fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 308
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-227 روز
-8530 روز
آرشیو پست ها
🇮🇷⚡️ኢራን አላት ተብሎ የሚገመተው የተብላላ ዩራኒየም 4 ኩንታል ነው። ይሄን 4 ኩንታል ነው፣ እነ አሜሪካ አሳልፈሽ ካልሰጠሽ የሚሉት። አራት ኩንታል ሲባል ትንሽ እንዳይመስለን፣ አንዷ ብናኝ ሀገር ታጠፋለች።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ኢራን፣ የተብላላው ዩራኒየሟን፣ ከ60 በመቶ የጥራት ደረጃ፣ ወደ 23 በመቶ በሀገሯ ውስጥ እንድታቀጥነው ትራምፕ የተስማማ መሆኑ ተገለጸ። ከዚህ በፊት አሜሪካ የኢራን ዩራኒየም መቅጠን ካለበት ከኢራን ውጭ ሊሆን ይገባል የሚል አቋም ነበራት AXIOS *-*-*- ዩራኒየም 70 በመቶ የጥራት ደረጃ ላይ ተብላልቶ መድረስ ከቻለ፣ የኒውክሊየር ቦንብ ሊያስገነባ ያስችላል። ኢራን ከ60-63 በመቶ የጥራት ደረጃ ላይ እንዳደረሰችው ይገመታል። ትንሽ ነው የቀራት። አሁን አቅጥኚው ተብላ አብሲት ልትጥል ነው።

🇮🇱🇺🇸⚡️🇮🇷 የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ አመሻሽ ላይ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጋር ከኢራን ጋር ወደ ድርድር ለመግባት ስለተደረሰው የመግባቢያ
🇮🇱🇺🇸⚡️🇮🇷 የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ አመሻሽ ላይ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጋር ከኢራን ጋር ወደ ድርድር ለመግባት ስለተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት ተነጋግረዋል። ምንም እንኳን፣ እስራኤል የመግባቢያ ስምምነቱ አካል ባትሆንም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድርድሩ ማጠቃለያ ላይ የመጨረሻው ስምምነት ሊሆን ይገባዋል ያሉትን ምክረ ሐሳብ ለፕሬዝዳንቱ ለግሰዋል። የበለፀገውን ዩሬኒየም ማስወገድ፣ የማበልፀጊያ መሠረተ ልማቶችን ማፍረስ፣ የሚሳኤል ምርትን መገደብ እና ኢራን በክልሉ ለሚገኙ የአሸባሪ ወኪሎቿ የምታደርገውን ድጋፍ ማቆምን ያካትታል ለፕሬዚዳንት ትራምፕ ላደረጉት ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

🇺🇸 ቀዩ ሰንጠረዥ ዛሬ ጠዋት የነበረውን የአሜሪካ የገበያ ግብይት ያሳያል፣ ገበያው ቀዝቀዝ ያለ ስለነበር (ሌሊቱን በነበረው የኢራን ጦርነትና በተፈጠረው ያለመረጋጋት ሁኔታ)፣ ከገበያው $1.1 ት
+2
🇺🇸 ቀዩ ሰንጠረዥ ዛሬ ጠዋት የነበረውን የአሜሪካ የገበያ ግብይት ያሳያል፣ ገበያው ቀዝቀዝ ያለ ስለነበር (ሌሊቱን በነበረው የኢራን ጦርነትና በተፈጠረው ያለመረጋጋት ሁኔታ)፣ ከገበያው $1.1 ትሪሊዮን ዶላር በንኖ ጠፋ (ኪሳራ)። አረንጓዴው ሰንጠረዥ፣ የከሰዓት በኋላው ግብይት ነው። ትራምፕ ወጥቶ፣ ከኢራን ጋር ያለው ጉዳይ በመስተካከል ላይ ነው አለ፣ ያንን ተከትሎ ገበያው ደስ አለው። በዚያም ከጧት የነበረውን ኪሳራ አካክሶ $1.7 ትሪሊየን ዶላሩን አፈሰው። $600 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ወደ ኪስ፣ አይ አሜሪካ አለ ሰውዬው። ታዲያ አሜሪካ ብትደነቅ ያንስባታል ትላላችሁ?

