የቀጠናው ተመልካች
رفتن به کانال در Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 307
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-227 روز
-8530 روز
آرشیو پست ها
4 306
🇺🇸🇷🇺 የሩሲያ ረጅም ርቀት ቦንብ ጣይ አይሮፕላን፣ TUPOLEV TU -22M3፣ በስልጠና ላይ እያለ ኢርኩትስ ግዛት ውስጥ መከስከሱ ተነገረ። ሁለቱ ፖይለቶች ቀድመው በመውጣት መትረፋቸው ተሰምቷል። ይሄ፣ ከፈረንጆች 2024 ጀምሮ፣ የተከሰከሰ 4ኛ TUPOLEV ነው።
በተመሳሳይ ቀን፣ ዛሬ፣ የአሜሪካው ረጅም ርቀት ስትራቴጂካል ቦንብ ጣይ አይሮፕላን፣ B52 Stratoforester, ምክኒያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በካሊፎሪያ ሞጃቭ በረሃ እንደተከሰከሰና በውስጡ የነበሩ 8 የበረራ አባላት ወዲያው ሕይወታቸው እንዳለፈ ታውቋል።
4 306
🇮🇷🇺🇸 ኢራን የመታቻቸው አረቦች፣ መልሰው በገንዘባቸው ኢራንን ሊገነቡ ነው።
New York Post
ኢራን በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት የመልሶ ግንባታ ካሳ ለማግኘት፣ በሩ ክፍት እንደሚሆንላት አሜሪካ ተናገረች።
$300 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ለኢራን ሊለቀቅ ይችላል።
አሜሪካ፣ ለዚህ ሥራ ወደ ሚቋቋመው አቁማዳ፣ የገልፍ አረብ ሀገራት ገንዘብ በማምጣት እንዲከቱ (በኢንቨስትመንት ስም) የምታመቻች እና ኢራን የስምምነቱን ነጥቦች እያንዳንዱን ያሟላች ጊዜ፣ ገንዘቡን በመቆጣጠር፣ በሂደት ለኢራን መልሶ ግንባታ የምትለቅ መሆኑ ተነግሯል።
*-*-*
አይ አረብ ይል ነበር ጋዳፊ፣ ነብሱን ይማረውና። አረቦች 'ስትመታው ይጠብቃል' አይደሉም፣ 'ስትመታው ይፈታል' ናቸው።
4 306
🇮🇷🇺🇸 ኢራን የመታቻቸው አረቦች፣ መልሰው በገንዘባቸው ኢራንን ሊገነቡ ነው።
New York Post
ኢራን በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት የመልሶ ግንባታ ካሳ ለማግኘት፣ በሩ ክፍት እንደሚሆንላት አሜሪካ ተናገረች።
$300 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ለኢራን ሊለቀቅ ይችላል።
አሜሪካ፣ ለዚህ ሥራ ወደሚቋቋመው ፈንድ፣ የገልፍ አረብ ሀገራት ወደ ገንዘብ እንዲያመጡ (በኢንቨስትመንት ስም) የምታመቻች እና ኢራን የስምምነቱን ነጥቦች እያንዳንዱን ያሟላች ጊዜ፣ ገንዘቡን በመቆጣጠር፣ በሂደት ለኢራን መልሶ ግንባታ የምትለቅ መሆኑ ተነግሯል።
*-*-*
አይ አረብ ይል ነበር ጋዳፊ፣ ነብሱን ይማረውና። አረቦች 'ስትመታው ይጠብቃል' አይደሉም፣ 'ስትመታው ይፈታል' ናቸው።
4 306
🇺🇦🇷🇺 እንገናኝና እኔ እና አንተ እንነጋገር፣ ምን ያስበጭጨሃል? -- ዘለንስኪ ለፑቲን
ፑቲን ጋር በየትም ለመገናኘት ግብዣ አቅርበንለታል፣ በየትም ውነተኛ ውሳኔዎች በሚወሰኑበት መድረክ ላይ! አልፈለገም።
እኛ ከአሜሪካ እና ከፈረንሳይ ጋር፣ ሁሉም ዲሞክራሲያዊ ሀገሮች በሚገኙበት፣ በ G7 ስብሰባ ላይ፣ ከሩሲያ ጋር ለመገናኘት ጠይቀነዋል፣ አልፈለገም።
ትናንት፣ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር፣ አሜሪካ ውስጥ በሚዘጋጅ የግንኙነት መድረክ ላይ ለመገናኘት ሐሳብ አቅርበንለታል። ቢያንስ ፑቲን ትራምፕን እንደሚፈራው እና እምቢ እንደማይለው እናውቃለን። መልሱን እየጠበቅን ነው።
