NegadRas™ FX Academy
Ir al canal en Telegram
Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
4 716
Suscriptores
-824 horas
+57 días
+23630 días
Archivo de publicaciones
4 717
ሰርክ ዓርብ ዓርብ ምሽት የምናካሄደው የ"ሸንጎ" የፋይናንሺያል ማርኬት ፖስድካስታችን ስለብሮከሮች እና ስለአለምአቀፉ የፋይናንስ ተቋማት እና አደረጃጀቶቻቸው በጥልቀት በተዘጋጀ መልኩ በሌክቸር መልክ የሚቀርብበት ይሆናል። ሊያመልጣችሁ የማይገባ ላይቭ ነውና ትቀላቀሉን ዘንድ ለመጋበዝ ወደድን።
https://vt.tiktok.com/ZS9MapyRqwFLx-HWrFB/
4 717
#The_Interview
#S02E09
#With_Dr_Eyosiyas #BirrForex
The Interview የተሰኘችው ሰርክ ቅዳሜ ምሽት ከሶስት ሰዓት ጀምሮ የምናዘጋጃት የኢትዮጵያውያን ትሬደሮች የቃለመጠይቅ መድረክ በዚህ ሳምንት በኢትዮጵያ ውስጥ ፎሬክስን መስራት እና ማስተማር ከጀመሩት ግምባር ቀደም ትሬደሮች መካከል የሆነውን ዶር እዮስያስ [@BirrForex] እንግዳዋ አድርጋላችሁ ትቀርባለች። በዚህ መድረክ ከ8 አመት ያላነሰ እና በተግባርም ራሱን ያሳየን ትሬደር ልምድ እና እውቀት ለመጋራት ሁላችሁም ተጋባዥ ታዳሚዎቻችን እንድትሆኑ ጥሪያችንን አቅርበናል። በፕሮግራሙ ላይ ልታቀርቧቸው የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች በኮሜንት በኩል አጋሩን፤ በመድረኩ የናንተም ጥያቄዎች አካተን ለመቅረብ እንሞክራለን። የማቀር ፕሮግራም ነውና ቅዳሜ ምሽትን ከኛ ጋር ለማድረግ ፕሮግራማችሁን ያዙ።
መልካም ምሽት።
4 717
Session Highs & Lows (የክፍለ-ጊዜዎች ጫፎች)
- Session Highs & Lows ማለት በተለያዩ የገበያ ክፍለ-ጊዜዎች (Asian, London, New York Sessions) ውስጥ ዋጋው የደረሰበትን ከፍተኛ (High) እና ዝቅተኛ (Low) ነጥቦች ማለት ነው። በተለይ የAsian Session High እና Asian Session Low ለብዙ ባለሙያ ትሬደሮች አስፈላጊ የ Liquidity ቦታዎች ናቸው።
- ብዙ ጊዜ የለንደን ገበያ ሲከፈት ወይም የኒውዮርክ ገበያ ሲጀምር፣ ዋጋው መጀመሪያ የAsian Session High ወይም Lowን በመንካት እዚያ የተሰበሰበውን Stop Loss እና Pending Orders (Liquidity) ይሰበስባል። ከዚያም ብዙ ጊዜ ዋናውን አቅጣጫ ይጀምራል። ይህንን ሂደት Liquidity Sweep ወይም Stop Hunt በመባል ይታወቃል።
- ስለዚህ እነዚህን የSession Highs & Lows ነጥቦች አስቀድሞ በቻርት ላይ ማስመር እና ከዚያ በኋላ የMarket Structure Change (MSS/CHOCH)፣ Break of Structure (BOS) ወይም ሌሎች የመግቢያ ማረጋገጫዎችን በመጠበቅ መግባት ከፍተኛ ጥራት ያለው የግብይት ውሳኔ ለመስጠት ይረዳል። ነገር ግን Session High ወይም Low ብቻ በመመልከት መግባት ተገቢ አይደለም፤ ሁልጊዜ ከሌሎች የቴክኒካል ማረጋገጫዎች ጋር በማጣመር መጠቀም ይመከራል።✍️ Education Department 📣 Powered By: ETN Ecosystem™ 🤝 Partners: CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy ▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy
4 717
Repost from CryptoTalk-Ethiopia™🇪🇹
የፋይናንስ ግላዊነትዎን ለመጠበቅ፣ ዘመናዊ non-custodial walletዎች ለሚቀበሉት ለእያንዳንዱ ነጠላ ግብይት አዲስ public address በራሳቸው የሚያመነጩበትን (address rotation) ባህሪ ይጠቀማሉ።
እነዚህ ሁሉ አድራሻዎች ለውጭው ዓለም ፍጹም የተለያየ ቢመስሉም፣ ሁሉም በምስጢር ከእርስዎ ዋና private key ጋር የተሳሰሩ ናቸው።
ይህ መለዋወጥ የውጭ አካላት የእርስዎን የሀብት ክምችት ታሪክ በኦን-ቼይን ላይ ለመከታተል በጣም አስቸጋሪ ያደርግባቸዋል።
Read the full Article... 👇
🔗 Link - The Ultimate Wallet Blueprint
Freedom, Storage, and the Power if Self-Custody
4 717
The Gambler's Fallacy (የቁማርተኛው የተሳሳተ እምነት)
The Gambler's Fallacy በሳይኮሎጂ ውስጥ የሚታወቅ የአእምሮ ስህተት (Cognitive Bias) ሲሆን፣ ቀደም ሲል የተከሰቱ ውጤቶች የሚቀጥለውን ውጤት እንደሚወስኑ የሚያስብ የተሳሳተ እምነት ነው። በትሬዲንግ ውስጥ ይህ ስህተት ብዙ ጊዜ የተሳሳተ የውሳኔ አሰጣጥን ያስከትላል።
ለምሳሌ፣ አንድ ትሬደር በተከታታይ ሦስት ወይም አራት ትሬዶችን ከተሸነፈ በኋላ "አሁንማ የግድ ማሸነፍ አለብኝ" ብሎ ሊያስብ ይችላል። በተመሳሳይ ሁኔታ ደግሞ በተከታታይ ብዙ ጊዜ ካሸነፈ "አሁን መሸነፌ አይቀሬ ነው" በማለት ሊያስብ ይችላል። ሁለቱም አስተሳሰቦች በዕድል ላይ የተመሠረቱ የተሳሳቱ ግምቶች ናቸው።
እውነታው ግን እያንዳንዱ ትሬድ ራሱን የቻለ ክስተት (Independent Event) ነው። ቀድሞ የተገኘው ውጤት ቀጣዩን ውጤት አይወስንም። የሚቀጥለው ትሬድ ትርፍ ወይም ኪሳራ የሚያስገኝ መሆኑ በገበያው ሁኔታ፣ በተጠቀሙበት ስትራቴጂ እና በሪስክ አስተዳደር ላይ የተመሠረተ ነው፤ በቀድሞ ውጤቶች ላይ አይደለም።
ይህንን የአእምሮ ስህተት የሚያጋጥማቸው ትሬደሮች ብዙ ጊዜ በስሜት ተነስተው ውሳኔ ይሰጣሉ፣ ያለ ጥራት ያለው ሴትአፕ ትሬድ ይገባሉ፣ የሎት መጠናቸውን ያለምክንያት ይጨምራሉ እንዲሁም ከትሬዲንግ ፕላናቸው ውጭ እርምጃ ይወስዳሉ።
ስለዚህ Professional ትሬደር እያንዳንዱን ትሬድ እንደ አዲስ እድል ይመለከታል። የቀደመው ትርፍ ወይም ኪሳራ ቀጣዩን ውሳኔ እንዲቆጣጠር አይፈቅድም። የትሬዲንግ ውሳኔዎች ሁልጊዜ በስትራቴጂ፣ በዲሲፕሊን እና በትክክለኛ የሪስክ አስተዳደር ላይ መመስረት አለባቸው፣ እንጂ በተከታታይ ትርፍ ወይም ኪሳራ ላይ አይደለም።✍️ Education Department 📣 Powered By: ETN Ecosystem™ 🤝 Partners: CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy ▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy
4 717
Confirmation Bias (የራስን ሃሳብ ብቻ የመደገፍ ወጥመድ)
ትሬዲንግ ላይ ትልቁ ጠላትህ ቻርቱ ሳይሆን የገዛ አዕምሮህ ሊሆን ይችላል። Confirmation Bias የሚከሰተው አንድን ማርኬት ለመግዛት (Buy) ወይም ለመሸጥ (Sell) አስቀድመህ ስትወስንና አዕምሮህ ያንን ውሳኔህን የሚደግፉ ምልክቶችን ብቻ መርጦ ማየት ሲጀምር ነው።
ወጥመዱ እንዴት ይሰራል?
