es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
4 256
Suscriptores
-824 horas
+887 días
+1 19430 días
Archivo de publicaciones
"እኛ አቅቶናል እያለቅን ነው '' አለ የጦር ጄነራሉ የብልጽግና ወንበር ጠባቂ ሰራዊት መሪ ተብየው ብ/ጀኔራል አዲሱ ማህመድ በከባድ መሳሪያ ጋጋታ ታጅቦ በጎጃም መራዊ ከተማ በመገኘት ልመና አይሉት
"እኛ አቅቶናል እያለቅን ነው '' አለ የጦር ጄነራሉ የብልጽግና ወንበር ጠባቂ ሰራዊት መሪ ተብየው ብ/ጀኔራል አዲሱ ማህመድ በከባድ መሳሪያ ጋጋታ ታጅቦ በጎጃም መራዊ ከተማ በመገኘት ልመና አይሉት ምሬት ሲናገር ተደምጧል። ጄነራሉ በቆይታው "እኛ አቅቶናል እያለቅን ነው፡ እባካችሁ በሕብረት ውጡና አግዙን" ሲል ሕዝቡን ተማፅኗል።

የድል ዜና! የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር በዛሬው ዕለትም በጠላት ላይ ታላቅ ድልን ተጎናጽፏል። ታኅሳስ 16/2018 ዓ.ም የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር በዛሬው ዕለትም በጠላት ላይ  ታላቅ ድልን ተጎናጽፏል። ዘራፊና ጨፍጫፊ የሆነው የብልጽግና ወራሪ ሠራዊት ከሞት የተረፈ ግብስብስ ሠራዊቱን በመያዝ ወደ ማርዘነብ ታዳጊ ከተማ ባቀናበት ጀግኖቹ የ14ኛ ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት ማለትም የአንበሳ ደቦሎቹ የቀስተ ደመና ሻለቃ ፋኖዎች፣ ነበልባሎቹ የክፍለ ጦሩ ኮማንዶዎችና የክፍለ ጦሩ ጥምር ጦር አባላት   በሌሊት በመግባት ጠላትን በእሳት ሰይፋቸው ሲቀስፉት አርፍደዋል። በጠላት ዙ-23 የታገዘው ውጊያ በጀግኖቹ የፋኖ ሠራዊት አባላት የጨበጣ ተኩስ የበላይነት የታየበት ሲሆን በጠላት ላይ በርካታ ኪሳራን አድርሷል። እንደ አበደ ውሻ እዚህም እዚያም እየተክለፈለፈ፤ ያገኘው ሁሉ የሚገርፈው የታሪካውያን ጠላቶቻችን ቀኝ እጅ የሆነው የብልጽግና ወራሪ ሠራዊት የጀግኖቹን ምድር እንደዋዛ የሚረግጣት አልሆነም፤ ስም አጠራሩ የጠላትን ልቡና በሚያርበደብደውና ብልት ለይቶ በሚመታው ጀግና ሠራዊታችን የእሳት በትር እየተገረፈ ምድሪቷ   ብልት ለይቶ በሚመታው ጀግና ሠራዊታችን የእሳት በትር እየተገረፈ ምድሪቷ ገሃነም ሆናበት እንደ እሳት እራት እርር ኩምትር እያለ ቀረ እንጅ። በሌሊት በተጀመረው ውጊያ በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ኃይል የተቀጠቀጠ ሲሆን ጠላት አስከሬኑንና ቁስለኛውን ሲጎትት ውሏል። በውጊያውም   አንድ አይሱዙ  አስከሬን ተነስቷል፣   03 አምቡላንስና 03 ፓትሮል ቁስለኛ የተነሳ ሲሆን ከዚህም መካከል 03 አምቡላንስ ቁስለኛ ሆስፒታል ገብቷል፤ ሶስት ፓትሮል ቁስለኛ ደግሞ በራሱ (በጠላት) ካምፕ ለመታከም ገብቷል። ድል ለአማራ ፋኖ! ክብር ለሰማዕታቱ! ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት!​

በዚህ መግለጫ መሰረት ፖለቲከኛው ማነው? አቶ ወርቁ?ወይስ አግምማስ? አግማስ የተሰኘ በጎ አድራኦት ድርጅት ለተፈናቃዮች እያደረገ ባለው የእርዳታ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ከአቶ ወርቁ ዓይተነው የተለገሰውን 15 ሚሊዮን ብር አልቀበልም በማለት ይህን መግለጫ አውጥቶ ዐየሁ። የአቶ ወርቁን ድጋፍ የማይቀበለውም፤ ከፖለቲካ ጋር ይገናኝብኛል በማለት እንደሆነም ገልጿል። -የበጎ አድራጎት ድርጅቱ አመራሮች እዚህ ላይ ሰብዓዊ እርዳታን ከፖለቲካ ጋር እንዴት እንደቀላቀሉት ባይገባኝም ፤ ከዚህ መግለጫ በመነሳት "ፖለቲከኛው ማነው?"