fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 293
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-217 روز
-9130 روز
آرشیو پست ها
— 🇮🇷/🇶🇦 ኢራንን መጥፎ ጎረቤት ለሚሉ የባሕረ ሰላጤው አረቦች… ሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ባህሬን ከኳታር ጋር ግንኙነታቸውን ሲያቋርጡ እና የኢኮኖሚ እገታን ሲጥሉ፣ ምግ
— 🇮🇷/🇶🇦 ኢራንን መጥፎ ጎረቤት ለሚሉ የባሕረ ሰላጤው አረቦች… ሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ባህሬን ከኳታር ጋር ግንኙነታቸውን ሲያቋርጡ እና የኢኮኖሚ እገታን ሲጥሉ፣ ምግብ እና ሰብአዊ እርዳታዎችን ሙሉ በሙሉ በነጻ በመላክ በሕይወት እንዲቆዩ ያደረገችው ኢራን ነበረች። እ.ኤ.አ ከ2017-2021, ለአራት ዓመታት በዘለቀ ሳዑዲ መራሽ ማዕቀብ፣ የአረብ ሀገሮች፣ ኳታርን አክራሪዎችን ትደግፊያለሽ፣ አልጀዚራ የተሰኘው የዜና ማሰራጫ ጣቢያሽም ስማችንን እያጠፋ ነው በሚል ሰበብ፣ በየብስም፣ በአየርም የትራንስፖርት እቀባና የኢኮኖሚ ማዕቀብ በመጣል አሽተዋት ነበር። ኳታር ልትሰበርና በረሃብ ልትጠበስ ትችል ነበር፣ ለኢራን ባይሆን ኖሮ። ኢራን ከዓለም መገናኛ በሮችን በሷ በኩል ለኳታር በመክፈትና የምግብ ፍጆታዎችን በየቀኑ በነፃ በመላክ ሕይወቷን አስቀጥላለች። 1100 ቶን አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም 60 ቶን የበሬ ሥጋ በየቀኑ ለአራት ዓመታት ልካላታለች።

🇮🇱⚡️🇱🇧 ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከጥቂት ጊዜ በፊት በቴል አቪቭ በሚገኘው ኪሪያ ከመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እና ከጄኔራል ስታፍ አለቃ ሜጀር ጄኔራል ኢያል ዛሚር ጋር የደህንነት ምክክር አድርገዋል። እስራኤል ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ Yellow Line የሚባለውን በሊባኖስ የሚገኝ ድንበርን ተሻግራ ወደ ፊት እየገፋች ነው። ቤሩት ሲቀር በመላው ሊባኖስ በአሁኑ ሰዓትም ድብደባዎች እየተካሄዱ ናቸው። እስራኤል፣ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ሊደረስበት ያለውን ስምምነት ለማምከን፣ ፍላጎት ያላት ይመስላል።

🇮🇷 ከሦስት ወር መጥፋት በኋላ በኢራን ኢንተርኔት ተለቋል። እዛ ያላችሁ ነዋሪዎች እንግዲህ ለቀጠናው መረጃዎችን በማስተላለፍ እንድታግዙን እንማጠናለን 😂😂
🇮🇷 ከሦስት ወር መጥፋት በኋላ በኢራን ኢንተርኔት ተለቋል። እዛ ያላችሁ ነዋሪዎች እንግዲህ ለቀጠናው መረጃዎችን በማስተላለፍ እንድታግዙን እንማጠናለን 😂😂

—❗️🇺🇸/🇮🇷 ሰበር ዜና፦ እንደ Wall Street Journal ዘገባ የአሜሪካ የባሕር ኃይል በሆርሙዝ ወሽመጥ 'ፕሮጀክት ፍሪደም'ን እንደገና ሊያስጀምር ነው። ባለሥልጣናት እንደተናገሩት፣ የ
—❗️🇺🇸/🇮🇷 ሰበር ዜና፦ እንደ Wall Street Journal ዘገባ የአሜሪካ የባሕር ኃይል በሆርሙዝ ወሽመጥ 'ፕሮጀክት ፍሪደም'ን እንደገና ሊያስጀምር ነው። ባለሥልጣናት እንደተናገሩት፣ የባሕር ኃይሉ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ሱፐርታንከሮችን እና የኮንቴይነር መርከቦችን ጨምሮ ወደ አንድ ደርዘን የሚጠጉ የሲቪል መርከቦችን በሆርሙዝ መተላለፊያ ለማገዝ እና ለመሸኘት አቅዷል።

FPV የሚባሉ የ$100 ዶላር ድሮኖች እንደ ትንኝ ናቸው፣ ጥዝ ጥዝ እያሉ ሰላምህን ይቀሙሃል፣ ከዚያ በሂደት ትለፈልፋለህ። ** — 🇮🇱/🇱🇧 የእስራኤል የፋይናንስ ሚኒስትር፣ ቤዛሌል ስሞትሪች፣ በሊባኖስ ላይ የዘር ጭፍጨፋ ለማድረግ ያለውን ሐሳብ በግልጽ አውጇል፣ ይላሉ በዚህ ንግግሩ የቀጠናው ተንታኞች። ሚኒስትሩ ግን ሂዝቦላን ለማስቆም ብቸኛው መንገድ ይሄ ነው፣ ነው የሚለው።
ሂዝቦላን ለማስቆም በጣም ውጤታማው መንገድ ለእያንዳንዱ የFPV ድሮን በቤሩት ውስጥ 10 ሕንፃዎች እንደሚወድሙ ማስታወቅ ብቻ ነው። ለምሳሌ፣ ሰባት ድሮኖች ካሉ፣ ከዚያ 70 ሕንፃዎች፣ ቁጭ። 15 ቢሆኑ፣ 150 ሕንፃዎች ይደመሰሳሉ። እና በቤሩት ያሉት ሕንፃዎች ሁሉ ከጠፉ፣ ወደ ጢሮስ፣ ሲዶና እና ወደ ቤቃአ ሸለቆ እንሄዳለን።' 

🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 "እሺ አሁን ለልጆቻችን ምን ብለን ነው የምንነግረው? አሁንም በድጋሜ ተሸነፍን ብለን ነው? ውድቀት አይበቃንም? አውሮፓ ራሱ አልፈልጋችሁም እያለን እኮ ዛሬ፣ እንዲያውም ካሁን በኋላ ደቡብ አሜሪካ ነው የምንሄደው፣ እዛ ይሻለናል።" አውሮፓዊት አይሁድ በእስራኤል ቲቪ። ** እስራኤላዊያን ኢራን ያለመፍረሷን እና በእኩል ከአሜሪካ ጋር በድርድር ጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጧን እንደ ሽንፈት ቆጥረውታል። በእርግጥ እስራኤል በኢራን ጦርነት ብዙ ነገር አጥታለች፣ በዋናነት ሞራሏን። ረዘም ያለ መደበኛ ጦርነት፣ መንግሥት ካለው ነፃ ሀገር ጋር፣ ብዙም እንደማችይሉ ያዩበት ጦርነት ነው። ምናልባት ሽምቅ ተዋጊ ቡድኖችን፣ እንደ ሐማስ እና ሂዝቦላ ያሉ፣ ላይ ጠንካራ ትሆናለች። በሀገረ ደረጃ ካለ ጦር ጋር ግን፣ አቅማቸው ውስን እንደሆነ ያወቁበት ነው። በዚህ ጦርነት አሜሪካ ከእራኤል ጎን ባትሆን ብላችሁ አስቡት፣ እስራኤል ኢራንን ትችላታለች? ከአሜሪካ ጋር ሆናም ኢራንን ማንበርከክ አልቻሉም።

— 🇮🇷/🇸🇦 ዛሬ በአረፋ ቀን በመካ የነበሩ ኢራናዊ ሐጃጆች በእስራኤል እና በአሜሪካ ላይ ውግዘቶችን እንዲሁም አያቶላ ኻመኂን በመደገፍ መፈክሮችን አሰምተዋል በሐጅ ወቅት የፖለቲካ መፈክሮችን እንዲያሰሙ በሳውዲ ዓረቢያ የሚፈቀድላቸው ብቸኛው የሐጃጆች ቡድን ኢራናውያን ናቸው።

🇺🇦⚡️🇷🇺 የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፦ ሞስኮ በኪየቭ ላይ ከባድ ጥቃቶችን አቅዳለች። በኪየቭ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ ለቅቃችሁ
🇺🇦⚡️🇷🇺 የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፦ ሞስኮ በኪየቭ ላይ ከባድ ጥቃቶችን አቅዳለች። በኪየቭ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ ለቅቃችሁ እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን።