🇺🇸 ቀዩ ሰንጠረዥ ዛሬ ጠዋት የነበረውን የአሜሪካ የገበያ ግብይት ያሳያል፣ ገበያው ቀዝቀዝ ያለ ስለነበር (ሌሊቱን በነበረው የኢራን ጦርነትና በተፈጠረው ያለመረጋጋት ሁኔታ)፣ ከገበያው $1.1 ት
+1
🇺🇸 ቀዩ ሰንጠረዥ ዛሬ ጠዋት የነበረውን የአሜሪካ የገበያ ግብይት ያሳያል፣ ገበያው ቀዝቀዝ ያለ ስለነበር (ሌሊቱን በነበረው የኢራን ጦርነትና በተፈጠረው ያለመረጋጋት ሁኔታ)፣ ከገበያው $1.1 ትሪሊዮን ዶላር በንኖ ጠፋ (ኪሳራ)። አረንጓዴው ሰንጠረዥ፣ የከሰዓት በኋላው ግብይት ነው። ትራምፕ ወጥቶ፣ ከኢራን ጋር ያለው ጉዳይ በመስተካከል ላይ ነው አለ፣ ያንን ተከትሎ ገበያው ደስ አለው። በዚያም ከጧት የነበረውን ኪሳራ አካክሶ $1.7 ትሪሊየን ዶላሩን አፈሰው። $600 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ወደ ኪስ፣ አይ አሜሪካ አለ ሰውዬው። ታዲያ አሜሪካ ብትደነቅ ያንስባታል ትላላችሁ?

🇺🇸⚡️🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ያለው ጦርነት በይፋ ማብቃቱን እና በአውሮፓ የሰላም ስምምነት እንደሚፈረም ተናግረ። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ድርድሩን በተመለከተ ከኳታር፣ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ እና ከሳዑዲ አረቢያ መሪዎች ጋር ተወያይቷል ተብሏል። ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከውይይቱ ውጭ ሆኗል።

ከኢትዮጵያ የሚያስተላልፉ የቴሌግራም ስፖርት ቻናሎች ያሳዝናሉ፣ ክሊፕ መለጠፍ አይችሉም መሰለኝ፣ ስዕል ብቻ ነው የሚለጥፉት። የቀረውን በጥሁፍ ነው፣ አገባ፣ በቀይ ካርድ ተባረረ፣ የጅ ወረወረ … ክሊፖቹን ልለጥፍላችሁ ያስፈልጋል? ወይስ ቀጠናዎች ላይ ብቻ እናተኩር?

🇺🇸🇮🇷⚡️ — ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ተደረሰ ስለተባለው ስምምነት፡
ኢራን በምንም ተዓምር፣ ይዘት እና ሁኔታ፣ የኒውክሊየር ቦንብ አትገነባም አትገዛምም!
ትራምፕ፣ አሜሪካ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ እንደደረሰች እና የቀረው ቀን ቆርጦ መፈራረም እንደሆነ በሰፊው እያወራ ነው። ኢራን በበኩሏ ፕሬዝዳንቱ ከየት አምጥቶ እንደሚያወራ አናውቅም፣ ልንፈርም ያልነውም፣ ደርሰንበታል የተለም ስምምነት የለም፣ ብላለች። *-*-*-*- ሁለቱም ትናንት በኳታር ልዑካኖች በኩል ሲነጋገሩ ነበር። ሐሳቦችን ተለዋውጠዋል። ከድብደባው በፊት የኳታር አደራዳሪዎች ቴህራን ነበሩ፣ ከለቀቁ በኋላ ነበር ድብደባው የጀመረው። እናም ትራምፕ፣ እየተነጋገርን ነው ሲል፣ በተወሰነ ውነት ይኖረዋል።

