fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 316
مشترکین
-824 ساعت
-117 روز
-8230 روز
آرشیو پست ها
🇮🇷⚔️🇮🇱 ኢራን፣ የእስራኤልን የሃይፋ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ ባለስልጣናት መጀመሪያ ላይ ካመኑት በላይ፣ ከፍተኛ ውድመትን አድርሳበታለች። በጊዜው፣ ጥቃቱ ዋናውን የቤንዚን ማጠራቀሚያ ሙሉ በ
🇮🇷⚔️🇮🇱 ኢራን፣ የእስራኤልን የሃይፋ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ ባለስልጣናት መጀመሪያ ላይ ካመኑት በላይ፣ ከፍተኛ ውድመትን አድርሳበታለች። በጊዜው፣ ጥቃቱ ዋናውን የቤንዚን ማጠራቀሚያ ሙሉ በሙሉ ያወደመ ሲሆን፣ የእንፋሎት እና የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያቀርበውን የውስጥ ኃይል ማመንጫም አሰናክሏል፣ የጋዝ ተርባይኖችን፣ ማሞቂያዎችን እና መቆጣጠሪያ ክፍሎችንም ሙሉ በሙሉ አጥፍቷል። ጥቃቱ፣ 60 በመቶውን የእስራኤልን የሀገር ውስጥ የነዳጅ ምርት ያሽመደመደ የነበረ ሲሆን፣ ይህም በመላው እስራኤል ከፍተኛ የቤንዚን እጥረት አስከትሎ ነበር። እጥረቱንም፣ በአፋጣኝ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመጨመር እና በአሽዶድ ማጣሪያ ውስጥ ያለውን ምርት ከፍ በማድረግ ማስተካከል ተችሏል። ጥገናውን ለማፋጠን፣ መንግሥት መደበኛውን የአካባቢ እና የግንባታ ደንቦችን እና ሕግጋቶችን በማለፍ ወደ ሥራ እንደገባና፣ ሙሉ እድሳቱ አሁን በ2029 ብቻ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል። አሁን ጥገና እየተደረገለት ሳለ እንኳ፣ በተደጋጋሚ እሳት እንደሚነሳበት እና እየተበላሸ እንዳስቸገረ ታውቋል። የአካባቢ ጥበቃ ቡድኖችም፣ መንግሥት የግንባታ ሕጎችን እና ደንቦችን ጥሶ ወደ ሥራ መግባቱን ለተፈጠረው እንደ ምክኒያት እያነሱ እየከሰሱ ናቸው። በዚህ ዓይነት፣ እስራኤል በሌሎች ወሳኝ በሆኑ መሠረተ ልማቶቿ ላይ በኢራን የደረሰባትን የጥቃት ጉዳት እያሳነሰች ሊሆን ይችላል።

🇪🇹⚡️በኢትዮጵያ፣ አሁን ያለው ገዢ ፓርቲ ወደ ሥልጣን ከመጣበት ማግስት አንስቶ፣ ከዚህ በፊት በጥቂት መንግሥት አልባ ሀገራት ብቻ ይታዩ የነበሩ፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ፣ አውሬያዊ እና ሰይጣናዊ ድርጊቶች፣ በብዛት ወደ ሀገር እንዲገቡ ተደርጓል። እነዚህ አውሬያዊ እና ሰይጣናዊ ድርጊቶች ከገቡ በኋላም፣ ላለፉት 8 ዓመታት፣ በደንብ እንዲሰራጩና እንዳይጠፉ በመንግሥት ደረጃ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ። ከእነዚህ ኢሰብአዊ ድርጊቶች አንዱ፣ 'ለብር' ተብለው የሚደረጉ ጠለፋዎች፣ እገታዎች እና ያንን ተከትለው የሚመጡ ግድያዎች እና እርዳቶች ናቸው። በአሁን ሰዓት፣ በዓለማችን ውስጥ፣ የሰው ልጅ እንደ ከብት የሚታረድበት ሀገር ብልፅግና ፖርቲ በጠቅላይ ሚኒስቴር በአቶ አብይ አሕመድ አሊ ተወክሎ በሚመራት ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻና ብቻ ነው። ሌላ ሀገር ካለ፣ እንድታሳውቁን ስንል እንጠይቃለን። እኒህና መሰል ብዙ ሰዋዊነትን የተሻገሩ ሰይጣናዊ እና አውሬያዊ ወንጀሎች ናቸው፣ ዛሬ በብዙ የኢትዮጵያ ቦታዎች ሕዝቡን አማርረው በገዢው ፓርቲ ላይ መሳሪያ እንዲያነሳ ያስደረጉት።

🇮🇱🇵🇪 ልክ በአርጀንቲና እና በቺሌ እንደሚያደርጉት ሁሉ፣ የእስራኤል ቱሪስቶች፣ በፔሩ 'ግዛታቸውን' በምልክት ሲያጥሩ ይታያሉ። በቱሪስት ካምፖች አካባቢ እና ዙሪያውን፣ የወታደሮችን ምስል በመለጠፍ እና 'መግባት አይቻልም' ምልክቶችን በመትከል፣ 'ግዛታችን' ነው እያሉ አጥረው ይቀመጣሉ። *-*-*- እስራኤላዊያን ቱሪስቶችን በዓለም ላይ በግንባር ቀደምትነት 'እንዳይመጡብን' ከሚባሉ ቱሪስቶች የሚጠቀሱ ናቸው፣ ይሏቸዋል። ፀባይ እና ሥርዓት ፈፅሞ የላቸውም፣ የሚቀመጡበትን ያበላሻሉ፣ ክፍያ በሥርዓት አይከፍሉም፣ አንድ ነገር ሲነገራቸው ዘለው ፀረ ሴማዊነት፣ ፀረ አይሁድነት ለማለት ይቃጣቸዋል፣ በየሄዱበት በተለየ ጥንቃቄ እንዲታዩ ይሻሉ እና … ብዙ ብዙ ምክኒያቶች የተነሳ በዋና ዋና ቱሪስት መዳረሻ ሀገሮች አይወደዱም። በአውሮፓ 'አትምጡብን' እስከማለት የደረሱ ሀገሮች በርካታ አሉ። ታይላንድ፣ ጃፓን፣ እና ሩቅ ምሥራቅ ሀገሮችም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእስራኤል ቱሪስቶች ተማረው ብዙ ተዳርሰው እንደነበር ይታወቃል። በአርጀንቲና (ሁለተኛ ሀገራቸው) እና በቺሌ እነዚሁ ቱሪስቶች በብዙ ወንጀሎች በሕብረተሰቡ እስኪጠሉ ሆነዋል። ነገር ግን፣ እንደተለመደው፣ አብዛኛውን በፀረ ሴማዊነት እና በፀረ አይሁድነት ክስ አሸማቅቀውታል።

🇮🇱 - ካን 11 ዕብራይስጥ ቻናል - IDF ሐማስ በፍጥነት እራሱን እያደሰ መሆኑን በመግለጽ ሁሉን አቀፍ እና ዝርዝር ዘገባ ለእስራኤል መንግስት አቅርቧል። ሰነዱ የተዘጋጀው በአዲሱ የሞሳድ ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ሮማን ጎፍማን የኔታንያሁ ታማኝ ነው። ሐማስ እየጠነከረ መምጣቱ እውነት ሊሆን ቢችልም፣ ከእስራኤል አጠቃላይ ምርጫ በፊት በከፍተኛ ሁኔታ በተደመሰሰችው ጋዛ ውስጥ አዲስ የመሬት ዘመቻ መጀመር እንዳለበት ለማስረዳት ኔታንያሁ ያደረገው የመጨረሻ ሙከራ ነው። ይህ፣ የኔታንያሁ ማዘናጊያ ነው።

🇷🇺⚡️🇺🇦 ዩክሬን የድሮን መንጋዎችን ወደ ክራይሚያ እና ምዕራብ ሩሲያ መላኳን ቀጥላለች።
🇷🇺⚡️🇺🇦 ዩክሬን የድሮን መንጋዎችን ወደ ክራይሚያ እና ምዕራብ ሩሲያ መላኳን ቀጥላለች።

🇺🇸🇽🇰 ኮሶቮ የአሜሪካን 250ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን በዋና ከተማዋ፣ ፕርስቲን፣ በርችት አከበረች። በጣም ትልቅ የኮሶቮ ድፎ ዳቦም የቆረሰች ሲሆን፣ 250 ሻማዎችንም አብርታለች።

⚡️🇮🇷🇺🇸 የኢራን ፓርላማ አፈጉባኤ መሀመድ ባገር ጋሊባፍ፣ በኢራን ላይ የተጣለው የነዳጅ ማዕቀብ መነሳቱን እና የኢራን ድፍድፍ አሁን በ20 በመቶ ከፍ ባለ ዋጋ እየተሸጠ ሲሆን ገቢው እየተቀመጠ ነው ብለዋል። ቴህራን ዩናይትድ ስቴትስ የገባችውን ቃል ከጣሰች ምላሽ ለመስጠት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኗንም አስጠንቅቀዋል።
"አንዳንዶች አሜሪካ በነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አነሳለሁ ማለቷ ባዶ ቃል ኪዳን ነው ይሉ ነበር። ማዕቀቡ አስነስተናታል። ዛሬ የኢራን ዘይት በ20 በመቶ የበለጠ ውድ በሆነ ዋጋ እየተሸጠ ሲሆን ገንዘቡ በሂሳባችን ውስጥ እየተቀመጠ ነው። አሜሪካ የገባችውን ቃል ማፍረስ ትችላለች? አዎ፣ ይችላሉ፣ ሲጀመር እኛ እነሱን አናምንም። እንድናምናቸውም አይጠበቅብንም። ለማንኛውም የተገላቢጦሽ እርምጃ ዝግጁ ነን። አሜሪካ መታገል ከፈለገች እኛም በመዋጋት ረገድ በጣም ጎበዝ ነን።

🇮🇱🇹🇷 ኔታንያሁ ለኤርዶጋን፡ "እኔ የቱርክ እያደገ የመጣው ትቢቷ አሳስቦኛል… ኤርዶጋን ቢረጋጋ ይሻለዋል፣ ያለበለዚያ ምን ማድረግ እንደምንችል ጠንቅቆ ያውቃል።"

🇮🇱 ኔታንያሁ: "አስፈላጊ ከሆነ ኢራንን ለሦስተኛ ጊዜ እናጠቃታለን።"

የዌስት ባንክ የፍልስጤም መንግሥት ታጣቂዎች( አል-ፋታህ)፣ በማህበራዊ ሚዲያ የእስራኤል ጦር በጋዛ የሐማስን 'ቢጫ መስመር' እያለፈ ሙሉ ጋዛን ወደ መያዝ እየሄደ ባለበት፣ ሐማስ ምንም አለማድረጉን በማንሳት፣ በቡድኑ ላይ እያሾፉበት ታይተዋል። *-*-*- የዌስት ባንክ ፍልስጤሞች እና የጋዛ ፍልስጤሞች እርስ በርስ እንደማይዋደዱ በባለፈው ፅሑፌ ሰፋ አድርጌ፣ ከነ ምክኒያቱ፣ አንስቼ ነበር።  ገዢዎቻቸው ብቻ አይደለም የማይዋደዱት፣ የእርስ በርስ ጥላቻው በህብረተሰቡም ዘንድ የወረደ ነው። ዌስት ባንኮች፣ የጋዛን ውድመት በማውገዝ፣ ሰልፍ እንኳ እምብዛም አይወጡም። እንደ ማንኛውም የአረብ ማህበረሰቦች፣ ፍልስጤማውያንም በጎሳ ብዙ የተከፋፈሉ ናቸው።

🇪🇹⚡️የፈረንጅ የወንጀል ምርመራ ባለሙያዎች፣ FBI መሥሪያ ቤት እና ሳይኮሎጂስቶች የሚስማሙበት እና የሚሉት አንድ ነገር አለ፡ እንስሳን፣ በተለየ ደግሞ ውሻ እና ድመትን ሆን ብለው የሚገድሉ ሕፃ
+3
🇪🇹⚡️የፈረንጅ የወንጀል ምርመራ ባለሙያዎች፣ FBI መሥሪያ ቤት እና ሳይኮሎጂስቶች የሚስማሙበት እና የሚሉት አንድ ነገር አለ፡ እንስሳን፣ በተለየ ደግሞ ውሻ እና ድመትን ሆን ብለው የሚገድሉ ሕፃናቶች፣ ሲያድጉ፣ የጅምላ ገዳይ (Serial Killers) የመሆን ዕድላቸ ሰፊ ነው። የጅምላ ገዳዮች የኃላ ታሪክ፣ የሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ፣ ይህ አለበት። በሕፃንነታቸው ድመት እና ውሻ ይገድሉ ነበር (እንዲገድሉ እና ሲሞቱ እንዲያዩ ይደረጉ ነበር)። በዚህ ጉዳይ ብዙ ፔፐሮች ተፅፈዋል፣ ብዙ ጥናቶችም ተካሂደዋል፣ ፈልጎ ማንበብ ይቻላል። ይህ የተረጋገጠ እውነት ነው። በሆሳዕና፣ በመንግሥት አካላት ድጋፍ እና ውትወታ ሕፃናቶች ሆን ብለው፣ ያሳደጓቸውን የራሳቸውን ውሻዎች እንዲህ ባለ ጭካኔያዊ ግድያ በአደባባይ አውጥተው፣ እየሰቀሉ እና እየጨፈጨፉ እንዲገድሉ ማድረግ፣ ከበስተኋላው የተቀናበረ ሰይጣናዊ አጀንዳ ለመኖሩ አመላካች ነው። በሚመጣው ትውልድ፣ በእነዚህ ሕፃናቶች እጅ፣ በሰው ልጆች ላይ ወደፊት የበዙ የጅምላ ግድያዎች እንዲፈፀሙ ተፈልጓል።

🇸🇩🇪🇹🇦🇪 - የአለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች ጥምረት ICC፣ በሱዳን የጦር ወንጀሎችን፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎችን እና የዘር ማጥፋት ጀኖሳይድን በማሳለጥ የተባበሩት አረብ ኢሚሬ
🇸🇩🇪🇹🇦🇪 - የአለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች ጥምረት ICC፣ በሱዳን የጦር ወንጀሎችን፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎችን እና የዘር ማጥፋት ጀኖሳይድን በማሳለጥ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና የጎረቤት ሀገራት ባለስልጣናትን እንዲመረመሩ አሳስቧል። የተባበሩት መንግስታት የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ቢጣልም፣ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ አየር ማረፊያዎች በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ በኩል በሚተላለፉ የአቅርቦት አውታሮች በኩል የጦር መሳሪያ እና የሎጂስቲክስ ድጋፍ ወደ RSF እንዲደርስ በማድረግ እና በመሬት ላይ ላሉ ወንጀለኞች ብቻ ሳይሆን ግጭቱን በማስቀጠል ለተከሰሱት የውጭ ኔትወርኮችም ተጠያቂ እንዲደረጉ ጥሪ አቅርቧል።

🇷🇺 አሜሪካዊው የፖለቲካ ሳይንቲስት ጃን ሜርሻይመር፡ 'ፑቲን፣ የምዕራቡ ዓለም የመጨረሻ ግብ፣ የሩሲያ ሽንፈት እንደሆነ እርግጠኛ ነው። ይህ እንዲሆን በእርግጥ የሚፈቅድ አይደለም። ስለዚህ የሚነሳው የሚቀጥለው ጥያቄ፣ እንዲያ ከሆነ ታዲያ የፑቲን ምላሽ ምን ይሆናል? የሚለው ነው። በግሌ ሩሲያ በአውሮፓ ውስጥ ወታደራዊ ኢላማዎችን በተለመደው የጦር መሳሪያ ለመምታት በዝግጅት ላይ መሆኗን የሚያሳዩ ብዙ ምልክቶች እንዳሉ አምናለሁ። ይህ ደግሞ የተፈለገውን ውጤት ካላመጣ፣ የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ ከመጠቀም ሊከለክለው የሚችል ነገር አይኖርም።

: 🇮🇱 የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ በዛሬው ዕለት እንደተናገረው፡ እስራኤል ከምድር በላይ ሆነው ሥራዎችን ለማካሄድ የታቀዱ እና በጠፈር ላይ የተመሰረቱ የሌዘር አቅሞችን እያዳበረች ነው፣ ብሏል።

🇺🇦🇷🇺⚡️- ኔቶ ከዩክሬን ጋር በጋራ በመሆን፣ በሩሲያ ግዛት ውስጥ ዘልቀው ያሉ ሩቅ የአየር ማረፊያዎችን ጭምር፣ ለማጥፋት የሚያስችላቸውን የጦር መሳሪያ እየፈጠሩ ናቸው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር *-*-*- ታዲያሳ! ይሄን አላወቃችሁም እስካሁን? የኃይል መሠረተ ልማቶቻችሁን ረጅም ርቀት መጓዝ የሚችሉ ድሮኖችን ፈጥረው ዘልቀው በመግባት እንዳወደሙባችሁ፣ አሁን ደግሞ አየር ማረፊያዎቻችሁን ርቀትተጉዘው መጥተው፣ ሊያወድሙባችሁ የሚሉባቸውን ሚሳዬሎች እየፈጠሩ ናቸው። ያሳኩታል፣ ይመቱታል። ከዚያ አየር ኃይሉ መብረር እንዳይችል ሆኖ ሽባ ይሆናል ማለት ነው። ፑቲን እና ሰዎቹ፣ ገና እንደተኙ ናቸው። አላወቁትም እየመጣባቸው ያለውን።

🇮🇷 የኢራን መገናኛ ብዙሃን ፋርስ ዜና አገልግሎት፡ - "እስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን፣ የሚቃጡባትን ወታደራዊ አማራጮች ከጠረጴዛው ላይ ለማስወገድ፣ የአቶሚክ ቦምብ ከማግኘት ውጪ ሌላ አማራጭ የላትም። *-*- ቦንቡን ከታጠቅህ ዝንብህን እሽ የሚል አይኖርም፣ እያሉ ነው።

🇷🇺⚡️🇺🇦 ምሽቱን ከ800 በላይ የድሮን መንጋዎች ወደ ሩሲያ ግዛት ተልከዋል።
🇷🇺⚡️🇺🇦 ምሽቱን ከ800 በላይ የድሮን መንጋዎች ወደ ሩሲያ ግዛት ተልከዋል።

🇮🇱🇮🇷🇺🇸🇹🇷📰💢የእስራኤል ቻናል 12: በኩርዶች እርዳታ በኢራን ያለውን መንግሥት ለመገልበጥ ታቅዶ የነበረውን የሞሳድ ሚስጥርን ለኤርዶጋ ሹክ ያለውና ያሰናከለው ጄዲ ቫንስ እና የእሱ
🇮🇱🇮🇷🇺🇸🇹🇷📰💢የእስራኤል ቻናል 12: በኩርዶች እርዳታ በኢራን ያለውን መንግሥት ለመገልበጥ ታቅዶ የነበረውን የሞሳድ ሚስጥርን ለኤርዶጋ ሹክ ያለውና ያሰናከለው ጄዲ ቫንስ እና የእሱ ሰዎች ናቸው!

🇿🇦⚡️ - በመላው ደቡብ አፍሪካ፣ የፀረ-ስደተኛ ጥቃት እየተባባሰ በመምጣቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ሰነድ የሌላቸው ከርታቶች በመንግሥት ህንጻዎች፣ በአብያተ ክርስቲያና
🇿🇦⚡️ - በመላው ደቡብ አፍሪካ፣ የፀረ-ስደተኛ ጥቃት እየተባባሰ በመምጣቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ሰነድ የሌላቸው ከርታቶች በመንግሥት ህንጻዎች፣ በአብያተ ክርስቲያናት እና በሕዝብ መናፈሻዎች ውስጥ መጠለያ እንዲፈልጉ እና ከሀገሩ እንዲሰደዱ እየተገደዱ ናቸው፣ ሲል The Wall Street Journal ዘግቧል። የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት በበኩሉ፣ ድርጊቱ የሀገሩን መንግሥት እንደማይወክል በማስመልከት፣ ስደተኞች ይፈልሱባቸዋል ወደ ሚባሉ የአፍሪካ ሀገሮች፣ ዲፕሎማችን ሊልክ መሆኑና የደቡብ አፍሪካን ገፅታ በተዛባ ምልከታ እንዳያዩ ሊያሳምን በዝግጅት ላይ እንደሆነ ተናግሯል። *-*-*- ሆሳዕና ውስጥ ከሕፃናቱ ጋር አብረው እየቦረቁ በየ ቤቱ ያደጉትን ውሾች በሕፃናቱ በራሳቸው፣ በዛፍ ላይ በገመድ ሲጥ አድርገው እንዲገድሉ እያደረጓቸው ይገኛሉ። ዛፍ ላይ በገመድ በማነቅ፣ ሲቃቸው ራሱ ያስተኛል እንዴ? ሰላምስ ይሰጣል? በደቡብ አፍሪካ ያሉ የዚያ አካባቢ ልጆች፣ ይሄን ነውር በሙሉ ድምፅ ሊያወግዙ ይገባል።

🇺🇸⚡️🇮🇷ትራምፕ፡  ኢራን ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካን ለመገናኘት ቀጠሮ ይያዝልኝ ብላ በጠየቀችው መሠረት፣ ነገ በኳታር ዶሃ ችግሮቿን ለመስማት እንገናኛለን። ኢራን፡ አልጠየቅንም፣ ውሸቱን ነው፣ ግን እንገናኛለን።