fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Strong Islam

Strong Islam

رفتن به کانال در Telegram

WELL COME TO STRONG ISLAM ❤️

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
333
مشترکین
-424 ساعت
-67 روز
+130 روز
آرشیو پست ها
ስፈልግ አልቅሼ ጌታዬ ምነው እለዋለሁ🤲 🥺 ስፈልግ ንጭንንጭ እልበታለሁ 🥺 ስፈልግ ሳምንት ከዛም በላይ አኮርፈዋለሁ 🥺 ስፈልግ በራህመትህ እዘንልኝ እለዋለሁ 🥺 ስፈልግ እንደፈለክ አድርገኝ ሀቅህ ነኝ እለዋለሁ ስፈልግ... መኖሬ ኸይር ካለው አቆየኝ መኖሬ ኸይር ከሌለው ወዳንተ አስጠጋኝ እለዋለሁ 😭🥺 የኔ አላህ....ስንቱን ቻለኝ 🤲🤲🤲 @strong_islama

''የማትቆይ ከሆነ አትንካት💔💔 የማትቆይ ከሆነ ሂወቷን አታበላሽ'' .የማትዳይ ከሆነ አላህ ጋር አታጣላት'' የማትቆይ ከሆነ አንገቷን አንድትደፋ አታድርጋት'' @strong_islama
''የማትቆይ ከሆነ አትንካት💔💔 የማትቆይ ከሆነ ሂወቷን አታበላሽ'' .የማትዳይ ከሆነ አላህ ጋር አታጣላት'' የማትቆይ ከሆነ አንገቷን አንድትደፋ አታድርጋት'' @strong_islama

ሶብር የሌለው ሰው ዲን የለውም ሶብር ማለት ከዲን ዋናው እሱ ነው ሶብር የሌለው ዲን ጭንቅላት እንደሌለው አካል ነው መታገስ ግዴታ ነው የሰው ልጅ በዚች አለም  አደጋዎች ያጋጥሙታል ድካም ያጋጥመዋል  መከራዎች ያጋጥሙታል መታገስ አለበት ጌታውን እስኪገናኝ መቻል አለበት ።              አላህ ከታጋሾች ያድርገን

12 SurahYusuf ReciterDrMisbah Sani.m4a30.88 MB

~ ለጌታዋ የምትጠይቀው፣ እንዲሰጣት የምትፈልገው፣ እንዲያስተካክልላት፣ እንዲያሽራት፣ የልቧን መሻት እንዲፈፅምላት የምትከጅለው ብዙ ነበር። ግና «ያ ረብ…»  ብላ ከማልቀስ ውጪ ሌላ ቃላት ማውጣት አልቻለችም። እህቴ እንኳንም ጌታሽ ዘንድ አለቀስሽ። አብሽሪ! @strong_islama

ከልክ በላይ ሰው መውደድ ለካ ጉዳት ነው !

እሁድ እንዴት ነበር
Anonymous voting

ትናፍቀኛለህ!   በምላስ ወለምታ አስቀይሜሃለው፤ አንተ ስትጠጋኝ እኔ ርቄሃለው፤ ብዙ ችለህኛል ኮርቼብሃለው፤ ላትመለስ አትሂድ እናፍቅሃለው።        ያኔ......... መቅበጥ ማሽካካቴ፤ ውዬ እዚያ መቅረቴ፤ መሽቀርቀር መኩራራቴ፤ ከጎኔ ስላለክ ላንተ ራሴን መስጠቴ፤ ነበር ያ ቅብጠቴ። ዛሬ በዚህ ጀንበር በማለዳ ፀሐይ፤ ስትወጣ ስትገባ በዓይኔ አንተን እንዳይ፤ ነበረ ምኞቴ....! ግን አንተ ዬለህም ከሩቅ እንኳ አትታይ፤ እባክህ አትጣለኝ ትናፍቀኛለህ፥ደህና እሆናለው ባዓይኔ አንተን ሳይ😊 @strong_islama Masasebiya ene altsafkum share adereku enji😁