🇺🇸⚡️🇮🇷 አረቦች እና እስራኤል፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ እባክዎን ኢራንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያጥፋልን፣ ካለጣፉልን እንዴት ሆነን በጉርብትና ከእነዚህ ጋር እንዘልቃለን? በአንድ ሰፈር መኖር የማይታሰብ ነው፣ ይጥፉ! አውሮፓ፣ ፓኪስታን እና ቱርክ፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ እባክዎን ተረጋጉ። እነዚህን አይስሟቸው፣ እነዚህ ከሰይጣን ናቸው። ኢራንን ይተው፣ ያነጋግሯቸው እና ሰላም አውርዱ። ትናምፕን እነዚህ ሀገሮች ከግራ እና ከቀኙ ሆነው ይሄን ነው የሚሉት። ትራምፕ በጣም ብልህ ሰው ነው፣ አይቸኩልም። ስሜታዊ አይደለም። ግን ይመስላል፣ ለማያውቀው። ትራምፕ፣ በቀለጠው መንደር (የአሜሪካ መርካቶ) ተወልዶ ያደገ ነው። አራዳ ነው። ትራምፕ ከአሜሪካ በሻሻ (ጆርጂያ፣ ቨርጂኒያ…) የመጣ የኦቾሎኒ ገበሬ ልጅ አይደለም። ትራምፕ በኒውዮርክ ሲያድግ፣ ያደገው ከአይሁዶች፣ ከፐርሺያዎች፣ ከአይሪሾች፣ ከፖሊሾች፣ ከጣሊያኖች፣ ከሊባኖሶች፣ ከኩባዎች … ከሁሉም ጋር ነው። ሰዎች የሚያስቡት የማይገባው ሰው አይደለም። አረቦች እና አይሁዶች የዘረጉለትን ወጥመድ በደንብ አስተውሎታል፣ ጠልፈው ከተው ሊያርዱት እንዳሰቡ ነው የተረዳው። እንዳይከፋቸው ብቻ፣ የሆነ ቦንብ ወስዶ ውሃ ላይ ወይም ተራራ ላይ እየጣለ ይመለሳል እንጂ፣ እንደፈለጉት በጦርነቱ ተዘፍቆ ሊበላ አልፈቀደም። ሲናገር፣ ሲሠራ ሞኝ፣ የማያውቅ ይመስላል፣ ሽፋኑ ነው።

🇺🇸⚡️የብዙ ደሃ ሀገሮች ደጋፊዎች፣ በዓለም ዋንጫ ሰበብ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ቪዛ መከልከላቸው ተሰማ፣ ሾልከው የገቡ ካሉም ወደ ስቴዲየሞች እንዳይገቡ ታግደዋል። *-*-*- አስባችሁታል ኢትዮጵ
🇺🇸⚡️የብዙ ደሃ ሀገሮች ደጋፊዎች፣ በዓለም ዋንጫ ሰበብ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ቪዛ መከልከላቸው ተሰማ፣ ሾልከው የገቡ ካሉም ወደ ስቴዲየሞች እንዳይገቡ ታግደዋል። *-*-*- አስባችሁታል ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ብታልፍና አዘጋጇ አሜሪካ ብትሆን፣ 1 ሚሊዮን የባለሥልጣናት ልጆች፣ ዘመዶች፣ ዘመዳ ዘመዶች፣ የሀብታም ልጆች፣ የልጅ ልጆቻቸው፣ ሁሉም ለዓለም ዋንጫ ስፔሻል ቪዛ ያመለክት ነበር … በዚያው ለመቅረት።

🇺🇸🇦🇪🇶🇦🇵🇰🇸🇦🇵🇸🇧🇭🇪🇬🇹🇷🇮🇷 ሰበር ዜና፡ እንደተጠበቀው፣ ትራምፕ፣ ለዛሬ ምሽት አቅዶት የነበረውን የቦንብ ድብደባ፣ እንደሰረዘው ተናገረ። ለሰላም ስል፣ በበርካታ
🇺🇸🇦🇪🇶🇦🇵🇰🇸🇦🇵🇸🇧🇭🇪🇬🇹🇷🇮🇷 ሰበር ዜና፡ እንደተጠበቀው፣ ትራምፕ፣ ለዛሬ ምሽት አቅዶት የነበረውን የቦንብ ድብደባ፣ እንደሰረዘው ተናገረ። ለሰላም ስል፣ በበርካታ ሀገሮች ወትዋችነት እና ከኢራን ጋር በከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል ንግግሮቻችንን ከፍ ለማድረግ በማቀዳችን፣ ጥቃቱን ትቼዋለሁ፣ ብሏል ፕሬዝዳንቱ በመግለጫው።