ይህንን ዕድል የሚያሳልፍ ከሆነ ግን፣ አዝናለሁ። በሩሲያ ላይ ጫናችን እናጠናክራለን።
*-*-*
ፑቲን፣ ከዩክሬን ጋር ለመገናኘት ሞስኮ ካልሆነ የትም አይሆንም ብሏል። ዩክሬን ደግሞ፣ ሞስኮ እንድንገናኝ የምትፈልገው 'አሸናፊ መስለህ ለመታየት' ነው፣ መገናኘት ካለብን ገለልተኛ ሜዳ ይሁን ብላለች።
ፑቲን ከሞስኮ ለመውጣት ያልፈለገው ለምን እንደሆነ ግልጽ አይደለም።
4 306
🇺🇸🇮🇷⚡️- ሰበር ዜና: ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እና የኢራን የፖርላማ አፈ- ጉባኤ ሙሐመድ ባጋር፣ በኢሌክትሮኒክስ የመግባቢያ ስምምነቱን ተፈራረሙ። በአካል፣ ዓርብ እንደ ፈረንጆች June 19 2026, በጄኔቫ የሚፈራረሙ ይሆናል።
4 306
ሱማሌላንድ ታሪካዊ ስምምነቶችን ከእስራኤል ጋር፣ በኢኮኖሚ፣ በፀጥታ፣ በማህበራዊ እና በጤና ዘርፎች መፈራረሟ ተገለፀ። ቆንስላ ጽሕፈት ቤቷንም በኢየሩሳሌም ከፍታለች።
*-*-*
የሱማሌላንዱ አብዱላሂ፣ ከበሻሻው ጉብል በላይ በዓለም አቀፉ ፖለቲካ ውስጥ ቁልፍ ሰው እየሆነ እንደሆነ ያሳያል። የበሻሻው ስልክ ዛሬ ላይ በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ እራሱ የሚነሳለት አይመስለኝም። Trendዱ ከመረቡ ላይ ጠፍቷል።
4 306
🇮🇱 የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር እና በመጪው ምርጫ ተወዳዳሪ እጩው፣ ናፍታሊ ቤኔት -
• "የእስራኤልን ማህበረሰብን የሚያዝል፣ ተጠባባቂ ሠራዊታችንን የሚያደክም፣ ኢኮኖሚውን የሚያላሽቅ እና ዓለም አቀፍ አቋማችንን በእጅጉ የሚጎዳ ቀጣይነት ያለው ጦርነት መኖር፣ የእስራኤል መርህ ሆኖ አያውቅም።
• ከዚህ መንግስት ጋር ሌላ አራት ዓመት፣ ኢኮኖሚ አይኖረንም፣ ማህበረሰብ አይኖረንም።
• "ኔታንያሁ በቀላሉ ከአሁን በኋላ ምንም ማድረግ የሚችለው ነገር የለም። ሕዝባችን በፖሊሲዎቹ ብቭታ ውስጥ ነው፣ ድካም ውስጥ ነው። ጦርነቶችን ማሸነፍ አይችልም። ወንጀልን መቋቋም አይችልም። ዋጋን ዝቅ ማድረግ አይችልም። አልትራ-ኦርቶዶክስን ከእስራኤል ማህበረሰብ ጋር ማዋሃድ አይችልም።" (The Times of Israel)
🔗
4 306
—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባቃይ -
- በመግባቢያ ስምምነቱ መሠረት ኢራን ከኦማን ጋር በመቀናጀት በሆርሙዝ ባህር በኩል የሚደረገውን መተላለፊያ የማስተዳደር ሃላፊነት ይኖርባታል።
- ኢራን ክፍያ ለመጫን እየፈለገች አይደለም። ነገር ግን ለአሰሳ አገልግሎቶች፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለኢንሹራንስ እና ለሌሎች የባሕር አገልግሎቶች በምላሹ አስፈላጊውን ክፍያ ትሰበስባለች።
***-*-
"ክፍያ ትሰበስባለች" የሚለው ዋና ቁም ነገሩ ነው። የቆዳም በለው የኮቴ፣ ገንዘብ መሰብሰብ ነው። ይሄ ሁሉ ከዚህ በፊት ያልነበረ ክፍያ ነው፣ አሁን ኢራን የምትሰበስበው።
ኢራን ሀብታም ልትሆንላችሁ ነው ። ኬላ ባሕር ላይ ዘርግታ፣ ይሄን ሆዱን ሩዝ የቆዘረውንና ቀሚሱን እየጎተተ ሲያስቸግር የከረመውን አረብ፣ "ና አንተ፣ ወዴት ነው የምታልፈው፣ ና ወዲህ! ክፈል! ጎሽሽ እያለች ቋ ልታደርገው ነው። አላርፍ ብሎ ነበር ከአይሁድ ጋር እያንዛረጠ፣ ያዘችው።