🇹🇷 የቱርክ የመገበያያ ገንዘብ የሆነው ሊራ፣ በታሪኩ ተፈጥፍጦ የማያውቀውን መፈጥፈጥ ተፈጥፍጧል። በአሁኑ ጊዜ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ 45.70 የቱርክ ሊራ እየተመነዘረ ነው። መጠኑ፣ የዛሬ ሁለ
🇹🇷 የቱርክ የመገበያያ ገንዘብ የሆነው ሊራ፣ በታሪኩ ተፈጥፍጦ የማያውቀውን መፈጥፈጥ ተፈጥፍጧል። በአሁኑ ጊዜ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ 45.70 የቱርክ ሊራ እየተመነዘረ ነው። መጠኑ፣ የዛሬ ሁለት ዓመት ከነበረው የምንዛሬ መጠን ጋር ሲነፃፀር -99.99% ውድቀት አሳይቷል ተብሏል። ኢኮኖሚስቶች፣ ይህን የቱርክ ኢኮኖሚ መንደባለልን 'እጅግ አሳሳቢ እና ፍጥነት ያለው መፍትሄ የሚሻ' ሲሉ ገልፀውታል። IMFም በአሁኑ ሰዓት እንደ ጆፌ አሞራ እየዞራት ይገኛል። ቱርክ፣ ተቀማጭ ገንዘቧን ሁሉ ሌላ የታመመ የኢኮኖሚ ዘርፏን ለማከም ብላ አውጥታ መጨረሷንና፣ ብዛት ያለውን የወርቅ ክምችቷንም በገፍ መሸጧ ታውቋል።

🇪🇹 ⚡️በትናንትናው ዕለት፣ በወለጋ አማራ ታጣቂዎች (ፋኖ) እና በመንግሥት ታጣቂዎች መካከል በነበረ ውጊያ፣ የተገደለው የወታደር አዛዥ ማንነት የታወቀ ሲሆን፣ የቀብር ሥነ ስርዓቱ ዛሬ መገባደዱ
🇪🇹 ⚡️በትናንትናው ዕለት፣ በወለጋ አማራ ታጣቂዎች (ፋኖ) እና በመንግሥት ታጣቂዎች መካከል በነበረ ውጊያ፣ የተገደለው የወታደር አዛዥ ማንነት የታወቀ ሲሆን፣ የቀብር ሥነ ስርዓቱ ዛሬ መገባደዱ ተገልጿል። በዚህ ጦርነት ሌላ የማዕከላዊ እዝ ከፍተኛ አመራርም አብሮ መገደሉ ታውቋል። በዚህ ውጊያ አንድ ሬጅመንት ማለቁን እና ስምንት ወታሀራዊ ተሽከርካሪዎች መማረካቸውን የፋኖ ቃል-አቀባይ ለሚዲያ ገልጿል። በዚህ ጥቃት ምክትሉ የተገደለበት የማዕከላዊ እዝ አዛዥ፣ ጄኔራል ዘውዱ በላይ፣ ጦሩን ለበቀል እንዲዘጋጅ እያደረገ እንደሆነ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና የአሜሪካ ማዕከላዊ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ለ FOX NEWS: ዛሬ፣ በዚህ ሰዓት፣ ከኢራን የተቃጣብንን ጥቃት ለመቀልበስ እና እራሳችንን ከጥቃቶቻቸው ለመከላከል፣ በተለያዩ የኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ፣ እርምጃዎችን ወስደናል። ፈጣን የጦር ጀልባዎችን፣ የሚሳዬል ማስወንጨፊያዎችን እና የተለያዩ ወታደራዊ ዒላማዎችን መተናል። አሁንም፣ ትንኮሳው ከኢራን በኩል የሚቀጥል ከሆነ፣ እራሳችንን ለመከላከል ዝግጁ ነን!'

