fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 303
مشترکین
-124 ساعت
-217 روز
-8630 روز
آرشیو پست ها
🇺🇦 ዘለንስኪ፡ በአውሮፓ ዩክሬንን የሚስተካከል ጦር ሰራዊት ያለው ሀገር አለ ብዬ አላምንም። ዩክሬን አውሮፓን ከምትፈልገው በላይ፣ አውሮፓ ዩክሬን ያስፈልገዋል። አውሮፓን ከሩሲያ ቅዥብና የመጠበቅ አቅም ያላት ዩክሬን ብቻ ናት። በተቻለ ፍጥነት ኔቶን እንድንቀላቀል ይሁን!

🇮🇱❌🇮🇷 - የIDF ዋና አዛዥ ኢያል ዛሚር - IDF ወደ ኢራን እና ወደ ጦርነት ለመመለስ ንቃተ ህሊናውን እና አፋጣኝ ዝግጁነቱን ጠብቆ ቀጥሏል። ሁሉም የመከላከያ እና የጥቃት ሥርዓቶቻችን ን
🇮🇱❌🇮🇷 - የIDF ዋና አዛዥ ኢያል ዛሚር -
IDF ወደ ኢራን እና ወደ ጦርነት ለመመለስ ንቃተ ህሊናውን እና አፋጣኝ ዝግጁነቱን ጠብቆ ቀጥሏል።
ሁሉም የመከላከያ እና የጥቃት ሥርዓቶቻችን ንቁ እና ዝግጁ ነበሩ። ለዚያም ነበር፣ በእኛ ላይ የተተኮሱትን ጥቃቶች አክሽፈን ኢራንን በፍጥነት እና በኃይል ያጠቃነው። በኢራን ያደረግነው ጥቃት፣ ለበለጠ ጉልህ እና ከባድ ድብደባ ዝግጅት ነበር። ተመልሰን በኢራን ላይ ሌላ ከባድ እና ጥልቅ ጉዳት ለማድረስ ዝግጁ ነን።

🇺🇦 'የቀድሞ የቸልሲ ክለብ ባለቤት፣ የሮማን አብራሞቪች ብር፣ ለዩክሬን ሊሰጥ ይገባል' ዘለንስኪ ዘለንስኪ የብሪታንያ መንግስት በቅርቡ በባንክ የተያዘውን የአብራሞቪችን ገንዘብ ወስዶ ወደ ዩክሬን እንዲያስተላልፍ ሀሳብ አቅርቧል፣ ሲል ዘ ጋርዲያን ዘግቧል። ዘለንስኪ፣ የሩሲያው ባለ ሀብት፣ አብራሞቪች፣ ከቼልሲ እግር ኳስ ክለብ ሽያጭ የተቀበለውን $2.4 ቢሊዮን ፓውንድ ለዩክሬን እንዲሰጥ እና የአየር መከላከያ መቃወሚያዎች ለመግዛት እንዲውል ጠይቋል። ባሳለፍነው ሳምንት፣ ፑቲን፣ አብራሞቪችን ወደ ዩክሬን ከዘለንስኪን ጋር ጦርነቱን በማብቃት ዙሪያ እንዲያነጋግረው ልኮት እንደነበር እና እሱም ከዘለንስኪ ጋር ተገናኝቶ እንደተወያየ ይታወቃል። 

🇦🇱 የአልባኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢዲ ራማ፣ ለትራምፕ ቤተሰብ የተሸጠውን ጥብቅ ደሴት በተመለከተ የተነሳበትን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ የተሸጠው መሬት "ለሀብታሞች ብቻ ነው፣ ባለቤቶቹ እነሱ ናቸው፣ የአልባኒያ ሕዝብ አይደለም" ሲል በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ተናግሯል። በአልባኒያ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞው ያየለ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ በአስቸኳይ ሥልጣኑን እንዲለቅ በመጠየቅ ላይ ነው።

