es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
4 133
Suscriptores
+224 horas
+4237 días
+1 19130 días
Archivo de publicaciones
ከህዝባችን ጋር ሁነን ትንኞች ሸልከዉ ሊያልፉበት የማይቻላቸዉ አስተማማኝ የደህንነት መረብ ዘርግተናል!!! የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር ሰብሳቢ #ፋኖ_አንሙት_ጌታሁን!! መገናኛ እና ጂፒኤስ ይዞ በስቢል አለባበስ ሲንቀሳቀስ የነበረ የፋሽቱ አብይ አህመድ መታደራዊ መረጃ ዛሬ ታህሳስ 28/2018 ዓ/ም በጀግኖቹ የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ሻለቃ ልጆች ቁጥጥር ስር ዉሏል። ይህ የ304ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሻለቃ መገናኛ ባለሙያ እንደሆነ የተናገረዉ  ደመቀ ታረቀኝ የተባለ የጠላት ደህንነት በምርመራ ወቅት እንዳስረዳዉ ከሆነ ወደ ፋግታ የገባዉ የጠላት ጦር በማህበረሰቡ ላይ ሊፈፅም ያሰበዉን ፀረ አማራነት ተግባር ጨምሮ ብዙ ጉዳዮችን  አጋልጧል። ከሰዉ እስከ ትንኝ ሁሉም ነገር በፋኖ የደህንነት እይታ ስር ነዉ!! አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!! ታህሳስ 28/2018 ዓ/ም

ሰበርርር ያለ የድል ዜና !✊ አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ መቅደላ ወረዳ ፤ ተንታ አጅባር ወረዳና ከለላ ወረዳን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ ፊት እዬገሰገሰ ይገኛል። ሌላው ነገር ጎጃም ጠቅላይ ግዛት የሚባል ኃ
+3
ሰበርርር ያለ የድል ዜና !✊ አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ መቅደላ ወረዳ ፤ ተንታ አጅባር ወረዳና ከለላ ወረዳን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ ፊት እዬገሰገሰ ይገኛል። ሌላው ነገር ጎጃም ጠቅላይ ግዛት የሚባል ኃይል ቤተአማራ ምድር ላይ አንድም ቦታ የለም። ምድረ ቀ--ዳዳ አትበጥረቅ። አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ይችላል። የ801ኛ ኮር ቅምጥሎች ለበአል ተብሎ የተሰረቀውን ሰንጋ በሬ ሳይበሉት በአይናቸው እንደዞረ ተሸበለሉ🤣🤣

🔥#ቡምምምምም🔥 #ምኒሊክ_ቀጠና_ብልፅግና_እየተለበለበ_ነው‼️ ምኒልክ ቀጠና ከለሊቱ 9 አካባቢ ጀምሮ እየተደረገው ባለው ትንቅንቅ ጠላት እንደ ጎመን እየተቀረደደ የጠላት ምሽግ በደም የጨቀየ ሲሆን
🔥#ቡምምምምም🔥 #ምኒሊክ_ቀጠና_ብልፅግና_እየተለበለበ_ነው‼️ ምኒልክ ቀጠና ከለሊቱ 9 አካባቢ ጀምሮ እየተደረገው ባለው ትንቅንቅ ጠላት እንደ ጎመን እየተቀረደደ የጠላት ምሽግ በደም የጨቀየ ሲሆን እጅ የሰጡት ህይዎታቸውን እያተረፉ ሲሆን እምቢኝ ያሉት እየተደመሰሱ፣ ሊፈረጥጡ የሚሞክሩ ተሽከርካሪዎች በአናብስቱ ጥይት #እየጋዩ ይገኛል💪 ከፋኖ ሊያመልጥ የነበረ ወታደራዊ ኦራል በዚህ መልኩ ጋይቷል💪 መረጃው ለቅምሻ ያህል ነው በርካታ ጀብድ ተፈፅሟል💪 28/ዐ4/2018 ዓ.ም

ቀደም ሲል በደጋ ዳሞት በቅርብ ግዜ ደግሞ በቢቡኝ፣ በሞጣ እና በሌሎችም አካባቢወች እየተዘዋወረች ንፁሃንን ስትጨፈጭፍ፣ ስትዘርፍ እና ስትደፍር የነበረችዋ 25ኛ ክፍለ ጦር ሰሞኑን ስናን ላይ በተደረ
ቀደም ሲል በደጋ ዳሞት በቅርብ ግዜ ደግሞ በቢቡኝ፣ በሞጣ እና በሌሎችም አካባቢወች እየተዘዋወረች ንፁሃንን ስትጨፈጭፍ፣ ስትዘርፍ እና ስትደፍር የነበረችዋ 25ኛ ክፍለ ጦር ሰሞኑን ስናን ላይ በተደረገባት ልዩ ኦፕሬሽን ከጠላት ክፍለ ጦሮች ዝርዝር ወጥታለች። በሌላ አገላለፅ የቴወድሮስ እዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር ይችን ክፍለ ጦር ታሪክ አድርጓታል። ነባሩ የክፍለ ጦሯ አዛዥ ኮሎኔል ብርሃኑ በጡረታ መገለሉን ተከትሎ በግዜያዊነት ክፍለ ጦሯን ይመራት የነበረው ሻለቃ ከበደም በሰሞኑ ውጊያ ከባድ ቁስለኛ ሆኖ ከአገልግሎት ውጭ ተደርጓል። ይህንን ተከትሎ ምሊሻ እና አድማ ብተና በመሰብሰብ ክፍለ ጦሯን ያለች ለማስመሰል እንዲሰራ በጀነራል ብርሃኑ ጥላሁን ትዕዛዝ የተሰጠው እና ፎቶው ከታች ያስቀመጥነው የ75ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል መብራህቱ ኃይሌ ጭንቅ ውስጥ ገብቷል። ክብር የብልፅግናን የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ እንደ ጉም ላተነኑት ጀግኖቻችን! አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ

"የኮረኔል ውዴ 25ኛ ክ/ጦር የነፍስ አድን ጥሪ ለ75ኛ ክ/ጦር አቅርባለች" 206ኛ ኮር ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም =================================== በዚህ በተንጣለለው አዳራሽ ለዓይን ሳይሞሉ ጥርሳቸው እረግፎ ድዳቸው አግጥጦ የሚታዩ ወታደሮች ታህሳስ 24/ 2018 ዓ.ም በስናን ቀጠና ወደ ጮቄ ተራራ ለመውጣት ከተሰማሩት ከኮረኔል ውዴ 800 ሰራዊት መካከል ከሞትም ከምርኮም የተረፉ የ25ኛ ክ/ጦር አባላት ናቸው። እነዚህ ወታደሮች ቆሌውም አድባሩም ከድቷቸዋል የጮቄ ተራራ ውርጭ ከ206ኛ ኮር የጥይት ሀሩር ጋር ተደባልቆ የዘነበባቸው በረዶ እስከ አሁን እያንቀጠቀጣቸው ይገኛሉ። የታጠቁትን 8 ብሬን ፣ አምስት ስናይፐር፣ 4ዲሽቃ፣ ሁለት ሞርተር፣ ከ230 በላይ ክላሽና ከ61 በላይ የሰራዊት አባል አስረክበው ሻለቃ መሪዎቻቸውን በባቄላ ማሳ ተዘርረው አስክሬናቸውን እየረገጡ የፈረጠጡ ከየ ሻለቃው ተሸራርፈው ከሞትም ከምርኮም የተረፉ የሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን የልጅ ልጆች ናቸው። ብዙዎች እስካሁን በሰመመን ውስጥ ሁነው እየተከዙ ሲሆን ጥርሳቸውን የሚያንቀጫቅጩ እና በቁማቸው የሚቃዡትን እንዲያረጋጋ የተላከው ደግም የ75 ክ/ጦር አዛዥ ኮረኔል መብርሕቶም ሀይሉም የሚመራውን ሰራዊት ይዞ ዕረቡ ገበያ መግባቱ ያቺ ስትንቀዠቀዥ የነበረችው ክ/ጦር መበተኗን እንድናስብ ያስገድደናል። 25ኛ ክ/ጦር ከሞጣ እስከ ደጋ ዳሞት ከፍኖተ ሰላም እስከ ደጀን ከተልከፈከፈች በኋላ በአራት መከራክር ግርጌ እርግፍግፏ ወጦ መበተኗን ተከትሎ ናሙናዋንም ስሟንም ለማትረፍ የቀሩ ሁለት ሻምበሎችን 75ኛ ክ/ጦር ተረክባ እያፅናናች ትገኛለች። የስናን ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ከዚህ ቀደም የዘገብናቸውን ድሎች በማጠናከር ዛሬ በሚስጢር የተደረገውን ስብሰባ ይፋ ስላወጣችሁል እያመሰገን የ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ታማኝ በእውነታ ላይ የተመሰረቱ የሰራዊታችንን ተጋድሎና ድል ያለ መሸራረፍ እንደሚያቀርብ በዚህ አጋጣሚ ልናረጋግጥ እንወዳለን። አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የአደረጃጀት ዜና፤ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ትግሉ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የትግሉ ሂደት ምን ይመስል እንደነበር ጥልቅ ግምገማ እና ምክክር ካደረገና የወደፊት የትግል አቅጣጫዎችን በመለየት ለቀጣይ ትግሉን ወደተሻለ ምዕራፍ ያሸጋግራሉ ያላቸውን አርበኞች ወደፊት ለማምጣት ያስቻለ የአደረጃጀት ሪፎርም ከትንናንት በስቲያ ማለትም ታህሳስ 26 ቀን 2018 ዓ/ም አድርጓል። በዚህም መሰረት ስማቸው ከስር የተጠቀሱት አርበኞች ኮሩን እንድመሩ ተሰይመዋል፤ 1. የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ - አርበኛ አብነው ታደሰ 1.1. ምክትል ሰብሳቢ እና ወታደራዊ አዛዥ - አርበኛ እንድሪስ ይማም 1.2. ምክትል ወታደራዊ አዛዥ - አርበኛ አበበ መኩሪያ 1.3. ምክትል ሰብሳቢ እና የፓለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ - አርበኛ ብሩክ ሞገስ 1.4. የፓለቲካ ጉዳዮች ም/ኃላፊ - አርበኛ ተመቸው ጀንበሩ 2. ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ - አርበኛ ጌትነት አበበ 2.1. ዘመቻ መምሪያ ም/ኃላፊ - አርበኛ ጎሹ ታረቀኝ 3. የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ - አርበኛ ቃለአብ ወርቅዬ 3.1. የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ም/ኃላፊ - አርበኛ አርበኛ ሙሉጌታ አረጋው 4. የመዝናኛ እና ኪነጥበብ ዘርፍ ኃላፊ - አርበኛ ካሣሁን ታደሰ 4.1. የመዝናኛ እና ኪነት ዘርፍ ም/ኃላፊ - አርበኛ አባተ አብነው 5. አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ - ኦንጅነር ተመስገን ለማ 5.1. አስተዳደር ዘርፍ ም/ኃላፊ - አርበኛ ሼህ ይማም ሙሀመድ 6. የሎጅስቲክስ አቅርቦትና ስርጭት ኃላፊ - አርበኛ አያሌው አሰፋ 6.1. የሎጅስቲክስ አቅርቦትና ስርጭት ም/ኃላፊ - አርበኛ ኤሊያስ በለጠ 7. የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ - አርበኛ አህመድ ሁሴን 7.1. የፋይናንስ ዘርፍ ም/ ኃላፊ - አርበኛ አበበ ነጋ 8. ኦድተር - አርበኛ መከተ ካሳው 9. ኦርድናንስ- አርበኛ በፍቃዱ ገንብር 9.1. ምክትል ኦርድናንስ- አርበኛ አላምረው ደስታ 10. የወታደራዊ ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ - መቶ አለቃ በላይ መከተ 10.1. የወታደራዊ ስልጠና ዘርፍ ም/ኃላፊ - ኮማንዶ ኡመር ምሳው 11. የመረጃ እና ደህንነት ኃላፊ - አርበኛ ×××××××××× 11.1. የመረጃ እና ደህንነት ም/ ኃላፊ - አርበኛ ××××××× 12. የጤና ዘርፍ ኃላፊ - አርበኛ መርከብ አበራ 12.1. የጤና ዘርፍ ም/ኃላፊ - አርበኛ ሚካኤል ጋሻው 13. የሰው ሀይል ዘርፍ ኃላፊ - አርበኛ ተፈራ ብሩ 13.1. የሰው ሀይል ዘርፍ ም/ኃላፊ - አርበኛ ታደሰ መሰረት 14. የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ - አርበኛ ሳራ ካሳዬ 14.1. የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ም/ኃላፊ - አርበኛ ሀይማኖት ጎቼ 15. የህግ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ - አርበኛ ታምራት በሽር 15.1. የህግ አገልግሎት ዘርፍ ም/ኃላፊ - አርበኛ ሰይድ ካሳ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የአደረጃጀት ሪፎርም በሰራ በማግስቱ የውጊያ እቅድ በማውጣት በስሩ ላሉት አምስቱም ክፍለ ጦሮች ስምሪት ሰጥቶ በምዕራብ ወሎ ግንባር በዛሬው እለት ከፍተኛ የጦር ሜዳ ጀብዱ ተፈፅሟል። ዝርዝሩ በምሽት ጥቅል የውሎ ዘገባችን የሚካተት ይሆናል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ ቃለአብ ወርቅዬ ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት አስታውቋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም

ይህ ትግል በአሸናፊነት የሚደመደመው በመሣሪያ ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በያዝነው የሞራልና የሰብአዊነት የበላይነት ነው። የፍቅር ጥይት፤ ለአገዛዙ ወንበር የመጣኸው ወታደር ሆይ፣ በሕዝብ እቅፍ ውስጥ መሆንህን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን። በነፃነትና በሕልውና ትግል ግንባሮች ላይ የምናየው ትዕይንት፣ ዓለምን የሚያስደንቅና የትግላችንን መንፈሳዊ ልዕልና የሚያሳይ ነው። አንተ! ወደህም ይሁን ተገደህ የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም፣ ሕዝብን በድሮንና በከባድ መሣሪያ እንድትጨፈጭፍ ታጥቀህ የመጣህ ወታደር ዙፋን ጠባቂ ወታደር ነበርህ። ነገር ግን፤ የተማረክህ ዕለት የገጠመህ ሞት ሳይሆን ሕይወት ነው፤ በጥላቻ የታወረ አፈሙዝ ሳይሆን በፍቅር የተዘረጋ የሕዝብ እጅ ነው። አንተ! ልትገድለው፣ ቤቱን ልታፈርስና ልጆቹን ልታሳጣ የመጣኸው ይኽ "ጠላት" ያልከው ሕዝብ፤ ዛሬ የቆሰለ አካልህን በጨርቅ እየጠቀለለ ያክምሃል። ጥይት ልታጎርሰው የመጣኸው ሕዝብ፣ ካለው ጥቂት ጉርሻ አከፋፍሎ አብልቶሃል። ይህ ተግባር ትግላችን ከወንበርና ከጥቅም በላይ መሆኑን የሚያሳይ ከፕሮፖጋንዳ ያለፈ ድንቅ ተግባር ነው። እኛ የምንዋጋው የሥርዓቱን ግፍ እንጂ የአንተን ማንነት አይደለም። ደጋግመን እንደተናገርነው፣ ትግላችን የጥላቻ ሳይሆን የነፃነት፣ የፍትሕና የእኩልነት ነው። ዓላማችን፤;እኩልነት የጠፋባትን፣ ፍትሕ የራቃትንና በንጹሐን ደም የምትታጠበውን ሀገር ነፃ ማውጣት ነው። አገዛዙ አንተን ለሥልጣኑ "መሣሪያ" አድርጎ ሲጠቀምብህ፣ እኛ ግን እንደ "ሰው" እናከብርሃለን። አንተን መግደል ሳይሆን አንተ ጋር የተሸረበውን የባርነት ሰንሰለት መበጠስ የትግላችን አካል ነው። እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም የምናስተላልፈው መልዕክት! በየግንባሩ ያላችሁና ለአገዛዙ ጥላቻ ተሰልፋችሁ የምትገኙ ወታደሮች ሆይ፤ አስተውሉ! ጠላታችሁ ማን ነው? ጠላታችሁ የተራባችሁ ዕለት የሚያበላችሁ፣ የተጠማችሁ ዕለት ውኃ የሚያጠጣችሁ ይህ የዋህና ጀግና ሕዝብ ነውን? በገዛ ወገኑ ላይ ድሮን የሚያዘንብ አገዛዝ ወይስ የቆሰለ ምርኮኛን የሚያክም ሕዝብ የትኛው ነው ለሀገር የሚቆረቆረው? ለአገዛዙ ሰራዊት የቀረበ የሕሊና ጥያቄ፤ ወታደር ሆይ! ይህን ፎቶ በጥልቀት ተመልከተው፤ የታጠቀው ማን ነው? አንተ የጥፋት መሣሪያ ታጥቀህ መጣህ፤ አርሶ አደሩ ግን የሕይወት መሣሪያ የሆነውን "እንጀራ" ይዞ ቀረበልህ። ጠላትህ ማን ነው? አዛዦችህ "ሽፍታና ጽንፈኛ" ብለው ሊያስገድሉህ የላኩህ ሕዝብ፣ ዛሬ በረሃብ እንዳትዝል የላብ እህሉን እያቀረበልህ ነው። ለማን ትሞታለህ? አንተ ቆስለህ ስትማረክ ጀርባውን የሰጠህ አገዛዝ ወይስ የቆሰለ አካልህን አክሞ ያበላህ ሕዝብ የትኛው ነው ለክብርህ የሚመጥነው? ይህ ትግል በአሸናፊነት የሚደመደመው በመሣሪያ ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በያዝነው የሞራልና የሰብአዊነት የበላይነት ነው። አፈሙዝ ታጥቀህ ልትገድለው ብትመጣም፣ ሕዝባችን በፍቅርና በሰብአዊነት ይዞሃል። ይህ ፍቅር ነገ ለምትፈጠረው አዲስና ፍትሐዊት ኢትዮጵያ መሠረት ነው። ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ማውቅ ያለበት ዋና ነገር፤ ይህ ትግል የሁለት ታጣቂዎች ሽኩቻ አይደለም። ይህ ትግል በግፈኛ አምባገነንነት እና በሰብአዊነት መካከል ያለ ግብግብ ነው። አገዛዙ በንጹሐን ላይ ድሮን ሲያዘንብ፣ የነፃነት ኃይሎችና ሕዝቡ ግን ለምርኮኞች የጄኔቫን ስምምነት (Geneva Convention) በላቀ ሁኔታ በተግባር እየተረጎሙት ይገኛሉ። ዓለም ሊያውቀው የሚገባው ሀቅ ቢኖር፣ በኢትዮጵያ ምድር ፍትሕንና ሰላምን ሊያመጣ የሚችለው አፈሙዙን ለሰው ልጅ ክብር ዝቅ የሚያደርገው በፋኖ ኃይል እንጂ፣ ሕዝቡን እንደ ጠላት ፈርጆ የሚጨፈጭፈው አምባገነን ሥርዓት አለመሆኑን ነው። ጥላቻን በፍቅር እናሸንፋለን! ትግላችን ለፍትሕ፣ ለእኩልነትና ለነፃነት ነው! ክብር ለሰብአዊነት ዘብ ለቆመው ሕዝባችን! አዲስትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!         ታህሳስ 28/2018ዓ.ም

በጉጉት እየጠበቅን ነው! ​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የሚያወጣው ሰበር ዜና በአካባቢው ያለውን ወታደራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚቀይር ትልቅ መረጃ እንደሚሆን ይታመናል። በተለይ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም ከተመዘገበው ድል በኋላ የሚመጣ መረጃ በመሆኑ የሁኔታውን ግስጋሴ ያሳያል። ​መረጃው እንደደረሰን እናደርሳለን፦

ተጨማሪ ዜና ከወደ ጣና ደቅ ደሴት !! ከቀናት በፊት በ102ኛ ኮር አባላት ተመተው ከሰመጡት ጀልባዎች መካከል አንዷ አሁን በብዙ ፍለጋ ተገኝታለች ። አካባቢው ላይ ካሜራ ማንሳት ፣ ስልክ ማውራት አ
ተጨማሪ ዜና ከወደ ጣና ደቅ ደሴት !! ከቀናት በፊት በ102ኛ ኮር አባላት ተመተው ከሰመጡት ጀልባዎች መካከል አንዷ አሁን በብዙ ፍለጋ ተገኝታለች ። አካባቢው ላይ ካሜራ ማንሳት ፣ ስልክ ማውራት አይቻልም በሚል ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ ቢሆንም ከቦታው እንዳረጋግጠነው አሁን የተገኘችው ጀልባ 70 ኮማንዶ ይዛ እንደነበር በአንደበታቸው ተናግረዋል ። ጀልባዋ ስትገኝ አንድም አስክሬን ማግኘት አለመቻላቸውን አረጋግጠናል ። ሁለተኛዋ ጀልባ በከባድ የባህር ላይ አሳሾች እየተፈለገች ነው ። የሰጠሙት ኮማንዶዎች ቁጥር ባለፈው ከጠቀስነው በእጥፍ እንደጨመረ እና እስከ 150 እንደሚደርስ አረጋግጠናል ። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!

ብልፅግና 25ኛ ክፍለ ጦር መደምሰሷን አመነ ! ============== በተከታታይ በሰናን ፋኖ የተጎናፀፈውን ድል ስንዘግብ መቆታችን ይታወቃል:: 25ኛ ክፍለ ጦር ጡት ቆራጭ ወራሪ ሙት ቁስለኛ እና
+1
ብልፅግና 25ኛ ክፍለ ጦር መደምሰሷን አመነ ! ============== በተከታታይ በሰናን ፋኖ የተጎናፀፈውን ድል ስንዘግብ መቆታችን ይታወቃል:: 25ኛ ክፍለ ጦር ጡት ቆራጭ ወራሪ ሙት ቁስለኛ እና ምርኮኛ ሆና ሙሉ ለሙሉ መደምሰሷ በወቅቱ ተዘግቧል:: 25ኛ ክፍለ ጦር መደምሰሷን ተከትሎ 75ኛ ክፍለ ጦር ወደ ሰናን ወረዳ መግባቱን ይህ መረጃ ጠቁሟል:: 28/04/2018 ዓ.ም

አማራነታቸው ወንጀል ሁኖ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ያለፍትህ እየተሰቃዩ የሚገኙ ጋዜጠኞች የሰባአዊ መብት ተሟጋችች ሙህራኖች ኤሊቶች የህሌና እስረኞችን እናስታውሳቸው 🙏 ልባሙ ፋኖ

ቅድሚያ ለሰብአዊነት እንሰጣለን!!! ከዓላማችን ዝንፍ የማንል ድርጅታችንን እንዳይን ብሌን የምንጠብቅ የድርጅታችንን ተልእኮ በአግባቡ ለታሪክ በሚመጥን ደረጃ እየፃፍን እንገኛለን። ቀበኞችና አስመሣዮች
+1
ቅድሚያ ለሰብአዊነት እንሰጣለን!!! ከዓላማችን ዝንፍ የማንል ድርጅታችንን እንዳይን ብሌን የምንጠብቅ የድርጅታችንን ተልእኮ በአግባቡ ለታሪክ በሚመጥን ደረጃ እየፃፍን እንገኛለን። ቀበኞችና አስመሣዮችን በአደባባይ እናሰጣቸዋለን። ድል ለአማራ ፋኖ!!!

ቀን 28/04/2018ዓ/ም አውራ እንደሌላት ንብ ይገነፍል ጀመር አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ#109ኛ ኮር#99ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሻለቃ ስቦ በማስከዳት ስራዋን አሃዱ ብላ ጀምራዋለች በዛሬው
+1
ቀን 28/04/2018ዓ/ም አውራ እንደሌላት ንብ ይገነፍል ጀመር አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ#109ኛ ኮር#99ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሻለቃ ስቦ በማስከዳት ስራዋን አሃዱ  ብላ ጀምራዋለች     በዛሬው ቀን ማለትም 28/04/2018ዓ/ም እራሱን 23ኛ ክ/ጦር ብሎ ከሚጠራው ሰራዊት ውስጥ የአገዛዙ ብሔርተኝነት አልተስማማንም በወገናችን ላይ ጥይት አናጮህም በማለት አመዲ ኪሩዲ እና ድንቃየሁ ይሳቅ  የተባሉ ወታደሮች የ99ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል። Silesh Alemayehu የ99ክ/ጦር ህዝብ ግንኘነት

በኦሮሚያ ክልል ደገም ወረዳ ዓሊ ዶሮ እና ኢስት አፍሪካ ሲሚንቶ ፋብሪካ አቅራቢያ በሦስት ተሽከርካሪዎች ላይ በተሳፈሩ መንገደኞች ላይ ከባድ ጥቃት ተፈጸመ። 👉 ስድስት ሕይወታቸው አልፏል። 👉 20 የሚሆኑት ሆስፒታል ገብተዋል። 👉 85 በላይ የሚሆኑት በታጣቂዎቹ ታግተው ተወስደዋል! ጥቃት የተፈጸመባቸው ለገና በዓል ከአዲስ አበባ ወደ ዐማራ ክልል ተጓዦች ናቸው! ጥቃቱ የተፈጸመው ዛሬ ታኅሣሥ 27/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ገደማ ነው!! ©በለጠ ካሣ

የአ.ፋ.ብ.ኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ(ትልቁ) አርበኛ ሲሳይ አሸብር አርበኛ አስምሮ ፍቃዴ የኛ ኩራቶች ልክ እንደ አባቶቻቸው በሚያስቀና ፍቅር ፣በፅናት፣ በዕምነት ፣
+2
የአ.ፋ.ብ.ኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ(ትልቁ) አርበኛ ሲሳይ አሸብር አርበኛ አስምሮ ፍቃዴ የኛ ኩራቶች ልክ እንደ አባቶቻቸው በሚያስቀና ፍቅር ፣በፅናት፣ በዕምነት ፣በተስፋ ፣ግዙፍ ጦር በመምራት ለአማራ ህዝብ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ። በጣም ነው የምሳሳላችሁ ወንድሞቼ ክፉ አይንካችሁ ሰማዕቱ ሁሌም በድል ያጎናፅፋችሁ። ድል ለአማራ ህዝብ ድል ለአማራ ፋኖ እውነት ያሸንፋል 💪💪

የአብይ አህመድ አገዛዝ 17 ንፁሃንን በግፍ ጨፈጨፈ! ******// ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም አዮ ጓጉሳ ወረዳ እሁዲት የመሸገው የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ጨፍጨ*ፊ ፀረ አማራ ሠራዊት ከምሽቱ  11 ሠዓት አካባቢ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109 ኮር የ88ኛ ክ/ጦሯን ቃኝና መሀንዲስ ሻለቃን (6ኛ ሻለቃን) ለማጥቃት እንቅስቃሴ አድርጓል። መረጃው የደረሳት ሻለቃዋ ጠላትን በደፈጣ መምታት ችላ ከ8 በላይ አቁስላ ከ10 በላይ ቅጥረኛ ጨፍጫፊውን ወደ ማይመለስበት ሽኝታዋለች። ያልጠበቀው የምት ውርጅብኝ የገጠመው ይህ ፀረ አማራ ቡድን ወደ ኋላ ተመልሶ አዮ ቀበሌ በመግባት 16 ንፁሃን ወጣቶችን ከመዝናኛ ቦታ እና ከስራ ቦታቸው ሠብስቦ በግፍ እረሽኗል። ስርዓቱ ፋኖን ለማጥፍት የአማራ ህዝብ ማጥፍት እንደ ወታደራዊ ስልት እየተጠቀመ ያለ እና አማራን መዝረፍ፣ መግደል፣ ሐብት ንብረት ማውደም፣ ፆታ እና እድሜ ሳይለይ በቡድን መድፈርን እንደ ተጨማሪ የጦር ስልት አድርጎ እየተጠቀመ ያለ ከኢትዮጵያ ባህል ያፈነገጠ የባዕድ ተልዕኮ አንግቦ ሁለ ገብ ጦርነት የከፈተ አለማቀፉን የጦር ህግን የማይቀበል የጦር ወንጀለኛ የሆነ አሸባሪ ኃይል ነው። በግፍ ከተረሸኑት መካከል:- 1. ዳዊት ቀናው 2. ተውስል ምሬ 3. ብርሃኑ አረጋ 4. ክንዱ ታደሰ 5. እንዳለ ተስፉ 6. ሽኩር ጋሻው 7. አህመድ ሁሴን 8. አውላቸው አለነ 9. ትግስቱ ጌታቸው 10. ቸኮለ አስራደ 11. ምንባለ ቢተው እና 6 የቀን ስራ የሚሰሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ይገኙበታል። ይህ ግፈኛ ፀረ አማራ ቡድን አስከሬን አላስነሳም ያለ ሲሆን ወንድሞቻችሁ ናቸው የገደሉን እኛም እናንተን እንገላለን እያለ እንደረሸናቸው ማረጋገጥ ተችሏል። ቡድኑ ሌላ ተጨማሪ ከ10 በላይ ንፁሃን ወጣቶችን አግቶ ወደ እሁዲት ወስዷል። 👉ይህ አሸባሪ ስርዓት ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም ሌሊት ከቡራፈር ቀበሌ 6 እና ከሻምብላ ቀበሌ 2 በድምሩ 10 አ/አደሮችን አግቶ መሰወሩ ይታወሳል። ለሞቱት ነፍሳቸውን ይማር! ለወዳጅ ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን!! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም