ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más3 954
Suscriptores
+22224 horas
+3937 días
+1 35930 días
Archivo de publicaciones
አሳምነው ክፍለ ጦር ለከበባ የመጣን ጠላት ስበው በማስገባትና በርካታ ሃይሉን በመደምሰስ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::
የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ዛሬ ጥር 27/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ ከወልድያ ከተማ በመነሳት በርካታ እግረኛ ሰራዊት ወደ ጃርሳ ታዳጊ ከተማ ቢያዘምትም አሳምነው ክፍለ ጦር 4ኛ እና 5ኛ ሻለቃ ባግባቡ በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ በርካታ ሃይል ሙትና ቁስለኛ አድርገው ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦር ጠላትን ተደጋጋሚ ጊዜ የመቱበት ወልድያ ከተማ ዙሪያ ዛሬም የፋሽስቱ ሰራዊት መቀበሪያ ሆኗል:: ጀግኖቹን ለመክበብና ለማፈን የተንቀሳቀሰው የጠላት ሰራዊት የጀግኖቹን ክንድ ቀምሶ ወደመጣበት ተመልሷል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም
የጥንቃቄ መልዕክት
በሰሜን ሸዋ ዞን የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል ተብሏል። በቀጠናው የምትገኙ ፋኖዎች የመረጃ መረባችሁን እንድታስተካክሉ ይሁን‼️
ለወልድያ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ የጥንቃቄ መልክት!
የሰሜን ወሎ ዞን እና የወልድያ ከተማ አመራሮች ፋኖን ከህዝብ እንነጥላለን በሚል ስሌት ባለፉት ሁለት አመትና ከዛ በላይ ጊዜያት ህዝቡ ላይ በርካታ ግፎች መፈፀማቸውን በማስረጃ ማጋለጣችን ይታወቃል::
ይህ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ተግባር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎ ከዚህ በታች በተዘረዘሩትና በተጠቀሱት ስምና ስልክ ቁጥሮች እየተደወለ በፋኖ ስም ከማህበረሰቡ ገንዘብ አምጡ እያሉ እንደሆነ በማስረጃ ለማረጋገጥ ችለናል:: ይህንን ድርጊትም የሚፈፅሙት በስውር በሚሊሻ እና አድማ ብተና አባላቶች እንደሆነ አረጋግጠናል!
ስለሆነም ጀምበር የጠለቀችበት ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ጣረ ሞት ላይ በመሆኑ ስልጣኔን ያቆይልኛል ያለውን ሁሉ ከማድረግ አይቆጠብምና ህዝባችን ይህንን በመገንዘብ መወሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች ሁሉ እንዲወስድ ስንል መልክታችንን እናስተላልፋለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 27/2018 ዓ.ም
የምስራቅ አማራ ፋኖ በሂደት ውስጥ ያለፈባቸውን መዋቅራዊ ለውጦች እና የስም ሽግግሮች ማየት፣ የትግሉን እድገትና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የመጣውን የዓላማ አንድነት ለመረዳት ይረዳል።
እርስዎ በጠቀሱት ቅደም ተከተል መሰረት፣ የሽግግሩን ታሪካዊ ሂደት እንደሚከተለው በዝርዝር ማየት ይቻላል፦
1. የምስራቅ አማራ ፋኖ (የመጀመሪያው መሠረት)
ይህ አደረጃጀት በዋናነት በወሎ (በተለይም ራያ ቆቦና ወልዲያ አካባቢ) በነበረው የወረራ ስጋት ምክንያት የተነሳ የአካባቢ መከላከያ ባህሪ ነበረው።
* መነሻው፦ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት አካባቢውን ከጥቃት ለመከላከል በገበሬውና በከተማው ወጣት የተመሰረተ ነበር።
* ሚናው፦ የህልውና ትግሉን የመቀስቀስና ህዝቡን የማንቃት ትልቅ የቤት ስራ ሰርቷል።
2. የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አምሓራ)
የትግሉ ስፋት እየጨመረ ሲመጣ፣ አደረጃጀቱ ከአካባቢ ጥበቃ አልፎ መላውን የወሎ ክፍለ ሀገር (ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን እና ዋግ ኽምራን) ለማስተባበር የአማራ ፋኖ በወሎ በሚል መጠሪያ ራሱን አደራጀ።
* ቤተ አምሓራ፦ ይህ መጠሪያ ፋኖው በታሪካዊው የወሎ (ቤተ አምሓራ) ምድር ላይ ያለውን ጥልቅ መሰረትና ማንነት የሚያንፀባርቅ ነበር።
* ዓላማው፦ በወሎ ምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፋኖ ቡድኖችን ወደ አንድ ማእከላዊ ዕዝ የማምጣት ጅምር ነበር።
3. የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይለ ምንሊክ ዕዝ (ምስራቅ አማራ ቀጠና)
ይህ ምዕራፍ የፋኖ አደረጃጀት ከቀጠናዊ ስሜት ወጥቶ ወደ ብሔራዊና ስትራቴጂካዊ መዋቅር የተሸጋገረበት ወቅት ነው።
* ኃይለ ምንሊክ ዕዝ፦ ታሪካዊውን ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምንሊክን ስም በመያዝ፣ ትግሉ ለአንድ አካባቢ ብቻ ሳይሆን ለመላው አማራ ህዝብ መሆኑን አወጀ።
* ምስራቅ አማራ ቀጠና፦ በዚህ ዕዝ ስር ምስራቅ አማራ (ወሎ) እንደ አንድ ግዙፍ የጦር ቀጠና ሆኖ ተደራጀ። ይህም ወታደራዊ ስልጠናውና አመራሩ ይበልጥ እንዲቀናጅ አደረገ።
4. የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን/AFBN)
በመጨረሻም፣ ትግሉ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ድጋፍ እንዲኖረው፣ እንዲሁም መላውን የፋኖ ኃይል በአንድ ማዕከላዊ የፖለቲካ ፕሮግራም ለመምራት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ተመሠረተ።
* ተቋማዊ ሽግግር፦ ከአንድ ወታደራዊ ዕዝነት ወደ ሰፊ "ንቅናቄ" (Movement) ተሸጋገረ።
* አሁናዊ ሁኔታ፦ አፋብን በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ውስጥ ካሉ ግንባር ቀደም አደረጃጀቶች አንዱ ሆኖ፣ ሰፊ ሠራዊትና ግልጽ የሆነ የትግል ግብ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ከ10 የቀበሌ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ውይይት ተካሔደ
➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾
ጥር27/2018ዓ.ም
ከዓለም ካርታ ሊያጠፋን የመጣን ጠላት በልኩ ለህዝባችን በየቀኑ ማስረዳት የእኛ የአዲሱ ትውልድ ስራ ነው።
ቢቡኝ ወረዳ በቴዎድሮስ ዕዝ በ201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር ውስጥ የሚገኝ 19ቀበሌዎችና 3የወረዳ ከተማ ያሉት ወረዳ ሲሆን ከጅምሩ የአማራ ትግል ሲጀመር በህዝባዊ እንቢተኝነት የጀመረ የተፈጥሮ ጀግንነት ያለው ማህበረሰብ የሚገኝበት 16ቱን ቀበሌዎች ፍፁማዊ አማራዊ አደረጃጀት ከህዝባዊ ኃይል እስከ አ.ፋ.ጎ እናም እስከ አ.ፋ.ብ.ን የትግል ደረጃ ድረስ የማይዋልል አደረጃጀት ያለበት ቀጠና ነው።
ሆኖም በነበረው የትግል ግለትና አሁናዊውን የትግል ደረጃ ለ8 የቀበሌና ለ2 የከተማ ወሳኝ ኮሚቴዎች ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል።
በስብሰባው ትግልን የወከለና ህዝብን ያማከለ የአካሔድና የስርዓት አጀንዳዎችን አንስተን በጋራ መግባባት አብሮነትን ወንድማማችነትን አሳይተናል።
በስብሰባው የ54ኛ ክ/ጦር አመራሮችና የወረዳው ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች በጋራ ሁነው የቀጠናዉን የጮቄነት ግርማ አይደፈሬነት በትናንት ማንነቱ እንዲቀጥል አቅጣጫ ተቀምጧል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮርህዝብ ግንኙነት
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በደም የተመሰረተ ድርጅት ነው።
ደም የገበርንበት ትግል ለድል እንዲበቃ ደግሞ መሰረታዊ አጀንደዎቻችን ላይ ልናተኩር ይገባል!!
