fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

SU|ኤስዩ

SU|ኤስዩ

رفتن به کانال در Telegram

የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር [Scripture Union Ethiopia] #ኤስ.ዩ፣ ከ1957 ጀምሮ የኃይስኩል ተማሪዎችን እያገለገለ ይገኛል። #ራዕያችን "ኢየሱስን እየተከተሉ፤ በቃሉ እየታነፁ፤ ማኅበረሰባቸውን የሚያገለግሉ ተማሪዎችን ማየት" ነው በዚህ ቻናል:— በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት ነክ መረጃዎች ይተላለፍበታል።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
672
مشترکین
+224 ساعت
+47 روز
+230 روز
آرشیو پست ها
photo content
+9

photo content
+9

photo content
+1

photo content
+9

photo content
+9

#ከሚሴ_ኃይስኩል_ክርስቲያን_ተማሪዎች_ህብረት ----- ----- ------- ------ ቅዳሜ፣ ታህሳስ 18 ፥ በሰሜን ምስራቅ ክልል፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አካባቢያዊ ቢሮ፣ #ለከሚሴ ክርስቲያን ተማ
+8
#ከሚሴ_ኃይስኩል_ክርስቲያን_ተማሪዎች_ህብረት ----- ----- ------- ------ ቅዳሜ፣ ታህሳስ 18 ፥ በሰሜን ምስራቅ ክልል፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አካባቢያዊ ቢሮ፣  #ለከሚሴ  ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት መሪዎችና አባላት ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው፣ #የእግዚአብሔር_ልብ_ለኃይስኩል (God's Vision for Highschool )፣ #የተማሪ_ህብረትና_የቤተሰብ_ቡድን (School Fellowship and Family Group ) ፣ #የትምህርት_ልህቀትና_የትምህርት ምርጫ (Acedamic Excellence and Choice) እና #እውነተኛ_አምልኮና_ፀሎት (True Worship and Prayer ) ርዕሶች ላይ የተሰጠ ሲሆን፤ በተጨማሪም የተማሪ ህብረትን Reshape እና Repurpose በማደረግ ዙሪያ ምክክርና ፀሎት ተደርጓል። በፕሮግራሙ ላይ የተማሪ ህብረት አገልግሎት ላይ አንድም ጊዜ ተሣትፈው የማያውቁ ተማሪዎች መገኘት የቻሉ ሲሆን፣ በመገኘታቸው እንደተጠቀሙና በቀጣይ በህብረት ታቅፈው ለመቀጠል እንደተበረታቱ ተናገረዋል። ክብር ለጌታ ይሁን እግዚአብሔር አካባቢውን ሰላም እንዲያደርግ፣ አዳዲስ የተመሰረቱ ህብረቶች እንዲጸኑና ፍሬያማ እንዲሆኑ እንፀልይላቸው ========== #ኤስዩ #ሰሜን_ምስራቅ_ክልል #ከሚሴ #ኦሮሞ_ብሔረሰብ_ዞን_አካባቢያዊ_ቢሮ #ኢየሱስን_እየተከተሉ_በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ_ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ_ተማሪዎች_ማየት