🇺🇸⚽️ በዓለም ላይ ኳስ የማይወድ ሕዝብ እና ሀገር ጥራ ብባል፡ 1ኛ አሜሪካ 2ኛ አሜሪካ 3ኛ አሜሪካ 4ኛ ካናዳ 5ኛ ጃፓን 6ኛ አውስትራሊያ 7ኛ ቻይና 8ኛ ሕንድ 9ኛ እስራኤል (እስከዚህም ናቸው) 10ኛ ሩሲያ (እስከዚህም ናቸው) አሜሪካንን ማን ይስተካከላታል ኳስ ባለመውደድ? የዓለም ዋንጫ ዛሬ ነው፣ ነገር ግን ስለ እግር ኳስ የሚያወራ አንድ የስፖርት ሚዲያ የለም፣ የሚጽፍ አንድ ጋዜጣና ጋዜጠኛ ማግኘት ይከብዳል፣ ሰው፣ አየሩ፣ ድባቡ ሁሉ፣ በራሳቸው ስፖርቶች ዙርያና ዙሪያ ብቻ ነው የሚያጠነጥኑ። ምንም ነገር ያለ አይመስልም። ሀገሩ የተቃጠለው በቅርጫት ኳስ እና በእጅ ኳስ (American Football) ነው፣ 24/7. እነሱ ካልሆኑ፣ Baseball ነው፣ ያ ካልሆነ Hockey ነው፣ ያ ካልሆነ UFC ነው፣ Boxing ነው … … የዓለም ዋንጫን ስቴዲየም ገብተው የሚታደሙ አሜሪካዊያን ካሉ፣ የሚገቡት እንደ ቱሪስት ነው። እንደ ቱሪዝም አጋጣሚ ነው የሚያዩት። ስቴዲየም ሞልቶ ካያችሁ፣ 99.9% ፐርሰንት ታዳሚው ስደተኛው ነው፣ ላቲኖች፣ አፍሪካዊያን እና ከአውሮፓ የሚመጡ ታዳሚዎች ናቸው። ስደተኛው ከሀገሩ ስለሚያውቀው ይገባል። ስደተኛውም ግን፣ በአሜሪካ 15-20 ዓመት ከተቀመጠ በኋላ፣ እነሱኑ ይመስላል። እሱም እንደ አሜሪካኖች የእነሱን ስፖርቶች ተመልካች ሆኖ ያርፈዋል፣ የአሜሪካን ውሃ የጠጣ፣ ከእግር ኳስ ይርቃል። አሜሪካ በጣም ነው የምታስቀኝ፣ በአንድ በኩል በጣም አደንቃታለሁ። የራሷን ብቻ ነው የምታጎላው፣ ለቤቷ ጉዳይ ነው ከማንም በፊት ክብር የምትሰጠው።