🇬🇧🇺🇸 - የዩናይትድ ኪንግደም የሀገር ውስጥ መሥሪያ ቤት፣ ጎግል እና አፕል ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ተጠቃሚዎችን ተደራሽነት፣ እንዲገድብ ጠይቋል። የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ወላጆች የልጆቻቸውን የመስመር ላይ ተደራሽነት እንዲገድቡ የሚያስችላቸውን ተግባራት (Age Restrictions) አስቀድመው እንዳቀረቡ መልሰዋል። ዩናይትድ ኪንግደም ይሄ በቂ አይደለም፣ ለአቅመ-አዳም ያልደረሱ ልጆች ከማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ በካምፓኒዎቹ እኝዲታገዱ እፈልጋለሁ፣ ካልሆነ በኩባንያዎቹ ላይ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች። *-*-*- በነገራችን ላይ፣ በአሜሪካም፣ በተለይ በካሊፎርኒያ ግዛት የሚገኙ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች (1280) እንደ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ፣ ሶሻል ሚዲያዎችን ከትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ስለማገድ እና ከ21 ዓመት በታች ያሉ በምንም ሁኔታ ለሶሻል ሚዲያ access እንደይኖራቸው በመገደብ ላይ ውሳኔ ሊያሳልፉ ጫፍ ደርሰዋል።

ኢራን ሐማስን ገሸሽ ያደረገችው የሚመስለኝ፣ ለእስራኤል እጅ በመስጠቱ ነው። በይፋ፣ መሸነፉን አምኖ ነጭ ባንዲራ በማውለብለቡ ነው። ኢራን ይሄን አልወደደችውም። እንደምናየው ኢራን ጋር 'እጅ መስጠት' የሚባል ነገር የለም። 'ድል ወይም ሞት' የሚለውን አባባል ትርጉም የወሰዱት፣ ከነ ጥሬ ትርጉሙ ነው። ለዚያም ነው የ12 ቀኑንም፣ ይኼኛውንም ጦርነት፣ እንደ በርካታ ምዕራባዊያን ተንታኞች ድምዳሜ፣ ያሸነፉት። እጅ ባለመስጠት። አስታውሱ፡ ለኢራን ማሸነፍ ማለት አለመንበርከክ ማለት ነው። ካልተንበረከኩ አሸንፈዋል። ለእስራኤል እና ለአሜሪካ ደግሞ መሸነፍ ማለት ኢራንን አለማንበርከክ መቻል ነው። ካላንበረከኳት፣ ተሸንፈዋል።

🇮🇷⚡️በአልሃዳዝ ቻናል የቀረበ ዘገባ ብዙዎችን አስገርሟል፡- የጋዛ ነዋሪዎች ኢራንን ክፉኛ እየወቀሱ ናቸው ያሉት። ኢራን በቤይሩት በዳሂህ ላይ ለደረሰው የቦምብ ጥቃት በሰጠችው ምላሽ እና እስራኤል በጋዛ ላይ ላደረሰችው የቦምብ ጥቃት ምላሽ ባለመስጠቷ ጋዛውያን ኢራን ላይ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ኢራን በድርድሯ ላይ ሊባኖስን አካትታ ሳለ፣ እኛን እንዴት አላካተተችንም? ሊባኖስን ቀይ መስመሬ ናት ስትል፣ እኛንስ ለምን ተወች? የሚል ነው የጋዛውያን ቅሬታ። ለኢራን በ12ቱ ቀን ጦርነት ወቅት ብዙ ድጋፍ አድርገንላታል የሚሉት ጋዛውያን፣ ኢራን በዚህ መልኩ የረሳቻቸው ስለመሰላቸው ተበሳጭተዋል። ለምንድነው ፍልስጤማውያን በነዚህ ድርድሮች ውስጥ ያልተካተቱት? ሲሉም ይጠይቃሉ። ኢራን ለዓመታት ሐማስን እና ፍልስጤማዊያንን ከማንኛውም አረብ ሀገር በላይ ስትደግፍ እና ድምጽ ስትሆንላቸው መቆየቷ ሊታወስ ይገባል።

🇮🇱🇺🇸🇱🇧⚡️— ሮይተርስ፡ ኔታንያሁ ለትራምፕ፡ 'ከኢራን ጋር ምንም ፍጠር ምንም፣ ሂዝቦላህ ዒላማችን ሆኖ ይቆያል።

🇮🇷🇺🇸 የእስራኤል አቋም ምንም ይሁን ምን፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ጋር ስምምነት መፈለጓን ትቀጥላለች -- ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ።