#ምስራቅ_ሐረርጌ_ባቢሌ #ሕብረት_ተደራጅቷል ---- ----- ----- ----- #በምስራቅ_ኢትዮጵያ የቃለ እግዚአብሔር  አንባቢዎች ማህበር (ኤስዩ) ከሚያስተባብራቸው ከተሞች መካከል በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የምትገኘው #የባቢሌ ከተማ አንዷ ነች:: በእግዚአብሔር እርዳታ እንዲሁም በከተማው አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ትብብር የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ፌሎሽፕ ድጋሚ የመመስረቻ እና የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተከናውኗል። በከተማው ከዓስር አመት በፊት የኃይስኩል ተማሪዎች ህብረት አገልግሎት የነበረ ቢሆንም በተፈጠሩ አንዳንድ ችግሮች ምክንያት ተቋርጦ ቆይቷል። በዝግጅቱ በባቢሌ ከተማ የሚገኙ የኃይስኩል ፌሎሽፕ ተማሪዎች እንዲሁም ከአጎራባች ከተሞች፣ #ከሐሮማያ እና #አደሌ ከተማ ጥሪ የተደረገላቸው የተማሪ ህብረት መሪዎች ተገኝተዋል። በመርሐ ግብሩ፣ #የእግዚአብሔር_ልብ_ለኃይስኩል ፣ #የቤተሰብ_ቡድን_ስልት እንዲሁም #ዓለምአቀፍ_የእግዚአብሔር_ተልዕኮ የሚሉ ስልጠናዎች በቁጥር 50 ለሚሆኑ ተማሪዎች መስጠት ተችሏል:: ከስልጠናው ጎን ለጎን በከተማው ከሚገኙ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር ሰፊ የምክክር እና ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ተሰርቷል። ለቤተክርስቲያን መሪዎች ፣ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሤት፣ እና የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል። በዝግጅቱ ተማሪዎች ደስተኞች እንደሆኑ ገልፀዋል። የተሰጡት ስልጠናዎችም ለግል ህይወት እና ለአገልግሎት የሚኖራቸውን ቁልፍ ጠቀሜታ አንስተዋል። የቤተክርስቲያን መሪዎች በበኩላቸው፣ በኤስ.ዩ የተማሪዎች አገልግሎት ደስተኞች እንደሆኑ እና አብረው በትብብር ለመስራት ያላቸውን ሙሉ ፈቃደኝነት ገልፀዋል። አያይዘው፣ ለተማሪዎች ሕብረት የሚደረገው ድጋፍና ክትትል በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። የባቢሌ ከተማ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ548 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። በምስራቅ ክልል ለሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶች እንድትፀልዩ እንለምናለን! ከቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) #ተልዕኮ መካከል #ተማሪዎች፣ #ለፀሎት_እና_ለእግዚአብሔር_ቃል_ጥናት የሚሰባሰቡበትን #ሕብረት_ማደራጀት ቀዳሚው ነው። በምስራቅ የኤስዩ ክልላዊ ቢሮ የተማሪዎችን አገልግሎት በትጋት እያከናወኑ ያሉትን ሁሉ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቸው። ======= #ኤስ_ዩ #ምስራቅ_ክልል #ባቢሌ #ሐሮማያ #አደሌ #ኢየሱስን_እየተከተሉ #በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ #ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎች_ማየት

photo content
+8

photo content
+8

#ጂንካ: #የኃይስኩል_ፌሎሽፕ_መሪዎችን_የማስታጠቅ_መርሐ_ግብር ----- ------ ------ ----- #ደቡብ_ኤስዩ_ክልላዊ_ቢሮ፣ በአሪ ዞን፣ በጂንካ ከተማ የኤስ.ዩ አካባቢያዊ ቢሮ ለኃይስኩል የ
+7
#ጂንካ: #የኃይስኩል_ፌሎሽፕ_መሪዎችን_የማስታጠቅ_መርሐ_ግብር ----- ------ ------ ----- #ደቡብ_ኤስዩ_ክልላዊ_ቢሮ፣ በአሪ ዞን፣ በጂንካ ከተማ የኤስ.ዩ አካባቢያዊ ቢሮ ለኃይስኩል የተማሪዎች ሕብረት መሪዎች ስልጠና ተካሂዷል፡፡ የስልጠናው የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረትን ማጠናከር እንዲሁም ስለ ቤተሰብ ቡድን ( Family Group) የአገልግሎት ስልት ግንዛቤ መፈጠርን ዐላማ አድርጎ የተዘጋጀ ነው። በሕይወት ብርሃን አጥቢያ ቤ/ክ በተሰናዳው ፕሮግራም፣ #በጂንካ የሚገኙ የኃይስኩል ፌሎሽፕ መሪዎች፣ የአገልግሎት ዘርፍ አስተባባሪዎች ፣ እንዲሁም ተተኪ መሪዎች ተሣታፊ ሆነዋል። በዕለቱ #የዘፍጥረት_መጽሐፍ ላይ ያተኮረ መልዕክት ቀርቧል። የቤተሰብ ቡድን አሰራር ( #Family_Group_Strategy) እና ወዳጃዊ ወንጌልን የመመስከር ስልት ( $PCS: Pray-Care-Share) በዞኑ እያገለገሉ በሚገኙ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) ስታፎች ተሰጥቷል። በተጨማሪም፣ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ) አገልግሎትና አሰራርን በተመለከተ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል። ከስልጠና ባሻገር የእግዚአብሔር መገኘት የነበረበት #የፀሎት_መርሐ_ግብርም ተካሂዷል። ጅንካ ከአዲስ አበባ የ615 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። በአሪ ዞን፣ ጅንካ ከተማ እያገለገሉ የሚገኙት #የኤስዩ_አሶሼት_ስታፎች አስደናቂ አገልግሎት እየሰጡ ነው። አገልግሎታቸውን በታላቅ ትጋት፤በብዙ መሰጠት እያገለግሉ ነው። እግዚአብሔር አብዝቶ ፀጋውን ያብዛላቸው። አካባቢው ከነበረበት የጤና ስጋት ድባብ ወጥቶ ነገሮች በመስተካከላቸው እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። @suethio

photo content
+9

photo content

#የኃይስኩል_ክርስቲያን_ተማሪዎች_አገልግሎት #በሰሜንምዕራብ_ኤስዩ ----- ----- ----- #በሰሜን_ምዕራብ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) ክልላዊ ቢሮ አገልግሎት ተኮር ምክክር፣ ጉብኝት እና ስልጠና እየተካሄደ ይገኛል። #ባህርዳር ፣ #አዲስዘመን ፣ #ወሮታ፣ #ጋይንት እና #ደብረማርቆስ የተከናወኑት ጉዳዮች ምንድናቸው? በ #ባህርዳር፣ ከባህርዳር ከተማ አብያተክርስቲያናት መሪዎች እና የወጣት ህብረት አገልግሎት መሪዎች  ጋር የምክክር ፕሮግራም ተካሂዷል። በነበረው የምክክር መርሀ ግብር አገልግሎትን  ውጤታማ እና ተመጋጋቢ በሆነ መልኩ ለማገልገል መከተል ስለሚኖርብን ቀጣይ አቅጣጫዎች ገንቢ ውይይት ተካሂዷል። በዝግጅቱ ተሣታፊ የነበሩት መሪዎች በከተማው እንዲሁም በክልላዊ ቢሮ እየተከናወነ ስላለው የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) አገልግሎት ገለፃ ተደርጎላቸዋል። #አዲስዘመን_እና_ወሮታ ---- ---- ---- ------ እንዲሁም በደቡብ ጎንደር ዞን ፣ አዲስ ዘመን እና ወሮታ ከተማ የሁለት ቀን የጉብኝት መርሐ ግብር ተካሂዷል። በሁለቱም ከተሞች ከኤስዩ አሶሼት ስታፎች ፣ ከተማሪዎች እና ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር የተማሪ አገልግሎትን በተመለከተ ጠቃሚ ምክክር አድርገናል። በሁለቱም ከተሞች የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ተመስርቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። #ጋይንት_እና_ደብረማርቆስ እንዲሁም በጋይንት እና በደብረ ማርቆስ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶች በአሶሼቶች አማካይነት ተቋቁሟል። ከመሪዎች ጋር የተማሪ አገልግሎትን በተመለከተ ሰፊ ውይይ ተካሂዷል። እንዲሁም የተማሪ አገልግሎት ታሪክ፣ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሤት፣ የትኩረት አቅጣጫ እና የአሰራር ስልት በተብራራ መልኩ ቀርቧል። በአሁኑ ሰዓት ተማሪዎች መደበኛ ሕብረት ማድረግ ጀምረዋል። ከቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) ተልዕኮ መካከል ቀዳሚው ፣ ተማሪዎች ለፀሎትና የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት የሚሰባሰቡበትን ሕብረቶችን ማደራጀት ነው። በአካባቢው በብዙ ዋጋ መክፈል እያገለገሉ ተማሪዎችን እየደገፉ ስላሉ አጥቢያ በተክርስቲያናት ጌታን በብዙ እናመሰግናለን። ፀጋ ይብዛላቸው። የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) ከቤተክርስቲያን ጋር ፤ለቤተክርስቲያን ፤በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰራ አጋዥ ተቋም ነው። በሰሜን ምዕራብ የኤስዩ ክልላዊ ቢሮ እየተሰጠ ስላለው ድንቅ አገልግሎት ጌታ የተመሰገነ ይሁን። #በፍኖተሰላም እና #በእንጂባራ ከተሞች እየተከናወነ ስላለው አስደናቂ የኃይስኪል ፌሎሽፕ አገልግሎት በቀጣይ በሰፊው እነናቀርባለን። እግዚአብሔር ስለሰጠን ትጉ አሶሼት ስታፎችም ምስጋናችን ብዙ ነው። #ፀሎት በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ የተዘጉ ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ እንፀልይ God at work among High School Students in The NorthWest SU Region ----- ----- ------ ------ In the Northwest Region, a ministry-oriented consultation, visit, and training program was conducted at the regional office of the Scripture Union of Ethiopia (SU). In Bahir Dar, a consultation program was held with church leaders and youth ministry leaders from across the city. During this gathering, participants engaged in constructive discussions on future directions to serve students more effectively and efficiently. The leaders were also briefed on the various ministries of the Scripture Union of Ethiopia that are being carried out both in the city and through the regional office. #Addis_Zemen_and_Worota A two-day visit program was also conducted in the South Gondar Zone, specifically in the towns of Addis Zemen and Worota. In both locations, valuable discussions were held with SU Associate Staff, students, and local church leaders, focusing on student ministry. As a result, High School Christian Student local fellowships were established in both towns. We thank God for this encouraging development. #Gayint_and_DebreMarkos In addition, High School Christian Student local fellowships have been established in Gayint and Debre Markos through the dedicated work of SU Associates. Students have begun gathering regularly to pray and worship together and to study the Word of God. We praise God for this success. One of the primary missions of Scripture Union is to establish and strengthen high school student fellowships where students can gather for prayer and the study of God’s Word. We thank the Lord for the many local churches that are sacrificially serving and supporting students. May God’s abundant grace rest upon them. Scripture Union is a parachurch ministry that works with the church, for the church, and in the church. We praise the Lord for the wonderful ministry being carried out by the SU Regional Office in the Northwest, and we are deeply grateful for the committed SU Associate staff God has entrusted to us. #Prayer_Request Let us pray for lasting peace in the region and for the reopening of closed schools. ------- #ኤስ_ዩ #ሰሜን_ምዕራብ_ክልል #ኢየሱስን_እየተከተሉ #በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ #ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎች_ማየት