የሚል ጥያቄ እንድናነሳ እንገደዳለን። እዚህ ላይ የፖለቲካ አቋም የያዙት አቶ ወቁ ናቸው? ወይስ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ አመራሮች? -እስካሁን የፖለቲካ ፓርቲ ስለመሆናቸው በግልጽ ከማይታወቀው ከአቶ ወርቁ የተለገሰውን ድጋፍ የገፉት የድርጅቱ አመራሮች፤ ከብልጽግና ፓርቲ ድጋፍ ቢሰጣቸው ኖሮ ይገፉት ነበር ወይ? -(ለወደፊቱ በምታደርጉት የእርዳታ ማሰባሰብስ ግንዛቤው እንዲኖረን) ሰዎች ተርበው "ድረሱልን!" እያሉ በሚማጸኑበት ሰዓት በእናንተ በኩል ለሰብዓዊ ጥሪ ምላሽ መስጠት ያለባቸውን እና የሌለባቸውን አካላት በዝርዝር ልታሳውቁን ትችላላችሁ? ይህን ጥያቄ ያነሳሁት ነገሩ ስለገረመኝ ነው እንጂ፤ በርካታ እርዳታ አሰባሳቢ ድርጅቶችና ግለሰቦች በሞሉበት ሰዓት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ "ከእነ እገሌ የሚሰጠንን አንቀበልም" የሚል የፖለቲካ አቋም ከያዘ ድርጅት ጋር በግድ "ገንዘብ ተቀበሉ" የሚል ሙግት ውስጥ ለመግባት አይደለም። የአቶ ወርቁም ሆነ የሌሎች ሰዎች ድጋፍ በተገቢው መንገድ ለተፈናቃዮቹ ይደርሳል። በዚህ መግለጫ ላይ ፖለቲከኛ ሆኖ ያገኘሁት አግማስን እንጂ አቶ ወርቁን አይደለም። በተለይ በብዙሀኑ ተሰሚነት ያላችሁ ሰዎች ለምታደርጉትና ለምትሉት ነገር ከፍ ያለ ጥንቃቄ አድርጉ። ይህም ያልፋልና!

ጥቆማ .... ይህ ከታች በአገዛዙ የሚዲያ ሰራዊት የሚራወጥ ፎቶ የፋኖ የህክምና ቦታ እና ቃታ መሳሪያዎች  ብርሸለቆ ማሰልጠኛ የሚገኝ ቦታ ሲሆን የፋኖ የህክምና ቦታ የተባለው ግራውንድ ግንባታ ብርሸለቆ ማሰልጠኛ ዋጠው በመባል የሚታወቅ እስር ቤት  አባል ሲያጠፋ የሚቀጣበት ቦታ ነው  መሳሪያዎቹ ምልምል ሰልጣኞች የሚሰልጥኑበት ሰባራ መሳሪያዎች ናቸው ::   አገዛዙ በተደጋጋሚ መኪና ሲጋጭም በጋንቤላም የጎሳ ግጭትም ሲነሳ ፅንፈኛው በፈጠረው ግርግር የሚል የውሸት መረጃወች እንዲሰራጩ እና በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በሌሎች ብሔሮች እንዲሳደዱ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል ::  በመሆኑም መላው የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የትግሉ ደጋፊወች ነገሮችን በትኩረት እንድትፈትሹ እያልን ... የብልፅግና መሬት ላይ የሌለን የውሸት የሚዲያ ስርጭት   በማጋለጥ እንድታግዙን  ማለት እንወዳለን :: መሳሰቢያ ፦ ማነኛውም ከአገዛዙ የሚዲያ ሰራዊት የውሸት ፕሮፖጋንዳ አገዛዙ በሚያደርገው የአማራ ሕዝብ የዘር ማጥፋት ወንጀል በቀጥታም ይሁን  በተዘዋዋሪ ተሳታፊ ላለመሆን ራሳችሁን ጠብቁ  ❗️❗️❗️

የያዝነው የህልውና ትግል እንጅ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የሚያልቅ ተራ የሰፈር ጫወታ አይደለም። አይደለም ሺ ሆነን እልፍ ትጥቅ ታጥቀን ቀርቶ ያኔም አንድ ክላሽ ይዘን በሷ እያስፈራራን በገጀራ እና መጥረቢያ
የያዝነው የህልውና ትግል እንጅ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የሚያልቅ ተራ የሰፈር ጫወታ አይደለም። አይደለም ሺ ሆነን እልፍ ትጥቅ ታጥቀን ቀርቶ ያኔም አንድ ክላሽ ይዘን በሷ እያስፈራራን በገጀራ እና መጥረቢያ ታንክ እና ዙ 23 ስንገጥም አልፈራንም።ምንም ያህል ትግሉ ጎምዛዛ ቢሆንላንጨርስ አልጀመርንም እና እናሸንፋለን ። ወደፊት ብቻ 💪💪💪 የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ላስታ አስምነው ኮር አዛዥ አርበኛ ወድሙ ማሩ!!!

በምዕራብ ዐምሓራ ቀጠና በፋኖ ቁጥጥር ስር በሚገኙ አከባቢዎች ላይ ተከታታይ የሆነ የድሮን ቅኝት እየተደረገ ነው።  ዛሬ ታህሳስ 16/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ በደምበጫና በአከባቢው፣ በማቻከል፣ በደብረ ኤልያስና በአከባቢው እንዲሁም በሌሎች የምዕራብ ዐምሓራ ቀጠናዎች ተከታታይ የሆነ የድሮን ቅኝት እየተደረገ ነው። አገዛዙ በርከት ያለ የሰዎች ስብስብ ካገኘ ጥቃት ከመፈፀም ወደኋላ እንደማይል ከዚህ ቀደም በፈፀማቸው ጥቃቶች ያሳየ ሲሆን፡ ስለሆነም ማሕበረሰቡ እንደ ገበያና የሐይማኖት ስፍራዎች እንዲሁም መሠለ መሰባሰቢያ ስፍራዎች ላይ ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ምንጮቻችን አሳስበዋል።

እንደ ቸጉቬራ ከህክምና ሙያ ወደ ጫካ ለነፃነት ያመራው የጎንደሬ በጋሻው ጀግና ቸ ጉቬራ  ማን ነው ? አርበኛ አዝመራው ካፒታል  ከአባታቸው ከአቶ ካፒታል ታረቀኝ እና ከእናታቸው ወ/ሮ የሮም ደረጀ መጋቢት 27 ቀን በ1980 ዓ/ም በለምለሟ ጣቁሳ ወረዳ በቅመማ ቅመም ታጅቦ  አቸራ ጋላየ ቀበሌ ተወለደ። የልጅነት እድሜውን በደንቢያ ሜዳ እንደ እንቦሳ እየፈረጠጠ ትምህርቱን  ደግሞ እሰይ ደብር ፣ ጎይ እና ደልጊ  ት/ቤት እያለ ዘልቆ በክኒኒካል ነርሲንግ በጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  እና በጎንደር በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ ሲሆን በሙያው  ህብረተሰቡን  ከገጠር ጤና ጣቢያወች እስከ ሆስፒታሎች  ድረስ  ለአስራ አንድ አመታት በቀንነት ፣በግልፀኝነት ፣በታማኝነት ፣ስራውን አክብሮ ሲያገለግል ቆይቷል ። የህልውና ውጊያው ሲጀመር ይሰራበት ከነበረው አርባያ ሆስፒታል  ወደ ወልቃይት በመዝመት በማዕከላዊ ጎንደር የጤና ቢሮ  ትዛዝ  ከሌሎች  ባለሙያዎች  ጋር በመሆን ተዘግቶ የነበረውን የወልቃይት ሆስፒታል በማስከፈት በርካታ  ቁስለኞችን ከቆራሪት ፣ከማይጋባ፣ ከዛሪማ  ፣ከሱር ካም ፣ ከአዲጎሹ ፣ከሁመራ  ድረስ በአምቡላንስ በመንቀሳቀስ  ቁስለኛችን እና  በሌሎች በሽታዎች የሚጠቁ በሽተኞችን በማከም  ህይዎት ታድጓል ። አርበኛ አዝመራው የአማራ ፋኖ ትግል ጎንደር ከተማ ላይ ሀምሌ 27 ቀን 2015 ዓ/ም ሲፈነዳ ለአስራ አንድ አመት አብረውት የዘለቁትን ጓንትና ሲሪንግ ወርውሮ ፣ ቤትና ትዳሩን ጥሎ ፣ ጮማና ማሩን ንቆ በምትኩ ክላሽ አንግቦ ፣ኮቸሮ ቋጥሮ፣ ጫካ ነው ዘመዴ በማለት  ከፊት  መሪ ሁኖ  ከምዕራብ በለሳ ዋና ከተማ አርባያ 50  የሚሆኑ አርበኞችን በማስተባበር ጉዞን  ጎንደር ከተማ በማድረግ  የአገዛዙን ስርዓት ከሌሎች የፋኖዎች ጋር ሁኖ መፋለም  ጀመረ አስጀመረ። አርበኛ አዝመራው  ቁር እና ብርድ ፣ ድንጋይና አፈር ላይ መተኛት  ፣እርሃብ እና ውሃ ጥም ሳይበግሩት  ባንክና ታንክ ያለውን ስርዓት እየተፋለመ እንደ እንቧይ ካብ መናዱንና ማፍረሱን ቀጥሎበታል  ። አርበኛ አዝመራው የፋኖ ሻለቆችና ብርጌዶች ሲመሰረቱ በመስራችነት የተሳተፈ ሲሆን መብረቅ ብርጌድን ከአርበኛ ያለው አዱኛ ጋር በመሆን፣ የዳግማዊ ቴውድሮስ ብርጌድን ከአርበኛ ሚናስ አለማየሁ ጋር በመመስረት ለረጅም ጊዜ የብርጌዷ ምክትልና ዋና አዛዥ በመሆን ወደ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አመራርነት እስኪመጣ ድረስ መርቷል። በዚህ ወቅት  በርካታ ጀብዶችንና ድሎችን  በጎንደር ፣ በማክሰኝት ፣በአርባያ በለሳ፣በኪንፋዝ በገላ፣ በወርአህላ፣ በሮቢት በገላ፣ በቁልቋል በር  ፣ በግራኝ በር፣ በባንዴራ ጎጥ፣ በአይባ ፣ በአምባጊወርጊስ እና በሌሎች አውደ ውጊያዎች  ጠላትን  ደምሷል፣ ማርኳል ፣ታጥቋል አሸንፏል። በነጭ ጋወን የደመቀባትን አርባያ ከተማ በብሬንና በክላሽ በተደጋጋሚ ጎብኝቷታል፣ አርበኛው አርባያ ከተማ  ሲገባ  ከህዝብ በተዘረፈ ሀብት ቦርጫቸው ያበጠው አመራሮች  መውጫ መግቢያ ጠፍቷቸው  እንደ ታላቁ ሩጫ በጀምላ ከአርባያ ደጎማ በመሮጥ ኩምሽሽ ጭብጥ ብለው መከላከያ ካምፕ ውስጥ ተደብቀው ነብሳቸውን  ያተርፋሉ ጀግና ፊት የሚቆም ሌባና የለም ። አርበኛ አዝመራው ካፒታል አሁን ላይ የግዙፋ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ በመሆን በቀጠናው የፋኖን አደረጃጀት  በማዘመንና በማስፋት ሁሉም በቻለው  ለነፃነት አስተዋፅኦ በማድረግ አገዛዙን አሽቀንጥሮ እንዲጥል እያደረገ ይገኛል። ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በሚያስተዳድረው ቀጠና  የሚነሱ  የዲሞክራሲ ፣የፍትህ፣የነፃነት፣የእኩልነት እና የአንድነት  ጥያቄዎችን ፣ በመፍታት ህዝቡ ዘመናዊ  አስተዳደርን እንዲለማመድ እያደረገ ይገኛል። አርበኛ አዝመራው እንደ አርጀንቲናዊዩ የነፃነት ታጋዩ ቸጉቬራ  ከህክምና ሙያው እና ከተደላደለ ኑሮው  ወደ ጫካ  ለነፃነት  የወጣ በመሆኑ አድናቂዎቹ የጎንደሬ  በጋሻው ቸጉቬራ ይሉታል ። ቸጉቬራ ኩባን ጨምሮ ሌሎች ሰባት ለሚደርሱ ሀገራት ነፃነት እንደተዋደቀው ሁሉ  አርበኛ አዝመራው/ጎንደሬው ቸጉቬራ  /  የአማራን ህዝብ ከተከፈተበት ሁለንተናዊ  የጥፋት ዘመቻ  ነፃ ያወጣ ይሆን አብረን እናያለን።    ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!! በአርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ   ተህሳስ /2018 ዓ/ም

በዳባት ዙሪያ ውጊያ ጠ*ላ*ት ኪ*ሳ*ራ ደረሰበት!! ዘራይ ክ/ጦርና ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦሮች የተወጣጡ ሸጋው ውበትና ይታየው ብርጌዶች በዳባት ከተማ ዙሪያ ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም የአርሶ አደር የ
+1
በዳባት ዙሪያ ውጊያ ጠ*ላ*ት ኪ*ሳ*ራ ደረሰበት!!      ዘራይ ክ/ጦርና ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦሮች የተወጣጡ ሸጋው ውበትና ይታየው ብርጌዶች በዳባት ከተማ ዙሪያ ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም የአርሶ አደር የጦር መሳሪያ ለመዝረፍ ተሰማርቶ የነበረን የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት በመፋለም ባደረሱበት ብርቱ ክንድ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል። *የተ*ደ*መ*ሰ*ሰ  31 *የቁስለኛ  የቆሰለ 55 *የተ*ማ*ረ*ከ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ 16     ከ4ኛ ደጃዝማች  ኮር ዘራይ ሸጋው ብርጌድ ከ5ኛ ዳ/ቴዎድሮስ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ይታየው ብርጌድ በዳባት ዙሪያ በተለይም ቀረሃ በተባለ ቦታ የዓብይ ፋሽስታዊ ሰራዊትን በመምታት ቀሪው ነብሱን ለማትረፍ ወደ ዳባት ሸሽቶ መግባቱ ይታወቃል።            ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!                           አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ              ህ/ግንኙነት መምሪያ