4 306
⚡️🤝 የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሱማሌላንድ ፕሬዝዳንት ጋር፡
ለእስራኤል ማንም ወሳኝ አይሆንም፣ ለሱማሌላንድ ማንም ወሳኝ አይሆንም፣ ከማን ጋር ዲፕሎማቲካዊ ግንኙነት ማድረግ እንዳለብን።ትናንት የተጀመረው የሱማሌላንድ የእስራኤል ጉብኝት ዛሬም እንደቀጠለ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ የእስራኤል ፕሬዝዳንትን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝቶ ተወያይቷል። *-*-*- በሱማሌላንድ እና በእስራኤል መቀራረብ የተነሳ ቱርክ ከፍተኛ ድብርት ውስጥ የገባች ሲሆን፣ ከሷ ባሻገር፣ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትርም እንዲሁ፣ በቀጠናው የነበረው ቁልፍ ሚና፣ በመንግስቱ በተደጋጋሚ በሚፈፀሙ ጅምላ ግድያዎች፣ የእርስ በርስ ጦርነቶች እና የባሕር በር አልባነት ጋር ተደማምሮ እና በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በመገለሉ የተነሳ ተሸርሽሮ ገደል ገብቷል።
4 306
+2
🇱🇧🇺🇸🇮🇷🇮🇱 በደቡብ ሊባኖስ ዛሬ ንጋት ጀምሮ፣ የኢራን-አሜሪካ ስምምነት መታወጁን ተከትሎ ነዋሪዎች ወደ ቄያቸው እየተመለሱ ይገኛሉ። የተዘጋጉ መንገዶች በመከፈት ላይ እንደሆኑ እና ረጃጅም የመኪና መዘጋጋቶች እንደተፈጠሩ ለማየት ተችሏል።
በሌላ ሮይተርስ በዘገበው ዜና፣ የሂዝቦላ ከፍተኛ ባለስልጣን፣ ቡድኑ ሁለቱ ሀገሮች ስምምነት ላይ መድረሳቸው ከታወቀ በኋላ፣ በእስራኤል ኃይሎች ላይ ምንም ዓይነት ወታደራዊ ጥቃት እንዳልፈፀመ ተናግሯል። ነገር ግን፣ የእስራኤል ጦር በሀገራችን "የመንቀሳቀስ ነፃነት" እንዲኖረው አንፈቅድም ብሏል።
4 306
🇷🇺🇺🇦 የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት በርዝማኔው የአንደኛ የዓለም ጦርነትን በለጠ።
• የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት 1570ኛ ቀኑን ይዟል። ከሁለቱም ወገን በሚሊዮኖች ሞተዋል፣ በሚሊዮኖች ቆስለዋል። በሚሊዮኖችም ከቀያቸው ተሰደዋል። እጅግ ዘመናዊ እና ሰው ጨራሽ መሳሪያዎች (እንደ FPV ድሮን) ያሉ በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉበት፣ በLive የሚታይ ጦርነት ነው። ከፍተኛ የተዋጊዎችን ሕይወት የቀጠፈ በድሮ ዘይቤ የሚደረግ ዘመናዊ ጦርነት ሆኗል፣ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት።
• ጦርነቱ የተጀመረው እንደ ፈረንጆች በFebruary 24 2022 ይባል እንጂ (የቀናቱ ቁጥር በዚህኛው ጅማሮ ላይ የተመሠረተ ነው) የቀጠናውን ሁኔታ በደንብ ለሚያውቅ፣ የተጀመረው ከዚያ ስምንት ዓመት ቀደም ብሎ እንደ ፈረንጆች 2014 ላይ ነበር።
4 306
🇷🇺🇺🇦 የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት በርዝማኔው የአንደኛ የዓለም ጦርነትን በለጠ።
• የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት 1570ኛ ቀኑን ይዟል። ከሁለቱም ወገን በሚሊዮኖች ሞተዋል፣ በሚሊዮኖች ቆስለዋል። በሚሊዮኖችም ከቀያቸው ተሰደዋል። እጅግ ዘመናዊ እና ሰው ጨራሽ መሳሪያዎች (እንደ FPV ድሮን) ያሉ በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉበት፣ በLive የሚታይ ጦርነት ነው። ከፍተኛ የተዋጊዎችን ሕይወት የቀጠፈ በድሮ ዘይቤ የሚደረግ ዘመናዊ ጦርነት ሆኗል፣ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት።