🇮🇷⚡️🇺🇸 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፡ አሜሪካ የተያዘብንን ገንዘብ ትልቀቅልን እንጂ፣ በገንዘቡ ድሮንና ሚሳዬሎችን፣ ቦንቦች እና ሮኬቶችን እንሰራበታለን።

— 🇺🇸/🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ በTruth Social ላይ፦ 'የበለጸገው ዩራኒየም (የኒውክሌር አቧራ!) ወይ ወዲያውኑ ወደ አሜሪካ ተላልፎ እዚሁ ሀገር ቤት ይወገዳል ወይም፣ በተሻለ ሁኔታ፣ ከ
— 🇺🇸/🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ በTruth Social ላይ፦
'የበለጸገው ዩራኒየም (የኒውክሌር አቧራ!) ወይ ወዲያውኑ ወደ አሜሪካ ተላልፎ እዚሁ ሀገር ቤት ይወገዳል ወይም፣ በተሻለ ሁኔታ፣ ከኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጋር በጋራ እና በቅንጅት፣ በቦታው ላይ ወይም ተቀባይነት ባለው ሌላ ቦታ፣ የአቶሚክ ኢነርጂ ኮሚሽን ወይም ተመጣጣኙ የዚህ ሂደት እና ክስተት ምስክር ሆኖ ባለበት ይወገዳል። ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ስለሰጡ እናመሰግናለን!'
** ኢራን 'ዩራኒየሜን ለአሜሪካ አልሰጥም፣ ለሦስተኛ ወገን (ቻይና) ብሰጥ እመርጣለሁ'፣ ማለቷ ልብ ሊባል ይገባል። ኢራን የዩራኒየም አቧራውን ለአሜሪካ ማስረከብ አትፈልግም። ለሦስተኛ ሀገር መስጠትን ግን በአደራ ያስቀምጡልኛል (ስፈልግ ይመልሱልኛል) በሚል የምትፈልገው ነው። በመጀመሪያ ለዚህ አደራ ሩሲያ ታስባ ነበር፣ አሜሪካኖች ስላልተስማሙ ቀርቷል። በሌላ በኩል ኢራን፣ አቧራውን ለማንም ከምሰጠው ራሴው አሁን ካለበት 60% ጥራት አቅጥኜ ወደ 20% እና 30% የጥራት ደረጃ (ከዚያ ለኒውክሌር መሳሪያ አይሆንም) አደርገዋለሁ ትላለች። ይህን ሐሳብ አሜሪካ ልትገዛው ትችላለች። ለአሁን በቻይና ሊስማሙ ይችላሉ።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ በርካታ ፍንዳታዎች በኢራን እየተሰሙ ናቸው፣ የአሜሪካ ድሮን በሁለተኛ ትልቁ ከተማዋ፣ በኢስፋሃን፣ ባሁኑ ሰዓት ይበራል፣ እንደ አካባቢው ምንጮች።
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ በርካታ ፍንዳታዎች በኢራን እየተሰሙ ናቸው፣ የአሜሪካ ድሮን በሁለተኛ ትልቁ ከተማዋ፣ በኢስፋሃን፣ ባሁኑ ሰዓት ይበራል፣ እንደ አካባቢው ምንጮች።

—❗️🇮🇷/🇮🇱/🇱🇧 ኢራን በቤይሩት ላይ የሚደረግ ማንኛውም የእስራኤል ጥቃት ከባድ መዘዝ እንደሚኖረው እና 'የዲፕሎማሲያዊ መንገዱን ሙሉ በሙሉ ከመስመር ሊያወጣ' እንደሚችል ለአሜሪካ አስጠን
—❗️🇮🇷/🇮🇱/🇱🇧 ኢራን በቤይሩት ላይ የሚደረግ ማንኛውም የእስራኤል ጥቃት ከባድ መዘዝ እንደሚኖረው እና 'የዲፕሎማሲያዊ መንገዱን ሙሉ በሙሉ ከመስመር ሊያወጣ' እንደሚችል ለአሜሪካ አስጠንቅቃለች – አል ጀዚራ

ደረቱን ለአርሴናል የሚሰጠው ኢትዮጵያዊ ትውልድ። ምግብ ውስጥ ነው ወይስ ውሃ ውስጥ ነው ማምከኛውን የጨመሩበት?

