fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 301
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-137 روز
-8030 روز
آرشیو پست ها
🇸🇦🇰🇼🇺🇸 ሳዑዲ እና ኩዌት ጦር ሰፈሮቻቸውን ለአሜሪካን "ወታደራዊ ተደራሽነት ለሆርሙዝ ተልዕኮ" ወደነበረበት ይመልሳሉ። ሳውዲ ዓረቢያ እና ኩዌት፣ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮቻቸው እና የአየር ክልላቸው ላይ የጣሉትን ገደቦች በማንሳት፣ ዋሽንግተን በሆርሙዝ ባሕር ውስጥ ያሉ መርከቦችን ለመጠበቅ ሥራዎችን ዳግም እንድትጀምር መንገድ ጠርገዋል። ገደቦቹ የተጣሉት የባሕረ ሰላጤው ሀገራት ስለ ኢራን የበቀል እርምጃ ስጋት ካነሱ እና በቅርቡ በክልሉ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ተከትሎ የአሜሪካን የደህንነት ዋስትናዎች ከጠየቁ በኋላ ነው። የአሜሪካ ባለስልጣናት ቁልፍ የሆነው፣ የነዳጅ ማጓጓዣ መንገድን እንደገና ለመክፈት ያለመ የባሕር ኃይል አጃቢ ተልዕኮ፣ በዚህ ሳምንት ሊቀጥል ይችላል ብለዋል።

- 🇮🇱 /🇱🇧/ 🇮🇷 ትኩስ ዜና፡ እስራኤል ትናንት በቤሩት ያደረገችው የግድያ ሙከራ አልተሳካም ወይም 'ዒላማውን አልመታም' ስትል ተናግራለች። ይህን ያለችው የRedwan ክፍለ ጦር አዛዥን በቤሩት በድሮን መግደሏን ትናንት ከገለፀች በኋላ ነው። አሁን እንደወጣ መረጃ ግን፣ አመራሩ በሕይወት እንዳለ ያሳያል። እስካሁን ድረስ እስራኤል በዚህ ጦርነት ወቅት ምንም የተሳካ ከፍተኛ ግድያ አልፈፀመችም። ሂዝቦላህ ከፈረንጆች 2024 ጀምሮ ደህንነቱን እና ሰኪውሪቲውን ያስተካከለ ይመስላል።

- 🇺🇸 / 🇮🇷 IRGC ሜጀር ጄኔራል ሙህሲን ረዛ፡ "አሜሪካ ኢራን ዘገምተኛ ሀገር እንደሆነች አድርጋ ነው የምታስበው። በወታደራዊ ዛቻ ወይም በማስገደድ መብቷን የምትሰጥ ዘገምተኛ ሀገር ነች ብላ ታስባለች። ይህ የምኞት አስተሳሰብ ነው፣ የኢራን ህዝብ እንዲህ ዓይነቱን ነገር ፈጽሞ አይቀበልም። 'መገዛት' የሚለው ቃል ሙሉ በሙሉ ከመዝገበ-ቃላታችን ውጪ ነው፣ የለም! በአእምሮ ያልተረጋጋ እና በሥነ ምግባር ብልሹ ፕሬዝዳንት ያላቸው አሜሪካውያን ናቸው።"

🇺🇸 እንቅልፋሙ ባይደን ብዙ አጥፍቶ ነበር፣ አሁን ግን አንሰራርተን ተመልሰናል - ፕሬዝዳንት ትራምፕ በፖስቱ
🇺🇸 እንቅልፋሙ ባይደን ብዙ አጥፍቶ ነበር፣ አሁን ግን አንሰራርተን ተመልሰናል - ፕሬዝዳንት ትራምፕ በፖስቱ

🇺🇸 🇮🇷 የአሜሪካ ፕሮፖዛል: ዩናይትድ ስቴትስ ኢራን ዋነኛ የኒውክሊየር ማብላሊያዎቿን እንድታፈራርስ፣ ዩሬንየም ቅመማን ለ20 ዓመታት እንድታግድ፣ የተቀመመውን ዩሬኒየም አሳልፋ እንድትሰጥ እና ሱፐርቫይዝ ለመደረግ ፈቃደኛ እንድትሆን ትፈልጋለች። በWall Street Journal ተዘግቧል። ** ባለፈው ኢራን ውድቅ ካደረገችው ፕሮፖዛል ጋር ይሄ ምንም ልዩነት የለውም።