‎ ‎በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም  ፪ኛ ኮር ኃይለ ማርያም ማሞ ክ/ጦር ተደጋጋሚ ኦፕሬሽን የተደናገጠው የብልጽግና ሰራዊት በደመ ነብስ የሞርተር ቅንቡላ ወዳገኘበት ሲወረውር ዋለ። ‎=============== ‎በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር ተደጋጋሚ ኦፕሬሽን ተስፋ የቆረጠው የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት በደመ ነብስ በሚወረውረው የሞርተር ቅንቡላ የንሀሃን ቤት እና ቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው:: ‎ ‎ተስፋ የቆረጠው የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ከሰፈረበት ካምፕ ሳይወጣ የኃይለ ማርያም ማሞ ክ/ጦር ቦጋለ ሻለቃን አገኛለሁ በማለት በሚወረውረው የሞርተር ቅንቡላ በአካባቢው በሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የቤት እንሰሳት እና ቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት ደርሷል:: ‎ ‎የብልጽግና ሰራዊት የኃይለ ማርያም ማሞ ክ/ጦር ቦጋለ ሻለቃ ጎርፎ በተባለ ቦታ ምሽግ ይዟል ብሎ በመደናገጥ የሞርተር ጥቃት እየፈጸመ እንደሆነ ከውስጥ የመረጃ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል:: ‎ ‎በዚህም የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን በተፈጸመ የሞርተር ጥቃት በቄስ ከለላው ይረዱ መኖሪያ ቤት ተኝቶ የነበረ ህጻን ላይ የአካል ጉዳት ሲደደርስ በመክበቢያ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ_ክርሥቲያን በረንዳ ላይ በወደቀ ቅንቡላ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ አካል ጉዳት ደርሶበታል:: ‎ ‎በተጨማሪም በፍረሀት ቆፈን የአብይ አህመድ መከላከያ በዘፈቀደ የወረወረው የሞርተር ቅንቡላ በአቶ ነጋሽ ተፈረዴ ቤት አካባቢ ወድቆ በልጆቹ እና በቤት እንሰሳት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል:: ‎ ‎መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አርበኛ ይታገሱ  ጌታሁን  ነው። ‎                 " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።     ‎ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም     

በምዕራብ ዐምሓራ ቀጠና በፋኖ ቁጥጥር ስር በሚገኙ አከባቢዎች ላይ ተከታታይ የሆነ የድሮን ቅኝት እየተደረገ ነው።  ዛሬ ታህሳስ 16/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ በደምበጫና በአከባቢው፣ በማቻከል፣ በደብረ ኤልያስና በአከባቢው እንዲሁም በሌሎች የምዕራብ ዐምሓራ ቀጠናዎች ተከታታይ የሆነ የድሮን ቅኝት እየተደረገ ነው። አገዛዙ በርከት ያለ የሰዎች ስብስብ ካገኘ ጥቃት ከመፈፀም ወደኋላ እንደማይል ከዚህ ቀደም በፈፀማቸው ጥቃቶች ያሳየ ሲሆን፡ ስለሆነም ማሕበረሰቡ እንደ ገበያና የሐይማኖት ስፍራዎች እንዲሁም መሠለ መሰባሰቢያ ስፍራዎች ላይ ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ምንጮቻችን አሳስበዋል።

አዲሱን የድርጅታን የአደረጃጀት ማሻሻያ ተከትሎ ወደ ትግላችን ሰርገው የገቡ የጠላት የተልዕኮ እጆች ቀን በቀን እየተቆረጡ ይገኛሉ። አዲሱን የድርጂታዊ መዋቅርና የሰራዊታችንን አደረጃጀት በሻለቃ፣ በክፍለጦር፣በኮር እና በዕዝ መልሶ ከማደራጀት ጎንለጎን በሂደት ሀገር ተራካቢ ሰራዊትና አመራር ለመፍጠር በሚያስችል አግባብ ተቋማዊነትን በጊዜያዊ የመንግስት አስተዳደር መዋቅር ውስጥ ጭምር  በማዋቀር ህዝብንና ትግልን አንድ አድርጎ መምራት እና ማፅናት ላይ እንገኛለን። ይሁን እንጂ የኦሮሙማው አማራ ጠል  ስርዓት  ማህበረሰቡን እየዘረፈ ፣በፆም ወተት አምጡ ከዚያም ቅመሽ እያለ ኢ- ሀይማኖታዊ ተግባር አየፈፀመ ይገኛል። ሌላው ደግሞ  የገጠመውን የፋይናንስ ችግር ለማስታገስ ጊዜ ለመግዛት በግብር ሰበብ 1.ለአንድ ቋት ወፍጮ 20,000ሺ ብ ር፣ 2.ለሱቆችና ተመሳሳይ ነጋዴወች እስከ 50,000ብር እየጠየቀ ስለሆነ ህዝቡ መክፈል እንደሌለበት እናምናለን። ስለዚህ ህዝባችን ማወቅ ያለበት ነገር፦ አዲሱን አደረጃጀት ስለጨረስን በቅርቡ ኦፕሬሽን ሰርትን ጠላትን ቀጠናውንም ሆነ ህዝባችን ነፃ ለማድረግ ዝግጂታችን ጨርሰናል።። ይህንን የማጥራት ዘመቻ ተከትሎ የጠላትን ስውርና ግልፅ ተልዕኮወች ተቀብሎ በባንዳነት የሚያስፈፅምም ሆነ በተለያዩ ድህረ ገፆች የምታራግቡ ግለሰቦች ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ ካልሆ ግን ድርጂታዊ እርምጃ እንድንወስድ እንገደዳለን። ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!!! የአጊአመ ህ/ ግንኙነት ፋኖ በረከት ፀሐይነህ

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ: አረመኔው   አሸ  ባሪ ዘር አጥ* ፊ    የውንብድና ሠራዊት በገነት አቦ ከተማ ሁለት የዐማራ አባላቱን ረሸነ ═══════════❁✿❁═══════════ (ታኅሣስ 15/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ) በዐፋብኀ 102ኛ ኮር የ33ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድረው ቀጠና በገነት አቦ ከተማ የመሸገው አረመኔው   አሸ  ባሪ ዘር አጥ* ፊ    የውንብድና ሠራዊት በገነት አቦ ከተማ ሁለት የዐማራ አባላቱን በግፍ ረሽኗል። አገዛዙ እነዚህን ሁለት አባላት በአደባባይ የረሸነው "ከድታችሁ ፋኖን ልትቀላቀሉ አስባችኋል" በሚል ምክንያት መኾኑን የውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን ያሳወቁ ቢኾንም፤ ለማኅበረሰቡ ግን "በአስገድዶ መድፈር እና በዝርፊያ ወንጀል የተገኘባቸው ናቸው" በማለት ለማስተባበል ሞክረዋል። በሟቾች ሬንጀር "ደፋሪና ዘራፊ" የሚል ጽሑፍ ጽፈው ማንም እንዳያነሳቸው በመከልከል አስከሬናቸው በአደባባይ ውሏል። በመጨረሻም በአካባቢው ቅን የሀገር ሽማግሌዎች ተማፅኖ እምነታቸውን ግምት ውስጥ ያስገባ ሥርዓተ ቃብር ሊፈጸምላቸው ችሏል። ✔ በሁለት አቅጣጫ ተሰልፈን ከምንሞት በአንድ አቅጣጫ ታግለን ሞትን እንግደል‼ ✔ ሰላም ለሁሉም ፥ ሞት ለማንም‼ ✔ ዐማራዊ አንድነት ያሸንፋል‼ የአረጋ ከበደ ስብሰባ በመርዓዊ ከሽፏል ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። በዛሬው ዕለት ማለትም ታህሳስ 15/2018 ዓ/ም መርዓዊ ከተማ ላይ የባንዳዎች ፊት አውራሪ አረጋ ከበደ የተመራው ልዑክ በመርዓዊ ህዝብ ፊት ተዋረደ። የመርዓዊ ህዝብ የአረጋ ከበደን ልዑክ በአዳራሽ ተገኝቶ አቀባበል እንዲያደርግና የአማራን ህዝብ ትግል ጠልፎ የሚጥል ሀሳብ እንዲሰነዝሩ ከአገዛዙ ጥሪ ቢደረግም ሜጨኞቹ ግን አንድም የብልፅግና አመራር ለመቀበል ዝግጁ አይደለንም እኛ የአማራ ህዝብ ትግል ቆስቋሽም ታጋይም ነን በማለት በራቸውን ዘግተዋል። በዚህ የተበሳጨው የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ ቡድን ቤት ለቤት እየዞረ ወደ ስብሰባው እንዲገቡ ለማስገደድ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም የመጨረሻ ያለውን ሀይል በማሰባሰብ ከባህር ዳር ደብረ ማርቆስ በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ተሳፍረው የሚንቀሳቀሱ ተሳፋሪዎችን በማስገደድ ተሳፋሪዎች የመርዓዊ ከተማ ነዋሪ መስለው እንዲሰበሰቡ ለማድረግ ቢሞክርም የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር በኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ሻለቃ ኢፌሳና አማሪት ጎደሀ ቀጠና በማካለል መርዓዊ ከተማ ላይ በሞርተርና በዲሽቃ የታገዘ ውጊያ በማድረግ ስብሰባው እንዲከሽፍ ተደርጓል። በዚህም ዕቅዱ የከሸፈበት ቡድን ያገኘውን ሁሉ በሀይል በዱላና ሰደፍ እየደበደበ የጤና መድን ክፈሉ እናንተ ሜጨኞች የፅንፈኛው ቀድኛ ደጋፊ ናችሁ በማለት በተለይ ሴቶችን እያንገላታ እንደነበር ለማረጋገጥ ችለናል። የዛሬው ድል አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የመዋቅር ማሻሻያ እና ጦሩን በኮር የማደራጀት ስራ ሰርተን ባጠናቀቅንበት ማግስትና የስርዓቱ አገልጋዮች ሜጫ ላይ የቸደራጀ የፋኖ አወቃቀር በቸለይም በቀድሞ አጠራሩ የኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ የሚባለውን ሀይል ሙሉ በሙሉ ደምስሰን በትነነዋል ብለው የተለመደ የተፈበረከ ዜናቸውን ከመስራታቸውን ማግስት መርዓዊ ላይ ገብቶ የአረጋ ከበደን ስብሰባ መበተንና ጠላትን ሙትና ቁስለኛ ማድረጋችን ልዩ ያደርገዋል። ታህሳስ 15/2018 ዓ/ም የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቴዎድሮስ የደሜ የአባት አርበኞች ጦር ጥቃት ፈፅመዋል " ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም በ201ኛ ኮር 74 ክ/ጦር የእናርጅ እናውጋ ወረዳ የዲያጠባ ቀበሌ አባት አርበኞች ጦር የገበሬውን የግል የጦር መሳሪያ ለመዝረፍ የተንቀሳቀሰውን የምኒሻና እና አድማ ብተና ቡድን ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም 4 ምኒሻ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል።    በዚህ የአባት አርበኞች ጦር ቁስለኛ ካደረጎቸው የሚሊሻ አባለት ፦ 1. ሞላ አንዳርጌ 2. አባትነህ ዋለ 3. ስላባት በቀለ 4. ቢሰነብት የወጉ የተባሉ የብልፅግና ተላላኪ የምኒሻ አባላት በደፈጣ ጥቃቱ በጠና ቆስለው  ደ/ወርቅ ሆስፒታል መግባታቸውን አረጋግጠናል።   በአሁኑ ወቅት 74ኛ ክፍለ ጦር አባላት እና የቀጠናው የአረበኞች ጦር ታሪክን በተግባር ሰርተው አርያ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ አዱስተስፋ" የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር  ህዝብ ግንኘነት #ዳሞት_ያስተፋል_ሃሞት በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን15/04/2018 ዓ / ም የ109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለጦር የደጋዳሞት ሻለቃ ታላቅ ድልን ተጎናፀፈ።በኮሩ ዘመቻ መምርያ ኃለፊ በሆነው በኮማንዶው ፲ አለቃ ንብረት ደሴ እና በክፍለጦሩ ዘመቻ መምርያ ኃላፊ በሆነው በሻለቃ አባይነህ እየተመራ ወደ ግንባር የተመመው የደጋዳሞት ሻለቃ የብርሃኑ ጁላ የእጅ ጓንት የሆነው መከላከያ እና የዘመኑ ተረፈ ይሁዳዎች የሆኑት ሚሊሻዎች መሽገውበት የነበረውን ቅዳሜ ገብያን ተቆጣጥረውት ውለዋል።ድልን መጎናፀፍ የዘወትር ሥራው የሆነው ይሁ ሻለቃ ዛሬም የሕዝብ አውንታዊ ወኔ ቀስቃሽ የሆነ ድልን እንሆ ብሎናል።በጥበብ መምራትን ከአባታቸው ከጀኔራል ዝናቡ የወረሱት ፲ አለቃ ንብረት ደሴ እና ፲፻ አለቃ አባይነህ በጥበብ ተራምደው የጥበብን ዉጤት አሳይተውናል።<<ጥበብ ቤቷን ሰራች >>ማለት ይህ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የፋኖ ክንድ መፈርጠሙን እና የአገዛዙ የዥዋዥዌ ጉዞውን የተገነዘቡ የዓብይ ተፃምሮተ ተባይ የነበረው መከላከያ እየካደ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው። ለዚህም ማሳያ በቀን15/04/2018 ዓ  /ም ፈረስቤት ከተማ ላይ ተወሽቆ ከነበረው የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ሁለት መሰረታዊ ወታደሮች ሁለቱም እያንዳንዳቸው ጥቁር ክላሽ በመያዝ ወጥተው የደጋዳሞትን ሻለቃ ተቀላቅለዋል። -አድነው እንየው የተባለው መሰረታዊ ወታደር አንድ ጥቁር ክላሽ እና 91ጥይት በመያዝ -ንግሩ ደመቀ የተባለው መሰረታዊ ወታደር አንድ ጥቁር ክላሽ እና 110 ጥይት ይዘው በመውጣት ፋኖን የተቀላቀሉ ሲሆኑ ሁለቱም አንደኛ ሬጅመንት ፡ሦስተኛሻንበል እንደነበሩገልፀዋል። ወለጋ!! በቢዛሞ ሻሾበር ከተማ በአረመኔው አገዛዝ በርካታ ሴቶች እና ህፃናት በከባድ መሳሪያ እና በስ-ለ-ት አንገታቸው እ-የ-ተ-ቆረ-ጠ እ-የተ-ገ-ደ-ሉ ነው :: ከተማዋንም አ-ው-ድ-መ-ዋታል ። ከቀናት በፊት መከላከያ አካባቢውን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ በብዙ ሺህ የሚቆጠር የልዩ ሐይል ፣ ጋቼና ሲርና ፣ ሚሊሻ በጥምረት ወደ ቦታው በመግባት ንፁ-ሐ-ንን ለመ-ጨ-ፍ-ጨ-ፍ ሙከራ ሲያደርግ ጀግናው ቢዛሞ ዕዝ በቦታው ደርሶ ከ216 በላይ ሐይል ደ-ም-ስሶ ነበር ። በትናንትናው ዕለት የበ-ቀ-ል እ-ር-ም-ጃ ለመውሰድ መከላከያውን አስከትለው ተመልሰው በመግባት በርካታ እናቶችን እና ህፃናትን በአ-ሰ-ቃቂ ሁኔታ እ-የገ%ደሉ ይገኛል ። ጀኔራል ኃይሉ ከበደ ክፍለ ጦር እና ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በጥምረት ከ105 በላይ የአገዛዙን ሰራዊት በመደምሰስና ከ80 በላይ በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፀፉ! ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ጄኔራል ኃይሉ ከበደ ክፍለ ጦር እና ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በጥምረት ባደረጉት ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በጠላት ላይ የበላይነትን በመቀዳጀት ታላቅ ጀብዱ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media) - Estadísticas y analítica del canal de Telegram @mezmure122124