🇺🇸🇸🇦 — ሳዑዲ ዓረቢያ አጥፍቶ ጠፊ ድሮን ልትሠራ ነው። ፋብሪካው በሪያድ አቅራቢያ በመገንባት ላይ ይገኛል። በአሜሪካ ክፍለ ሀገር በUTAH ውስጥ በተመሠረተው Vector Defense እና በ
🇺🇸🇸🇦 — ሳዑዲ ዓረቢያ አጥፍቶ ጠፊ ድሮን ልትሠራ ነው። ፋብሪካው በሪያድ አቅራቢያ በመገንባት ላይ ይገኛል። በአሜሪካ ክፍለ ሀገር በUTAH ውስጥ በተመሠረተው Vector Defense እና በሳዑዲ በቅርብ ጊዜ በተቋቋመው SR2 Defense Systems መካከል፣ SR2Vector የተባለ የጋራ ጥምረት በመፍጠር፣ ለሳዑዲ ዓረቢያ ድሮን ሊሠራ ነው። ይህ ድሮን ለሀገር ውስጥ አገልግሎት የሚውል እና ለአጋር ሀገራት የሚላክ ነው የተባለ ሲሆን፣ የኢራን ሸሂድ ድሮንን እንደ መነሻ እና ማበረታቻ ወስዶ ተመሳሳዩን እንደሚያመርት ተናግረዋል። ፋብሪካው፣ በአሁኑ ሰዓት በሪያድ አቅራቢያ እየተገነባ ይገኛል። ድሮኑ እስከ 1,500 ኪሎ ሜትር ርቀት ያሉ ኢላማዎችን የመምታት አቅም ሲኖረው፣ ይህም በግምት ከሳዑዲ ዓአረቢያ ሰሜን ምስራቅ የባሕር ዳርቻ እስከ ቴህራን ካለው ርቀት ጋር የሚዛመድ ነው። ፕሮጀክቱ በሳውዲ አረቢያ በቪዥን 2030 ስር የአካባቢውን የመከላከያ ማምረቻ ለማስፋፋት ከሚደረጉ ሰፊ ጥረቶች አካል ነው። 

—❗️🇮🇱/🇱🇧/🇮🇷 ትኩስ ዜና፦ እስራኤል በቤሩት ላይ ጥቃቶችን የሚያካትት 'የእሳት ቀስቶች ዘመቻ' ያለችውን እቅዶችን አጽድቃለች። በጥቂት ሰዓታት ድብደባ ትጀምራለች ተብሏል። እስራኤል፣ የአሜሪካ እና ኢራንን የድርድር ሂደት እንዲህ ባሉ እርምጃዎች ማደናቀፍ የፈለገች ይመስላል። ጦርነቱን ለማቆም አንዱና ዋነኛው የኢራን ቅድመ ሁኔታ ወይም በድርድሩ መካተት አለበት የምትለው፣ የሊባኖስ ጉዳይ ነው። 'በሊባኖስ ላይ የሚደረገው ጥቃት መቆም አለበት' የሚለው ነው።

🇱🇧⚡️🇮🇱 ቤሩት፣ ሕዝቡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ እስራኤል ልትደበድብ ነው በሚል ከተማውን ለቅቆ እየወጣ ነው።

❗️❗️ይሄ፣ በጋዛ በጥቂት ወራቶች የተፈጸመ ነው፣ ከምድረ ገጽ ደልዛቸዋለች እስራኤል። ይሄን አይቶ ዘር ማጥፋት ወይም ጀኖሳይድ አይደለም የሚል አይኖርም። በሀገራችን ኢትዮጵያም፣ ይህ በብዛት ተፈጽሟል፣ ዛሬም እየተፈጸመ ያለ ነው። ባለፉት አንድ አሥርተ ዓመታት፣ የሕዝብ ፍጅቶችን መስማት የሁል ጊዜ መደበኛ መረጃ ነው። ሕዝብ ድለዛ በተለያዩ ቦታዎች ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በአብዛኛው ገጠር ውስጥ ስለሚኖር፣ በሞንታርቦም ተጩኾለት ሁኔታው ሳይሰማ ቢቀር እንጂ፣ የማይታወቅ አይደለም። እጅግ ብዙ የገጠር መንደሮች፣ በእንዲህ ያለ ሁኔታ፣ ከነ ሕዝባቸው፣ መንግሥት ባነሳሳቸው በዘር ጥላቻ የታወሩ ሰዎች፣ ሙሉ በሙሉ ተደልዘዋል። በከተማዎች እምብርትም፣ ከጋዛ የበለጠ ሕዝብ ጎዳና ወድቆ ለማኝ ሆኗል። እንደ ጋዛ በግላጭ የሚታይ ስለሆነ የሚካድ ነገር አይደለም። ሀገሮች 'ኢትዮጵያን እንዳትመስሉ' ማለት ጀምረዋል፣ ሲያስጠነቅቁ ሕዝባቸውን።