🇺🇦🇷🇺 ፑቲን እየቻለ፣ አልጨርስም ብሎ ሲርመጠመጥ፣ ዩክሬኖች በድሮን በጦር ሜዳ ግንባሮችም፣ በመሃል ሀገርም እየጨረሱት ነው። ይህ በአንድ መስመር ላይ፣ በአንድ ሳምንት የሆነ ነው። በግንባሮች በቀን፣ ከ2800 በላይ ወታደሮች ከሁለቱም ወገን ይሞታሉ።

🇺🇦🇷🇺 ፑቲን እየቻለ፣ አልጨርስም ብሎ ሲርመጠመጥ፣ ዩክሬኖች በድሮን በጦር ሜዳ ግንባሮችም፣ በመሃል ሀገርም እየጨረሱት ነው።

⚡️🇺🇸🇮🇷 NYT: አንድ የአሜሪካ ጦር AH-64 Apache ሄሊኮፕተር፣ በሆርሙዝ ባሕር ዳርቻ መውደቁ ታውቋል። ሁለቱም የአውሮፕላኑ አባላት በደህና ተርፈዋል። የአደጋው መንስኤ በምርመራ ላይ ነው።

🇺🇸 ፕሬዝደንት ትራምፕ በዛሬው ምሽት በ NBA ፍጻሜዎች ጨዋታ ላይ በኒውዮርክ ተገኝቶ፣ በአውጋዥ ድምጾችን ባሕር ሲዋኝ አምሽቷል። የሀገሩ የኒው ዮርክ ነዋሪዎች፣ እሱን መጥላት ይወዳሉ፣ ቢሆንም እሱ ኬረዳሽ ብሎታል። የዛሬው ምሽት፣ የኒክስ እና ስፐርስ ጨዋታ መግቢያ ትኬት $42,000 ዶላር ነበር።

🇦🇱 የአልባኒያ ፀረ ሙስና ተቃውሞ 9ኛ ቀኑን ይዟል። ሰልፈኞች፣ ቀይ የአልባኒያ ባንዲራዎችን እና ባነሮችን በማውለብለብ መሃል ቲራና ሞልተውት ነበር። ተቃዋሚዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ኢዲ ራማ ስልጣኑን እንዲለቅ እየጠየቁ ነው። *-*-*-*- ሰልፍ ከዚያ ሰይፍ

🇺🇸🇸🇴 ሱማሊያዊው የፊፋ ዳኛ ከአሜሪካ ተጠረዘ፡ The New York Times ዑመር አብዱልቃድር፣ ስመ-ጥር እና ብዙ ሽልማቶችን ያሸነፈ የፊፋ ዳኛ ሲሆን፣ መጪውን የዓለም ዋንጫ ለመዳኘት ወደ
🇺🇸🇸🇴 ሱማሊያዊው የፊፋ ዳኛ ከአሜሪካ ተጠረዘThe New York Times ዑመር አብዱልቃድር፣ ስመ-ጥር እና ብዙ ሽልማቶችን ያሸነፈ የፊፋ ዳኛ ሲሆን፣ መጪውን የዓለም ዋንጫ ለመዳኘት ወደ አሜሪካ በማያሚ አየር መንገድ ሲገባ ነበር፣ ቪዛው ተሰርዞ ወደ ሱማሊያ መጠረዙ የተነገረው። የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ FIFA፣ በአሜሪካ ሕግ ዙሪያ ጣልቃ መግባት እንደማይችል ገልፆ፣ ተተኪ ዳኛ እንዳዘጋጀ ገልጿል። እንደ አንዳንድ ምንጮች ዘገባ፣ በአሁኑ ሰዓት ዑመር እያለቀሰ ይገኛል።

🇮🇷🇺🇸 — ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለ ኢራን:
በኢራን ውስጥ መደምሰስ ያለበት ሁሉ ደምስሰናል!

🇺🇸🇮🇱⚡️🇮🇷 ትራምፕ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በኢራን ላይ "ጠቅላላ ድል" እንደሚያውጁ ተናግሯል:: ያንን ጦርነት እያሸነፍን ነው ብዬ አስባለሁ፣ ነገር ግን አጠቃላይ ድልን ስናውጅ
🇺🇸🇮🇱⚡️🇮🇷 ትራምፕ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በኢራን ላይ "ጠቅላላ ድል" እንደሚያውጁ ተናግሯል:: ያንን ጦርነት እያሸነፍን ነው ብዬ አስባለሁ፣ ነገር ግን አጠቃላይ ድልን ስናውጅ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብዙ ነገር ይስተካከላል ብሏል። አጠቃላይ ድል ይሆናል። በጣም በቅርቡ ይከሰታል፣ እና የነዳጅ ዘይት ዋጋ እያሽቆለቆለ ይመጣል።

