es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ብርሃን ፍለጋ{نور الهدى}

ብርሃን ፍለጋ{نور الهدى}

Ir al canal en Telegram

​"በወንጀል ጨለማ ለዛለች ነፍስ፣ወደ አላህ ብርሃን የምታደርገው ጉዞ።ቀልብን የሚያርሱ ምክሮችና የንቃት ጥሪዎች።"​የቀልብ ረፍትና የነፍስ ስንቅ ፍለጋ።ለማንኛውም ጥያቄ፣ አስተያየት ወይም ምክር እዚህ ያገኙናል፦ @BerhanFelega_Contact_bot

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
303
Suscriptores
Sin datos24 horas
-27 días
-630 días
Archivo de publicaciones
Repost from Abu~Mahi Channel
​«አላህ ሆይ! ማውራት በማልችልበት ሰዓት… ልቤን ስማው!» ​አንዳንዴ ቃላት ያጥሩናል። ከንፈሮቻችን መንቀሳቀስ ያቆማሉ፤ ጉሮሯችን በለቅሶና በሐዘን ይተናነቃል፤ አንዳንዴ ደግሞ ሕይወት ስትከብደን፣ ሐሳብ ሲበዛብን እና ብቸኝነት ሲሰማን ምን ብለን ዱዓ ማድረግ እንዳለብን እንኳን ይጠፋናል። ​ግን አላህ ሆይ… አንተ ከቃል በላይ ነህ! ​አንተማ የደረቴን ስፋት፣ የልቤን መቃተት፣ በውስጤ ተቀብሮ የሚንገበገበውን ምስጢር ከማንም በላይ ታውቃለህ። ቋንቋዬ ተዘግቶ፣ ምላሴም ከብዶ እንባ ብቻ ሲተካ፣ „አላህ ሆይ! በሰዓቱ ማውራት ባልችልም… ልቤን ስማው! ሹክሹክታውን፣ ጭንቀቱን፣ እና ወደ አንተ ያለውን ጥልቅ ጥማት ተረዳለት“ እላለሁ። ​ ሰው አፍ ሲዘጋ ዝምታ አለ ብሎ ያስባል፤ ነገር ግን በፈጣሪ ፊት ዝምታ ትልቁ ጩኸት ነው። ከንፈር ሳይንቀሳቀስ፣ ከዓይን የሚወርደው አንዲት እንባ ጠብታ ከሺህ ንግግሮች በላይ ጌታዋን ታነጋግራለች። አላህማ ሐሳባችን ከመፈጠሩ በፊት የሚያውቅ ጌታ ነው! ​ ዓለም ስታሸንፈን፣ መፍትሔ ሲጠፋን እና ብቻችንን ስንቀር… ማንም ሰው ሊረዳን በማይችልበት ሰዓት ሱጁድ ውስጥ መውደቅ ምን ያህል መታደል ነው! እዚያ ቦታ ላይ ቃላት አያስፈልጉም፤ ልብ ብቻ በቂ ነው። ልብ እንባን ይዞ ወደ ጌታው ሲያመለክት፣ መላእክት እንኳን ሰምተው የሚደነቁበት ፀጥታ የሰፈነበት ውብ ዱዓ ይሆናል። ​ ልባችን ተሰብሮ "ማን ይሰማኛል?" ብለን በምንጨነቅበት ቅጽበት፣ እሱ ግን "እኔ እኮ ከተጋነነ የደም ስርህ ይልቅ ቅርብ ነኝ" ይለናል። የልባችንን ምት የሚቆጣጠረው ጌታ፣ የልባችንን ስብራትም መጠገን ከብዶት አያውቅም። ​«ጌታ ሆይ! በምላሴ ልገልጸው ያልቻልኩትን፣ በውስጤ የታመቀውን የደከመ ልቤን ሐሳብ አንተ ታውቀዋለህና… ዱዓዬን ተቀበለኝ፤  ጭንቀቴንም አስወግድልኝ።» 🤲 https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris

አሰላምአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች! 👋 ​ቻናላችንን የበለጠ ለማነቃቃት እና እናንተን የሚጠቅሙ ነገሮችን ብቻ ለማቅረብ አስበናል። ​በዚህ ቻናል ላይ በብዛት ምን አይነት ይዘቶች (መረጃዎች/ትምህርቶች/ቪዲዮዎች) እንዲለቀቁላችሁ ትፈልጋላችሁ? ​ሀሳብና አስተያየታችሁን በኮመንት (Comment) አጋሩኝ፤ የሁላችሁንም አስተያየት በጥንቃቄ አነባለሁ! 👇💭

Repost from Abu~Mahi Channel
​"ኒቃቢስቷ ጀግና" — የጽናትና የብርታት ተምሳሌት ​አልሃምዱሊላህ፣ ለፈጣሪያችን ምስጋና ይሁን። ​ጀግናዋ እህቴ! ኒቃብ የለበሺውን ያህል የልብሽን ጥንካሬ፣ የህሊናሽን ነፃነትና የእምነትሽን ፅናት ያሳያል። አንቺን የሚጨቁኑሽ፣ በደል የሚያደርሱብሽና የሚያጥላሉሽ ሰዎች፣ አንቺ የምትከተይውን የእምነት መንገድም ሆነ ያሳየሽውን የፅናት ጥልቀት ሊረዱ አይችሉም። የእነሱ ጨለማ በአንቺ ላይ የሚታየውን ብርሃን ሊያደበዝዘው አይችልም። ይልቁንስ፣ በአንቺ ፅናት ውስጥ የሚያዩት የህሊና ነፃነት እነሱን ይረብሻቸዋል። ​አንቺ ግን እንደ ተራራ የጸናሽ ነሽ። ኒቃብሽ የመንፈስሽን ክብር፣ የእምነትሽን ጥልቀትና የራስሽን ማንነት ለመግለፅ የመረጥሽው የተቀደሰ መንገድ ነው። በለበሺው ኒቃብ የተነሳ የሚደርስብሽ ጭቆናና በደል ሁሉ የእምነትሽን ጥንካሬና የባህሪሽን ጀግንነት ይበልጥ የሚያጎላ ነው። እነሱ የሚያጥላሉሽ በክፋትና በጥላቻ ቢሆንም፣ አንቺ ግን በተስፋና በብርታት የተሞላሽ ነሽ። ​አንቺን የሚጨቁኑሽ ሰዎች፣ የእነሱ ጨለማ በአንቺ ላይ የሚታየውን ብርሃን ሊያደበዝዘው አይችልም። ይልቁንስ፣ በአንቺ ፅናት ውስጥ የሚያዩት የህሊና ነፃነት እነሱን ይረብሻቸዋል። አንቺ ግን እንደ ተራራ የጸናሽ ነሽ። ኒቃብሽ የመንፈስሽን ክብር፣ የእምነትሽን ጥልቀትና የራስሽን ማንነት ለመግለፅ የመረጥሽው የተቀደሰ መንገድ ነው። በለበሺው ኒቃብ የተነሳ የሚደርስብሽ ጭቆናና በደል ሁሉ የእምነትሽን ጥንካሬና የባህሪሽን ጀግንነት ይበልጥ የሚያጎላ ነው። ​የአማኝና የጀግናዋ እህቴ የፅናትና የብርታት ተምሳሌት ​ጀግናዋ እህቴ! የእምነትሽን ፅናትና የመንፈስሽን ክብር በጸና ጥንካሬሽን አሳይተሻል። ኒቃብ በመልበስሽ ምክንያት የደረሰብሽን ጭቆናና በደል ሁሉ ተቋቁመሽ፣ በብርታትና በፅናት የቆምሽ ጀግና ነሽ። በአማኝ ልብሽ ውስጥ ያለው የተስፋና የብርታት ብርሃን፣ በማንኛውም ጨለማ ውስጥ የሚያበራ ነው። አንቺ የእምነትና የጽናት ተምሳሌት ነሽ። ​አንቺን የሚያደንቁ፣ የሚያከብሩና ለአንቺ በውስጣቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው ሁሉ በአንቺ ፅናትና ብርታት ይኮራሉ። አንቺ የምትከተይውን የእምነት መንገድም ሆነ ያሳየሽውን የፅናት ጥልቀት የሚረዱሽ ሰዎች በአንቺ ፅናት ይበረታታሉ። የእምነትሽ ብርሃን በማንኛውም ጨለማ ውስጥ የሚያበራ ነው፣ አንቺ ግን እንደ ተራራ የጸናሽ ነሽ። ተፃፈ፣ በወንድማችሁ አቡ ማሒ ኢብኑ ኢድሪስ https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris

Repost from Abu~Mahi Channel
ለአማኝና ለጀግናዋ እህቴ የጻፍኩት የብርታትና የተስፋ መልእክት፦ ​"ኒቃቢስቷ ጀግና" — የጽናትና የብርታት ተምሳሌት በሚል "ከጁመዓ ሶላት በኋላ" በአቡ ማሒ የቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን። ተፃፈ፣ በወ
ለአማኝና ለጀግናዋ እህቴ የጻፍኩት የብርታትና የተስፋ መልእክት፦ ​"ኒቃቢስቷ ጀግና" — የጽናትና የብርታት ተምሳሌት በሚል "ከጁመዓ ሶላት በኋላ" በአቡ ማሒ የቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን። ተፃፈ፣ በወንድማችሁ አቡ ማሒ ኢብኑ ኢድሪስ https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris

Repost from Abu~Mahi Channel
ሴት ልጅ "እኔ ማን ነኝ?" የሚለውን ጥያቄ በልበ ሙሉነት መመለስ ስትችል እና የራሷን መስመር አክብራ ስትሄድ፣ ከውጫዊ ውዳሴ ይልቅ እውነተኛና ዘላቂ ክብርን ታገኛለች። ​ሴት ልጅ ሞገስ ናት፤ ክብሯ በውስጣዊ ስብዕናዋ፣ በሰከነ አእምሮዋ እና በሞራል ልዕልናዋ እንጂ በከንቱ ወሬና በውጫዊ ገጽታ ብቻ አይለካም። ​ሴት ልጅ ትኩረቷን በሌሎች ህይወት ላይ ሳይሆን በራሷ እድገት፣ አላማና እሴት ላይ ስታደርግ አእምሮዋ ነፃ ይሆናል፤ ክብሯና ስብዕናዋም ይበልጥ ይደምቃል። ​የራሷን ህይወት የመራችና የራሷ አላማ ያላት ሴት የሰዎችን ፈጣን ጉዞ ወይም ስኬት ለማየት አትቸኩልም። የራሷን መንገድ በደስታና በጽናት ትራመዳለች። ​ጊዜዋንና ውድ ሕይወቷን በሐሜት፣ በሰዎች ጉድ ማጣራትና በአሽሙር አታባክንም። ​ጊዜ አንዴ ካለፈ የማይመለስ የሕይወት ትልቁ ሀብት መሆኑን በጥበብ ትረዳለች። ስለዚህ ይህን ውድ ጊዜ በሰዎች ስንጥቅና ውድቀት ላይ ማባከን የራስን እድልና የወደፊት ራዕይ እንደመግደል ይቆጠራል። የራሷን ሕይወት በማበጠር፣ አቋሟን በማጥራት እና በአላማ ላይ ታተኩራለች እንጂ።​ለሰው ሁሉ ደስ ለማሰኘት ወይም ጊዜያዊ ውዳሴን ለማግኘት ስትል ማንነቷንና መርሆዋን አታዛባም፤ ቃሏ ቃል፣ አቋሟም የማይናወጥ ነው። ​ሴት ልጅ አስተዋይ ናት፤ ቅሬታ እንኳን ቢኖራት በብስለትና በቁምነገር ትጋፈጠው እንጂ በጓሮ በር ነገር አትወረውርም። ​ችግሮችን ወይም ቅሬታዎችን በጀርባ ከመወርወር ይልቅ ፊት ለፊት በብስለት መነጋገር የእውነተኛ ጥንካሬና የከፍተኛ ስብዕና ምልክት ነው። ከንቱ ወሬና ነገርን ማባላት የደካሞች መለያ መሆኑን ታውቃለች። ​እውነተኛ የሴትነት ጥንካሬ ቋንቋን በመጠበቅ፣ ስሜትን በልባዊ ብስለት በመግዛት እና በጸጥታ ታላቅ ስራዎችን በመስራት ላይ ነው። ምላሷን የገዛች ሴት አእምሮዋንና አጠቃላይ ሕይወቷን ትቆጣጠራለች። ​ለሰው ሁሉ ደስ ለማሰኘት ወይም ጊዜያዊ ውዳሴን ለማግኘት ስትል ማንነቷንና መርሆዋን ማዛባት ለክብሯ የሚመጥን አይደለም። ​ሰው ሁሉ እንዲወደኝ ብላ እውነቱን መሸሸግ፣ ወይም የ ሰዎችን ይሁንታ ለማግኘት ስትል የእሷ ያልሆነን ባህሪ ለመላበስ መሞከር የራሷን እውነተኛ ማንነት ያሳጣታል። ​𝓪𝓫𝓾 𝓶𝓪𝓱𝓲 https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris

Repost from Abu~Mahi Channel
«وَاللَّهُ خَيْرُ الْمَاكِرِينَ» – የአላህ እቅድ ከማንም በላይ አሸናፊ ነው! ​ሰዎች ሲያሴሩ፣ በድብቅ ሊጎዱህ ሲታገሉ ወይም በዙሪያህ ያለው ሁኔታ ጨለመብኝ ብለህ ስትጨነቅ ልብህ
«وَاللَّهُ خَيْرُ الْمَاكِرِينَ» – የአላህ እቅድ ከማንም በላይ አሸናፊ ነው! ​ሰዎች ሲያሴሩ፣ በድብቅ ሊጎዱህ ሲታገሉ ወይም በዙሪያህ ያለው ሁኔታ ጨለመብኝ ብለህ ስትጨነቅ ልብህን የሚያረጋጋው አንዱና ብቸኛው እውነት ይህ አያት ነው። የቁርአኑ መልእክት ልብ ብላችሁት አስተንትናችሁት ከሆነ ልብን የሚነካና ተስፋን የሚሰጥ ነው፦ ​«وَاللَّهُ خَيْرُ الْمَاكِرِينَ» (ሱረቱል አንፋል - አንቀጽ 30) (አላህም ከሁሉ በላይ ሴራን አክሻፊና እጅግ ውብ እቅድ አውጪ ነው።) ​የፍጡራን ጥረት ገደብ አለው ሰዎች በአንተ ላይ መጥፎ ነገር ለማቀድ፣ ዝናህን ለማጥፋት ወይም እውነትን ለመሸፈን ቢጥሩም፣ የአላህን ውሳኔ ግን ማስተካከል ፈጽሞ አይችሉም። ​የአላህ ጥበቃ ድብቅ ነው የሰዎች ሴራ ግልጽ ወይም የከበደ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን የአላህ ጥበቃና እቅድ ከሁሉም በላይ ኃያልና አሸናፊ ነው። ​ትዕግስትና መረጋጋት በሰዎች ሴራ ወይም በፈተና ውስጥ ስትሆን፣ ጉዳዩን ለፈጣሪህ በመተው ልብህን ማረጋጋት ትልቁ የድል መሣሪያ ነው። ወዳጄ ፣​ጭንቀትህና ሀዘንህ ሁሉ በጌታህ ፊት የታወቀ ነው። እርሱ አንተን የሚጠብቅና ከሚሰነዘሩብህ ሴራዎች ሁሉ በላይ ሐቅን አሸናፊ የሚያደርግ አምላክ ነው። ​ይህ እውነት በህይወትህ ውስጥ ምን ዓይነት መረጋጋትን ይፈጥርልሃል? https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris

Abu~Mahi Channel: ንያችሁን ለማሳወቅ ከፈለጋችሁ በውስጥ ላኩልኝ @Abu_Meymuna_Al_Asseriy በሉ እንጂ ጀግኖቼ ነይቱ መስጂዳችንን እንገባ

Repost from Abu~Mahi Channel
​🌙 ለ “መስጂደ አስ-ሱና” የግንባታ ድጋፍ ጥሪ ​የተከበራችሁ ወንድሞችና እህቶች! ​ነቢዩ (ሶለል አላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ ​"ለአላህ ብሎ መስጂድን የገነባ፤ አላህ በጀነት ውስጥ
​🌙 ለ “መስጂደ አስ-ሱና” የግንባታ ድጋፍ ጥሪ ​የተከበራችሁ ወንድሞችና እህቶች! ​ነቢዩ (ሶለል አላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
​"ለአላህ ብሎ መስጂድን የገነባ፤ አላህ በጀነት ውስጥ ለእርሱ ተመሳሳይ ቤትን ይገነባለታል።"
​ይህንን ታላቅ የኸይር እና የጀነት መንገድ አጋጣሚ በመጠቀም፣ ለመስጂደ አስ-ሱና ግንባታና ልማት የሚሆን ችሮታችሁን እና ድጋፋችሁን በቻላችሁት መጠን እንድታበረክቱ በታላቅ አክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን። ​እስከ ቂያማ ቀን ድረስ ምንዳው የማይቋረጥ የቋሚ ሶደቃ (ሶደቀቱል ጃሪያ) ባለቤት ይሁኑ። አላህ ዘንድ በትንሹ የሰጡት መልካም ነገር በታላቅ ምንዳ ተባዝቶ ይመለሳል። ​🏦 የመስጂደ አስ ሱና የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች         ◈ ​የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000469830277         ◈ ​ዘምዘም ባንክ፦ 0005649620101           ◈​ ሂጅራ ባንክ፦ 1000030300001 ​(የባንክ ሂሳቦቹ በ መስጂደ አስ-ሱና ስም የተመዘገቡ ናቸው።) ​💡 "ኸይር ስራን የጠቆመ እንደ ሰሪው ነው!" ይህንን ጥሪ ለሌሎች ወንድምና እህቶች በማጋራት (Share) በማድረግ የዚህ ታላቅ አጅር ተካፋይ ይሁኑ! ​ጃዛኩሙላሁ ኸይረን!

