ወደ ኢየሱስ ደረት
رفتن به کانال در Telegram
Romans 8÷1 There is therefore now no condemnation to them which are in Christ Jesus, who walk not after the flesh, but after the Spirit.
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
277
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
-530 روز
آرشیو پست ها
277
የጥዋት በረከት ልባርካችሁ
ከመጣችሁበት አመት በላይ አሁን መበርታት ይሁንላችሁ፣ያነበባችሁት የእግ/ርቃል ከሆዳችሁ እንደ ምንጭ መፍለቅ ይጀምር ፣በዚህ አመት እና ባለፉት አመታት የፀለያቹት ፀሎት ያነባችሁበት ጉዳል በብዙ ፍሬ መብቀል ይጀምር፣ክርስቶስን የሚያስታውስ የህይወት መአዛ ይክበባችሁ፣እድሜያችሁ ሲጨምር ሀይላችሁ ይጨምር፣በእግ/ርም በሰውም ዘንድ በሞገስ እደጉ፣ያሰባችሁትን ሳትፈፅሙ ክፉ አይቅደማችሁ🙌🙌🙌🙌🙌
አሜን
277
ነበር......
የስንፍና ኑሮ የትግል ጉዞ
እየለፊ በባዶ መቅበዝበዝ
ከፍ እያሉ እታች መውረድ
ብዙ እየዘሩ ፍሬ ማጣት
እየወሰኑ እንደገና መስነፍ
በቃኝ እያልን እዛው መክረም
ብዙ አቅደን ከምንም አለመሆን
የአዚምን ምኞት ማስቀደም
ሲገባን እራሳችንን መውቀስ
ላንሻሻል እራሳችንን መቅጣት
መልሰን ለእዚያው እስረኛ መሆን
ካሁን ሰአት ጀምሮ ይባልልን ነበር
277
የ እኛ ቤተሰብች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ውጤት የሰማችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።
ስለሆነው ነገር ሁሉ እግ/ር ይመስገን
እርሱ ሳያውቅ የሚሆን አንዳች ነገር የለም።
የኢየሱስ ልጆች በሁሉ ነገር አሸናፊዎች ናቸው ምክንያቱም አባታቸው ክርስቶስ ብቸኛው አሸናፊ ስለሆነ።🫡
ኢየሱስ ጌታ ነው።🫡
277
ውዱን ለውዴ✨
ሉቃ 7÷37-50
↔በዚህ ክፍል አንዲትን ሀጥያተኛ ከሰው የተገለለችን ሴት እናያለን ።ኢየሱስም በአንድ ስምኦን የሚባል ፈሪሳዊ ቤት ለማዕድ ተቀምጦ ነበር ።ይህንን ወሬ ሰምታ ኢየሱስ ወዳለበት መጣች አንድ ነገር ግን ተማምናለች ኢየሱስ የሀጥያተኞች ወዳጅ እንደሆነ የተቸገሩትን እንደሚረዳ የታመሙትን ከስጋ በሽታም ከመንፈስ በሽታም እንደሚፈውስ እምነት ነበራት።ይችህ ሴት ኢየሱስ እንደሚቀበላት አምና ውዱን ይዛ የሰውን ሁሉ ነቀፌታ፣ ትችት ፣ንቀትን አልፋ የንቀት ቃል ከአፉ እንደማይወጣ እርግጠኛ ሆና በእንባ ውድ የሆነውን የአልባስጥሮስ ሽቱ ይዛ እግሩ ስር ወደቀች።
↔ይህ ኢየሱስ ሰው የናቀውን የሚያከብር፤ አንገትን ደፍተው በህግ ገመድ ታስረው የተጨነቁትን ቀና የሚያደርግ ፤አርነት የሚያወጣ፤ ደጉ ጌታ ጉዳዩ ከሰራችሁ ሀጥያት ጋር ሳይሆን ከእርሱዋ ጋር እንደሆነ በሰዎች ፊት አረጋገጠላት ሰው በሀጥያቷ ምክንያት ይፀየፏታል ኢየሱስ ግን ያየላት እድፈቷን ሳይሆን ልጅነቷን ነው።
ወዳጄ በብዙ ሀጥያት ወድቀህ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ኢየሱስ ጉዳዩ ከሀጥያትህ ጋር ሳይሆን ካንተ ጋር ነው።ስለዚህ አትጨነቅ እርሱ ሚፈልገው አንተን ነው እንጂ ታሪክህን ደለም።ስለዚህ ወደ እርሱ ለመሄድ ከእቅፉ ለመግባት ፍቃደኛ ሁን።
ለኢየሱስ ውዱ ነገር አንተ ነህ/አንቺ ነሽ።
↔ ያቺ ሴት ኢየሱስ ጋር ስትገባ ከእረሱ ጋር የነበሩ ሐዋሪያት ፊታቸውን ሲቀያይሩባት ሌላው ደሞ ሲንኮሻኮሽ አንዱ ደሞ በውስጡ እየናቃት ሲያስብ ግድ የሚለው ጌታ ዝም አላሰኘውም ውዱን እያቀረበችልኝ ነው ይልቁንስ ከእናንተ በተሻለ እያመለከችኝ ነው አምላክነቴ ገብቷታል አትንኳት ለአምላክነቴ የሚገባኝን ውድ አልባስጥሮሱዋን እያፈሰሰች በእንባዋ እግሬን እያራሰች በፀጉሩዋ እያበሰች ነው እኔም ደስ አሰኝቶኝ አምልኮዋን እነተቀበልኩ ነኝ አለ።የርሷን ከተሰበረ ልብ የመጣውን መስዋዕት አሸተተላት አረካው። ከሰው አይን የሌለች በጌታዋ ዘንድ ግን መወደድን አገኘች።እኛም ዛሬ ውዱን ለውዳችን ማፍሰስ ይሁንልን በእውነት በእርሱ ዘንድም በሰው ዘንድም የማይረሳ አምልኮ እናቅርብለት ያሽትትልን ሽቶዋችንን።
↔ውዱ ነገራችን ለኛ ምንድ ነው፦ ወጣትነትነው፣
እድሜ፣ ጊዜ ነው፣ ቤተሰብ፣ ጉዋደኛነው፣ በቃ ለሱ ይሁን🙌
ላንተ ከተባለ
ውድ አልባስጥሮሴን ፊት ሰብረዋለው
ጥእሙን ሽቶዬን ከእንባ ቀላቅዬ አፈስልሀለው
ላንተ ከተባለ ......♥
277
ክርስቶስ የወይኑ ግንድ ነው እኛ በእርሱ ያመንን ቅርንጫፎች ነን ገበሬውም አብ ነው።እኛ በክርስቶስ ብንኖር ቃሎችም በእኛ ቢኖሩ እኛም ብዙ ፍሬን እናፈራለን በዚህም በአብ ይከብራል።በእያንዳንዱ ስራ ቅርጫፍ ከግዱ ጋር ይነጋገራል ቅርንጫፍም የሚያስፈልገውን ከግንዱ ይወስዳል ከራሱ አንዳች የሚያደርገው ነገር የለም እኛ ክርስቲያኖችም like that ስለዚህ ለህይወታችን መሰረት ምንጭ ከሆነው ከኢየሱስ የሚያስፈልገንን vitamin,energy...ለመኖር የሚያስፈልገንን ነገር ካልወሰድን በቃሉ ወተት ካልጠነከርን እንደርቃለን ስለዚህ የህይወት ምንጭ ከሆነው ከኢየሱስ እንጣበቅ።
ዮሐ 15:1-11
277
"ሁሉን በጊዜው ውብ ያደርጋል።”
መክብብ 3፥11
ምናልባት ዛሬ ብዙ ጥያቄዎች ይኖሩብን ይሆናል። ተምረን ውጤት ላይመጣልን፣ ተመርቀን ሥራ ላናገኝ፣ ማግባት ፈልገን ላይሳካልን ይችላለን… እና ብዙ “ለምን?” የሚሉ ጥያቄዎች ልባችንን ሊሞሉት ይችላሉ።
ነገር ግን እግዚአብሔር ዝም ብሎ አይደለም፤ የሚሻለውን እያዘጋጀልን ነው። የእኛ ጊዜ እና የእርሱ ጊዜ ይለያያሉ፤ ነገር ግን የእርሱ ጊዜ ፍጹም ነው።
አንድ ቀን ወደኋላ ተመልሰን፣ “እግዚአብሔር ሆይ፣ ትክክል ነበርህ፤ ሁሉንም በጊዜው ውብ አድርገህልኛል” እንለዋለን።
277
Repost from N/a
ጊዜ የለኝም
ጊዜ የለኝም ያለው ሰው ጊዜውን አጠፋ።
ጊዜ የለኝም ብሎ የተነሳው ሰው ጊዜውን ለማግኘት ጊዜ ሲፈልግ፣ ያለውን ጊዜ በጊዜ ማጥፋቱ ተዘገበ። ጊዜ የለኝም ብሎ ጊዜ የገደለው ሰው፣ ጊዜው ሲደርስ ጊዜውን እንዳጠፋ ለማወቅ ጊዜ ወሰደ፤ ጊዜ እንዳለው ሲያውቅ ግን ጊዜው አልነበረውም፣ ጊዜ እንዳልነበረው ለማስረዳት ግን ጊዜ ነበረው፤ ጊዜ ለመቆጠብ ብሎ ጊዜ አጠፋ።
ጊዜ ለማግኘት ብሎ ጊዜ ፈለገ፣ ጊዜ ሲያገኝ ግን ያገኘውን ጊዜ እንዴት ሊጠቀምበት እንደሚችል ለማሰብ ሌላ ጊዜ ወሰደ። ያንንም ጊዜ ሲያስብ ጊዜው አለፈ፣ ጊዜው እንዳለፈ ሲያውቅ ጊዜ ለመመለስ ጊዜ ይኖረኛል ብሎ ጠበቀ፣ ጊዜ ግን አልጠበቀውም።
ስለዚህ ጊዜው ሲያልቅ ጊዜ እንደነበረው አስታወሰ፣ ግን ያስታወሰበት ጊዜ ጊዜውን የሚያድንበት ጊዜ አልነበረም። ስለዚህ ጊዜ የለኝም ብሎ ያጠፋውን ጊዜ እያሰበ ያለውን ጊዜ ማጥፋት ጀመረ፣ እና ጊዜው እያለፈ መሆኑን እያወቀ እንኳን ጊዜ የለኝም ማለቱን ለመቀጠል ጊዜ አገኘ።
በመጨረሻም ጊዜ እንደሌለው የሚያስብ ሰው ጊዜ እንዳለው ሲያውቅ ጊዜው አልፎ ነበር፤ ጊዜን የሚጠብቅ ጊዜ ያጣል፣ ጊዜን የሚያጠፋ ግን በመጨረሻ የሚያጠፋው ጊዜ ብቻ ሳይሆን ጊዜው መሆኑ ተገለፀ።
✍Alazer Teshome