🍁"የሰብር " ከባዱ ክፍል ከነፍስህ ፣ከአይምሮህ እና ከልብህ ጋር የሚደረገውን ጦርነት መዋጋት ነው🍂 @strong_islama

Repost from N/a
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ​📌 ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ​«ጊዜ ወርቅ ነው» ይባላል፤ እስኪ እናስብ! ስንት ጊዜያችንን ነው በዚህ ዘመናዊ መሣሪያ (እንደ TikTok እና መሰል ማኅበራዊ ሚዲያዎች) በማይጠቅም ነገር ላይ ያሳለፍነው ? እናስብ በአላህ ወላሂ ግዝያችን በቁርአን በዒልም በሙሃደራ ማዳመጥ ብናሳልፍ ግዝያችን ሰንት በተጠቀምን ወላሂ ። የኛ አንድ ሰከንድ ማለት ነው እነዛ ቀብር ያሉ ሰዎች እስዋን ይመኙታል የኛ አንድ ሰከንድ ማለት ነው ምን ለማረግ ነው ሚመኝዋት ወደዚች ዱንያ መጥተው ምን ሊሰሩባት ? አላሁ ሱብሓመሁ ወተዓላ አንዲህ ይላል : حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ رَبِّ ارْجِعُونِ አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! (ወደ ምድረ ዓለም) መልሱኝ፡፡ لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ ۚ كَلَّا ۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَائِلُهَا ۖ وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ «በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» (ይህን ከማለት) ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት፡፡ ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አልለ፡፡ ምን ይመኛሉ የሞቱት ሰዎች ወደዚች ዱንያ መጥተው ምን ሊሰሩ ነው በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ ነው ሚሉት እኛ በማይሆን በአሉ ባልታ ወሬ በማይሆን ነገር የምናጠፍት ጊዜ ለነሱ ውድ ነች አንድ ሰከንድ ተስቢሕ (አላህን ማወደስ) ሱብሓነላህ  ሊሉባት  ይመኛሉ ወላሂ እኛስ ምን ተጠቀምን አስኪ ራሳችን እንፈትሽ ? ከአምስት ነገሮች በፊት አምስት ነገሮች!  ረሱል (ሰለላ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿اغْتَنِمْ خَمْسًا قبلَ خَمْسٍ: شَبابَكَ قبلَ هِرَمِكَ، وصِحَّتَكَ قبلَ سَقَمِكَ، وغِناكَ قبلَ فَقْرِكَ، وفَراغَكَ قبلَ شُغْلِكَ، وحَياتَكَ قبلَ مَوْتِكَ.﴾ “አምስት ነገሮች ወዳንተ ከመምጣታቸው በፊት በአምስት ነገሮች ቅደማቸው። ወጣትነትህን እርጅና ከመምጣቱ በፊት፣ ጤንነትህን በሽታ ከመምጣቱ በፊት፣ ሀብትህን ድህነት ከመምጣቱ በፊት፣ ትርፍ ግዜህን ትርፍ ግዜ ከማጣትህ በፊት፣ ህይወትህን ሞት ከመምጣቱ በፊት።” ሸይኽ አልባኒ በሶሂህ አተርጊብ ውስጥ ሶሂህ ብለውታል: 3355 ኣሻሂድ የዚህ ሐዲሥ ዋና መልእክት—ትርፍ ጊዜህን በሥራ ከመጠመድህ በፊት ተጠቀምበት ነው። በቂ ጊዜ እያለህ ያልሠራኸውን መልካም ነገር፣ ነገ የኑሮና የሥራ ጫና ሲበዛብህ ልትሠራው አትችልምና ዛሬውኑ ተጠቀምበት! አንድ 82 የደረሰ እድሜው አባት ከቤት ወደ መስጂድ ነው ቅርብ ነው ቤታቸው እና መስጂድ ነው ሚውሉት ይሄ ይሄ ብለው አያቁም መጥፎ ተናግረው አያቁም አኽላቃቸው ወላሂ በጣም ያማረ ነው ከዛ አንድ ቀን ስለ ጊዜ አጠቃቀም ሙሃደራ ሳሰማቸው ግዝያችን በከንቱ «ጊዜያችንን በከንቱ አሳለፍነው» ብለው ተከዙ።