ካልተፈራረመ ጦርነቱ እንደሚቀጥልና፣ ኢራን እነዚህን ሀገሮች ልትመታቸውና ሊጎዱ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያዊ ፍንጭ ሰጥቷል።

🇦🇪⚡️ 🇸🇩 ዩናይትድ አረብ ኤሜሬት ከደቡብ አሜሪካ ኮሎምቢያዊያንን እየከፈለች በማምጣት በሱዳን ጦርነት ውስጥ እያሳተፈች ነው ተብላ ተከሰሰች። የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቋም እንዳለው፣ ኤ
🇦🇪⚡️ 🇸🇩 ዩናይትድ አረብ ኤሜሬት ከደቡብ አሜሪካ ኮሎምቢያዊያንን እየከፈለች በማምጣት በሱዳን ጦርነት ውስጥ እያሳተፈች ነው ተብላ ተከሰሰች። የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቋም እንዳለው፣ ኤሜሬት የኮሎምቢያ ተዋጊዎችን በዳርፉር ጀኖሳይድ በመፈፀም ከተፈረጀው ጃንጃዊድ ወይም RSF ጎን በማሰለፍ እያዋጋች እንደሆነ ከሷል። ከዚህ በፊት የተባበሩት መንግሥታት እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኤሜሬት በሱዳን እልቂት ግንባር ቀደም ተጠያቂ እንደሆነች ሲናገሩ ቆይተዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድም በሱዳን ጭፍጨፋ ዋነኛ ተዋናኝ የሆነውን RSFን በመደገፍ እና የኤሜሬትን ተከፋይ ገዳዮች በሀገሩ በማሰልጠን እና መጠለያ በመስጠት፣ ክፉኛ ሲወቀስ መሰንበቱ ይታወቃል። ** ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በዓለም ላይ የጦርነት አራጋቢ እና የአለመረጋጋት ምንጭ ሆናለች፣ በተለይ በምሥራቅ አፍሪካ። በእኛም ሀገር ይሄን የሚያግዛት ጥሩ መሪ አግኝታለች። በዚህና በሌሎችም ብዙ ምክኒያቶች ነው የኢራንን በኤሜሬት ላይ መነሳትን ብዙዎች የሚደግፉት። የገንዘብ ምንጫቸው ሲደርቅ፣ ወደራሳቸው ይሰበሰባሉ።

🇺🇸📞🇮🇷— የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ድርድሮች ላይ፦
አሁን ላይ ኢራን ስምምነት ማድረግ ብቻ ነው የምትፈልግ የሚመስለው። ለስምምነት ቋምጠዋል።ኢኮኖሚያቸው ያለ ገደብ በነፃነት እየተንደባለለ ነው። 250% የዋጋ ግሽበት አላቸው። ገንዘባቸው ምንም ዋጋ የለውም። መላው የኢኮኖሚ ስርዓታቸው ተበላሽቷል።