fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

(( مركز نور الإسلام للتعلم والتعليم ))Nur Al-Islam Center for Teaching and Learning

(( مركز نور الإسلام للتعلم والتعليم ))Nur Al-Islam Center for Teaching and Learning

رفتن به کانال در Telegram

التعلم والتعليم

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
223
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+830 روز
آرشیو پست ها
🌹 ለጋብቻ "እድሜና ቁንጅናን" ብቻ መስፈርት ለሚያደርጉ ወንድሞች የተላከ ወርቃማ ምክር 🌹 *(አላህ የራራላቸው ሲቀሩ እንዚህ ወንዶች ምንኛ በዙ!)* 🛑 "ሚስት አጣሁ" የሚል ምክንያት አታቅርብ! ወዳጄ ሆይ! መልካም (ሷሊህ) ሴቶችማ እንደ አሸን ፈልተው ነበር፤ ነገር ግን ያንተ መስፈርቶች ከሴቶቹ ቁጥር በላይ በዙ እንጂ! 💡 እስኪ ራስህን ፈትሽ..? አንዳንድ ወንድሞች (አላህ ይምራቸውና) "መልካም ሚስት (ሷሊሃ) ነው የምፈልገው" ብለው ይሞግታሉ። ነገር ግን ከጀርባ የሚያቀርቧቸው መስፈርቶች አላግባብ የከረሩ ናቸው፡- 👉 "እድሜዋ በጣም ለጋ ትሁን..." 👉 "አይኖቿ እንዲህ ይምሰሉ..." 👉 "ፀጉሯ ቀለሙ፣ ርዝመቱ፣ ልስላሴው..." እያሉ ይቀጥላሉ። ጉድ እኮ ነው! ወንድሜ.. አንተ እኮ በዚህ ምድር ላይ በሰው ቆዳ የተፈጠረች "ሁር አል-ኢን" (የጀነት ቆንጆ) ነው እየፈለግክ ያለኸው! 💎 ምክሬን ስማኝ! የነቢዩን (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ዱካ ተከትለህ ለምን "ሱኒያዋን" (ባለ ዲኗን) በመምረጥ አትታደልም? የአላህ መልዕክተኛ  ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም  እንዲህ ብለው መክረውሃልና፡- "ባለ ዲን የሆነችውን ምረጥ፤ እጆችህ አቧራ ይልሱ (ደስታና በረካ ያግኙ)።" 📜 ታላቁ ሊቅ ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ ፈርኩስ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ፡- "በሸሪዓችን ለትዳር አጋር ምርጫ መመዘኛው 'እድሜ' አይደለም፤ መመዘኛው 'ዲን' (ሃይማኖታዊ ጥንካሬ) ነው እንጂ። ለዚህም ማስረጃው ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- *'ሴት ልጅ ለአራት ነገሮች ልትገባ (ልትዳር) ትችላለች፡ ለገንዘቧ፣ ለዘር ክብሯ፣ ለቁንጅናዋ እና ለዲኗ። አንተ ግን ባለ ዲኗን ምረጥ፤ (ይህን ካላደረግክ) እጆችህ አቧራ ይልሳሉ።'* ✨ ትክክለኛዋ ቆንጆ ማናት? በቁርኣንና በሐዲስ የተወደሰችው 'መልካም ሴት' ማለት ልንመርጣት የሚገባን አይነት ሴት ናት። አላህ እንዲህ ይላል፡- 'መልካሞቹም ሴቶች (ለባሎቻቸው) ታዛዦች፣ አላህ (ሚስጥርን) እንደጠበቀ በሩቅ (ነገር) ጠባቂዎች ናቸው።' (አን-ኒሳእ፡ 34) እንዲሁም ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- *'ሴት ልጅ አምስት (ወቅት ሰላቷን) ከሰገደች፣ ወሯን (ረመዳንን) ከጾመች፣ ብልቷን ከዝሙት ከጠበቀች እና ባሏን ከታዘዘች፤ ከፈለግሽው የጀነት በር ግቢ ትባላለች።'* 💖 እድሜ መግፋት ለትዳር እንቅፋት አይሆንም! የአንዲት ሴት እድሜ መግፋት ከእርሷ ጋር ትዳር ላለመመስረት ምክንያት ሊሆን አይገባም። ለዚህም ነቢዩ (ሶ.ሰ) እናታችንን ኸዲጃን (ረ.ዐ) ማግባታቸው የቀጠለ ላንተ በቂ እና ህያው ማስረጃ ነው። *   ♥ እናታችን ኸዲጃ በእድሜ ከነቢዩ በዓመታት ትበልጣቸው ነበር። *   ♥ ነገር ግን ከሰዎች ሁሉ ለሳቸው በጣም ተወዳጅ ሚስት ነበረች። *   ♥ ከሌሎች ሚስቶቻቸው በተለየ መልኩ ልጆችን ያፈሩት ከእርሷ ነው። *   ♥ የሐሰን እና የሁሴን (ረ.ዐ) የዘር ሐረግ የተገኘው ከእርሷ ነው። ስለሆነም "እድሜ መግፋት"፤ አንዲት ሴት በዲን እንድትተጋገዝህ፣ እንዲሁም አላህ በቁርኣኑ የጠቀሰውን የመረጋጋት (ሰኪና)፣ የፍቅር (መወደህ) እና የእዝነት (ራህማ) ጸጋን በትዳርህ ውስጥ እንዳታገኝ እንቅፋት አይሆንም። 📖 አላህ እንዲህ ይላልና፡- *"ከነፍሶቻችሁ ለእናንተ ሚስቶችን ወደነሱ ትረጋጉ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አሉ።"* (አር-ሩም፡ 21) 📚 [ፈታዋ አል-ኡስራህ ቁጥር (296)] ፀሀፊው ሌላ ነው። https://t.me/merkeznurilislam

💍  የትዳር ፍሬዎች! 💍 የኔ የሚሉትን ደጋፊና ተቆርቋሪ ታማኝ ወዳጅ ከጎን ያገኙበታል። እሱ ለሷ አሷም ለሱ ከማንም በላይ ጓጊና አዛኝ ይሆናሉና። « وَمِنْ آَيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُمْ مِنْ أَنْفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِتَسْكُنُوا إِلَيْهَاوَجَعَلَ بَيْنَكُمْ مَوَدَّةً وَرَحْمَةً إِنَّ فِي ذَلِكَ لَآَيَاتٍ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ» « ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ ፤ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። በዚህም ውስጥ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ተዓምራቶች ኣልሉ። » « هُوَ الَّذِي خَلَقَكُمْ مِنْ نَفْسٍ وَاحِدَةٍ وَجَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا لِيَسْكُنَ إِلَيْهَا » « እርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከኣደም) የፈጠራችሁ ከእርሷም መቀናጆዋን ወደርሷ ይረካ ዘንድ ያደረገ ነው » የህብረተሰቡም ክብርና ዝርያ ይፀዳበታል። የአላህ መልእክተኛ  ﷺ እንዳስጠነቀቁን « إذا جاءكم من ترضون دينه وخلقه فأنكحوه إلا تفعلوا تكن فتنة في الأرض وفساد كبير …… » «ዲኑንና ስነምግባሩን የምትወዱለት ሰው ለጋብቻ ፍለጋ ሲመጣችሁ አጋቡት። ይህ ካልሆነ ግን በምድር ላይ ከባድ የሆነ ፈተናንና ብልሽትን ታሰፍናላችሁ » قال إِمَامُ الحَرَمَيْنِ أَبِي المَعَالِي عَبْدُ المَلِكِ الجَوَيْنِيِّ -رَحِمَهُ الله ( والنكاح من أسباب زوال الجنون ، كما أن العزبة من أسباب الجنون ) [ نهاية المطلب 12/ 43] "ላጤነት (ትዳር አለመመስረት) የእብደት መንስዔ እንደሆነው ሁሉ ማግባት ደግሞ እብደት ከሚወገድባቸው ሰበቦች አንዱ ነው።" https://t.me/merkeznurilislam

‏[الجاهل لا يعرف العالم] قال شيخ الإسلام ابن تيمية -رحمه الله-: «العالِمُ يَعْرِفُ الجاهلَ؛ لأنه كان جاهلاً، والجاهلُ لا يَعْرِفُ العالِمَ؛ لأنه ما كان عالماً». አዋቂ (ዓሊም) መሃይምን ያውቀዋል፤ እርሱ ቀድሞ መሃይም ነበርና። መሃይም ግን አዋቂን(ዓሊምን) አያውቀውም፤ ምክናየቱም እርሱ አዋቂ (ዓሊም)ሆኖ አያውቅምና።" [جواب الاعتراضات المصرية على الفتيا الحموية (ص 172)] ويُروى هذا القول عن عبد الله بن المعتز كما عند الخطيب في الفقيه والمتفقه. https://t.me/merkeznurilislam

قَالَ شَيْخُ الْإِسْلَامِ ابْنُ تَيْمِيَّةَ رَحِمهُ الله : ”ٱلتَّوْحِـــيدُ ٱلتَّوْحِــيدُ يَا إِخْــوَةٌ وَٱللَّهِ لَيْسَ لَنَا عِــزٌ وَلَا رِفْــعَةٌ وَلَا شَـأْنٌ وَلَا صَـلَاحٌ وَلَا فَــلَاحٌ وَلَا نَـجَاحٌ وَلَا نَصْـرٌ وَلَا تَمْكِـينٌ فِي ٱلدُّنْـيَا وَلَا فِي ٱلآَخِـرَةِ إِلَّا بِهذَا ٱلتَّوْحِــيدُ ؛ وَٱللَّهِ لَوْ تَنَفَّـخَتِ الجِـبَاهُ مِنْ كَـثْرَةِ السُّجُـودِ وَدُقَّـتِ العِـظَامُ مِنْ كَـثْرَةِ الصِّـيَامِ وَالقِـيَامِ فَالجَـــنَّةُ حَـــرَامٌ إِلَّا بِهـذَا ٱلتَّوحِـــيدُ“ 📓مجموع فتاوى ابن تيمية (٢٣٥/٢٤). https://t.me/merkeznurilislam

▪️ يقول الله تعالى: {وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِمَّنْ دَعَا إِلَى اللَّهِ} ويقول النبي ﷺ: (بَلِّغُوا عنِّي ولو آية) رواه البخا
▪️ يقول الله تعالى: {وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِمَّنْ دَعَا إِلَى اللَّهِ} ويقول النبي ﷺ: (بَلِّغُوا عنِّي ولو آية) رواه البخاري 📌 صفحة بلغ ولو آية.. على مركز نور الإسلام إن شاء الله تعالى https://t.me/merkeznurilislam