es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
4 389
Suscriptores
-324 horas
+2587 días
+1 43630 días
Archivo de publicaciones
#የአማራ_አንገቱ_አንድ_ነዉ!" የነቁ ወንድሞቻቸዉ ወደ አማራዊ ቤታቸዉ እየመጡ ነዉ!!! አዲስ ቅዳም ከተማ ከተከማቸዉ የአሸባሪዉ ብልፅግና ታጣቂዎች ዉስጥ በአድማ ብተና ተቀላቅለዉ የነበሩ 9 ወንድሞ
+4
#የአማራ_አንገቱ_አንድ_ነዉ!" የነቁ ወንድሞቻቸዉ ወደ አማራዊ ቤታቸዉ እየመጡ ነዉ!!! አዲስ ቅዳም ከተማ ከተከማቸዉ የአሸባሪዉ ብልፅግና ታጣቂዎች ዉስጥ በአድማ ብተና ተቀላቅለዉ የነበሩ 9 ወንድሞቻችን ዛሬ ህዳር 15 ለ16 2018 ዓ/ም ለሊት ከአራጁ የአብይ አህመድ ታጣቂ ላይ በሁለት አቅጣጫ ተኩስ ከፍተዉ ከበባዉን በመጣስ የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድን በሰላም ተቀላቅለዋል። አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!! ©ፋኖ ተሻገር አደመ

ህዝባዊ ምክክርና አደረጃጀቶች ዛሬም ተጠናክርው ቀጥለዋል!! የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ አንደኛ ኮር ናደው ክፍለ ጦር በመርሐቤቴ ወረዳ ጎራንዳ ማርያም ሰርቃ ቀበሌ ህዝብ ጋር ሰፋ ያሉ ውይይቶች ተደርገዋል ። ናደው ክፍለ ጦር ከትግሉ ጎን ለጎን ነፃ ባወጧቸው ቀጠናዎችና በሚያስተዳድራቸው አካባቢዎች ጠንከር ያለ ህዝባዊ ውይይትና አደረጃጀቶችን በማዘመን ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል። በመሆኑም በውይይት መድረኩ ትግሉን በሚመጥንና ትግሉን አሻጋሪ የሆኑ ከታች ባሉት ነጥቦች ማለትም 1. ትግሉ በአሁን ሰዐት ላይ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል። 2.ህዝባችን ከፋኖ ጎን እንዴት መሰለፍ መቻል አለበት 3. የመልካም አስተዳደር አፈታትና አሰራርን እና በመሳሰሉት አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያና ውይይት ተደርጓል። በመድረኩን የአፄ ዘርያቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር ድርጂታዊ ጉዳይ ሀላፊ ፀጋው ታፈሰ፤ አደረጃጀታዊ መምሪያ ሀላፊ ሸዋንግዘው እና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አበባው ፍሰሃ እንዲሁም ሌሎች አመራሮች በተገኙበት አስተማሪና ለነገ አሻጋሪ ሀሳቦችን በማንሳት ከህዝቡም ጠንከር ያሉ ሀሳቦችን በማንሳት የጋራ መግባባትና አሰራር ላይ ተደርሷል። በመጨረሻም የአማራ ህዝቡ ከእንግዲህ ትግሉ በሚጠይቀው እረገድ ከፋኖ ጎን ተሰልፍ የትግሉ አንዱ አካል እንደሚሆን በሀሳባቸው ገልፀዋል። መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ህዳር 15/03/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር በተቆጣጠረባቸው ቀበሌዎች የህዝብ አድረጃጅቶችን ከሊቀመንበሩ እስከ ፍርድ ሸንጎ ያዋቃራቸውን አመራሮች ስልጠና ሰጠ። ይህ ቤንዲህ እንዳለ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር ከአገዛዙ ነፃ ያወጣቸውን ቀጠናዎች ማለትም መስቀል በር፤ ማጀቴ 01 ፤አንቃር ኮበኮብ፤ መስኖ፤ ገተም ጎጆውሃ፤አግላ ማጀቴ፤ ካብሳራምባ ደጉቸ፤አገርማሪያም ዋጨራ ሎርጊሰርት ቀበሌዎች በቅርቡ በተለይም የአብይ አህመድ አገዛዙ ወንበር አስጠባቂው ብአዴን የህዝብ መሪዎች ከቀበሌ ሊቀመንበር እስከ ፍርድ ሸንጎ ሲያዋቅር ለእራሱ በሚመች በተለይም በዘመድ አዝማድ እየመረጠ በህዝባችን ላይ ያለ የሊለውን በትር ሲጠቀም የቆየ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እና ህዘቡ በተለይም መሪውን በእራሱ ወዶና ፈቅዶ በመምርጥ ከአማራ ፋኖ ከትግሉ ጎን ለጎን አብሮ ሆኖ የማይቀር የነፃነት ትግል እየሰራ ይገኛል። ሆኖም የህዝብ መሪዎች ስልጠና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፤ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር እንዲሁም የዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለጦር አመራሮች እና በህዝ የተመረጡት የቀበሌ አመራሮችና የፍርድ ሸንጎ ፍትህ አካላት በተገኙበት ቀጣዩ የአማራ ፋኖ የትግሉን እንቅስቃሴ በማግዝ ከትግሉ ጎን ለጎን ህዝብ ወክለው የተመረጡት አመራሮች ስልጠና በመስጠት ቀጣይም አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል። በመጨረሻም እኛ በምንኮርበት ህዝባችን የተመረጠንው አመራሮች ከእናንተ ከአማራ ፋኖዎች ጋር ከትግላችሁ ጎን ለጎን አብርን ለመስራት እድል ስላገኘን ከምንም በላይ ደስተኛም ነን በመቀጠለም ለህዝባችን በታማኝነት ከህዝብ በፊት እራሳችንን አስቀድመን ለመስራት እርግጠኛ ነን በማለት ስልጠናው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የነፃነት ትግል በሚመጥ መንገድ ስልጠናው ተሰጥቷቸዋል። መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ህዳር 15/03/2018 ዓ.ም

ችግሩን በፈጠረው አስተሳሰብ እና አእምሮ ለችግሩ መፍትሔ ማግኘት አይቻልም!! ይህንን አባባል  በጥሩ መልኩ ሊገልፅ የሚችል ፖለቲካዊ አካሄድ ውስጥ የገባው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የወልቃይት የወሰን እና የማንነት ጥያቄ የሚመለሰው ህገ-መንግስታዊ መዋቅሩን በመከተል ነው ብሏል።በአገዛዙ ፍላጎት እና ድጋፍ የተቋቋመው የተከዜ ዘብ ተጨማሪ የሠራዊት አባላትን አሰልጥኖ ባስመረቀበት ዕለት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለሰልጣኞቹ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ለዓመታት እንዲፈርስ እና እንዲናድ የታገሉትን ህገ-መንግስት የወልቃይትን ጥያቄ የሚመልሰው አይነተኛ መሳሪያ ነው በማለት በነፃነት ውስጥ ከተጋፈጡት እንግልት ይልቅ በባርነት ድሎት ውስጥ የሚጎነጩትን የውሻ አሟሟትን መርጠዋል።ክቡርነትዎ ሆይ ይህንን ንግግር እርስዎን አምኖ የህይወት መስዋዕትነትን ጭምር ለመክፈል ለተዘጋጁ የተከዜ ዘብ አባላት ሲናገሩ የአማራ ልዩ-ሃይል በአገዛዙ እምነት ተልዕኮውን ጨርሷል በተባለበት ወቅት በአንድ የተበትናችሗል ፊሽካ እንደፈረሰ ዘንግተውት ይሆን?ወይንስ እርሶዎ የቤተ-መንግስቱ ምንደኛ ባለሟል ስለሆኑ የተከዜ ዘብ እንደ አማራ ልዩ-ሃይል በአንድ ቁራጭ ወረቀት ሊፈርስ አይችልም ወደሚል ለጅልነት በተጠጋ የፖለቲካ የዋህነት መቀመቅ ውስጥ ገብተው ይሆን?? በእኔ እምነት የወልቃይት፣የራያ፣የደራ፣የመተከል እና መሰል የአማራ ሕዝብ የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎች  በሁለተናዊ መልኩ የሚመለሱት በአገዛዙ ይሁንታ እና ፈቃድ በሚቋቋሙ አደረጃጀቶች እና ተቋማቶች ሳይሆን በአማራ ሕዝብ ላይ የህልውና አደጋ የጋረጡትን አስተሳሰቦች፣ፖሊሲዎች፣ህግጋቶች እና ተቋማቶችን አሸንፈን የአማራን ሕዝብ ዘላቂ ጥቅም እና ፍላጎት ሊያሳካ የሚችል ስርዓተ-ማህበር ስንገነባ ብቻ ነው። አርበኛ ዳሞት አለኸኝ

Statement Issued By Amhara Fano National Force (AFNF)‼️
+1
Statement Issued By Amhara Fano National Force (AFNF)‼️

ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!           የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ማዕከላዊ ኮማንድ

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ: ኅዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም "የብልፅግና አገዛዝ አስገድዶ መድፈርን እንደ ጦር ስልት እየተጠቀመ ነው" ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የተሰጠ መግለጫ ```````````````````````````````````````````````` የአማራ ህዝብ ላይ የተጀመረው ይፋዊ የዘር ማጥፋት ጦርነት ከተጀመረ ሶስት ዓመታትን ሊደፍን ተቃርቧል። የብልፅግና አገዛዝ ዓለም አቀፍ የጦር ህግጋትን በመጣስ በተለይም ተፋላሚ ኃይሎች ሲቪያሊያንን ከጥቃት የመጠበቅ ግዴታቸውን እንዲወጡ የሚያስገድደውን መሰረታዊ ህግ በመቃረን እና ሁሉንም የጥፋት ስልቶች በመተግበር በአማራ ህዝብ ላይ ሁለንተናዊ የጦር ስልትን በመተግበር ላይ ይገኛል። ይኸ ሁሉን አቀፍ የጥፋት ስልት ንፁሃንን በመግደል፣ በማህበራዊ እንቅስቃሴ ላይ ያለውን ያልታጠቀ ህዝብ በጅምላ ጨራሽ መሳሪያወች በመጨፍጨፍ፣ የሰላማዊ ነዋሪወችን ንብረት እና ገንዘብ መዝረፍ፣ እናቶች እና ህፃናትን በጅምላ እና በተናጥል አስገድዶ መድፈር፣ የሚደፈሩ ሴቶችን ገላ መቆራረጥ፣ ባለትዳር ሴቶችን በመድፈር ማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ቀውስን መፍጠር እና ሌሎች የሽብር ተግባራትን ያካትታል። አገዛዙ እነዚህን እና መሰል ድርጊቶችን መፈፀም ህዝብን የማጥቂያ ስልት አድርጎ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ያሰማራው አረመኔ ሰራዊት በገባባቸው ቦታወች ሁሉ እነኝህን ዘግናኝ የጦር ወንጀሎች መፈፀም መለያ ባህሪው ወደ መሆን ተሸጋግሯል። የአብይ አህመድ አረመኔ ቡድን ስልጣን በያዘ ማግስት በራሱ ህዝብ ላይ በጀመረዉ የጦርነት ፕሮጀክት የሺወችን መደፈር፣ የንፁሃንን በጅምላ መገደል እና መዘረፍን የተመለከተው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና መላው ኢትዮጵያዊ በግዜው ተመጣጣኝ እርምጃ እና ምላሽ ባለመውሰዱ ምክንያት በአማራ ህዝብ ላይ በጀመረው ጦርነት ይህ ህዝብን የማጥቂያ ዘዴ በአይነትም፣ በብዛትም፣ በሽፋንም እጅጉን ተጠናክሮ ቀጥሏል። ግብር ከፍሎ በሚያስተዳድረው ሰራዊት እናቶች እና ታዳጊወች በጅምላ የሚደፈሩበት ከኢትዮጵያ ህዝብ በስተቀር በዓለም ላይ የለም። ይህ የዘመናችን እንቆቅልሽ ነው። ከሰሞኑ ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ያለው BBC ይህንን ጉዳይ ውቅያኖስን በጭልፋ እንዲሉ ጥቂት ማሳያወችን ዋቢ በማድረግ ካወጣው የምርመራ ሪፖርት በስተቀር አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፅማቸው የጦር ወንጀሎች ዛሬም የዓለም ጆሮ እንደተነፈጉ ናቸው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ባደረገው የዳሰሳ ጥናት መሠረት ያለማቋረጥ በቀጠለው ጦርነት በአማራ ክልል የሰፈረው የብልፅግና ሰራዊት ከ100,000.00(አንድ መቶ ሺ) የሚልቁ እናቶችን እና ታዳጊወችን በጅምላ እና በተናጥል መድፈሩን አረጋግጠናል። ለክብሩ ቀናኢ የሆነው የአማራ ህዝብ ላይ የስነ ልቦና ችግር ለመፍጠር እና ለማዋረድ በሚል ስሌት በዚህ የመድፈር ወንጀል በተለዬ ሁኔታ ባለ ትዳር እናቶች፣ ካህናት እና ቄሶችን ጨምሮ የኃይማኖት አባቶች ሚስቶች፣ ታዳጊ ተማሪወች ሰለባ ከመሆናቸው በተጨማሪ እናቶችን ከባሎቻቸው እና ከልጆቻቸው ፊት ፣ታዳጊ ሴቶችን ከቤተሰቦቻቸው ፊት፣ መምህራንን ከጓደኞቻቸው እና ከተማሪወቻቸው ፊት በመድፈር የአገዛዙ ሰራዊት የአረመኔነቱን ጥግ አሳይቷል። የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የቀውስ ጠማቂ የሆነው አብይ አህመድ ያሰማራው ሰራዊት የማህበረሰቡን ቅስም በመስበር የገጠመውን ህልውናውን የመታደግ የመከላከል ጦርነት የመመከት ስነ ልቦናውን ለመንጠቅ አስቦ በፈፀማቸው የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ቀውስ ፈጥሯል፤ በርካቶችን አስረግዟል፤ አባት አልባ ልጆች እንዲበራከቱ አድርጓል። በመሰረቱ እነኝህ ወንጀሎች አብይ አህመድ በፓርላማ እና በሌሎች መድረኮች ባደረጋቸው ንግግሮች፣ የሰራዊቱ ጀነራሎች በተለያየ ግዜ ባቀረቧቸው መልዕክቶች ይሁንታ የተቸራቸውም ጭምር ናቸው። በቅርብ ግዜም የብልፅግና መዋቅር አካለ መጠን ያልደረሱ ታዳጊወችን እና የእዕምሮ ህሙማንን ለውትድርና የመመልመል እና ህገ-ወጥ የሰወች ዝውውር ተግባር ላይ መሳተፉን የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል። የሰራዊቱ መኮንኖች ነጋዴወችን በማገት እና በማጎሪያ ካምፖች በማሰር ከፍተኛ ገንዘብ እና ንብረት እየተቀበሉ አጋጣሚውን የግል ኪሳቸውን ለመሙላት እየተጠቀሙበትም ይገኛሉ። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ መላው ኢትዮጵያዊ እና የአማራ ህዝብ ይህንን የብልፅግና አረመኔያዊ ተግባር ታግሎ የማያስቆመው ከሆነ የበለጠ አጠናክሮ ሊቀጥልበት እንደሚችል ግልፅ ነው። ስለሆነም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ጥሪወች ያቀርባል። 1) ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ለዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ እና የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ተቋማት ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው የሰብአዊ መብት ሰነዶች፣ የተዋዋለቻቸው የሁለትዮሽ ስምምነቶች እና ሌሎች አስገዳጅ የቃል ኪዳን ሰነዶች በመንግስትነት ስም የተቀመጡ ቡድኖች የሰብአዊ መብቶችን እንዳይጥሱ እና እንዲያስጠብቁ ይደነግጋሉ። በመሆኑም የአብይ አህመድ አገዛዝ የቀጠናው የሰብአዊ ቀውስ አባት በመሆን ከሚፈፅመው ትርምስ በተጨማሪ በአማራ ህዝብ ላይ በይፋ በከፈተው ጦርነት ለፈፀማቸው የጦር ወንጀሎች እና ሌሎች የሰብአዊ መብቶች የመጣስ ጥፋቶች ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወሰድበት፣ የብልፅግና መዋቅር እና ባለስልጣናቱ ላይ ማዕቀብን ጨምሮ ሌሎች እርምጃወች እንዲወሰዱ እና ለአገዛዙ የሚደረጉ ማናቸውም የዲፕሎማሲ እና ወታደራዊ ድጋፎች እንዲቆሙ በማድረግ ለሰብአዊ መብት መከበር የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ እንጠይቃለን። 2) በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ለምትሰሩ ኢትዮጵያዊያን የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪወች እና ተቋማት የንፁሃንን ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር እና ዝርፊያን እንደ ጦር ስልት እየተጠቀመ ያለው የብልፅግና አረመኔያዊ አገዛዝ ከድርጊቱ ይታቀብ ዘንድ የቆማችሁለትን ዓላማ ለማሳካት የምትጠቀሙትን ማንኛውም የትግል ስልት በመጠቀም ህዝባዊ  ወገንተኝነታችሁን እና ሰብአዊ ርህራሄያችሁን እንድታሳዩ እንጠይቃለን። 3) ለመላው የአማራ ህዝብ የአማራን ህዝብ ህልውና ለማስጠበቅ በየ ጦር ግንባሩ ጠላትን ከሚፋለመው የፋኖ ሰራዊት ውጭ ያለው የማህበረሰብ ክፍል በየአደረጃጀቶቹ የሚያደርገው ተጋድሎ የብልፅግናን አረመኔያዊ ተግባር ለማስቆም ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም ሰፊው የማህበረሰብ ክፍል በአገዛዙ እየደረሰ ያለውን ህዝብን የማጥፋት እና የማዋረድ ተግባር ለማስቆም እና ህልውናውን ለማስከበር በነቂስ በመነሳት የህልውና አደጋ የሆነውን የብልፅግና አገዛዝ ለመቅበር የምናደርገው ተጋድሎ አካል እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን 4) ለዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት፣ ማህበራት፣ ዩኒቨርሲቲወች እና ሌሎችም:- በኢትዮጵያ የመንግስታት የጭቆና ታሪክ ውስጥ በልዩ ሁኔታ የሚጠቀሰውን የአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተ ሁለንተናዊ ጥቃት ትኩረት ማጣቱ አገዛዙ በድርጊቱ እንዲቀጥልበት ምክንያት ሆኗል። ይህ ጉዳይ በቂ ትግል እንዳይደረግበት እና እንዲዳፈን የሆነውም በእናንተ እና መሰል ተቋማት ስንፍና እና ቸልተኝነት ጭምር ነው። በዚህ ረገድ ቢቢሲ ለጀመረው የአገዛዙን ህገ ወጥ ድርጊት የማጋለጥ ተግባር ምስጋና እያቀረብን አሁንም ተመሳሳይ የሰብአዊ ተግባራት እንዲሰሩ፣ ገለልተኛ ተቋማት ጉዳዩን እንዲያጣሩ እና ተጨማሪ ምርመራወች እንዲደረጉ የሞራል እና የህግ ግዴታችሁን እንድትወጡ እየጠየቅን አፋብኃ ምርመራ ለሚያደርግ ማንኛውም ገለልተኛ አካል ሙሉ ትብብር የሚያደርግ መሆኑንም እናረጋግጣለን።

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የተሰጠ መግለጫ
+2
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

መብረቅ ክፍለጦር ለስድስት ወራቶት ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ:: ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለጦር ለስድስት ወራቶች ያሰለጠናቸውን በርካታ ቁጥር ያላቸው ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች ህዳር 14/2018 ዓ.ም በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል:: ምኒልክ ዕዝ አደረጃጀቱን በማዘመን የህልውና ትግሉን አጠናክሮ እየታገለ ያለ ሲሆን ሰራዊቱን በመደበኛ እና በልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች ደረጃ በሰው ሃይል እና በጦር መሳሪያ ማጠናከሩን በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራበት ይገኛል:: መብረቅ ክፍለጦር ባለፉት ጊዜያት ተደጋጋሚ ስልጠናዎችን በመስጠት ሰራዊት እያስመረቀ ራሱን በሰው ሃይል አጠናክሮ የመጣ ሲሆን ዛሬም በርካታ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎችን በማስመረቅ የቀደመ ተግባሩን እያስቀጠለ ይገኛል:: "እየሰለጠንን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!" መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ ክፍል ህዳር 15/2018 ዓ.ም

የሚሊሻ አባል ሆነው ከብልፅግናው አገዛዝ ጋር በመተባበር ወገናቸው የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀሙ እንደሆነ የገባቸው የአማራ ልጆች አገዛዙን እየከዱ በስፋት ፋኖን እየተቀላቀሉ ነው:: በዚህም ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በመደራጀት ላይ ያለችውን በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ የተቀላቀሉ የሚሊሻ አባላት (በብልፅግና አጠራር ሰላም አስከባሪ) ሁሉም ወደ ፋኖ መምጣት ነው የሚፈልገው እኛም ፋኖን በመቀላቀላችን እጅግ ላቅ ያለ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 15/2018 ዓ.ም

የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት በቡግና ወረዳ ህዝብ ላይ አሰቃቂና ዘግናኝ ድርጊት ፈፀመ! በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር እና ከብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት፣አድማ ብተና፣ፖሊስና ሚሊሻ መካከል ከባድ ትንቅንቅ ላይ መቆየታችን ይታወቃል። ስለሆነም ይህ አማራ ጠል የማፊያ ስብስብ 61ኛና 65ኛ ክፍለ ጦር፣ፖሊስ፣አድማ ብተናና ሚሊሻ ሦስት ዙ-23፣አንድ መድፍ፣አራት ባለ 82 ሞርተር፣አንድ ባለ 120 ሞርተር በመያዝ በምድር ሲገረፍ አልበቃው ብሎ በሰማይ ድሮን ቱርክ ሰራሽ ባይራክታር ቲቪ-2 በማሰለፍ አንድም ፋኖ ሳይጎዳ በዘመቻ አደም አሊ (አባ ናደው) ግዳን ወረዳ ሙጃ ማርያም ከተማ ላይ በፋኖ ተማርከው ህክምና ሲያገኙ የነበሩትን እነ ኮሎኔል ዘሪሁን ማሙየን ጨምሮ ሌሎች ሰባት ንፁሃንን መጨፍጨፉን ከዚህ በፊት መረጃ ማድረሳችን ይታወቃል። ይህ የመዋጋት አቅምና ሞራል የሌለው የትሮይ ፈረስ ሠራዊት የከባድ መሳሪያ ቅምቡላዎችን በዘፈቀደ በመወርወር ማህበረሰቡ ላይ፣እንስሳቶቹ ላይ፣ሰብሉ ላይ እያረፈ እንስሳትን፣ንፁሃን ዜጎችን እየገደለ የገበሬውን ክምር እያቃጠለ የማህበረሰባችን አንገት እያስደፋ በመሆኑ ገበሬው ለፍቶ እንዳለፋ እንዳይሆን ባደረግነው ለተወሰኑ ቀናቶች ገዥ መሬቶችን ወይም ገዥ ቦታዎችን የያዝን ሲሆን ነገር ግን የአማራን ህዝብ እንደ ግሪሳ እያደቀቀ የሚገኘው የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ከሰሞኑ በቡግና ወረዳ ህዝብ ላይ አሰቃቂና ዘግናኝ ድርጊት እየፈፀመ ይገኛል። መነሻውን ከቡግና ወረዳ አይና ከተማ በማድረግ 08 ቀበሌ ቅዱስ ሐርቤ በመሄድ አማራ ጠሉ የብልፅግና ሰራዊት "የፋኖ እህል ነው" በማለት በባንክ ብድር የሚሰራውን የአንድ ምስኪን ነጋዴ 30 ኩንታል ቦሎቄና 35 ኩንታል ባቄላ ወደ ከተማ ጭኖ ወስዶ ለመሸጥ ባጠራቀመበት መጋዘን ጭነው ወስደውበታል። የተዘጉ ሱቆችንም በመክፈት ዶሮ ብታልም ጥሬዋንእንዲሉ፤ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው በሚል እንደ ህፃን ልጅ ከረሜላ፣ጆሊጁስ፣ጭማቂ፣ብስኩትና የተለያዩ የሱቅ ዕቃዎችን ሱቆችን እየሰባበሩ በልተው የተረፈውን ውጭ ላይ አውጥተው መድፋታቸው፣ እዛው ቅዱስ ሐርቤ ቀበሌ ላይ የአባት አርበኛ ቤት ነው እያሉ ወደ ማህበረሰቡ ውስጥ በመግባት ሁለት ልጃገረዶችንና አንድ የአባውራ ሚስትን ደፍረው ሂደዋል። በዚህም የዘራፊነትና ሴሰኝነት ጥሙ አልረካ ያለው ጋለምታ የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት 010 ቀበሌ ቋሮ በመሄድ አማራን እንኳን ትጥቁን ቀበቶውን እናስፈታዋለን ብሎ ወደ አማራ ክልል ዘው ብሎ የገባው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት የ78 እና የ84 ዓመት አዛውንቶችን በካራማራ ጦርነት የተሳተፉ አርበኞችን ማስታወሻ ጓንዴና ውጅግራ መሳሪያ የአሁኑ አባት አርበኞች መሳሪያ ነው በማለት ሲወስዱባቸው የግለሰብ ቤት እየጎረጎሩ ቋጠሮ እህል ሳይቀር ከእጅ ወደ አፍ በልቶ የማያድር ማህበረሰብን ረሃብ ላይ ያለ በዕርዳታ ያገኘውን እህል ሳይቀር በመኪና ደርድሮ ጭኖ መውሰዱና ሊጋገር የተዘጋጀ የተቦካ ሊጥ ሳይቀር ቋሮ ቀበሌ ላይ አውጥተው ደፍተዋል። የግፍ ፅዋ ሞልቶ እንዲሉ እዚያው 010 ቀበሌ ቋሮ ላይ የፋኖ ቤተሰቦች ናቸው በማለት የትግላችን ችቦ ለኳሽ የአሳምነው ፅጌ የበኩር ልጅ አብሪ ኮኮባችን የሆነውን የአርበኛ ኮማንዶ ሃምሳ አለቃ ፍቅሩ ሙሉዬ እናት ቤት በመሔድ እርሳቸውን ሲያጧቸው አጥሩንና ቤታቸውን በማቃጠልና ንብረታቸውን በማውደም የሌሎቹንም አርበኞች ቤተሰቦች ቤትና ንብረት በእሳት እንዲጋይና እንዲወድም አድርገዋል፤ በተያያዘም አንድ የአባውራ ሚስት ለሁለት ደፍረው የእነ ፍቅሩ ሀገር ነው እያሉ የእህቶቻችንን አንገት አስደፍተው ሂደዋል። ፋኖን መግጠም ሲያቅታቸው ሲቪል ማህበረሰቡ ላይ ግፍ መፈፀማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን አይና እየሱስ ከተማ ላይ አንዲትን ሴት ለሦስት የደፈሯት ሲሆን መሠረት የሚባልን የአዕምሮ ህመምተኛን ወጣት የፋኖ መረጃ ነህ በሚል ተልካሻ ምክኒያት በማንበርከክ በስምንት ጥይት ደረቱና ጭንቅላቱ ላይ አከታትለው በመተኮስ ረሽነውታል። የአይና እየሱስ ቤተ-ክርስቲያን መጠበቂያ የነበረ ከአፄ ያለው ዘመነ መንግስት ጀምሮ የነበረን ጓንዴ መሳሪያ አሁን ላይ ቤተ-ክርስቲያኗ በቅርስነት ያስቀመጠችውን የቤተ-ክርስቲያኗን ክብርና ስርዓት በሚያንቋሽሽ መልኩ በከስክስ ጫማ ለምዕመኗ እንኳን የማይፈቀደውን ቤተ-መቅደሷ ድረስ በመግባት የወሰዱት መሆኑና የቤተ-ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ውስጥም መካነ ቀብር ሳይቀር ሁሉ እየቆፈሩና እያስቆፈሩ ፋኖ የደበቀውን እናገኛለን እያሉ ትኩስ መካነ መቃብር እየፈነቀሉ ከአማራ ማህበረሰብ ዕሴት ባፈነገጠ መልኩ የሙታንን ነፍስ ዕረፍት እየነሱ ይገኛሉ። በመጨረሻም ከ500 ዓመት በኋላ ዘርህ፣ማንነትህ፣ዕሴትህ፣ባህልህና ወግህ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ የተፈረደብህ የአማራ ህዝብ ሆይ የግፍ ፅዋው ሞልቶ እየፈሰሰ መሆኑን የተረዳኸው ሲሆን እኛ ልጆችህ የጄኔራል አሳምነው ፅጌ እስትንፋሶች፣የአፄ ምኒልክ፣የአፄ ቴዎድሮስና የአርበኛ በላይ ዘለቀ ወራሽ የልጅ ልጆች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የብልፅግናንና ጄሌዎቹን እስትንፋስ ለመቁረጥና የህዝባችንን ዕምባ የምናብስበት ቀን ቅርብ መሆኑንን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን ሲሉ በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የግዙፉ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ምክትል አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ሃምሳ አለቃ ፍቅሩ ሙሉዬ አሳስበዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ  ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 15/2018 ዓ.ም

----====== የትንሳኤው ዋዜማ ላይ ነን!!-----===== ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ከውስጥ ወንድሞችና ከውጭ ጠላቶች ጋር ሲያጋጨን በኖረው በሕዝባችን ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ በሆነው አዲስ ርዕዮታለም (አዲስ አስተሳሰብ)የተቀረፀ  ሕዝባችን ወደ መከበሩና መታፈሩ የቀደመ ልዕልናው መልሶ እስከ ምፅዓት ድረስ አጽንቶ የሚያቆይ አዲስ የሀይል ግንባታ(አዲስ ትውልድ)ፈጠራ ስራችን በህልማችን ልክ እየሄደ ነው። ሕዝባችን እስካሁን ድረስ በተለይም ከ1960 ወዲህ "መሪህ ነን" በሚሉት ጠላቶቹ ሀሳብ  የመሞቻ ኮዱ ሲመዘዝ፣ "ጠባቂህ ነን"በሚሉት ገዳዮቹ ሀይል  ሲሳደድ፣ሲገደል በጅምላ ሲቀበር ኖሯል። ይህ የሕዝባችን የመከራ ዘመን በኛ  ያበቃ ዘንድ የደማዊ ጠላቶቻችን ዘመን ዘለል የስቃይ መልክ በቅጡ ከመረዳትና መውጫ መንገዱን በብልሀት ከመትለም የጀመረው አዲሱ  ትውልድ የራሱን መቋሚያ ሀሳብ አሰናድቶ በመቋጨት አዲሱ ርዕዮታለማዊ መቋሚያ የሰረፀበት አዲስ ትውልድ ግንባታውን ደጁ ድረስ የመጣውን አረመኒያዊ ሰራዊት በየ ዕለቱ ከመግጠምና ከማሸነፍ፣በጠላት ወለድና ተፈጥሯዊ ሁነቶች ከመባዘን (እሳት ከማጥፋት)ባሻገር እያጠናቀቀ የአማራን እና የመላው ኢትዮጵያን ሕዝብ ትንሳኤ ለማብሰር የመጨረሻው ምራፍ ላይ ይገኛል። ከወቅታዊ ሁኔታው ባሻገር አስልተን እና አቅደን እየገነባነው ያለው ግዙፍ ኃይል ለማንም ስጋት የማይሆን የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ነባር እሴቶችን የጽንሰ ሀሳባዊ ስልጠናው አካል አድርገን የገነባው የጋራ ጠላት የሆነውን አረመኒያዊ ስርዓት ብቻ በጠላትነት ፈርጆ የተነሳ ነጻነትን ለሚናፍቀው መላው ኢትዮጵያዊ ብቸኛው ተመራጭ ሀይል ነው!!! ይህ የኃይል ግንባታ ስራ በትጋት ከመኪናወንባቸው ቀጠናዎች ውስጥ የ105ኛ ኮር 66ኛ ክፍለ ጦር አንዱ ሲሆን ክፍለ ጦሩ ከድርጅታችን ስልጠና  መምሪያ የወረደለትን መአከላዊ እቅድ በቪዲኦው በምናየው መልኩ በትጋት እየፈጸመ ይገኛል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!! የአፋብኃ ቴወድሮስ እዝ አደረጃጀት መምሪያ ሐላፊ አርበኛ እሸቱ ጌትነት በላይ

+2
ሕዝብ ላቡን ጠብ አድርጎ የሰራቸው የቀበሌ ተቋማት በአረመኔው ሰራዊት እንዲህ እየነደዱ ነው። በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ወርቅማ ቀበሌ የሚገኘውን የቀበሌ አዳራሽ በትናንትናው ዕለት የአብይ አህመድ ሰራዊት እንዲህ አውድሞታል። ይህ ጨካኝ አንባገነን ስርዓት  አማራንና የአማራ የሆነውን ሁሉ እያጠፋ ነው ያለው ። ላለመጥፋት በሚደረገው የህልውና ትግል ሁሉም አማራ የራሱን ድርሻ ሊወጣ ይገባል።

=====ህዝባዊ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል====== ################################### ድርጅታችን አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ይፋ ባደረገው አዲስ መዋቅር መሰረት በአዲስ በተደራጀው 201ኛ ኮር 74ኛ ክፍለ ጦር እና በስሩ ባሉት የወረዳ ጊዜያዊ መስተዳድሮች የድርጅታችንን ቁመና ፣ አዲሱን መዋቅር ማስረዳትና ማደራጀት እንዲሁም ህዝባችንን ማወያየት ቀጥለናል። ዛሬ በቀን 07/03/2018 ዓ/ም በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ነባርና በቅርቡ ከጠላት ነፃ የወጡ ሰኞ ገበያ ንዑስ ወረዳንና እኔሳ ቀበሌን  የጊዜያዊ መንግስቱ አመራሮች በቀጠና በመከፋፈል አወያይተናል። በውይይታችንም፦ የቀበሌ መዋቅር የሌላቸውን አዋቅረናል፣ የድርጅታችንን ወቅታዊ ቁመና አስረድተናል፣ የግል ታጣቂውን በሻለቃ አደራጅተን የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅና በወል  መሬትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮችን የመጨረሻ እልባት ሰጠናል፤ ማህበረሰቡም አጥቶት የነበረውን ነፃነቱን በማግኘቱ ደስታውን ገልፆ ይህንን ነፃነት ለማፅናት የትኛውንም ድጋፍ እንደሚያደርግና መስዋዕትነትንም ለመክፈል ዝግጁ እንደሆነ በሙሉ ድምፅ ገልፆልናል። አማራ ያሸንፋል!! ድል ለአማራ ፋኖ! ! የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሚዲያና ኮምኒኬሽን ሀላፊ ፋኖ ይበልጣል ጥሩነህ