NurMunir
رفتن به کانال در Telegram
NurMunir is a Qur'an recitation streaming platform where anyone can record and upload or listen to short Qur'an recitations. As a listener you can scroll through recitations from feed, like, save and share recitations, and also follow qaris you like.
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
244
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+27 روز
-430 روز
آرشیو پست ها
244
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
244
+4
እቺ ግጥም በዱንያ ወከባ፣ በስራና በዕለት ተዕለት ኑሮ ውጥረት እና እረፍት ማጣት ምክንያት ከቁርኣን ቃል የራቀችን ልብ የውስጥ ጥማት የሚያወጣ፣ የብዙዎቻችንን የእለት ተእለት ውዝግብና የነፍስ መራብ የምታንፀባርቅ ጥልቅ መልእክት ያላት ግጥም ናት።
ግጥሙ የሰው ልጅ በፈተናና በስራ ሲወጠር ከጌታው ቃል የሚርቅበትንና የሚቆጭበትን ስሜት ያቀርባል።
የህይወት እውነተኛ ብርሃን፣ እረፍትና ሰላም የሚገኘው ወደ አላህ ቃል (ቁርኣን) በመመለስ ብቻ ነው። ታድያ ቁርኣንን እናድምጥ፡፡ የልባችን እረፍትና ሰላም የምናገኝበትን ልብ የሚያርሱ የቁርኣን ቅጂዎች NurMunir ላይ እናገኛለን። በየትኛውም ሁኔታ ሆነን ቁርኣንን እናድምጥ!
244
ጌታዬ
ጎትጓች ወስዋሽ ነገር ከቦኝ በዙሪያዬ
የማይረባ ጠፊ አጥፊን ተከትዬ
ላሳቀ ላፌዘ ለጠፍ ተታልዬ
አፈር ለሚበላው ህልሜን አቆልዬ
ልቤ ሸፍቶብኝ ወዲያ ማዶ ውዬ
አልነቃም ወይ ምን ሆንኩ መች ይሁን መምጫዬ
ነገ ነገ እያልኩ ባከነ ጊዜዬ
አፈር በላኝ ጠፋሁ ምን ይሻል ጌታዬ
...
እርሜን ማታስወጣኝ ጀነት ልታስገባኝ
ዘልቆ ከሚያመው ከሳት ልታድነኝ
ብርሃን ብትልክልኝ ና ወዲህ ብትለኝ
አዋጭ ትርፋማውን ሚሻልን ብትነግረኝ
ታድያ ለምን ሸፈትኩ ለምን እምቢ አልኩኝ
ለምን ለቁም ነገር ጊዜ ጠበበብኝ
ምትለኝን ልኖር ላደምጥ ካልገራሁኝ
ምን ተለየሁ ታድያ ካለው ምናገባኝ
ያላቂው የዱንያው ምናለ ቢቆየኝ
ወዳንተ ብመለስ ምናለ ቢቀናኝ
244
✨ የዕለቱ ልዩ ቲላዋ ግብዣ | Today’s Special Recitation Selection ✨
አንዳንድ ጊዜ በዕለት ተዕለት ሁከት እና በህይወት ፈተናዎች መካከል ልባችን ፍፁም የሆነ እረፍት እና ሰኪናን ይፈልጋል። አላህ ደግሞ ለመረጣቸው ባሮቹ በከበሩ ቃላቱ ለነፍሳቸው እረፍት ይሰጠናል። አላህ በከበረ ቃሉ «
أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ
» (እወቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረጋጋሉ) እንዳለው።
ዛሬ ለእናንተ የመረጥነው ልዩ የቁርዓን ግብዣ በአሚር ዘይኑ (Amir Zeynu) ድንቅ እና ልብን በሚነካ ድምፅ የተቀራውን ሱረቱል መርየም (ከአያ 16-33) ነው:: 🕊️❤️
🌿 ከልብ የምንማረው ትምህርት:
እነዚህ አንቀጾች መርየም (ዐ.ሰ) ከሰው ልጅ እይታ ተገልላ በነበረችበት ከባድና ጨለማ ጊዜ፣ የአላህ ድንቅ ተአምርና እዝነት እንዴት እንደወረደላት የሚያወሱ ናቸው።
ከማንም በላይ አላህ አብሮህ አለ: መርየም በብቸኝነትና በጭንቀት በተከበበች ጊዜ፣ አላህ የፅናቷን ፍሬ ሰጣት። ህይወትህ ሁሉ የተዘጋ ቢመስልህ እንኳ አላህ ካንተ ጋር መሆኑን አትርሳ።
ሶላትና የወላጅ ሀቅን መጠበቅ: በሕፃንነቱ የተናገረው ኢሳ (ዐ.ሰ) የመጀመሪያ መልዕክቱ ሶላትን እና ለእናቱ መልካም መሆንን ነበር። ይሄም በየትኛውም የህይወት አጋጣሚ ሶላት እና የወላጆች ሐቅ ምን ያህል ታላቅ እንደሆኑ ያሳየናል።
ትንሽ ፋታ ወስዳችሁ፣ የጆሮ ማዳመጫችሁን በማድረግ ይህንን ውብ ቲላዋ አዳምጡት፤ ለልባችሁ እረፍትንና ሰኪናን ስጡ።
ይህንን በረካ ለወዳጅ ዘመድ በማጋራት (Share) የኸይር እና የሰኪና ምክንያት ሁኑ!
የቅጂው ሊንክ 🔗✨: https://nurmunir.com/recitation/ff5b2252-a0dc-4c24-8ee1-1366029ac0a8
244
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
244
በኢብኑ ሰማን በሚያምር መልኩ የተቀራው ሱረቱል ሙልክ የዛሬ ግብዣችን ነው ።
ሱረቱል ሙልክ ትልቅ ቦታ ያላት ሱራ ናት፤ በሀዲስ እንደተዘገበው እሷን በየምሽቱ የቀራ የቀብር ቅጣት አይነካውም (Al-Sunan al-Kubra, Hadith 10546 / Vol. 6, p. 179)፣ የባልደረባውም ወንጀል እስኪማር ድረስ ያማልዳል Sunan Abi Dawud (Hadith 1400) / Jami` at-Tirmidhi (Hadith 2891) ።
ታድያ እቺን ትልቅ መልዕክት የያዘች ሱራ እያስተነትንን እናድምጣት።
hቁርኣን ጊዜ ለመስጠት ረመዷንን አንጠብቅ!
244
