ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más3 678
Suscriptores
+2624 horas
+3797 días
+1 10930 días
Archivo de publicaciones
በጎንደር ማጥቃታችን ተጠናክሮ ቅሏል!!
ከባ/ዳር ቅርብ ርቀት የምትገኘው ቁልፍ የመገናኛ ከተማ የፎገራዋ ሞንሟና ወረታ ከተማ በሰራዊታችን እቅፍ ውላለች።
በወረታ በፊት ለፊት የምድር ጦር ውጊያ የተደቆሰው አገዛዙ ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ የድሮን ጥቃት ሰንዝሯል።በንፁሃን ላይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳትም አድርሷል።
የንፁሃን ወገኖቻችን የግፍ ጥቃት አስር እጥፍ እየመለስን እንገናለን።ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
#ወረታ_ከተማ_ገቢ_ሆናለች‼️
በምድር ሲያቅተው መጣ በሰማይ
መሬት ከለቀቀ መንግሥት አለ ወይ?
የአገዛዙ ኃይል በምድርም በሰማይም ያለ የለለ ኃይሉን ቢጠቀም የድሮን ጥቃት ቢፈፅምም አናብስቱ ፋኖ የፎገራዋ ፈርጥ የሆነችውን ወረታ ከተማ ዛሬ የካቲት 08/2018 ዓ/ም ንጋት ጀምሮ በተደረገ ውጊያ በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባቷን አናብስቶች ለንስር አማራ ገልፀዋል‼️
የፋኖን የምህረት አዋጅ አንቀበለም ያሉ ሆዳደሮች ተደምስሰዋል‼️
08/ዐ6/2018 ዓ.ም
የእራስን ችግር በእራስ የመፍታት ጥበብ በመጠቀም
64ኛ ክ/ጦሩን ወደ ቀድሞው ቁመናው የመመለስ ስራዎች ተሰርተዋል!!
የካቲት 08/2018 ዓ.ም
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ እና 201ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች
በተገኙበት የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ እና የሽፈራው ገርባው ልጆች 64ኛ ክፍለ ጦር ላይ ተፈጥሮ የነበሩ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ክፍለ ጦሩን ወደ ቀድሞው ቁመናው የመመለስ ስራዎች ተሰርተዋል።
የአብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ በዚህ ሶስት ዓመታትን እያካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማስቆም እና የአማራ ህዝብ ከተደቀነበት የህልውና አዳጋ ለመመከት የበላይ ዘለቀ እና የሽፈራው ገርባው ልጆች #64ኛ_ክፍለ_ጦር አመራር እና አባላት የውስጥ ችግራቸው በመደማመጥ፣ በመከባበር የድርጅቱ ታላላቅ መሪዎችን እና የአካባቢው ማህበርሰብ ክፍል እሴቶችን በማክበር ለትግላችን እና ለድርጅታችን የሚበጃቸውን ስራዎች እውን ለማድርግ ቤታችንን ዘግተን መክረናል።
በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል በቁጥር ቆጥረን የማንጨርሳቸው ንፁሃን አማራዎች ውድ ህይወታቸውን ገብርዋል። የአብይ አህመድ አገዛዝ በዚህ ሶስት ዓመት በአማራ ህዝብ ላይ ጭካኔ በተሞላበት በሰማይ ድሮን፣ በምድር ታንክ፣ መድፍ እና መካናይዝድ ጦር መጠቀም ሀገር የገነበው የአማራ ህዝብ ላይ በርካታ ግፎችን፣ በደሎችን፣ ውድመቶችን እየፈፀመ እንደሚገኝ እና በዚህ የቀውስ ትግል ትግሉን የሚመሩ፣ ትግሉን የሚያሸጋግሩ አስተዋይ ህዝብ እና ትግሉ የሚፈልጋቸው መሪዎችን ከታች የማብቃት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ አስረድተዋል። ብዙ ዋጋ የተከፈለበት፣ የተለፋበት፣ የተደከመበት ለአማራ ህዝብ አሉ የሚባሉ የትኛውም አይነት ጥያቄዎችን ለማስመለስ አንድነት እና መሪ አስፈላጊ መሆኑን በማስረዳት የአማራ ትግል ከአራቱም የአማራ ማዕዘን የተወጣጡ ጠንካራ መሪዎችን መርጦ ወደ አንድ መምጣቱን በማስረዳት ድርጅቱ የሚሰጠው የትኛውም አይነት ትዛዝ ለመፈፀም ወታደሩ ዝግጁ እንዲሆን የቴዎድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራር አርበኛ እሸቱ ጌትነት በአክብሮት ገልፀዋል።
በእነማይና ሸበል በረንታ ወረዳ ስር የሚገኘው 64ኛ ክፍለ ጦር የብዙ ጀግኖች መፍለቂያ በርካታ ገድሎች የተፈፀበት ቦታ መሆኑን በማስረዳት ዛሬ ላይ በአምባ ገነኑ አብይ አህመድ እየተተራመሰች የምትገኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ከዚህ አካባቢ በነበሩ አርበኞች፣ ጀግኖች መስዋትነት ከውጭ ወራሪ እና ከውስጥ ባንዳ ሰላቶ ሳትደፈር የቆየች መሆኗን በማስገንዘብ ዛሬ ላይ የአማራ ህዝብ እያካሄደ በሚገኘው የህልውና ትግል የዚህ አካባቢ የፋኖ አመራር እና አባላት እድለኛ መሆናቸውን በመግለፅ የዛ ታሪክ ባለቤት የነበሩ አርበኞችን ታሪክ መዘከር ብቻ ሳይሆን ዛሬ ላይ ታሪክ ሰሪ መሆን እንዳለባቸው የቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር አመራሮች አስረድተዋል።
#የጠላት_እራስ_መታቱ #የውስጥ_ተለላኪ_ባንዳ መድሃኒቱ #የትግል_የደም_ነጋዴዎች_መድሀኒት በጀግኖች በበሳል እና አስተዋይ፣ እንግዳ ተቀባይ መሪዎች የሚመራው #64ኛ_ክፍለ_ጦር የያዘው መልካ ምድር ለውጊያ የማይመች ቢሆንም ከነፍስ ወከፍ እስከ ቡድን መሳሪያ በመታጠቅ የሰለጠነ ወታደራዊ የሰው ሀይል በማደራጄት የበላይ ዘለቀ እና የሽፈራው ገርባው ልጆች ህዝባቸውን ሳያስደፍሩ የአብይ አህመድ አገዛዝ ሰራዊት እና ተለላኪ ባንዳ ላይ ከባድ እርምጃ በመውሰድ የአገዛዙን አረመኔዊ ሰራዊት ሰላም በመንሳት የውስጥ ችግራቸውን በውስጥ የመፍታት ጥበባቸው በመጠቀም ህዝባችን እና ድርጅቱ የሚሰጣቸውን ትዛዝ በመቀበል እየፈፀሙት ያለውን ተግባር በተመለከተ በድርጅቱ ሰብሳቢ ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ በስልክ መልዕክትና ላቅ ያለ ምስጋና አስተላልፈዋል።
እኛም የጀግኖች አርበኞች ምድር መሰባሰቢያ የሆነው 64ኛ ክፍለ ጦር አመራርና አባላት የአብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እና ጦርነት ለመመከት የአማራ ህዝብ መሪ ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ የሰጠንን ትዛዝ ተቀብለን በቀጠናው ከትላንቱ የተሻለ ስራ ለመስራት ቃል ገብተናል።🙏🙏🙏
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
የካቲት 08/2018 ዓ.ም
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
የሰይፍ እና የቅዱስ ፍቅር የዘር ማዳን ትግል !! ⚖️🩸
👉ሳትሰለቹ እስከመጨረሻዉ እንድታነቡት☝️
ታሪክ በደም እንጂ በብርድ ልብስ አይጻፍም። ዛሬ የምናነበው "የአማራ የደም ሰነድ" ተራ ቁጥርና ስም ዝርዝር አይደለም፤ እርሱ የአንድ ግዙፍ ሕዝብ የሕይወት ዋጋ እና የሥርዓተ-መንግሥት ውድቀት የታተመበት ጥቁር መዝገብ ነው።
ከ እስከ አሁኗ ሰዓት በኢትዮጵያ ምድር የፈሰሰው ደም ዓለምን "ለምን?" ብሎ የሚጠይቅ የሕሊና ጩኸት ነው።
የአምላክ ምስክርነት እና የንጹሐን ጩኸት
ወላዲተ-አምላክን ብዬ እምልላችኋለሁ፤ በእኔ አእምሮ ውስጥ ለዘላለም የማይጠፋ፣ የአማራን በታላቅ ሁኔታ መመታትና መቁሰል ቀንና ሌሊት የሚነግረኝ አንድ መሪር ጩኸት አለ። እርሱም በቶሌ ጭፍጨፋ ወቅት የገዳዮችን ሰይፍ አይታ፦ "ወላሒ... ከአሁን በኋላ አማራ አልሆንም!" ብላ የጮኸችው የሕፃኗ ድምፅ ነው።
ይህ ድምፅ ተራ የፍርሃት ጩኸት አይደለም፤ ይህ ድምፅ በፈጣሪ ዙፋን ፊት የቀረበ የታሪክ ክስ ነው። የአላህ ፍቅር የሰው ልጅ ጠንቅቆ ያውቃል፤ ለፈጣሪውም በሚገባ ይገዛል። ነገር ግን በሕፃን አንደበት "አላህዬ! እባክህን አማራ አታድርገኝ" ብሎ መማፀን፣ በታሪክ የታየውንና ዓለምን ያስገረመውን የጀርመን ናዚዎች በ6 ሚሊዮን አይሁዶች (Jews) ላይ የፈጸሙትን የሆሎኮስት (Holocaust) ጭፍጨፋ የሚያስንቅ ግፍ ነው። ለዚህም በሕፃኗ አንደበት የተጠራው አላህ ራሱ ምስክር ነው።
የታሪካችን ትልቁ ሀዘንና ልዩነት ግን እዚህ ጋር ነው፦ አይሁዶች የተጨፈጨፉት በባዕድ ሀገር ዜጋ (በጀርመኖች) ነበር፤ እኛ አማራዎች ግን በገዛ ሀገራችን፣ በገዛ መሪዎቻችን እና በገዛ ሰራዊታችን ነው የታረድነው። ገዳዩ የባዕድ ቋንቋ ተናጋሪ ሳይሆን፣ "ሀገር እመራለሁ" የሚለውና በግብራችን የምናውቀው የራሳችን አገዛዝ መሆኑ ቁስሉን እጥፍ ያደርገዋል። ይህች ሕፃን አማራነትን የጠላችው ማንነቱን ጠልታ ሳይሆን፣ አማራነት ለሞት የሚያስረክብ "የጥፋት ምልክት" ተደርጎ ስለተቀረጸ ነው። ዛሬም ቢሆን የአማራ ምሁራን፣ ነጋዴዎችና ባለሥልጣናት ይህን የሕፃኗን ጩኸት ሰምታችሁ ካልተንቀጠቀጣችሁ፣ በምድርም በሰማይም ከቶ አታመልጡም። የዚያች ሕፃን ቃል በአማራ ታሪክ ውስጥ ከፈሰሰዉ የአማራ ደም እና ከረገፈዉ ሒወት ጋር እንደ ርዕስ በቀይ ብዕር የማይደርቅ ደም ሆኖ ተመዝግቧል።
እናማ አማራ መሆን ለሞት የታጨ መሆን ከሆነ፣ ታሪካችንን በደም ሳይሆን በነፃነት የምንቀይርበትን ህግ እናጠናለን !!
የሰይፍ እና የቅዱስ ፍቅር ስልታዊ ጥምረት
የአማራን ሕዝብ ማዳን ማለት የዓለምን ሰብዓዊነት ማቆየት ማለት ነው። ትግላችንን "በቅዱስ ፍቅር" ልንመራው ይገባል። ራሳቸውን የሚያጠፉን አካላት እንኳን እስኪያፍሩ ድረስ የሞራል የበላይነታችንን ልናሳያቸው ይገባል።
ለፋኖዎች ስልታዊ ጥሪ፦ እውነተኛ የሕዝብ ኃይል መለያው ምርኮኛን ማከም ነው። ጠላትን በጦር ሜዳ ስንመታ፣ የተማረከውን ግን ነፍስ እንዳይጠፋ በጥንቃቄ በማከም የዓለምን ትኩረት መሳብ አለብን። ይህ የአማራ ርኅራኄ የዲፕሎማሲያችን ትልቁ መሣሪያ ነው።
ለታጠቀው የጠላት ኃይል የሕሊና ጥሪ፦ ዛሬ በአሁኑ መንግስት ሰራዊት ውስጥ ያለህ አማራ ወጣት ሆይ! የገዛ ወገንህን ደም እንድታፈስ የሚያዝህ ሥርዓት፣ ነገ አንተንም እንደ መሣሪያ ተጠቅሞ ይጥልሃል። ፋኖን መቀላቀል የፖለቲካ ምርጫ ሳይሆን የሰውነት ግዴታ ነው።
ስራችን እንስራ
ምሁራንና መምህራን ሆይ! ዝምታችሁ የገዳዮች ግብረ-አበር ያደርጋችኋል።
ምሁራን ስለአማራ በእስር ቤት እንደሚገኙት ፕሮፌሰሮች ሁኑ!!
መምህራን ከማስተማራችሁ በፊት ስለአማራ የህሌና ፀሎት አስቀድሙ።
ተማሪውም በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ሆኖ በሐሳብ ሪቮሊሽን (Ideological Revolution) ውስጥ ሊሳተፍ ይገባል።
በትግራይ ወንድሞቻችን ላይ የደረሰው ስነ-ልቦናዊ መገለል ለኛ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው። ዛሬ ካልነቃን የኛም እጣ ፈንታ ከምድረ-ገጽ መጥፋት ነው።
ልንገራችሁ
እኔን እህቴን!! ሕፃኗ አማራዋ እህቴ "ወላሒ... አማራ አልሆንም!" ስትል የፈሰሰው እምባ፣ የሁላችንም የቤት ሥራ እንደሆነ ይታወቃል። እነለአለም እነ ናሁሰናይ ሌሎች ሰማዕት አማራም ሠዎች ናቸዉ። ፍትህ ሊያገኙ ይገባል።
ጠላቶቻችን "ሞኝ" ይሉን ይሆናል ሞኝስ እነሱ።
እኛ ከፈጣሪ ጋር እኛን እናድናለን!!
አማራን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው፤ ኢትዮጵያን ማዳን ደግሞ የሰው ልጅን ክብር ማቆየት ነው።
የተደረገብንን ፍጥረት ሁሉ ይረዳ ያድነንም!!
ህልውናችን በደማችንና በዕውቀታችን እናም በትግላችን እንታደግ ።
እርግማን👉 አማራ እየተገደለ'ና እየተሳደደ እንቅልፍ የሚተኛ ካለ በተኛበት አይነሳ።
የአማራን እናት ለቅሶ የሚረሳ እስከሰባት ትዉልዱ የመከነ ይሁን!!
አሌክስ/አዲስ ነኝ
ከፈረሰዉ መንደሬ ✍️
+4
የማንሰራራት ዘመን!!! የብልግና ቱርፋት በአማራ ክልል!!
ብልጽግና የሚባል አረመኔ እና ገ*ዳይ ቡድን ከ ቱርክ እና ከ አረብ ኤምሬትስ በተዋሰው ድሮን የአማራን ህዝብ ከምድረ ገጥ ለማጥፍት በርትቶ እየ*ጨፈጨፈን ይገኛል።
የአረመኔው ስርዓት በ29/05/2018 ዓ.ም በይልማና ዴንሳ ወረዳ ጎሽዬ ቀበሌ ላይ የቄ/ሐይማኖትን መኖሪያ ቤት አቃጥሎታል ዛሬ ቦታው ላይ ማለትም 07/06/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦርና ሻለቃ አመራሮች እንዲሁም የይልማና ዴንሳ ጊዜያዊ መንግስት የሚዲያ ክፍል ቦታው ላይ በመገኘት የተቃጠለውን ቤትና ንብረት የተመለከትነ ሲሆን :-
1,የክ/ጦሩ ዘመቻ መምሪያ ዘላለም አለሙ
2,የ3ኛ ሻለቃ ም/አዛዥ ፍቃዱ አለኸኝ
3,የ3ኛ ሻለቃ ም/ዘመቻ ዳዊት አንማው
4,የይ/ዴንሳ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት የሚዲያ ክፍል ሳሙኤል ስለሺ
ቦታው ላይ ቆመን እንደተመለከትነውና በፎቶም እንደሚታየው ዶርሙ ሙሉ ለሙሉ የወደመ ሲሆን ዋነው ትልቁ ቤት በማህበረሠቡ ርብርብ በከፊል ማትረፍ የተቻለ ቢሆንም ግን አገልግሎት መስጠት የማይችል መሆኑን ከፎቶ ማስረጃችን ማየት ይቻላል::
ቤቱ ሲቃጠል ውስጥ ላይ የነበረን እህል እስከቻሉ ድረስ ጭነው የወሰዱት ሲሆን የቀረውን ሌላ ንብረትና እቃዎችን እንዲሁም ሙሉ አልባሳትን ያቃጠሉት ሲሆን ሴትዮዋንም አብረን እናቃጥላት እያሉ ይጨቃጨቁ እንደነበር ከተበዳይ አንደበት መስማት ችለናል::
ቤቱ ሲቃጠልም 8ቀፎ ንብ አብረው መቃጠላቸውን ገልፀዋል
ሙሉ የተቃጠሉ ንብረቶችን ዝርዝር በማስረጃ የምናቀርብ ይሆናል::
ሳሙኤል ስለሺ የይልማና ዴንሳ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት የሚዲያ ክፍል!!
ከውስጥ አርበኛ የደረሰን መረጃ!
በተለያየ ምክንያት ጠፍቶ የነበረ የውስጥ አርበኛችን ይህንን መረጃ ይዞ ብቅ ብሏል። አራዊት ሰራዊቱ በተለይ በጎጃም ቀጠና አዲስ የውጊያ እቅድ አውጥቶ ለትግበራ በዝግጅት ላይ ይገኛል።
1) በምስራቅ ጎጃም ግንደወይን፣ መርጦለማርያም ያለውን የአፋብን ፋኖዎች ከየጁቤና ደብረኤሊያስ ካሉ የፋኖ ኃይሎች ጋር አለመግባባቶችን መፍጠር አቅደዋል፤ ለዚህም እነ አሳማው ማስረሻ እየሰሩ እንደሚገኙ ተነግሯል። አለመግባባቶችን ለመፍጠርም እንደምሳሌ በፋኖ አመራሮች መካከል "እገሌ ከገሌ ይበልጣል" የሚል ፉክክር መፍጠር፣ ስብሰባዎች ያለ ስምምነት እንዲያልቁ ማድረግ ወዘተ ይገኝበታል ተብሏል።
2) ሌላው "ለፋኖ የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት ስቦ መምታት" የሚል እቅድም አውጥተዋል። ለዚህ ከተመረጡ ቀጠናዎች ውስጥም ሰሜን ጎጃም ብራቃት 19ኪሜ ቀጠና ፋኖን ስቦ መቶ መቆጣጠር፣ ግንደወይን የሳሙኤል ክ/ጦር ማክሰም እና የሞጣ እና የ ግንደወይን ሙሉ ለሙሉ ነጻ ማውጣት፣ መርጦለማርያም መካነሰላም ቀጠና በተመሳሳይ ሁለት ተራራዎችን መቆጣጣር፣ ጮቄ ዙሪያ የቦቅላ፣ቁይ፣ጁቤ ዋብር ፋኖን በመሳብ ጮቄን መቆጣጠር፣ ወዘተ መሰል ዝርዝር እቅዶች ደርሰውናል። ለዚህ መፍትሔው አፋብን ከሚደርሱት የውጭ መረጃዎች ባሻገር፣ የእራሱን የደህንነት መዋቅር በማንቀሳቀስም ከእንቅስቃሴና ጥቃት በፊት መረጃ መሰብሰብና መተንተን ያስፈልጋል እንላለን።
3) ሌላው ደግሞ የፋኖ ስልጠና ቦታዎች ብለው ባሰቧቸው አካባቢዎች ለምሳሌ በቢቸና እና ደብረወርቅ አካባቢዎች የአየር ጥቃቶችን መፈፀም የሚል እቅድም ማውጣታቸው ተነግሯል።
የሆነው ሆኖ ይህ የተንኮታኮተ አራዊት ሰራዊት የሚያድነው ወይም የሚያፀናው የኦህዴድ ስርዓት አይኖርም፤ ነገሮች ወደ መቋጫው ተቃርበዋል።
የፊስቡክ አካውንታችን ስለተዘጋ ይወዳጁን ቤተሰብ https://www.facebook.com/share/1CS5smADnB/
የሥርዓተ-መንግሥት መጥለቅ እና የታሪክ ግዴታ፦ በደም እና በብልሃት መካከል ያለ የህልውና ጉዞ ⚖️
ታሪክ የራሱ ቋንቋ አለው። ዛሬ በአማራ ምድር የምንሰማው ድምፅ የተራ ግጭት ሳይሆን፣ ለአሥርተ ዓመታት የተሸረበ "መዋቅራዊ ግፍ" የመጨረሻውን ምዕራፍ እየዘጋ መሆኑን የሚያበስር የታሪክ ነጎድጓድ ነው። እንደ ያለንበትን ሁኔታ እኔ ሳስበዉ፣ አሁን ያለውን ሁኔታ በሦስት መሠረታዊ የፍልስፍናና የስትራቴጂ አውዶች እንደሚከተለው ላሳያችሁ
1. የሙያ እና የሰብአዊነት ሞት (Technocratic Tyranny)
የአፋብን ምኒልክ ዕዝ የጤና መምሪያ ያወጣው መግለጫ አንድን አስከፊ እውነት ይነግረናል። ሥርዓቱ ህክምናን እንደ ጦር መሣሪያ (Weaponization of Healthcare) እየተጠቀመበት ነው። ዶ/ር ፀጋሁን ስሜን የመሰሉ የሕክምና ምሁራንን መግደል ተራ ወንጀል ሳይሆን፣ የአንድን ሕዝብ የወደፊት ተስፋ የመቁረጥ "የታቀደ የዘር ማጥፋት" አካል ነው። ፈላስፋው ሶቅራጥስ "እውቀት ለበጎነት ነው" ይላል፤ ዛሬ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ እውቀት ለጥቃት ኢላማ ሆኗል። የጤና ባለሙያዎች ወደ ትግሉ እንዲቀላቀሉ የቀረበው ጥሪ፣ ሥርዓቱ ከሥነ-ምግባር አጥር ውጭ መውጣቱን የሚያሳይ የሞራል ፍርድ ነው።
2. የወታደራዊ ስልት ብስለት፦ "አሳምነው" እና "ከሰም"
በከሰም ፪ኛ ኮር እና በነበልባል ክፍለ ጦር የተመዘገበው ድል፣ ወታደራዊ ሳይንስን በተግባር የገለጸ ነው። የአገዛዙ "ሪፐብሊካን ኮማንዶ" በጀግኖቹ ሻለቃዎች (መብረቁ እና ራስ በኃይሉ) ወጥመድ ውስጥ ገብቶ መፈራረሱ፣ ጦርነት የሚሸነፈው በልዩ ሥልጠና ሳይሆን በፍትሐዊ ዓላማ መሆኑን ያረጋግጣል። የጠላት ጦር በሽንፈት ስካር አእምሮ ሕመምተኛውን "ፍሰሃ ሚሊዮንን" መረሸኑ፣ ሥርዓቱ ወታደራዊ ብቻ ሳይሆን "ስነ-ልቦናዊ ውድቀት" ውስጥ መግባቱን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
3. የዲፕሎማሲያዊ መጋረጃ እና የአፍሪካ ኅብረት ዝምታ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለአፍሪካ ኅብረት የላከው ደብዳቤ ትልቅ የፖለቲካ ብስለት ነው። እስካሁን የነበረው ክፍተታችን "የተደራጀ የዲፕሎማሲ ድምፅ" ማጣት ነበር። ፈላስፋው ኤድመንድ በርክ "ክፉዎች እንዲያሸንፉ ብቸኛው መንገድ ደጎች ዝም ማለት ነው" እንዳለው፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት ዝም ያሉት እኛ መጮህ ስላልቻልን ነበር። አሁን ግን ትግሉ ከሜዳው ወጥቶ ወደ ዲፕሎማሲው አደባባይ እየተሻገረ ነው። የአፍሪካ ቀንድ ሰላም ከአማራ ሕዝብ ህልውና ጋር የተሳሰረ መሆኑን ዓለም እንዲረዳ የማድረግ ስራ አሁን ተጀምሯል።
4. የሽግግር ወቅት ጥሪ፦ ተቋማትን ማዳን
በአማራ ሳይንት (አጅባር) እየታየ ያለው የመሬት ሽያጭ እና የሃብት ዘረፋ፣ ሥርዓቱ "የመጨረሻውን ራት" እየበላ መሆኑን ያሳያል። ሕዝቡ ንብረቱ እንዳይዘረፍ ማሳሰቢያ መሰጠቱ ብልህነት ነው። ሥርዓቱ ሲወድቅ ተቋማት መቆም አለባቸው። የደብረ ብርሃን የለቅሶ ጥሪ ደግሞ የሁላችንም የሞራል ፈተና ነው። ከወለጋ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በደጃፋችን እየረገፉ እኛ "አሸንፈናል" ብለን ድል የምናከብር ከሆነ፣ ድላችን ትርጉም የለሽ ይሆናል። እውነተኛ ድል የተፈናቀሉትን መመለስና የቆሰሉትን ማከም ነው።
ማጠቃለያ፦ ከስሜት ወደ ስልታዊ መሪነት!
የነፃነት ጉዞው በፎከራ ሳይሆን በጥልቅ ስልት (Strategy) ሊመራ ይገባል። ጠላትን በኃይል ስንመታ፣ ሕዝባችንን ግን በፍቅርና በተግባር ልንደግፈው ይገባል። የትላንት ተማሪ፣ የዛሬ ታጋይ፣ የነገው መሪ ሆይ! የታሪክ ማዕበል መጥቷል። መደራጀት ወይስ መጥፋት? ምርጫው የሁላችንም ነው።
ባለን አቅም ሁላችንም እንታገል!!!
"ሰይጣንም ቢሆን ከጥፋት ኃይል የሚታደገን ከሆነ እንቀበለዋለን፤ በኋላ ንስሐ እንገባለን እንጂ አሁን ዘር የማትረፍ ጉዳይ ነው!"
አሌክስ/አዲስ ከፈረሰዉ መንደሬ ✍️
ቁስለኛ የሀምዳን ዳጋሎ ወታደሮች በድሬዳዋ ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ተሰምቷል‼️
ወታደሮቹ ከሳምንታት በፊት የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ላይ የአየር ጥቃት በመፈፀም ጉዳት ያደረሰባቸው መሆናቸውን የመረብ ሚዲያ ወታደራዊ ምንጮች ገልፀዋል።
የብልፅግናው አገዛዝ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ከቻይና በኪራይ ባስመጣቸው የጦር ሄሊኮፍተሮችና ድሮኖች "ሰማዩም የኛ ነው" በሚል ትርኢት እያሳየ በነበረበት ወቅት በተመሣሣይ ሰዓት የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ከሚገኙ አከባቢዎች ጀምሮ የኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሶ በመግባት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አከባቢዎች ላይ የአየር ድብደባ መፈፀሙን ጣቢያችን መረብ ሚዲያ በወቅቱ መዘገቡ አይዘነጋም።
የብልፅግናው አገዛዝ የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ አየር ኃይል ንብረት የሆኑ F-16 ስድስት ተዋጊ ጄቶችን እና ስድስት AH-64 Apache ሄሊኮፍተሮችን እንዲሁም ከቻይና ለ10 ደቂቃ 120,000 ዶላር ከፍሎ በተከራያቸው ድሮኖች "ሰማዩ የኛ ነው" በሚል <የእውቀት አክፍሎተኛ> የሚባሉ ተከታዮቹን ይዞ ሲደሰኩር ነበር።
ኦህዴድ መራሹ የብልፅግና ቡድን በተውሶ የጦር ጄቶችና በኪራይ ድሮኖች "ሰማዩም የኛ ነው" በሚል ሀሰተኛ ድስኩር ባሰማበት ወቅት፡ በተመሣሣይ ሰዓት በጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርኻን የሚመራው የሱዳን መንግስት ጦር የኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሶ በመግባት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጥቃት መፈፀሙን ነው በዕለቱ ጣቢያችን በዘገባው የጠቀሰው።
የአየር ድብደባው ያነጣጠረው በኦህዴድ መራሹ አገዛዙ ይሁንታ በኢትዮጵያ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በኢትዮጵያ አዋሳኝ በሆኑ የሱዳን አከባቢዎች የጦር ሰፈር መስርተው በሚንቀሳቀሱ የሄሜቲ ወታደሮች ላይ ሲሆን፡ በዚህም በርካቶች ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ መቁሰላቸውን ነው ወታደራዊ ምንጮቻችን የገለፁት።
እነዚህ ቁስለኛ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ወታደሮች በድሬዳዋ ከተማ ምስራቅ ዕዝ ደረጃ ሦስት ሆስፒታል ተኝተው ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የገለፁት የመረብ ሚዲያ ወታደራዊ ምንጮች፡ እነዚህ የሄሜቲ ወታደሮች በአማራ ክልሉ ጦርነት ቆስለው በሆስፒታሎች መጨናነቅ ምክኒያት ወደ ደሬዳዋ ተልከው እየታከሙ ከሚገኙ የምስራቅ ዕዝ ወታደሮች የተለየ እንክብካቤና ሕክምና ይደረግላቸዋል ብለዋል።
"በአማራ ክልሉ ጦርነት ቆስለው በዚህ ሆስፒታል ተኝተው እየታከሙ የሚገኙ የምስራቅ ዕዝ ወታደሮች ምግብ የሚቀርብላቸው በቀን አንዴ ነው እሱም፡ የቀዘቀዘ ሽሮ ነው፡ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አባላት ግን በተመረጡ ሼፎች የሚዘጋጁ ሰውነት የሚጠግኑ ምግቦች በየሰዓቱ ይቀርቡላቸዋል" ያሉን ምንጮቻችን፡ በዚህ የተበሳጩ በርካታ የምስራቅ ዕዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት ቁስላቸው ሳይድን ከሆስፒታሉ ወጥተው መጥፋታቸውን አክለው ገልፀዋል።
ደረጃ ሦስት ተብሎ የሚጠራው ሆስፒታል ድሬ ዳዋ ከተማ ልዩ ቦታው ኩባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኝ በመሐመድ ተሰማ የሚመራው የምስራቅ ዕዝ ንብረት የሆነ ሆስፒታል ነው።
07/ዐ6/2018 ዓ.ም
ከአፋብን ምኒልክ ዕዝ የጤና መምሪያ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ‼️
ፍፁም ሰብአዊ በሆነው የጤና ሙያ ውስጥ የምትገኙ ወንድሞቻችን/እህቶቻችን ኑ ተጋግዘን ኢ-ሰብአዊ የሆነውን ሥርአት እንቀይር!
አማራ ተኮር የሆነው የዘር ማጥፋት ጦርነት በተለየ መልኩ በይፋ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ የጤና ተቋማት፣ የጤና ሙያተኞች እና የጤና አገልግሎት የፋሽስታዊዩ ሥርአት አይነተኛ ኢላማዎች በመሆናቸው ሥርአቱ ህክምና መከልከልን እንደጦር መሣሪያ እንደሚጠቀም ግልፅ ማስረጃዎች ናቸው። ሥርአቱ ጤና ተቋማትና ግብአቶቻቸው ላይ የሚፈፅመው የጦርና የሠብአዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች አለም ያወቃቸውና ፀሐይ የሞቃቸው ጉዳዮች በመሆናቸው እነኚህን ጉዳዮች አሁን ላይ ደግሞ መናገር ለአብዛኞቻችሁ ለቀባሪ መርዶ እንደመናገር እንደሚሆን አያጠያይቅም።
ዘይግይቶም ቢሆን ግን የአለም ጤና ድርጅትም ሳይቀር የህዝባችንን የህልውና ችግርና የጤና አገልግሎቱ የገጠመውን ሥርአት መር ፈተና መረዳቱን በዋና ዳይሬክተሩ በኩል የዶ/ር ፀጋሁን ስሜን የግፍ ግድያን ተከትሎ በመግለፁ ሥርአቱ የሞት ጣር ላይ መድረሱን በግልፅ አመላክቷል። በዚህ አጋጣሚ ዶ/ር ፀጋሁንን የመሠለ የህክምና ዶክተር ለማፍራት በትንሹ ሩብ ክፍለዘመን የሚጠይቅ መሆኑን እንድታውቁት እና በህዝባችን ላይ ምን ያክል ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ የዘር ማጥፋት እንደሚፈፀም እንድትረዱት አንፈልጋለን። ለዶ/ር ፀጋሁን ቤተሠቦችና ወዳጆች ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን።
ጥያቄው ይህ ዘግናኝ ወንጀል እስከመቼ እና ስንት ሙያተኞቻችን እስከሚያልቁ ቁጭ ብለን እንመለከታለን? ነው። ከመቼውም ጊዜ በላይ የተጠናከረው እና መንግስትን ተክቶ አገር የመምራት ቁመና ላይ የሚገኘው ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄም ይሁን ዕዛችን የጤና ሙያተኞቻችን ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙ የአሸባሪው ስርአት አባላት ላይ እርምጃ እንዲወስድ ወይም በአለም አደባባይ ለፍርድ እንዲያቀርብልን የምኒልክ ዕዝ ጤና መምሪያ አበክሮ ይጠይቃል።
በመጨረሻም ምንም አይነት ከለላ ሊሠጣችሁ የሚችል ሀይልም ይሁን ሥርአት በሌለበት በአሸባሪው መንግስት ቀጠና ውስጥ ሆናችሁ ይህን ሁሉ ግፍና መከራ የምትቀበሉ የሙያ ጓዶቻችን ኑ ተጋግዘን ይህን አስከፊ ሥርአት በጋራ እንቀይር እያለ የምኒልክ ዕዝ ጤና መምሪያ የተለመደ ጥሪውን ያቀርብላችኋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 7/2018 ዓ.ም
07/ዐ6/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና‼️
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር በተለያየ አቅጣጫ በጠላት ላይ ድል ተቀናጀ ።
ይካቲት 07/2018 ዓ.ም፡ አፋብን ደ.አ.ቀ. አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክፍለ ጦር አናብስቶችን ቦታ አስለቅቃለሁ ብሎ የተንቀስቀሰው የብልፅግና የሰፈር አወደልዳዩ ሪፐፕሊካን ኮማንዶ ጥበቃ 5ኛ ክፍለ ጦር እንደ እባብ ሲቀጠቀጥ መዋሉ ተገለፀ ።
ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ መነሻውን በተለያየ አቅጣጫ በማድረግ የነበልባል ክፍለ ጦር ፋኖ አባላቶችን ለመክበብ በአራት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰውን የብልፅግና ሎሌን፤ የነበልባል ክፍለ ጦር አራተኛ (፬ኛ) መብረቁ ሻለቃና ሶስተኛ (፫ኛ) ራስ በኃይሉ ሻለቃ በጋራ በመሆን ቀይ ቦኔቱን ከነ ቅንጭሌው ሲበጥሱለት መዋላቸውን ተነግሯል ።
ይህ የተንኮሎች ሁሉ አባት በሆነው ብልፅግና የሚዘወረው "መከላከያ" ተብየው - የአቢይ አህመድ አሽከር ጥቃቱን የጀመረው በራሱ ተቅበዝባዠነት ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ ሲሆን፤ አባዳሌ በተባለ አካባቢ በጀግኖቹ በራስ በኃይሉ ሻለቃና በመብረቁ ሻለቃ በጋራ በመሆን ከፍተኛ የሰው ኃይሉን በጀመረበት ቦታ በመምታትና ወደ ማይሆን ቦታ ስቦ በማስገባት አሁንም ተግተልትሎ ወጥመድ ውስጥ የገባውን ቀይ ቦኔት ለባሹን ኮማንዶ፤ በኢንጆራር አማኑኤል እንዲሁም መስቀለኛ በተባለ ቦታ በማስገባት በክንደ ብርቱዎቹና በአይደፈሬዎቹ በመብረቁ ሻለቃና በራስ በኃይሉ ሻለቃ ፋኖዎች በጋራ በመሆን እስከ 6:35 ደቂቃ ድረስ ሲቀጠቀጥ መዋሉ ታውቋል ።
የነበልባል ክፍለጦር'ን ወደ ጫካ ሲገቡ ለማጥቃት ቀድሞ ከአረርቲ ከተማ ተነስቶ በወሌንሱ አድርጎ ወደ ከሰም ወንዝ የገባው የብልፅግና ገረድ ሰራዊት በሸንኮራ የገባው ኃይሉ ክፉኛ መመታቱን ሲስማ ለመድረስ ሀሳቡን በመቀየር በክራርጌ አቦ በኩል ወደ ሸንኮራ ቢያቀናም እንኳን ሌላ ሊያተርፍ እራሱን ከበባ ውስጥ በማስገባት ተቀጥቅጦ ተመልሷል ።
ይህም ከቀኑ 8:30 ደቂቃ ላይ ከፍተኛ የማጥቃትና የከበባ ስራ የተሰራው የከሰም ፪ኛ ኮር ተወርዋሪዎች (ቃኚና መሃንዲስ) ከነበሩበት ቦታ በፍጥነት በመነሳትና ከነበልባል ክፍለ ጦር ራስ በኃይሉ ሻለቃ ፋኖዎች እና መብረቁ ሻለቃ ፋኖዎች ጋር አንድ ግምባር በመፍጠር፤ ለአጋዥነት በክራርጌ የወጣውን የአገዛዙ ተላላኪ መከላከያ ሰራዊት በቆረጣ በመግባት ከፍተኛ የሆነ ሙትና ቁስለኛውን አስታቅፈውት መዋላቸው ነው መረጃው የሚያመላክተው ።
በመጨረሻው ስቦ በማጥቃት የከሰም ፪ኛ ኮር ቃኚና መሃንዲስ በቆረጣ በመግባት እንዲሁም መብረቁ ሻለቃ እና ራስ በኃይሉ ሻለቃ በጋራ በመሆን በወሰዱበት መብረቃዊ ምት ከዙ-23 እስከ ሞርተር እና ድሽቃ ድረስ፤ በአርሶ-አደሮች መንደር ላይ ስያፈስ ወሎ በንፁሃን ዜጎች ላይ ቁሳዊና ሰበዓዊ ጉዳቶችን አድርሶ፤ በነበልባሎቹ ክንደ-መራርነት ያለ ውጤት አንገቱን ደፍቶ እንዲመለስ ተገዷል ።
በመጨረሻም ሽንፈቱን ያሳበደው የ5ኛ ሪፐፕሊካን ጥበቃ ክፍለ ጦር አመራሮች በክርስቶስ ሰምራ ቤተክርስቲያን ተጠልሎ የነበረ አንድ የአእምሮ ህመምተኛ #ፍሰሃ_ሚሊዮን የተባለ ግለሰብን በግፍና ጭካኔ ሲመለሱ እንደረሸኑት የአይን እማኞች አሳውቀውናል ሲል አፋብን ደ.አ.ቀ. አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር ሪፖርተራችን አርበኛ እንግዳ መረጃውን ከስፍራው አድርሶናል ።
© አፋብን ደ.አ.ቀ. አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር አርበኛ ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ ።
- አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ ።
ሸዋ
የጥንቃቄ መልዕከት 7/6/2018
የብልፅግና ጉጅሌ በአሁኑ ሰዓት በሸንኮራ በኩል ክርስቶስ ሰምራ የደረሰ ሲሆን በወሌንሱ በኩል ደሞ ያለው ደፋርሳ አካባቢ ደርሷል ምንታምር ያለው ወደ አክርሜት ተንቀሳቅሷል ።
ሸር ይደረግ
Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከሌሊቱ 6:40 በደብረ ማርቆስ ከተማ በፈፀመው የቦምብ ጥቃት ሶስት ሚኒሻዎች ተገድለዋል ።
የካቲት 7/2018ዓ.ም
===================================
አስደናቂ ጀብድ በመስራት የጠላትን ካምፕ በቦምብ የሚያጋዩት 206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ዛሬም በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 6:40 ተክለ ኃይማኖት ጨረቃ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በፈፀመው የቦምብ ጥቃት ሶስት ሚኒሻዎች ሲገደሉ ሁለት ሚኒሻዎች ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል።
በተጠና መልኩ በደብረ ማርቆስ ከተማ በጠላት ካምፕና ተሽከርካሪዎች ላይ የተጠናከረ ጥቃት የሚያደርሰው አዳኝ ቡድኑ አገዛዙ የሚመካባቸውን የሰራዊት አባላት በተናጥልና በቡድን በመለየት በተደጋጋሚ እያከናወነ ባለው ኦፕሬሽን ያለ ምንም አይነት መስዋትነት በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ መቻሉን አስታውቋል።
በተመሳሳይ ከቀይ ከተማ በመነሳት ወደ ደቤት የአርሶአደር እህል ለመዝረፍ በተንቀሳቀሰው የአረመኔው ሰራዊት ላይ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ባደረገው የደፈጣ ጥቃት የጠላትን ኃይል አስክሬን አሸክሞ መልሶታል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ስለ ብሩኬ በኮማንዶ ሽመለስ ተጻፈ
የትግል ጽናትና የክፋት መጋረጃ
ያኔ በአማራ ወጣቶች አደረጃጀት ምስረታ "ሀ" ተብሎ በተጀመረው የትግል ምዕራፍ በደብረ ብርሃን ከተማ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን የሕዝቡን የፍትህ ጥያቄዎች በአደባባይና በሰላማዊ መንገድ ያስተጋባው እርሱ ነበር። በኋላም የሰላማዊ ትግል በሮቹ ሲዘጉና አፈናው ሲበረታ ነፍጥ አንስቶ የአማራን የህልውና ትግል በድጋሚ "ሀ" ብሎ ለማስጀመር ግንባር ቀደም የሆነውም ይኸው ብላቴና ነው።
በዚህ የህልውና ትግል ውስጥ የሦስተኛው ትውልድ ታሪክ እንዲያብብና ፍሬ እንዲያፈራ ከሸዋ ሸንኮራ እስከ ጎንደር ቋራ በእግሩ ተጉዞ አፋብኃ እንዲመሰረት የብኩርና ድርሻውን ተወጥቷል። በድጋሜም ንቅናቄው ሲመሰረት የ"አሳምነው ዕዝ" የጣለበትን የአመቻችነት ኃላፊነት በብቃትና በታማኝነት በመወጣት ለየትኛውም ኃላፊነት ብቁም ዝግጁም መሆኑን ያስመሰከረ የመርህ ሰው ኢንጂነር ብሩክ ስለሺ ነው።
ይህ የሦስተኛው ትውልድ የተነሳበት ዓላማ ግቡን ይመታ ዘንድ እውቀቱንና ጉልበቱን ሳይሰስት በቅንነት ድርሻውን እየተወጣ ያለው "ትንሹ ልዑል" ሆኖ ሳለ ከከፍታው መድረስ ያልቻሉ ድኩማኖች ባልተሟሸ አፋቸውና የበታችነት ስሜት በወለደው ጥላቻ ሊከሱት ሲዳዳቸው አየሁ ሰማሁ እናም ይቺን ለማለት ወደድሁ "ቅናት" የሚሉት በሽታ መድኃኒት የሌለው የእኛ ትውልድ መገለጫ አይሆንም እና እንዲህ ፈገግ ሳቅ ብለህ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ በሸውርኔ አይተህ እለፋቸው።
ብዙ ጊዜ ጠንካራ ባለራዕዮች ለመምታት አንድም ከጥላት አንድም ከውስጥ ባንዳ የሚውርውር ፍላፃ ይኖራል እና ጥቃቱ የሚመነጨው ካከናወኑት ስራ ግዝፈትና ተቺዎቹ ካላቸው የብቃት ማነስ ስጋት መሆኑ የታወቀ ነው። ስለዚህ ጓዴ ሆይ! "ንቆ መተው" እና "ስቆ ማለፍን" የመሰለ ትልቅ በቀል የለምና እንዲህ ብለህ ሳቅባቸው። በትልልቅ ዓላማዎች ላይ ያተኮረ ሰው ጥቃቅን መሰናክሎችን በዝምታ ማለፉ የውስጥ ሰላሙን ከመጠበቁም በላይ ለጠላቶቹ የማይቀምስ ምላስ ነው።
እናም ጓዴ ዝምብልህ ሳቅባቸው!