1. አድልዎ (Bias)፦ ቻርቱን ገና ስትከፍተው "ይሄ ማርኬት Buy መሆን አለበት" ብለህ ታስባለህ።
2. ምርጫ (Selective Attention)፦ አዕምሮህ ያሰብከውን የሚደግፉ ምልክቶችን ብቻ (ለምሳሌ፡ የSupport ዞን መኖር ወይም አንድ አረንጓዴ ካንድል) ፈልቅቆ ያወጣል።
3. አይን መጨፈን (Ignoring Risks)፦ በሌላ በኩል ማርኬቱ ሊወርድ እንደሚችል የሚያስጠነቅቁትን ግልፅ ምልክቶች (ለምሳሌ፡ የBearish አወቃቀር፣ የResistance መጣስ አለመቻል ወይም የTrendline ስብራት) ሆን ብለህ እንዳላየህ ትሆናለህ።
ባጭሩ፦ ማርኬቱ የሚነግርህን እውነታ ሳይሆን፣ አንተ ማየት የምትፈልገውን ምስል ብቻ በቻርቱ ላይ ታያለህ።አደጋው ምንድን ነው? ይህ ወጥመድ ያለ ምንም ጥንካሬና ያለ ስትራቴጂህ ህግጋት ትሬድ ውስጥ እንድትገባ ያደርግሃል። ውጤቱም ማርኬቱ አንተ ወደፈለግከው ሳይሆን ወደ እውነተኛው አቅጣጫ ሲሄድ ትልቅ ኪሳራ (Stop Loss መመታት) ያስከትላል። እንዴት እንከላከለው? • ተቃራኒውን ፈልግ (Devil's Advocate)፦ ለምሳሌ Buy ለማድረግ ካሰብክ፣ ትሬዱን ከመግባትህ በፊት "ይሄ ትሬድ ሊከስር የሚችልበት 3 የSell ምክንያቶች ምንድን ናቸው?" ብለህ ራስህን ጠይቅ። • በህግ ተመራ (Rule-Based)፦ በስሜት ወይም በግምት ሳይሆን፣ በChecklist (የስትራቴጂህ መስፈርቶች) ሙሉ በሙሉ እስኪሟሉ ድረስ ብቻ ታገስ።
ማርኬትን ለማሸነፍ መጀመሪያ የራስን አዕምሮ ወጥመድ ማወቅ ይቀድማል።ል።✍️ Education Department 📣 Powered By: ETN Ecosystem™ 🤝 Partners: CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy ▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy

3. አይን መጨፈን (Ignoring Risks)፦ በሌላ በኩል ማርኬቱ ሊወርድ እንደሚችል የሚያስጠነቅቁትን ግልፅ ምልክቶች (ለምሳሌ፡ የBearish አወቃቀር፣ የResistance መጣስ አለመቻል ወይም የTrendline ስብራት) 🙈 ሆን ብለህ እንዳላየህ ትሆናለህ።
ባጭሩ፦ ማርኬቱ የሚነግርህን እውነታ ሳይሆን፣ አንተ ማየት የምትፈልገውን ምስል ብቻ በቻርቱ ላይ ታያለህ።አደጋው ምንድን ነው? ይህ ወጥመድ ያለ ምንም ጥንካሬና ያለ ስትራቴጂህ ህግጋት ትሬድ ውስጥ እንድትገባ ያደርግሃል። ውጤቱም ማርኬቱ አንተ ወደፈለግከው ሳይሆን ወደ እውነተኛው አቅጣጫ ሲሄድ ትልቅ ኪሳራ (Stop Loss መመታት) ያስከትላል። 📉 እንዴት እንከላከለው? • ተቃራኒውን ፈልግ (Devil's Advocate)፦ ለምሳሌ Buy ለማድረግ ካሰብክ፣ ትሬዱን ከመግባትህ በፊት "ይሄ ትሬድ ሊከስር የሚችልበት 3 የSell ምክንያቶች ምንድን ናቸው?" ብለህ ራስህን ጠይቅ። 🧐 • በህግ ተመራ (Rule-Based)፦ በስሜት ወይም በግምት ሳይሆን፣ በChecklist 📋 (የስትራቴጂህ መስፈርቶች) ሙሉ በሙሉ እስኪሟሉ ድረስ ብቻ ታገስ።
ማርኬትን ለማሸነፍ መጀመሪያ የራስን አዕምሮ ወጥመድ ማወቅ ይቀድማል።ል።✍️ Education Department 📣 Powered By: ETN Ecosystem™ 🤝 Partners: CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy ▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy
4 717
ሰላም እንዴት ናችሁ ጋይስ ፡
በዛሬው ምሽት ፕሮግራማችን አንድ ፕሮፌሽናል ትሬደር ሊኖረው የሚገብውን ትክክለኛ ማንነት እና ባህሪያት ነጭ ነጩን ከሙያው አንፃር የምናወራበት መድረክ ይሆናል። ለመሆኑ ትክክለኛ ትሬደሮች ናችሁ? እስቲ ኑና ራሳችሁን ፈትሹ። ላይቩን ተቀላቅላችሁ እንድንማማር ልንጋብዛችሁ ወደድን።
https://vt.tiktok.com/ZS9MBnewKn3mY-0rz0z/
4 717
VIX ምንድን ነው?
VIX የCBOE Volatility Index ምህጻረ ቃል ነው። ይህ መረጃ ጠቋሚ (Index) የሚለካው የአሜሪካን የአክሲዮን ገበያ (S&P 500) ለሚቀጥሉት 30 ቀናት የሚኖረውን የዋጋ መዋዠቅ (Volatility) የሚጠብቁትን የኢንቨስተሮች ግምት ነው።
📉 ገበያው ሲረበሽ፡ VIX ምን እያለዎት ነው?
ብዙ ትሬደሮች የዋጋ መዋዠቅ ሲፈጠር ግራ ይገባቸዋል። ነገር ግን በገበያው ውስጥ ያሉ "ትልልቅ ባለሀብቶች" ስሜት የሚለካበት መሳሪያ እንዳለ ያውቃሉ?
VIX በትክክል ምንድን ነው?
የፍርሃት መለኪያ፡ VIX በገበያ ውስጥ ያሉ ባለሀብቶች ምን ያህል ፍርሃት ወይም ስጋት ውስጥ እንዳሉ የሚያሳይ መለኪያ ነው።
የዋጋ መዋዠቅ ምልክት፡ ይህ መለኪያ ሲጨምር፣ በገበያ ውስጥ ያልተረጋጋ የዋጋ እንቅስቃሴ (Price Volatility) እንደሚኖር ያሳያል።
ለምን ለትሬዲንግ ወሳኝ ነው?
በቀላሉ ለመረዳት፣ VIX በጨመረ ቁጥር ገበያው በአደገኛ ሁኔታ መዋዠቁን ያሳያል። ይህንን መረጃ በመጠቀም፦
1. ስጋትን መቆጣጠር፡ ገበያው ሲረበሽ የትሬዲንግ መጠንዎን ማስተካከል ይችላሉ።
2. የተሻለ ትንተና፡ የገበያውን ስሜት (Sentiment) በማወቅ፣ አላስፈላጊ ኪሳራን መቀነስ ይቻላል።
ማጠቃለያ:- ስለዚህ፣ በሚቀጥለው ጊዜ ትሬድ ሲያደርጉ የገበያውን "የሙቀት መጠን" ወይም ፍርሃት ለመለካት የVIXን አመልካች መመልከት አይርሱ።የገበያውን ስሜት (Market Sentiment) መረዳት ማንኛውም ስኬታማ ትሬደር ሊኖረው የሚገባ ክህሎት ነው። VIX ሲያድግ፣ ገበያው ያልተረጋጋ መሆኑን በመረዳት የትሬዲንግ ስልታችንን ማስተካከል እንችላለን።✍️ Education Department 📣 Powered By: ETN Ecosystem™ 🤝 Partners: CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy ▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy
4 717
ነጋድራሱ ቅፅ ፪ ነገ ሀምሌ 1 2018 ዓም በጉጉት ሲጠብቋት ለነበሩ አንባቢዎች ለገበያ ትቀርባለች።
ሰላም ጋይስ እንዴት ናችሁ ፡
ነጋድራሱ ቅፅ ሁለት መፅሀፍ ከነገ ሀምሌ 1, 2018 ዓም ጀምሮ ለገበያ የምትቀርብ ሲሆን በ24 ሰዓታት ውስጥ ለሚገዙ አንባቢያን የ50% ቅናሽ ስለሚኖራትም ይህቺን ለመጀመሪያ ጊዜ በአማርኛና አገር በቀል በሆነ ሁነት የተዘጋጀች የትሬዲንግ ሳይኮሎጂ መፅሀፍ ሁላችሁም መግዛት የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እወዳለው።
እንደተለመደው ባዘጋጀነው ቦት አማካኝነት ከነገ ጠዋት ጀምሮ ማግኘት የምችትሉ ይሆናል። ቦታችን ፡- https://t.me/thenegedrasbot