🇬🇧🇦🇺 የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስተር፣ ኬይር ስታርመር፣ በቀናት ውስጥ አዳዲስ የኢንተርኔት ገደቦችን ይፋ ሊያደርግ ነው። በአውስትራሊያ የተደረገውን የማህበራዊ ሚዲያ እገዳን በተምሳሌትነት በመው
🇬🇧🇦🇺 የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስተር፣ ኬይር ስታርመር፣ በቀናት ውስጥ አዳዲስ የኢንተርኔት ገደቦችን ይፋ ሊያደርግ ነው። በአውስትራሊያ የተደረገውን የማህበራዊ ሚዲያ እገዳን በተምሳሌትነት በመውሰድ፣ ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ እና "ከፍተኛ ተጋላጭ" ሕፃናቶች ወደ ሶሻል ሚዲያ መድረኮች እንዳይደርሱ የሚገድብ እና ጠንካራ የዕድሜ ማረጋገጫ ቼኮችን የሚያስተዋውቅ ሕጎችን ተግባራዊ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ሚኒስትሮች፣ ባሁኑ ሰዓት እንደ አውቶፕሌይ፣ ማለቂያ የሌለው scrolling፣ የ"LIKE" ቁልፎች፣ መጋሪያዎች እና የቀጥታ ስርጭት Live ባሉ ባህሪያት ላይ እገዳዎችን እያጤኑ ነው። 📎 ዩሮፓ *-*-* ደስ አይልም? የሰለጠኑ ሀገር መሪዎች እንዲህ ናቸው፣ ዜጎቻቸውን አንዱን ከአንዱ ሳይለዩ በቻሉት ለማገልገል ይጥራሉ፣ ከመጥፎ ነገሮች ለመጠበቅ፣ እንደ መንግሥት ርቀትን ለመሄድ፣ እስከቻሉት አይፈሩም። ጎበዝ፣ ቅኖች ናቸው። ያልሰለጠኑ ሀገሮች በአእምሮ ደሃ መሪዎች የዚያ ግልባጮች ናቸው። ለሕዝባቸው ደህንነት እና ለልጆቻቸው እድገት እምብዛም አይጨነቁም። ሲጀመርም፣ እንዲህ ያለን ጉዳይ ማሰብ ቅንጦት ነው የሚመስላቸው። እንዲያውም የዚህ ተቃራኒውን፣ ልቅነቱን ማስፋፋቱን ይወዱታል። የሰለጠኑ ይመስላቸዋል አንድ፣ ትውልድን ይቀጩበታል፣ ሁለት። ቅንነት የላቸም፣ በሕዝባቸው ላይ መቅሰፍትን ሸርን ሥልጣን ላይ ለመቆየት ሲተበትቡ ይውላሉ።

🇷🇺⚡️🇺🇦 የዩክሬን የስለላ ኤጀንሲ አባላት፣ በሩሲያ በምትገኘው በቤልጎሮድ ከተማ ዘልቀው በመግባት፣ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ዴፖውን ሙሉ በሙሉ አውድመዋል።

🇺🇸🇮🇱 ትራምፕ ለእስራኤል ቻናል 12 እንደተናገረው፣ ባለፉት 24 ሰዓታት ከኔታንያሁ ጋር ባደረገው ውይይት፣ የእስራኤል ጥቃቶች ወደ ሰፊ ጦርነት ከተለወጡ፣ ከኢራናውያን ጋር ብቻቸውን እንዲዋጣ
🇺🇸🇮🇱 ትራምፕ ለእስራኤል ቻናል 12 እንደተናገረው፣ ባለፉት 24 ሰዓታት ከኔታንያሁ ጋር ባደረገው ውይይት፣ የእስራኤል ጥቃቶች ወደ ሰፊ ጦርነት ከተለወጡ፣ ከኢራናውያን ጋር ብቻቸውን እንዲዋጣላቸው ሊተወው እንደሚችል አስጠንቅቆታል። ያንን ተከትሎ፣ እስራኤል ጦርነቱን ከማባባስ ተቆጥባለች።