• ጦርነቱ የተጀመረው እንደ ፈረንጆች በFebruary 24 2022 ይባል እንጂ (የቀናቱ ቁጥር በዚህኛው ጅማሮ ላይ የተመሠረተ ነው) የቀጠናውን ሁኔታ በደንብ ለሚያውቅ፣ የተጀመረው ከዚያ ስምንት ዓመት ቀደም ብሎ እንደ ፈረንጆች 2014 ላይ ነው።
4 306
🇮🇱 የእስራኤሉ Yediot Ahronot እንደዘገበው፣ ኔታንያሁ ለትራምፕ የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ እንደማይወጣ እና ባለበት እንደሚቆይ ነግሮታል።
4 306
🇷🇺🇺🇦 የኪየቭ ከንቲባ ክሊትሼንኮ፣ በመላው የከተማው ወረዳዎች እሳት ነበር ሲል ተናግሯል።
ሩሲያ የዩክሬንን ዋና ከተማ ስትደበድብ አድራለች።
4 306
🇺🇦⚡️🇷🇺 ዩክሬን፡ "$20 ቢሊዮን ዶላር ስጡኝ፣ ሩሲያን ላቃጥላት" አለች። POLITICO
ዩክሬን፣ ለጋሽ ሀገሮች $20 ቢሊዮን ዶላር እንዲያዋጡላት ፍላጎቷ እንደሆነ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ተናግሯል። ጥያቄዋን፣ በይፋ በመጪው በአንካራ በሚካሄደው የኔቶ ስብሰባ ላይ ታቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል።
የኔቶ ፕሬዝዳንት፣ ማርክ ሩቶ በበኩሉ፣ አባል ሀገራቱ፣ እያንዳንዳቸው ከ$2-$6 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ መዋጮ በራሳቸው ላይ አስበው እንዲያዋጡ፣ ዩክሬንም ከጠየቀችውም በላይ፣ $60 ቢሊየን ዶላር እንደሚሰጣት መናገሩ ታውቋል።
*-*-*-*
ከሩሲያ መንኮታኮት በኋላ፣ ሁሉም 'የቂጣውን ቁራሽ' ለማግኘት በከፍተኛ ሁኔታ ቋምጧል። እያንዳንዳችሁ አስር ቢሊዮን ቢባሉም፣ ያዋጣሉ።
4 306
🇺🇦⚡️🇷🇺 ዩክሬን፡ "$20 ቢሊዮን ዶላር ስጡኝ፣ ሩሲያን ላቃጥላት" አለች።
ዩክሬን፣ ለጋሽ ሀገሮች $20 ቢሊዮን ዶላር እንዲያዋጡላት እንዲሰጧት ፍላጎቷ እንደሆነ ተሰምቷል። ጥያቄዋንም በይፋ በመጪው በአንካራ በሚካሄደው የኔቶ ስብሰባ ላይ ታቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል።
የኔቶ ፕሬዝዳንት፣ ማርክ ሩቶ በበኩሉ፣ አባል ሀገራቱ ላይ በእያንዳንዱ ከ$2-$6 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ መዋጮ እንደሚጣል፣ ዩክሬንም ከጠየቀችውም በላይ፣ $60 ቢሊየን ዶላር እንደሚሰጣት መናገሩ ታውቋል።
4 306
🇺🇦⚡️🇷🇺 "ዩክሬን፡ $20 ቢሊዮን ዶላር ይሰጠኝ፣ ሩሲያን ላቃጥላት" አለች።
ዩክሬን፣ ለጋሽ ሀገሮች $20 ቢሊዮን ዶላር እንዲያዋጡላት እንዲሰጧት ፍላጎቷ እንደሆነ ተሰምቷል። ጥያቄዋንም በይፋ በመጪው በአንካራ በሚካሄደው የኔቶ ስብሰባ ላይ ታቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል።
የኔቶ ፕሬዝዳንት፣ ማርክ ሩቶ በበኩሉ፣ አባል ሀገራቱ ላይ በእያንዳንዱ ከ$2-$6 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ መዋጮ እንደሚጣል፣ ዩክሬንም ከጠየቀችውም በላይ፣ $60 ቢሊየን ዶላር እንደሚሰጣት መናገሩ ታውቋል።
