fa
Feedback
Leikov's Thought

Leikov's Thought

رفتن به کانال در Telegram

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
192
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+27 روز
-430 روز
آرشیو پست ها
ውስጡን የሚቆጣጠር ጠቢብ የውጪው ዓለም ጫና በፊቱ ኢምንት ነው።

የፍልስፍና መምህሩ ወደክፍል ውስጥ ይገባና ለተማሪዎቹ የመጨረሻውን ፈተና ሊሰጥ ተዘጋጀ:: አንድ ወንበር በማንሣት ከጠረጴዛ ላይ አስቀመጠና፡- «እስከዛሬ በዚህ ኮርስ የተማራችሁትን ቁምነገር ከግምት ውስጥ በማስገባት ይኸ ወንበር አለመኖሩን አረጋግጡልኝ›› አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ተማሪዎች የዚያን ወንበር አለመኖር ወይም መኖሩ እውነት አለመሆኑን ለማረጋገጥ መጻፍ ጀመሩ፡፡ ብዙዎቹ ለሰዓታት የፈጀ ጥናታቸውንና ማብራሪያቸውን ሲፅፉ አንድ ተማሪ ግን በሰላሳ ሴኰንድ ውስጥ መልሱን ጽፎ ለመምህሩ በማስረከብ ክፍሉን ለቅቆ ሄደ፡፡ በነጋታው ፕሮፌሰሩ የተማሪዎቹን ውጤት ይዞ መጣ፡፡ ከሁሉም ተማሪ ከፍተኛውን ውጤት ያገኘው በሰላሳ ሴኰንድ ፈተናውን ጨርሶ የሄደው ነበር፡፡ ፕሮፌሰሩም እንዲህ አለ፡፡ «ብዙዎቻችሁ የወንበሩን አለመኖር ለማሳየት ብዙ ደክማችኋል፡፡ ይኸ ተማሪ ግን ከሁላችሁም በላቀ መንገድ ወንበሩ አለመኖሩን አረጋግጦልኛል›› አለ፡፡ ተማሪው ለጥያቄው የሰጠው ምላሽ እንዲህ የሚል ነበር፡- «የቱ ወንበር?»

"ሰው ከእንስሳ የሚለየው በማሰቡ ነው" የሚለው ህግ ለሶቅራጥስ ቦታ የለውም። ምነው ቢሉ " ማሰብ የለየው ሰውን ከእንስሳ ሳይሆን ሰውን ከሰው ነው " ይለናል።

ከጠገበ አሳማ የራበው ሰው ይሻላል

'ሽማግሌ ነኝ ፥ ብዙ ጭንቀቶችን አሳልፌያለሁ ፥ አብዛኞቹ አልሆኑም' Mark Twain

"ዐውቃለሁ የሚል ሰው፣ ማወቅ የሚገባውን ያህል ገና አላወቀም።" ዕውቀት ካለው ሰው አንደበት እኔ ዐዋቂ ነኝ የሚል የትዕቢት ንግግር ሲወጣ አትሰሙም ፥ ምክንያቱም ብዙ ሲያውቅ ብዙ እንደማያውቅ ነው የሚያውቀው። ባወቅን ቁጥር ገና የሚታወቅ ነገር ብዙ እንዳለ እየገባን ይመጣል ፥ ካወቅነው ይልቅ ያላወቅነው እንደሚሰፋ እንረዳለን ፥ ብዙ ስናውቅ ብዙ ለማወቅ ጥረት እናደርጋለን ፥ ያላወቅነው ነገር ስለሚበዛ ያወቅናት ጥቂቷን እንደሆነች እንረዳና እንደ ሶቅራጥስ እንዲህ እንላለን " I know that I know nothing " እኔ የማውቀው ምንም እንደማላውቅ ነው። በተቃራኒው በትዕቢት እኔ ዐውቃለሁ የሚል ሰው ደግሞ ማወቅ የሚገባውን ያህል ገና አላወቀም!

ሰዉ ከየት ከየት ነው ቀልድ ሚመጣለት ግን " የእንጀራ ገመዴ ላይ ልብስ ያሰጣችሁ ሰዎች - ደርቋል አንሱልኝ " ከት ብዬ ነው የሳቅሁት😂😂

ሚያስጨንቀው እኮ ማጥፋትህ አይደለም ፥ ጥፋቱን እንደምትደግመው ማወቅህ እንጂ።

ውጤታማነት መለካት ያለበት ምን ያህል ስራ ሰራሁ በሚለው እንጂ ምን ያህል ጊዜ ስራው ላይ አሳለፍኩ በሚለው መሆን የለበትም!

ሀሳቦቻችን ይጋጩ ፣ ይፋጩ እኛ ግን በሰላም እንኑር እኛ ሀገር የተለመደው ነገር በሀሳብ ከተለያየህ በአካልም መጠቃቃት አለብህ አይነት አስተሳሰብ ነው። የሀሳብ ልዩነት ሁሌም ቢሆን ያለ የሚኖር ነው። ቢያንስ በአንድ ርዕስ እንኳን ሁለት ሰው ሳይለያይ አይቀርም። ባለን እምነት ፣ ባለን የህይወት መርህ ፣ የፖለቲካ አቋም ፣ ባህል ፣ በምንደግፈው የእግር ኳስ ቡድን ወዘተ.. እንዲህ አይነት ልዩነቶችን ይዘን በማንስማማባቸው ነገሮች ላይ መወያየት ፣ መነጋገር ፣ መሟገት ክፋት የለውም። ግን አንዱ ሌላውን ለምን የእኔን ሀሳብ አልተቀበልክም በሚል መሳደብ ፣ ማንቋሸሽ ፣ ማግለል ወዘተ ትክክል አይደለም ። በሀሳብ ተለያይቶም ጓደኛ መሆን ይቻላል። በእምነቱ የእኛ ቡድን ያልሆነ ሰው ቢሆን እንኳን አሪፍ ብቃት ካለው ማድነቅ ይቻላል። ተግባብቶ ተረጋግቶ መኖር ይቻላል። ሀሳብ እየተጋጨ በአካል በሰላም ተቻችሎ መኖር ይቻላል። ሀሳባችን ተጋጭቷል ማለት እኛ ተጋጭተናል ማለት አይደለም። በሃሳብ ስላልተግባባን ተጣልተናል ማለት አይደለም። የተሻለው ሀሳብ ስላሸነፈ ሰውየው ተሸንፏል ማለት አይደለም ፣ ሀሳቡ እንጂ። የሀሳብ ልዩነትንና ጥላቻን እንለይ!

ዛሬ የበታች ነው ብለህ አስበህ ግፍ የሰራህበት ሰው ነገ የበላይህ ሆኖ ሊመጣ ይችላል

ሁሉም ችግራችን ምንጩ መንፈሳዊ ነው

ከትችት ይልቅ ሙገሳ ያስፈራኛል ሲያሞግሱህ እላይ ሰቅለውሃል - ሊፈጠፍጡህ ይችላሉ - የተገነባ ማንነት ከሌለህ ሲፈጠፍጡህ ትሰበራለህ ስትተች - መጀመሪያም ታች ስለረጋገጡህ የሚያስፈራህ የለም - መነሳትህ አይቀርም

ሼክስፒር
ሼክስፒር

photo content

photo content

አንዳንዱ ደግሞ እንደፈለገ ያስቀይምህና ምንም እንዳልተፈጠረ አይነት መጥቶ ለሰላምታ እጁን ይዘረጋልሃል😒 ይቅርታ መጠየቅ ልመዱ! ይቅርታን ተማምናችሁ ሰውን አትበድሉ!

አሁን ያለህበትን አይነት ኑሮ ለምን እየኖርክ እንደሆነ ለማወቅ ዛሬ የዋልክበትን አዋዋል ገምግም

ከሀገር መውጣት እንደ ስኬት የሚቆጠርባት ሀገር ውስጥ ነው የምንኖረው 😥