🇺🇸⚽️ በዓለም ላይ ኳስ የማይወድ ሕዝብ እና ሀገር ጥራ ብባል፡ 1ኛ አሜሪካ 2ኛ አሜሪካ 3ኛ አሜሪካ 4ኛ ካናዳ 5ኛ ጃፓን 6ኛ አውስትራሊያ 7ኛ ቻይና 8ኛ ሕንድ 9ኛ እስራኤል (እስከዚህም ናቸው) 10ኛ ሩሲያ (እስከዚህም ናቸው) አሜሪካንን ማን ይስተካከላታል ኳስ ባለመውደድ? የዓለም ዋንጫ ዛሬ ነው፣ ነገር ግን ስለ እግር ኳስ የሚያወራ አንድ የስፖርት ሚዲያ የለም፣ የሚጽፍ አንድ ጋዜጣና ጋዜጠኛ ማግኘት ይከብዳል፣ ሰው፣ አየሩ፣ ድባቡ ሁሉ፣ በራሳቸው ስፖርቶች ዙርያና ዙሪያ ብቻ ነው የሚያጠነጥኑ። ምንም ነገር ያለ አይመስልም። ሀገሩ የተቃጠለው በቅርጫት ኳስ እና በእጅ ኳስ (American Football) ነው፣ 24/7. እነሱ ካልሆኑ፣ Baseball ነው፣ ያ ካልሆነ Hockey ነው፣ ያ ካልሆነ UFC ነው፣ Boxing ነው … … የዓለም ዋንጫን ስቴዲየም ገብተው የሚታደሙ አሜሪካዊያን ካሉ፣ የሚገቡት እንደ ቱሪስት ነው። እንደ ቱሪዝም አጋጣሚ ነው የሚያዩት። ስቴዲየም ሞልቶ ካያችሁ፣ 99.9% ፐርሰንት ታዳሚው ስደተኛው ነው፣ ላቲኖች፣ አፍሪካዊያን እና ከአውሮፓ የሚመጡ ታዳሚዎች ናቸው። ስደተኛው ከሀገሩ ስለሚያውቀው ይገባል። ስደተኛውም ግን፣ በአሜሪካ 15-20 ዓመት ከተቀመጠ በኋላ፣ እነሱኑ ይመስላል። እሱም እንደ አሜሪካኖች የእነሱን ስፖርቶች ተመልካች ሆኖ ያርፈዋል፣ የአሜሪካን ውሃ የጠጣ፣ ከእግር ኳስ ይርቃል። አሜሪካ በጣም ነው የምታስቀኝ፣ በአንድ በኩል በጣም አደንቃታለሁ። የራሷን ብቻ ነው የምታጎላው፣ ለቤቷ ጉዳይ ነው ከማንም በፊት ክብር የምትሰጠው ።

🇮🇷🇺🇸⚡️ - ኢራን ኻርጅ ደሴትን ለመቆጣጠር ላለመ የአሜሪካ ዘመቻ ለወራት ስትዘጋጅ ቆይታለች CNN በዘገባው። ኢራን ቀደም ሲል የአሜሪካን ወታደራዊ ጥቃቶችን ተከትሎ፣ የደሴቲቱን መከላከያ አ
🇮🇷🇺🇸⚡️ - ኢራን ኻርጅ ደሴትን ለመቆጣጠር ላለመ የአሜሪካ ዘመቻ ለወራት ስትዘጋጅ ቆይታለች CNN በዘገባው።
ኢራን ቀደም ሲል የአሜሪካን ወታደራዊ ጥቃቶችን ተከትሎ፣ የደሴቲቱን መከላከያ አጠናክራለች፣ ተጨማሪ ሠራዊት፣ የአየር መከላከያዎችን እና MANPADS (ከትከሻ የሚተኮሱ ከመሬት ወደ አየር ሚሳኤሎች) ማሰማራትን ጨምሮ፣ ብዙ ሥራ ሠርታለች። ኢራን የአሜሪካን እግረኛ በመጠባበቅ፣ በባሕር ዳርቻው እና በዙሪያው ፀረ-ሰው እና ፀረ-ትጥቅ ፈንጂዎችን አስቀምጣለች። የአሜሪካ ባለስልጣናት እና ወታደራዊ ባለሙያዎች፣ ደሴቲቱን ለመያዝ ያለመ ማንኛውም ዘመቻ የአሜሪካን ከባድ ጉዳት ጨምሮ ከፍተኛ አደጋዎችን እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል።


🇺🇸⚡️🇮🇷 ሰበር ዜና፡ ትራምፕ አሁን፡ 🔸ኢራን ነጭ ባንዲራ በፈለገችው ሰዓት ማውለለብ ትችላለች። እጅ ሰጥተናል እና አሜሪካ ኃያል ኃይል ናት ብላ ታውጅ። 🔸ድልድዮች ቀጣይ ዒላማዎቻችን ናቸው፣ ነገር ግን እኔ ይሄን ማድረግ አልፈልግም፣ ሕዝብ ይጎዳል። 🔸ስማ! እኔ ኻሪጅ ደሴቶችን መውሰድ እፈልጋለሁ፣ ግን ደግሞ እርግጠኛ አይደለሁም።