እውነት ለመናገር በነፃም ብሰጣችሁ ደስ ባለኝ ነበር። ነገር ግን በጊዜ ሂደት የተረዳሁት ነገር ምንም ነገር በነፃ ከቀረበ ዋጋውን ያጣል። በዚህ የመፅሀፍ ስራ ጉዞ በጣም ብዙ ድካምና ጊዜን ወስጄበታለው። እንደተለመዱት ስራዎቼ ወይም ፅሁፎቼ ሁሉም በነፃ ሊያገኛቸው በሚል ሊሰጣቸው የሚገባው ቦታ ሊያንስ አይገባውም የሚል እምነት ያለኝ በመሆኑም፤ በተጨማሪም በጣምምምምም ለረጅም ጊዜ በነፃ ትምህርትን በሰጠሁበት ሁነት ያን ያህል ቦታ እንዳይሰጣቸው ሆኖ አልፏልና ያንን ላለመድገም ስል ይህንን ዋጋ ላወጣበት ተገድጃለው። I hope እንደምትረዱኝ ተስፋ አለኝ።
መፅሀፉ ከአንደኛው ቅፅ እጅጉን በበለጠና በተደራጀ መልኩ የተዘጋጀ፤ የበዙ መረጃዎችን አጭቆ የያዘ እና በተለይ ከአዕምሮዋችን ጋር በተያያዘ በጣምምምምም ብዙ ለውጦችን እንድታዩበት ተደረጎ የተዘጋጀ፤ 15 ምዕራፎችን በ5 ክፍሎች በማደራጀት ተግባራዊ የትሬዲንግ ሳይኮሎጂ መፍትሄዎችንም በብዛት በመያዝ በ162 ገፆች ተጠናቅሮ የቀረበ መድብል ነው።
መልካም ንባብ።
4 717
Retail Sales (የችርቻሮ ሽያጭ ሪፖርት)
የችርቻሮ ሽያጭ (Retail Sales) ሸማቾች በየወሩ የሚያወጡትን አጠቃላይ የገንዘብ መጠን የሚለካ ኢኮኖሚያዊ መረጃ ነው። ፕሮፌሽናል ትሬደሮች የገበያውን የረጅም ጊዜ አቅጣጫ ለመተንበይ የሸማቾችን የግዢ አቅም እና የሴንትራል ባንኮችን ቀጣይ እርምጃ በዚህ ሪፖርት ይገመግማሉ።
1. የሪፖርቱ ተፅዕኖ በገንዘብ ዋጋ ላይ
ሪፖርቱ ጨምሮ (Positive) ሲወጣ ህዝቡ በብዛት እየገዛ መሆኑንና የኢኮኖሚ እድገት መኖሩን ያሳያል። ይህም የሀገሪቱን ገንዘብ (ለምሳሌ ዶላርን) ያጠናክራል።
ሪፖርቱ ቀንሶ (Negative) ሲወጣ የሸማቾች የግዢ አቅም እንደቀነሰ እና የኢኮኖሚ መቀዝቀዝ ምልክት መሆኑን ያሳያል። ይህም የሀገሪቱን ገንዘብ ያዳክማል።
2. ከሴንትራል ባንክ (Interest Rate) ጋር ያለው ቁርኝት
የችርቻሮ ሽያጭ በቀጥታ ከዋጋ ንረት (Inflation) እና ከወለድ ምጣኔ (Interest Rate) ጋር ይገናኛል።
ሽያጩ በጣም ከናረ፣ Inflation ይጨምራል፤ ሴንትራል ባንኩም Inflationን ለመቆጣጠር የወለድ ምጣኔን ይጨምራል። በዚህ ምክንያት የሀገሪቱ ገንዘብ ዋጋ ይጠናከራል።
ሽያጩ በጣም ከቀነሰ፣ የንግድ እንቅስቃሴ ይቀዘቅዛል፤ ሴንትራል ባንኩም ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት የወለድ ምጣኔን ይቀንሳል። በዚህ ምክንያት የሀገሪቱ ገንዘብ ዋጋ ይወርዳል።
የባለሙያ ምስጢር ጀማሪ ትሬደሮች በዜናው ሰዓት በሚፈጠረው ጊዜያዊ መዋዠቅ (Volatility) ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፤ ፕሮፌሽናል ትሬደሮች ግን ይህ ሪፖርት በሴንትራል ባንኩ ቀጣይ የወለድ ምጣኔ (Interest Rate) ውሳኔ ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ አስቀድመው በመገምገም ከትልልቅ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በአንድ አቅጣጫ ይሰለፋሉ።✍️ Education Department 📣 Powered By: ETN Ecosystem™ 🤝 Partners: CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy ▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy
4 717
ICE ኢንተርቪው ዝግጅታችን እስካሁን አቅርበን በማናውቀው ሁነት የሚካሄድን ከኳንት ትሬደር ጋር የሚደረግ ቆይታ እናረጋለን። ከPips pay my Bills ጋር የምናደርገውን ቆይታ የቀጥታ መድረክ ትሳተፉበት ዘንድ ጋብዘናቹሀል።
https://vt.tiktok.com/ZS9MFE1PVuqLW-LLuWv/
4 717
Inducement vs Real Breakout (ማታለያ ወይስ እውነተኛ ስብራት?)
ብዙ ትሬደሮች የሚያጡት ስትራቴጂ ስለሌላቸው ብቻ አይደለም፤ የገበያውን ዓላማ (Market Intention) ስለማይረዱ ነው። ገበያው በቀጥታ አይንቀሳቀስም፤ ከመንቀሳቀሱ በፊት Liquidity ይሰበስባል፣ ይህም Liquidity በአብዛኛው የትሬደሮች Stop Loss ነው።
Inducement (ማታለያ) ማለት ገበያው አቅጣጫውን የቀየረ እንዲመስል በማድረግ ትሬደሮችን ወደ የተሳሳተ ግብይት የሚያስገባ የሐሰት እንቅስቃሴ ነው። በአብዛኛው ትሬደሮች Breakout አይተው ወደ ግብይት ይገባሉ፣ Stop Loss በKey Levels ላይ ይሰበሰባል፣ Smart Money Liquidity ይሰበስባል፣ ከዚያም በኋላ እውነተኛው የገበያ አቅጣጫ ይጀምራል።
በሌላ በኩል Real Breakout (እውነተኛ ስብራት) የሚፈጠረው Liquidity ከተሰበሰበ በኋላ Structure (HH/HL/LH/LL) ሲሰበር፣ በኃይለኛ Momentum ሲንቀሳቀስ እና ገበያው አዲስ አቅጣጫ ሲይዝ ነው። ይህንን BOS (Break of Structure) ብለን እንጠራዋለን።
ማታለያን ከእውነተኛ Breakout ለመለየት ሦስት ነገሮችን በተለይ ተመልከት። መጀመሪያ Candle Close፤ Wick ብቻ አልፎ ከተመለሰ Liquidity Sweep ሊሆን ይችላል፣ Full Body Close ግን ከዞኑ ውጭ ከተዘጋ Real Breakout የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። ሁለተኛ Key Zone፤ Supply/Demand ወይም Order Block ሳይነካ Breakout ከተፈጠረ በጥንቃቄ ተመልከት። ሶስተኛ Market Timing፤ በLondon Killzone እና New York Open ወቅት የሚፈጠሩ ድንገተኛ እንቅስቃሴዎችን ሁልጊዜ በጥንቃቄ ተከታተል።
Golden Rule "ገበያው ከመሄዱ በፊት Liquidity ይፈልጋል።" ስለዚህ ማታለያውን ማየት ካልቻልክ፣ ማታለያው አንተን ራስህን ዒላማ ሊያደርግህ ይችላል።✍️ Education Department 📣 Powered By: ETN Ecosystem™ 🤝 Partners: CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy ▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy