✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
رفتن به کانال در Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
195
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-730 روز
آرشیو پست ها
በሃገራችን ሲቆሙ፣ ሲቀመጡ፣ የሆነ ነገር ሲገጥማቸው "እናቴ ድረሽ" የሚሉ ብዙ ናቸው። ይሄ ነገር እንዴት ነው? በሰዑዲያ ታላላቅ ዑለማዎች በጋራ ፈትዋ የሚሰጡበት ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ እንዲህ ይላል:—
"አንዳንዱ ሰው ሲቆም፣ ሲቀመጥ "እናቴ!" ማለቱ አይፈቀድም። ምክንያቱም የሩቅን ወይም የሞተን አካል በሆነ ጉዳይ ላይ እንዲረዳ መጣራት ነውና። ይሄ ደግሞ የሺርክ እምነት ነው። ስለሆነም ተውሒድን ለመጠበቅ እንዲሁም ከሺርክና ከመንገዶቹ ለመራቅ ሲባል ይህንን አነጋገር መተው ግድ ይላል።"
[ፈታዋ አለ፞ጅነቲ አዳ፞ኢማህ: 26/362]
ፈትዋውን የሰጡት ዓሊሞች:—
1/ በክር አቡ ዘይድ፣
2/ ሷሊሕ አልፈውዛን፣
3/ ዐብዱላህ አልጉደያ፞ን እና
4/ ዐብዱልዐዚዝ ኣሊ ሸ፞ይኽ
IbnuMunewor
ሀሰነል በስሪ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦
"በሄድክበት ቦታ የአላህን ትእዛዝ ከፍ አድርግ አንተንም በሄድክበት ቦታ አላህ ከፍ ያደርገሀል"
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል: –
أيعجز أحدكم أن يقرأ في ليلة ثلث القرآن؟
"አንዳችሁ በአንድ ሌሊት የቁርኣንን ሲሶ መቅራት ያቅተዋልን?"
"እንዴት የቁርኣንን ሲሶ ይቀራል?" ሲሏቸውም
قل هو الله أحد تعدل ثلث القرآن
"ቁል ሁወልላሁ አሐድ የቁርኣንን ሲሶ ትስተካከላለች!!"
[ሙስሊም]
አልኢማሙ አሽሻፊዒ አላህ ይዘንላቸውና፦
"አላህ ልቡን እንዲከፍትለትና እውቀት አንዲሰጠው የፈለገ ሰው፤
1· ለብቻው ተነጥሎ ጌታውን ይማጸን (ኸልዋ)፣
2· ምግቡን ይቀንስ፣
3· አላአዋቂ ሞኞችን ከመቀላቀል ይራቅ፣
4· አንዳንድ ፍትሃዊነትና አደብ የጎደላቸው ተማሪዎች ጋር መሆንን ይተው" ይላሉ።
[ቡስታን አልዓሪፊን (1/53)]
ይበለኝ
.
‹ይበለኝ ተወኝ› ይለኝ ነበር አንድ ወዳጄ በራሱ ጥፋት አንዳች ጥቃት የደረሰበት እንደሆነ፡፡
.
ትልቁ ጥፋታችን አጥፍተናል ለማለት ወኔ ማጣታችን፡፡ ካፈርኩ አይመልሰኝ ብለን መሸፈታችን፡፡
ጥሩ ሰው በሆንክ ጊዜና ካጠፋህ ጥፋትህን ተንበርክከህ መቀበል እንጂ ገላግሉኝ ብለህ ወገን አትጠራም፡፡
የሚተናነስ ሰው ደስ አይልም ወዳጆቼ! ….
አዎን ይበለኝ ተወኝ
~ ያለ ቦታዬ ተገኝቼ ከታማሁ፣
~ ሳልጠራ ከሆነ ቦታ ሄጄ ከተሰደብኩ፣
~ በማላውቀው ጉዳይ ተናግሬ ከተተረብኩ፣
~ ተቅዋ ያለውን ሰው ተከራክሬ ከተወቀስኩ፣
~ መመለስ የነበረብኝን የሰው ገንዘብ አዘግይቼ ስሜ ከጠፋ፣
~ ልኬን ሳላውቅ ቀደም ቀደም ብዬ ከተብጠለጠልኩ፣
~ ከኔ የሚጠበቅብኝን ትቼ ከኔ የማይጠበቅን ነገር ካደረግኩ፣
~ ቃል ሠጥቼ ቃሌን አጥፌ ቃል አባይ ነው ከተባልኩ፣
~ ሰዎች ካሰቡኝ ውጭ ሆኜ እሱ እኮ ንዲህ እንዲህ ነው ከተባልኩ ….
እኔ ነኝና ራሴን በራሴ ያዋረድኩት ይበሉኝ ተዋቸው፡፡ የእጄን ነውና በእጄ ያገኘሁት ይውጣላቸው አትገላግሉኝ፡፡
ከወንድም አቡ ሱፍያን
እህቶቻችንን ለማነው የምንተዋቸው?
~~
"ባለ ዲኗን ምረጥ" የተባለው እንዲተገበር እንጂ ወሬ ለማሳመር አይደለም። ነፍስያህን እያስቀደምክ በሰንካላ ምክንያቶች ለመሸፋፈን አትሞከር። ባለ ዲኗ እህትህን ለመጥፎ ምርጫ እየገፋህ፣ አልባሌ ቦታ ላይ ስትወድቅ ጠብቀህ ጭንቅላትህን ብትነቀንቅ ምን ትርጉም አለው?!
ወንድሜ ነብያዊው ምክር ዋጋ ይሰጠው። "ባለ ዲኗን ምረጥ።" ትርጉሙና ዋጋው ብዙ ነውና። ይህንን ስታደርግ ለራስህም፣ ለልጆችህም፣ ለምታገባት እህትህም፣ ለማህበረሰብህም ትልቅ ውለታ እየዋልክ እንደሆነ እወቅ። ጌታዬ ኢስላምን ከማውራት አልፈን የምንኖረው አድርገን።
=
IbnuMunewor
ጥቆማ!
~
የኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ የግል አካውንት ቢሰረዝም፣ የእውቀት ምንጩ አልደረቀም!-አልሐምዱ ሊላህ- የኡስታዝን ጠቃሚ የደርስ እና የዳዕዋ ፕሮግራሞች ለመከታተል ብቸኛውና ይፋዊው የቴሌግራም ቻናል መርከዝ ኢማሙ አህመድ ነው።
➥ ወቅታዊ የሆኑ ዳዕዋዎች
➥ ተከታታይ ደርሶች
➥ ኢማንን የሚያድሱ ምክሮች
አሁኑኑ ተቀላቀሉ፤ ለሌሎችም አጋሩ!
t.me/MerkezulimamiAhmed
t.me/MerkezulimamiAhmed
ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦
"ኢኽላስ ያለው(ስራውን ለአላህ ብቻ ብሎ የሚሰራ )ሰው ምሳሌ አሸዋ ላይ እንደሚራመድ ሰው ነው፣ሲራመድ የኮቴው ድምጽ አይሰማም ካለፈ በኋላ ግን የእግሩ ምልክቶች ይታያሉ"
جامع العلوم والحكم.
ታላላቆቻችን
~~~
① በ1420 ሂጅሪያ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ሞቱ።
② በ1420 ሂጅሪያ ሸይኽ አልባኒ ሞቱ።
③ በ1421 ሂጅሪያ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ሞቱ።
④ በ1422 ሂጅሪያ ሸይኽ ሙቅቢል ሞቱ።
ሁሉንም አላ፞ህ ይማራቸው። ፊርደውስንም ያድላቸው።
*
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ብንሞት ምን የማይቋረጥ መልካም ስራ አለን?
~
ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ:–
"የሰው ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል። ከሶስት ሲቀር።
① ቀጣይነት ያለው ሶደቃ፣
② ወይም ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት፣
③ ወይ ደግሞ ዱዓ የሚያደርግለት ጥሩ ልጅ።" [ሙስሊም]
የቱ ጋር አለህ? የቱ ጋር አለሽ?
① ከቻልን ህዝብ የሚጠቅም ሶደቃ ጥለን እንለፍ።
② ወይ ደግሞ ወይ አውቀን እናሳውቅ። ወይ የዑለማዎችን እውቀት እናስራጭ።
③ ልጆቻችንን ደግሞ በጥሩ ሁኔታ ኮትኩተን እናሳድግ። ከሁሉም አለመኖር ግን አሳዛኝ ብክነት ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
~ዛሬ ላይ …የዘመን ባቡር እንደ ጉድ ይከንፋል፣ቀኑ በብርሃን ፍጥነት የሚምዘገዘግ ይመስላል፤ በመሸ በነጋ ልክ የሆነ ቁጥር በዕድሜያችን ላይ ይጨምራል፤ ዕድሜያችን ይህን ያህል ብለን ለመናገር ፈራን እኮ ወዳጆቼ፡፡
ወዳጆቼ!ዱንያን የኖንርባት ሳይመስለን አሯሩጣ እዚህ አደረሰችን፡፡ የሄድንበትን መንገድ መለስ ብለን ስናስተዉለው የተረፈን ነገር ቢኖር የተሸበሸበ ፊት፣ የነጣ ፀጉር፣ የገረጣ ቆዳ፣ የደከመ ሰዉነት ነው …፡፡ በመጨረሻም አንድ ቀን ምንም ብናደርግ ልንከላከለው በማንችለው ሞት ፊት እንቆማለን፡፡
ወዳጄ…አንተ በዚህች ምድር ላይ ሕይወት እስካለህ ድረስ የዱንያ ላይ መብራት መሆንህን እወቅ፡፡ ዕድሜህ እንደ ሻማ ነው፣ ሰዓት ባለፈ ቁጥር ይቀልጣል፡፡ ጨለማን ለማብራት፣ መሃይምነትን ለመግፈፍ፣ መልካም ቃል ለማስተላለፍ፣ የከፋዉን ለማጽናናት፣ መሰናክልን ለማስወገድ ተናገር፣ ቅለጥ፣ፃፍ … አደራ፡፡ ባትችል እንኳ መልካም የሚፅፉትንና የሚናገሩትን አግዝ፡፡
ከአቡ ሱፍያን
በዲንህ ላይ ለሚያገኝህ ፈተና ላንተ የሚፈራልህ የቱ ነው? ቅጥ ያጣ የሃብት ማግበስበስ ወይስ በዲንህ ላይ የሚያፀናህ ድህነት?
ከአምሩ ቢን ዐውፍ አልሙዘኒ (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) ተይዞ፡ ነብዩ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
﴿فواللَّهِ ما الفَقرَ أخشى عليكُم، ولَكِنِّي أخشى عليكُم أن تُبسَطَ الدُّنيا عليكُم، كما بُسِطَت على مَن كانَ قبلَكُم، فتَنافسوها كما تَنافسوها، فتُهْلِكَكم كما أَهْلَكَتهُم﴾
“በአላህ እምላለሁ! በናንተ ላይ ድህነትን አልፈራላችሁም። ነገር ግን የምፍራላችሁ ዱኒያ ከናንተ በፊት ለነበሩት ሰዎች ተዘርግታ እንደነበረችው ለናንተም ተዘርግታ ከዚያም እነርሱ እንደተፎካከሩት እናንተም ተፎካክራችሁ እነሱን እንዳጠፋቻቸው እናንተንም እንዳታጠፋችሁ ነው።”
ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2961
የሱፍዮችና የአህባሾች አራት ዋና ዋና መገለጫዎች
*በሚያውቁት አይሰሩም
*የማያውቁትን ይሰራሉ
*የማያውቁትን አይማሩም
*ሰዎችንም ከኢልም ያግዳሉ
قال محمد بن الفضل البلخي رحمه الله: ذهاب الإسلام من أربعة : لا يعملون بما يعلمون ، ويعملون بما لا يعلمون ، ولا يتعلمون ما لا يعلمون ، ويمنعون الناس من التعلم .
قال الإمام الشاطبي معلقا إليه : هذا ما قال ، وهو وصف صوفيتنا اليوم ، عياذا بالله .
الاعتصام للشاطبي ٧٣