🇮🇷⚡️🇺🇸 የኢራን ፓርላማ ብሔራዊ ደህንነት ኮሚቴ ቃል አቀባይ፣ ኢብራሂም ረዛ፡ ታላቋ ኢራን አታወላውልም፣ ሸብረክምም አትልም። ማነው በዚህ ጦርነት እጅ መስጠት ያለበት ስለሚለው፣ መልሱ የሚያ
🇮🇷⚡️🇺🇸 የኢራን ፓርላማ ብሔራዊ ደህንነት ኮሚቴ ቃል አቀባይ፣ ኢብራሂም ረዛ፡ ታላቋ ኢራን አታወላውልም፣ ሸብረክምም አትልም። ማነው በዚህ ጦርነት እጅ መስጠት ያለበት ስለሚለው፣ መልሱ የሚያጠራጥር አይደለም። ትራምፕ ምርጫ የለውም፣ እጅ ይስጥ። እጅ መስጠት ነው ወይም እጅ መስጠት ነው ምርጫ የለም።

🇺🇸🇮🇷 "እነሱ እያለቀላቸው ነው፣ እየሞቱ ነው። ስምምነት ለመፈራረም በእንፉቅቅ እየለመኑኝ ነው። ስምምነት ማድረግ ይፈልጋሉ። የ$250 ሚሊዮን ቦንብ ነው አናታቸው ላይ ያዘነብነው። እነርሱ እጅ ሰጥተዋል፣ አንጃ ግራንጃ የለውም። የባነኑ ግን አይመስለኝም። እየሞቱ እንደሆነ ገና የባነኑ አይመስለኝም - ትራምፕ ለFOX NEWS

🇺🇸⚡️ሰበር ዜና፡ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አሜሪካ ዛሬ ምሽት ኢራንን በቦንብ እንደምትደበድብ እና የኻሪጅ ነዳጅ መጫኛ ደሴቶችን በቅርቡ በቁጥጥር ሥር እንደምታውል አስታወቀ። ዶናልድ
🇺🇸⚡️ሰበር ዜና፡ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አሜሪካ ዛሬ ምሽት ኢራንን በቦንብ እንደምትደበድብ እና የኻሪጅ ነዳጅ መጫኛ ደሴቶችን በቅርቡ በቁጥጥር ሥር እንደምታውል አስታወቀ። ዶናልድ ትራምፕ በፖስቱ፣ እንደ ቬኔዝዌላ ኢራንን የምንወስድበት ጊዜው ደርሷል፣ ሁሉም ይዘጋጅ፣ ሲል ተናግሯል።

🇮🇷 ባሁኑ ሰዓት፣ የኢራን ትልቁ 'ኒውክሊየር' መሳሪያዋ፣ ጥርጣሬን እና በቀጠናው ቋሚ ያልሆነ የተዘበራረቀ ዕጣ ፋንታን መፍጠር ነው። እሷ የምትዘውረው መስመር - ፋርስ ባሕረ ሰላጤ፣ አረቢያ ባሕረ ሰላጤ ሆርሙዝ፣ እና ከባቢው - በቋሚነት የማይረጋጋ እና 'ይረበሽ ይሆን፣ አይረበሽ ይሆን' ጥርጣሬ በዘላቂነት የማይወገድ ከሆነ፣ የመጫወቻው ካርድ ሁሌም በኢራን እጅ ላይ እንደሆነ ይቆያል። ኢራን ይሄንን በደንብ ተገንዝባለች! በመሆኑም፣ አሜሪካ እና በአካባቢው ያሉ ሀገሮች፣ ለራሳቸውም፣ ለዓለምም፣ ደህንነትና መረጋጋት ሲሉ፣ ኢራንን እንደ እንቁላል ተንባክበው የምትፈልገውን በመስጠት 'በቃ ተመለሺ' ካላሏት፣ ቀጠናው ወደፊት መኖር ወደ የማይቻልበት ደረጃ ይሸጋገራል።

🇮🇷⚡️የኢራን ሸሂድ ድሮን፣ በሱብሂ አዛን፣ እንደ አሞራ በኩዌት ሰማይ እየበረረ፣ ምግቡን እያደነ ነው። ሩዝ ይሆን የሚበላው?