+2
🇹🇷🇪🇹🇸🇩🚀 የሱዳን መንግሥት አየር ኃይል፣ "የአየር ክልሌን ጥሶ ገባ" ያለውን፣ የኢትዮጵያን ቱርክ ሰራሽ ባይራክታር Ackinci (UCAV) ድሮንን፣ ዛሬ መትቶ መጣሉን አስታወቁ። የአብይ አህመድ መንግሥት ከኤሜሬት መንግሥት ጋር በጋራ በመሆን፣ በሱዳን RSF የተባለን አማፂ ቡድን በመደገፍ፣ የሱዳንን መንግሥት ለማፍረስ እየሰሩ መሆናቸው የሚታወቅ ነው።

⚡️🇺🇸🇰🇼🇮🇷 ኩዌት "Project Freedom" ለተባለው የአሜሪካ የሆርሙዝ ዘመቻ፣ አየር ክልሏን እና መሬቷን መከልከሏ ታውቋል። እንደ ሳዑዲ ሁሉ፣ በዚህ ዘመቻ ኩዌትም ለአሜሪካ ጀርባዋን ሰጥታለች።

🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይሄ ግራፍ "ይጠና" ብሏል። "Wow" ብሎ በአድናቆት ነው የለጠፈው።
🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይሄ ግራፍ "ይጠና" ብሏል። "Wow" ብሎ በአድናቆት ነው የለጠፈው።

🇺🇸🇮🇷⚡️ - ሰበር ዜና፡ ሳዑዲ ዓረቢያ ለዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሰፈሮቿን እና የአየር ክልሏን ለProject Freedom ዘመቻ እንዳትጠቀምበት ከለከለች። በዚህም የተነሳ፣ ዘመቻው በታወጀ በ 24 ሰዓት ውስጥ፣ ትናንት፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኦፕሬሽኑን ለማቆሙ ቁልፍ ምክንያት ነበር። - NBC NEWS እንደዘገበው።

🇸🇴⚡ - ሰበር፡ በሱማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ኃይለኛ ግጭት ተከስቷል። በተኩስ ልውውጡ መድፍ እና ታንኮች ጥቅም ላይ እየዋሉ ናቸው። ከጥቂት ሰዓታት በፊት በርካታ የሱማሊያ ወታደራዊ ክፍሎች ደመወዝ ለወራት አልተሰጠንም በሚል፣ መንገድ ዘግተው ውለዋል። በመከላከያ ሚኒስቴር ላይም እንደሚዘምቱ እያስፈራሩ ናቸው። ሲቪሎችን ጨምሮ በርካታቶች እስካሁን ተገድለዋል ።

⚡️🇺🇸🇮🇷 Politico ያነጋገራቸው የአካባቢው ከፍተኛ አረብ ባለስልጣን፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገውን ጦርነት ለማብቃት እና ከጦርነቱ ለመውጣት እጅግ በፅኑ ይፈልጋል። ነገር ግን፣ ቴህራንም የራሷን ገፅታ ለማዳን ስለምትፈልግ፣ ከግጭቱ ለመውጣት የሚያስፈልገውን መውጫ መንገድ ልትከፍትለት እስካሁን ፈቃደኛ አልሆነችም። ከኢራን ይልቅ አሜሪካ ጦርነቱን በመቀጠል ላይ ተዳክማለች።

✡️🇱🇧 የIDF አዛዥ ኢያል ዛሚር ለወታደሩ 'አረንጓዴ መብራት' ሰጥቷል። በሊባኖስ 'በኃይል አጠቃቀም ላይ ምንም ገደብ የለም' ብሏቸዋል። ወታደሮቹ በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኙ መንደሮችን ሲያፈርሱ ተመልክቶ ለጦሩ እንዲህ ብሏል፡ 💬
የእናንተ ተልዕኮ እያንዳንዱን ስጋት ማስወገድ ነው። ሁሉም የIDF አቅሞች በእጃችሁ ናቸው፣ በኃይል አጠቃቀም ላይ ምንም ገደቦች የሉም። ቀጠናውን በምንፈልገው ለመቅረጽ ታሪካዊ ዕድል አለን።
 የገንዘብ ሚኒስትሩ ቤዛሌል ስሞትሪች በቅርቡ ልጁ ከሂዝቦላህ ጋር ሲዋጋ ቆስሎ ነበር፣ እናም
ልጄ በኋላ መጥቶ የሚያፈርሰው ቦታ እንዲኖረው ከሊባኖስ ትንሽ ቦታ እንድተውለት ጠይቆኛል
ሲል መቀለዱ ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ፣ በጋዛ ውስጥ እንደ ራፋህ እና ቤትሃኑን ተመሳሳይ የመጫወቻ መንገድ በመከተል በሊባኖስ የሚገኙ ሁሉም የድንበር መንደሮች እንደሚወድሙ ቃል ገብቷል።

🇮🇷⚡️ኢራን፣ በሆርሙዝ አዲስ ኦፊሴላዊ አሠራር መዘርጋቷን አስታውቃለች። 🇮🇷⚓ የፋርስ ባሕረ ሰላጤ ወሽመጥ ባለስልጣን ወደ ሆርሙዝ መድረስ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ማለፍ ለሚያስፈልጋቸው
🇮🇷⚡️ኢራን፣ በሆርሙዝ አዲስ ኦፊሴላዊ አሠራር መዘርጋቷን አስታውቃለች። 🇮🇷⚓ የፋርስ ባሕረ ሰላጤ ወሽመጥ ባለስልጣን ወደ ሆርሙዝ መድረስ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ማለፍ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉም የንግድ መርከቦች መመሪያ ሰጥቷል - ☑️ የማለፊያ ክፍያ በሪያል (በኢራን ብር) ወይም በ crypto  መደረግ አለበት ☑️ በቅርብ ጊዜ በተካሄደው ጦርነት በኢራን ላይ ጉዳት ያደረሱ ወይም ጉዳት ለማድረስ አስተዋፅዖ ያደረጉ ሀገራት መርከቦች፣ የመተላለፊያ ፈቃድ ከማግኘታቸው በፊት ካሳ መክፈል አለባቸው። ☑️ ኢራን ላይ ማዕቀብ የጣሉ ወይም የኢራንን ንብረት የከለከሉ ሀገራት ታግደዋል ☑️ ከላይ የተጠቀሱትን መመሪያዎች አለማክበር የመርከብን መያዝ እና ከጭነት ዋጋው 20% ጋር የሚመጣጠን ቅጣትን ያስከትላል ☑️ ሁሉም መርከቦች በኢራን ባሕር ሐይል በተገለፁት የባህር ኮሪደሮች ውስጥ ብቻ ማለፍ አለባቸው። ☑️ 'የጽዮናውያን' አገዛዝ ንብረት የሆኑ መርከቦች፣ ከተያዙት ፍልስጤም ወደቦች (ሃይፋ፣ አሽዶድ፣ ኢላት) የሚመነጩ ወይም ወደ የትኛውም ወደቦቿ የሚያመሩ መርከቦች በባሕር ወሽመጡ ውስጥ እንዳያልፉ ሙሉ በሙሉ ተከልክለዋል ☑️ ትክክለኛው ስም 'የፋርስ ባሕረ ሰላጤ' በሁሉም ሰነዶች ላይ መፃፍ ይኖርበታል።

🇮🇷🇱🇧 ቴህራን ከቤሩት መንግስት ይልቅ ለሊባኖስ የበለጠ አሳቢ መሆኑ የሚገርም ነገር ነው። ዛሬ ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረግ ማንኛውም ድርድር ላይ፣ የሊባኖስ ጉዳይ በድርድሩ የሚካተት ሊሆን
🇮🇷🇱🇧 ቴህራን ከቤሩት መንግስት ይልቅ ለሊባኖስ የበለጠ አሳቢ መሆኑ የሚገርም ነገር ነው። ዛሬ ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረግ ማንኛውም ድርድር ላይ፣ የሊባኖስ ጉዳይ በድርድሩ የሚካተት ሊሆን እንደሚገባው፣ የሊባኖስ ጉዳይ ካልተካተተ፣ በድርድሩ እንደማይሳተፍ ተናግሯል። በሌላ በኩል፣ የሊባኖስ መንግሥት በሀገሩ የደህንነት ጉዳይ ላይ ለዘብተኝነት ብቻ ሳይሆን እያሳየ ያለው፣ እንዲያውም ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር በመቀናጀት፣ 'ተቀናቃኜ' የሚለውን ሂዝቦላን ለማስመታት በሚል፣ መላውን ሀገሩን እያስመታ ይገኛል።

⚡🇮🇱🇱🇧 በኢንተርኔት ላይ እየተሰራጨ ያለው ምስል፡ አንድ እስራኤላዊ ወታደር በዴቤል ሊባኖስ የክርስቲያን መንደር ውስጥ በሃውልቱ አፍ ሲጋራ በማስገባት የድንግል ማርያምን ሃውልት ሲያረክስ የሚ
⚡🇮🇱🇱🇧 በኢንተርኔት ላይ እየተሰራጨ ያለው ምስል፡  አንድ እስራኤላዊ ወታደር በዴቤል ሊባኖስ የክርስቲያን መንደር ውስጥ በሃውልቱ አፍ ሲጋራ በማስገባት የድንግል ማርያምን ሃውልት ሲያረክስ የሚያሳይ ነው። IDF የፎቶውን ስርጭት ተከትሎ ክስተቱን እየመረመረ መሆኑን ገልጿል። ጉዳዩ የመጣው በዚያው መንደር ውስጥ አንድ የእስራኤል ወታደር የኢየሱስ ክርስቶስን ሐውልት በመዶሻ ሲያፈርስ ከተቀረጸና እስራኤል ዓለም አቀፍ ውግዘትን ካስተናገደች ከሳምንታት በኋላ ነው። ለዚያኛው ክስተት የእስራኤል መንግሥት ለመላው ሕዝበ-ክርስቲያን በይፋ ይቅርታ ጠይቆ ወታደሩን በሕግ እንደሚጠይቅ ተናግሮ እንደነበር ይታወሳል።

⚡️🇺🇸🇮🇷 U.S. ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ስምምነት ላይ ትደርስ ዘንድ የአንድ ሳምንት የጊዜ ገደብ መስጠቱ ታወቀ Fox News. ትራምፕ እንዳለው፣ ይሄ፣ ወደ ሆነ ተጨባጭ ነገር እንደሚያመራው እና በዘላቂነት አንድ ነገር እንደሚያመጣ ያምናል።

 🇺🇸 /🇮🇷/ 🇮🇱 ትኩስ፡ የእስራኤል ምንጭ ለCNN፡ አሜሪካ በኢራን ላይ ማዕቀብ ለማንሳት በቁም ነገር እያሰበችበት ነው፣ እና እስራኤል ስለ ጉዳዩ 'አሳስቧታል።'

🇺🇸 / 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለPBS 'የኢራን የበለፀገ ዩራኒየም ወደ አሜሪካ ይመጣል። ኢራን ከእኛ ጋር ከተስማማች ነገሩ ያበቃል ካልተስማማች በአናቷ ላይ ቦምብ ማፈንዳታችንን እንቀጥላለን።'

🚜 🚢 🌾 የኢነርጂ ቀውሱ በፍጥነት ወደ ምግብ ቀውስ እየተቀየረ ነው። - 30% የዓለም የማዳበሪያ ምርት ጠፍቷል። - 20% የአለም LNG (Gas) ምርት ጠፍቷል። - ማዳበሪያ በተፈጥሮ ጋዝ ላይ
🚜 🚢 🌾 የኢነርጂ ቀውሱ በፍጥነት ወደ ምግብ ቀውስ እየተቀየረ ነው። - 30% የዓለም የማዳበሪያ ምርት ጠፍቷል። - 20% የአለም LNG (Gas) ምርት ጠፍቷል። - ማዳበሪያ በተፈጥሮ ጋዝ ላይ የተመሰረተ ነው። - ~ አሁን ላይ 50% የሚሆነው የዓለም የምግብ ምርት፣ በማዳበሪያ ላይ የተመሰረተ ነው። ~ 40% የጋዝ ፍላጎት ውድቀት የሚከሰተው፣ ከማዳበሪያ ኢንዱስትሪዎች መዘጋት ጋር ነው። ስለዚህ፣ የኃይል ገበያውን ሚዛናዊ ለማድረግ፣ በግልፅ እንደሚታየው፣ የምግብ ምርትን እያጠፋን ነው። በየቀኑ ሆርሙዝ ተዘግቶ በቆየ ቁጥር፣ ወደ ክልላዊ ረሃብ አንድ እርምጃ እንቀርባለን! 📎 Haaretz

📢 🇺🇸 🇮🇷 ኢራን "የተስማማንበትን "አሳልፋ ለመስጠት" ፈቃደኛ ካልሆነች፣ የአሜሪካ ድብደባ ከባለፈው ጊዜ በላይ ተጧጡፎ የሚቀጥል ይሆናል፣ ትራምፕ። 📎 Faytuks News
📢 🇺🇸 🇮🇷 ኢራን "የተስማማንበትን "አሳልፋ ለመስጠት" ፈቃደኛ ካልሆነች፣ የአሜሪካ ድብደባ ከባለፈው ጊዜ በላይ ተጧጡፎ የሚቀጥል ይሆናል፣ ትራምፕ። 📎 Faytuks News