ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más4 039
Suscriptores
+6824 horas
+3957 días
+1 39230 días
Archivo de publicaciones
ትናንት ከቆቦ ከተማ ወጥተው የጠፉትን ወታደሮች ለመያዝ ፍለጋው ዛሬም ቀጥሏል።
ወታደሮቹ ምን አልባት በከተማዋ ውስጥ አድረው ከሆነ በሚል መውጫ መግቢያ ኬላዎች ላይ የተጠናከረ ፍተሻ እየተካሄደ ነው።
በከተማዋ የቀሩት ወታደሮች የከዱ ጓዶቻቸውን ለመያዝ በከባድ መሣሪያ ሽፋን ታግዘው በከተማዋ ዙሪያ በሚገኙ ገጠራማ መንደሮች ተንቀሳቅሰው አሰሳ እንዲያካሂዱ ከአዛዦቻቸው መመሪያ የተሰጣቸው ቢሆንም፡ ነገር ግን ወታደሮቹ የፋኖን ጥቃት በመፍራት መንቀሳቀስ አልቻሉም።
ወታደራዊ አዛዦቹም፡ የጠፉትን ለመፈለግ የምንልካቸው ወታደሮችም ሊጠፉብን ይችላሉ በሚል ስጋት፡ በየገጠሩ እየዞራችሁ ፈልጉ ብለው አውርደውት የነበረውን መመሪያ እንዲተገበር ለማስገደድ አልደፈሩም።
በከተማዋ ዙሪያ ከሚገኙ ገጠራማ መንደሮች አንድ አርሶ አደር የምግብ እህል ለማስፈጨት ዛሬ ጥር22/2018 ዓ/ም ማለዳ ወደ ቆቦ ከተማ እየገባ እንዳለ ኬላ ላይ በነበሩ ወታደሮች ተይዞ፡ "ስትመጣ የከዱ የኛ ጓዶችን አይተሃል ወይ" በሚል የተጠየቀ ሲሆን፡ አርሶ አደሩም "የከዳንና ያልከዳን መከላከያ መለየት አልችልም" የሚል ምላሽ በመስጠቱ ደብድበውታል።
በከተማዋ አሰሳ እያደረጉ የሚገኙት ወታደሮች አንዲት እናትን በተመሣሣይ "የኛ ጓዶች በዚህ ዘልቀዋል ተብለን፡ አይተሻል ወይ?" በሚል የጠየቋት ሲሆን፡ "ባፋፉ ዝለቁና ጥሯቸው" የሚል ምላሽ በመስጠቷ በጥፊና በቦክስ እንደመቷት የአይን እማኞች ተናግረዋል።
ከአላማጣ ከተማ ሸሽተው ወደ ቆቦ ከተማ ከገቡት የአገዛዙ ወታደሮች መካከል ከሁለት ጋንታ በላይ የሚሆኑ ወታደሮች ትናንት ጥር 21/2018 ዓ/ም አመሻሹን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ከየአሃዶቻቸው ከድተው መጥፋታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ለአማራ የባንዳ መጨረሻው ....!
የአማራን የኅልውና ትግል ክደው፤ሕዝባችን ለኅልውናው ማስጠበቂያ ይሆን ዘንድ ወዶ እና ፈቅዶ የገዛልንን ብሎም አበባ ወንድም እህቶቻችንን ገብረን የማረክነውን መሣሪያ ይዘው ለጠላት እጅ የሰጡ የእንቁላል ቀቃይ ልጆች ጉድ ሆነዋል። አረመኔው የአብይ አህመድ አገዛዝ እኒህን ከሀዲዎች በጠለምት፣ራያ እና አፋር ግንባር አሰልፎ የጥይት ማብረጃ ሊያደርጋቸው እንደሆነ አስተማማኝ መረጃ አለን።
የወንድሞችህን ክቡር ደም እረግጠህ ሄደህ ቀን ቀን ብርቅርቅ ቀለም የተቀባ ፎቅ እና የለመለመ ሳር እያስጎበኘ ሲያማልልህ እየዋለ ማታ ደግሞ ወፌ ላላ ገልብጦ ሲገረፍህ እንደሚያድር የማናውቅ መስሎሀል። ለማንኛውም አሁንም ጥሩ ቀዝቃዛ በቀል ይዞልህ መጥቷል። ግንባር ትሰለፋለህ የውሻ ሞት ትሞታለህ። Dawit fano
የክብር ሞትን ንቀህ የውርደት ሞት ትሞታለህ።
ድል ለአማራ ሕዝብ!
ድል ለፋኖ!
ጥር 22/2018 ዓ.ም
የወልቃይትና ራያ ቼዝ፦ የፋኖ አፈሙዝ እና የአገዛዙ የመጨረሻ ቁማር
በአሁኑ ወቅት በራያ፣ በአላማጣ እና በወልቃይት አቅጣጫ እየታዩ ያሉ ግራ አጋቢ ኩነቶች የድንገተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ውጤቶች ሳይሆኑ፣ አስቀድሞ የተተለመ እና በጥንቃቄ የተሰላ የፖለቲካ ቁማር ማሳያ ናቸው። ነገሩ አሁን ጥርት እያለ መጥቷል።
የብልጽግና አገዛዝ በዲጂታል ሰራዊቱ በኩል "ፋኖ የታለ?" የሚል አጀንዳ እያስጮኸ ያለው በዘፈቀደ ሳይሆን፣ የራሱን ስልታዊ ውድቀት ለመሸፈን እና የፋኖን ህዝባዊ መሰረት ለመናድ በነደፈው ፎርሙላ መሰረት ነው። ይህ ፎርሙላ የሚጀምረው በትግራይ ክልል ላይ የኢኮኖሚ እና የበጀት ጫናዎችን በማበርታት፣ የገንዘብ ኖት እጥረት በመፍጠር ህወሃትን የፕሪቶሪያ ስምምነት፣ ህልውናዬ ሲል ወደ ጦርነት አማራጭ እንዲገፋፋ በማድረግ ነው። በመቀጠልም ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም በራያ አላማጣ እና ኮረም አካባቢ የነበረውን የመንግስት ሰራዊት ያለምንም ተኩስ በማስወጣት ለወረራ መንገድ መጥረግን ያካትታል። በዚህ መንገድ ህወሃት በሩ ክፍት ተደርጎለት እንዲገባ ከተደረገ በኋላ፣ የሚዲያ ሰራዊቱ "ወረራ ተፈጸመ" የሚል ጩኸት በማስተጋባት ህዝቡ በስጋት እንዲዋጥ እና "ፋኖ የታለ?" የሚል ጥያቄ እንዲያነሳ ይገፋፋል።
ይህ ስልታዊ ወጥመድ ሁለት ዋና ግቦች አሉት። አንደኛው እና ዋናው ግብ፣ የፋኖን አፈሙዝ ከአዲስ አበባ እና ከአገዛዙ ላይ ነቅሎ ወደ ተለመደው የድንበር እና የብሄር ግጭት ማዞር ነው። መንግስት የፋኖ አይኖች በእሱ ላይ በተተከሉ ቁጥር ህልውናው አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ስለሚያውቅ፣ ትግሉን አቅጣጫ ለማስሳት የቆየውን የህወሃት ስጋት እንደገና ማንቀሳቀስ መርጧል። ሁለተኛው ግብ ደግሞ፣ በራያ እና ወልቃይት ጉዳይ እጅግ ስሜታዊ የሆነውን የአማራን ህዝብ ከፋኖ ጋር ማጋጨት እንዲሁም የፋኖ ሃይሎችን ለመከፋፈል ነው። ፋኖ ወደተከፈተው የጦርነት ወጥመድ ካልገባ "ህዝቡን ለጠላት አሳልፎ ሰጠ" በሚል የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ቅቡልነቱን ለመቀነስ ይሞከራል። ዛሬ በየማህበራዊ ሚዲያው "ፋኖን የበላ ጅብ አልጮህ አለ" የሚሉ ድምጾች፣ የዚሁ የተቀነባበረ ሴራ ውጤቶች እንጂ የእውነተኛ ደጋፊዎች ጭንቀት እንዳልሆኑ መረዳት ይገባል።
ይህ የፕሮፓጋንዳ ሴራ ምን ያህል ወጥነት የሌለውና በወቅታዊ ጥቅም ላይ ብቻ የተመሰረተ መሆኑን የሚያሳየው ደግሞ ከጥቂት ወራት በፊት የዚሁ አገዛዝ የሚዲያ አውታሮች ሲያስተጋቡት የነበረው አጀንዳ ነው። ያኔ "የፋኖ ትግል በህወሓት ተጠልፏል" የሚል የሀሰት ስዕል በመሳል በደጋፊዎች መካከል መጠራጠርን ለመዝራት ሞክረዋል። የዚህ መሰሪ ፕሮፓጋንዳ ዋነኛ አላማ የጎንደር እና የወሎ ፋኖዎች እንዲሁም ደጋፊዎቻቸውን በማስኮረፍ ፋኖዎችን እርስ በርስ እንዳይተማመኑ እና አንድነታቸው እንዲላላ ማድረግ ነበር። ያኔ ፋኖን "የህወሓት ተላላኪ" አድርገው ሲስሉ የነበሩት አካላት፣ ህወሓት ራያ ላይ በተግባር መንቀሳቀስ ሲጀምር ወዲያውኑ አጀንዳቸውን ቀይረው "ፋኖ የታለ?" ወደሚል ጥያቄ መዛወራቸው ትልቅ ምጸት ነው። በትናትናው እለት "ፋኖ ከህወሓት ጋር አብሮ እየሰራ ነው" ካሉ፣ ዛሬ ደግሞ "ፋኖ ህወሓትን ለምን አይመታም?" ብሎ መጠየቅ የፖለቲካ ንቃት ማነስ ሳይሆን፣ ህዝብን እንደማያውቅ የመቁጠር ድፍረት ነው። ይህ የሚያሳየው አገዛዙ ፋኖ ያደረገውን ቢያደርግ የሚከስበትን "የሁለትዮሽ ጥቃት" (Double Bind) ስልት እያከናወነ መሆኑን ነው።
ለእናንተ፣ እውነተኛ የትግሉ ደጋፊዎችና የራያና የወልቃይት ጉዳይ ከልብ ለሚያሳስባችሁ ወገኖች አንድ ወንድማዊ እውነትን ማጋራት ይገባል፤ ፋኖ ዛሬ የብልጽግናን የፖለቲካ ዜማ ተከትሎ ላለመደነስ የመረጠው በድክመት ሳይሆን በጥልቅ ስልታዊ ትዕግስት ነው። አገዛዙ ሆን ብሎ ሁኔታዎችን በማመቻቸትና መንገዱን ክፍት በማድረግ ፋኖ በችኮላና ያለ በቂ ዝግጅት ከትህነግ (ህወሓት) ጋር ወደ ፊት ለፊት ግጭት እንዲገባ እየገፋፋው መሆኑን ማስተዋል ያስፈልጋል።
ይህ ግፊት ፋኖን ከዋናው የፖለቲካ ግቡ ለማዘናጋት ብቻ ሳይሆን፣ በታጋዮቹና በአመራሩ መካከል 'ለምን አልዘመትክም? ለምን ቆምክ?' በሚሉ ጥያቄዎች የጥርጣሬ ክፍተቶችን ለመፍጠር ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ መሰሪ ስራ ነው። በእርግጥም ራያና ወልቃይት የህልውናችን ማገር፣ የማንነታችን መገለጫዎች ናቸው፤ ነገር ግን እነዚህን መሬቶች ለዘላቂነት ማስከበር የሚቻለው የችግሩን ምንጭ ከስሩ ማድረቅ ሲቻል ብቻ ነው።
አገዛዙ ራሱ የለኮሰውን እሳት ፋኖን እንደ 'እሳት አጥፊ' በመጠቀም አቅሙን እንዲበትንና የራሱን እድሜ እንዲያራዝም የሚሸርበውን ሴራ መንቃት ይገባል። ዛሬ መሬቱን ያለምንም ተኩስ ለጠላት አሳልፎ የሰጠው አካል 'ፋኖ የታለ?' ብሎ ለመጠየቅ የሚያስችል የሞራል ልዕልና የሌለው መሆኑን ተረድተን፣ ትኩረታችንን ከዋናው ግባችን ላይ ሳንነቅል በብስለትና በጽናት መጓዝ ይኖርብናል።
ስለዚህ የአማራ ህዝብና ደጋፊዎች በዚህ ፈታኝ ወቅት በስሜት ሳይሆን በብስለት መጓዝ ይኖርባቸዋል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄን አንድነት ለመናድ የሚነዙ የ"ጠለፋ" ወሬዎችም ሆኑ ዛሬ የሚደለቁ የ"ታለህ" ጥሪዎች ግባቸው አንድ ነው፦ ትግሉን ማዳከም። በየዩቲዩብ እና ቲክቶኩ የሚለቀቁ የተቀነባበሩ አጀንዳዎች የትግሉን አቅጣጫ እንዲያስቱ ሊፈቀድላቸው አይገባም። የፋኖ አቋም ግልጽ ነው፦ ትግሉ የህዝብን ስልጣን ለህዝብ ማስመለስ እንጂ፣ በአገዛዙ ዳኝነት በሚመራ የጥፋት አዙሪት ውስጥ ገብቶ አቅምን መበተን አይደለም። ራያ እና ወልቃይት የሚከበሩት ጠንካራና የማይናወጥ ማዕከላዊ የፖለቲካ ድል ሲመዘገብ ብቻ ነው። እስከዚያው ግን ደጋፊው የጠላትን የፕሮፓጋንዳ ፎርሙላ ነቅቶ በመጠበቅ፣ የታጋዩን ጀርባ ማጠናከር እና የጠላትን የሚጋጩ ትረካዎች እያነሳሳ በመሞገት የሴራውን ምንጭ ማጋለጥ ይኖርበታል።
👉 ከታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ ቶሎ ቀጥታውን ከግንባር መረጃዎችን እንዲደርሳችሁ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586538705973
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

+9
በባሶ ሊበን ወረዳ ህዝባዊ ውይይት ተካሄዴ
ጥር 22/2018
ህዝብን ከጎኑ ማሰለፍ ቀዳሚ ተግባሩ ያደረገው የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ 34ኛ ክ/ጦር በስሩ በሚያስተዳድራቸው አራት ወረዳዎች ላይ በተከታታይ ህዝባዊ ውይይቶችን እያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በባሶ ሊበን ወረዳ ታላቅ ውይይት አካሂዷሌ ።
በዚህ ውይይት የ206ኛ ኮር አመራሮች እንድሁም የወረዳው የጊዜያዊ መንግስት አመራሮች የተገኙ ሲሆን አድሱ ከተመሰረተው የማታገያ ድርጅት አፋብንን አስመልክቶ ለማህበረሰቡ እውቅና የተፈጠረ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ትግል ላይ ከእያንዳንዱ ማህበረሰብ ምን ይጠበቃል በሚል መክረዋል ።
በዚህ ውይይት በተመሰረተው ሁሉን አቀፍ በሆነው አንድ አማራዊ አታጋል ድርጅት አፋብን ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁት የወረዳው ነዋሪዎች ድጋፋቸው እንደማይለይና ለምናደርገው የህልውና ትግል ተባባሪ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።
ድል ለአማራ ፋኖ
ሐብታሙ ጌታቸው የ34ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት
ብልፅግና ወልቃይት ላይ የመዘዘው የመጨረሻ ካርዱ!
ከጥር 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ በአማራ ክልል ወልቃይት ቀጠና በማይ-ዳጉሻ በኩል የተጀመረው ውጊያ አድማሱን አስፍቶ በምስራቅ ጠለምት እና በምዕራብ ጠለምት ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ይገኛል።
ሦስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ውጊያ በሰላሬ፣ በመቃብር አንበሳ፣ ማይበረና ሰራር የተባሉ አከባቢዎችን ጨምሮ በምጫራ ግንባር በአጠቃላይ በሦስት ግንባሮች በከባድ መሣሪያዎች ታግዞ እየተካሄደ መሆኑን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
ብልፅግና፡ በባለቤቱ በአማራ ቁጥጥር ስር የሚገኘውን ወልቃይትን ከሕወሓት ታጣቂዎች የሚከላከል መስሎ ተኩስ ከጀመረ በኋላ፡ እንደለመደው በስልታዊ ማፈግፈግ ስም ወልቃይትን ሙሉ ለሙሉ ለሕወሓት በማስረከብ “ወልቃይትን ከወረራ እንዳልከላከል ፋኖ እንቅፋት ሆኖብኛል” የሚል ካርድ ለመምዘዝ መዘጋጀቱም ታውቋል።
ብልፅግናም ሆነ የብልፅግና ተላላኪው በአዴን የወልቃይት ጉዳይ ጉዳያቸው አይደለም። እነዚ ሁለት ፀረ አማራ ኃይሎች ወልቃይትን የሚፈልጉት ለፖለቲካዊ ትኩሳታቸው ማብረጃ ብቻ ነው።
ወዲህ ደግሞ በአዴን የወልቃይትን አጀንዳ የሚያነሳው ፋኖን እርስ በእርሱ ለመከፋፈልና ከሕዝቡ ጋር የመነጠል ስራ ለመስራት ነው።
እንጂማ በአዴን በየትኛው ጊዜና ሰዓት ነው የፌደራል መንግስቱ እግር አጣቢ ከመሆን ወጥቶ ለሕዝብ አስቦና ተቆርቁሮ የሚያውቀው።
የአማራን እርስት አሳልፈው የሰጡ በአዴኖች፣ ከክልሉ ውጭ ያለው አማራ ውክልና እንዳያገኝ በማድረግ ለዘር ፍጅት የዳረጉት በአዴኖች፣ ለመጣ ለሄደው የፌደራል መንግስት ዘዋሪ ቡድን ማጎብደድና መላላክ የማይሰለቻቸው በአዴኖች፣ የፌደራል መንግስቱ ከድሮንና ጄት ጀምሮ በአለም አቀፍ የጦር ሕግ የተከለከሉ መርዛማ መሳሪያዎችን ጭምር ታጥቆ የክልሉ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እንዲፈፅም የፈቀዱና አሁንም ይሄንን ዘግናኝ ድርጊት እየመሩና እያስተባበሩ የሚገኙት በአዴኖች፣ ሕዝቡ አማራዊ ስነልቦና እንዳይኖረው በአጥንትና ጉልጥምት ቆጠራ ተዘፍቆ፡ በጎጥና በመንደር ተወሽቆ እንዲቀር ለማድረግ ሌት ተቀን የሚታትሩት በአዴኖች ናቸው።
ከአማራ ባሕል ያፈነገጡ፣ አማራዊ ስነ ሰብ ያልተላበሱና ስልብ ስነልቦና ያላቸው፣ መላላክን እና መገረድን እንደክብር የሚቆጥሩት የበአዴን ሰዎች እንዴት አያሌ መስዋዕትነት ስለተከፈለበት ወልቃይት ሊያስቡ ይችላሉ?
የበአዴን ሰዎች ከአማራ ተቆርሰው ለተወሰዱ ለየትኛውም እርስቶች እዝነትም ሆነ መቆርቆር ፈጥሮባቸው አያውቅም። እንደውም ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ ሙሉ ወሎን በወራሪው ኦህዴድ ጠቅልሎ ለማስወሰድ ጫፍ ደርሰዋል።
ይህ ቡድን ሙሉጊዜውን በግርድና በማሳለፉ አሁን የአማራ ሕዝብ ላለበት ሁኔታ አጋልጦታል።
ይሄው የአማራ ሕዝብ የመከራ ምንጭ የሆነው በአዴን ከፌደራል መንግስቱ ጋር በመመሳጠር ከጥር 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ በወልቃይት በኩል አዲስ ጥቃት በመክፈት እንደለመዱት በስልታዊ ማፈግፈግ ስም ገና ነፃነቱን አጣጥሞ ያልጨረሰውን የወልቃይት አማራን ሕዝብ ዳግም ለወረራ ሊዳርጉት ቋምጠው ተነስተዋል።
ቡድኑ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ለመምታት ያስችለው ዘንድ፡ ከርስት በላይ የሆነውን የወልቃይትን ጉዳይ በመግፋት ሕዝቡን ለጥቃት ከመዳረጉም በላይ የፋኖን ኃይል ለማዳከምና እርሱ በእርሱ ለመከፋፈል “ፋኖ ከሕወሓት ጋር ተባብሮ” ወልቃይትን አስወረረብን የሚል አጀንዳ መምዘዙ እጅግ አስገራሚ ያደርገዋል።
ብልፅግና በወልቃይት ጥቃት እንዲመጀመር ማስደረጉ ዋነኛ ምክኒያት ከሰሞኑ የአማራ ፋኖ ወጥ የሆነ አደረጃጀት መመስረቱን ተከትሎ የፈጠረበት ከባድ ድንጋጤና ጭንቀት ነው።
የፋኖን የወደፊት አቅጣጫ ያዛባልናል ብለው ካሰቡት አንዱ የወልቃይትን ጉዳይ አጀንዳ በማድረግና ዳግም በማስወረር፡ አስወረርከን የሚል አማራ ከተነሳም፡ የሕወሓት ታጣቂዎችን ከወልቃይት እንዳላስወጣ ፋኖ እንቅፋት ሆኖብኛል የሚል ካርድ ለመምዘዝ አልሞ ነው።
ነውረኛውና ልፍስፍሱ ብልፅግና የሕወሓት ታጣቂዎች በወልቃይት የከፈቱትን ወረራ ለመቀልበስ መከላከያ ሰራዊቱን ካሰማራው ፋኖ ቀጥታ ያለከልካይ ወደ አራት ኪሎ ያመራብኛል የሚል የቂል መልስ እንደሚሰጥም ይጠበቃል።
ለዛም ነው ብልፅግና በወልቃይት ጥቃት መከፈቱን ተከትሎ አፀፋዊ ምላሽ ወሰድኩ የሚል የተለመደ ቀደዳውን በአክቲቪስቶቹ በኩል እያስነገር የሚገኘው።
ነገ ደግሞ “ስልታዊ” ብሎ የሚጠራውን የማፈግፈግ አይነት ያፈገፍግና ለምን የሚል ጥያቄ ሲነሳበት ወልቃይት ላይ የተቃጣውን ወረራ እንዳልመክት ፋኖ እንቅፋት ፈጠረብኝ በሚል የለቅሶ ፖለቲካ ለመስራት ካሁኑ ድንኳን ተከላ ጀምሯል።
ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ ጣፈጠም መረረም የአማራ ፋኖ እያደረገ ባለው የሕልውና ትግል ቀዳሚ አላማው የተከበረ፣ እርስቶቹ የተጠበቁለትና ማንነቱ የማያስጠቃው አማራ እንዲኖር ማድረግ፣ ሕልቆ መሣፍርት ግፍና መከራን ጨምሮ የዘር ጭፍጨፋ ለተፈፀመበት የአማራ ሕዝብ ፍትሕ ርትዕ ማስፈን መሆኑን ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው።
ሰላም የመሰላቸው ጊዜ
> ፋኖዎች ጃውሳዎች ናቸው
> ፋኖዎች ሀገር አፍራሽ ናቸው
> ፋኖዎች የአማራ ህዝብ እዳ ናቸው
> ፋኖዎች ፒሪሪረም ፣ፓራራረራም
ጦርነትና ጭንቅ የመጣ ሰአት
> ፋኖዎች ለምን አይዋጉም
> ለምን ጦርነትን አይመክቱም
> ለምን ለመንግስት አያገለግሉም
እኛ ~ በምን ጊዜ ነው የተፈጠራችሁት?
ወደ ኋላ አትመልከት እንደ #ሎጥ #ሚስት #የጨው #ሐውልት ትሆናለህ! አንተ አማራ ነህ። አንተ ከታላቁ አማራ ህዝብ አብራክ የወጣህ #ፋኖ ነህ። #የአማራውን ዘላቂ #መዳኛ ይዘህ ወደ ፊት ሂድ። ወደ ኋላ ሳትመለከት፤ ዳር አድርሰህ ቋጨው። አጀንዳ በመጣ ቁጥር አትሸበር። ብቻ ከቀዳሚ አጀንዳህ ለአፍታም ቢሆን #አይንህን አላማህን ከብልፅግናው ስራት አስፈፃሜ ኃይል ጋር #እንዳትነቅል!! ከድርጅታችን ከአፋብን ጋር ወደ ፊት ብቻ! እነሱ እንደሆን ይጩሁ ስራቸው ነው ቁራ ሌላ አመል የለውም መጮህ ብቻ ነው አላማው እናም አማራ ነህ አይደል ወደ ፊት እሱም ማሸነፍ ብቻ።
ለትግራይ ህዝብ ወልቃይትን ከሚሰጣቸው ከአቢይ አህመድ ይልቅ ወልቃይት የአማራ ነው የሚለው ፋኖ ይሻለዋል።
ነገሩ እንዲህ ነው። አቢይ አህመድ ትግራይና አማራ ለየብቻቸው ሀገር እንዲመሰርቱ አድርጎ የራሱን ሀገር ለመመሰርት እየሰራ ነው። ይህን ግን ለሕዝብ አይናገርም። ከተናገረማ ተቃውሞው ይበዛበታል። አንድ የእግር ኳስ ተጫዋች ተከላካዩን ለማለፍ ሲፈልግ ወደግራ የሚሄድ መስሎ ወደቀኝ የሚታጠፈው ተከላካዩን ለማታለል እንደሆነው ሁሉ አቢይ አህመድም ኢትዮጵያን የሚያፈርሳት “ኢትዮጵያ አትፈርስም’ እያለ ነው።
ይህን ያልተረዳ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፈጽሞ ሊገባው አይችልም።
አቢይ ያቀደው በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ወልቃይትን ለትግራይ አሳልፎ በመስጠት ትግራይን እንድትገነጠል ማግባባት ነው። የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለማስፈጸም አማራ ትጥቁን መፍታት አለበት ተብሎ ተወስኖ ነበር። ነገር ግን አማራው ትጥቁን መፍታቱ ቀርቶ የበለጠ ታጠቀ። ስለሆነም በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት አቢይ ወልቃይትን ለትግራይ ማስረከብ አልቻለም።
እና አሁን አብይ የሚመኘው ፋኖና ህዋሃት እንዲዋጉና በግርግሩ እሱ የራሱን ሀገር ለማወጅ ነገሮች እንዲመቻቹለት ነው። ቀደም ሲል መከላከያው መቀሌ ሊገባ ሲል አቢይ በቀጭን ትእዛዝ ያስቆመው ሀዋሃት አማራን ትቆጣጠርልኛለች ብሎ አቅዶ ነው። ሀዋሃት ባለመሞቷ ፋኖ ጋር ተጋጭታ ፋኖ አዲስ አበባ እንዳይገባ ታደርግልኛለች ብሎ አቅዷል። ከዛ በኋላ የራሱን መንግስት ያውጅና የተባበሩት መንግስታት ወይም የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ጦር በኦሮሚያ ድንበር እንዲሰፍር ማድረግ ነው የሚፈልገው። ኦሮሚያ የበለጸገች ሀገር ትሆናለች፤ አማራና ትግራይ ደግሞ በማያባራ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቀው በድህነት ሲማቅቁ ይኖራሉ ብሎ ያስባል።
እና ትግራይ ወልቃይትን ካገኘች ብትገነጠልና የራሷን ሀገር ብትመሰርት ምን ትጎዳለች ትሉኝ ይሆናል። ሌላው ሽወዳ እኮ ይኼ ነው። ወያኔ ከ1974 አም ጀምሮ ከኢትዮጵያ የመገንጠል ሀሳብ ኖሯት አያውቅም። ከዛ በፊት ትግራይ ውስጥ “እንገንጠላለን” የሚልና “አንገነጠልም” የሚል በሁለት ጎራ የተከፈለ ክርክር ነበር። በ1974 አም ግን ከኢትዮጵያ እንደማይገነጠሉ ነገር ግን ይህን ለማንም እንደማይናገሩ ተስማሙ። እንገነጠላለን የሚለው ፕሮፓጋንዳ አማራን ለማስፈራራትና ኦሮሞን ለማስደሰት ተጠቅመውበታል።
አንድ ማህበረሰብ ለመገንጠል የሚፈልገው የተሻለ ሀብት አለኝ ብሎ ሲያስብና የበታችነት ስሜት የሚሰማው ከሆነ ነው። ትግሬዎች ይህን አያሟሉም። ኦሮሞዎች ያሟላሉ። ስለሆነም ኦሮሞዎች የመገንጠል ፍላጎት ሲኖራቸው ትግሬዎች ግን የላቸውም። ለዚህም ነው 27 አመት በስልጣን ላይ ሲቆዩ መገንጠል እየቻሉ ያልተገነጠሉት።
በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላንን ሲያዘጋጁ ትግሬዎች ምንም አይነት ከኢትዮጵያ የመገንጠል ፍላጎት እንደሌላቸው የደመደሙት ኦነጎች ቄሮን አነሳስተው ከአማራ ጋር በመተባበር ወያኔን አባረሩ። ወያኔዎች ከስልጣን ከተባረሩ በኋላም ወልቃይትና ራያ በነሱ ቁጥጥር ስር እያለች መገንጠል እየቻሉ የመገንጠል ጥያቄ አላቀረቡም። “እንገንጠል” ቢሉ አቢይ “በአንድ አፍ !” ብሎ ይሸናቸው ነበር። እሱ ይህን ፍላጎቱን ለህዝብ በይፋ ባይናገርም አንድ ጊዜ ግን አዳነች አበቤ አፏ አምልጧት ትግሬዎቹን “ከፈለጋቹ መገንጠል ትችላላችሁ” ያለችውን እናስታውሳለን።
አዳነችም ሽመልስም ሌላው የአብይ አፎች ናቸው። እናም አቢይ አህመድ ወልቃይትን ለትግራይ ሰጥቶ በምትኩ ግን የራሳቸውን መንግስት እንዲመሰርቱ ያስገድዳቸዋል።
አቢይ አህመድ አማራንም ትቶ የራሱን ሀገር ሲመሰርት አማራና ትግራይ በወልቃይት ጉዳይ እድሜ ልካቸውን በጦርነት እንዲኖሩ ይገደዳሉ ማለት ነው። ይህን ግን የትግራይም ሆነ የአማራ ህዝብ አይፈልጉትም። አቢይ አህመድ በፋኖ አንድነት ከተደናገጠ በኋላ በጠለምት አስቸኳይ ድራማ በመስራት በትግራይና በአማራ ህዝብ ወይም በአማራ ሕዝብና በፋኖ መካከል ቅራኔ ለመፍጠር እየትሯሯጠ ነው። ይህ ካልተሳካ ገና ብዙ የችኮላ ድራማዎችን ይሰራል። የትግራይ ህዝብም ቢሆን በአቢይ ድራማ ይጠለፋል ብሎ ማሰብ ያስቸግራል።
ከዚህ ይልቅ ፋኖ አሸንፎ አራት ኪሎ ቢገባ የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ ይሆናል። ምክንያቱም ትግራይ ራሷን ችላ መኖር ከባድ ስለሚሆንባት የትግራይ ሕዝብ ወደቀረው ኢትዮጵያ በነጻነት በመንቀሳቀስ ሰርቶ መኖር ስለሚችል ነው። ወልቃይትም ቢሆን በሰላም ገብተው ለመኖር የሚከለክላቸው የለም። አዲስ አበባ ውስጥ የጀመሯቸውንም ፎቆች መጨረስና ቢዝነሳቸውን ማስቀጠል ይችላሉ። ከአቢይ ውድቀት በኋላ በሚፈጠረው ስርአት ወደሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተዘዋውረው በነጻነት ሰርተው መኖር ስለሚችሉ የተዘጋውን የጋምቤላውን እርሻቸውንም ማስቀጠል ይችላሉ ማለት ነው። በሌሎች አካባቢዎችም በግብርናም ሆነ በኢንዱስትሪ እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ ተሰማርተው በነጻነት ሰርተው በሰላም መኖር ይችላሉ ማለት ነው።
ታዲያ ለትግራይ ህዝብ ወልቃይትን ሰጥቶ ከሚያሰናብታቸው ከአቢይ አሀመድ ይልቅ ወልቃይት የአማራ ነው ብሎ ነገር ግን ወልቃይት ውስጥ በሰላም መኖር እንዲችሉ የሚፈቅድላቸው ፋኖ አይሻላቸውም?
➧ እኛ ለርስቶቻችን "ለወሰን እና ማንነቶቻችን" እምንታገለዉ በብአዴን - ብልፅግና በፈለገዉ ልክ ሳይሆን እኛ ባቀድነዉ ነዉ፡፡
➧ የህልዉና ትግሉ እና የማንነት ጉዳዮች ለእኛ የማይለያዩ የሳንቲም ገፅታዎቸ ናቸዉ፡፡
ነገሩ አሁን ጥርት እያለ ነው። የታሉ ፋኖዎች? የሚል አጀንዳ ዛሬ ደምቆ እየተሰማ ነው። ዲጂታል ሰራዊቱ ፎርሙላውን ተከትሎ እየሰራ ነው። ከአንድ ምንጭ የሚቀዳላቸውን አጀንዳ የቃላትም ሆነ የስርዓተ ነጥብ ልዩነት ሳያደርጉ መድረኩን እንዲያጠለቀልቁ ታዘዋል። ቅደም ተከተሉ እንዲህ ነው፥
ጠለምት ላይ የህወሀት ሰራዊት እንዲገባ ግብዣ ይደረግለት፥ በራያም የመንግስት ሰራዊት እንዲወጣና ህወሀት እንዲረከበው መንገዱ ይጠረግለት፥ ከዚያም ህወሀት ገደሉን ሳያይ ሳሩን ብቻ አይቶ ሲገባ ጠብቆ ተኩስ ይከፈትበት፥ ይህ ክስተት 'ህወሀት ጦርነት ከፈተ' የሚል ርዕስ ተሰጥቶት ለሚዲያ ሰራዊቱ ይላክለት፥ የሚዲያ ሰራዊቱም ትንፋሽ የሚያሳጣ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በመክፈት አጀንዳውን ከፍ ያድርገው፥ ህዝቡ 'ፋኖ የታለ?' የሚል ጥያቄ እስኪያነሳ ድረስ የህወሀት ወረራ በሚገባ ይራገብ፥ ህዝቡ ጥያቄውን የማያነሳ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ዲጂታል ሰራዊቱ 'ህወሀት ወረራ ከፈተ- የሚለውን ቀነስ አድርጎ ፋኖዎች የታሉ?' የሚል ጥያቄ በየገጾቻቸውና በየዩቲብና ቲክቶክ መድረካቸው በማንሳት ወደ ምንፈልገው መስመር አጀንዳውን ማምጣት አለብን።
.....ይህ ነው - ፎርሙላው። እስከአሁን አልተዛነፈም። ዛሬ ይኸው ጥያቄ በዲጂታል ሰራዊቱ ተነስቶ ''ፋኖን የበላ ጅብ አልጮህ አለ'' እያሉ ነው።
በአጭሩ የፋኖ አፈሙዝ ብልጽግና ላይ አነጣጥሯል። የፋኖ አይኖች ከብልጽግና ላይ ተተክለዋል። በብልጽግና ዜማ የሚደንስ ፋኖ የለም።
#የብልጽግና "#የህልውና_ስጋት" እና #የፋኖን_አንድነት_የመበተን_ስልት
የብልጽግና መንግስት አሁን ያለውን የጦርነት ድባብ የፈለገበት ምክንያት ከድንበር ጥበቃ ባለፈ፣ በቀጥታ የፋኖን መጠናከርና የአንድነት ጉዞ ለማደናቀፍ የታለመ ነው። ትንታኔው በሚከተሉት ቁልፍ ነጥቦች ይጠቃለላል፦
#፩. #የፋኖ_አንድነት የፈጠረው "የመንግስት መውደቅ" ስጋት
በቅርቡ የታየው የፋኖ ዕዞች መጠናከርና ወደ አንድ አመራር የመምጣት ሂደት ለመንግስት ትልቅ ድንጋጤ ፈጥሯል። ፋኖ በክልሉ ያለውን የህዝብ ተቀባይነት ይዞ በአንድነት ከገፋ፣ መንግስትን ከመቀመጫው የመንቀል አቅም እንዳለው ብልጽግና በሚገባ ተረድቷል። ስለዚህ ይህ ኃይል ሳይቀናጅና ወደ መሃል አገር ሳይገፋ ባለበት እንዲገታ ማድረግ የመንግስት ቀዳሚ አጀንዳ ነው።
፪. "#የትብብር_ስጋት" (The Fear of Alliance)
መንግስት በውስጥ በኩል ትልቅ ስጋት አለው፤ ይህም "ፋኖና ህወሃት የጋራ ጠላታቸው ብልጽግና መሆኑን ተረድተው ቢተባበሩስ?" የሚል ነው። ይህ እንዳይሆንና ሁለቱ ኃይሎች በጥርጣሬና በጠላትነት ተፋጥጠው እንዲቀጥሉ፣ ሆን ተብሎ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ የድንበር አካባቢዎችን ክፍት በማድረግ "የማይጠፋ የእሳት ቃጠሎ" በመሃላቸው መለኮስን መርጧል።
፫. #የፋኖን_አንድነት_በሃሳብ_የመከፋፈል_ሴራ (Internal Fragmentation)
ይህ ጦርነት ቢቀሰቀስ መንግስት በፋኖ ውስጥ ሁለት ተቃራኒ ጎራዎች እንዲፈጠሩ ይጠብቃል፦
"#እንዋጋ" የሚለው ወገን፦ የአማራ ህዝብ ለዳግም ወረራ መጋለጥ የለበትም፣ የህልውና ጦርነት ነው በሚል ስሜት ኃይሉን ወደ ድንበር እንዲያፈስ ይገፋፋል።
"#ወጥመድ_ነው_አንግባ" የሚለው ወገን፦ ይህ የመንግስት ሴራ ነው፣ ዋናው ትግላችን አዲስ አበባ ነው በሚል ጦርነቱን የሚሸሽ ጎራ።
#ውጤቱ፦ በእነዚህ ሁለት ሃሳቦች መካከል የሚፈጠር የጦርነት ስትራቴጂ ልዩነት፣ በቅርቡ የተመሰረተውን የፋኖ አንድነት በውይይት ሳይሆን በውዝግብ እንዲበተን ያደርገዋል።
፬. #የፋኖን_የኃይል_ሚዛን_ማስቀየስ
ፋኖ አሁን ባለው ቁመና መንግስትን ለመጣል የሚያስችል ወታደራዊ ዝግጅት ላይ ነው። መንግስት ግን ይህንን ኃይል "ተፈላጊነቱ በድንበር ጥበቃ ላይ ብቻ እንዲሆን" (Regional containment) ይፈልጋል። ፋኖ በድንበር ጦርነት ከተጠመደ፣ የመንግስትን ስልጣን የሚገዳደርበት ጊዜና ኃይል አይኖረውም፤ ይህም ለብልጽግና የትንፋሽ ጊዜ ይሰጠዋል።
#ማጠቃለያ
ብልጽግና ጦርነቱን የፈለገው ፋኖን በወታደራዊ ጥቃት ብቻ ሳይሆን፣ "በአንድነትና በሃሳብ ልዩነት" ለመምታት ነው። የፋኖ አንድነት በመንግስት የጦር መሳሪያ ሳይሆን በመንግስት "ተንኮልና ሴራ" እንዲፈርስ የታለመ ስልታዊ ቁማር ነው።
ሰበር...ከአላማጣ ከተማ ሸሽተው ወደ ቆቦ ከተማ ከገቡት የአገዛዙ ወታደሮች መካከል በርካቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው መኮብለላቸው ተሰማ!
ይሄንን ተከትሎ በቆቦ ከተማ በአንዳአንድ ሰፈሮች ቤት ለቤት ፍተሻ ሲካሄድ አምሽቷል።
ወታደሮቹ ከትናንት ምሽት ጀምሮ እስከ ንጋት ባለው ቆቦ ከተማ ከገቡ በኋላ ነው ደብዛቸው የጠፋው።
ወታደሮቹ ብዛታቸው ከሁለት ጋንታ በላይ እንደሚሆንና ከነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያ ጀምሮ ሙሉ ትጥቃቸውን እንደያዙ ነው የጠፉት።
የወታደሮቹን መጥፋት ተከትሎ በቆቦ ከተማ መግቢያና መውጫ አከባቢዎች ላይ ብርቱ ቁጥጥር እየተደረገ ሲሆን፡ በአንዳንድ የከተማዋ አከባቢዎች ላይ የቤተ ለቤት ፍተሻ ሲደረግ ማምሸቱን ምንጮች ገልፀዋል።
በተጨማሪም በቆቦ ከተማ ወታደሮቹ ሰፍረውባቸው በሚገኙ ካምፖች ተጨማሪ ወታደር እንዳይከዳ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ከዕዝ መምሪያዎች አስቸኳይ ትዕዛዝ ወርዷል።
ከፋኖ ጋር እየተካሄደ በሚገኘው ውጊያ አከርካሪው የተሰበረው መከላከያ ሰራዊቱ፡ ይህን በድል ሳይወጣ ሌላ አዲስ ጦርነት በመጀመሩ ለመማረክ እንኳን እድል እንደማያገኝ ስለተረዳ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ተሞልቶ እየተበተነ ይገኛል።