እኔም በውስጤ «ዓጀብ!» አልኩ። የሳቸውን አምልኮና መልካም አኽላቅ እያየሁ እሳቸው እንዲህ ካሉ—እኛማ ምን ልንል ነው? ወላሂ እጅግ የሚገርም ትምህርት ነው። تَزَوَّدْ مِنَ التَّقْوَى فَإِنَّكَ لا تَدْرِي إِذَا جَنَّ لَيْلٌ هَلْ تَعِيشُ إِلَى الفَجْرِ ​ ​አላህን በመፍራትና በመታዘዝ ስንቅን ያዝ፤ ምክንያቱም አታውቅምና፤ ሌሊቱ ሲመሽ እስከ ንጋት ድረስ በህይወት መቆየትህን! ​فَكَمْ مِنْ صَحِيحٍ مَاتَ مِنْ غَيْرِ عِلِّةٍ وَكَمْ مِنْ سَقِيمٍ عَاشَ حِينًا مِنَ الدَّهْرِ ​ ​ምንም በሽታ ሳይኖርበት በድንገት የሞተ ስንቱ ጤናማ ሰው አለ! ለረጅም ጊዜ በህመም እየማቀቀ በህይወት የኖረ ስንቱ ታማሚ አለ! ​إِذَا المَرْءُ لَمْ يَلْبَسْ ثِيَابًا مِنَ التُّقَى تَقَلَّبَ عُرْيَانًا وَإِنْ كَانَ كَاسِيًا ​ ​የሰው ልጅ የአላህ ፍራቻን (ተቅዋን) ልብስ አድርጎ ካልለበሰ፤ ልብስ የለበሰ ቢመስልም እንኳ በባዶ አካሉ የሚዞር ዕሩቅ ነው። ገጣሚው አንዲህ ይላል دَقَّاتُ قَلْبِ المَرْءِ قَائِلَةٌ لَهُ إِنَّ الحَيَاةَ دَقَائِقٌ وَثَوَانِي فَارْفَعْ لِنَفْسِكَ بَعْدَ مَوْتِكَ ذِكْرَهَا فَالذِّكْرُ لِلإِنْسَانِ عُمْرٌ ثَانِي ​ ​የሰው ልጅ የልብ ምት እንዲህ ስትል ትነግረዋለች፦ "ህይወት ማለት ደቂቃዎችና ሰከንዶች ብቻ ነች!" ስለዚህ ከሞትህ በኋላ የሚቀር መልካም ስምህን አስቀር/ገንባ፤ ምክንያቱም መልካም ስም ለሰው ልጅ ሁለተኛ ዕድሜ ነውና። እንዲህም ተብለዋል  በህይወቴ ውስጥ እንደ አንዲት ቀን እንደተጸጸትኩበት ነገር ተጸጽቼ አላውቅም፤ እርሷም ፀሐይ የጠለቀችባት፣ ዕድሜዬ የቀነሰበት ነገር ግን መልካም ሥራዬ ያልጨመረበት ቀን ነች።" يَسُرُّ المَرْءَ مَا ذَهَبَ اللَّيَالِي وَكَانَ ذَهَابُهُنَّ لَهُ ذَهَابَا تَمَنَّى أَهْلُ الأَقْبَارِ يَوْمًا مِنَ الدُّنْيَا وَأَنْتَ بِهِ تَلاعَبُ ​ ​ቀንና ሌሊቶች ማለፋቸው ሰውን ያስደስተዋል፤ የእነሱ ማለፍ ግን የእርሱም ዕድሜ ማለፍና መሄድ ሆኖ ሳለ! በመቃብር ያሉት ሰዎች ከዱንያ አንዲት ቀን ብቻ ተመልሳላቸው ቢሆን ብለው ይመኛሉ፤ አንተ ግን ያቺን ቀን እጅህ ላይ አድርገህ ትጫወትባታለህ! ​أَيَا مَنْ عُمُرُهُ يَمْضِي سِدًى فَالأَمْسُ قَدْ مَاتَ وَاليَوْمُ الِاحْتِضَارُ وَأَهْلُ القُبُورِ يَتَمَنَّوْنَ سَاعَةً وَأَنْتَ لَاهٍ وَالعُمُرُ يَنْهَارُ ​ ​ዕድሜው በከንቱ የሚያልፍበት ሰው ሆይ! ትናንትናህ ሞቷል፣ ዛሬህ ደግሞ በመቃረብ ላይ ነው፤ በመቃብር ያሉት ሰዎች አንዲት ሰዓት ብቻ ይመኛሉ፤ አንተ ግን በቸልተኝነት ተጠምደሃል፣ ዕድሜህም እየደረመሰና እየተጠናቀቀ ነው። اللَّهُمَّ إنَّا نَعُوذُ بِكَ مِنَ الْعَجْزِ وَالْكَسَلِ، وَنَعُوذُ بِكَ مِنْ تَسْوِيفِ الأَعْمَالِ وَضَيَاعِ الأَوْقَاتِ .
​«አላህ ሆይ! ከስንፍናና ከድካም፣ ሥራን ወደ ነገ ከማስተላለፍና ጊዜን በከንቱ ከማባከን በአንተ እንጠበቃለን።»
اللَّهُمَّ أَعِنَّا عَلَى اسْتِغْلاَلِ أَوْقَاتِنَا فِيمَا يُرْضِيكَ، وَلاَ تَجْعَلْ أَعْمَارَنَا هَبَاءً مَنْثُورًا.
​«አላህ ሆይ! ጊዜያችንን አንተን በሚያስደስት ነገር ላይ እንድንጠቀም እርዳን፤ ዕድሜያችንንም በከንቱ የሚበተን አታድርግብን።»
​اللَّهُمَّ اجْعَلْنَا مِمَّنْ طَالَ عُمُرُهُ وَحَسُنَ عَمَلُهُ، وَنَعُوذُ بِكَ مِنْ طُولِ الأَمَلِ وَقَسْوَةِ الْقَلْبِ.
​«አላህ ሆይ! ዕድሜው ረዝሞ ሥራው ከማረላቸው ሰዎች አድርገን፤ ከተስፋ ርዝመቱና ከልብ ድርቀት በአንተ እንጠበቃለን።»
​አላህ ሁላችንንም ባነበብነው የምንጠቀም ያድርገን።» السلام عليكم ورحمة الله وبركاته https://t.me/ibnuTe

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ደህና አደራቹ ነቃ ብላች እንድትውሉ ቡና መጠጣት አትርሱ

😢😢አውቃለው ጓደኞቼ የደረሱበት ቦታ እንዳልደረስኩ አውቃለው የቆምኩና የደከምኩ እንደሆንኩ አላህዬ ባንተ ግን ተስፋ አልቆረጥኩም 🥹🥺 @strong_islama

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🌸 ምክር ለውዷ እህቴ 🌸 ቅድምያ ባለሽበት ይጠብቅሽ እና የመጣሁበት ምክር ምን ልልሽ ነው አንቺ ውድ ነሽ የተከበርሽ ሴት ነሽ እና ውድ ነገር ካለ ቦታው ርካሽ እንደሆነ ሁሉ አንቺም ቦታሽን አወቂ ራስሽን ዝቅ የሚያደርግ ቦታ ራቂ በተለይ ኒቃብ አርጌሽ ካለ ለኒቃቡ የማይመጥን ቦታ ምትገኚ እህት አላህን ፍሪ ። ​🗣️ የጃሂሎች (አላዋቂዎች) ወሬ አይጉዳሽ ! ጃሂሎች (አላዋቂዎች) ኒቃብ አርጋ ስያይዋት ምን ይላሉ እስዋ እኮ እንደዚ ነበረች እንደዚ ነበረች ይላሉ እህቴ በጃሂል ንግግር ልብሽ እንዳይሰበር አእምሮሽ አንዳይጨናነቅ ልብ በይ እህቴ ጃሂል ሁሌ የመጣለት ነው ሚያወራው እና ብልህ ሁኚ የፈለገ ወንጀል ብትሰሪ ተፀፅተሽ ወደ አላሁ ሱብሓነሁ ወተዓ ከተመለሽ አላህ ይቅር ይልሻል ሰው ያወራ ቢያወራ ። ረሱል ሰለላ ዓለይሂ ወሰለም አንዳሉት التَّائِبُ مِنَ الذَّنْبِ كَمَنْ لاَ ذَنْبَ لَهُ" “ከወንጀሉ ተውበት (ንስሃ) የሚያደርግ ሰው ወንጀል እንደሌለበት ነው።” 📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 3446 ረሱል ሰለላ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ ﴿الْإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ - أَوْ : بِضْعٌ وَسِتُّونَ - شُعْبَةً، فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ : لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَأَدْنَاهَا إِمَاطَةُ الْأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ، وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الْإِيمَانِ ﴾ “ኢማን ከሰባ ሶስት እስከ ሰባ ዘጠኝ የሚደርሱ ቅርንጫፎች አሉት። በላጩ ንግግር፦ ‘ላኢላሃ ኢለላህ’ ማለት ሲሆን። የመጨረሻውና ዝቅተኛው መንገድ ላይ እንቅፋትን ማስወገድ ነው። ሃያዕ (እፍረት ማድረግ) የኢማን አንዱ ክፍል ነው።” ሙስሊም ዘግበውታል፡ 35 እዚህ ጋር የተፈለገበት ዋናው ነጥብ ሐያእ ሲሆን፣ ሐያእ ከኢማን መሆኑን የአላህ መልእክተኛ ሰለላ ዓለይሂ ወሰለም ነግረውናል። አንድ ድንቅ ታሪክ ልንገርሽ፦ አንዲት እናት ልጇ በድንገት ህይወቱ አልፎ ሰዎች ሊያጽናኗት ወደ ቤቷ ሲመጡ፣ እሷ ፊቷን ሙሉ በሙሉ በኒቃብ ተሸፍና ወጣች። ​፡ ከተሰበሰቡት ሰዎች አንዱ፦ "ልጅሽ በሞተበት በዚሁ አሰቃቂና አስቸጋሪ ሰዓት እንኳ ፊቱሽን ተሸፍነሽ (ኒቃብ አድርገሽ) ትወጫለሽ  ብሎ ጠየቃት። ​የእሷ ድንቅ መልስ፡ እሷም እንዲህ ስትል መለሰችለት፦  ​"ልጄን ማጣቴ ትልቅ ሙሲባ (መከራ) ነው፤ ነገር ግን ሐያኤን (እፍረቴንና ክብሬን) ማጣቴ ከልጄ ማጣት የበለጠ ሙሲባ እንዳይሆንብኝ ነው!" ኒቃብ የሴቷን ግርማና ክብር እንደሚያበዛ ሲገልጽ ገጣሚው እንዲህ ይላል ​وتنقَّبَت كَيلا تُرانَ، وَإِنَّما ... زادَت بِذاكَ العُيونَ فيكِ تَحَيُّرا ​ "እንዳይታይ ብላ ፊቷን በኒቃብ ተሸፈነች... ነገር ግን ያ መሸፈኛዋ ለሚያዩዋት ሰዎች ይበልጥ አግራሞትንና ክብርን ጨመረባት።" ​"ኒቃብ ያደረገች ሴት ልክ በጠባብ የታሸገ ውድ የዕውድ (የሽቶ) ብልቃጥ ናት፤ ክዳኑ ካልተከፈተ በስተቀር ጠረኑ እንደማይበላሽ እና እንደማይበላ ሁሉ፣ እሷም በኒቃቧ ምክንያት ክብሯና ውድነቷ ለትክክለኛው ባለቤቷ ብቻ ተጠብቆ ይኖራል።" እና እህቴ ኒቃብ አርጌ ማን ያገባኛል ማን ያየኛል ለትዳር አትበይ ውድ ነገር ተፈላጊ ነው ፈላጊሽ ደሞ ብዙ እና ብዙ ነው  እና ባለሽበት ቀጥ በይ አላህ ላንቺ ያለው መቼም አይቀርም ወደ ኸይር ነገር ተሽቀዳደሚ ሶላትሽን ጠብቂ ሁሌም ዱዓሽ አርጊ ። ኒቃብ ያላረጋቹ ደሞ ስንት እና ስንት ብልህ አላቹ አላህ ይጠብቃቹ እናንተም ኒቃብ ለማድረግ አስባቹ በሀሳባቹ ላይ ዝም ብሎ ኋላ ቀር የሆነ ሀሳብ ሸይጣን የሚያመጣላቹ ይሄንን ሀሳብ ተውቱና ወደ ኒቃባቹ ግቡ። የሐያእ አክሊልሽን፣ የኒቃብሽን ግርማ፣ አላህ ያክብርልሽ፣ ዓለም ሁሉ ይስማ፤ በሰው ወሬ አትዘኚ፣ በጃሂሎች ንግግር፣ አላህ ዘንድ ነው ያለው፣ ትልቁ ክብር! ኒቃብሽንና ሐያእሽን እንደ አክሊል እንጂ እንደ ሸክም አትዪው። የሰዎችን ወሬ ትተሽ በአላህ እዝነትና ምህረት ተስፋ አድርጊ፤ አላህ በዲንሽ ላይ ያጽናሽ ። ​አላህ መንገድሽን ያብራልሽ፤ በሄድሽበት ሁሉ በሐያእሽ፣ በዲንሽና በጽናትሽ የተከበርሽ ያድርግሽ ። አላህ ሆይ! ለሙስሊም እህቶቻችን በሙሉ የሐያእ (እፍረት) አክሊልን አልብሳቸው፤ በኒቃባቸው፣ በሂጃባቸውና በክብራቸው ላይ ጽናቱን ስጣቸው። ​አላህ ሆይ! ልቦቻችንን በዲንህ ላይ አጽና፤ ከዱንያ ፈተና፣ ከ ቀብር ቅጣት ከሸይጣን ወስዋስና ከሰዎች ክፉ ወሬና ትችት ጠብቀን። ​አላህ ሆይ! ወንጀሎቻችንን በሙሉ ይቅር በለን፤ ተውበታችንን ተቀበለን፤ ያለፉ ስህተቶቻችንን በኸይር ሥራዎች ቀይርልን። አላህ ሆይ! ትዳር የሌላቸውን እህትና ወንድሞቻችንን በዲናቸው ላይ የሚረዷቸውን ደጋግና ሶሊህ የትዳር አጋሮች ለግሳቸው። ​አላህ ሆይ! በቤቶቻችን ውስጥ እዝነትን፣ ፍቅርን፣ ሰላምንና በረከትን አስፍን። አስታውስ ማስታውስ አማኞችን ይጠቅማልና” ልብ ይበሉ  ​«ይህንን ፅሁፍ የማካፍላችሁ  ከእናንተ በልጬ ወይም አውቄ ሳይሆን... እንደ እህት/ወንድም የማሳወቅና የኸይር ነገር ማስታወሻ ያህል ነው! አላህ ሁላችንንም ባነበብነው የምንጠቀም ያድርገን።» السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ጀማው እኔ ሰው online እንደሆክ እሚያውቁ chanel ላይ ስፖስት ነው ምን ላድርግ 🤔

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የጁምዓ ኹጥባ ባጭሩ የአላህ ባሮች ሆይ አላህ ያዘዘንን በመታዘዝ የከለከለንን በመከልከል ሁሌም በሁሉም ጉዳይ ላይ በሁሉም ሁኔታ ላይ አላህን ሱብሓነሁ ወተዓላ ተገቢውን ፍራቻ እንፍራው። ለአኬራችን ስንቅ እንያዝ ከስንቆች ሁሉ በላጭ እና ተመራጭ ስንቅ አላህን መፍራት ነው እና ። ​አንድ ሰው አላህን ሊፈራ የሚችለው ቀልቡ (ልቡ) ጤናማ ሲሆን ብቻ ነው። የቀልብ መደርቅና መበላሸት በሰው ልጅ ሕይወት ላይ ትልቅ አደጋ፣ ጉዳትና መጥፎ አጋጣሚ ያመጣል። ስለዚህ የቀልብ መደርቅ መንስኤዎችን አውቀን ልንጠነቀቅ ይገባል። ​የቀልብ መደርቅ ዋናው መንስኤ ልብ በዱንያ ፍቅር መያዙ፣ ለዱንያ ብቻ መኖርና መሞት፣ እንዲሁም አኼራን መርሳትና ቸል ማለት ነው። የዱንያ ባሪያ የሆነ ሰው ኢማኑ እየቀነሰ ይሄዳል፤ መልካም ሥራዎችንና ኢባዳዎችን መስራት ይከብደዋል፤ ይሰለቸዋል። ደስታውና እርካታው በዱንያ ጥቅም (በገንዘብና በቁሳቁስ) ላይ ብቻ የተመሰረተ ይሆናል፤ ዱንያ ሲያጣ ደግሞ ተስፋ ይቆርጣል አንገቱ ላይ ገመድ ያስጠነጥላል። ​አላህ በቁርአኑ፦ «ሸይጧን ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነው፤ እናንተም ጠላት አድርጋችሁ ያዙት» ብሏል። ሰው በዱንያ ፍቅር ሲሰጥም ወደ ታች ቁልቁል ይወርዳል፤ ከኢማን መንገድ ወጥቶ በሸይጧን እጅ ይወድቃል። ቀደምት ሰለፎች እንዳሉት ​እያንዳንዱ ሰው ኣራት ዓይኖች አሉት፦ ሁለት  የግንባር ዓይን  እና ሁለት ደሞ የልብ ዓይን ነው ። ሁለት የግንባር አይን (ዱንያን የሚያይበት) ሁለት የልብ አይን ደሞ (አኼራንና አሻግሮ የሚያይበት ነው ) አላህ የወደደውና መልካም የሻለትን ባሪያ የልብ ዓይኑን ይከፍትለታል። ትክክለኛው ዕውርነት የግንባር ዓይን መደፈን ሳይሆን የልብ ዓይን መታወርና መደፈን እንደሆነ አላህ በቁርአን ገልጿል። ​አላህ በቁርአኑ፦ «ቁርአንን አያስተንትኑም በማለቱ ልቦቻቸው ላይ ቁልፎች አሉባቸውን?» ይላል። ቁርአን የመዳኛና የቅን መንገድ መሪ ሆኖ ሳለ፣ ቁርአንን አለማንበብና አለማስተንተን ልብ እንዲደርቅ ያደርጋል። ኸጢቡ: ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ አደም  ሓፊዘሁላህ ቦታው አዲስ አበባ ፉሪ በድር መስጂድ