photo content

photo content

photo content

photo content

======== Gorsaa fi Yaadachiisa Tiksee ——————————————— “Lafti kun gaarummaa keessaniif ni oolti.” Pastor Oliqaa ergaa kana kan dabarsan sagantaa baniinsa Daawwannaa fi Leenjii Hoggantoota Feelooshippii Mana Barumsaa Sadarkaa Lammaffaa magaalaa Nekemte, Wellega Bahaa keessatti geggeeffame irratti. Pastor Oliqaa haasaa isaanii keessatti walga’iin kun waraana kaayyoo qabu kan Waaqayyo walitti fide ta’uu ibsaniiru. Muuxannoo mataa isaa waggoota hedduu dura hoggansa High School Fellowship keessatti tajaajiluu yaadachuun yeroo isaa leenjii fi deeggarsa akkasii akka hin argamne hubateera. Dhaloonni ammaa kun mirga guddaa akka qabu cimsanii ibsuun, barattoonni carraa isaan dura jiru ogummaa fi itti gaafatamummaan akka itti fayyadaman jajjabeessaniiru. ''Dhaloota kanarraa abdii guddaan qaba,'' jedhan. “Waraanni kaayyoo qabu asitti walitti qabameera.Isin dhaloota haaraadha.Abdii hin dhabinaa. Wanti Waaqayyo har’a isiniif fidaa jiru amma guutummaatti hubatamuu dhiisuu danda’a, garuu waggoota muraasa booda bu’aa isaa ni argitu.Waaqayyo lafa kana gara gaariitti jijjiiruuf isinitti fayyadama.” Barattoonni ogummaa fi amantiin akka deeman dhaamaniiru. Pastor Oliqaa Nekemte keessatti Waldaa Kale Hiwot keessatti tajaajilaa ta’uun kan tajaajilan yoo ta’u, waajjira Mana Maree, kutaa hafuuraa keessattis tajaajilu. Tajaajiltoota Waldoota naannoo Nekemte keessatti amanamummaadhaan tajaajilaa jiran Waaqayyo baay'ee haa eebbisu.

#መጋቢያዊ_ምክርና_ማሳሰቢያ ---- --- ----- ----- ይህቺን ምድር ለመልካምነት እንድትዋጁ ይጠቀመባችኋል በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ በተካሄደው የኃይስኩል ፌሎሽፕ መሪዎች ጉብኝትና ስልጠና
+3
#መጋቢያዊ_ምክርና_ማሳሰቢያ ---- --- ----- ----- ይህቺን ምድር ለመልካምነት እንድትዋጁ ይጠቀመባችኋል በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ በተካሄደው የኃይስኩል ፌሎሽፕ መሪዎች ጉብኝትና ስልጠና መክፈቻ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ይኸንን መልዕክት ያስተላለፉት መጋቢ ኦሊቃ ናቸው። መጋቢ ኦሊቃ ዐላማ ያለው ሰራዊት በዚህ ተሰብስቧል እሳቸውም ከረጅም ዓመት በፊት በኃይስኩል ፌሎሽፕ መሪነት ተሳትፈው እንደነበረ አስታውሰው በእነሱ ጊዜ እንዲህ አይነት የስልጠና እገዛ እንዳልነበር ተናግረዋል። ይሄ ትውልድ ግን እድለኛ ነው ይኸንን እድል በአግባቡ ተጠቀሙበት ሲሉ ለተማሪዎች ምክር አስተላልፈዋል። አክለውም፣ "በዚህ ትውልድ ተስፋ አለኝ! ዐላማ ያለው ሰራዊት በዚህ ተሰብስቧል፤እናንተ አዲሱ ትውልድ ናችሁ። በፍፁም ተስፋ እንዳትቆርጡ እግዚአብሔር ዛሬ ወደ እናንተ የሚያመጣው ነገር ከጥቂት ዓመታት በኋላ ጥቅሙን ትረዱታላችሁ። እግዚአብሔር እቺን ምድር ለመልካምነት ለመለወጥ ይጠቀምባችኋል፣ " በማለት አስተዋዮች እንዲሆኑ አሳስበዋል። መጋቢ ኦሊቃ በነቀምቴ ከተማ የቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን እገልጋይ እንዲሁም በካውንስሉ የመንፈሳዊ ዘርፍ ላይ ያገለግላሉ። እግዚአብሔር በነቀምቴ ከተማ እያገለገሉ ያሉትን የአጥቤያ ቤ/ክ አገልጋዮች ይባርክ! --------------------- #ኤስ_ዩ #ምዕራብ_ክልል #ነቀምቴ #ኢየሱስን_እየተከተሉ #በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ #ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎች_ማየት

photo content