ተለቀቀ

​⛓️ «የወንጀል እስራት እና የዕንባ መፍቻ!» ​بسم الله الرحمن الرحيم ​ውድ ወንድሜ… የተከበርሽ እህቴ! ቆም ብለህአሰብክ ታውቃለህ ? ቆም ብለሽ አስበሽስ ታውቂያለሽ ? ወንጀል እጅና እግርን የማይታይ ሰንሰለት አግዶ የሚያስር፣ መንፈስን የሚያጠበብ፣ የልብን ብርሃን አጥፍቶ በጨለማ ክፍል ውስጥ የሚቆልፍ ከባድ እስራት ነው። ​ስንቶቻችን ነን በየቀኑ የሚደጋገሙ ጥፋቶቻችን ታስረን፡ ▾ ሶላት ለመስገድ ስንነሳ እግራችን የሚከብደን? ▾ ቁርኣን ለማንበብ እጃችንን ስንዘረጋ የሚዝልብን? ▾ ከአላህ ጋር ለመቀራረብ ስንል ልባችን ድርቅ ብሎ የሚፈታተነን? ​ይህ ሁሉ የሌላ ነገር ውጤት አይደለም—የወንጀል እስራት ነው! ​🔥 ወዳጆቼ ሆይ! አላህ ይዘንልንና… ለአንድ አፍታ እንኳ በሕይወታችን የሰራናቸውን ወንጀሎችና ጥፋቶች በቁጭት እሳትነት አቃጣይ ስሜት አስበናቸው እናውቃለን? ​አላህ እያየን፣ የሰጠንን ጸጋ በእጁ እየተቀበልን፣ በእሱ ላይ ደፍረን ስናመፅ የነበረበትን ጊዜ ስናስበው ልባችን አይነድም? እስከ መቼ ነው በዚህ የወንጀልና የእስራት እንቅልፍ ውስጥ የምንቆየው?» እስከ መቼ ነው በገዛ እጅህ የወንጀል ሰንሰለት እየተበተበህ የሸይጧን እና የነፍስህ ባሪያ ሆነህ የምትኖረው? እስኪ ንቃ! እስከ መቼ ነው በዚህ ውርደት ውስጥ የምትቆየው? ​ስንት ሌሊት ነው አላህ እየተመለከተህ በምስጢር ወንጀል ስትጨማለቅ ያደርከው? ሰዎች እንዳያዩህ በሩን ዘግተህ፣ መጋረጃውን ጣል አድርገህ፣ ስልክህን ደብቀህ ተደበቅክ… ነገር ግን የሰማይና የምድር ጌታ እያየህ እንደነበር አረሳኸውም? የሰዎችን እይታ ፈራህ፤ የአላህን እይታ ግን አቀለልከው! ከዚህ በላይ ምን የሚያስቆጭና የሚያሳፍር ውርደት አለ? ​እስኪ አስበው… ያንተን ጥፋትና ነውር አላህ ለሰዎች ቢገልጥብህ ኖሮ ዛሬ ማን ያከብርህ ነበር? ማን አብሮህ ይቆም ነበር? እሱ ግን ስትበድለው እንኳ ነውርህን ደብቆልህ፣ የአየር እስትንፋሱን ሳይከለክልህ፣ ጤናህን ሳይነጥቅህ እስከ ዛሬ ታገሰህ! ​አንተ ግን በምታገኘው እያንዳንዱ ጸጋ እሱን ስታመፅበት አልፈራህምን? በዓይንህ አላህ የከለከለውን ስታይ፣ በጆሮህ የተጠላውን ስትሰማ፣ በእግርህ ወደ ወንጀል ስትራመድ… «የሞት መልአክ አሁን በዚች ቅጽበት ነፍሴን ቢነጥቃት አላህ ፊት በምን ፊት እቆማለሁ?💦 » ብለህ አልደነገጥክም? ቁጭቱና ፀፀቱ አያቃጥልህም?💦 ​"ነገ እመለሳለሁ፤ ነገ ተውበት አደርጋለሁ፤ ገና ወጣት ነኝ..." እያልክ እራስህን አታልለህ አትተኛ! "ነገ አለህ… አንተ ግን በነገ ውስጥ ላይኖርህ ትችላለህ!" የሞት መልአክ በርህን ለማንኳኳት ያንተን ዕድሜ ማጠናቀቅ እንጂ ያንተን "ነገ እመለሳለሁ" የውሸት ምኞት አይጠብቅም። ​ነገር ግን ተስፋ አትቁረጥ! አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እኮ እንዲህ ይላል፦ ​«በላቸው፡- እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ አላህ ኃጢአቶችን ሙሉ በሙሉ ይምራልና። እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና።» (ዙመር፡ 53) ​ዛሬ የዚያን የጠነከረ ልብህን ዕንባ መፍቻ ቀን አድርገው! የአላህ ፍርሃት ከልብህ መንጭቶ በጉንጭህ ላይ የምታፈሳት አንዲት የቆጨች ዕንባ… አላህ ዘንድ እጅግ የተወደደች ናት። ያች ዕንባ የእስራትህን ሰንሰለት