የድርጅታችን ዋና ዋና አጀንዳዎች ውስጥ ግንባር ቀደሙ የአማራን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ ነው።
ስለሆነም ድርጅታችን አፋብን ትኩረት አድርጎ ከሚሰራባቸው ነገሮች አንዱ የአጀንዳ እና የአላማዎቻችን ተደራሺነት ላይ ነው።
ተደራሺነት የሌለው አጀንዳ ህዝባዊ መሰረት የለውም።
ስለዚህ የትግላችን ማህበራዊ መሰረት የሆነው የአማራ ህዝብ የአፋብንን አጀንዳዎች አንድ በአንድ ሊያውቃቸው እና በመርህ እና በዕሴቶቻችን ዙሪያ ያለውን ነገር በሙሉ ማህበራዊ ስርፀት እንዲኖራቸው መስራት አለብን🙏❤
በተለይም አፋብን እንደ ድርጅት በፍጥነት የሚከተሉትን ስራዎች በትኩረት መስራት መልካም ነው ብየ አስባለሁ።
01.ስትራቴጅካዊ ስራዎችን መለየት
02.መዋቅራዊ ስራዎችን ማጠናቀቅ
03.ስልታዊ ዕቅዶችን ማቀድ ወደ ተጨባጭ ስራዎች መግባት ይጠበቅብናል!!
የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰሩ ተግባራትን መለየት ለድርጅዊ ስርፀታችንም ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ልናስተውል ይገባል!!
ተቋም መትከል እና ድርጅታዊ ተደራሺነትን መፍጠር የሚቻለው በመዋቅራዊ ስራችን መስፋት እና መጥበብ በመሆኑ የትግላችንን አጀንዳዎችን በፍጥነት ማዳረስ ለዋናው ድላችን ምቹ ሁኔታ መሆኑንም በጥልቀት ማሰብ ይጠይቃል።
መደረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሸንፋል!!
ዝንታለም አማራ
ወይራው አማራ
ሰበር የድል ዜና‼️
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና
አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር ድል ተቀናጀ ።
ጥር 27/05/2018 ዓ.ም፡ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር ጠላት ላይ ባደረሰው የደፈጣ ምት ድል መቀዳጀቱን ተገለፀ ። የጦርነት አዙሪት የተጠናወተው የብልፅግው መንግስት ከፋኖ ጋር የገባውን ጦርነት ከመንበረ-መንግስቱ ሊያወረደው ከጫፍ ደርሶ በመንገዳገድ ላይ እያለ የሚደግፈውና ከጎኑ ያሰለፋቸው ተዋጊ ሰራዊቶች ከመሠረታዊው ወታደር እስከ ኮሎኔን እና ጀነራልነት ማዕረግ ያላቸው እየከዱት ፋኖን መቀላቀላቸው ያሰግው ብልፅግና አዲስ የማደናገሪያ ዜና ሲሰራ እንደከረመ ሰሞኑን መዘገባችን የሚታወስ ነው ።
ይህም "ቀይ ባህርን ላስመልስላችሁ ነው በግድ ደግፉኝ" በማለት የተመናመነበትን ሰራዊት በወደብ ሰበብ ለመሙላት ከቅስቀሳ ወደ አፈሳ መሻገሩን ሁሉም ያወቀው ፥ ፀሐይ የሞቀው ሀቅነው ። ታዲያ ይህንን ተግባሩን ይመሩልኛል ያላቸውን በሰመ አማራ በጥቅም የተገዙ ሆድ አደር ባንዳ ሚሊሻና ፖሊስ በማስቀደም የለመደውን አፈሳ ለማፈስ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኢራንቡቲ ቀበሌ ቆቦ አካባቢ የተንቀሳቀሰው ሰራዊት ላይ፤ በነበልባል ክፍለ ጦር አራተኛ (፬ኛ) መብረቁ ሻለቃ በተወሰደበት የደፈጣ ምት ከፍተኛ የሰራዊት አባላቶቹ እስከ ወዲያኛው የተሸኙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ መንገድ ሲመሩ ከነበሩት የእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎች ውስጥ
1ኛ. ፲ አለቃ ዘላለም አስናቀ ---- ከዚህ በፊት በፋኖ ስም ሲነግድና ሲያጭበረብር የነበረ፤ ከዚያም የአማራን ህዝብ ከድቶ ሚሊሻ በመሆን ማህበረሰቡን ሲያስጨንቅ የቆየ ግለሰብ ነው ።
2ኛ. ቦጋለ ጌታቸው --- የሚሊሻ አባል
3ኛ ዘርዬ ----- የሚሊሻ አባል
4ኛ. ለጊዜው አንድ ስሙ ያልታወቀ የፖሊስ አባልና ከ23 በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባል በመብረቁ ሻለቃ እስከ ወዲያኛው የተሸኙ ሲሆን ለአፈሳ የመጣው የብልፅግና ጥምር ጦር በክንደ ጠንካራው ነበልባል ክፍለ ጦር መብረቁ ሻለቃ በምትኩ የሬሳ ክምር ሰራታለት አምሽታለች ። ይህ ደፈጣ የታሰበለትን አላማ ያሳካ ነበር ያሉን የመብረቁ ሻለቃ አዛዥ ናቸው ።
የዚህ ደፈጣ ዋና አላማችን የናት ጡት ነካሽ የሆነውን የአስር አለቃ ዘላለምን ታርጌት ያረገ ነበር ያሉት ደግሞ የመብረቁ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ነበሩ ።
ከዚህ ቀደም የኛ አባል በመሆንና በዘመቻነት ተመድቦ መረጃችንን ለጠላት አሳልፎ በመስጠትና ጦሩን የተለያየ ያልተጣሩ የሀሰት ወሬዎችን በሰራዊቱ መካከል በማስወራት ጦሩን ለመበተን ያደረገው ሙከራ በመጋለጡና ከፍተኛ ክትትል እየተደረገበት እያለ በክዳት ወደ ቀጣሪው ብልፅግና ከፍተኛ ገንዘብ በመዝረፍ መግባቱ ይታወቃል። እናም ይህ ስግብግብና ወገኑን የካደ ባንዳ ዘላለም የለመደውን የዝርፊያና የበደል ስራውን በከተማው ህዝብ ላይም በማድረስ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በርከት ያሉ የችግሩ ሰለባ የሆኑ ንፁሃን ዜጎች በተደጋጋሚ የሰራውን ግፍና በደል ነግረውናል ።
'መስረቅ የለመደ እናቱን ያስማማል' እንደተባለው ሁሉ ባንዳ ዘላለም የብልፅግና ታማኝነቱን ለመግለፅ የገዛ ህዝቡን እያፈሰ ሲያስረክብ ከፍተኛ የሆነ የውሎ አበል በንፁሀን አርሶ አደሮች ደም በመከፈሉ አፈሳውን ለሱና ለግበረ አበሮቹ እንደ የገቢ ምንጭ ቆጥሮ ከግብራበሮቹ ጋር የለመደውን የድሃ ልጅ ለማፈስ ሲንቀሳቀስ በመረጃ በመከታተል እና ታርጌቱን ሙሉ ባንዳ ዘላለም ላይ በማረግ የማያዳግም እርምጃ መብረቁ ሻለቃ መውሰዱን አስታውቋል ።
ይህ የመጀመሪያም የመጨረሻም አይደለም ከእኛ የከዱና መረጃችንን ለጠላት አሳልፈው የሰጡ ላይ ልዩ ክትትል በማረግ እርምጃችንን የምንቀጥል ይሆናል ሲሉ የመበረቁ ሻለቃ አዛዥ በድጋሜ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
ከዚሁጋ በተያያዘ ዜና፤ በእዚያው በኢራንቡቲ ቀበሌ ዙሪያ ቀጠናውን በማስፋት ወደ ተለያየ አቅጣጫ ለመንቀሳቀስ የሞከረው የብልፅግና ጥምር ጦር በራስ በኃይሉ በሶስተኛ(፫ኛ) ሻለቃ በተወሰደበት እርምጃ ወደ ኋላ ለመመለስ እንደተገደደ የራስ በኃይሉ ሻለቃ አዛዥ አሳውቀውናል ሲል አፋብን ደቡብ አማራ በቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር ሪፖርተራችን አርበኛ እንግዳ መረጃውን አድርሶናል ።
© አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር አርበኛ ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ
ብልፅግና የሚባል አማራ ጠሉ ወሮ በላ ኃይል ስልጣን ከመጣ ማግስት ጀመሮ ከተዘጉብኝ 10 የFB አካውንቶች ብልጽግና በአማራ ህዝብ ላይ ሲደረግ የነበረውን ጭ*ፍ*ጨፋ በመቃወም ፣ ሲደረጉ የነበሩትን የሀሰት መረጃዎችን በማስረጃ ስላጋለጥን ብቻ ትኩረት ተደርጎባቸው በአንድ ቀን ሳይቀር የተዘጉ አሉ ። እናም ውድ የአማራ ፋኖ ደጋፊዎች ጆይን በማድርግ ወዳጅነታችሁን እንድታደርጉ ስል በትህትና እጠይቃለሁ!! የፊስ ቡክ ፒጃችን ይወዳጁት
https://www.facebook.com/share/18NHgsHCgL/
#የአገዛዙ_ሰራዊት_ወደ_ፋኖ‼️
አንድ ሀሙስ ከቀረው ስርዓት ጋር ስም የሌለው ሞት ከምንሞት ከፋኖ ጋር አላማ ያለውና የዕውነተኛ ትግልና ክብር ያለው ሞት ብንሞት ይሻላል።በማለት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የጎፍ ክፍለጦርን የተቀላቀሉ ሁለት አድማ ብተናዎች የየጎፍ ክ/ጦር አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል። በዚህ ሰዓት ስርዓቱን የሚደግፉት ተስፋ የቆረጡ፣መሄጃ የሌላቸው በተለያዬ ሱስ የተጠመዱ ብቻ ናቸው።ሌላው ፋኖን መቀላቀል ይፈልጋል እዛም ሆኖ ፋኖና የፋኖ ደጋፊ ነው በለቅርብ ሰዓት ሁሉም ፋኖን ይቀላቀላል ብለው መግለፃቸውን የየጎፍ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ ሱልጣን የሱፍ ገልፀዋል‼️
+5
ይህ የአረመኔው አብይ አህመድ የመከላከያ ኮለኔል በጀግኖች የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ግንባር ግንባሩን የተባለው ጡት ቆራጩ ኃይል ስብስብ ነው ተው ብለና አማራን የነካ የለውም በርካ ነው።
ቀን ጥር 27 /2018 ዓም
የክፍለ ጦር ምስረታ መግለጫ
=====//=======//=====
ሕዝባችን የአማራ እንደ ሕዝብ የገጠመውን ሁለተናዊ የህለውና አደጋ ለመቀልበስ በሚደረገው ፖለቲካዊ የትጥቅ ትግል ለሕዝባችን እና ለትግሉ ታምነን ለድል እንደምንበቃ እርግጠኞች ነን።
የትግላችን መሰረት የሆነውን ሕዝባችንን ክደው ብቻ ሳይሆን በእጅጉ አጎሳቅለው ፣ ማህበረሰባዊ ስሪቱንና ግብሩን ጥላሸት ቀብተው በኮበለሉ ፣ የጀግኖቻችን መስዋት ባረከሱና ከንቱ ባደረጉ ፣ አንድ እግራቸውን ፋሺስታዊ ስርዓቱ ተክለው በነበሩ ፣ የአማራ ፋኖን አንድነት በእጅጉ ሲፈትኑ እና በእጅጉ ሲበጠብጡ በነበሩ ቅርብ አዳሪ ስናዳሪዎች ሕዝባችን በእጅጉ እንዳዘነ ተገንዝበናል። ይኽ ብቻም ሳይሆን ወደፊት የአባቶቻችን የእነ ገብርዬ ታሪክ እንዴት መመለስ እና መጠበቅ እንዳለብንና አበክሮ መስራትም እንደሚጠበቅብን ሕዝባችንም አደራ ሰጥቶናል። እኛም በኩራት ተቀብለናል።
የትግላችን መዳረሻ ግብ ሕዝባችን የገጠመውን ሁለተናዊ የህልውና አደጋ በመቀልበሰ ፣ ፍትሕ ፣ እንኩልነት ፣ነፃነት እና ሰብዓዋነትን የተላበሰ እና የአባቶቻችን የስነ-መንግስት ጥበብ አሁን ዓለም ከደረሰበት አስተዳደራዊ ፍልስፍና ጋር በማቀናጀት የተረጋጋ ስር-ዓተ መንግስት ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በመሆን መትከል እንደሆነ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በመግለጫው ከዚህ በፊት መግለፁ ይታወቃል።
በመሆኑም የክፍለጦራችን መነሻ የሆነውን የራስ ጋይንትና አካባቢው ማህበረሰብን በሚመጥን ለትግሉ ፍፁም ታምነን ፤ ለድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቃናቄ (አፋብን) ታዛዥ ሆነን ራሳችን በራሳችን አደራጅተን "ራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለጦርን" የመሰረትን ሲሆን ወደ ፊት ድርጅቱ በሚያወርደውን ማንኛው ትዕዛዝ እና መምሪያ ለመቀበል ዝግጁ መሆናችም እንገልፃለን።
ስለሆነም:-
1, ፋኖ ታደሰ ሀይሌ...... ሰብሳቢ
2,ፋኖ አሸናፊ ካሳ ........ም/ ሰብሳቢ
3, ፋኖ ስመኘው ፈንታው ....ወተደራዊ አዛ
4, ፋኖ ማስሬ እባቡ...... ም/ወ/ አዛዥ
5, ፋኖ እሰየ ሲሳይ....... ዘመቻ መሪ
6, ፋኖ ሀብቱ ባለህ...... ም/ ዘመቻ
8, ፋኖ ወንድምነው ካሳ ...... ወታደራዊ አስተዳደር
7, ፋኖ እያያ አየነው.... ልዩ ዘመቻ
8, ፋኖ አድስ ጌታሁን.... ስልጠና መምሪያ
9,ፋኖ ጌታለም ጎበዜ.... ፋይናንስ ኋላፊ
10, ፋኖ ሳሙኤል ጌታሁን ....ፖለቲካ ዘርፍ ኋላፊ
11,ፋኖ አባይ አስቻለው ...... ህዝብ አስተዳደር
12,ፋኖ ሻምበል ተስፋ...... ህዝብ ግንኙነት
13, ፋኖ *** .............. መረጃና ደህንነት
14, ፋኖ ጌታው.................. አድስ ሎጀስቲክ
15,ፋኖ ፍቃዴ ሙላቴ......... ግዥ ክፍል
* የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ
*ድል ለአማራ ህዝብ
*ድል ለአማራ ፋኖ
* ራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
