Genesis Within
رفتن به کانال در Telegram
Thoughts • Life • Everything in between — Literary Works — ◇ Genesis Z.◇ Because a person's life isn't one-dimensional 😉
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
248
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-130 روز
آرشیو پست ها
I made this funk track 3 months ago, been vibing to it alone; now I’m releasing it for you guys to enjoy. Thanks for listening!
Repost from N/a
ቆጣሪ ተገኝቷል🫠😇ዛሬ በአለምአቀፍ ደረጃ እኔን ጨምሮ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚጠቀሙበትን 1 የቴሌግራም bot ላስተዋውቃችሁ ነወ። Bot'ኡ "Birthday Countdown" ይባላል። የልደት ቀናችሁን ከሞላችሁበት በኋላ በየቀኑ ለልደታችሁ ይህን ያህል ቀን ነው የቀረው እያለ ያስታውሳችኋል። ቀኑ ሲቃረብ ደግሞ በልዩ ሁኔታ ያስታውሳችኋል። 🤩🥳 የሚቀጥለው ልደታችሁን በተለየ መንገድ ለማክበር ያሰባችሁ ካላችሁ ተጠቀሙበት። በትክክል እንድትዘጋጁበት ይረዳችኋል። እንደእኔ አይነት የልደት ቀን በአእምሯችሁ ለማስታወስ የምትቸገሩ ብትጠቀሙት አይከፋም።👌🤗 2 ወይም ከዛ በላይ የቴሌግራም Account ካላችሁ ደግሞ የሌላ ልደቱን ለማክበር ያሰባችሁትን ሰው የልደት ቀን መሙላት ትችላላችሁ። 🤫😉 Link ከታች አስቀምጥላችኋለሁ። ⭐️⭐️ @birthdaycountbot
ክፍል ፩አይኖቼን አቀናሁ፣ እግሬም ተንጠራራ እጆቼን ዘረጋሁ ለአፍታ አንገቴን ቀና ከፍ፣ ነቅ ነቅ አረኩና ፊት ለፊት ተጋጠምኩ ከጠሀይቱ ጋራ። ከቀን ክፉ ታዲያ በቀትር ጠራራ አፌን ከፈትኩና... ራሴን አከኩና... ከወዲያ ከወዲህ ዞርኩ አማተርኩና ሚያዝ የሚጨበጥ የማደርገው ባጣ ያዝኩት ተያያዝኩት ውጊያን በደፈና። #AmharicPoem #GenesisWithin @GenesisSpeaks
በጀ አትበል!
እውነት እየጠፋች በሐሰት ተጋርዳ፣
አጎንባሽ በዝቶባት ፈቃዱን የከዳ፤
ለባዕድ በትር ለከንቱ መናኛ፣
እንቢታን ልበሰው አትሁን ዝምተኛ፤
ልብህ እያወቀው ግፉን እየገፋህ፣
"በጀ" አትበል ፍጹም ቆይ እንደበረታህ።
ለጨለማ አንገትህን ደፍተህ አትገዛ፣
ነጻነት ወጋገን በውስጥህ ደብዝዛ፤
መኖር ከወደድህ በክብር ልዕልና፣
"እምቢ" ማለት ልመድ ለጽድቅ አብርና።
#AmharicPoem #GenesisWithin
@GenesisSpeaks
Started with big plans,
but somehow I’m here writing poems like I’m about to publish a ግጥም መድብል 😅
Bear with me till then :)
ጥሙ ሳይረካለት ሳይበላ እየራበው፣
ተቀብሮ ስሜቱ ሰው እንዳይታዘበው፣
ለሌላው እየኖረ ለራሱ ባይተዋር፣
ከውስጡ ተቀምጦ ልቡን ያርደዋል።
ሳቁንም ይለካል አልቅሶም አይረካ፣
በሰው ሚዛን ሆኗል ኑሮው የሚለካ፤
የውስጡን የልቡን በውሸት ሸፋፍኖ፣
ይኖራል ምስኪኑ ለሰው ‘ይሁን’ ብሎ።
ታዲያ ምን ይባላል የዚህ ደዌ ስሙ?
ሰው እንዳይቀየም ራስን መውቀሱ፤
ካላወቁት በቀር የአያያዙን ነገር
ይሉኝታ መርዝ ነው፣ ቀስ እያለ ሚገድል።
#AmharicPoem #GenesisWithin
@GenesisSpeaks
ሰው አፉ ሲከፈት፣ ምላሱ ሲሰላ
ላንቃው ተከፍቶለት፣ ጉሮሮው ሲላላ
ቃላት ተሰድረው፣ በደርዝ ተሰልፈው
ይከታተሉታል፣ ዘገም ፈጠን ብለው።
ታዲያ ተናጋሪው፣ ሐሳብ አክሎበት
ወረፍ ቢያደርገውም፣ ዘፈቀዳዊነት
ይግባባል ሰው ከሰው፣ አወይ ሲችልበት!
ዋ! ግን ምነው ቸሩን፣ ደጉን ቢያውራበት
አልታደለም መሰል፣ አንዴ ሲፈርድበት
ክፉውን ክርድዱን፣ ያንን መርዘኛውን
ያግተለትለዋል፣ ካልተገራ አንደበት።
ምነው ባይፈጠር፣ ዝምታ ወርቅ ነው!
ሰው ለከትን ቢያበጅ፣ አፉንም ቢገራው
የማታ የማታ፣ ፍሬው በረከት ነው።
#AmharicPoem #GenesisWithin
@GenesisSpeaks
ይህ ሁሉ ተባለና፣ 'ለመሆኑ በዚህ ገጽ ምን ይጠብቀናል?' የሚል ጥያቄ ቢፈጠርባችሁ፤ በተቻለ መጠን በዘርፈ ብዙ አቅጣጫዎች ዘልቀን ለመጓዝ እንሞክራለን። በሥነ-ጽሑፍ ሥራዎች፣ በሕይወት ተሞክሮዎችና ወጎች እንዲሁም እንደ ሕክምና ተማሪነቴ ከሙያው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች እናነሳሳለን። (ምናልባት አሁን ላይ ተማሪነቱ ጎልቶ ሊታይ ቢችልም፣ የኋላ የኋላ ግን ሙያው ሥር ሲሰድ ብዙ እንደምናወጋ ተስፋ አደርጋለሁ!)
ደግሞ የእናንተን ሐሳብና አስተያየት በታላቅ አክብሮት እናስተናግዳለን።😊
ለነገር ሁሉ ጅማሬ እንዳለው እሙን ነው። በዚህች አጭር ሀተታ ላይ ተስማምተን ነገሬን ልቀጥል። ፍጥረታትን ብንታዘብ፣ አስተውለንም ብናጤናቸው፤ ከውልደታቸው ዕለት ጀምሮ ምድር በቃኝ ብላ እስክታሰናብታቸው ድረስ ያለ ማቋረጥ ይለወጣሉ፤ ይለዋወጣሉም። ይወለዳሉ፣ ያድጋሉ፣ ሕይወትንም ይኖሯታል፤ በመጨረሻም ያልፋሉ። ኧረ እንዲያውም ርቀን ሳንሄድ የገዛ ማንነታችን የዚሁ እውነት ፍንትው ያለ ማሳያ አይደለምን?ይሁን እንጂ፣ ለመንደርደሪያ ይህን ያህል ካልኩ፤ ወደ 'ገደለው' ብገባ እንደ ዘመኑ ሰው ነገር የማላበዛ መሆኔን ሳይመሰክርልኝ አይቀርም። ለመሆኑ ይህ ሁሉ ዳር ዳርታ ምን ሊነግረን ፈልጎ ነው? በሕይወት ጉዟችን ከብዙዎች ጋር በብዙ መልኩ እንቆራኛለን፤ መስተጋብርም ይኖረናል። ከሌሎች ልንማር፣ ከእኛም ዘንድ ለትምህርት የሚሆን ፍሬ ነገር ሊገኝ እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው። ይህ እውን ሆኖ ሳለ፣ ነገሩን ወደ ራሴ ሳመጣው ብዙ አወጣሁ አወረድኩ፤ በዚህም 'ቻናል' (Channel) በርካታ ሐሳቦችን ሳሰፍር ቆየሁ። የኋላ ኋላ ግን፣ 'ለምን ሐሳቦቼን በልኩ አድርጌ ለሌሎች አላጋራም?' የሚል ሐሳብ ነፍሴን ክፉኛ ሲያሳስባት ከረመ😅። እንዲያውም አንዳንዶች ለአያሌ ቀናት 'ሐሳብህን እንጋራህ' እያሉ ሲጠይቁኝ እንደነበር አልክድም። ብቻ እርስዎ ይህንን ጽሑፍ በአንድም በሌላም አስበውበት ይሁን፣ አሊያም በአጋጣሚ በዚህ በኩል ጎራ ያሉት ወዳጄ፤ እዚሁ አብረውን እንዲከርሙ በአክብሮትና በትሕትና ጋብዤዎታለሁ። --- ጠሪ አክባሪዎ፣ የጽሑፉ ባለቤት