ስብርብር አድርጋ የምትጥል፣ የነፍስህን የቆሸሸ ገጽታ አጥባ የምታጠራ ልዩ አሲብ ናት። ​ዛሬውኑ ወስን ወስኒ💦! ▾ እስኪ ​ወደ ኋላ ተመልከት፦ ያበላሸኸውን ታሪክ በቅን ተውበት እጠበው። ያለፉትን የጨለማ ቀናትህን፣ ከአላህ መንገድ የራቅክባቸውን ዓመታት፣ የወደቅክባቸውን አሳፋሪ ወንጀሎች አስባቸው። ነገር ግን ተስፋ ልትቆርጥ ሳይሆን፣ በቁጭትና በዕንባ ልታጥባቸው ወደ ኋላ ተመልከት! አላህ ያለፈውን ጥፋትህን ሙሉ በሙሉ ደምስሶ በበጎ ሥራዎች የመለወጥ ቃል ገብቶልሃል። ታሪክህ ምንም ያህል ቢበላሽ፣ በአላህ እዝነትና በእውነተኛ ተውበት የማይታደስበት ምንም ምክንያት የለም፤ ዛሬ አዲስ ገጽ ክፈት!» ▾ ​አሁኑኑ ቁም፦ "ነገ" የሚባለውን የሸይጧን ማታለያ ቀለበት በጥስ። "ነገ እመለሳለሁ፣ ነገ እቀየራለሁ፣ ነገ ተውበት አደርጋለሁ..." እያልክ እራስህን አታታል! ሸይጧን ስንቱን በ"ነገ" ማታለያ ተስፋ እያሰጠ ቀስ እያለ ከቀጥተኛው መንገድ አወጣው? ስንቱ ሰው "ነገ እቀየራለሁ" እያለ ሳይቀየር በመጣበት ቅጽበታዊ ሞት ተነጥቆ ወደ ቀብር ወረደ? ​"ነገ" ያንተ አይደለችም፤ ዛሬ ግን በእጅህ ላይ ናት! አሁኑኑ ተነሥ፣ የወንጀልን ሰንሰለት በጥስና ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነት አድስ። አሁኑኑ ካልቆምክ፣ ነገ በሚባለው ሀሰተኛ ተስፋ ውስጥ ተሸውደህ እስከወደቅክበት ልትቀር ትችላለህ!» ▾ ​እጆችህን ዘርጋ፦ በብቸኝነት አላህ ፊት ተንበርከክና እውነተኛ ዕንባህን አፍስስ፤ ሰዎች በሙሉ በተኙበት፣ በዚያ በጨለመው የሌሊት ክፍለ ጊዜ፣ ማንም የማያይህና የማይሰማህ ቦታ ላይ በብቸኝነት ተንበርከክ። የሠራኸውን ነውር ሁሉ ለአላህ እያመንንክ፣ በሠራኸው ጥፋት ልብህ በቁጭት እየነደደ፣ እጆችህን ወደ ሰማይ ዘርጋ። ​ከዓይንህ የምታፈሳት አንዲት የቆጨችና ከአላህ ፍርሃት የተነሳች ዕንባ… የጀሀነምን እሳት ለማጥፋት ብቁ ናት! ጌታህ እኮ ከሰው ይልቅ ለአንተ አዛኝ ነው፤ እጆችህን ባዶአቸውን ወደ እሱ ዘርግተህ ባዶህን ሊመልስህ ያፍራል። ዛሬ በብቸኝነት አላህ ፊት አልቅሰህ ልብህን አርሳት፣ የወንጀልን ሰንሰለት በዚያች እውነተኛ ዕንባህ በጥስ!» "ጌታዬ ሆይ! ተመለስኩብህ፣ ተቀበለኝ" በለው! ​“ጌታዬ ሆይ! በወንጀል የቆሸሸችውን ነፍሴን፣ በምስጢር ያጠፋሁትን ጥፋቴን፣ የታከትኩበትን እድሜዬን ይዤ በደጅህ ወድቄአለሁና አትመልሰኝ! እስከ ዛሬ በባከነ መንገድ ላይ የተጓዝኩበት ይበቃኛል፤ እባክህ ማረኝ፣ ተቀበለኝ!” በለው!» «ወንድሞቼና እህቶቼ ሆይ! ይህንን ማስታወሻ ወደ እናንተ ስልክ፣ እኔ ከእናንተ የተሻልኩ፣ ከወንጀል የጠራሁ ወይም ከማንም በላይ አላህን የምፈራ ሆኜ አይደለም። እኔ ራሴ የወንጀልና የጥፋት ባሪያ፣ የአላህ ምህረትና እዝነት ከአንደበቴ በላይ እጅግ የሚያስፈልገኝ ምስኪን ባሪያ ነኝ። ​ነገር ግን ነፍሴንና እናንተን ባስታወስኩ ቁጥር “አላህ ሁላችንንም ይማረን፣ ይዘንልን” ከሚል የልብ ቁጭት የተነሳ የቀረበ የወንድማማችነት ጥሪ ነው። ​አላህ እኔንም እናንተንም ከወንጀል እስራት አውጥቶ፣ በእውነተኛ ተውበት ልቦቻችንን ያድስልን፤ መጨረሻችንንም ያሳምርልን! 🤲» ​✍️ የጌታው ምህረት ከጃይ አቡ ማሒ ሙሐመድ ብን ኢድሪስ ​🔗 ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/BerhanFelega https://t.me/BerhanFelega

​⛓️ የባርነትና የወንጀል እስራት ይበቃሃል!… ​ወንድሜ ሆይ! እስከ መቼ በወንጀል ሰንሰለት ታስረህ፣ በጨለማ ክፍል ውስጥ ተቆልፎብህ ትኖራለህ? እስከ መቼስ ነው "ነገ እመለሳለሁ" እያልክ በሀሰተኛ
​⛓️ የባርነትና የወንጀል እስራት ይበቃሃል!… ​ወንድሜ ሆይ! እስከ መቼ በወንጀል ሰንሰለት ታስረህ፣ በጨለማ ክፍል ውስጥ ተቆልፎብህ ትኖራለህ? እስከ መቼስ ነው "ነገ እመለሳለሁ" እያልክ በሀሰተኛ ተስፋ እራስህን የምታታልለው? ​የነፍስህ እሰራት የሚበጠስበት፣ ልብህ በዕንባ ታጥቦ የሚጠራበት እና ወደ አላህ የምትመለስበት ሰዓት አሁን ነው! ​ለእናት፣ ለአባት፣ ለወንድምና ለእህት የሚሆን… ልብን የሚያርስና የዐይን ዕንባን የሚያፈስ ገራሚ አስተማሪ ጽሑፍ ይዘንላችሁ ልንቀርብ ነው። ​«የወንጀል እስራት እና የዕንባ መፍቻ!» ​⏰ ከጁሙዐ ሶላት በኋላ ይጠብቁን! ​🔗 ለሌሎችም ያጋሩ፦ https://t.me/BerhanFelega

​በአላህ ፈቃድ ሌላ አዲስ የጁሙዐ ቀን ደረሰልን። ጁሙዐ የሳምንቱ በዓላችን፣ የዱዓችን መልስ ማግኛ፣ እና የልባችንን እድፍ በኢስቲግፋር የምናጥርበት የተባረከ ቀን ነው። ​ዛሬን እንዲሁ በተላላፊ ወሬና በዱኒያ ጉዳይ ብቻ አንሸኘው። አላህ የሰጠንን ይህን ውድ ዕድል እንጠቀምበት፡ ​በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት፡ ​"በእኔ ላይ በጁሙዐ ቀን ሶለዋትን አብዙ፤ ሶለዋታችሁ በእኔ ዘንድ ትቀርባለችና።" (ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ) اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ https://t.me/BerhanFelega

Repost from Abu~Mahi Channel
​ለራሳችን የምንሰጠው ምክንያት/ምክንያት አሳማኝ ነውን? 🕋 ​በቪዲዮው ላይ የምታዩአቸው አዛውንት እድሜያቸው ከ90 ዓመት በላይ ቢሆንም፣ በምርኩዝ እየተደገፉና እየተጎተቱ ወደ አላህ ቤት (መስጊድ) በማምራት ላይ ይገኛሉ። አካላቸው ቢደክምም፣ መንፈሳቸውና ለአላህ ያላቸው ፍቅር አልደከመም። ​እኛ ግን ጤና፣ ጉልበት፣ ወጣትነትና ሙሉ አካል እያለን ከሶላት የምንቀረው በምን ምክንያት ይሆን? ​"ስራ በዛብኝ..." ​"ደክሞኛል..." ​"ጊዜ የለኝም..." ​እነዚህ ሁሉ አላህ ፊት ዋጋ የሌላቸው ደካማ ምክንያቶች ናቸው። ሰላት የነፍስ ምግብ፣ የልብ እርካታና የስኬት ሁሉ መክፈቻ ነው። ​ ጊዜ ሳይረፍድ፣ ጉልበታችን ሳይከዳንና ህይወታችን ሳይያልቅ ወደ ሶላት እንመለስ። አላህ የመጨረሻችንን ያምርልን!  https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris

ወንድ ልጅ ቀጥተኛ ነው። ቢገባው ያመሰግናል፣ ባይገባው በጥበብ ይጠይቃል፣ ካልተመቸው ደግሞ በክብር ይርቃል። ከጀርባ በሚወረወር ቃልና አሽሙር ጊዜውንና ወንድነቱን አያረክስም። ለሰው ሁሉ ደስ ለማሰኘት ወይም ሰዎችን አላስፈላጊ ቦታ ለማስደሰት ስትል አቋምህን አታዛባ። የሚታመን፣ ቃሉ ቃል የሆነና ወጥ የሆነ ሰብዕና ይኑርህ። ወንድ ልጅ ክብር አለው! ወንድነት በዝምታና በቁምነገር፣ በጠንካራ ሰብዕናና በሃላፊነት ስሜት እንጂ በከንቱ ወሬ፣ በአሽሙርና በነገር ፍጆታ አይለካም። ​ወንድ ልጅ ግልጽ ነው፤ ቅሬታ እንኳን ቢኖረው በቁምነገር ተጋፍጦ እንጂ በጓሮ በር ነገር አይወረውርም። አሽሙርና ነገርን ማባላት የጠንካራ ወንድ መለያ ሳይሆን የውስጥ ድክመትና የመተማመን ማነስ ምልክት ነው፤ የቆመበትን የማያውቅ ሰው የሚጠቀምበት ደካማ መሳሪያ ነው። እውነተኛ ጥንካሬ ሰውን በቃል መውጋት ወይም አሽሙር መወርወር ሳይሆን፣ ስሜትን መግዛትና በብስለት መናገር ነው። ምላሱን የገዛ አእምሮውንና ሕይወቱን ይገዛል። ​ወንድ ልጅ ማበጠር ያለበት ሕይወቱንና አቋሙን እንጂ የሰውን ጉድ አይደለም። አቋምህ ይንገስ፣ ቃልህ ይከበር፣ ወንድነትህም በቁምነገርህ ይደምቅ! 𝓪𝓫𝓾 𝓶𝓪𝓱𝓲 https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris

«ሕመምህን ሰው እንዲረዳህ ማስረዳት አለብህ፤ አላህ ግን ሳይነገረው የልብህን ሕመም እና የውስጥህን ጭንቀት ያውቃል።» ​አንዳንዴ በሕይወታችን ውስጥ በቃላት ልንገልጸው የማንችለው፣ ለሰው አውርተንም ቀላል የማይሆን ከባድ የውስጥ ሕመም ያጋጥመናል። ለቅርብ ሰው እንኳን ለማስረዳት ቃላት ያጥሩናል፤ አሊያም ደግሞ "ሰው አይረደኝም" በሚል እጣፋንታ ዝምታን እንመርጣለን። ሰው ሕመምህን እንዲረዳህ በረጅም አብራርተህ ማስረዳት አለበት፤ ያን ያህል ደክመህ አብራርተህ እንኳን አንዳንዴ ሙሉ በሙሉ ሊረዳህ አይችልም። ​አላህ ግን እንዲህ አይደለም! ​እሱ የልብህን ትርታ፣ የዓይንህን ዕንባ፣ እና በውስጥህ የሚመላሰውን ጭንቀት ሁሉ ሳይነገረው ያውቃል። በልብህ ውስጥ የተቀበረውን ስቃይ ለመግለጽ ቃላትን ማደራጀት አይጠበቅብህም። ዝም ብለህ በዓይንህ ዕንባና በልብህ ስብራት ወደ እሱ ስታዞር፣ እሱ የውስጥህን ስቃይ ሰምቶ መልስ ይሰጣል። ​የሰው ረዳትነት ወሰን አለው ሰው ሊያዝንልህ ይችላል፣ ሊያዳምጥህ ይችላል፤ ነገር ግን የልብህን ክብደት ከውስጥህ አውጥቶ ሊቀንስልህ አይችልም። ​የአላህ እውቀትና እዝነት ግን ወሰን የለውም ያልተናገርከውን ያውቃል፣ ያላወጣኸውን የውስጥ ቁስል ያክማል፣ የልብህንም ስብራት ይጠግናል። ​ስለዚህ፣ ሰው አልተረዳኝም ብለህ አትጨነቅ። የልብህን ጭንቀትና ሕመም የሚያውቅ፣ ሳይናገሩ የሚያዳምጥ፣ ሲለምኑት ደግሞ የማይሰለች ጌታ አለህ። ውስጣችሁን በእሱ ላይ ጣሉ፤ በዝምታችሁ ውስጥ ያለውን ድምፅ እሱ ብቻ በትክክል ይሰማዋል! @BerhanFelega @BerhanFelega

ቀኑን በሰላም አውሎ አሁን ላደረሰን አላህ ምስጋና ይገባው! አልሀምዱሊላህ። ​"ቢስሚከ ረቢ ወዷዕቱ ጀንቢ ወቢከ አርፈዑህ..." (ጌታዬ ሆይ! በስምህ ጎኔን አሳረፍኩ፤ በስምህም አነሳዋለሁ...) ​ያረብ! በድካም ለዋሉት እረፍቱን፣ ለታመሙት ሽፋውን፣ ለተጨነቁት ፈረጃውን የምትለግስበት የተባረከ ምሽት አድርግልን። ​🌟 መልካም ምሽት! ​🔗 ሼር ያድርጉ ➪ @BerhanFelega

Repost from Abu~Mahi Channel
​🔥 ቆፍጠን በል! በሐቅ ላይ አቋም ይኑርህ! ​ወንድሜ ሆይ! ሃይማኖትና መንሐጅ የጨዋታ እቃ አይደሉም። ዛሬ ላይ ትልቁ ፈተና የዒልም ማነስ ብቻ ሳይሆን የጽናትና የአቋም መሸርሸር ነው። ​ለሰው ብለህ አታዳላ፤ ለማንም ብለህ አትለሳለስ! ሐቅ አንድ ብቻ ናት—እሷም በነቢዩ ﷺ እና በሶሐቦች መንገድ (በሰለፎች አሰረ-ፍኖት) ላይ መጓዝ ብቻ ናት። ​እዚያም እዚህም የምትለከሰከሰዉ እስከ መቼ ነው? "ሰለፊይ ነኝ" እያልክ በቃላት እየተጫወትክ፡ ​በአንድ በኩል ከሐቅ መንገድ ጋር፣ በሌላ በኩል ደግሞ አየር በነፈሰበት አቅጣጫ ከሚነዱት ጋር አብረህ አትወዝወዝ! ​የሰዎችን ወገንተኝነትና ሙገሳ ፍለጋ ስትል ሐቅን አታደብዝዝ፤ ​ለሆድህ፣ ለስምህ ወይም ለጥቅምህ ብለህ የያዝከውን ቀጥተኛ መንሐጅ አትሸጥ! ​ወንድ ከሆንክ በሐቅ ላይ ቆፍጠን በል! የሰለፊያ መንገድ የጽናት መንገድ እንጂ የአጋጣሚዎች መጠቀሚያ አይደለም። ዱኒያ አጫጭርና አታላይ ናት። ዛሬ በሰዎች ዘንድ ለመወደድ ብለህ የምታደርገው መለስለስና ማቻቻል፡ ነገ አላህ ፊት ሲቆም አንዳች አይጠቅምህም። ​አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይላል፡
​«በታዘዝከው ነገር ላይ ቀጥ በል!» (ሁድ፡ 112)
​ተውሂድን ይዘሃል? ቀጥ በል! ሱናን ጨብጠሃል? አትወዝወዝ! ቢድዓንና ጥመትን ትተሃል? አትለሳለስ! ​ሰው ቢደሰትም ቢጠላም፤ ዓለም ቢከተልህም ቢተውህም—አንተ ግን በሐቅ ላይ እንደ ተራራ ጸንተህ ቁም። ዱኒያ በቅርብ የምታልፍ ህልም ናት፤ አታላይ ሽንገላዋ አይዝጋህ። ​ወንድሜ ሆይ! ራሰህን ፈትሽ… ዛሬውኑ አቋምህን አስተካክል! ​@Abu_Mahi_Ibnu_Idris ​@Abu_Mahi_Ibnu_Idris

​🍯 አዲስ እና ንፁህ የተፈጥሮ ማር ይፈልጋሉ? 🍯 ​ለጤናዎና ለቤተሰብዎ የሚሆን፣ ምንም አይነት ቅይጥ የሌለው፣ ተፈጥሯዊ ጣዕሙና መዓዛው እንደተጠበቀ የተቆረጠ አስተማማኝ ማር ይዘንልዎ መጥተናል።
+6
​🍯 አዲስ እና ንፁህ የተፈጥሮ ማር ይፈልጋሉ? 🍯 ​ለጤናዎና ለቤተሰብዎ የሚሆን፣ ምንም አይነት ቅይጥ የሌለው፣ ተፈጥሯዊ ጣዕሙና መዓዛው እንደተጠበቀ የተቆረጠ አስተማማኝ ማር ይዘንልዎ መጥተናል። ​✨ የእኛ ማር ልዩ የሚያደርገው፡ ​100% ተፈጥሯዊና ንፁህ ማር ​ለጤና፣ ለምግብነት እና ለህክምና ተመራጭ ​ጥራቱን የጠበቀና በተፎካካሪ ዋጋ የቀረበ ለማዘዝ አሁኑኑ ያነጋግሩን፡ 📞 ስልክ፡ [09 12 89 98 94 ] ➠ቴሌግራም[@Abu_Meymuna_Al_Asseriy] ​🚚 አሁኑኑ ይደውሉልን፤ ባሉበት ቦታ እናደርሳለን! ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር (Share) ያድርጉ! 🔗 የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ፦ https://t.me/Al_Faiz_online_shopping

የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ልጆች ~ የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ስድስት ወንዶችና አንዲት ሴት፣ በድምሩ ሰባት ልጆች ነበሯቸው። [ሀ] የ"ኣሉ ሸይኽ" (የሸይኽ ቤተሰብ) ዝርያ የቀጠለባቸው አራት ልጆች ናቸው። ዛሬ ድረስ በሳዑዲ ዐረቢያ ውስጥ "እከሌ ኣሉ ሸይኽ" እየተባሉ የሚጠሩት የእሳቸው ዝርያዎች ናቸው። ይሄ የእሳቸው ዝርያ የቀጠለው በአራቱ ልጆቻቸው በኩል ሲሆን፣ ሁሉም ታላላቅ ዐሊሞችና ዳኞች ነበሩ። እነሱም፦ 1. ሸይኽ ሑሰይን ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1224 ሂ.)፦ ከአባታቸው በኋላ በዲርዒያህ ከተማ ውስጥ ዳኛ (ቃዲ) ሆነው አገልግለዋል። ታላቅ ዐሊም እና የዲርዒያህ መስጂድ ኢማም ነበሩ። * ከእሳቸው የ"ኣሉ ሑሰይን" (የሑሰይን ቤተሰብ) ቅርንጫፍ ተዘርግቷል። 2. ሸይኽ ዐብዱላህ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1224 ሂ.)፦ ከታላላቅ ዐሊሞችና ፀሐፊዎች አንዱ ነበሩ። ዲርዒያህ ውስጥ ቃዲ የነበሩ ሲሆን፣ ዲርዒያህ ከግብፅ በተነሳው የኦቶማን ቱርክ ጦር ስር ስትወድቅ ወደ ግብፅ ተወስደው እዚያው ሞተዋል። * ከእሳቸው በኩል የ "ኣሉ ዐብዲላህ" (የሑሰይን ቤተሰብ) ቅርንጫፍ የተገኘ ሲሆን፣ "ተይሲሩል ዐዚዝል ሐሚድ" የተሰኘውን ታዋቂው የኪታቡ ተውሒድ ሸርሕ ያዘጋጁት ልጃቸው ሱለይማን ብኑ ዐብዲላህ ናቸው። 3. ሸይኽ ዐሊይ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1245 ሂ.)፦ ታላቅ የፊቅህ ዐሊምና አላህን ፈሪ ሰው ነበሩ። የዳኝነት ሹመት ቢቀርብላቸውም አልተቀበሉም። * ሙሐመድ ከተሰኘው የእሳቸው ልጅ የ "ኣሉ ዐሊይ" ወይም "ኣሉ ሙሐመድ" ቅርንጫፍ ተገኝቷል። 4. ሸይኽ ሐሰን ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ፦ አባታቸው በሕይወት እያሉ ነው የሞቱት። ነገር ግን "ፈትሑል መጂድ" የተሰኘውን ታዋቂ የኪታቡ ተውሒድ ሸርሕ ያዘጋጁትን ልጃቸውን ዐብዱረሕማን ብኑ ሐሰንን ተክተው አልፈዋል። ከእሳቸው የ"ኣሉ ሐሰን" ቅርንጫፍ ተዘርግቷል። [ለ] ሌሎች ልጆች (ዝርያ ያልቀጠለባቸው) 1. ሸይኽ ኢብራሂም ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1250 ሂ.)፦ እውቀት ያላቸው ዐሊም ነበሩ። በዲርዒያህ የማስተማሪያ ሐለቃህ ነበራቸው። በኋላም ወደ ግብፅ ሄደው እዚያ ነው የሞቱት። 2. ዐብዱልዐዚዝ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ፦ በልጅነታቸው በአባታቸው የሕይወት ዘመን ነው የሞቱት። 3. ፋጢማ ቢንት ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ፦ የተከበረች ዐሊማ (የእውቀት ባለቤት) የነበረች ሲሆን ተማሪዎችን ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ያስተምሩ ነበር። ዲርዒያህ በኦቶማን ጦርነት በወደቀች ጊዜ ተሰዳ ቆይታ በመጨረሻም በሪያድ ከተማ ሞታለች። አስተውሉ! ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ከአንድኛው በስተቀር ልጆቻቸውን በሙሉ በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤተሰቦች ስም ነው የሰየሟቸው። ዐብዱላህ፣ ኢብራሂም እና ፋጢማ በቀጥታ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ልጆች ስም ሲሆን ሐሰን እና ሑሰይን ደግሞ የልጅ ልጆቻቸው ስም ነው። ዐሊይ ደግሞ የነብዩ ዐለይሂ ወሰለም የአጎት ልጅ እና አማቻቸው የሆነው የታላቁ ሶሐቢይ ስም ነው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor