es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
4 389
Suscriptores
+2924 horas
+2547 días
+1 45030 días
Archivo de publicaciones
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር በዛሬው እለት የአገዛዙ ጥምር ሀይል መነሻውን ከአለፋ ወረዳ ሻሁራና አፀደማርያም ከተማ ፣ ከሰሜን አቸፈር ሊበን ከተማ እና ከቋራ ወረዳ ደለጎ በማድረግ ወደ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የተንቀሳቀሰ ሲሆን ሰሞንኛ  አጀንዳው  ፋኖን በየቀጠናው አፅድቻለሁ በህዝቡ ላይም የተሻለ ቅቡልነት አግንቻለሁ እያለ ቅዠት ላይ ያለ ቢሆንም  አሁን ላይ በጨለማ በመንቀሳቀስ የአርሶ አደሩን ትጥቅ ለማስፈታት እና ዘረፋ ለመፈፀም አቅዶ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ፣ ማህበረሰቡ ከፋኖ ሀይል ጋር መረጃ ቀድሞ በመለዋወጥ ከፋኖ ጎን በመሆን በሁሉም ቀጠና ማለትም በአለፋ ወረዳ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የፋሽስት ሰራዊት አድዋ ክ/ጦ ከማህበረሰቡ ጋር በመጣመር የጠላትን እቅድ ከማክሸፍ ባሻገር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ሲቻል ከደለጎ ከተማ ተነስቶ ወደ ኮሩ ቀጠና የገባው በቋራ ኦሜድላ ነብሮ ብርጌድ አማካኝነት በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ በትር ማሳረፍ ተችሏል። ይህ በንዲህ እንዳለ የፋኖ ሀይል አሰላለፉን በመቀያየር የአገዛዙን ሰራዊት ከበባ ውስጥ በማስገባት መግቢያ መውጫ እያሳጣው ይገኛል።አውደ ውጊያው አሁንም እንደ ቀጠለ ይገኛል አህዛዊ የድል ዜናዎችን በቀጣይ የዜና ጥንቅራችን የምናቀርብ ይሆናል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ        ህዳር 25/2018

#ሰበር_ዜና_ግሽ_አባይ_ሰከላ ‼ #የብልፅግና_ባንዳ_ስሩ_ተቆረጠ_በሰከላ‼ በአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ሰከላ ላይ በወሰደዉ እርምጃ የሰከላ ወረዳ አስተዳድር ዋና ባንዳ #ይልማ_ጥላሁን ጨምሮ ከሁለት ደርዘን በላይ የሚነሻና የመከላከያ አባላት ተወግዷል። የስቦ መምታት ጥበበኞች 44ኛ ክፍለ ጦር  ጠላትን #ከሰከላ #ከማንኩሳና #ከቡሬ በመተንኮስ ወደ ቀጠናቸዉ  ድረስ ሰተት አድርገዉ በማስገባት #ሰከላ ላይ የቀረዉን ሰፈር ጠባቂ፣ ዘራፊ ሚኒሻና ሆድ አደሩን የብልፅግና አመራር መሃል ሰከላ ላይ አራምጠዉታል። "ፋኖን ባለበት አሳድጄ አጠፋዋልሁ" እያለ ሲፎክር የነበረዉ ዋና አስተዳድር እና አምስት ሚኒሻ ሲማረክ ብዛት ያለዉ ሰራዊት ደግሞ እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል። አረመኔው ቡድን በአጉትና ባሽፋ ከማንኩሳ ፔንፔ፣ዘ_23 ከሰከላ ግትልትል ሰራዊቱን በማስከተል #ምላስና #ብልት በመቁረጥ የስድስት ንፁሃንን ህይወት በቀጠፈበት ቀጠና እየተልከሰከሰ የባህር ኩበት በሆነበት ሰሃት ጀግኖቹ የ44ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች ሰከላ ከተማ የሚገኘውን የብልፅግና ጦር በመቀጥቀጥ #12 ክላሽንኮፍና በሺዎች የሚቆጠር ተተኳሽ ማርኳል። ከዚህ በተጨማሪ መንግስታዊ ስርዓት አስቀጥላለሁ በሚል ሃሳዊ ህልም ሲገለገልባቸዉ የነበሩ  ኮምፒወተሮችና ላብቶቦች ማተሚያ ማሽኖች ሲማረኩ፤ የወረዳዉ መገልገያ ተቋም በሙሉ ፓትሮሎችን ጨምሮ ከጥቅም ውጭ ሁኗል። ከተማዋ ላይ የተሰገሰጉ በመረጃነት የሚያገለግሉ እንቁላል ቀቃይ ባንዳዎች መዉጫ መግቢያ ጠፍቷቸዉ ብዙዎቹ ተሸኝተዋል። ቁሞ መግጠም ያልቻለዉ አረመኔ ቡድን ከተለያ የቦታ እያፈነ እስረኛ ያደረጋቸዉን የሰከላ ወረዳ 25 ንፁሃን እስረኞችን ጭምር ከአረመኔዉ መንጋጋ ማስለለቅ ተችሏል። በተደጋጋሚ ቀጠናዉን እየረገጠ የጣለዉን እየጣለ ቁስለኛዉን ጭምር ሳያነሳ ወደ ቆፈረው ጉድጓድ የሚሮጠዉ አረመኔው ቡድን ዛሬም እንደልማዱ ከግሽ አደባባይ ጀምሮ እስከ ድንጋይ ገበጣ ሩጦ በመግባት ህይወቱን ሊተርፍ ችሏል። ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም 44ኛ ክፍለ ጦር ባደረገዉ ትንቅን በተደጋጋሚ ጀብደኝነቱን ያስመሰከረ፣ የጠላትን ቅስም የሰበረ፣ ብዙ ባንዳዎችን ቀልብ የቀየረበት፣ የድል ቀን ሆኖ  ተመዝግቧል። #በተደጋጋሚ_ተናግረናል_ጀምረናል_እንጅ_አልጨረስነዉ‼ #ላናሸንፍ_የጀመርነዉ_ትግል_የለም_ድልችን_ቅርብ_ነዉ‼ የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት   ፋኖ አለበል አወቀ።

መብረቁ እውነትም መብረቅ ሆነዋል ‼️ #ሞጣከተማ_ኮሊሳ_ላይ_ጠላት_ተቀጥቅጧል ህዳር 24/2018 ዓ.ም አይበገሬወች በተግባር አስመስክረዋል ስም እና ምግባር ማለት ይኸ ነው በዛሬው እለት ጠላትን ሲያ
+1
መብረቁ እውነትም መብረቅ ሆነዋል ‼️ #ሞጣከተማ_ኮሊሳ_ላይ_ጠላት_ተቀጥቅጧል ህዳር 24/2018 ዓ.ም አይበገሬወች በተግባር አስመስክረዋል ስም እና ምግባር ማለት ይኸ ነው በዛሬው እለት ጠላትን ሲያስለፈልፉት የዋሉ ሲሆን ሽንፈቱን ማረጋገጥ ያቃተው የጁላ ጦር የጀግኖችን ቀየ መድፈር አልቻለም። በ201ኛ ኮር በ54 ክ/ጦር ውስጥ ከሚገኙት ወረዳወች መካከል በሞጣ ኮሊሳ ዙሪያ ተንቀሳቅሶ ለመክበብ ቢሞክርም ነገሩ ተገልብጦ በቆንጆወቹ ከበባ ውስጥ ለመውደቅ ችሏል። #መብረቆቹ_ጠላትን_መውጫ_መግቢያ_አሳጥተው የብርሀኑ ጁላ ጦር በየቦታው ሲያዝረከርኩት የዋሉ ሲሆን ከ ከ11 በላይ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን በርካታ ቁስለኞችን በአንቡላንስ ሲያመላልስ አርፍዷል። የኖወችን ብትር መቋቋም ሲያቅተው አስክሬን እና ቁስለኞችን ለማንሳት ከከበባው ለመውጣት ከሞጣ ተጨማሪ ሀይል ዙ= 23 በማስመጣትና ለማምለጥ ቢሞክርም የተማረከው ተማርኮ ሙትና ቁስለኛውን አስታቅፈው ሸኝተውታል። የምርኮ ፎቶወች እንደደረሰን እናጋራቹሀለን..?! የአፋብኃ ቴድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ህዳር 25/2018 ከGojjam Damot yetewesede

የአደረጃጀት ዜና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር የአመራር ሪፎርም አደረገ:: ቀናትን የፈጀ ውይይት እና ግምገማ ከተደረገ በኋላ አዳዲስ አመራሮች የተሰየሙ ሲሆን ከነባሮች የኃላፊነት ርክክብ አድርገዋል:: የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አብነው ታደሰ በተገኘበት የተካሄደው የውውይት እና ግምገማ መድረክ በስኬት መጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን ጉባኤተኞች ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩትን አርበኞች የክፍለ ጦሩ አመራሮች አድርገው መምረጣቸውን ነው ከስፍራው የደረሰን መረጃ የሚያመላክተው:: በዚህም፦ 1ኛ. አርበኛ ስንደው ገዜ - የክፍለ ጦሩ አዛዥ 2ኛ. አርበኛ ዱቤ አሻግሬ - የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ 3ኛ. አርበኛ ንጉሥ ጌታቸው - ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ 3.1. አርበኛ መብሬ ጫብሲ - ዘመቻ መምሪያ ምክትል ኃላፊ 4ኛ. አርበኛ መብሬ ምስጌ - ወታደራዊ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ 5ኛ. አርበኛ ደምሰው ጎቼ - ሎጀስቲክ ሃላፊ 6ኛ. አርበኛ ደመቀ አረጋ - የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ 7ኛ. አርበኛ አስማማው ፈንታው - የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ 8ኛ. አርበኛ ጀንበሩ ጌታቸው - ስልጠና መምሪያ ኃላፊ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም

🔥#ፀዳሉ_ደሴና_ጓዶቹ_በአገዛዙ_እይታ‼️ በሰሜን ምዕራብ ዕዝ ግቢ ውስጥ የጸዳሉን ፎቶ አንድ የመከላከያ ከፍተኛ አመራር ሲልክልኝ እንዲህ አለኝ,,,,,,,"ዕጅ የሚሰጡትን በጣም ነው የምንስቅባቸው፣
🔥#ፀዳሉ_ደሴና_ጓዶቹ_በአገዛዙ_እይታ‼️ በሰሜን ምዕራብ ዕዝ ግቢ ውስጥ የጸዳሉን ፎቶ አንድ የመከላከያ ከፍተኛ አመራር ሲልክልኝ እንዲህ አለኝ,,,,,,,"ዕጅ የሚሰጡትን በጣም ነው የምንስቅባቸው፣በጣም ነው የምንንቃቸው፣ለእኛ ዕጅ ሲሰጡ የምንፈልጋቸው ለዜና ብቻ ነው፣ዜና ከተሰራባቸው በኋላ የሚፈልጋቸው ባለመኖሩ የትም ቢሄዱ አይመለከተንም። የፖለቲካ አመራሮችም ዜናው ከተሰራ በኋላ ዞር ብለው አይጠይቁንም። ጸዳሉ የሚባለው ደህንነት መሆን እፈልጋለሁ ብሎ ግቢ ውስጥ እንደ ስደተኛ ሲንከባለል ይውላል። ወደ እኛ ሲመጣ መጠቋቆሚያ ነው የምናደርገው። እኛ ቤተሰብ አፍርተን ልጆች ወልደን ለእነሱ መኖሪያ ስንል ደሞዝ እየበላን ከውስጥ እንታገላለን፣ወጣቱ ታግሎ እኛንም ነጻ ያወጡናል ብለን ስንጠብቅ ዕጅ ሲሰጡ ያሳቅቁናል። መከላከያ በቅርቡ አይኖርም። እውነቱን ልንገርህ መንግስት ደክሞታል። ደሞዝ በቅርብ ቀን ይቋረጣል እየተባለ ነው" በማለት አጫውቶኛል። ዕጅ የሚሰጡት በእነሱ ዘንድ እንደዚህ ከተናቁ በሌላው ማህበረሰብ ዘንድማ አስቡት! አስፈላጊ ከሆነ ቪዲዮም አለኝ። ነገር ግን ዕጅ ለሰጠ ሰው ጊዜ ማቃጠሉ ተገቢ ነው ብየ አላምንም። ሰሞኑን ማስረሻ ሰጤም በአንዱ የዕዝ መመሪያ ግቢ ውስጥ ሆኖ እናየው ይሆናል። ክብርን የሚያውቀው በክብር ያደገ ሰው ነው። ለጁላ ዕጅ የሚሰጥ ከእሱ ያነሰ ማንነት በመያዙ ነው። 25/ዐ3/2018 ዓ.ም

ግሽ ዓባይ ከተማ በፋኖ እጅ የብልጽግና ሴራ በሚሊሻ ላይ ሲጋለጥ: ======== ነገሩ እንዲህ ነው:- ሰከላ ወረዳ የመሸገው ወራሪ ሀይል እኛ ብቻ እየሞትን ሚሊሻ ገብቶ ማይዋጋ ለምንድን ነው በማለት ቅሬታ እንደነበረው የውስጥ መረጃዎቻችን አድርሰውናል። በዚህ የተናደደው ጠላት ሚሊሻን እና ፖሊስን ግሽ አባይ ከተማ በማስቀመጥ ሚስጥር ሳይነግራቸው ወደ አጉት ተንቀሳቅሷል። ሚሊሻ ከምኝታው ሲነቃ ግሽ አባይ ከተማ በፋኖ ቁጥጥር ውስጥ ሆና ተገኘች። ሚሊሻም ሆዬ እለቅሶውን ቢያቀልጠውም ሚደርስለት አጥቶ በደንብ ሆኖ ተወቅቷል። 👉ብትነገር አልሰማ ያልህ ባንዳ መጨረሻህ ይሄ ነው። አሁንም እድሉ አለህ እሱን ተጠቀሙበት። 👉ሙሉ ዝርዝሩን እንመለስበታለን። ©የቻለ አድማሱ

እንደዛሬው ሳይሆን መንደሬው ጎጠኛው ሳይበዛ፣ አንተ አንተን ሰተሃል አወይ አማራነት የነበረው ለዛ🥹 አንተ የወደክበት ምድር ናሁሰናይ ወ አቤኔዘር አደባባይ ተብሎ ሳይሰየም እና ሀውልትህ ሳይቆም  በጎጡ በመንደሩ ተወሽቆ ሳያሸነፍ አማራነቱን አሳንሶ በአውራጃ ታጥሮ  የሚቀር አማራ የለም። አማራው ጀብደኛው ሻለቃ ናሁሰናይ አንዳርጌ ሊሰዋ እንደሚችልም እያወቀ "ድንገት ከሞትኩ ብሎ ማስታወሻ "ብሎ ለታሪክ አስቀምጦልናል አንተን መርሳት በፍፁም አይቻልም 🥹 የወንድነት ልክ! ድል ለአማራ ፋኖ!

የባንዳ መድኃኒት

በደፈጣ ጥቃት ተፈፀመ ሁለት ፓሊሶች ላይ እርምጃ ተወሰደ ህዳር 25/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ እና74ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ ገዳያሱ ቀ
+1
በደፈጣ ጥቃት ተፈፀመ ሁለት ፓሊሶች ላይ እርምጃ ተወሰደ ህዳር 25/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ እና74ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ ገዳያሱ ቀበሌ እና መርጦ ለማራይም ከባድ ተጋሃድሎ ሲያካሂድ አድሯል። በሸበል በረንታ ወረዳ ወፍትማ ጎጥ ህዳር 24/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት በነበረው የጨለማ የጨበጣ ውጊያ በረካታ የአረመኔዊ ሰራዊት አባላት ሲደመሰስ በረከት ታደሰ የሚባል1 የአገዛዙ ሰራዊት አባል በንስሮች የበላይ ዘለቀ ልጆች እና የሽፈራው ገርባው ልጅች የተማረከ ሲሆን መርጦለማርያም ላይ ሁለት ፓሊሶችላይ እርምጃ በመውሰድ ጀብድ ሰርቶ መውጣት ተችሏል። በውጊያ የ64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮችእና ጥምር ጦሩ እና1ኛ እሪጅመንት እና የሸበል በረንታ ደጀኑ ህዝባችን ተሳትፈዋል። ህዳር 25/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ ፣ዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ

#በጣረ_ሞት_አፋፍ_ላይ_የሚገኘው_የብአዴን_ቅዥት_በቢቸና_ከተማ ህዳር 24/2018 ዓ.ም በቢቸና ከተማ የክልል እና የዞን ፅጥታ ዘርፍ የብአዴን አመራሮች ተገኝተዋል። 1. ዶ/ር አማኑኤል ፈረደ - የአብክመ በር/መ/ር ማዕረግ የአስተዳደር ጉ/ክላስተር አስተባባሪ 2. ሜ/ጀ ብርሃኑ ጥላሁን - 6ዕዝ አዛዥ 3. ሜ/ጀ ሶፊያን ሙሃመድ- 6 ኮር አዛዥ 4. አቶ ኑርልኝ ብርሃኑ - ✍️ዶ/ር አማኑዔል:- ●ለውይይት መነሻ የሚሆን በሚል ፅንፈኛው ት/ት በማገድ ትውልድን እየገደሉ ነው፣ ህዝቡ ተንቀሳቅሶ መነገድ አልቻለም፣ መ/ሰራተኛው ዘመድ መጠየቅ እሴቱን ከልክለውታል፣ እናት አባቱ ዘመድ ሲሞት እንዳይቀብር ተከልክሏል፣ አ/አደሩን ይዘርፉታል፣ ይገሉታል፣ ያጎሳቁሉታል። ✍️ የህዝብ አስተያት:- ●በስብሰባው የተሳተፈው የተለያዩ የህ/ሰብ ክፍሎች ቢሆንም ጥያቄ እንዲያነሱ ዕድሉ የተሰጠው ሁሉም የብልፅግና እግር አጣቢ ሚሊሻ ብቻ ነው። በጣም የገረመኝ ይህ ነው። 1. ይርጋ ብዙአለም - የዲቢሳው ሊቀ መንበር 2. ሰይፍ ጫኔ የብቸና ውሃብይ ተላላኪ 3. አሰግድ የተባለ የጎተራ ጠማዳ ሚሊሻ 4. ጤናው የብቸና ደብር ትጥቅ ያወረደ ሚሊሻ 5. ከካህናት ፣ ሸሆች፣ ሰይዴና ሽሜ የሚባል ሙስሊም ውጭ ውጭ 12 ሰው እድል የተሰጠው ሲሆን 10ሩም ሚሊሻ ናቸው።አለባበሳቸው ኑዋሪውን ህዝብ መስለው የገቡ ሲሆን በንግግራቸው በ5 ሺህ ብር ደመወዝ ንሮው ከብዶናል፣ በቆርቆሮ ቤት እየኖርን፣ መሬታችን ስለደለመ ሰብል የለንም በንሮ ውድነት ቤተሰብ መምራት አልቻልም በሚል ንግግራቸው ሚሊሻ መሆናቸው ለችግር ተጋልጠናል ሲል ሁሉም የደመወዝ ጥያቄ አቅርበዋል። ●6 ቀበሌ ይዘን እንዴት ልማት ማልማት ይቻላል፣ መንግስት ፋኖን ማጥፋት አቅቶት አይደለም ለምን ዝም አላችሁ፣ ቤተ ክ/ን አትቀበሩም ተብለናል፣ የሃይማኖት አባትና ሽማግሌ ግዴታቸውን አልተወጡም? ✍️ተሰብሳቢው:- ● ህዝብ የወለጋ፣ አርሲን እና የመተከልን ግፍን ትተን በአማራ ክልል ጡት፣ ምላስና ብልት፣ መቆረጡ እየታወቀ፣ የሰው ልጅ መታረዱ ፣ በደ/ኤልያስ ከ500 በላይ መነኩሳት በሰው በላው መከላከያ መታረዳቸው፣ መረሸናቸው የቅርብ ትውስታችን ቢሆንም ፅንፈኛው 78 ሰው ረሽኗል ፣ እጅ ቆርጦል፣ ጀሮ እየቆረጠ ነው ይሉናል። ●ዲማ ቅ/ጊዮርጊስ ገዳም የመነኮሳት ሳይሆን የፅንፈኛው ምሽግ ሆኗል፣ ዲማ፣ ሰቀላ፣ የቀበሃና፣ መንግስቶ ቀበሌዎችን መያዝ ባለመያዙ ምክንያት ህዝቡ ፍትህ ፍለጋ እየሄደ ነው (የእነማይ ወረዳ ፍ/ቤት የክስ አፈጻጸም እንዲያስፈፅም ለፋኖ ደብዳቤ እንደተጻፈለት ስላልሰሙ ይመስላል )፣ ለምን እነዚህን ቀበሌዎችን መያዝ አይችልም፣ ዲማን ከተያዘ ፅንፈኛ መግቢያ ስለሌለው እጅ ይሰጣል፣ ፅንፈኛው ዛሬም እያሰለጠነ እያስመረቀ ነው ምን እስኪሆን ነው የምንጠብቀው ●ፅንፈኛው በጫካ ስልጣን እየተፋጀ፣ እየተታኮሰ ነው ●በመምህራን ላይ የተነሳ ውርጅብኝ:- ትውልድን እየገደሉ ነው የግል ስራቸውን ሲያሯሩጡ ነው የሚውሉት፣ ለፅንፈኛው የ1 ወር ደመወዝ ከፍለዋል። መረጃ አቀባይ ናቸው። በዜግነት የሚከፈላቸው ሰዎች ናቸው። በግ ነጋዴ ሆነዋል። መ/ር ዲማ መሄድ የለባቸውም ነበር። ✍️ሰይዴ ጫኔ ጥያቄ • ከቀበሌ እስከ ክልል አመራር ምስጋና ይገባችኋል። • የሃይማኖት አባት፣ ሽማግሌና የከተማ ነጋዴ ለችግሩ ዋና ተጠያቂ ናቸው • በፅንፈኛ ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰድ? • በሀይማኖት መካከል አንዱ መንግስትን ሌላኛው ፅንፈኛ ደጋፊ ማስመሰል አለ? • ፅንፈኛው ብቸና 04 ሙስሊም አባት ከነልጁ ተገለውል? • 50 ሙስሊም ነጋዴዎች በፅንፈኛውና በግብር ጫና ተሰደዋል? ✍️ጤናው የብቸና ደብር ሊቀ መንበር • 2 አይነት ውጊያ አለ የውስጥና የውጭ • ቅድስቴ ሄዶ ከፋኖ ጋር ዳቦ የቆረሰ ባለሙያ ላይ እርምጃ አልተወሰደም • ፅንፈኛው የእኛን መሬት እንዳይታረስ አድርጎ የእነርሱ ሱቅ ተከፍቶ እየሰሩ ነው። • ሞገስ ውዱ መድሃኒት ቤቱ ስሙን በመቀየር እየነገደ ነው እንዲሁም የአባቴነህ ፎቅ በደንብ እየሰራ ነው። ●በጦርነት ፋኖን ማሸነፍ እንደማይችሉ አምነዋል፣ ህዝቡ ልቡ ከፋኖ ጋር እንደሆነ ተርድተዋል፣ ፋኖን ለማሸነፍ ህዝቡ ከጎናችን ይሁን፣ ሁሉም የድርሻውን ይወጣ፣የፋኖ ቤተሰብ እየመከራችሁ ልጆቻችሁን አምጧቸው፣ ሽማግሌዎች ወጣቱ ሞቶ ሲያልቅ ማን ሊጦራችሁ ነው በሚል ምክር ስጡ ተብለዋል። ●የዲማ ፋኖ ቀጣይ ትኩረቱ ወደ እርሱ ስለሆነ መጠንቀቁ አይከፋም። • በቀጣይ በውስጥ የፋኖ ደጋፊዎች ላይ ባሏቸው ባለሃብቱና መ/ሰራተኛው ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል። ✍️ ማሳሰቢያ:- ከህዳር 25 ቀን ጀምሮ የወረዳና ቀበሌ አመራሮች ወደ ደብረ ማርቆስ ስልጠና ማዕከል ይሄዳሉ። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!! ህዳር 24/2018 ዓ.ም

#ሰበር ሰከላ ግሽ አባይ‼️ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር መብረቁና ናደው ሻለቃ በጥዋቱ የወረዳ አስተዳድሩን ጨምሮ የሚሊሻ አዛዡንና በቁጥር ብዛት ያለው ሚኒሻን ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏ
#ሰበር ሰከላ ግሽ አባይ‼️ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር መብረቁና ናደው ሻለቃ በጥዋቱ የወረዳ አስተዳድሩን ጨምሮ የሚሊሻ አዛዡንና በቁጥር ብዛት ያለው ሚኒሻን ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ፣ እንዲሁም በርከት ያለ አጥቦ አይለብሴ ተሸኝቷል። ዝርዝር ይዘን የምንመለስ ይሆናል 25/ዐ3/2018 ዓ.ም

#የመጨረሻ_ማስጠንቀቂያ_መልዕክት ‼️ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትን ከተማ፣መንደር 3፣መንደር 14 እና መንደር 22 አካባቢ ብልፅግና ያሰማራቸው የሌባ እና ዘራፊ ቡድን እንዳለ
+1
#የመጨረሻ_ማስጠንቀቂያ_መልዕክት ‼️ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትን ከተማ፣መንደር 3፣መንደር 14 እና መንደር 22 አካባቢ ብልፅግና ያሰማራቸው የሌባ እና ዘራፊ ቡድን እንዳለ ከህዝብ በደረሰን ጥቆማ አረጋግጠናል ። ፋኖን ከህዝብ ለመነጠል እና የፋኖን ስም ለማጠልሸት በተለይም በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ መሪዎችን ስም እየጠቀሱ የሱ ልጆች ነን እንዲሉ ከብልጽግና ተልዕኮ የተሰጣቸው እንዚህ እኩይ የጥፋት ሃይሎች። የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እየመዘበሩ ይገኛሉ። በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ በአሙሩ ወረዳ እንዳደረግ ነዉ ሁሉ በዚህ የዉብድና ተግባር ላይ የተሳተፉ ላይ ፋኖ የማያዳግም ዕርምጃ የሚወስድ መሆኑን ለሰፊዉ ህዝባችን ለመግለጽ እንወዳለን። ፋኖ ዲ/ን ክንዱ አሸናፊ የአፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ህዳር 25/2018 ዓ/ም

የጦሩ መሐንዲስ መቶ አለቃ አርበኛ አበበ ሰው መሆን
የጦሩ መሐንዲስ መቶ አለቃ አርበኛ አበበ ሰው መሆን

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር እና ከአፋሕድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዓፄ ዐምደፂዮን ኮር የተውጣጣ የፋኖ ኃይል በምዕራብ ወሎ ግንባር ከላላ ወረዳ ውስጥ ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፀመ:: በቅንጅት በተሰራው ኦፕሬሽን ከ20 በላይ ጠላት የተማረከ ሲሆን ጠላት 3 መኪና የሚሆን ሙት እና ቁስለኛ ጭኖ ፈርጥጧል:: በትናንትናው እለት በደገር ግንባር የተጀመረው ጦርነት ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በስተመጨረሻ ፋኖ ከተማይቱን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏታል::   ከዚህ በተጨማሪ ከደገር ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኙት ቲርቲራ እና ቆርኬ ታዳጊ ከተሞችም በፋኖ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል:: ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ትንቅንቅ በቲርቲራ በኩል የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ ሸዋንግዛው ካሳ ተሾመ ሻለቃ ጠላትን ሲያስፈረጥጠው ቆርኬ ላይ ደግሞ የዚሁ ክፍለ ጦር አካል የሆነችው 2ተኛ እንድሪስ ተሾመ ሻለቃ ታሪክ ሰርታለች:: የፋኖዎችን ምት መቋቋም ያቃተው ጠላት ከቲርቲራ ጎራ ወርዶ እየፈረጠጠ ተጉዞ ቀነሶ መንደር ሲደርስ አቶ ሁሴን ከማል የተባለ ገበሬን በአጨዳ ላይ ሳለ እረሽኖታል:: በቆርኬ ግንባር 17 የጠላት ኃይል የተመታ ሲሆን 5ቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ 12ቱ ቁስለኛ ሆነዋል::  ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ዋሲል ክፍለ ጦር በጃማ ግንባር በተለይም በአቦልድ፣ ዘርቃሚ እና ደጎሎ በኩል የጠላትን አከርካሪ መስበሩ ተረጋግጧል:: የወረዳው መቀመጫ የሆነችው ደጎሎ ከተማ እስከ ዛሬ ጧት ድረስ በተኩስ ስትናጥ እንደነበረ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመላክታል:: ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ የዋሲል ክፍለ ጦር 2ተኛ መብረቅ ሻለቃ አባላት ጠላትን እረፍት ነስተውት ሰንብተዋል:: በዚህ የተበሳጨው ጠላት ከአረብ ሀገር ከመጣች 1 ወር በትክክል ያልሞላትን እህታችንን መረሸኑም ታውቋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም

ከ1ቲም በላይ 10 የጠላት ሀይል 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቀሉ።‼️ #ያለምንም_ዉጊያ_ጦሩን_እያፈረስነው_ነው በሸበል በረንታ መረገጭ ከተማ የአገዛዙ ስረዓት ከ6ኛ ዕዝ 601ኮር 52ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ እሪጅመንት ቀኝና መሀንዲስ የነበሩ አገዛዙን በመክዳት ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቀሉ። 1ኛ.አማኑኤል የሽዋስ 2ኛ.ነፃነት አበበ 3ኛ.ማሩ ውለተው በተጨማሪም በደራ ወረዳ የሚገኘው የአገዛዙ ሰራዊት 6ኛ ዕዝ 601 ኮር እና 605 ኮር 26 ክፍለ ጦር 1ኛ እና 5ኛ እሪጅመንት አባል የነበሩ ፦ 1ኛ.ይሆንስ ምስጋነው 2ኛ.ግዛቸው ክንፉ 3ኛ.ደሳለኝ ደሞዝ 4ኛ.ብርሀኑ ጥላሁን 5ኛ.ሞሀበው እንዳልኬ 6ኛ.ሞገስ ዳዊት 7ኛ.ሞላልኝ ይበን የተባሉ ከሰሜን ሽዋ ደራ ወረዳ ሰለልኩላ ቀበሌ የአገዛዙን ስረዓት በመክዳት 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቀሉ። #ስቦ_የማስከዳት_ስራ_በሰፊው_እየሰራን_ነው‼️ የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ! ህዳር 24/2018 ዓ.ም