اللهم صل وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين وسلم تسليما كثيرا إلى يوم الدين.
اللهم صل وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين وسلم تسليما كثيرا إلى يوم الدين.

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته بسم الله الرحمن الرحيم በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡ ምክር ለውድ ወንድሞቼ በቅድምያ እራሴንም እናንተንም አላሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ተገቢውን ፍራቻ እንፍራው ለአኬራችን ስንቅ እንያዝ ከስንቆች ሁሉ በላጭ እና አዋጭ ስንቅ አላህን መፍራት ነው እና አላህን እንፍራው እላለሁ ። የመጣሁበት ርእስ አንዳንድ ወንድሞች በማይሆን ነገር ወድቀው ስለተመለከትኩ ነው የወደቁበት ነገርም በ telegram group ላይ አንዲት አህት በውስጥ መጥተው አንተዋወቅ ብለው ጀምረው እምቢ ይቅርብኝ መተዋወቁ ስትላቸው ስሜታቸው አሸንፍቸው   የማይሆን አፀያፊ የ p*o*r*n*o Sticker ይልካሉ  ወንድሞች አላህን ፍሩ ወላሂ ነገ አላህ ፊት ትጠየቃለህ ባየሀው ነገር በሰራሀው ነገር post ባረከው ነገር ነገ አላህ ፊት አንደምትጠየቅ አትርሳ አንተ ለስዋ በላክላት sticker እሱዋም ስሜትዋ አሸንፍዋት ከተጠቀመቺው ወንጀሉ ወዳንተም እንደሆነ አትርሳ ። ​👉 ለመሆኑ ይህ ነገር በገዛ እህትህ፣ በእናትህ ወይም በልጅህ ላይ እንዲደረግ ትፈልጋለህ? አትፈልግም ስለዚህ ባንተ የሆኑ ሰዎች እንዲሆን የማትፈልገው ነገር ባንተ በሚርቁ  ሰዎችም  ላይ አታርግ ። አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል 📖፦ أَفَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَٰهَهُ هَوَاهُ وَأَضَلَّهُ اللَّهُ عَلَىٰ عِلْمٍ وَخَتَمَ عَلَىٰ سَمْعِهِ وَقَلْبِهِ وَجَعَلَ عَلَىٰ بَصَرِهِ غِشَاوَةً فَمَن يَهْدِيهِ مِن بَعْدِ اللَّهِ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን፣ አላህም ከዕውቀት ጋር ያጠመመውን፣ በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን፣ በዓይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው አየህን! ታዲያ ከአላህ በኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሠጹምን? ወንጀልን አትናቅ ወንጀልን አትናቁ፤ ምክንያቱም ትናንሽ ወንጀሎች ተሰብስበው ሰውን የሚያጠፉ ትላልቅ ተራራዎችን ይፈጥራሉ።" ​«اتِّبَاعُ الْهَوَى يُعْمِي الْعَقْلَ، وَيَحْجُبُ الْقَلْبَ عَنِ الْحَقِّ، وَمَنْ كَانَ عَبْدًا لِهَوَاهُ لَا يَسْتَطِيعُ أَنْ يَرَى نُورَ الْحَقِّ.» ስሜትን መከተል አእምሮን ያውራል፤ ልብንም ከእውነት ይጋርዳል። የስሜቱ አገልጋይ የሆነ ሰው የእውነትን ብርሃን ማየት አይችልም።" (ስለ ስሜት መርዝነት ገጣሚው እንዲህ ይላል) ​«وَكَمْ مِنْ لَذَّةٍ كَانَتْ سُمُومًا ... تُورِثُ بَعْدَهَا حُزْنًا طَوِيلًا» ​"ስንትና ስንት ጊዜ ጥቂት ደስታ መርዝ ሆና አገኘናት... ከእሷ በኋላ ረጅም ሀዘንንና ጸጸትን የምታወርስ።" ​«وَخَالِفِ النَّفْسَ وَالشَّيْطَانَ وَاعْصِهِمَا ... وَإِنْ هُمَا مَحَّضَاكَ النُّصْحَ فَاتَّهِمِ» ​ "ነፍስህንና ሸይጣንን ተቃወማቸው፣ እምቢም በላቸው፤ ጥራዝ ነጠቅ ምክር እንኳ የሰጡህ ቢመስልህ ጠርጥራቸው።" ልብ በል ወንድሜ! ☀️ አላህ መላኢኮችን አቅል ሰጣቸው ስሜት የላቸውም እንስሳዎችን ስሜት ሰጣቸው አቅል ከለከላቸው ..... የሰውልጆችን ግን አቅልም ስሜትም ሰጣቸው ...
አንተ ስሜትህ ካሸነፈህ ከእንስሳ  የበታች ነህ ስሜትህን ካሸነፍክ ግን ከመላእኮችም የተሻልክ ትሆናለህ !
እና ወንድሜ ከእንስሳት በታች እንዳትሆን ስሜትህን አሸንፍ ስሜትህን አይጋልብህ የስሜትህ ተጓዝ አትሁን በአእምሮህ ብልህ ሆነህ ተጓዝ ወንጀልን እንደ መርዝ ፉሩት ይሉ ነበር ቀደምት ሰለፎች እና ወንጀልን እንደ መርዝ እንፍራው እላለሁ ። ​«اللَّهُمَّ آتِ نُفُوسَنَا تَقْوَاهَا، وَزَكِّهَا أَنْتَ خَيْرُ مَنْ زَكَّاهَا، أَنْتَ وَلِيُّهَا وَمَوْلاَهَا، اللَّهُمَّ إِنَّا نَعُوذُ بِكَ مِنْ هَوَى النَّفْسِ وَمِنْ مُنْكَرَاتِ الأَخْلاَقِ. أمين يارب العالمين » ​"አላህ ሆይ! አእምሮአችንን በስሜታችን ላይ አሸናፊ አድርግልን፤ በውስጥም በውጭም ካሉ ጥፋቶችና ወንጀሎች ጠብቀን።" ​"አላህ ሆይ! ነፍሳችንን ከተንኮሏና ከስሜቷ መጥፎነት ጠብቅልን፤ አላህን የሚፈራና የሚታዘዝ ንጹሕ ልብም ስጠን።" "አላህ ሆይ! በስሜታችን ሳንሆን በዕውቀትህና በፍርሃትህ የምንመራ አድርገን፤ ከከንቱ ጥፋት አድነን።" ​"አላህ ሆይ! ከጊዜያዊ ደስታ በኋላ ከሚከተል ረጅም ጸጸትና ሀዘን ጠብቀን፤ የመልካም ባህሪና የጽናት ባለቤት አድርገን።" "አላህ ሆይ! ዓይኖቻችንን እና ልቦቻችንን ከማይበጅ ነገር ጠብቅልን፤ ስሜታችንን አሸንፈን የአንተን መወደድ የሚያስገኝ መልካም መንገድ እንድንከተል አቅሙን ስጠን።" ​"አላህ ሆይ! አእምሮአችንን ከስሜታችን በላይ ብሩህ እና አሸናፊ አድርግልን፤ በድብቅም ሆነ በግልጽ አንተን የመፍራትና የታዛዥነት ልብ ስጠን።" ውድ ወንድሞቼ! ​ይህ መልእክት ማንንም ለመንቀፍ ሳይሆን፣ ሁላችንም እራሳችንን ፈትሸን ወደ አላህ እንድንመለስ የሚጋብዝ የወንድማማችነት ጥሪ ነው። ሁላችንም በየቀኑ አላህ የሚያያትና የሚመዘግባት ነፍስ አለችን፤ ስለዚህ ያለፈውን በተውበት አልፈን፣ የቀረውን ጊዜ አላህን በመፍራትና በመታዘዝ እንድናሳልፍ አደራ እላለሁ። ወሰላሙ ዓለይኩም ወረሑመቱላሂ ወበረካቱሁ

የቡና ሱሴ ባሰብኝ
የቡና ሱሴ ባሰብኝ

Repost from Strong Islam
የቡና ሱሴ ባሰብኝ
የቡና ሱሴ ባሰብኝ