fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

رفتن به کانال در Telegram

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም 2ተኛ ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
1 845
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+337 روز
+13130 روز
آرشیو پست ها
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ በበኩለቸው ማኑዋሎቹ በሁሉም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወጥ የሆነ የመማሪያ ጥጎች ተግባራዊ ለማድረግ እና የህጻናቱን ሁለንተናዊ እድገት በአግባቡ ለመመዘን የሚያስችል የመመዘኛ መስፈርት ለማዘጋጀት የሚያግዙ መሆናቸውን ጠቁመው ስራ ክፍሉ ሁሉም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች ማኑዋሎቹን በአግባቡ ተግባራዊ ማድረጋቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የተዘጋጀውን የህጻናት እድገትና የትምህርት ምዘና መመሪያ እንዲሁም የመማሪያ ጥጎች አደረጃጀት ማኑዋልን በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ (መስከረም 29
+6
ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የተዘጋጀውን የህጻናት እድገትና የትምህርት ምዘና መመሪያ እንዲሁም የመማሪያ ጥጎች አደረጃጀት ማኑዋልን በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም ባዘጋጀው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የህጻናት እድገትና የትምህርት ምዘና መመሪያ እንዲሁም የመማሪያ ጥጎች አደረጃጀትና አጠቃቀም ማኑዋልን መሰረት በማድረግ ለክፍለከተማ የስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎች፤አስተባባሪዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ውይይት አካሂዳል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ አበራ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የህጻናት ሁለንተናዊ እድገት መሰረት የሚጣልበት የትምህርት ደረጃ ከመሆኑ በሻገር ተማሪዎቹ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ዝግጁ የሚሆኑበት መሆኑን አስታውሰው በሁለቱ ማኑዋሎች ላይ በቂ ግንዛቤ በመጨበጥ በሁሉም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንዲሆን አስፈላጊውን የክትትልና ድጋፍ ስራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የ 2019 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ግምገማ አካሄዱ:: (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ
+2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የ 2019 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ግምገማ አካሄዱ:: (መስከረም 29/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የ2019 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት የቁልፍና አበይት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሂደዋል:: በውይይቱ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት የተገኙ ሲሆን የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ጌታሁን ለማ አማካኝነት በሩብ አመቱ የተከናወኑ ቁልፍና አበይት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም ሥራዎቹ ሲከናወኑ የነበሩ ጥንካሬዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች በሪፖርቱ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ አስተባባሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ ቀደም ሲል በየሥራ ክፍሉና በየዘርፉ ግምገማ የተካሄደበት መሆኑን ገልፀው ሪፖርቱ የዝግጅት ምዕራፍ ስራው በተቀመጠው እቅድ መሰረት በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑን ያሳያል ብለዋል:: አክለውም በጋራ ውይይቱ የተነሱ ሀሳቦች ተካተው በቀጣይ ለፕሮሰስ ካውንስል እና ጠቅላላ ሰራተኛ ውይይት እንደሚቀርብ መሆኑን ተናግረዋል:: ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

📚Amharic grade 4 🧿Size 6.4 MB

📚English book-2 grade 4 🧿Size 1.4 MB

📚English book-1 grade 4 🧿Size 1.7 MB

📚Maths grade 4 🧿Size 2.0 MB

📚General science grade 4 🧿Size 16.8 MB

📌GRADE 4 BOOKS📗📗📗

ማስታወቂያ! 5 (መስከረም 28/2019 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
+9
ማስታወቂያ! 5 (መስከረም 28/2019 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

ማስታወቂያ! 4 (መስከረም 28/2019 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
+9
ማስታወቂያ! 4 (መስከረም 28/2019 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

ማስታወቂያ! 3 (መስከረም 28/2019 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
+9
ማስታወቂያ! 3 (መስከረም 28/2019 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

ማስታወቂያ! 2 (መስከረም 28/2019 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
+2
ማስታወቂያ! 2 (መስከረም 28/2019 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

ማስታወቂያ! 1 (መስከረም 28/2019 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
+9
ማስታወቂያ! 1 (መስከረም 28/2019 ዓ.ም) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ቡድን መሪ አቶ ተሾመ ቀናሳ በበኩላቸው የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ የተዘጋጀው ስትራቴጂ በሶስት መርሀግብሮች ማለትም ከትምህርት ሰአት በፊት እንዲሁም ከትምህርት ሰአት በኋላ እና ዘወትር ቅዳሜ በክላስተር ደረጃ በሚሰጥ የማጠናከሪያ ትምህርት ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆኑን አስታውሰው ድጋፍና ክትትሉ በየትምህርት ቤቱ ስትራቴጂው ምን ያህል ተግባራዊ እንደሆነ በማየት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

ቢሮው ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ ተግባራዊ ያደረገው ስትራቴጂ የሚጠበቀውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ። (መስከረም 28/2019 ዓ
+9
ቢሮው ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ ተግባራዊ ያደረገው ስትራቴጂ የሚጠበቀውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ። (መስከረም 28/2019 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ አተገባበርን መሰረት በማድረግ በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ድጋፍና ክትትል ለሚያካሂዱ ሱፐርቫይዘሮች ኦረንቴሽን ሰጥቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ጥላዬ ዘውዴ በከተማ አስተዳደሩ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ የሚያስችል ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውሰው የ2019 ዓ.ም ትምህርት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ስትራቴጂው በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ምንያህል ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ በማረጋገጥ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እንዲቻል ድጋፍና ክትትሉን ማካሄድ ማስፈለጉን አመላክተዋል። ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘውም ድጋፍና ክትትሉን የሚያካሂዱ ሱፐርቫይዘሮች ስትራቴጂው በሁሉም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአግባቡ ተግባራዊ ሆኖ በከተማ አስተዳደሩ በ2019 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆኑ እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት መረጃዎችን በማሟላት ግብረ መልስ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።

ዘንድሮ የልህቀት ማዕከል ሆኖ በአዲስ መልክ ስራ በጀመረው ምስራቅ ጎህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ (መስከረም 28/
+5
ዘንድሮ የልህቀት ማዕከል ሆኖ በአዲስ መልክ ስራ በጀመረው ምስራቅ ጎህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ (መስከረም 28/2019 ዓ.ም) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በመሀል ካሳንችስ የሚገኘውና ዘንድሮ የልህቀት ማዕከል ሆኖ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ መልክ ስራ የጀመረው ምስራቅ ጎህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ትምህርት ቤቱ በ2019 የትምህርት ዘመን በሳይንስ ትምህርት ተሰጥኦ ያላቸዉን ተማሪዎች በመቀበል ብቁ በሆኑ የትምህርት አመራሮችና መምህራን አማካኝነት ትምህርት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ስታንዳርዱን ጠብቆ በተገነባው ትምህርት ቤቱ ውስጥ ለመማር ማስተማር ስራዉ የሚያገለግሉ ግብዓቶች የተሟሉለት ከመሆኑም ባሻገር ዘመናዊ የስፖርት ሜዳ ተገንብቶለታል፡፡ ይህም የከተማ አስተዳደሩ ለዘርፉ የሰጠዉን ልዩ ትኩረት የሚያሳይ ነው፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc