es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
4 413
Suscriptores
+2224 horas
+437 días
+1 38430 días
Archivo de publicaciones
⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️ ባለጊዜ የዳንግላ ባንዳ መዘጋጃ ቤት ሀላፊ ተብየዎች ነዋሪዎችን የመዝረፊያ ዘዴዎችን በመቀየስ እሰከ ታህሳስ 20 ገንብቶ የይዞታ site ማረጋገጫ ያልያዘ ተነጥቆ ወደ
⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️ ባለጊዜ የዳንግላ ባንዳ መዘጋጃ ቤት ሀላፊ ተብየዎች ነዋሪዎችን  የመዝረፊያ ዘዴዎችን በመቀየስ እሰከ ታህሳስ 20 ገንብቶ የይዞታ site ማረጋገጫ ያልያዘ  ተነጥቆ ወደ መሬት ባንክ በማስገባት፤ እርምጃ እንወስዳለን፤100% በተግባር እናደርገዋለን፤ በማለት፤ በዚህ ወቅት በኢኮኖሚ ሽባ ሆነው መስራት፤መገንባት ያልቻለ ማህበርሰብን ግምት ውስጥ ያላስገባ እና ያላገናዘበ ውሳኔ ነው ብለን ብንጠይቃቸውም፤ ከቻልክ ስራ፤ካልቻልክ ትነጠቃለህ የሚል ምላሽ ሰጥተው፤ ህ/ ሰቡን በማስጨነቅ፤ ድባቴ ውስጥ በመክተት በጭንቀት ውስጥ ተወጥሯል፤ መላ ሊባሉ ይገባል፨

✊የአማራ ልዩ ሀይል ፈርሶ ከካምፕ ወደ ጫካ ሲገባ የመጀመርያው ፈር ቀዳጅ አቸፈሬው ኮማንዶ ፈቃዱ ጌትነት! ያኔ ይህንን ብሎ ነበር :: "አሁን እኛ ወደ ጫካ እየገባን ነው ማን መጦ ትጥቅ እንደሚያስ
✊የአማራ ልዩ ሀይል ፈርሶ ከካምፕ ወደ ጫካ ሲገባ የመጀመርያው ፈር ቀዳጅ አቸፈሬው  ኮማንዶ ፈቃዱ ጌትነት! ያኔ ይህንን ብሎ ነበር :: "አሁን እኛ ወደ ጫካ እየገባን ነው ማን መጦ ትጥቅ እንደሚያስፈታን እናያለን:: የፌድራል መንግስት ትጥቅ ሊያስወርደን ከመጣ ያለምንም ማመንታት እንገጥመዋለን:: ግን ደግሞ እኛ የማን ልጆች መሆናችንን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ አይሞክሯትም ከሞከሯት ይምጡ ደስተኞች ነን:: "የክልሉ መንግስትም አሻፈረኝ ብሎ እኛን ትጥቅ ሊያስወርድ የሚመጣ ካለ እንዳስፈላጊነቱ እሱም ይመታል በማለት ድምጹን አስተጋባ:: ብዙዎችም ተከተሉት:: ';አርበኛ ኮማንዶ ፍቃዱ'' በስሙ እና በደሙ ተቋም ገንብቶ አለፈ:: እኛም ወንድሞቹ የወደቀለትን ትግል በጽናት እናሻግራለን ይህ የማይታበይ ቃላችን ነው::

በሱዳን አማፅያን የኤል ፋሸር ከተማን ከተቆጣጠሩ በኋላ ከ2,000 በላይ ንፁሃን ገድለዋል ተባለ የሀገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት የጀመረው በፈረንጆቺ በሚያዝያ 2023 ሲሆን፣ በጦር ሠራዊቱ እና ቀደም ሲል ለመንግሥት ይገዛ በነበረው ፈጣን ምላሽ ሰጪ ኃይል (Rapid Intervention Forces - RIF) መካከል ነው። የሱዳን ዶክተሮች ኔትዎርክ እንደገለጸው፣ ታጣቂዎቹ ከተማዋን ከተቆጣጠሩ በኋላ በአካባቢው በሚገኘው ሆስፒታል ውስጥ የነበሩትን ሁሉንም ሰው ገድለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት  ትጥቅ ያልታጠቁ ወንዶች ሲተኮሱ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች መኖራቸውን ገልፇል። በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ታግተው የተያዙ ሲሆን፣ እስከ 10 ሚሊዮን የሱዳን ፓውንድ የሚደርስ ቤዛ እንዲከፈልባቸው እየተጠየቁ ነው። በከተማዋ ውስጥ ወደ 260,000 የሚጠጉ ሰዎች፣ ግማሾቹ ህፃናት ሲሆኑ፣ ቀርተዋል፤ በረሃብ ምክንያትም የእንስሳትን መኖ እየበሉ ነበር። ከግጭቱ መጀመሪያ አንስቶ ከ150,000 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና ከ3.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ስደተኞች መሆናቸውን የሚዲያ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ቪዲዮ: የማኅበራዊ ሚዲያ።

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የጎንደሬ በጋሻው ክ/ር አባላት ሰብል ስብሰባ ማህበረሰቡን በማገዝ ላይ።

~~~~~~~~~~~| አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነሰላም ላይ ሚሊሻ ሲሞት ሃይማኖቱ ተፈልጎ ይለቀስለታል። ኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ውስጥ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሰፈር እየተለቀሙ ሲ'ታረዱ
+6
~~~~~~~~~~~| አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነሰላም ላይ ሚሊሻ ሲሞት ሃይማኖቱ ተፈልጎ ይለቀስለታል። ኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ውስጥ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሰፈር እየተለቀሙ ሲ'ታረዱ ግን ሃይማኖት የላቸውም። በሌላ በኩልም ቢሆን የ1000 አማራ ህዝብ ሞት ከአንድ የቀቤና ማህበረሰብ ንብረት የሆነች ፍየል በመኪና ተገጭታ መሞት ጋር እኩል ሚዛን እንዳይኖረው ተደርጎ የተሠራ ትርክት እና ሃገራዊ ሥርዓት ውስጥ ነው የምንኖረው። በኦህዴድ/ብልፅግና የምትመራዋ ሃገር ማለት ይህቺ ናት። እንዴት እንደምንቀጥል ወደ ፊት እንነጋገራለን!

ሰበር ሰበር!! "ጥሬ ስጋ ብቻ" እየበሉ ሰልጥነዋል የተባሉ የኦሮሚያ ልዩ ኮማንዶዎች በነበልባሉ የአማራ ፋኖ ተማረኩ። ምርኮኞቹ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ተስፋ ፋኖ ነው ሲሉ የገለፁ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆነ አናውቅም ሐገሪቱን ለማፍረስ ተልዕኮ እየተሰጠን ያለው እኛ ደግሞ በዚህ ደስተኛ ስላልሆን ለመማረክ ፈቅደናል ብለዋል። እስኪ የሚሉትን አዳምጧቸው

"... አስቸኳይ ጥንቃቄ‼፦ "...#ወደ ፋኖ የሚቀላቀሉ ማንኛውም የፀጥታ አባላት ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ። "...#በገበያ ቀናት ጨምሮ በመደበኛ ጊዚያት ቀበቶ፣መስቀልና ሌሎች ዕቃዎችን በመያዝ ወደ ገጠራማ ቀበሌዎች የሚንቀሳቀሱ 'ነጋዴ መሳይ' የመንግስት መረጃዎችን ተጠንቀቁ። "...#የቀን ሠራተኛ በመምሰል ወደ አጨዳ የሚሄዱ ፀጉረ-ልውጦች እንደተሠማሩ የራሳቸው የውስጥ ሠዎች እየነገሩን ነው። "...#አሳዛኝ ህፃን የሚመስሉ ዲያቆንና ሌሎችም ወጣቶች በፋኖ ላይ ተሠማርተዋል። "...#አጠቃላይ ቆቦ ዙሪያ የሚገኝ ካቢኔ እያንዳንዱ በግሉ(በስሩ) አምስት አምስት የመረጃ ሠዎችን መልምሎ ብልፅግናን እንዲታደግ ትዕዛዝ ተላልፏል። "...ቤተሠብ፣ጓደኛ፣ወዳጅና የቀን ወጭ የሚያሳስበው ሱሰኛ ሁሉ የዚህ ተልዕኮ ተሣታፊ ሆኗል። "... በተለይ ደግሞ የፋኖ አመራሮች የሚጠቀሙባቸውን ስልክ ቁጥሮች የሚያመጣላቸውን 'ምርጥ ምላሳም' ከፍተኛ ትኩረት ተሠጥቶት እየተሠራ ነው። '...የፋኖ አመራር ቤተሠቦችን በረቀቀ መንገድ በመወዳጀት የሚያወሩባቸውን መስመሮች ለማግኘት እጅግ ትልቅ የቤት ስራ ተደርጎ ወደ ተግባር ተገብቷል። "...በአጠቃላይ የራሳችሁን የደህንነት መዋቅር ከማጠናከርም በላይ መረጃው ለሚመለከተው አካል እንዲደርስ ይደረግ።  ድል ለተገፋው አማራ!! ድል ለጀግናው ፋኖ 💪!!

ሙሉ ኤርትራን የሚያክል ኢትዮጵያውያንን የጨረሰው አብይ አህመድ! ጨቅላው አብይ አህመድ ኤርትራን ለማስፈራራት ከሰሞኑን ባሰማው ዲስኩር "ኢትዮጵያ በዓመት 3 ሚሊዮን ህዝብ ትጨምራለች፤ ይህም ማለት በዓመት አንድ ኤርትራ ትጨምራለች ማለት ነው" ሲል ተደምጧል። የሰውዬውን ኩታራነት ለጊዜው ትተነው፣ እሱ እስካሁን የጨረሳቸውና ያስጨረሳቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር በጥቅሉ 3 ሚሊዮን የሚሻገር በመሆኑ "ኤርትራን የሚያክል ህዝብ ጨፍጭፏል" የሚል ከእራሱ ንግግር በመነሳት ተመሳሳይ ንፅፅር ማቅረብ ይቻላል። ለማንኛውም በኦሮሞ ብልጽግ እና በኤርትራ መካከል የሚከፈተውን ጦርነት በጉጉት በመጠበቅ ላይ ነነ… እግራችንን ሰቅለን ከፈንድሻው እየዘገን የአሰብ ኢሬቻ አክባሪዎችን ፈንጠዝያ ለመመልከት ዝግጅት ጨርሰናል። አፍጥኑልን! አፍጥኑትማ 😁 የሆነው ሆኖ በብልጽግና ሰዎች "ባንዳዎች" እንደመባል ሃሴት የሚፈጥር ነገር ግን አለን?!

🔥#ሰበር‼️ #በአንድነት_ምግስት_ሚሊሻ_ተናደ‼️ ስትመታ ጠበቅ አድርገህ ምታ የእስቴ ሚኒሻ እንዲህ በሰልፍ እጁን ለፋኖ አስረከቧል። ይቀጥላል 👌 ሌላህም ና ግባ አማራነትን፣ ሀገርን በአንድነት እናድን‼️ #እናት_ዓለም_ጎንደር💪 21/ዐ2/2018 ዓ.ም

እሄ ነው መብሰል በቃ 👏👏👏👏 ጎንደር እስቴ ወረዳ በርካታ ሚሊሻ ከእነ ትጥቃቸው ወደ ፋኖ ተቀላቅለው በሰልፍ ሲገቡ ፋኖዎቻችን በጭብጨባ በሞራል ነው አቀባበል ያደረጉላቸው በጣም የሚደንቅ ነው እንዲህ ስንደማመጥ ደስ ይላል 👏👏 ከትላንት ወዲያም ከ252 በላይ ሚሊሻዎች ሸዋ በሚዳ እና ሬማ ወረዳ ፋኖን ተቀላቅለው ጥሩ አቀባበል ሲያደርጉላቸው አይተናል ሚሊሻ እንዲህ ገብቶት ወደ ፋኖ ሲቀላቀል እንደዚህ በሞራል ልዕልና አቀባበል ተደርጎላቸው ቢቻል በአበባ ጉንጉን አቀባበል ቢደረግላቸውም ለሌላውም መማሪያ ነው 👏 ያው እስከ ጥግ ባንዳ የሆነ ላይ መቀጣጫ እንደሚወሰድ ሁሉ እንዲህ የጠላትን እኩይ ተግባር አማራን ከምድረ ገፅ የማጥፋት ተግባር ገብቷቸው ሚሊሻዎች ሲመለሱ ታላቅ የክብር አቀባበል ይደረግላቸዋል✊ የእስቴ ወረዳ ሚሊሻ ❤

ሰላም ነው ወንድሜ ጤናህን እንዴት ነህ ይህን መረጃ ለመላው እትዮጵያን አድረረስ የብልጽግና የዘር ጭፈጨፋ ሴፈ በአረሲ ንጽሕና ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ አላማው እና እቅድ የአማራ ፋኖ ለእረቅ እና ለድረድር ይጠቅመኛል በኦሮሚያ ክልል ያሉ አማራ ተወላጆች የፋኖ ትግል ለአደጋ ይደረጋል በሰላም ፋኖ እረቅ እዳደረግ የጥቅመኛል የዘንድሮ ሞርጫ ያስቀርልኛል በሚል እሳቤ ባለፉት 5 አመት በኤርትራ በኦሮሚያ ክልል የሰለጠኑ ህዋትን አሸባራ ብሎ ለማስፈረጅ ከአልሸባብ ጋራ ግንኙነት ያላቸው የብልጽግ ሸኔ ወታደሮች ከባሌ ከቦረና የአርቴፊሻል ጸጉር አልብሶ በሸኔ ስም ያሰማራቸው በለሊት እያጋጋዘ በአሩሲ ዞን በአራባጉጉ በዙ ወረዳዎች በአቦምሳ  አባጀማበስሬ በጀጅ በሽረካ በአሰኮ በጎለልቻ በመረቲ ጀጅ በጎለልቻ በጮሌ በዲክስስ በአሰላ የቡዙ ዜጎች ለመታገት ለመፈናቀል ለጅምላ ጭፍጨፋ ምክናያት የሆኑበት በቀጥታ በአብይ አገዛዝ በአቶ አዲሱ አረጋ በሽመልስ አብዲሳ የሚፋጸም ሲሆን ሙሉ የገጠሩ ማህበረሰብ ወደ ከተማ እዲፈናቀል እንዲራብ ምክናያት ሲሆን በአጠቃላይ በሽረካ በጀጅ በአቦሞሳ በአሰኮ በመረቲ ጀጅ የታገቱት እና የሞቱት ቁጥር ያማይታወቅ በጣም ቡዙ ሺዎች በለፉት 8 ወረት መታገታቸው ሞሞታቸው ለሚዲያ ያልቀረበ የቆየ የሰቆቃ ምድር ሆናል በመላው አገራችን የተቃውሞ ዘመቻ። በመላው አገራችን ይታወጅል ይላሏ በመላው ኢትቴ የሚኖሩ ቤተሰቦች

ምዕራብ ሐረርጌ ሒሪና ወረዳ 2018 ዓ.ም ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጸመ። 2017 ዓ.ም አግተው የወሰዷቸውንም እስካሁን አልመለሷቸውም። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ወጣት እንዲህ ከምድሪቱ እየተጸዳ ነው።
+4
ምዕራብ ሐረርጌ ሒሪና ወረዳ 2018 ዓ.ም ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጸመ። 2017 ዓ.ም አግተው የወሰዷቸውንም እስካሁን አልመለሷቸውም። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ወጣት እንዲህ ከምድሪቱ እየተጸዳ ነው። ወረዳዎችን ከኦርቶዶክስ ነፃ ለማድረግ አራጆቹ ያለ ማንም ከልካይ ፕሮጀክታቸውን በዕቅዳቸው መሠረት እየሠሩ ነው። ከሞት የተረፉት ወዳ ከተማ እየሸሹ ነው።

ከደጋው መብረቅ ኮር የተሰጠ የአንድነት ብሥራት መግለጫ የአማራ ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ሞት ከጥላው የቀረበ መሆኑንና የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የአገዛዙ ኃይልና አማራ ጠል ኃይሎች በአማራው አንገት ላይ ያለማቋረጥ ሠይፍ እያሳረፉ ያሉበት ጊዜ መሆኑን ለአፍታም እንኳን የማንዘነጋው ጉዳይ ነው። አማራን በሌሎች ወገን ሕዝቦች ለማስጠላት የተኬደበት ርቀትም ረጅም ነው፤ በቢሮክራቲክ ተቋማት፣ በፖለቲካዊ ሹመት፣ በዲፕሎማሲው ረገድ ሳይቀር አማራው ከፍተኛ በደል እየደረሰበት ይገኛል፡፡ የአማራ ፋኖን ትግል በድል ለመቋጨት የአማራ የህልውና ታጋዮች አንድነት ወሳኝ ነው፡፡ እኛ የአማራ ፋኖዎች ወደ በረሃ የወረድነው፣ ቤታችንን ዘግተን ዱር ቤቴ ያልነው፣ የአማራ ሕዝብ ላለፉት ዘመናት በጎበጠ የፖለቲካ ትርክት ምክንያት ተገዳይና ተሳዳጅ መሆኑ እንዲያበቃ፣ ነጻነቱን እንዲያገኝ ነው። እኛን ከክፋት ሠሪዎች ጋር ፊት ለፊት በጠመንጃ አፈሙዝ እንድንጋፈጥ ያደረገን ወገናችንን በሀገሩ ላይ ከእኩልነት ደረጃ አውርደው በሕልውና ጥያቄ ቅርቃር ውስጥ ስላስገቡት ነው። የአማራ ሕዝብ የህልውናና የፍትሕ ትግል በሞራል፣ በሰብአዊነት፣ በሃይማኖት፣ በማኅበራዊና ዓለም አቀፋዊ የሕግ ሚዛኖች ሁሉ ፍትሓዊ ብቻ ሳይሆን ሰው ሆኖ መፈጠር የሚያስከትለውን ራስን በክብር የመጠበቅ ተፈጥሮአዊ እዳን የመክፈል የማይቀር ትግል ነው። ታላቁ ሰማዕት ፕ/ር አሥራት ወልደየስ “አማራ የለም” ለሚሉ ጠላቶች ምላሽ ሲሰጡ “አማራ የለም ትላላችሁ፤ ለመግደል ስትፈልጉት ግን ታገኙታላችሁ” እንዳሉት ጠላቶቻችን በጅምላ ሊጨፈጭፉን የሚፈልጉን ሕዝቦች ነን፡፡ ይኸውም ከወለጋ እስከ ባሌ፣ ከሞያሌ እስከ ማይካድራ ድረስ የተደረገ የትላንት ታሪክና እስከ ዛሬ የቀጠለ በአለም ፊት በገሃድ እየተፈጸመ ያለ ሐቅ ነው፡፡ ጠላቶቻችን መርጠው የማይገድሉን፣ በጋራ የዘመቱብን፣ በአማራነታችን ብቻ በጅምላ የሚፈጁን ከሆነ እኛ በአንድነት በመሠለፍ ትግላችንን ከድል ምዕራፍ ለማድረስ የሚያግደን ምናለ? ሥልጣን ነውን? ገዳይ በበዛበት፣ ሕዝባችን ዕለት ዕለት እየሞተ ባለበት ሁኔታ የትኛው ሥልጣን አጓጉቶን ነው? ዝና እና ሕዝበኝነት ነውን? ሕዝባችን በሞትና በስደት መከራ በሚያይበት ሀገር ላይ ሆነን እኛ ታጋዮች ስለ ምን ዝና መናገር እንችላለን? ፍትሕ በተጓደለበት ሕዝባችን ፊት ስለምን ዝና ልናወራ እንችላለን? ኃብትና ገንዘብ ነውን? ለመሞት ወስነን ዱር ቤቴ ያልን መቼና እንዴት በምን ሁኔታ ልንሞት እንደምንችል እያወቅን ኃብትና ገንዘብ ምናችን ነው? ለአንድነታችን እንቅፋት የሚሆንብን ምክንያት ሁሉ ከሕዝባችን ክብርና ሕልውና በታች ነው፡፡ ሆኖም ግን ሰበብ በማብዛት አንድ ላይ ለመቆም የሚቆዝም ቢኖር ከጠላቶቻችን ጋር የተሰለፈ አልያም ለግል ፍላጎቱ ያደረ ነውና ባንዳ መሆኑን በዚህ እናውቀዋለን። ስለሆነም እኛ ቀደም ሲል የአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አመራሮች ከአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ አመራሮች ጋር በአማራ ሕዝብ የትግል መስመር፣ መዳረሻ ዓላማና ግብ፣ መዋቅራዊ የግንኙነት መስመር፣ የትብብርና የአጋርነት ማዕቀፍ ላይ ባደረግነው ተከታታይ ጥብቅ ውይይት በዝርዝር ከተወያየን በኋላ ከዚህ ቀደም የነበሩ ቅሬታዎችን በወንድማዊ ይቅርታ በመዝጋት ፍጹም መግባባት ላይ ደርሰናል፡፡ በመሆኑም ይህ መግለጫ ከተሰጠበት ከዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የደጋው መብረቅ ኮር በሚል አምስት ክፍለ ጦሮችን የያዘ አደረጃጀት ያለው ግዙፍ ኃይል አደራጅተን በአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጋር በመዋሐድ በአንድ መዋቅር ለመታገል መስማማታችንን አንድነታችንን ለምትናፍቁ ወገኖቻችን ስናበሥር በታላቅ ደስታ ነው። በደጋው መብረቅ ኮር የተካተቱ ክፍለጦሮች:- 1. ፅናት ክፍለጦር 2. ደጀን ክፍለጦር (የቀድሞው የደጋው መብረቅ ክ/ጦር) 3. አንሻ ሰይድ ክፍለጦር 4. ሰንጥቅ ክፍለጦር 5. ቀኝ-አዝማች ተበጀ ክፍለጦር እንዲሁም በሻለቃ አደረጃጀት ያሉ ሀይሎችን ያካተተ ኮር  መሆኑን ለመላው የትግሉ ደጋፊ እና ታጋዩ መግለፅ እንፈልጋለን። የደጋው መብረቅ ኮር አመራሮች እና ኃላፊነታቸው ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ሰብሳቢ ……………………… አርበኛ ኃብቴ አባቡ ወታደራዊ አዛዥ ……………. አርበኛ ተመስገን አለባቸው ምክትል ወታደራዊ አዛዥ …... አርበኛ ማረጉ አስፋው ፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ………… አርበኛ መ/ር ብርሃን አረጋ ዘመቻ ኃላፊ …………………. አርበኛ አስፌ አበጋዝ ም/ል ዘመቻ………………………. አርበኛ ጨለፍ ተስፋው ሎጂስቲክስ …………….…….. አርበኛ መሳፍንት ደሴ ቃል አቀባይ ………………….. አርበኛ መ/ር መኩሪያ አጋዥ ፋይናንስ ……………………… አርበኛ 10 አለቃ ሙላቱ ሰጠ ም/ል ፋይናንስ...................አርበኛ ፍቅር አራጌ የሰው ኃብት አስተዳደር …….. አርበኛ መካሽ የኋላው መረጃና ደህንነት ……………. *** ስልጠና መምሪያ ……………. አርበኛ 100 አለቃ ሲሳይ ም/ል ስልጠና መምሪያ.......አርበኛ ጋሻው ቢያርጎ ሕግ ክፍል             ..............አርበኛ 100አለቃ ፈለቀ ጌትነት ህክምና መምሪያ……………………… አርበኛ ዶ/ር መላኩ የሻነው ወታደራዊ አስተዳደር …………………… አርበኛ ናቲ ውዱ ም/ል ወታደራዊ አስተዳደር...............አርበኛ ውበት ደምሴ ሚዲያ ክፍል………………………. አርበኛ እሸቱ አባተ ኦርዲናንስ ................................አርበኛ ሙሉጌታ አሻግር ሴቶች ጉዳይ ………………… ፋኒት መቅደስ  ብርሃን የሕዝብ አስተዳደር …………… አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ … አርበኛ አወቀ ብዙአየሁ የኮር ልዩ ዘመቻ ……………………. አርበኛ አበበ ቢራራ የኮር ም/ል ልዩ ዘመቻ..................አርበኛ ኪዳን ወዳጄ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ………….. አርበኛ አንደበት ወረታ የኮር አማካሪ ………………….. አርበኛ አለሙ ገላው የኮር ም/ል አማካሪ.............አርበኛ እንዳለማው ፈጠነ ግዥ …………………………… አርበኛ አለበል ተካልኝ ወታደራዊ አደረጃጀት ………….. አርበኛ ሻለቃ ወንድሙ፡ ም/ል ወታደራዊ አደረጃጀት ...........አርበኛ ሻምበል ደመቀ እንየው በዚህ አጋጣሚ በተለያዩ የአማራ ቀጠናዎች የምንገኝ ፋኖዎች ለድል የምንበቃውና የወገናችንን ግፍ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በፍጥነት እንዲያከትም የምናደርገው በአንድነትና በመተባበር መታገል ስንችል ብቻ ነው፡፡ ዛሬ የታወጀው አንድነት በወሎ ቀጠና ይሁን እንጂ አገዛዙ የሀገር በጀት ይዞ ያለ እረፍት በገፍ እያሰለጠነ የሚልከውን የጠላት ኃይል የክተት ጦርነት መክቶ ድል ለማድረግ በሌሎችም የአማራ ቀጠናዎች በልዩነት የምትገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች ወደ አንድነት እንድትመጡ ያስፈልጋልና ወንድማዊ ጥሪያችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን፡፡ በመጨረሻም፣ በተፈጠረው አንድነት የተሰማንን ከፍተኛ ደስታ እየገለጽን በቀጣይ የሚጠብቀን ትግል ውጣ ውረድ ያለበትና ከፍተኛ መሥዋዕትነትን የሚጠይቅ በመሆኑ መላው የአማራ ልጆች ሁለንተናዊ ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! በአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም.

የወርቅ አባይ ብርጌድ የተሳካ የደፈጣ ውጊያ ፈጸሙ... (አፋብኃ ምዕ/ አ/ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ፭ኛ ክፍለ ጦር ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም) ወደ አዮ እንቅስቃሴ ያደራገው #ጡት ቆራጩ ስርዓት አገልጋ
የወርቅ አባይ ብርጌድ የተሳካ የደፈጣ ውጊያ ፈጸሙ... (አፋብኃ ምዕ/ አ/ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ፭ኛ ክፍለ ጦር ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም) ወደ አዮ እንቅስቃሴ ያደራገው #ጡት ቆራጩ ስርዓት አገልጋዮች በምድር ድሮኗ በወርቅ አባይ ብርጌድ በደፈጣ ሙት እና ቁስለኛ አድርገው ወደ መጣበት ወደ እሁዲት ከተማ መልሰውታል። በተፈጸመው የደፈጣ ውጊያም በተጨበጭ 3 የሞቱ እንዳሉ እና እንዲሁም ቁጥራቸው ያልታወቁ የሞቱ መኖራቸውን እና መቁሰላቸውን የወርቅ አባይ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ሓላፊ መረጃውን አድርሰውናል። የአረመኔው የጡት ቆራጩ ስርዓት አገልጋዮች የተከፈተባቸውን የደፈጣ ውጊያ መቋቋም ሲያቅታቸው እሬሳቸውን እና ቁስለኛቸውን እየጎተቱ ወርቅ እንደሚያሸልም እሩጫ እየተሽቀዳደሙ ወደ እሁዲት ከተማ መግባታቸውንም አክለው ገልጸውልናል። ⭐ ዘገባውን ያጠናከረው ፋኖ አይቸው ጌታሰው ነው።   አዲስ ትውልድ!     አዲስ ተስፋ!      አዲስ አስተሳስብ!   ፲ አ/ ኢ/ር ዘመኑ አማረ 5ኛ ክ/ጦር ህ/ግ መምሪያ ሓላፊ

ስዕለ አድኅኖ ይቀደድባታል ፣ በጽላቱ ይቀለድባታል ፣ የአምልኮ መፈጸሚያ እቃዋን ማንም ይናጠቀዋል ፣ ልጆቿ ነጠላ ለብሰው ጊቢ መግባት አይችሉም ፣ መስቀልና ጥምቀት ማክበርያ ይዞታዋን ይነጥቋታል ፣
ስዕለ አድኅኖ  ይቀደድባታል ፣ በጽላቱ ይቀለድባታል ፣ የአምልኮ መፈጸሚያ እቃዋን ማንም ይናጠቀዋል ፣ ልጆቿ ነጠላ ለብሰው ጊቢ መግባት አይችሉም ፣ መስቀልና ጥምቀት ማክበርያ ይዞታዋን ይነጥቋታል ፣ ለሌላው የሚፈቀድ ቦታ ለእርሷ አይፈቀድም ፣ ልጆቿ ይገደሉባታል ፣ እንደ ችቦ ያነዷታል ፣ አባቶቿን ማቃለል ማንቋሸሽ መብት ነው ፣ ለምን ብላ መጠየቅ አትችልም .... ሰውየው ሊከስ ወደ ማመልከቻ ጸሐፊ ዘንድ ሄደ አሉ ... እና ጸሐፊው በደንብ የተበዳይን ሐሳብ በደንብ ከሰማ በኋላ ምርጥ አድርጎ ጻፈለት ተበዳይም በጸሐፊው የተከሸነችውን ጽሑፍ ሰማና.. እዬዬዬዬ ብሎ አለቀሰ ምን ሆንክ ? ሲባል ለካስ ይህን ሁሉ ተበድያለሁ ! እና የተደረገብን ብዙ ነውና በብዕሩም በተግባሩም አንድ የሚያደርገን አባት የመጣልን ዕለት ....  እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ የሆን  ዕለት.. © abrham eshetu

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር 4ኛ ቀን የያዘው እልህ አስጨራሹ ውጊያ የስርአቱ አስፈፃሚ ግብስብስ ጥምር አራጅ ቡድን በደለጎና በሻሁራ ቀጠና 4ኛ ቀኑን በያዘው አውደ ውጊያ ከፍተኛ ሽንፈትን እያስተናገደ ይገኛል። በዛሬው እለት ጥቅምት 21/2018 የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አድዋ ክ/ጦ ከሁለቱ ከተሞች ሻሁራና አፀደማርያም ተስቦ ወደ ሞት ቀጠና በከበባ ውስጥ የገባው ፀረ አማራ ቡድን ከጧቱ 12:00 ስዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 7:30 ድረስ በተደረገው አውደ ውጊያ ከፍተኛ ድል ማስመዝገብ ተችሏል። በዛሬው አውደ ውጊያ የተገኘ ድል: ሙት= 36; ቁስለኛ=44 ሲሆን አሁንም አውደ ውጊያው እንደቀጠለ ይገኛል። 2ኛው አውደ ውጊያ በቋራ ደለጎ የቋራ ኦሜድላ ክ/ጦ ከጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ጋር በመጣመር የአገዛዙን ወንበር አስጠባቂ ጥምር ሀይል 4ኛ ቀኑን በተጠናከረ መልኩ በሚደረገው አውደ ውጊያ ከፍተኛ ድልን ማግኘት ተችሏል።የጠላት ሀይልም ለጊዜው በውል ያልታወቀ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ሲሆን ውሏል አሁንም በአናብስቶቹ ከበባ ውስጥ በመግባቱ  እግር አውጭኝ ብሎ ተራራ ላይ ተሰቅሎ ቀና ሲል ሰማይ ዝቅ ሲል መሬት ሁኖበታል።      ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!      አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ            ጥቅምት 21/2018 ዓም

በሚዳና ሬማ ቀጠና 264 የሚኒሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ለፋኖ መስጠታቸው ታወቀ! በቀጠናው ከነበረው የሚኒሻ ኃይል መካከል ከ80% በላይ የሚሆነውን ማፈራረሱን ፋኖ አስውቋል። ለፀረ አማራው ብልፅግና ኃይል ተላላኪ እና የአማራን ሕዝብ የከዳ የባንዳ ስብስብ የሆነው የበአዴን ቡድን በሸዋ ቀጠና በሚዳና ሬማ ወረዳ ያሰፈረው "የጭንቅ ቀን አሻጋሪየ" በሚል የሚጠራው የሚሊሻ ኃይል እየፈራረሰ እጁን ለፋኖ እየሰጠ መሆኑን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል። የተላላኪ ተላላኪ በመሆን በራሱ ሕዝብ ላይ ህልቆ መሳፍርት ግፍና መከራ እየፈፀመና እያስፈፅመ ካለው እራሱን "የሚኒሻ ኃይል" እያለ የሚጠራው የሆድ አደር ስብስብ፡ በመስተመጨረሻም የነሽመልስ አብዲሳ ቡድን <<አማራን ከአማራ ጋር የማጫረስ ሴራ>> ገብቶት ከነ ሙሉ ትጥቁ ከስምሪት ቀጠናው በመጥፋት ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል። ፀረ አማራውና የሆድ አደሮች እንዲሁም የባንዳዎች ስብስብ የሆነው የበአዴን ቡድን በሸዋ ቀጠና በሚዳና ሬማ ወረዳ አስፍሮት ከነበረው የሚኒሻ ኃይል መካከል በቁጥር 264 አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በአፋሕድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር ስር የሚገኘው አፄ ዳዊት ክ/ጦርን ስለመቀላቀላቸው የኮሩ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል። በሚዳና ሬማ ወረዳዎች ስር ከሚገኙ ቀበሌዎች ማለትም፡ ከቄጠማ እና ሙህሬ ቀበሌ 32 የሚኒሻ አባላት፣ ከይጎቢያ ቀበሌ 79፣ ከአዝማ ቀበሌ 28፣ ከጠባቢት ቀበሌ ዘጠኝ(09)፣ ከመጅት ቀበሌ 35፣ ከአላቦ ቢራባ ቀበሌ 81፡ በድምሩ 264 የሚኒሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው አፄ ዳዊት ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል ነው ያለው የኮሩ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ። እነዚህ የሚኒሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ለፋኖ መስጠት የጀመሩት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መሆኑን ለጣቢያችን የገለፀው የኮሩ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ክፍል፡ በሁለቱም ወረዳዎች ከ80% በላይ የሚሆነውን የሚኒሻ ኃይል ሙሉ ለሙሉ ማፍረስ ችለናል ብሏል።