የቀጠናው ተመልካች
رفتن به کانال در Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 321
مشترکین
+824 ساعت
-47 روز
-7130 روز
آرشیو پست ها
4 321
🇮🇷 የኢራን ፕሬዝዳንት መስዑድ ፐዝሽኪያን ለኢራን መገናኛ ብዙሃን ስለ ኻሚኒ ሞት ዛሬ የተናገረው፡
"ትልቅ ኪሳራ ነው፣ በምንም ነገር አናካክሰውም። እሳቸውን በማጣት ከደረሰብን ህመም እና ስቃይ መውጣት አንፈልግም።"
4 321
🇮🇷❌🇺🇸 - ትኩስ፡ የኢራን የጸጥታ ምንጭ ለፕረስ ቲቪ፡ የኢራን ጦር ኃይሎች ትዕግስት ወሰን እንዳለው እና ዋሽንግተን እገዳዋን ከቀጠለች አሳማሚ ምላሽ አስፈላጊ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል።
🔹የኢራን ጦር ኃይሎች ያሳዩት ትዕግስት ለዲፕሎማሲ እድል ለመስጠት እና ዋሽንግተን የኢራንን ሁኔታ እንድትረዳ ጊዜ ለመስጠት ታስቦ ነበር።
🔹 የአሜሪካ ግትርነት በዚህ ከቀጠለ እና የኢራን ፍላጎት ውድቅ ከተደረገ፣ ጠላት በቅርቡ ለእገዳው የተለየ ምላሽ መጠበቅ አለበት።
4 321
🇦🇪 UAE ከተጨማሪ ዓለም አቀፍ ተቋማት እወጣለሁ በማለት እያስፈራራች ነው። ትናንት ከዓለም የነዳጅ አምራቾች ማህበር (OPEC) አባልነት ራሷን ማስወጣቷ ይታወቃል።
UAE በተምሳሌነት እየተከተለች ያለችው ሀገር እስራኤል ይመስላል። እንዲህ ዓይነቱን እንቅስቃሴ፣ እስራኤል ከዓለም አቀፍ ተቋማት ራሷን በማግለል፣ ያለ ተያዥ እና ሀይ ባይ፣ ከተጠያቂነት ርቃ የፈለገችው ለማድረግ ረድቷታል።
4 321
🇪🇬 🇦🇪 የኤሜሬት ተፅእኖ ፈጣሪ፣ መጅድ አል አምሪ፣ እንዲህ ሲል በ X አካውንቱ ላይ ጽፏል፡
"ባሁኑ ጊዜ በዚህ ግጭት 'ገለልተኛ ነኝ' ብሎ የሚል ካለ፣ ከጠላትህ ጎን ነው። ወራዳ ስለሆነ ግልፁን አይናገርም።"
ታዋቂው ግብፃዊ የጥበብ ሰው አምር ዋቂድ፣ ለመጅድ እንዲህ ሲል መልሶለታል፡ "አትጨነቅ፣ እኛ ገለልተኛ አይደለንም - ሁላችንም ከኢራን ጎን ነን!"
4 321
🇺🇦 🇷🇺 ዩክሬን ዛሬም በጥቁር ባሕር ዳርቻ የሚገኘውን ግዙፉን የሩሲያ ነዳጅ ማጣሪያ እና ዴፖ፣ በሦስት ዙር የድሮን ጥቃት እንዳወደመችው እና ክሬምሊን በ Krasnodar ክፍለ ሀገር ዋና ከተማ የአደጋ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ነዋሪው ከአካባቢው እንዲወጣ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ተሰምቷል።
4 321
+1
🇺🇬 ሰበር፡ ዩጋንዳ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ 231 የውጭ ሀገር ዜጎችን በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል በቁጥጥር ሥር ማዋሏን አስታወቀች።
ኡጋንዳ፣ "ወራቶች በወሰደ" ባለችው በዚህ ዘመቻ፣ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ፣ የናይጄሪያ፣ የሕንድ፣ የፓኪስታን፣ የባንግላዴሽ፣ የቻይና እና የበርማ ዜጎችን በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ክስ በቁጥጥር ሥር አውላለች።
***
ኢትዮጵያዊያን የሀገራቸውን ሕዝብ፣ በተለይ ሕፃናት ሴቶችን ለዓረብ ግርድና ለመከራ እና ስቃይ በባርነት ከመሸጥ አልፎ፣ አሁን የጎረቤት ሀገር ሰዎችንም እየሸጡ ናቸው።
4 321
🇱🇧⚡️🇮🇱 በቤሩት የምትኖር የ13 ዓመቷ ሕፃን ትምህርት ቤቷ የሂዝቦላህ የጦር መሳሪያ እንዳከማቸ በመግለጽ ለእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ በኢንስትግራም ላይ የአየር ድብደባ እንዲደረግ መጠየቋ ድንጋጤ ፈጥሯል። መልእክቱ ከክፍል ለመቅረት እንደ ቀልድ ታስቦ የተፈፀመ ነበር ተብሏል። ታዳጊዋ እና ወላጆቿ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበር ሲሆን ነገር ግን ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ እንደተለቀቁ ነው የተነገረው። ትምህርት ቤቱ እና ወላጆች ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድ ላይ ናቸው ተብሏል።
4 321
🇺🇦 🇷🇺 ፑቲን፣ ዩክሬን በሲቪል መሠረተ ልማት ላይ እየወሰደችው ያለው የድሮን ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ተናገረ።
'የቅርብ ጊዜ ምሳሌዎች፣ ለምሳሌ ትናንት ምሽት በ Tupse ሩሲያ ውስጥ በኋይል ተቋማት ላይ የደረሰው ጥቃት አንዱ ማሳያ ነው' ሲል ተናግሯል።
'ከባድ አካባቢያዊ መዘዞችን ሊያስከትል ይችላል' ም ብሏል።
ትናንት ምሽት በሩሲያ Tupse በሚገኘው ግዙፍ ነዳጅ ማጣሪያ ላይ በደረሰው ጥቃት፣ በአካባቢው ያለው ባሕር በሚሊዮኖች ሊትር በሚቆጠር ነዳጅ ተበክሏል ተብሏል። እሳቱ እስካሁን አልጠፋም።
4 321
🇺🇸🇩🇪🇮🇷⚡ትራምፕ የጀርመኑ ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝ፣ "የሚናገረውን የማያውቅ… የሚመራውም ሀገር በኢኮኖሚውም በሌላው የሾቀ ነው" ብሎታል።
4 321
🇱🇧 | የእስራኤል ጦር የቢንት ጁበይል ስታዲየምን አፍርሰዋል። እ.ኤ.አ. በ 2000 የእስራኤል ጦር ከደቡብ ሊባኖስ ካፈገፈገ በኋላ የሂዝቦላው መሪ፣ ሰይድ ሀሰን ናስራላህ፣ ታዋቂ ንግግር ያደረገበት ቦታ በመሆኑ ይህ ቦታ ለሂዝቦላህ ትልቅ ደረጃ የነበረው እና ተምሳሌታዊ ሥፍራ ነበር።
4 321
🇵🇰🇮🇷🇺🇸⚡️ - በፓኪስታን ያሉ አደራዳሪዎች ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ያቀረበችውን ፕሮፖዛ እንደማይቀበሉ ካሳወቁ በኋላ በሚቀጥሉት ቀናት ኢራን ጦርነቱን ለማስቆም የተሻሻለ ፕሮፖዛል ታቀርባለች ብለው ይጠብቃሉ፣ ሲል CNN ዘግቧል።
➡️ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ሩሲያን ከጎበኙ በኋላ ዛሬ ወደ ቴህራን የተመለሱ ሲሆን ከከፍተኛ አመራሮች ጋር መመካከር አለባቸው ተብሎ ይጠበቃል። ያሉበት ቦታ በሚስጥር ከተያዘው ከጠቅላዩ መሪ ሙጅታባ ካሜኔይ ጋር ለመግባባት አስቸጋሪ በመሆኑ ሂደቱ አዝጋሚ ይሆናል ተብሏል።
➡️ ንግግሮች ቀጣይ ሆነው ይቆያሉ፣ ይህ በአብዛኛው የሚወሰነው ግን ኢራን አሜሪካን ሊያስማማ የሚችል የተሻሻለ ፕሮፖዛል ስታቀርብ ብቻ ነው።
4 321
- 🇺🇸 / 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ "የኢራን አመራር በከፍተኛ ሁኔታ እየተፈረካከሱ እንደሆነና ገበናቸውን እስኪያስተካክሉ ድረስ፣ የሆርሙዝ ወሽመጥን እንድንከፍትላቸውም እየተማፀኑን ይገኛሉ። እንደሚያስተካክሉ አምናለሁ።"
4 321
🇸🇦 ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ፣ በኢራን ጥቃት በደረሰበት ውድመት ምክኒያት፣ የሳዑዲ ዓረቢያው ARAMCO ጋዝ ወደ ውጭ መላክ እንደሚያቆም አስታወቀ።
የ ARAMCO ባለቤት የሆሀው የሳዑዲ መንግሥት በመግለጫው እንዲህ ብሏል፡
የጋዝ ማውጫ ፋሲሊቴዎቼ በጥቃቱ ምክኒያት ከሥራ ውጭ በመሆናቸው፣ የጋዝ ምርትን እና ኤክስፖርት ለማቆም ተገድጃለሁ።
4 321
- 🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኢሚሬት ለምን OPEC+ን ለቃ ወጣች? ነገሩን ቀለል ለማድረግ -
> አሁን ላይ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ነው፣ ይሄንን ትራምፕ አይፈልግም። መፍትሄ ያስፈልገዋል።
> የተባበሩት አረብ ኢሚሬት ከኦፔክ በመውጣት ብዙ ዘይት ማምረት እና ወደ ውጭ መላክ ትችላለች ምክንያቱም ከአሁን በኋላ በኮታ ስለማትታሰር
> ይህ ደግሞ በገበያው የነዳጅ ዝውውር እና አቅርቦትን ይጨምራል
> ተጨማሪ አቅርቦት ቢያንስ ለጊዜው በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋን ይቀንሳል
> የነዳጅ ዋጋ መቀነስ፣ እንደ ሳዑዲ ዓረቢያ ላሉ ሀገራት፣ ምርቱን በማሳደግ ማካካስ ለማይችሉ ሀገራት፣ መጥፎ ስለሆነ መቆጣታቸው የማይቀር ነው።
ባጭሩ ይህ ትራምፕ የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ ምክንያት የተፈጠረውን የነዳጅ ዋጋ ቀውስ፣ ለመቆጣጠር ያቀዱት ዕቅድ ነው።
4 321
🇱🇧 ❌ 🇮🇱 ❗️ - የዲፕሎማቲክ ምንጭ ለሊባኖስ ጋዜጣ አል-አክባር -
የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከግብፅ ግልጽ መልእክት ተቀብለዋል። ከሊባኖስ ፍላጎት ጋር የተጣጣመ ውጤት ሳይገኝ ከእስራኤል ጋር ወደ ድርድር መጣደፍ፣ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል ።
4 321
ሰበር፡ 🇦🇪 UAE፣ የነዳጅ አምራች አገራት ማህበርን (OPEC) በመጪው ወር መግቢያ ለቅቃ እንደምትወጣ አስታወቀች።
UAE ከሳዑዲ እና ኢራቅ ቀጥላ ሦስተኛዋ ግዙፍ ነዳጅ አምራች ስትሆን፣ በሌላዋ የማህበሩ አባል፣ ኢራን፣ ለወራት መቀጥቀጧን ለመውጣቷ እንደ ምክኒያት አቅርባለች። ውሳኔዋ በነዳጅ ገበያው ላይ ድንጋጤን ፈጥሯል።
4 321
+1
🇸🇦 🇦🇪 🇰🇼 🇧🇭 🇶🇦⚡️🇮🇷 ሳዑዲ አረቢያ በኢራን ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የመጀመሪያውን የባሕረ- ሰላጤ አገራትን መሪዎች ስብሰባ፣ ዛሬ ልታስተናግድ ነው -- ሮይተርስ።
የማክሰኞው ስብሰባ፣ የባሕረ- ሰላጤው ግዛቶች በሺዎች በሚቆጠሩ የኢራን ሚሳኤሎች እና ድሮኖች በኋይል እና በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ለደረሰው ጉዳት ምላሽ እንዲሰጥ ያለመ እና በዘላቂነት ቀጠናው ምን ለማድረግ አስቧል በሚለው ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው ተብሏል።
