ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más4 411
Suscriptores
-724 horas
+137 días
+1 18630 días
Archivo de publicaciones
#እዛ_ሰፈር_ጫጫታው_በዝቷል😂
አማራዊያን የጎንደር አንድነት የሰማው የብልፅግና ቡድን እንደለመደው ዲስኩሩ AI (በ Artificial Intelligence ) የተሰራ ነው ማለት ጀምሯል ነገ የአንድነት ፈርጣማ ክንዱን እስኪቀምስ አላምንም እያለ ነው😂😂😂
#የዳይፐር_ነጋዴ_መጠቀሚያው_ጊዜው_አሁን_ነው😂
ለማንኛውም
+1
እንኳን ደስ አለን!!!
አንድ መራር ሀቅ ለማንኛውም ፋኖ በዚ ሰዓት መሳሪያ ይዞ ከሚፋለም ሰው በላይ እስከሞት ድረስ ሊወደው እና ሊታመንለት የሚችል ወንድምም ሆነ ቤተሰብ የለም!!!
እነዚያ አብረውን ጭቃ እየተቃቡ ውሀ እየተራጩ ያደጉት የልጅነት አብሮ አደጎቻችን፣እነሱ ከሌሉ እህል ውሀ ከጉረሯችን አይወርድም የምንላቸው የትምህርት ቤት እና የቢሮ ጓደኞቻችን፣ከኔ በፊት እሱን ያድርገው የምንልለት የናታችን ልጅ ወንድማችን አሁን ከጎናችን የሉም፣ቁስለኛ አያገሉም፣ከወደቅንበት አንስተው አይቀብሩም፣አብረውን ደፈጣ አያደሩም፣ምሽግ ይዘው ጠላትን አይጥሉም!!!!
ፊታችን ልናጠቁርባቸው፣ልባችን ልናደነድንባቸው የማይቻለን የነፍስም የስጋም ወንድሞቻችን አፈሙዝ አንስተው ጫካ አብረውን ያሉ ወንድሞቻችን ናቸው።
ስለነሱ ሲባል የትላንት ሁሉም በደል ይረሳል፣የትላንት ሁሉም ክስ ይሰረዛል!!!
በድጋሜ እንኳን ደስስስስ አለን!!!!
አርበኛ እሸቱ ጌትነት በላይ
የአፋብኃ ቴወድሮስ እዝ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ
+2
ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ.ም
አርበኛ ዘመነ ካሴ ለጎንደር ወንድሞቹ ያስተላለፈው መልዕክት
____
ወንድሞቻችን!አንድ ቃል እንድትናገሩ፥እንዳታዝኑ፥ፍፁማንም እንድትሆኑ፥ሁላችሁንም፦በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እማልዳችኋለሁ፥እንዳትለያዩም አንድ ልብና አንድ ሃሳብ ሆናችሁ ኑሩ።
(የሃዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ቆረንጦስ ሰዎች-1)
እንኳን ደስ ያለን!
ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!
አንድ አማራ!
እስከምፃት አማራ!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!
አርበኛ ዘመነ ካሴ
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን እና ፊስቡክ ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
https://www.facebook.com/share/p/17FBBgD9xG/
+1
ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ.ም
አርበኛ ዘመነ ካሴ ለጎንደር ወንድሞቹ ያስተላለፈው መልዕክት
____________
ወንድሞቻችን!አንድ ቃል እንድትናገሩ፥እንዳታዝኑ፥ፍፁማንም እንድትሆኑ፥ሁላችሁንም፦በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እማልዳችኋለሁ፥እንዳትለያዩም አንድ ልብና አንድ ሃሳብ ሆናችሁ ኑሩ።
(የሃዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ቆረንጦስ ሰዎች-1)
እንኳን ደስ ያለን!
ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!
አንድ አማራ!
እስከምፃት አማራ!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!
አርበኛ ዘመነ ካሴ
የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ ከሰፈረው በኮሎኔል መብሬ አስማማው ዋሴ ከሚመራው አድማ ብተና መካከል የ22ተኛ ሻለቃ አዛዥ የሆነው ኢ/ር አዝመራውን መደምሰሱ ተረጋገጠ::
ከደቡብ ወሎ ዞን መቀመጫ ደሴ ከተማ በስተምዕራብ ከሚገኙት 11 ወረዳዎች አንዷ የሆነችው መሀል ሳይንት ወረዳ መቀመጫ ደንሳ ከተማ ውስጥ ሰሞኑን በተከታታይ ለ3 ቀናት የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰራዊት የማጥቃት እርምጃ ወስዶ የጠላትን ኃይል መደምሰሱ፣ ማቁሰሉ እና መበታተኑ የተገለፀ ሲሆን ኮሩ ካቀፋቸው ክፍለ ጦሮች መካከል የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር፣ መብረቅ ክፍለ ጦር እና ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር የተወሰኑ አሃዶች በውጭጩ ወደ መሀል ሳይንት የላኩት ኃይል ከፍተኛ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፅሞ ከአድማ ብተና ሻለቃ አዛዥ በተጨማሪ የኮሎኔል መብሬ አስማማው ዋሴ አጃቢ የሆነ ስናይፕር ተኳሽ እንዲሁም ሔኖክ የተባለ የ22ተኛ ሻለቃ ዘመቻ መሪን እና 3 የብልጽግና አመራሮችን ከበርካታ የጠላት ሰራዊት አባላት ጋር መደምሰሱ ተረጋግጧል::
የመሀል ሳይንት ወረዳ ኮማንድ ፓስት ከዚህ ቀደም የያዛቸው የግፍ እስረኞችን ሰብስቦ ወደ ካምፕ ወስዶ ለጦርነት ከለላነት እንደተጠቀማቸውም ታውቋል:: ደንሳ ከተማ ዳር እየተገነባ ያለው ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የመሸገው ጠላት የሆስፒታሉን ህንፃዎች እና እስረኞችን እንደ ጋሻ ተጠቅሞ ራሱን ለመከላከል ቢሞክርም እነ ሞት አይፈሬ ካምፑን ተጠግተው በቦንብ ስላጋዩት ብትንትኑ ሊወጣ ችሏል::
የደንሳውን ድንገተኛ ኦፕሬሽን ተከትሎ አንድ ጋንታ አድማ ብተና ሙሉ በሙሉ ተበትኗል:: የጋንታው አባላት ከነበሩት ሶስቱ ወደ ኮሩ ሰራዊት በገዛ ፍቃዳቸው ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ሲከዱ 15 ሰላም አስከባሪዎችም ጠላትን ከድተዋል::
የኮሩ ሰራዊት ደንሳ ከተማን ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠር የጠላት ኃይል ከጎረቤት ወረዳዎች የሰው ኃይል ጭማሬ ጠይቆ ከመካነሰላም በኩል አጋዥ ቢላክለትም አስከሬን አጅበው ቀብር ከመፈፀም ውጭ የሰጡት የተለየ ድጋፍ የለም:: በዛሬው እለት ማለትም መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጭምር የለቅሶ ስነ-ስርዓት ላይ ጥይት ሲተኩሱ ማርፈዳቸውን ነው ለማወቅ የቻልነው:: ከትናንት በስቲያ አመራሮች ሲቀበሩም የቡድን መሳሪያ ተኩስ ጭምር እንደነበር ተረጋግጧል::
የደንሳውን ኦፕሬሽን የመሩት የምኒልክ ዕዝ ም/ዘመቻ መሪ ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ፣ የዕዙ ም/ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ፣ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አዛዥ ሻለቃ አብነው ታደሰ፣ የባለሽርጡ ክፍለ ጦር ወታደራቂ አማካሪ ሻለቃ ክንዱ ሰውነት፣ የባለሽርጡ ክፍለ ጦር ዘመቻ መሪ መቶ አለቃ ታደሰ አስፋው እንዲሁም የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ወታደራዊ አዛዥ ፋኖ አበበ መኩሪያ እና የኮሩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ፋኖ ጌትነት ሲሆኑ በኮሩ ስር ካሉት ክፍለ ጦሮች መካከል ከ3ቱ የተውጣጣ ኃይል በመያዝ ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ መፈፀም ተችሏል:: በተለይ የ22ኛ ሻለቃ አዛዥ ኢ/ር አዝመራው እና ሔኖክ የተባለው የሻለቃው ዘመቻ መሪ መደምሰሳቸው የጠላት ኃይልን አጣብቂኝ ውስጥ ከቶት የተበተኑትም ተመልሰው ወደ ካምፕ አለመግባታቸውና አድራሻቸው መጥፋቱ ታውቋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን እና ፊስቡክ ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
https://www.facebook.com/share/p/17FBBgD9xG/
ሁለት የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት አባላት በደፈጣ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በ602ኛ ኮር 7ኛክ/ጦ 5ኛ ሬጅመንት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት በአባ ኮስትር ብርጌድ የውስጥ የመረጃ ደህንነት ክትትል በተሰጠው የደፈጣ ኦፕሬሽን ሁለት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።
1ኛ.ኦብሳ አብዴላ ብሬን ተኳሽ እና ድሽቃ ምድብተኛ እና
2ኛ.አብድል ኑር ረዲ አህመድ ሞርተር ተኳሽ ድሽቃ ምድብተኛ የነበረ የካባቢውን ማህበረሰብ አለባበስ በመመሳሰል በጉዞ ላይ እንዳሉ በአባ ኮስትር ብርጌድ የውስጥ መረጃ ደህንነት ክትትል አማካኝነት በኮስትር ልጆች በደፈጣ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት አባላት አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ፣ግፍ፣እና በደል በመረዳ አገዛዙን በመክዳት ወደ ቤተሰቦቻችን ለመሄድ በጉዞ ላይ እያለን ነው በአባ ኮስትር ብርጌድ የፋኖ አባላት በቁጥጥር ስር የዋልነው ብለዋል።
አዲስ ትውልድ፤አዲስ አስተሳሰብ፤አዲስ ተስፋ!
ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ግሼራቤል ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ በነበረው የሕዝብ ውይይት ላይ የኮሩ ዋናዘመቻ መምሪያ ሀላፊ ፋኖ አርበኛ አበበ ጥላሁን ያስተላለፉት አስደናቂ መልዕክት
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ግሼራቤል ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ በነበረው የሕዝብ ውይይት ላይ የኮሩ ዋናዘመቻ መምሪያ ሀላፊ ፋኖ አርበኛ አበበ ጥላሁን ያስተላለፉት አስደናቂ መልዕክት
👇👇👇👇
[#ከአርበኛ_ሸጋ_ጌታቸው/ ቋረኛው የተላለፈ መልዕክት ]‼️
ጠላቶቻችን አጠፋናቸው ሲሉ በዝተን የምናድር ባልዋልንበት ሲያውሉን በእውነት የቆምን።
እንደ ወርቅ የነጠርን እደ ብረት የተነከርን የግዜው የነጻነት ምጽአት ነን በእውነት የቆምነን የነጻነት ምሳሌ ነን።
ብቻ እንጠንክር የዘመኑ ነጻነት እኛው ነን።
ለመከራ የተፈጠርን ሳይሆን
ለነጻነት የታደልን ልጆች ነን።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በለይ ዘለቀ እዝ
ም /ክ/ ወታደራዊ አዛዠ አርበኛ ሸጋ ጌታቸው !
ህልውናችን በተባበረ ክዳችን !
#የጥሪ_ማስታወቂያ‼️
ቀን 03/02/2018 ዓ/ም
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የዳ/ቴ/፭ኛ ኮር
የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልዉና አደጋ ለመቀልበስና ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ከአፓርታይዱ ስርዓት ጋር ትንቅንቅ ከጀመረ ዓመታትን እንዳስቆጠረ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያወቀዉ የአደባባይ እዉነታ ነዉ ።
በመሆኑም ይህን ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገርስሶ ለመጣል ሰራዊታችን እና የጦር መሳሪያዎችን እያዘመንን ወደፊት እየገሰገስን ሲሆን ተጨማሪ የጦር ልምድ ያላቸዉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች እንደሚያስፈልጉን ስላመንን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በሙሉ ከጥቅምት 03/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳዉቃለን ።
1 ) በሁሉም የስርዓቱ የጸጥታ ዘርፍ ያገለገለ በስርዓቱ በአማራነቱ ተገፍቶ ራሱን ከስርዓቱ ያገለለ / ያገለለች
2 ) የአማራ ተወላጅ የሆነ / የሆነች እና በብሔርተኛነት ትግሉ ሙሉ በሙሉ ያመነ/ ያመነች
3) ማንኛውንም ሃይማኖት ማክበር የሚችል /የምትችል
4 ) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ግሉል የሆነ አባልም ያልነበረ/ ያልነበረች
5 ) ስለተወለደበትና ስለሚኖርበት አካባቢ ( የትዉልድ ቦታ ) ሙሉ መረጃና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል / የምትችል
በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሰረት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን !!!
ስልክ ቁጥር 0986376500
ኅልዉናችን በተባበረ ክንዳችን !!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የዳግማዊ ቴዎድሮስ( ፭ኛ) ኮር
04/ዐ2/2018 ዓ.ም፥ረጨ
ሰበር አዲስ ቅዳም‼️
19 ተመክሮ አይድን በጥዋቱ ተሸኝቷል!
ዛሬ ጥቅምት 4/2018 ዓ/ም ከለሊቱ 12:00 ስዓት ጀምሮ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ አዲስ ቅዳም ከተማ ዉስጥ በመግባት ባደረገችዉ የእጅ በእጅ ዉጊያ የታገዘ ድንገተኛ ኦፕሬሽን በጠላት ላይ ከፍ ያለ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።
በዚህ ከለሊቱ 12:00 ስዓት እስከ እረፋድ 5:00 ስዓት ድረስ ለተከታታይ 5 ስዓታት በቆየ ልዩ ኦፕሬሽን
አዲስ ቅዳም ስላሴ ፣ አባ አይናለም ፣ከብት ገበያ እና ባታ ቤተክርስቲያን መሽጎ የነበረዉ ከሞት የተረፈ ጠላት በፋኖዎች አረር የተሸኙ 19 እድለቢስ ጓዶቹን ሳያነሳ ቁስለኛ እና ቁሳቁሱን በእየ ሜዳዉ እያንጠባጠበ ሙሉ በሙሉ ምሽጉን በመልቀቅ ወደ አድጓሚ ተራራ ፈርጥጧል።
አጠቃላይ በዛሬዉ የአዲስ ቅዳም ከተማ ልዩ ኦፕሬሽን
_19 የብልፅግና ታጣቂ ሲወገድ
_27 ቁስለኛ ሁኖ
_16 ክላሽንኮቭ መሳሪያ ብዛት ካለዉ ተተኳሽ ጋር በምርኮ ገቢ ተደርጓል።
ፋኖነት አሸናፊነት‼️
ይበልጣል የዉነቱ (እሳቱ)
◊◊ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር የጠላት ወታደራዊ የማዘዣ ቦታ የሆነችውን ደጎማ ከተማን ከበባ ውስጥ በማስገባት በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወሰደ ።
ዛሬ ጥቅምት 04 / 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር መብረቅ ክ/ጦር ፣ ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ፣ ፋናየ ውቤ ክ/ጦርና ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ነብዩ አሳምነው ብርጌድ በ4 አቅጣጫ ከጠላት ምሽግ ድረስ በመግባት የጨበጣ ውጊያና ቦንቦ ውርወራ የደረሰ እልህ አስጨራሽ ውጊያ አድርገዋል።
በሴጋ ፣ በአንባጨራ ፣ በአንባ ዙሪያና በደንጎርሳ ምሽጎች የጠላት ኃይል የተቀጠቀጠ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ጥምር ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።
ከማክሰኝት ደጎማና ከአርባያ ደጎማ የሚወስዱ ሁለቱን መንገዶች ዝግ በማድረግ ውጊያው የተካሄደ ሲሆን የጠላት ኃይል ድጋፍ ለመስጠት በከፍተኛ ሁኔታ ችግር ውስጥ መግባቱም ታውቋል።
በዚህም ሰበብ ክፋኛ የቆሰሉትን የጠላት ኃይላት ወደ ከፍተኛ ህክምና ማድረስ አለመቻላቸውም ተገልጿል።
በውጊያው የተገኙ ድሎች መካከል
** 15 እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል።
** 23 ቁስለኛ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በደጎማ ጤና ጣቢያ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንሆነ ታውቋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በትላንትናው እለት ጥቅምት 03/ 2018 ዓ.ም በ6 አቅጣጫ ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦርንና ታድሎ ብርሃን ክ/ጦሮችን ለመበተን ከፍ ሲልም ደግሞ ለመደምሰስ በሚል አቅዶ የመጣውን የጠላት ኃይል አሳፍረው መመለሳቸው ታውቋል።
ውጊያው ከምንዝሮ አርሴማ እስከ አይባ ደንቀዝ ከፍተኛ ቦታዎችን ያካለለ ሲሆን የጠላት ኃይል ከፍተኛ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ኪሳራዎችን አስተናግዶ ሊመለስ ችሏል።
ከአዘዞ ፣ ከአምባ ጊዮርጊስ ፣ ከደጎማና ከአርባያ ተውጣጥቶ የመጣው የብልጽግና ወንበር አስጠባቂ ኃይል የዘወትር ግብሩ የሆነውን ሞትና ቁስለትን በክንደ ፈርጣማዎቹ ፋኖዎች ተከናንቦ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ወደመጣበት እየተመለሰ መሆኑ ታውቋል።
** በውጊያው 9 የሞተ ሲሆን 6 ቁስለኛ ተደርጓል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ጥቅምት 04 / 2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን እና ፊስቡክ ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
https://www.facebook.com/share/p/17FBBgD9xG/
